Wednesday, November 23, 2022

በቴድሮስ ጸጋዬ ሚዲያ የቀረበው የትግሬ 10ቱ ቃላት ነዳፊው አሉላ ሰለሞን የሁቱ 10ርቱ ቃላት ነዳፊው ሓሰን ንገዜን የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታ ናቸው። ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 11/13/22


በቴድሮስ ጸጋዬ ሚዲያ የቀረበው የትግሬ 10ቱ ቃላት ነዳፊው አሉላ ሰለሞን የሁቱ 10ርቱ ቃላት ነዳፊው ሓሰን ንገዜን የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታ ናቸው።

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay 11/13/22

የርዕየት ሚዲያ አዘጋጁ ቴድሮስ ጸጋዬ፤ ወያኔ እንዳልለው በጣም ነበር ስጠነቀቅ የነበረው። አሁን ለይቶለታል፡ ስለዚህ በግልጽ የወያኔ ቆብ ለብሷል። ጸረ አማራ ፕሮፓጋንዲስቶች ወደ ሚዲያው ሲቀርቡ ያለወትሮው እንደ ንብ ሲናደፍ የነበረው ምጠቅ ምላሱ “ሆን ብሎ” ሲሸብበው በተደጋጋሚ አይቻለሁ። እንደፈለጉት ሲጋልቡ እያደመጠ ዝም ብሎ የፈለጉትን ሲያቦኩ ይለቃቸዋል። እንደ ቴድሮስ የመሰለ የጥያቄና መልስ ልምድ ያለው ሕግ የተማረ ሰው እንዲህ ወርዶ ሳየው ምንም እንኳ በተለያየ ጎራ ብንሰለፍም እንዲያ ያለ ምጡቅ ሕሊና ጠውልጎ በትግራይ አክራሪ እቡይነት ተሸብቦ ሳየው አዘንኩኝ።

<< ትግራይና ኢትዮጵያ ምን እና ምን ናቸው? ከዚህ በህዋላስ ወዴት?” በሚል ርዕስ አሉላ ሰለሞን ካሁን በፊት ያወጃቸው የጥላቻ አዋጆቹን አስመልክቶ  እንዲያብራራ ጠይቆት ሲመልስ አዋጆቹን እያጣመመ እንዳሻው ሲመልሳቸው ቴድሮሰ ሆን ብሎ አሉላ በጽሑፍና በድምፅ ያወጃቸው 10ቱ የአሉላ የዘር ቅስቀሳ ወንጀል መሆናቸውን እያወቀ ቴድሮስ ከ10 ውስጥ ነጠላ አዋጅዋን ብቻ መዝዞ እንዲያብራራለት ጠይቆት አሉላ እንዲያ እያወላገደ አንዳንዴም እንደጀግንነት ቆጥሮት አዋጁ “ግቡን የመታ ስኬታማ” እንደሆነ በደስታ ሲገልጽለት አጥብቆ ላላመጠየቅ እንዲህ ያለ ወንጀል በቸልታ ዝም ብሎ እንዲያላግጥ ለቅቆታል።

 ቴድሮስ ጸጋዬ የአሉላ ሰለሞን የዘር ቅስቀሳ ሕግጋቶች ተስማምቶት ካልሆነ በስተቀር ቴድሮስ ባለው የሕግ ዕውቀት አሉላን የሚወጥርበት መሟገቻ ፍሬ ነገር ያጣል ብሎ መገመት የዋህነት ነው። አሉላ ሰለሞን የደረሳቸው 10ቱ የጥላቻ መመሪያዎች ፈረንጀቹ እንደሚሉት ሕብረተሰባዊ ኑሮን የሚያደፈረስ “የሞት ቲኬት” የሚሉት ነው። ይህ አደገኛ ጥሪ ያወጀው የትግሬው “ሐሰን ንገዜ” ጋዜጠኛ ቴድሮስ ጸጋዬ አቅልሎ ማየቱ አንድ ቀን በዚህ ርዕስ ሰዎች አንስተው በታሪክ ይወያዩበታል።  

እንደምታውቁት ቴድሮስ ጸጋዬ ዳኒኤል ክብረት እንዲህ አለ ፤ሞገስ እንዲህ አለ እገሌ እንዲህ ጻፈ እገሊት እንዲህ ተናገረች እያለ እየተነተነ ጠረጴዛን የሚደበድብ በንዴት የሚንጨረጨር ሰው ነው። በትግራይ ሰው የተጻፉት ስለ 10ቱ ቃላት የጥላቻ ሕጎች በሚመለከት ግን መንጨርጨሩንስ ተውት ማታለሉን እንዳያሰናክልበት በጥንቃቄ ነበር የያዘው።

የሩዋንዳው ሓሰን ንገዜ በተመሳሳይ በወደጆቹ ሚዲያ ቀርቦ ቃለ መጠይቅ ሲደረግበት ሙልጭ አድርጎ በመካድ የተጻፉት አዋጆች እያጣመመ “ሰዎች በመሰላቸው” ሊያቀርቡት ችለው ይሆናል አንድም ማስረጃ በጽሑፌ ውስጥ ቱትሲዎቹ እንደሚሉት አላሳፈርኩም” እያለ እንደ አሉላ ሰለሞን ሲክድ በስምና በአገር የሌላ አገር ተወላጆች መሆናቸውን ካልሆነ በስተቀር “የትግሬው ሓሰን ንገዜ” እና “የሩዋንዳው ሐሰን ንገዜ” የባህሪ ተመሳሳይነት ይገርማል።

 ፍርድ ቤቱ ውስጥም ሲጠየቅ እንደ አሉላ እያጭበረበረ ሲመልስና ጣልቃ እየገባ ሄግ ፍርድቤቱ ሲረብሽ “የመሃል ዳኛዋ” (ፈረንጅ ነች) << አርፈህ ተቀመጥ ካልሆነ አስወጣሃለሁ!!>> ስትለው ነበር። በየ ኤምባሲው የሚርመጠመጠው የኢትዮጵያ የንግድ ማሕበረሰብና የሕግ ባለሞያዎች እንዲህ ያለች ዳኛ ዘንድ አሉላ ሰለሞን እንዲቀርብ ማድረግ ሳይችሉ “መቅረታቸው” ሁሌም ይገርመኛል።  

“የትግሬ 10ቱ ቃላት” ነዳፊው አሉላ ሰለሞን የሩዋንዳው “የካንጉራ” መጽሔት ዋና አዘጋጅ እንደነበረው “ሓሰን ንገዜ” የፍርድ ቤት ጥሪ ባይገጥመውም “ሓሰን ንገዜ” ግን ቀኑ ደርሶ ክስ ተመስርቶበት  ዕድሜ ይፋትህ ዕስራት በይግባኝ ወደ 35 አመት ዝቅ ብሎለት ታስሮ ይገኛል። የሁቱ ነገድ የሆነው ይህ ሰው ከተከሰሰበት አንደኛው ነጥብ በፈረንጆች ዘመን በ1990 በጻፋው “Hutu Ten Commandments” በመባል የሚታወቀው “የሁቱ 10ቱ ቃላት” በማወጁ ነበር። የትግራይ ሚዲያ ሓውስ ተብሎ የሚታወቀው የፋሺሰት ፕሮፓጋንዳ  የሚቀነቀንበት ጣቢያ መሪው “አሉላ ሰለሞን” ትግሬዎች ተግባራዊ እንዲያደርጓቸው ያስተላለፈው ጸረ አማራ፤ጸረ ኢትዮጵያ፤ ጸረ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሰ፤ ጸረ እስላም ጸረ ፕሮተስታንት፤ጸረ ካቶሊካዊት ተቋማት፤ ጸረ ኢትዮጵያዊያን ምግብ ቤቶችና ሱቅ ቤቶች እንዲሁም አማራ ያገቡ ባለትዳሮችና ፍቅረኞች በሚመለከት በሕዝብ መካካል ጸብና ጦርነት እንዲነሳ ያስተላላፋቸው ባለ 5 ርዕስ እና ባለ 5ንዑስ ዝርዝሮች የያዘ “በሕዝብና በጋብቻ ሰላምና አንድነትን የሚረብሽ የአሉላ ሰለሞን አዋጆች ከተጠቀሰው የሩዋንዳው ሰውየ ምንም ልዩነት የላቸውም በቁጥርም በዝርዝርም።

 በ10ቱ ቃላቶቹ ላይ የአጻጻፍ ጥቂት ልዩነት ቢኖራቸው እንጂ ብዙዎቹ ተመሳሳይ እና ሁሉም በሚባል መልኩ የዘር ጥላቻ እና የማሕበረሰብ ግንኙነት፤ በትዳርና በንግድ ማሕበረሶቦች ግብይት ላይ እሳት ለኳሽ እና አፍራሽ አዋጆች ያነጣጠሩ ናቸው።

ሓሰን በሃይማኖቱ ‘እስላም’ ቢሆንም “ከሁቱ በቀር ሌላ ሃይማኖት የለኝም” የሚል ነበር። ይህ ኣባባል ደግሞ በትግሬ ምሁራን እንደ ዶ/ር ሙሉወርቅ ኪ/ማርያም የመሳሰሉት “ከትግራዋይነት ሌላ ሃይማኖት የለኝም” ከሚሉት አክራሪ ብሔረተኞች የሚመሳሰል አደገኛ ሰው ነበር። ተመሳሳይነታቸው አልገረማችሁም?

የትግሬው ሓሰን ንገዜው “አሉላ ሰለሞንን”  << ትግራይና ኢትዮጵያ ምን እና ምን ናቸው? ከዚህ በህዋላስ ወዴት?” በሚል ርዕስ ቆይታ ላይ አሉላ ሰለሞንን ልክ እንደ አንጋፋ የታሪክና የፖለቲካ ሳይንቲሰት ቆጥሮ ስለታሪክ ስለ ፖለቲካ እንዲተነትን ጋብዞት “አጼ ቴድሮስ ትግሬ ናቸው” እስከማለት የደረሰ የአጼ ቴዎድሮስ የልጅ ልጆች ሁሌም የተቃወሙት ውሸት ቴድሮስ ጸጋዬ የታሪክ መሃይሙ አሉላ “ቴድሮስ ትግሬ ናቸው” ሲል ዝምብሎ አለፈው (አፄ ቴዎድሮስ ከኦሮሞ ከትግሬ ወዘተ…ልጆች ወለዱ እንጂ የትግሬ ተወላጅ አይደሉም” ይህ ደግሞ በልጅ ልጆቻቸው የተነገረ ነው። ቋራ ስለተወለዱም “ቅማንት ናቸው እያለ ብዙ ሰው ሲዘባርቅ ሰምቶ አሉላም ሲዘባርቅ ነበር” ልክ የአክሱም ዘመነ መንግሥት ትግራይ ውስጥ ስለነበር እኛ ትግሬዎችም እዛው ስለተወለድን አክሱም የትግሬ ብቻ ነው እያሉ በወቅቱ ትግሬ/ትግራይ/የሚለው እንኳ ተሰምቶም ተጽፎም በማይታወቀው አክሱም “የኛ ብቻ ነው” እያሉ ቴድሮስ ጸጋዬ እና አሉላ ቁና ቁና ሲዋሹ ነበር ።

ቴድሮስ ጸጋየ ደግሞ ማሃይሙ አሉላ ሰለሞን ስለ ዮሐንስ እንግሊዞችን ጋብዞና መርቶ ቴድሮስን እና ልጃቸው እንዲሁም ባለቤታቸውና በአገሪቷ ቅርጽ ላይ ውድመት እንዲደርስ በባንዳነት አላገለገሉም እያሉ ስለትብብራቸውም ያደረጉት ውል እንደ ጀግንንት ተቆጥሮ ሲመጻደቁ ነበር። “መተባባር” ማለት “ባንዳነት” አይደለም የሚሉን እነ ቴድሮስ ጸጋየ “አዲስ የትግሬ አማርኛ የፈጠሩ ይመስለኛል፡” ሌላ ቀርቶ የራስ አሉላ ባንዳነትም እንኳ በጣሊያኖች የተዘገበው ተጽፎም ሊያምኑ የማይፈልጉ ብዙ ትግሬዎች አሉ። ከነሱ ውስጥ አንደኞቹ “ከመሃል ትግራይ በመወለዴ እጅግ እኮራለሁ” የሚለው “ተምቤንዬው” ቴድሮስ ጸጋዬ ነው።  

ጦርነት ባህላዊ ጫዋታችን ነው፤ ከሌሎች ጋር አትገበያዩ

ወደ እሚለን “ትግሬው ሓሰን ነገዜ ቃለ መጠይቅ” ልግባ ቴድሮስ ጸጋዬ እንዲያብራራለት የጠየቀው ጥያቄ (አልጠየቀውም ላለመባል ማለት ነው) እንዲህ ይላል፡

<<  ጦርነቱ ከመጀመሩ በፊትም ሆነ በሗላ የተናገርካቸው ንግግሮች በከፍተኛ ደረጃ የቅስቀሳ “ጥሬ ዕቃ” ሆነው ጥቅም ላይ ሲውሉ ተመልክቻለሁ። የተጋባችሁ ካላችሁ ተፋቱ፤ ያልተጋባችሁ ካላችሁም አትጋቡ የሚሉ አስተያየቶች ብዙ ለቅስቀሳ ውለው ተመልክቻለሁ። እነዚህ አባባሎች ከምንም ጋር ሳናያይዛቸው ኢሞረላዊ እና “ስሕተት” አይደሉም ወይ? በነዚያ ንግግሮች ምክንያት ፤እነዚያ ቅስቀሳዎች ከተካሄዱ ሰዎችን ከተቀረው ኢትዮጵያ ክፍል አምጥቶ በማዝመት ተጋሩ እንዲገድሉ በመሆኑ ትግራይ ሕዝብ ላይ ተጨማሪ ችግር ፈጥሬ ይሆናል የሚል ልብህ ውስጥ አለ? >> ሲል ይጠይቀዋል።

አስገራሚው ቴድሮሰ ፀጋዬ ግን  በታወጀባቸው አማራ ማሕበረሰቦች ህይወትና ጋብቻ ግን ችግር ፈጥሬ ይሆናል የሚል ልብህ ውስጥ አለ ወይ? ብሎ አልጠየቀውም ፤ ቴድሮስ ያሳሰበው በዚህ ተንተርሶ በትግሬዎች ላይ የደረሰው ችግር ብቻ ነበር ትኩረቱና ልቡ! ያውም አዋጁ “ስሕተት” በሚል ቀላል ስሕተት አድርጎ  መሳሉ ይገርማል።

 

አሉላ ሲመልስ ደግሞ እንዲህ ይላል፡

<< መልካም። አመሰግናለሁ፡ መብራራት ስላላበት ለማብራራት ይህ ዕድል ሰለሰጠኸኝ አመሰግናለሁ።” በማለት ስለ ትግሬ ባህላዊ ጨዋታ ነው ስላለው የዘበራረቀውን ማምለጫውን ልተውና ስለ ጻፋቸው 10ቱ ቃላቶቹን እንዲህ ይመልሳል፡

< በወቅቱ ትግራይ ውስጥ ሚዲያ ተዘግቶ ስለነበር አዲስ አበባ ላይ የሉ የትግራይ ተወላጆች የሚደርስባቸው ዛቻና የጥላቻ ንግግር በየቀኑ ነበር የሚደርሰኝ፤ ከሌላ ማንነት ካላቸው ጋር የተጋቡ በየትዳሩ ሳይቀር በተለይ ከአማራ ጋር የተጋቡ የትግራይ ተወላጆች “እንዲህ እያለኝ ነው፤ካንቺ ነው የምጀምረው፤ልናጠፋችሁ ነው እያሉን ነው” የምትል እህት ብዙ መልዕክቶች ይደርሱኝ ስለነበር፡ ይህ ነገር ወደ ጀኖሳይ እየተቀራራበ እንደሆነ ወደ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ሳይቀር እየቀረብኩ በተለይ ፍራንስ 24 ሚዲያ ቀርቤ ይኼ ‘ጀነሳይድ” አንደሆነ አስረድቻለሁ። ሌላ ቀርቶ ከፌደራል መ/ቤቶች ከአየር መንገድ፤ከመከላከያ፤ከፖሊስ ያሉት ትግሬዎች አንተም ታውቀዋለህ “አንድ ባንድ” ተለቅመው ነው አንዲወጡ የተደረጉት።በያንዳንዱ ቤት ሊደርስ የነበረ ሰቀቀን ከምትገምተው በላይ ነበር። እና ሕጋዊ ከለላ በሚያገኙበት አካባቢዎች ትግሬዎች ሰላማዊ ትግል ማካሄድ እንዳለባቸው ነው (የቀሰቀስኩት ?) ። መጻህፍቶችን አነብ ነበር፤ የተለያዩ ጥቁር አሜሪካኖች ትግል አየሁኝ ፤የማልካም ኤክስ የማርቲን ሉተር ኪንግ ካነበብኩ በሓላ የትግራይ ሕዝብ በተመሳሳይ ትግል ማድረግ እንዳለበት “ጡቁሮች” ከጨፍጫፊዎቻችን ጋር ጸሎት አናደርግም ብለው የራሳቸው ቤተጸሎት እንደሰሩት ሁሉ እኔም ከዚያ ተመክሮ ተነስቼ…..ጦርነቱን የደገፉ ወይንም አይተው እንዳላዩ በትግራይ ጀነሳይደ ሲፈጸም ዝም ያሉ፤ በጭፍቸፋው ላይ ሲሳተፉ  …….የነበሩ ለገዳዮቹ የኢኮኖሚ ፈርጣማ ክንድ እንዲኖራቸው መፍቀድ የለበትም በሚል ነው ያደረግኩት……።  “ጋብቻ”  የምተለዋ ቃል፤ ሰዎች አትኩረዋል፤ ጓደኝነትም ጭምር አንስቻለሁ። ቴድሮስ ቤተሰቦችህ ጭምር ሲሰቃዩ ቤተሰቦችህ ያሉበትን ሁኔታ የማይጠይቅ ጓደኛ ነው ብሎ ተደላድሎ የሚቀጥል ሰው ካለ ልታሳዩኝ ይገባል። ከዚህ ሰው ጋር ወዳጅነት መቀጠል አያስፈልገኝም የማለት መብት አለህ።” እያለ እራሱን ከወንጀል ነጻ ለማድረግ ሲመጻደቅ “ሆን ብሎ ተሸብቦ የነበረው የቴድሮሰ ምላስ ድንገት አፈትልኮት እንዲህ ሲል ይጠይቀዋል

<< ግለሰባዊና… ማሕበረሰባዊ ግንኙት ምርጫ ገብቶ በዛ ደረጃ “ኢቬሲቭ” (ማግለል/ማራቅ/ ለማት ይመስለኛል እንግሊዝኛውን ሲጠቀም ቴድሮስ) ማድረግ  ከሞራላዊ ከማሕበራዊ ዕይታ አንጻር ነው ጥያቄው የነተነሳው እና ባጭሩ ንገረኝ እና ወደ ሌላ ርዕስ እንገባለን። >> የሚል ጠንካራ ጥያቄ ከመጠየቅ ይልቅ መላቅጡ የጠፋው ጥያቄ ጠይቆት

 

“ካቡጋው” አሉላ ለ10ቱ ቃላቶቹ ለማወጅ ምክንያቶቹን እንመልከታቸው፡-

 << 1-ከአማራ ጋር የተጋቡ የትግራይ ተወላጆች “እንዲህ እያለኝ ነው፤ካንቺ ነው የምጀምረው፤ልናጠፋችሁ ነው እያሉን ነው” የምትል እህት ብዙ መልዕክቶች ይደርሱኝ ስለነበር፡ ይህ ነገር ወደ ጀኖሳይ እየተቀራራበ እንደሆነ ወደ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ሳይቀር እየቀረብኩ በተለይ ፍራንስ 24 ሚዲያ ቀርቤ ይኼ ‘ጀነሳይድ” አንደሆነ አስረድቻለሁ።አሉለ በሚገርም ሁኔታ ሳቅ እያለ እያሾፈ ማሕበራዊ፤ፖለቲካዊ እና ኢኮኒሚያዊ” የሚባሉ እኮ በኢትዮጵያዊያን ዘንድ “ጀነሳይድ ነው”  ጀነሳይድ ከባድ ወንጀል ነው እኔ ለኢትዮጵያዊያን ያቀረብኩላቸው ቀላል ነበር፤ ጀነሳይዱ ለተሳተፉ ብቻ ሳይሆን “ዝም ላሉ ጭምር ነው” መልዕከቱን ያስተላለፍኩት። ኢትዮጵያዊያን የስብዕና ልዕልና የላቸውም… >> እያለ ሲያሾፍ ቴድሮስ ምንም ሳይል በፈገግታ ወደ ሌላ ጥያቄ  ሸኘው።

የማርቲን ሉተር ኪንግ ትግል አንብቤ ከዚያው የቀሰምኩት የትግል ቀመር ነው የሚለን ጋብቻ የማፍረስ አዋጁ አሉላ እንዴት እንደተረጎመው እንመለከት።  << ባሌ እንዲህ እያለኝ ነው የምትል እህት ደውላ ስለነገረቺው” አሉላ መላውን ምስኪን ሰላማዊ ኑሮ የሚገፉትን አማራና ትግሬዎች ብቻ ሳይሆን ዝምብለው ኑሮአቸውን የሚገፉ ልጆች የወለዱ ሁኔታውን በቅጡ መርምረው ሊረዱ የማይችሉ ፤ፖለቲካ ያማያውቁ አማራዎች ከዚህም ከዚያም የሌሉበትንም ጭምር አብሮ የሚደፈጥጥ “ልጆቻቻው ያለ ሁለት ወላጆች ፍቅርና እንክብካቤ’ ሳያገኙ ተለያይተው እንዲያድጉ የፍቺ ጥሪ እንዲፈጽሙ ጥሪ አደረገ (ግድያም እስራትም የሚጨምር ቢሆን ኖሮ አሉላ ዝም ባሉትንም ጭምር ያንን ያውጅ ነበር ማለት ነው) ።

ይህ ሰው ፍርድ ቤት ቀርቦ ቢሆን ኖሮ የሚሰጠው መልስ ይህ ከሆነ፤ በህግ ሙያ የተማራችሁ ኢትዮጵያዊያን በዚህ የምትሉት ነገር ካለ እስኪ እንስማ (መቸም የዝሆን ጀሮ ስላላችሁ በዚህ ጉዳይ የምትሉት ነገር ይኖራል ብየ የሚል ሕልም ባይኖረኝም) እስኪ ዕድሉን እንስጣችሁ። አሉላም ሆነ ቴድሮስ ይህንን የወንጀል ተጠያቂነት ካለ በግለሰቦች ላይ ብቻ ሊወሰድ እንደሚችል እውነታ ላይ በመመስረ እንጂ የጋራ ቅጣት (ኮሌክቲቭ ፓኒሽመንት) የተከለከለ ነው እያሉ ሁለቱም ጠረጴዛ እየደበደቡ የሚከራከሩ ናቸው። በነቴድሮስ ጸጋዬ እና “በሓሰን አሉላ” “ኮሌክቲቭ ፓኒሽመንት” የማይሰራው አማራው ላይ ሲታወጅ ሳይሆን ያ የሚሰራው ለትግሬው ብቻ ሲሆን ነው። አማራው ላይ ሲደርስ ግን ፖለቲካው ያልገባቸው ዝም ብለው ትዳራቸውን የሚያራምዱ ልጆች የወለዱ ሰላማዊያን ሁሉ ያለምሕረት እንደሚመለከት ዛሬም ሳይሸማቀቅ ደግሞታል።

“እገሌ የተባለች ስልክ ደውላ አማራው ባሌ እንዲህ እያለኝ ነው” ስላለቺኝ የፍች አዋጅ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅሪቤአለሁ፡ የሚለው አሉላ “የሩዋንዳው ሓሰን ንገዜም” ስላደረገው ጥሪ ተጠይቆ ያቀረበው ምክንያት በሚገርም ሁኔታ አሉላ የመለሰው ዐይነት ነበር የደገመው (ተመሳሳይነታቸው የሚገርም ነው!!) ቴድሮስ ድንገት ከምላሱ አምልጣው አሉላን የጠየቀውን ትክክልኛ ጥያቄ ሳይገፋበት ባጭሩ ቀጭቶት ወደ ሌላ ጥያቄ መራው። ለምን?

አሁንም አማራውን በሚመለከት ወደ ሁለተኛው ምክንያቱ ልግባ፤

እንዲህ ይላል፡-

 < ከፌደራል መ/ቤቶች ከአየር መንገድ፤ከመከላከያ፤ከፖሊስ ያሉት ትግሬዎች አንተም ታውቀዋለህ “አንድ ባንድ” ተለቅመው ነው አንዲወጡ የተደረጉት።በያንዳንዱ ቤት ሊደርስ የነበረ ሰቀቀን ከምትገምተው በላይ ነበር። እና ሕጋዊ ከለለላ በሚየገኙበት አካባቢዎች ትግሬዎች ሰላማዊ ትግል ማካሄድ እንዳለባቸው ነው ያስተላለፍኩት መልእክት >> ይላል አማራን ያገቡ ትግሬዎች ፍቺ ማድረግ እንዳለባቸው የሰጠው አንዱ ምክንያት ይህ ነው።

ከፌደራል መ/ቤቶች ከአየር መንገድ፤ከመከላከያ፤ከፖሊስ ውስጥ ያሉ ትግሬዎች “አንድ ባንድ” ተለቅመው እንዲወጡ ሲደረግ ፤ይህ ወንጀል እንዲፈጸም ያዘዘው አሉላ እየነገረን ያለው ፈጻሚዎቹ “አማራዎች እና አገሪቱ የሚመራው የአማራ መንግሥት” እንደሆነ ነው ያለ ምንም መሸማቀቅና የታሪክ ፍራቻ እየነገረን ያለው።

በዚህ የፈጠራ  ውንጀላ በትዳር ላይ ያሉ ሰላማዊያን ሰዎች እንዲፋቱ በጽሑፍ እና በቴ/ቪዥን ሲታወጅ ያፋታቸው ሰዎች በቅጡ ባይታወቅም፤ በፍርድ ቤት ዳኛ ብየና ግን የሚያስከስስ አንድን ማሕበረ ቤተሰብ ከሌለው ማሕበረ ቤተሰብ በዘር ላማናከከስ የተወጠነ የፈጠራ/የውሸት/ ሽፋን መሆኑን የሕግ አዋቂዎች አይስቱትም ብያ እገምታለሁ። ያለ መታደል ሆኖ የሕግ ምሁራኖቻችን በዚህ ሁኔታ አንስተው ሲወያዩ አላየሁም። ካሉም እኔ እንደማደርገው መጥተው ያስነብቡን።  “የትግሬው ሓሰን ንገዜ” አዋጅ ብዙ ማለት ቢቻልም አዋጆቹን ለታሪክ የዘገብኩዋው ላስጨብጣችሁ

“ የአሉላ ሰለሞን የጥላቻ አዋጅ እና ምላስ ብቻ የሆነው ተግባረቢሱ የኢትዮጵያ ማሕበረሰብ! ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)Tuesday, December 08, 2020

https://ethiopiansemay.blogspot.com/2020/12/ethiopian-semay-sunday-december-06-2020.html

ብየ የዘገብኳቸው የአሉላ 10ቱ ዘረኛ አዋጆች አንዳንዶቹን ላስታውሳችሁና ልሰናበት


3- አማራ እና የእግዚአብሔር ሰላምታን በሚመለከት።

አማራዎች “ወንድሞቼ ሰላም እንባባል እንጂ ወንድማማቾች እኮ ነን  ምናምን ብለው “ሰላም” ቢሏችሁ ሰላም እንዳትሏቸው። ከአማራ ጋር ጭራሽ እንዳታነጋግሩዋቸው! አማራ የሚባል “ሱፐር ማርኬት፤ ሞል ፤ ሌላም ሌላ ቦታ ስታገኝዋቸው ሰላም አትበሏቸው። ወዳጅነት ኖሯችሁ፤  አብራችሁ ስተበሉ ስትጠጡ የነበራችሁ ሁሉ “አቁሙ!” ጦርነቱ ሳይደግፍ “ሳይለንት ሆኖ”  (ዝም ካለም) ፤ አማራ ነውና  አቁም! የትግራይ ሕዝብ ሲበደል አሳዝኖኛል ስትል ስላልሰማሁህ ጠላት ነህ ብላችሁ መልሱለት። ወዳጅነታችሁን አብሮ መብላት መጠጣትን አቁሙ። ስለትግራይ መበደል ምንም ያልተነፈሰ ሰው “ከዚህ ሰው ጋር በጋራ አብራችሁ “እንጀራ በሳህን” የምትበሉ የምትጠጡ ከሆነ ያ የምትመገቡት ምግብ ጸር ሆኖ ይገላችሗል። የምትጠጡትም የወንድሞቻችሁ ደም ማለት ነው። ስለዚህ በተለምዶ ተዋልደናል ትዳር መስርተናል ምናምን የሚባል “ዝበዝንኬ” ዛሬ አይሰራም።

4- ኢትዮጵያ ምናምን እያለች እራስዋን በኢትዮጵያ የምትሸሽግ ከሆነ

 

ሀ-ወዲያ በሏት! ከቤታችሁ አባርሯት ወይንም አባርሩት፤

 

ለ-ግንኙነታችሁ በጣጥሱት!!

 

ሐ-ጓደኝነት ከሆነም (ወዳጅነታችሁን) በጣጥሱት፤

 

መ-ትዳር ከሆነ አፍርሱት፤ ማሕበራዊ ግንኙት ከሆነ በሙሉ በጣጥሳችሁ ወደ ቆሻሻ መጣያ  ጣሉት!

 ሠ-ባጭሩ እንዲሰማቸው ማሳየት አለባችሁ!

(2)- “ቢዝነስ” በሚመለከት የሚከተለው ጥሪ አቀርባለሁ፤

የእንጀራ ቤቶች፤ ምግብ ቤቶች የሥጋ ቤቶች በጠቅላላ የኢትዮጵያዊያን ንግድ ተቋማት በሚባሉት ሁሉም ቦታ  ግብይት እንዳታደርጉ!! በገንዘብ እቅማቸውን ማጠናከር ብቻ ሳይሆን መርዝ አስገብተው እንዳይፈጅዋችሁ። ይፈጅዋችሗልም። እነዚህ ጨካኞች ናቸው!! ብምትመገቡዋቸው ምግቦች ውስጥ መርዝ አስገብተው እንዳይፈጅዋችሁ ተጠንቀቁ። በመርዝ ተመርዛችሁ ከመሞት ለመዳን ከፈለጋችሁ መፍትሄው ትግሬዎች፤ ኤርትራኖች እና በአካባቢያችሁ ባሉት የኦሮሞ ንግድ ቤቶች/ቢዝነስ/ ካሉ ከነሱ ጋር ተገበያዩ። በተለይ ደግሞ ያቺ ልሙጥ ባንዴራ የሰቀሉ ወይንም በንግድ ቤቶቻቸው ውስጥ ካያችሁ እንዳትገበያዩ ሌላ ቀርቶ ቅመምም ጭምር እንዳትገዙ።

ኢትዮጵያ የምትባል ጠላታችን ስለሆነች በኢትዮጵያ የሚጠራ ወይንም ኢትዮጵያ የሚባል ስም ያለባቸው ማሕበራት እንዳትገቡ። መረዳጃ ማሕበር ይሁን ምንም ይሁን “ኢትዮጵያ” የሚል ካለበት ከነዚህ ማሕበረሰቦች ጋር እንዳትቀላቀሉ። በሙሉ አግልሏቸው። ገንዘባችሁ በትግሬዎች ብቻ “Spend” አድርጉ። አንዳንዱ “አሉላ ሰለሞን” “ራዲካል” ሆነ ምናምን ሊሉዋችሁ ይችላሉ። ኖ! እስኪያማቸው ድረስ መነገር አለበት። ማወቅ አለባቸው። ኢትዮጵያዊያን ትግሬዎችን አይወዱህም እና ባጭሩ ከነሱ እራስክን ነጥል።”

እያለ ያወጃቸው ለዘር ጥላቻ እና ብጥብጥ በር የሚከፍት አበራታች ዩነበሩት ዛሬ እስር ቤት ላይ የሚገኙት የሩዋንዳ ሁቱ የሚዲያ ዘረኞች የ ‘አር ቲ ኤል ኤም’ ዋናው የራዲዮ አዘጋጅ “ፌሊስ ካቡጋ” እና ‘የካንጉራ’ መጽሔት ዋና አዘጋጅ የነበረው “ሐሰን ንገዜ” የትግሬው ዘረኛ ጸረ አማራው የ10ቱ ቃላት አዋጅ አሰራጭ አሉላ ሰለሞን የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታ ናቸው።

ጽሑፉ ታሪካዊ ሰነድ ነውና ተቀባበሉት

አመሰግናለሁ

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay

No comments: