Friday, March 24, 2023

ለበለጠ ችግር ማነሳሳት የትግራይ ህጻናት በሱዳን! ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 3/24/2023


ለበለጠ ችግር ማነሳሳት የትግራይ ህጻናት በሱዳን!

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay 3/24/2023

በዚህ ስዕለ ድምፅ (ቪዲዮ) የምትመለከትዋቸው የትግራይ ህጻናት በስደት አገር ሱዳን “ኡምራኩባ” በሚባል የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ የሚገኙ ናቸው። ህጻናቶቹ ከ10 እስከ 13 ዕድሜ ያላቸው ሲሆኑ፤ ወያኔዎች ዛሬም በስደት የሚገኙ የትግራይ ተወላጆች ህጻናት ሕሊና ላይ የሕሊና አጠባ ጨዋታቸውን አላቆሙም።

እነዚህ ህፃናት “አማራ ጠላታችን ነው” ከወልቃይት አስወጥቶ ቤተሰቦቻችን ጭፍጭፎብናል’’ እያሉ ከሚናገሩት ፍሬ ቃል  ከሚያስሰሙት ቃለ መጠይቅ ሌላ ፤ የትግራይ ሪፑብሊክ አገር ምስረታቸው ሕልም ዛሬን ስላልተውት ህጻኖቶቹ ‘የአካልእንቅስቃሴ እና የሰርከስ ካራቴ’ ትምህርት ስልጣና ሲያካሂዱ የሚያስደምጡት መፈክር፤ (ሃገረ ትግራይ ትስዕር) (ትግራዋይ  ይዕወት) “ሃገረ ትግራይ ታሸንፋለች” “ትግራዋይ አሸናፊ ነው”፤ በሚል ለበለጠ ችግር የሚያነሳሳ ትምህርትና ቅስቀሳ ሲሰጣቸው የሚያሳይ ማስረጃ ነው።

የወያኔ ወንጀለኞች ህጻናትን ለበለጠ ችግር አእምሮአቸው እንዲያዘጋጁ ሲያጥቧቸው ማየት ትናንት ወያኔዎች በሚሊዮን ሕዝብ ያስገደሉትና አካለ ስንኩል የሆነውን የትግራይ ወጣትና ምሁራን ከመጤፍ ሳይቆጥሩት ዛሬም እነዚህን ህጻናት “ትግራይ ታሸንፋለች” በሚለው የፋሺሰቶች አገር ምስረታ መፈክር  ፤ በህጻናት ነብስ የደም ጥማታቸው ለማርካት መጫወቻ ሊያደርጓቸው እንደሆነ ስንመለከት ከማዘን እና እነዚህ ወንጀለኞች ወደ አለም አቀፍ ፍርድ ቤት ከማቅረብ ሌላ እንደማይታረሙ ህያው ሰንድ ማሳያው ይህ ነው።

ብዙዎቹ ህጻናት ከሰጡት ቃለ መጠይቅ የሚሉት “በሰርከስና አካላዊ አንቅስቃሴ የላቀ ትምህርት ወስጄ “ለአገሬ ለሃገረ ትግራይ ስምዋ እንዲጠራ ማድረግ ነው ምኞቴ” ይላሉ፤ አንዱ ደግሞ “ህይወቴ ሙሉ ለሃገሬ ለሃገረ ትግራይ እሰጣለሁ” ይላል። ህልውናችን እና ደህንነታችን በጉልበታችን ይጠበቃል! ትግራይ ታሸንፋለች!” ይላሉ።

በሚገርም ሁኔታ ህጻናቱ ስደት አገር ውስጥ መኖር እንዳንገሸገሻቸውና “ሰርከስ” ትርኢት እያሳዩ እንደ ድሮው ህይወታቸው እንዲቀጥሉ ወደ አጋራችን መሄድ እንፈልጋለን ቢሉም፡ “ትግራይ ትዕወት” (ትግራይ ታሸንፋለች) የሚለው የትግራይ ሪፑብሊክ ምስረታ “ኦፊሲዮላዊ መፈክር” ካስደመጡን እና ትግራይ አገር እስክትሆን እና አገራችን የሚሏት ትግራይ እንደ አገር እስክትታወቅ ድረስ ፡ኡምራኩባ/ሱዳን’’ ከመቆየት ሌላ አማራጭ የላቸውም። “ነጭ መጭዋን” ነው የሚለው ብርቱው ኢትዮጵያዊው መድኩን በቀለ! ግልጽ ግልጹን እንነጋገር!!በነዚህ ህጸናት ላይ እየተረጨ ያለው ትምህርት ሰጪ አካላት በዓለም አቀፍ በሕግ ካልተጠየቁ  ለአገራችን በጣም አስቸጋሪ ክስትት እየፈጠሩ ናቸው። አብይ አሕመድ ጭምር ፍርድ ካልቀረበ አገር መምራት ስለማይችል ከድጡ ወደ ማጡ እየከተታት ነውና ችግሩ ብዙ ነው።

 በነዚህ ህጻናት ሕሊና “ትግራይ” እንጂ ኢትዮጵያ እንደ አገራቸው ስለማያውቋት፤ “አገራችን’ የሚሏት ትግራይ እስክታሸንፍና አገር እስክትሆንላቸው ድረስ ከመቆየት ሌላ አማራጭ የለም ሰንል በምክንያት ነው።ኢትዮጵያን እየጠሉ ትግራይን እንደ አገር እያዩ ከማኛው ጤፍ ላኩልኝ ፤ባጀቱም ሰንዴውም፤ማሩም ወተቱም ወደ ትግራይ ላኩ (እየበላን እየጠጣን ሃገረ ትግራይ እንመሰርታለን)፤ ጤፍ አምራችዋና ባጀት ላኪዋ “ኢትዮጵያ ጠላታች”ን ነችና አንታገላታለን፤ ዓይኑዋን አያሳየን የሚለው የዘንድሮ የትግሬዎች መፈክር ላንዴና ለመጨረሻ እንዲቆም ካልተደረገ ፤ አምና እና ታች አምና የተጠነሰሰው “ትግራይ ትዕወት ምስረታ ሃገረ ትግራይ” በህጻናት ሕሊና ላይ ስር የሰደደ ጭራቃዊ ችግር እንደገና መፈጠሩ አይቀሬ ነው።

ለወላጆችና ቤተሰቦቻቸው እንደወላጅነታቸው የምመክረው ምክር እነሆ!

የትም የማያደርሰው የጦርነት ቀስቃሽ መፈክር ለዳግም  የጦርነት ሰለባ ከመሆን  ልጆቻችሁ ለመመክር ባስቸኳይ እድትጀምሩ አሳስባለሁ። እንዚህ ህጻናት አገራችን ናፈቀን ይላሉ፡ ስለ "የትኛዋ አገራቸው" እያወሩ እንደሆነ ነግረውናል። ወደ ኢትዮጵያ መመለስ ከፈለጉ አገራችን ኢትዮጵያ የሚል የሕሊና መሰረት ማስያዝ አለባችሁ፡ ካልሆነ አገራችን ትግራይ ነች የሚሉ ከነሆነ “ሀገረ ትግራይ” አገር እስክትሆን ድረስ በአካል እየገለበቱ እንዳሉት አድገው ብረት ታጥቀው እስኪመጡ ድረስ ባሉበት ሰርከት ማሳየት ነው።  ከሥጋው ጿሚ ነኝ ከመረቁ ስጪኝ” ከሆነ ትንሽ ያራምድ እንደሆነ እንጂ ዘለቄታ ኣይኖሮውም።

 ወላጆችና ወዳጆች እነዚህ ልጆች ከልብ የምትወድዋቸው ከሆነ “አካለ ስንኩሎች” ከመሆን እንዲድኑ፤ በፋሺስት ርዕዮተ ዓለም አእምሮአቸው እንዲታጠቡ ከማድረግ ይልቅ ኢትዮጵያዊነታቸው እንዲወዱ በማድረግ “የድሮ አስደሳች ኑሮ ናፈቀን” እያሉ እየነገሩን ያሉት ህጽናት “የእምየ ኢትዮጵያ የድሮ ፍቅር” እንዲገባቸው ከማድረግ  ሌላ የተሻለ መንገድ የለም። ህጻናትን ለበለጠ ችግር ማነሳሳት ውጤቱ ትግራይ ውስጥ በቅርቡ ያየነው መከራ እንደገና እንዲከሰት ማድረግ ስለሆነ ከጦርነቱ በፊትም ሆነ ከጦርነቱ ወዲህ ደግመን ደጋግመን የምናስተላልፈው ምክራችን ዛሬም እነሆ አድምጡን እንላለን።

 

No comments: