የትግሬዎች ፎኒክሲዝም
ጌታቸው ረዳ
Ethiopian Semay
11/16/22
ፎኒክስ በግሪኮች የአፈ ታሪክ ስነ ትረካ “ቀይ እና ቢጫ” ቀለም ያላት እንደ ፒኮክ እጅግ ውብ የሆነች አንስት ወፍ ነች። የፎኒክስዋ ቀለም ከትግሬዎች ፋሺዝም ባንዴራ ጋር መመሳሰል በእውቀት የተቀየሰ ይመስለኛል።
በግሪኮቹ አፈታሪክ መሰረት ፊኒክስ ሞታ ዳግም የምትወለድ ጎጆዋ ውስጥ በእሳት ተቃጥላ አመድ ከሆነች በሗላ እንደገና በዳግም ውልደት ትንፋሽ ዘርታ የመኖር ባህሪ ያላት ናት ብለው ይተርካሉ። የግሪክ አፈታሪኮቹ የሚነግሩን የፎኒክስ ህይወት በዳግም ልደት ከቀን ወደ ቀን ከምትወጣና ከምትጠልቅ ፀሐይ ጋር ያነጻጽርዋታል። ይህች ታመረኛ ወፍ ሩሲያዊያኖቹም እንዲሁ “የእሳት ወፍ” ይሏታል።የፊኒክስ ህይወት በዳግም ልደት ከቀን ወደ ቀን ከምትወጣና ከምትጠልቅ ፀሐይ ጋርም ሆነ ሞቶ የዳግም ውልደት ትረካ ፋሺስቶች እጅግ ስለሚወዱት እራሳቸውን ከዚች ወፍ ጋር በማመሳሰል ተከታዮቻቸውን ለመሳብ ተጠቅመውበታል።
በዚህ ግምባር ተጠቃሽ የትግሬዎች ፋሺዝም ነው። ባለፈው ሰሞን ዶ/ር አሰፋ ነጋሽ በለጠፍኩት ቪዲዮ በሚገርም አቀራረብ በሰፊው ሄዶበታል። በጥሞና ካደመጣችሁት የትግሬዎች ፋሺዝም እና የዚህ አመት መፈክራቸውና በሙዚቃ የሚያጅቡት ዳግም ልደታቸውን
<< ሞይትና ዘይንሞት ሓመድ ልሒስና ዝተሳእና
ዓለም ዘገረምና
መስተንክር አፋጣጥራና >>
አማርኛ ትርጉም
(ክፈጡር ሁሉ ልዩ ፍጡራን ነን
ሞተን በዳግም ልደት አመድ ልሰን የተነሳን
ዓለምን ያስገረመ መስተንክር ስነ አፈጣጠራችን)
እያሉ በንግግራቸውም ሆነ በሙዚቃዎቻቸው የሚያስተጋቡት የፎኒክስዋ ታሪክ 99% ትግሬዎች የፎኒክስዋ ዳግም ልደትና የትግሬዎች ዳግም “አመድ ልሰን የተነሳን” ቅቡልነት የመፈክራቸው ተመሳሳይነት በዚህ 3 አመት በጆሯችሁና በዓይናችሁ ያያችሁትና ያደመጣችሁት አጋጣሚ ነው።
ባለፈው ወር “ትንሳኤ ትግራይ” (ወፎች ለዳግም ትንሳኤሽ እየዘመሩ ነው) የሚለው እጅግ የሚያኖሆልል ዜማ ነገር ግን “የትግሬዎች ፎኒክ-ሲዝም” የሚሰብክ አጃቢ ሙዚቃ በቅርቡ ታትሞ ተሰራጭቷል። አውድዮው ቀድቼው የዩቱቡ አድራሻ መያዙን ስለረሳሁት አንዳገኘሁት ቪዲዮውንና ትርጉሙን አንድ ቀን ተርጉሜ አቀርብላችሗለሁ። ይህንን አመድ ልሶ የመነሳት “የትግሬዎች ፎኒክሲዝም” ታሪክ በሚመለከት ከተዋጊዎቹ መካካል እጃቸው ለመንግሥት ከሰጡት አንዲት ወጣት ባደረገቺው ቃለ መጠይቅ እንዲህ ትላላች፡
“አመድ ልሰው ሳይሆን የተነሱት የኛን ደም ልሰውና ጠጥተው ነው ከሞት የተነሱት” ስትል የትግሬ ፋሺስቶች ከ700,000 ታዳጊ ወጣቶችን ወደ እሳት ማግደውና አስፈጅተው እንደሆነ ነግራናለች። አሜሪካዊው ሰዓሊ፣ አታሚ እና አስተማሪ ሃሪ ስተርንበርግ እ.ኤ.አ. 1947 በሳለው ካርቱን ፋሺዝምን የሚመለከተው “በሞት እና ውድመት መካከል “ሃይማኖትን፣ ስነ ጽሑፍን እና ባህልን” ወደ እራሱ ርእዮት መጠቀሚያ በማድረግ ሦስቱን ማሕበራዊ እሴቶችን እያጣመመ በማይገባ መለኩ የሚረግጥ ባለ ሶስት ራስ ጭራቅ ነው” ይለዋል።
የትግሬ ፋሺስቶች ከተፈጥሮ ሕግጋት ውጭ በዚህ የትምክህትና የዳግም ውልደት ቅዠት እየተመሩ ከ1967 ዓ.ም ውልደታቸው ጀምረው እስከ ዛሬ ድረስ የራሳቸው እና የሌሎች ኢትዮጵያዊያን ህይወት በማመሳቀል ከደም ወደ ደም እየተሸጋጋሩ ቢያንስ ከውልደታቸው ጀምረው እስከ ባድሜ ጦርነት እንዲሁም በዚህ ሁለት አመት ውስጥ በጠቅላላ የሞተ ሰው ቢቆጠር ከሚሊዮን ሕዝብ በላይ አስፈጅተዋል። በዚያ የፎኒክስዋ “አመድ ልሶ መነሳት” ትርክታቸው ክልላቸውንና አጎራባች ማሕበረሰቦችን አቃጥለው መጨረሻ የፎኒክሲዝም ቅዠት አፈታሪክነት እውን መሆን እንደማይችል ሲያውቁ ትጥቃቸው ለመፍታት ተስማምተው ለጊዜውም ቢሆን አረፍ ብለዋል። ፋሺዝም ጭራሽ ካልተደመሰሰ እሳት ከመጫር የማያርፍ ርዕዮት መሆኑን ብናምንም ለጊዘየው የተቃጠለው እሳቱን ለማጋገም እርፈት ወስዷል የሚል እምነት አለኝ።
ከዚህ እራስን በማቃጠል ወደ አመድነት የመለወጥ የፎኒክሲዝም አፈታሪክ እውን ለማድረግ የሄዱበት ጉዞ ቅዠት እንደሆነ ተምረውበት ይሆን? የሚለው አብረን የምናየው ይሆናል፡፡
ሌላኛው የሞት ፍርዱን እየተጠባበቀ ያለው ለ3000 አመት አንገዛችሗለን እያለን ያለው በሁሉም መአዝናት ተወጥሮ ያለው ዋርካ ዋርካ ፖለቲከኞች እና ጋዜጠኞችን በማሰርና እንዲሰደዱ በማድረግ እንዲሁም ከአስመራ ጀምሮ እስካሁን ድረስ በኦነግ አባልነቱ እያስታጠቀ እና ጽ/ቤት ከፍቶ ደሞዝ እየከፈላቸው አንዳንዶቹንም አምባሳደሮች እና አማካሪዎቹ በማድረግ በርካታዎቹ ወንጀለኞችም ፓርላማ አስገብቶ በፖሊስና በጦር ልፍሎች አስገብቶ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የአማራ፤የጋሞ ወዘተ…እናቶችና ህጻናት እያሳረደ ሥልጣን ላይ የተኮፈሰው “የአፓርታይዱ ንጉሥ የአብይ አሕመድ” ውድቀትም እንዲሁ መሳልሉ ሲከዳው ለአይቀሬው ዳግም ሞቱና ውርደቱ ለማየት በገጉት በመጠባበቅ ላይ እንገኛለን።
ጽሑፉን ብትቀባበሉት ሌላውን ታነቁበታላችሁ!
አመሰግናለሁ
ጌታቸው ረዳ
No comments:
Post a Comment