Wednesday, November 23, 2022

በቴድሮስ ጸጋዬ ሚዲያ የቀረበው የትግሬ 10ቱ ቃላት ነዳፊው አሉላ ሰለሞን የሁቱ 10ርቱ ቃላት ነዳፊው ሓሰን ንገዜን የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታ ናቸው። ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 11/13/22


በቴድሮስ ጸጋዬ ሚዲያ የቀረበው የትግሬ 10ቱ ቃላት ነዳፊው አሉላ ሰለሞን የሁቱ 10ርቱ ቃላት ነዳፊው ሓሰን ንገዜን የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታ ናቸው።

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay 11/13/22

የርዕየት ሚዲያ አዘጋጁ ቴድሮስ ጸጋዬ፤ ወያኔ እንዳልለው በጣም ነበር ስጠነቀቅ የነበረው። አሁን ለይቶለታል፡ ስለዚህ በግልጽ የወያኔ ቆብ ለብሷል። ጸረ አማራ ፕሮፓጋንዲስቶች ወደ ሚዲያው ሲቀርቡ ያለወትሮው እንደ ንብ ሲናደፍ የነበረው ምጠቅ ምላሱ “ሆን ብሎ” ሲሸብበው በተደጋጋሚ አይቻለሁ። እንደፈለጉት ሲጋልቡ እያደመጠ ዝም ብሎ የፈለጉትን ሲያቦኩ ይለቃቸዋል። እንደ ቴድሮስ የመሰለ የጥያቄና መልስ ልምድ ያለው ሕግ የተማረ ሰው እንዲህ ወርዶ ሳየው ምንም እንኳ በተለያየ ጎራ ብንሰለፍም እንዲያ ያለ ምጡቅ ሕሊና ጠውልጎ በትግራይ አክራሪ እቡይነት ተሸብቦ ሳየው አዘንኩኝ።

<< ትግራይና ኢትዮጵያ ምን እና ምን ናቸው? ከዚህ በህዋላስ ወዴት?” በሚል ርዕስ አሉላ ሰለሞን ካሁን በፊት ያወጃቸው የጥላቻ አዋጆቹን አስመልክቶ  እንዲያብራራ ጠይቆት ሲመልስ አዋጆቹን እያጣመመ እንዳሻው ሲመልሳቸው ቴድሮሰ ሆን ብሎ አሉላ በጽሑፍና በድምፅ ያወጃቸው 10ቱ የአሉላ የዘር ቅስቀሳ ወንጀል መሆናቸውን እያወቀ ቴድሮስ ከ10 ውስጥ ነጠላ አዋጅዋን ብቻ መዝዞ እንዲያብራራለት ጠይቆት አሉላ እንዲያ እያወላገደ አንዳንዴም እንደጀግንነት ቆጥሮት አዋጁ “ግቡን የመታ ስኬታማ” እንደሆነ በደስታ ሲገልጽለት አጥብቆ ላላመጠየቅ እንዲህ ያለ ወንጀል በቸልታ ዝም ብሎ እንዲያላግጥ ለቅቆታል።

 ቴድሮስ ጸጋዬ የአሉላ ሰለሞን የዘር ቅስቀሳ ሕግጋቶች ተስማምቶት ካልሆነ በስተቀር ቴድሮስ ባለው የሕግ ዕውቀት አሉላን የሚወጥርበት መሟገቻ ፍሬ ነገር ያጣል ብሎ መገመት የዋህነት ነው። አሉላ ሰለሞን የደረሳቸው 10ቱ የጥላቻ መመሪያዎች ፈረንጀቹ እንደሚሉት ሕብረተሰባዊ ኑሮን የሚያደፈረስ “የሞት ቲኬት” የሚሉት ነው። ይህ አደገኛ ጥሪ ያወጀው የትግሬው “ሐሰን ንገዜ” ጋዜጠኛ ቴድሮስ ጸጋዬ አቅልሎ ማየቱ አንድ ቀን በዚህ ርዕስ ሰዎች አንስተው በታሪክ ይወያዩበታል።  

እንደምታውቁት ቴድሮስ ጸጋዬ ዳኒኤል ክብረት እንዲህ አለ ፤ሞገስ እንዲህ አለ እገሌ እንዲህ ጻፈ እገሊት እንዲህ ተናገረች እያለ እየተነተነ ጠረጴዛን የሚደበድብ በንዴት የሚንጨረጨር ሰው ነው። በትግራይ ሰው የተጻፉት ስለ 10ቱ ቃላት የጥላቻ ሕጎች በሚመለከት ግን መንጨርጨሩንስ ተውት ማታለሉን እንዳያሰናክልበት በጥንቃቄ ነበር የያዘው።

የሩዋንዳው ሓሰን ንገዜ በተመሳሳይ በወደጆቹ ሚዲያ ቀርቦ ቃለ መጠይቅ ሲደረግበት ሙልጭ አድርጎ በመካድ የተጻፉት አዋጆች እያጣመመ “ሰዎች በመሰላቸው” ሊያቀርቡት ችለው ይሆናል አንድም ማስረጃ በጽሑፌ ውስጥ ቱትሲዎቹ እንደሚሉት አላሳፈርኩም” እያለ እንደ አሉላ ሰለሞን ሲክድ በስምና በአገር የሌላ አገር ተወላጆች መሆናቸውን ካልሆነ በስተቀር “የትግሬው ሓሰን ንገዜ” እና “የሩዋንዳው ሐሰን ንገዜ” የባህሪ ተመሳሳይነት ይገርማል።

 ፍርድ ቤቱ ውስጥም ሲጠየቅ እንደ አሉላ እያጭበረበረ ሲመልስና ጣልቃ እየገባ ሄግ ፍርድቤቱ ሲረብሽ “የመሃል ዳኛዋ” (ፈረንጅ ነች) << አርፈህ ተቀመጥ ካልሆነ አስወጣሃለሁ!!>> ስትለው ነበር። በየ ኤምባሲው የሚርመጠመጠው የኢትዮጵያ የንግድ ማሕበረሰብና የሕግ ባለሞያዎች እንዲህ ያለች ዳኛ ዘንድ አሉላ ሰለሞን እንዲቀርብ ማድረግ ሳይችሉ “መቅረታቸው” ሁሌም ይገርመኛል።  

“የትግሬ 10ቱ ቃላት” ነዳፊው አሉላ ሰለሞን የሩዋንዳው “የካንጉራ” መጽሔት ዋና አዘጋጅ እንደነበረው “ሓሰን ንገዜ” የፍርድ ቤት ጥሪ ባይገጥመውም “ሓሰን ንገዜ” ግን ቀኑ ደርሶ ክስ ተመስርቶበት  ዕድሜ ይፋትህ ዕስራት በይግባኝ ወደ 35 አመት ዝቅ ብሎለት ታስሮ ይገኛል። የሁቱ ነገድ የሆነው ይህ ሰው ከተከሰሰበት አንደኛው ነጥብ በፈረንጆች ዘመን በ1990 በጻፋው “Hutu Ten Commandments” በመባል የሚታወቀው “የሁቱ 10ቱ ቃላት” በማወጁ ነበር። የትግራይ ሚዲያ ሓውስ ተብሎ የሚታወቀው የፋሺሰት ፕሮፓጋንዳ  የሚቀነቀንበት ጣቢያ መሪው “አሉላ ሰለሞን” ትግሬዎች ተግባራዊ እንዲያደርጓቸው ያስተላለፈው ጸረ አማራ፤ጸረ ኢትዮጵያ፤ ጸረ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሰ፤ ጸረ እስላም ጸረ ፕሮተስታንት፤ጸረ ካቶሊካዊት ተቋማት፤ ጸረ ኢትዮጵያዊያን ምግብ ቤቶችና ሱቅ ቤቶች እንዲሁም አማራ ያገቡ ባለትዳሮችና ፍቅረኞች በሚመለከት በሕዝብ መካካል ጸብና ጦርነት እንዲነሳ ያስተላላፋቸው ባለ 5 ርዕስ እና ባለ 5ንዑስ ዝርዝሮች የያዘ “በሕዝብና በጋብቻ ሰላምና አንድነትን የሚረብሽ የአሉላ ሰለሞን አዋጆች ከተጠቀሰው የሩዋንዳው ሰውየ ምንም ልዩነት የላቸውም በቁጥርም በዝርዝርም።

 በ10ቱ ቃላቶቹ ላይ የአጻጻፍ ጥቂት ልዩነት ቢኖራቸው እንጂ ብዙዎቹ ተመሳሳይ እና ሁሉም በሚባል መልኩ የዘር ጥላቻ እና የማሕበረሰብ ግንኙነት፤ በትዳርና በንግድ ማሕበረሶቦች ግብይት ላይ እሳት ለኳሽ እና አፍራሽ አዋጆች ያነጣጠሩ ናቸው።

ሓሰን በሃይማኖቱ ‘እስላም’ ቢሆንም “ከሁቱ በቀር ሌላ ሃይማኖት የለኝም” የሚል ነበር። ይህ ኣባባል ደግሞ በትግሬ ምሁራን እንደ ዶ/ር ሙሉወርቅ ኪ/ማርያም የመሳሰሉት “ከትግራዋይነት ሌላ ሃይማኖት የለኝም” ከሚሉት አክራሪ ብሔረተኞች የሚመሳሰል አደገኛ ሰው ነበር። ተመሳሳይነታቸው አልገረማችሁም?

የትግሬው ሓሰን ንገዜው “አሉላ ሰለሞንን”  << ትግራይና ኢትዮጵያ ምን እና ምን ናቸው? ከዚህ በህዋላስ ወዴት?” በሚል ርዕስ ቆይታ ላይ አሉላ ሰለሞንን ልክ እንደ አንጋፋ የታሪክና የፖለቲካ ሳይንቲሰት ቆጥሮ ስለታሪክ ስለ ፖለቲካ እንዲተነትን ጋብዞት “አጼ ቴድሮስ ትግሬ ናቸው” እስከማለት የደረሰ የአጼ ቴዎድሮስ የልጅ ልጆች ሁሌም የተቃወሙት ውሸት ቴድሮስ ጸጋዬ የታሪክ መሃይሙ አሉላ “ቴድሮስ ትግሬ ናቸው” ሲል ዝምብሎ አለፈው (አፄ ቴዎድሮስ ከኦሮሞ ከትግሬ ወዘተ…ልጆች ወለዱ እንጂ የትግሬ ተወላጅ አይደሉም” ይህ ደግሞ በልጅ ልጆቻቸው የተነገረ ነው። ቋራ ስለተወለዱም “ቅማንት ናቸው እያለ ብዙ ሰው ሲዘባርቅ ሰምቶ አሉላም ሲዘባርቅ ነበር” ልክ የአክሱም ዘመነ መንግሥት ትግራይ ውስጥ ስለነበር እኛ ትግሬዎችም እዛው ስለተወለድን አክሱም የትግሬ ብቻ ነው እያሉ በወቅቱ ትግሬ/ትግራይ/የሚለው እንኳ ተሰምቶም ተጽፎም በማይታወቀው አክሱም “የኛ ብቻ ነው” እያሉ ቴድሮስ ጸጋዬ እና አሉላ ቁና ቁና ሲዋሹ ነበር ።

ቴድሮስ ጸጋየ ደግሞ ማሃይሙ አሉላ ሰለሞን ስለ ዮሐንስ እንግሊዞችን ጋብዞና መርቶ ቴድሮስን እና ልጃቸው እንዲሁም ባለቤታቸውና በአገሪቷ ቅርጽ ላይ ውድመት እንዲደርስ በባንዳነት አላገለገሉም እያሉ ስለትብብራቸውም ያደረጉት ውል እንደ ጀግንንት ተቆጥሮ ሲመጻደቁ ነበር። “መተባባር” ማለት “ባንዳነት” አይደለም የሚሉን እነ ቴድሮስ ጸጋየ “አዲስ የትግሬ አማርኛ የፈጠሩ ይመስለኛል፡” ሌላ ቀርቶ የራስ አሉላ ባንዳነትም እንኳ በጣሊያኖች የተዘገበው ተጽፎም ሊያምኑ የማይፈልጉ ብዙ ትግሬዎች አሉ። ከነሱ ውስጥ አንደኞቹ “ከመሃል ትግራይ በመወለዴ እጅግ እኮራለሁ” የሚለው “ተምቤንዬው” ቴድሮስ ጸጋዬ ነው።  

ጦርነት ባህላዊ ጫዋታችን ነው፤ ከሌሎች ጋር አትገበያዩ

ወደ እሚለን “ትግሬው ሓሰን ነገዜ ቃለ መጠይቅ” ልግባ ቴድሮስ ጸጋዬ እንዲያብራራለት የጠየቀው ጥያቄ (አልጠየቀውም ላለመባል ማለት ነው) እንዲህ ይላል፡

<<  ጦርነቱ ከመጀመሩ በፊትም ሆነ በሗላ የተናገርካቸው ንግግሮች በከፍተኛ ደረጃ የቅስቀሳ “ጥሬ ዕቃ” ሆነው ጥቅም ላይ ሲውሉ ተመልክቻለሁ። የተጋባችሁ ካላችሁ ተፋቱ፤ ያልተጋባችሁ ካላችሁም አትጋቡ የሚሉ አስተያየቶች ብዙ ለቅስቀሳ ውለው ተመልክቻለሁ። እነዚህ አባባሎች ከምንም ጋር ሳናያይዛቸው ኢሞረላዊ እና “ስሕተት” አይደሉም ወይ? በነዚያ ንግግሮች ምክንያት ፤እነዚያ ቅስቀሳዎች ከተካሄዱ ሰዎችን ከተቀረው ኢትዮጵያ ክፍል አምጥቶ በማዝመት ተጋሩ እንዲገድሉ በመሆኑ ትግራይ ሕዝብ ላይ ተጨማሪ ችግር ፈጥሬ ይሆናል የሚል ልብህ ውስጥ አለ? >> ሲል ይጠይቀዋል።

አስገራሚው ቴድሮሰ ፀጋዬ ግን  በታወጀባቸው አማራ ማሕበረሰቦች ህይወትና ጋብቻ ግን ችግር ፈጥሬ ይሆናል የሚል ልብህ ውስጥ አለ ወይ? ብሎ አልጠየቀውም ፤ ቴድሮስ ያሳሰበው በዚህ ተንተርሶ በትግሬዎች ላይ የደረሰው ችግር ብቻ ነበር ትኩረቱና ልቡ! ያውም አዋጁ “ስሕተት” በሚል ቀላል ስሕተት አድርጎ  መሳሉ ይገርማል።

 

አሉላ ሲመልስ ደግሞ እንዲህ ይላል፡

<< መልካም። አመሰግናለሁ፡ መብራራት ስላላበት ለማብራራት ይህ ዕድል ሰለሰጠኸኝ አመሰግናለሁ።” በማለት ስለ ትግሬ ባህላዊ ጨዋታ ነው ስላለው የዘበራረቀውን ማምለጫውን ልተውና ስለ ጻፋቸው 10ቱ ቃላቶቹን እንዲህ ይመልሳል፡

< በወቅቱ ትግራይ ውስጥ ሚዲያ ተዘግቶ ስለነበር አዲስ አበባ ላይ የሉ የትግራይ ተወላጆች የሚደርስባቸው ዛቻና የጥላቻ ንግግር በየቀኑ ነበር የሚደርሰኝ፤ ከሌላ ማንነት ካላቸው ጋር የተጋቡ በየትዳሩ ሳይቀር በተለይ ከአማራ ጋር የተጋቡ የትግራይ ተወላጆች “እንዲህ እያለኝ ነው፤ካንቺ ነው የምጀምረው፤ልናጠፋችሁ ነው እያሉን ነው” የምትል እህት ብዙ መልዕክቶች ይደርሱኝ ስለነበር፡ ይህ ነገር ወደ ጀኖሳይ እየተቀራራበ እንደሆነ ወደ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ሳይቀር እየቀረብኩ በተለይ ፍራንስ 24 ሚዲያ ቀርቤ ይኼ ‘ጀነሳይድ” አንደሆነ አስረድቻለሁ። ሌላ ቀርቶ ከፌደራል መ/ቤቶች ከአየር መንገድ፤ከመከላከያ፤ከፖሊስ ያሉት ትግሬዎች አንተም ታውቀዋለህ “አንድ ባንድ” ተለቅመው ነው አንዲወጡ የተደረጉት።በያንዳንዱ ቤት ሊደርስ የነበረ ሰቀቀን ከምትገምተው በላይ ነበር። እና ሕጋዊ ከለላ በሚያገኙበት አካባቢዎች ትግሬዎች ሰላማዊ ትግል ማካሄድ እንዳለባቸው ነው (የቀሰቀስኩት ?) ። መጻህፍቶችን አነብ ነበር፤ የተለያዩ ጥቁር አሜሪካኖች ትግል አየሁኝ ፤የማልካም ኤክስ የማርቲን ሉተር ኪንግ ካነበብኩ በሓላ የትግራይ ሕዝብ በተመሳሳይ ትግል ማድረግ እንዳለበት “ጡቁሮች” ከጨፍጫፊዎቻችን ጋር ጸሎት አናደርግም ብለው የራሳቸው ቤተጸሎት እንደሰሩት ሁሉ እኔም ከዚያ ተመክሮ ተነስቼ…..ጦርነቱን የደገፉ ወይንም አይተው እንዳላዩ በትግራይ ጀነሳይደ ሲፈጸም ዝም ያሉ፤ በጭፍቸፋው ላይ ሲሳተፉ  …….የነበሩ ለገዳዮቹ የኢኮኖሚ ፈርጣማ ክንድ እንዲኖራቸው መፍቀድ የለበትም በሚል ነው ያደረግኩት……።  “ጋብቻ”  የምተለዋ ቃል፤ ሰዎች አትኩረዋል፤ ጓደኝነትም ጭምር አንስቻለሁ። ቴድሮስ ቤተሰቦችህ ጭምር ሲሰቃዩ ቤተሰቦችህ ያሉበትን ሁኔታ የማይጠይቅ ጓደኛ ነው ብሎ ተደላድሎ የሚቀጥል ሰው ካለ ልታሳዩኝ ይገባል። ከዚህ ሰው ጋር ወዳጅነት መቀጠል አያስፈልገኝም የማለት መብት አለህ።” እያለ እራሱን ከወንጀል ነጻ ለማድረግ ሲመጻደቅ “ሆን ብሎ ተሸብቦ የነበረው የቴድሮሰ ምላስ ድንገት አፈትልኮት እንዲህ ሲል ይጠይቀዋል

<< ግለሰባዊና… ማሕበረሰባዊ ግንኙት ምርጫ ገብቶ በዛ ደረጃ “ኢቬሲቭ” (ማግለል/ማራቅ/ ለማት ይመስለኛል እንግሊዝኛውን ሲጠቀም ቴድሮስ) ማድረግ  ከሞራላዊ ከማሕበራዊ ዕይታ አንጻር ነው ጥያቄው የነተነሳው እና ባጭሩ ንገረኝ እና ወደ ሌላ ርዕስ እንገባለን። >> የሚል ጠንካራ ጥያቄ ከመጠየቅ ይልቅ መላቅጡ የጠፋው ጥያቄ ጠይቆት

 

“ካቡጋው” አሉላ ለ10ቱ ቃላቶቹ ለማወጅ ምክንያቶቹን እንመልከታቸው፡-

 << 1-ከአማራ ጋር የተጋቡ የትግራይ ተወላጆች “እንዲህ እያለኝ ነው፤ካንቺ ነው የምጀምረው፤ልናጠፋችሁ ነው እያሉን ነው” የምትል እህት ብዙ መልዕክቶች ይደርሱኝ ስለነበር፡ ይህ ነገር ወደ ጀኖሳይ እየተቀራራበ እንደሆነ ወደ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ሳይቀር እየቀረብኩ በተለይ ፍራንስ 24 ሚዲያ ቀርቤ ይኼ ‘ጀነሳይድ” አንደሆነ አስረድቻለሁ።አሉለ በሚገርም ሁኔታ ሳቅ እያለ እያሾፈ ማሕበራዊ፤ፖለቲካዊ እና ኢኮኒሚያዊ” የሚባሉ እኮ በኢትዮጵያዊያን ዘንድ “ጀነሳይድ ነው”  ጀነሳይድ ከባድ ወንጀል ነው እኔ ለኢትዮጵያዊያን ያቀረብኩላቸው ቀላል ነበር፤ ጀነሳይዱ ለተሳተፉ ብቻ ሳይሆን “ዝም ላሉ ጭምር ነው” መልዕከቱን ያስተላለፍኩት። ኢትዮጵያዊያን የስብዕና ልዕልና የላቸውም… >> እያለ ሲያሾፍ ቴድሮስ ምንም ሳይል በፈገግታ ወደ ሌላ ጥያቄ  ሸኘው።

የማርቲን ሉተር ኪንግ ትግል አንብቤ ከዚያው የቀሰምኩት የትግል ቀመር ነው የሚለን ጋብቻ የማፍረስ አዋጁ አሉላ እንዴት እንደተረጎመው እንመለከት።  << ባሌ እንዲህ እያለኝ ነው የምትል እህት ደውላ ስለነገረቺው” አሉላ መላውን ምስኪን ሰላማዊ ኑሮ የሚገፉትን አማራና ትግሬዎች ብቻ ሳይሆን ዝምብለው ኑሮአቸውን የሚገፉ ልጆች የወለዱ ሁኔታውን በቅጡ መርምረው ሊረዱ የማይችሉ ፤ፖለቲካ ያማያውቁ አማራዎች ከዚህም ከዚያም የሌሉበትንም ጭምር አብሮ የሚደፈጥጥ “ልጆቻቻው ያለ ሁለት ወላጆች ፍቅርና እንክብካቤ’ ሳያገኙ ተለያይተው እንዲያድጉ የፍቺ ጥሪ እንዲፈጽሙ ጥሪ አደረገ (ግድያም እስራትም የሚጨምር ቢሆን ኖሮ አሉላ ዝም ባሉትንም ጭምር ያንን ያውጅ ነበር ማለት ነው) ።

ይህ ሰው ፍርድ ቤት ቀርቦ ቢሆን ኖሮ የሚሰጠው መልስ ይህ ከሆነ፤ በህግ ሙያ የተማራችሁ ኢትዮጵያዊያን በዚህ የምትሉት ነገር ካለ እስኪ እንስማ (መቸም የዝሆን ጀሮ ስላላችሁ በዚህ ጉዳይ የምትሉት ነገር ይኖራል ብየ የሚል ሕልም ባይኖረኝም) እስኪ ዕድሉን እንስጣችሁ። አሉላም ሆነ ቴድሮስ ይህንን የወንጀል ተጠያቂነት ካለ በግለሰቦች ላይ ብቻ ሊወሰድ እንደሚችል እውነታ ላይ በመመስረ እንጂ የጋራ ቅጣት (ኮሌክቲቭ ፓኒሽመንት) የተከለከለ ነው እያሉ ሁለቱም ጠረጴዛ እየደበደቡ የሚከራከሩ ናቸው። በነቴድሮስ ጸጋዬ እና “በሓሰን አሉላ” “ኮሌክቲቭ ፓኒሽመንት” የማይሰራው አማራው ላይ ሲታወጅ ሳይሆን ያ የሚሰራው ለትግሬው ብቻ ሲሆን ነው። አማራው ላይ ሲደርስ ግን ፖለቲካው ያልገባቸው ዝም ብለው ትዳራቸውን የሚያራምዱ ልጆች የወለዱ ሰላማዊያን ሁሉ ያለምሕረት እንደሚመለከት ዛሬም ሳይሸማቀቅ ደግሞታል።

“እገሌ የተባለች ስልክ ደውላ አማራው ባሌ እንዲህ እያለኝ ነው” ስላለቺኝ የፍች አዋጅ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅሪቤአለሁ፡ የሚለው አሉላ “የሩዋንዳው ሓሰን ንገዜም” ስላደረገው ጥሪ ተጠይቆ ያቀረበው ምክንያት በሚገርም ሁኔታ አሉላ የመለሰው ዐይነት ነበር የደገመው (ተመሳሳይነታቸው የሚገርም ነው!!) ቴድሮስ ድንገት ከምላሱ አምልጣው አሉላን የጠየቀውን ትክክልኛ ጥያቄ ሳይገፋበት ባጭሩ ቀጭቶት ወደ ሌላ ጥያቄ መራው። ለምን?

አሁንም አማራውን በሚመለከት ወደ ሁለተኛው ምክንያቱ ልግባ፤

እንዲህ ይላል፡-

 < ከፌደራል መ/ቤቶች ከአየር መንገድ፤ከመከላከያ፤ከፖሊስ ያሉት ትግሬዎች አንተም ታውቀዋለህ “አንድ ባንድ” ተለቅመው ነው አንዲወጡ የተደረጉት።በያንዳንዱ ቤት ሊደርስ የነበረ ሰቀቀን ከምትገምተው በላይ ነበር። እና ሕጋዊ ከለለላ በሚየገኙበት አካባቢዎች ትግሬዎች ሰላማዊ ትግል ማካሄድ እንዳለባቸው ነው ያስተላለፍኩት መልእክት >> ይላል አማራን ያገቡ ትግሬዎች ፍቺ ማድረግ እንዳለባቸው የሰጠው አንዱ ምክንያት ይህ ነው።

ከፌደራል መ/ቤቶች ከአየር መንገድ፤ከመከላከያ፤ከፖሊስ ውስጥ ያሉ ትግሬዎች “አንድ ባንድ” ተለቅመው እንዲወጡ ሲደረግ ፤ይህ ወንጀል እንዲፈጸም ያዘዘው አሉላ እየነገረን ያለው ፈጻሚዎቹ “አማራዎች እና አገሪቱ የሚመራው የአማራ መንግሥት” እንደሆነ ነው ያለ ምንም መሸማቀቅና የታሪክ ፍራቻ እየነገረን ያለው።

በዚህ የፈጠራ  ውንጀላ በትዳር ላይ ያሉ ሰላማዊያን ሰዎች እንዲፋቱ በጽሑፍ እና በቴ/ቪዥን ሲታወጅ ያፋታቸው ሰዎች በቅጡ ባይታወቅም፤ በፍርድ ቤት ዳኛ ብየና ግን የሚያስከስስ አንድን ማሕበረ ቤተሰብ ከሌለው ማሕበረ ቤተሰብ በዘር ላማናከከስ የተወጠነ የፈጠራ/የውሸት/ ሽፋን መሆኑን የሕግ አዋቂዎች አይስቱትም ብያ እገምታለሁ። ያለ መታደል ሆኖ የሕግ ምሁራኖቻችን በዚህ ሁኔታ አንስተው ሲወያዩ አላየሁም። ካሉም እኔ እንደማደርገው መጥተው ያስነብቡን።  “የትግሬው ሓሰን ንገዜ” አዋጅ ብዙ ማለት ቢቻልም አዋጆቹን ለታሪክ የዘገብኩዋው ላስጨብጣችሁ

“ የአሉላ ሰለሞን የጥላቻ አዋጅ እና ምላስ ብቻ የሆነው ተግባረቢሱ የኢትዮጵያ ማሕበረሰብ! ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)Tuesday, December 08, 2020

https://ethiopiansemay.blogspot.com/2020/12/ethiopian-semay-sunday-december-06-2020.html

ብየ የዘገብኳቸው የአሉላ 10ቱ ዘረኛ አዋጆች አንዳንዶቹን ላስታውሳችሁና ልሰናበት


3- አማራ እና የእግዚአብሔር ሰላምታን በሚመለከት።

አማራዎች “ወንድሞቼ ሰላም እንባባል እንጂ ወንድማማቾች እኮ ነን  ምናምን ብለው “ሰላም” ቢሏችሁ ሰላም እንዳትሏቸው። ከአማራ ጋር ጭራሽ እንዳታነጋግሩዋቸው! አማራ የሚባል “ሱፐር ማርኬት፤ ሞል ፤ ሌላም ሌላ ቦታ ስታገኝዋቸው ሰላም አትበሏቸው። ወዳጅነት ኖሯችሁ፤  አብራችሁ ስተበሉ ስትጠጡ የነበራችሁ ሁሉ “አቁሙ!” ጦርነቱ ሳይደግፍ “ሳይለንት ሆኖ”  (ዝም ካለም) ፤ አማራ ነውና  አቁም! የትግራይ ሕዝብ ሲበደል አሳዝኖኛል ስትል ስላልሰማሁህ ጠላት ነህ ብላችሁ መልሱለት። ወዳጅነታችሁን አብሮ መብላት መጠጣትን አቁሙ። ስለትግራይ መበደል ምንም ያልተነፈሰ ሰው “ከዚህ ሰው ጋር በጋራ አብራችሁ “እንጀራ በሳህን” የምትበሉ የምትጠጡ ከሆነ ያ የምትመገቡት ምግብ ጸር ሆኖ ይገላችሗል። የምትጠጡትም የወንድሞቻችሁ ደም ማለት ነው። ስለዚህ በተለምዶ ተዋልደናል ትዳር መስርተናል ምናምን የሚባል “ዝበዝንኬ” ዛሬ አይሰራም።

4- ኢትዮጵያ ምናምን እያለች እራስዋን በኢትዮጵያ የምትሸሽግ ከሆነ

 

ሀ-ወዲያ በሏት! ከቤታችሁ አባርሯት ወይንም አባርሩት፤

 

ለ-ግንኙነታችሁ በጣጥሱት!!

 

ሐ-ጓደኝነት ከሆነም (ወዳጅነታችሁን) በጣጥሱት፤

 

መ-ትዳር ከሆነ አፍርሱት፤ ማሕበራዊ ግንኙት ከሆነ በሙሉ በጣጥሳችሁ ወደ ቆሻሻ መጣያ  ጣሉት!

 ሠ-ባጭሩ እንዲሰማቸው ማሳየት አለባችሁ!

(2)- “ቢዝነስ” በሚመለከት የሚከተለው ጥሪ አቀርባለሁ፤

የእንጀራ ቤቶች፤ ምግብ ቤቶች የሥጋ ቤቶች በጠቅላላ የኢትዮጵያዊያን ንግድ ተቋማት በሚባሉት ሁሉም ቦታ  ግብይት እንዳታደርጉ!! በገንዘብ እቅማቸውን ማጠናከር ብቻ ሳይሆን መርዝ አስገብተው እንዳይፈጅዋችሁ። ይፈጅዋችሗልም። እነዚህ ጨካኞች ናቸው!! ብምትመገቡዋቸው ምግቦች ውስጥ መርዝ አስገብተው እንዳይፈጅዋችሁ ተጠንቀቁ። በመርዝ ተመርዛችሁ ከመሞት ለመዳን ከፈለጋችሁ መፍትሄው ትግሬዎች፤ ኤርትራኖች እና በአካባቢያችሁ ባሉት የኦሮሞ ንግድ ቤቶች/ቢዝነስ/ ካሉ ከነሱ ጋር ተገበያዩ። በተለይ ደግሞ ያቺ ልሙጥ ባንዴራ የሰቀሉ ወይንም በንግድ ቤቶቻቸው ውስጥ ካያችሁ እንዳትገበያዩ ሌላ ቀርቶ ቅመምም ጭምር እንዳትገዙ።

ኢትዮጵያ የምትባል ጠላታችን ስለሆነች በኢትዮጵያ የሚጠራ ወይንም ኢትዮጵያ የሚባል ስም ያለባቸው ማሕበራት እንዳትገቡ። መረዳጃ ማሕበር ይሁን ምንም ይሁን “ኢትዮጵያ” የሚል ካለበት ከነዚህ ማሕበረሰቦች ጋር እንዳትቀላቀሉ። በሙሉ አግልሏቸው። ገንዘባችሁ በትግሬዎች ብቻ “Spend” አድርጉ። አንዳንዱ “አሉላ ሰለሞን” “ራዲካል” ሆነ ምናምን ሊሉዋችሁ ይችላሉ። ኖ! እስኪያማቸው ድረስ መነገር አለበት። ማወቅ አለባቸው። ኢትዮጵያዊያን ትግሬዎችን አይወዱህም እና ባጭሩ ከነሱ እራስክን ነጥል።”

እያለ ያወጃቸው ለዘር ጥላቻ እና ብጥብጥ በር የሚከፍት አበራታች ዩነበሩት ዛሬ እስር ቤት ላይ የሚገኙት የሩዋንዳ ሁቱ የሚዲያ ዘረኞች የ ‘አር ቲ ኤል ኤም’ ዋናው የራዲዮ አዘጋጅ “ፌሊስ ካቡጋ” እና ‘የካንጉራ’ መጽሔት ዋና አዘጋጅ የነበረው “ሐሰን ንገዜ” የትግሬው ዘረኛ ጸረ አማራው የ10ቱ ቃላት አዋጅ አሰራጭ አሉላ ሰለሞን የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታ ናቸው።

ጽሑፉ ታሪካዊ ሰነድ ነውና ተቀባበሉት

አመሰግናለሁ

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay

Sunday, November 20, 2022

መልስ ለዶ/ር ደረጀ ዘለቀ መኮንን - ተግባርና ትንተና አብሮ የማይሄድ የልሂቃን ዝቅጠት ጌታቸው ረዳ Ethiopain Semay 11/20/22

 

መልስ ለዶ/ር ደረጀ ዘለቀ መኮንን - ተግባርና ትንተና አብሮ የማይሄድ የልሂቃን ዝቅጠት

ጌታቸው ረዳ

Ethiopain Semay 11/20/22

ዶ/ር ደረጀ በአዲስ አባባ ዮኒቨርሲቲ የሕግ መምህር ነው። የሕግ ትምህርት ከተማሩት ጥቂት የትግራይ እና ኢትዮጵያ ምሁራን ጋር በየፌስቡኩ ስከራከራቸው የዶ/ሩ ቃል ልጠቀምና ፡ጭራሽ የደነቆሩ” ሆነው አግኝቻቸዋለሁ። ደ/ር ደረጀ ካሁን በፊት ስለ ባሕር ወደቦቻችን አንስቶ በሰጠው አስተያየት በኢትዮጵያን ሰማይ ድረገጽ በለጠፍኩት መልስ እንዳነበባችሁት ይታወሳል። እንደ የሕግ ባለሞያነቴ እያለ ሁሌም የሚሽከረከርበት ልግጫ “ዓሰብ ዓሰብ የሚሉ ጦርነት ውስጥ እራሳቸውን አያስገቡም” እያለ የወያኔ ን ፕሮፓጋንዳ እየደገመ የሚያሾፍ የሕግ ምሁር ነው።

ኤርትራን በሚመለከት ከሦሰት ጊዜ በላይ በተጣሱ የኮሎኒያል ሕጎች እንደተከናወነ ይታወቃል (ከፈራሚዎቹ ጀምሮ በጉልበትና በሻጥር የተከናወነውን እንዳለ ሆኖ በሕግ ከተነሳም እኛ እንዳልወከልናቸውና ዓለም ሕግም እንደሚደግፈን ሳላነሳ ማለት ነው)። ኢትዮጵያዊ መሪ ሲገኝ ያኔ ጉልበት ወይንም ሕግ የሚያነሳው ጉዳይ ሆኖ ያንን አሁን አልገባባትም፡ ሆኖም  ዶ/ር ደረጀን የተቸሁበትን June 6, 2019 ነጭ ባንዴራ አውለብላቢዎች (ክፍል ሁለት) ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay ድረገጽ)   https://ethiopiansemay.blogspot.com/2019/06/ethiopian-semay.html ማንበብ ትችላላችሁ።

ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ዶ/ር ደረጀ በሁለት ሚዲያዎች ቃለ መጠይቅ አድረጓል።በርዕዮት “ቴድሮስ ፀጋዬ” እና በቪ ኦ ኤው የድሮ ጋዜጠኛ አዲሱ አበበ የሚዘጋጀው “አዲሱ ሚዲያ” በሚባለው አውታር- ከመስከረም አባራ ጋር ያደረገው”።

 ደረጀ አማራን አስመለክቶ በርካታ ሃሳቦቸን ሰንዝሯል።

 ወደ ሰጠው አስተያየት እንምልከት፤

ወደ አዲሱ ሚዲያ ከመግባቴ በፊት ከርዕዮት (ቴድሮስ ጸጋዬ) ጋር ያደረገው “በእራሱ መዳን ላይ የቆለፈው አገር? ለኳሽ ሀሳቦችና ተንኳሽ እውነቶች . . .| ቆይታ ከዶ/ር ደረጀ ዘለቀ ጋር 11/19/22” በሚል ውይይት ስለ ደርግ ስርዓት ተነስቶ ሲተነትን “ደርግ ማንም ሰው ያለ ምንክንያት አይገድልም” ይላል። “ብጹእ አቡነ ቴዎፍሎስ የተገደሉበት ምክንያት በምክንያት እንደሆነና እሳቸውም ኦሮሞ ስለሆኑ ኦነግ ጋር እየሄዱ ሲሞዳሞዱ እንደነበር ባንድ መጽሄት ስላነበብኩ ደርግ በዛው ምክንያት ገድሏቸዋል” እያለ የሌለ ታሪክ እየፈጠረ የደርግ ገዳይነት በምንክያት እንደነበር የሕግ ዕውቀቱ ጎርፍ እንደወሰደበት አመላካች ንግግር ተናገሯል።

በዛውም አላበቃም፡ ስለ አማራ ብሔረተኛነት አንስቶ ሲናገር ፡ ማንኛውንም ብሔረተኛነት ኩፍኛ ሲኮንን ይደመጣል። እኔም ያንን አይነት መስመር ሳካሂድ ነበር። ሆኖም ውሎ አድሮ የተማርኩት መሬት ላይ ያለው የአማራ መገፋት ወደ አማራዊ ብሔረተኛነት እንዲቆሙ ያደረጋቸው ምክንያት እና ደረጀ እየተናደደበትና እየዘለፋቸው ያለው አማራዊ ብሔረተኛነት ከሚለው ጋር አይገናኝም። ጥቂት የአማራ አክራሪዎች አሉ- ያ ግን ሙሉ አማራዊ ጤነኛ ብሔረተኛውን ሙሉ በሙሉ “ቁስሉን” መደፍጠጥና ምክንያቱን ማናናቅ  ሕግ እያለ የሚሽከረከርብት የመስደቢያ ቆብ ተጻራሪ ነው።

የብሔረተኛነት ትርጉም ኢትዮጵያ ውስጥ ሰሞኑን “ኦነጎች አማራዎችን  አንድ ሞት ሳይሆን ብዙ ጊዜ እንዲሞቱ አርደው እንደ ከብት ሰውነታቸውን በቢላዋ እየቆራራጡ ሲበልዋቸው እራሳቸው ባሰራጩት ቪዲዮ ተምልክታችሗል (እኔ እንኳ ገና ጫፉን ከፍቼ ሳይ ደንግጬ ማየቱን አቆምኩኝ)”። የአማራን ነብስ ለማዳን ግማሹ ጫካ ጠመንጃ ይዞ ለመዋጋት “ሃ ብሎ ለተነሳው አማራዊ ብሔረተኛውን”፤ብዙዎቹ ደግሞ በተደራጀ እና ባልተደራጀ መልኩ የአማርን ብሶት እያስተጋባ ሕዝቡ እራሱን መከላካል እንዳለበት አሁን ያለው መንግሥትና ወኪሎቹ ጋር ፍልሚያ እንዲያደርግ እና እየደረሰበት ያለው ግድያና መፈናቀል እንዲቆም እየታገለ ያለውን አማራዊው ክፍል ጭራሽ ምክንያት እንደሌለው “ጭፍን ብሔረተኛ” (ደረጀ የሚያከብረው በወያኔው አፍቃሬ “ሃገረ ትግራይ” በቴዎድሮስ ጸጋየ ገለጻ“ ያገጠጠ ብሔተኛ” የሚለውን አድርጎ  ደረጀ አማራዎቹን ይፈርጃቸዋል።

ደረጀ “ብሔረተኛነት” ሲገልጽ “ኣእምሮን ቁጭ አድርጎ በስሜት የሚነዳ ትምክሕተኛ የሚያደርግ ስሜታዊነት ነው” ሲል ይገልጸዋል። እኔ ደግሞ እነ ደረጀ የመሳሰሉትን ለማስረዳት የከበደኝ ነገር “አማራው ስለ አማራ ሲቆም ስሜት ነድቶት ሳይሆን ተግባር ነድቶት ነው”” አማራ ላይ እየደረሰ ያለው ግፍ “ስሜት” ሳይሆን “ጨካኝ ተግባር” ስለሆነ አማራው በስሜት አልተነሳሳም፤ በትምክሕት አልተነሳሳም፤የበላይነት ተሰምቶት አልተነሳም።  የገፋፉት ‘እስካሁን ድረስ በላዩ ላይ እየተደረጉ ያሉ የ30 አመት ጨካኝ ግፎች ናቸው”።  አማራው አጣብቂኝ እንደገባ ደረጀ እራሱ የውቃል። አማራው ኢትዮጵያ ብሎ ሲታገል “የድሮ ሥርዓት ናፋቂ” ይባላል፤ “አማራ ብሎ ሲነሳ ደግሞ “ያገጠጠ ብሔረተኛ” ይባላል፡ ምን ይሁን ነው የምትሉት? እዚህ ላይ “ስሜት” የት አለ? ደረጀ አማራውን ከመታረድና ከመፈናቀል ነፃ ለማውጣት ንድፍ ነድፈህ ሕዝብ የመራኸው የትግል ስልት የለም። አንተ በሌለህ ‘ባዶ ስልት’ አማራው ምን ይሁን ነው የምትለው? ዝም ብሎ እየታረደ የኦነጎች ምግብ ይሁን ነው የምትለው? ትግሉን መምራትና መንደፍ ካልቻልክ እንደ ጨዋ “አፍን መዝጋት” ምን ይከብዳል? ባንተው ቃል ኢትዮጵያ የሚባል ሕዝብ “ጨካኝ ማሕበረሰብ ነው” ስትል አማራው ጨካኝ በሆነው አርዶ ሰውን በሚበላ በጉምዝ ጫካና በኦሮሞ ከተሞችና ጫካዎች “ለእርድ ቅርጫት” ሲከበብ አማራው ብሔረተኛ ከመሆን ሌላ “ምን ይሁን” ነው የምትለው? ስሜት ጋር ምን አያያዘው? ሁሉንም ሞከረው አልተሳካም! የደሞዝ ጭማሪ አይደለም እየጠየቀ ያለው፤ የመኖርና ያለመኖር ጥያቄ ነው የተጋረጠበት። ስሜት ገባ እንበልና አማራዎች እየታረዱ ሰው የሚበሉ የሰው አራዊቶች ምግብ ሲሆኑ አይቶ በስሜትና በቁጣ ቢነሳ ይፈረድበታል? ሰው ግፍ ሲፈጸምበት ስሜታዊ ከመሆን እንዴት ሊርቅ ይቻላል (የተፈጥሮ ሕግ ነው፤ ሆኖም ምክንያታዊ ስሜት እና ትዕቢታዊ ስሜት ለየብቻ ናቸው፡ሁኔታውን መረዳት አለብን)።

የሚገርመው ደግሞ ደረጀ እንዲህ ይላል፡

<< የአማራ ብሔረተኛነት ድግሞ ጭራሽ ወደ ዕብደት የደረሰ ነው -Almost ወደ near madness የደረሰ ነው) ያ ደግሞ በኔ ላይ ሲፈጸም አይቼዋለሁ (ከመስከረም አበራ ጋር ባደረገው ውይይት ነው እየተናገረ ያለው)ባጠቃላይ “ናሺዘናሊዝም” ሲባል ከ ‘ሪዝን’ (ከምክንያት) የሚፋታበት ነው፤ ለራሱ ትርክት የሚሆኑት ፋክቶች በኪሱ ይዞ የሚሄድ የሚንቀሳቀስበት ሂደት ነው። ለምሳሌ ጀርመን የነ ሲግሞይድ የነ ካርል የነ ብዙ ሊቃውንት ሀገር ነው….ሰው እስከ መቀቀል ድረስ ያበደ ብሄረተኝነት ያደረሰው ብሔረተኛነት ነው……>>

እያለ ይተነትናል።

ደረጃ የሳተው ነገር አለ። አርደው ቀቅለው እየበሉት ያለው የኢትዮጵያ ናዚዎች አማራው ሁለት ጊዜ ተጠቂ ሆኗል። አንዱ በነ ደረጀ የመሳሰሉ መጽሐፍን ብቻ በሚያነበንቡ ምሁራን ዓኢን “ብሔረተኛ” ተብለው እንደ ናዚዎቹ ስም ሲለጠፉበት፤ ሌለው ደግሞ አራጆቹ አርደው የሚበሉት “የአብርሃም በግ”  ሆኗል።

 በሕግ አስተማሪዎች በእነ ዶ/ር ደረጀ ዘ መኮንን ፍርድ አማራው ብሔረተኛ “ከምክንያት የተፋታ፤ ለራሱ ትርክት የሚሆኑት ፋክቶች በኪሱ ይዞ የሚሄድ ተንቀሳቃሽ በስሜት የሚጓዝ” ሆኖ ሲሳል መስማት እንኳን ለአማራው ለሌላውም ያሳምማል።

አልፎም የኢትዮጵያ ብሔረተኞች ሁለት ናቸው ይላል ደረጀ

<< የመጀመሪያው ብሔረተኛው “የእየየ ናሺናልዝም” ነው፡ በድለውን ጡታችን አርደውን፤እንዲህ አድርገውን  …የሚሉት ‘የአልቃሾች ናሺናሊዝም’ ነው፤ ሁለተኛው ደግም የናዚ ጀርመን ናሺናሊዝም አይነት ነው። ይህ ደግሞ የሱፐርየር (የባላይነት) የሚደልቅ የዘር ልዕልና የሚያንጸባርቅ ነው፤ ሌለው ዘር መትቶ ደማችንን አቆሸሹት የሚለው ነው። >>

እያለ በሁለት መልክ ይተነትናቸዋል።እየየ ናሺናሊስቶቹ (አልቃሾች) የሚላቸው ኦነግና ኦሆዴዶች እንደሆኑ ይገልጻል። የበላይነት (ሱፕረማሲሰት) የሚላቸው ደግም

“ትግሬና አማራ” ናቸው።  << ለናዚው አይነት የበላይነት ለማንጸባረቅ “ፖተንሻሊቲ” ያላቸው ይላቸዋል።

በዚህ ትንታኔው ውስጥ የድሮ ታሪክ ከተነተነ በሗላ  

እያወገዘው የነበረውን ያገጠጠ የአማራ ብሔረተኛ የሚለውን “አማረራዊ ብሔረተኛ” ተመልሶ ምን ሲለው ይደመጣል? ይኼው አድምጡልኝ፤

<< አሁን የአማራ ናሺናሊዝም የሚባል የለም ነው የምለው >> << ከኖረ ግን እግዚአብሔር አይቅናው ቀንቶት ሥልጣን ከያዘ የአማራ ናሺናሊዝም የሂትለርን የሚመስለው ፋሺዝም ነው እዚች ሃገር የሚያሰፍነው! >> ሲል በሚያስቅ እና በሚያስደነግጥ ሁለት አስተያየቶች ይተነትናል።

 የሚያስቀው (አየሚያስቅ ከሆነ ) መጀመሪያ  የአማራ ብሔረተኛነት እንዳለ እራሱ እንዲህ ይገልጻል፤

<< << የአማራ ብሔረተኛነት ድግሞ ጭራሽ ወደ ዕብደት የደረሰ ነው -Almost ወደ near madness የደረሰ ነው) ያ ደግሞ በኔ ላይ ሲፈጸም አይቼዋለሁ >> ሲል ቆይቶ ተመልሶ እንደገና እራሱን በሚቃወም መንገድ

<< አሁን የአማራ ናሺናሊዝም የሚባል የለም ነው የምለው >> ይላል ዶ/ር ደረጀ ።

አንድ የሕግ ምሁር ያውም የየኒቨርሲቲ መምህር  እርሱ በሚያስተምርበት ክፍል ውስጥ እነዚህ ሁለት ተቃራኒ ነገሮች አንስቶ ቢያስትምራቸው ተማሪው የትኛውን ይያዝ ቢባል “የትኛውን ይይዛል”?

ሌለው በጣም የሚገርመው ደግሞ የትግሬዎች ናሺናሊዝም ልክ እንደ ጀርመኖቹ የትግሬ ናዚዎች/ ወይንም “የትግሬዎች ፋሺዝም” ላለማለት << “የወያኔ እየየ ብሔረተኛነት” >> እያለ ይጠራዋል። አማራው ጋር ሲደርስ ግን

<< “የአመራ ናሺናሊዝም የለም እንጂ ከኖረ እና ቀንቶት ሥልጣን ከያዘ የሂትለር የሚመስለው ፋሺዝም ነው እዚች አገር የሚያሰፍው” >> ይላል።

27 አመት ያየነው የትግሬ ፋሺዝም “በእየየ አልቃሻ ናሺዘናሊዝም” ቃል ብቻ ሲፈርጀው የአማራው ብሔረተኛ ግን  “ወያኔ ያላደረገው የናዚ አይነት ፋሺዝም” እንደሚያመጣብን ሳያመነታ ይናገራል።  ይህ የፖለቲካ ድንቁርና ወይስ ፍርደገምድል?

የአማራው ናሺናሊዝም(ያውም እንደ ሌለ እና እንደ ናዚ ይሆናል የሚለንን እርግጣኛ ሳይሆን ግምታዊ መሆኑን ነው የነገረን)  ከትግሬው ናሺናሊዝም በተለየ መንገድ “የአማራው እንደ ጀርመን ናዚ” ሊሆን የሚችልበት ምክንያት ምን ይሆን? ጠያቂውም አልጠየቀውም (ብዙም ባይጠበቅም)።

ደረጀ ለአንድ አመት “ዲፕረሺን” (ድብርት) ታምሞ በዛው ድብርት ሕመሙ ላይ ሲያስተምር እንደነበር ገልጾልናል።ከምላሱ የሚናገራቸው ካንድ የሕግ ምሁር የማይጠበቁ ቆሻሻ ቃላቶች ሲናገር “ምናልባት በጤና ቀውስ ሊሳበብበት ይችል ይሆናል” ሆኖም ደረጀ ከበሽታ የራቀ ጤናማ ሰው ነው። በሽታው ግን “ድንቁርና” ሊሆን  ይችል ይሆናል። በዚህ ድንቁርናው እንዲህ ይላል፡

<<  አይበልና አማራ ብሔረተኞች ሥልጣን ብይዙ በግልጽ ነው ዛሬ የምናገረው ‘ይኼ ወላሞ፤ ሻንቅላ ምናምን እያሉ ካገር የሚያባርርዋቸው ነው የሚመስለኝ። ወይንም ሂትለር እንዳደረገው በጋዝ ቸምበር አስገብቶ አይሆዱን አንደጨረሰው እነዚህም ሥልጣን ከወጡ የተጠቀሱትን ነገዶች ሰብሰው የሬሳ ማቃጠያ ውስጥ አስገብተው እንደሚያቃትልዋቸው ነው የማምነው።>> አብየት ቴድሮስ ጸጋዬና ወያኔዎች እንዲሁም ኦነጎች እንዴት ደስ ብሏቸው ይሆን ይህንን ሲሰሙ!?

እንዲያ ያለ ነውረኛ ትንቢት እጅግ የሚገርም ዘግናኝ የትንቢት ውንጀላ ይገልጻቸዋል ።ይህ ድንቁርና ብቻ ሳይሆን ወላሞችና ሻንቅላ የሚላቸውን ነገዶች (ሌሎችም ጭምር) አማራው ይበልጥ እንዲጠቃ ለማናከስ የሚቀሰቅስ ንግግር ነው። ፕሮፌሰር ምስፍን ወልደማርያም በጻፉት አናካሽ ጽሑፍ (ስለዚያኛው በዚህ ድረገጼ ላይ ፈትሹት አሁንም አለ) አማራን አስምልክቶ ለሶማሊዎች የጻፉትን ታሪክ የዶ/ር ደረጀ ንግግር ተመሳሳይ ብቻ ሳይሆን አጅግ የከፋ የማናከስ ቅስቀሳ ቀስቅሷል። ለዚህ ወንጀላው ደግሞ አማራ ብሔረተኞች የሚላቸውን እነ ምምህርት መስከረም አበራን የመሳሰሉት ቅን ሰዎችን ነው ለወደፊቱ ሥልጣን ቢይዙ ይህ አሰቃቂ የናዚ ድርጊት ያደርጋሉ እያለ በቆሸሸ ምላሱ የሚተነብየው። ይህ አደገኛ ንግግር ከድንቁርና ብቻ ሳይሆን ያልተፈተሸ አንድ ነገር ከውስጡ የሚረብሸው ገፊ ነገር እንዳለ ምልክት ነው።

ያ አልበቃ ብሎት “ዛሬ ታጥቄ መጥቻለሁ” ባለው ድንቁርናው ስለ ኦሮሞና አማራ ሲናገር ‘የአማራ ናሺናሊሰቶች ጋላውን ግጥም እየገጠሙ ገና ወጣት ሆኜ ነው የሰማሁት” እያለ የተገጠመን ሁሉ ገጣሚው አማራ ነው እያለ ማስረጃ ሳያቀርብ ይወነጅላል ይህንን በተመለተ ነብስ ይማር ፕሮፌሰር ጌታቸው ሃይሌ የጻፉትን ቢያነብ እመክረዋለሁ)። ይሁን እንበልና አሮሞውስ ያኔም ሆነ ዛሬ ተመሳሳይ ስድብ ሲሳደብ እንደነበረ ደረጀ ለምን ማንሳት አልፈለገም?

ዶ/ር ደረጀ ሆይ!

 በአማራና ኦሮሞ መካከል ቀዳዳ ለመክፈት ከሆነ ሙከራህ በሌሎች አናካሾች በኩል “ከቀዳዳነት አልፎ በር የሌለው የተገነጠለ ክፍት ሆኖ አማራዎች በኦሮሞ ምድር በኦሮሞ ልጆች መፈናቀል ብቻ ሳይሆን አንደ ከብት ታስረው ታርደው ስጋቸው እየታረዱ ተቀቅለው እየተበሉ ነውና እንዳንተው ኣይነት ፀብ ለኳሾች በሰነጠቁት ስንጥቅ በሩ ተገንጥሎ አማራውና ኦሮሞው ወደ እማይተያዩበት መንገድ ሄዷል።

አንተም ነግረኸናል እኮ “ከ አዲስ አባባ ወጥተህ አዳማ ድረስ መሻገር አይቻልም” ብለኸናል አደለም እንዴ? ስለዚህ ያንተ የድሮ ግጥም አምጣህ አላማጣህ ብርሌ ከነቃ አይሆን ዕቃ ነውና አናካሾች ካንተ በፊት ብርሌውን ሰንጥቀውታል።  

ያውም እኮ በአማራና ኦሮሞ ጥላቻ የለም ይል እና እያደረ እንጭጭ እየሆነ በሄደበት ንግግሩ “የኦሮሞ ሕዝብ አማራ እርጉዞችን እየጨፈጨፈ እንደሆነ” ሳይታወቀውም ሆነ አውቆ ነግሮናል።

እንዲህ ይላል፡

 << የኦሮሞ ኤሊቶች ለሰፊው ኦሮሞ ሕዝብ ይነግሩታል፤ ሰፊው ሕዝብ ይህንን ይሰማል ዋጋው የሚከፍለው ማነው ? ዕርጉዝ አማራ ትታረዳለች በዚህ “ናሬሺን” ምክንያት፤ ህጻናት አማራዎች በግፍ ይጨፈጨፋሉ። ኦሮሞ ኤሊቶች ደግሞ ለሰፊው ኦሮሞ ሕዝብ ምን ብለው ይነግሩታል ‘ምኒለክ የሴተችን ጡት ቆርጦ፤እንዲህ አድርጎ…..እየሉ ሲነግሩት የኦሮሞ ሕዝብ ገጀራውን ይይዝና በአማራ ሕዝብ ላይ ጭፍጨፋ ያካሂዳል። >>

ሲል በግልጽ ኦሮሞ ሕዝብ አማራን እየጨፈጨፈ እንደሆነ በግልጽ ነግሮናል።

ስለዚህ አማራ ስለ ጋላ ግጥም ገጥሞ ነበር ብለህ ለማናከስ የሞከርከው ምንም ፍሬ የለውም፤ 27 አመት ኦሮሞዎች ልክ እንደ ትግሬዎቹ  በልሂቆቻቸው እየተመሩ እዚህ ባለንበት እርከን ስለደረሱ በማናከሱ ጉዳይ “ተቀድመሃል” ብትባል እውነት ነው። ድንቁርናው እየተለጠጠ ሲሄድ ደግሞ ይህ ከላይ የገለጸው “ኦሮሞዎች ገጀራ ይዘው በአማራ ዕርጉዞች እና ህጻናትን ያለ ምሕረት ይጨጭፋሉ” ሲል ቆይቶ “በሊህቃን መካካል እንጂ ሕዝብ ለሕዝብ ምንም ቁርሾ የለም” እያለ “ጨፍጫፊው ሕዝብ” እያለ የነገረንን “ከደሙ ንጹህ” አድርጎ ለማቅረብ ሲጥር “እውነትም በሽታ ወይስ ድንቁርና?” ያስብላል።

አንድ ሕዝብ ገጀራ አንስቶ ዕርጉዞችና ህጻናትን ጭፍጨፋና ግድያ ውስጥ ገብቶ የወንጀል ተዋናይ ከሆነ “አገር ካፈረሰ” በሁለቱ ሕዝቦች መካካል ቁርሾ/ፀብ/የለም ማለት እንዴት እንችላለን? ከጭፍጨፋው ያመለጡ ሰዎች እኮ ወደዚያው ተመልሳችሁ ሂዱ ሲባሉ “ወደ ጠላቶቻችን መሬት አንሄድም፤ የፈጁን ሕዝቡ ጎረቤቱ ሁሉ ነው” እያሉ ሰምተናል ፤ አደለም እንዴ? ታዲያ በሕብ መካካል ጸብ የለም ብሎ ድንቁርና ምን እሚሉት የሕግ ዕውቀት ነው? አማራዎች እየታረዱ እኮ ወደ ምግብነት ተለውጠው እየተበሉ ነው! እግዚኦ መሃረነ!!!

እሰኪ በዚች በመጨረሻ ውይይቱ ላይ የዶ/ር ደረጀ ዘመኮንን ድንቁርና ልደምድም።

ልጥቀስ

<< እኔ እንደ የየኔታ መስፍን ወልደማርያም አማራ የሚባል ሕዝብ የለም የሚል እምነት አለኝ። አማራ የሚባል የለም! >>

 ይልና በየመድረኩ ሲናገር የምትሰሙት ግን “አማራና ኦሮሞ፤ የአማራ ኤሊት እንጂ ሰፊውን የአማራ ሕዝብ፡ እያለ ሲጠቀም ትሰሙታላችሁ። አማራ የሚባል ሕዝብ ከሌለ ለምንድነው እራስህ  አማራ፤አማራ፤አማራ እያልክ በየንግግርህ የምትጠቀመው? መስፍን ወልደማርያም በጃንሆይ ጊዜ በጻፉት በራሳቸው ጽሑፍ አማራ እንዳለ ባመኑበት ጽሑፋቸው እኛ ጥቂት ጸሐፍት እንዳጋለጥናቸው ሁሉ አንተም በራስህ አንደበት “አማራ” እንዳለ ተናግረሃል። እንዲህ ስትል፡

 <<<< የኦሮሞ ኤሊቶች ለሰፊው ኦሮሞ ሕዝብ ይነግሩታል፤ ሰፊው ሕዝብ ይህንን ይሰማል ዋጋው የሚከፍለው ማነው ? ዕርጉዝ አማራ ትታረዳለች በዚህ “ናሬሺን” ምክንያት፤ ህጻናት አማራዎች በግፍ ይጨፈጨፋሉ።>>>> ትላለህ አማራ እርጉዝ አማራ ሕጻን መኖሩን አምነህ እንደገና አማራ የሚባል ሕዝብ የለም ብሎ ክርክር ዕብደት ወይስ ድንቁርና?

በክፍል ሁለት ከመስከረም አበራ ጋር ያደረገው ውይይት ጊዜ ካገኘሁ ስለ ትግሬዎች ጦርነት የተናገረውን እስክመለስ ድረስ ይህንን ጽሑፍ አሰራጩት። ይህንን ስርጭት ካየሁ በሗላ እመለሰላሁ፤ካልሆነ ከንቱ ድካም መድከሙ የኔን ጊዜና ጉልበት ማባከኑ አይታየኝም።

ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay

 

 

 

 

 

 

 

Wednesday, November 16, 2022

የትግሬዎች ፎኒክሲዝም ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 11/16/22

 የትግሬዎች ፎኒክሲዝም

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay 

11/16/22

ፎኒክስ በግሪኮች የአፈ ታሪክ ስነ ትረካ “ቀይ እና ቢጫ” ቀለም ያላት እንደ ፒኮክ እጅግ ውብ የሆነች አንስት ወፍ ነች። የፎኒክስዋ ቀለም ከትግሬዎች ፋሺዝም ባንዴራ ጋር መመሳሰል በእውቀት የተቀየሰ ይመስለኛል።

በግሪኮቹ አፈታሪክ መሰረት ፊኒክስ ሞታ ዳግም የምትወለድ ጎጆዋ ውስጥ በእሳት ተቃጥላ አመድ ከሆነች በሗላ  እንደገና በዳግም ውልደት ትንፋሽ ዘርታ የመኖር ባህሪ ያላት ናት ብለው ይተርካሉ።  የግሪክ አፈታሪኮቹ የሚነግሩን የፎኒክስ ህይወት በዳግም ልደት ከቀን ወደ ቀን ከምትወጣና ከምትጠልቅ ፀሐይ ጋር ያነጻጽርዋታል። ይህች ታመረኛ ወፍ ሩሲያዊያኖቹም እንዲሁ “የእሳት ወፍ” ይሏታል።የፊኒክስ ህይወት በዳግም ልደት ከቀን ወደ ቀን ከምትወጣና ከምትጠልቅ ፀሐይ ጋርም ሆነ ሞቶ የዳግም ውልደት ትረካ ፋሺስቶች እጅግ ስለሚወዱት እራሳቸውን ከዚች ወፍ ጋር በማመሳሰል ተከታዮቻቸውን ለመሳብ ተጠቅመውበታል።

በዚህ ግምባር ተጠቃሽ የትግሬዎች ፋሺዝም ነው። ባለፈው ሰሞን ዶ/ር አሰፋ ነጋሽ በለጠፍኩት ቪዲዮ በሚገርም አቀራረብ በሰፊው ሄዶበታል። በጥሞና ካደመጣችሁት የትግሬዎች ፋሺዝም እና የዚህ አመት መፈክራቸውና በሙዚቃ የሚያጅቡት ዳግም ልደታቸውን

<< ሞይትና ዘይንሞት ሓመድ ልሒስና ዝተሳእና

   ዓለም ዘገረምና

   መስተንክር አፋጣጥራና >>

አማርኛ ትርጉም 

(ክፈጡር ሁሉ ልዩ ፍጡራን ነን

ሞተን በዳግም ልደት አመድ ልሰን የተነሳን

ዓለምን ያስገረመ መስተንክር ስነ አፈጣጠራችን)

እያሉ በንግግራቸውም ሆነ በሙዚቃዎቻቸው የሚያስተጋቡት የፎኒክስዋ ታሪክ 99% ትግሬዎች የፎኒክስዋ ዳግም ልደትና የትግሬዎች ዳግም “አመድ ልሰን የተነሳን” ቅቡልነት የመፈክራቸው ተመሳሳይነት በዚህ 3 አመት በጆሯችሁና በዓይናችሁ ያያችሁትና ያደመጣችሁት አጋጣሚ ነው።

ባለፈው ወር “ትንሳኤ ትግራይ” (ወፎች ለዳግም ትንሳኤሽ እየዘመሩ ነው) የሚለው እጅግ የሚያኖሆልል ዜማ  ነገር ግን “የትግሬዎች ፎኒክ-ሲዝም” የሚሰብክ  አጃቢ ሙዚቃ በቅርቡ ታትሞ ተሰራጭቷል። አውድዮው ቀድቼው የዩቱቡ አድራሻ መያዙን ስለረሳሁት አንዳገኘሁት ቪዲዮውንና ትርጉሙን አንድ ቀን ተርጉሜ አቀርብላችሗለሁ። ይህንን አመድ ልሶ የመነሳት “የትግሬዎች ፎኒክሲዝም” ታሪክ በሚመለከት ከተዋጊዎቹ መካካል እጃቸው ለመንግሥት ከሰጡት አንዲት ወጣት ባደረገቺው ቃለ መጠይቅ እንዲህ ትላላች፡

 “አመድ ልሰው ሳይሆን የተነሱት የኛን ደም ልሰውና ጠጥተው ነው ከሞት የተነሱት” ስትል የትግሬ ፋሺስቶች ከ700,000 ታዳጊ ወጣቶችን ወደ እሳት ማግደውና አስፈጅተው እንደሆነ ነግራናለች። አሜሪካዊው ሰዓሊ፣ አታሚ እና አስተማሪ ሃሪ ስተርንበርግ እ.ኤ.አ. 1947 በሳለው ካርቱን ፋሺዝምን የሚመለከተው “በሞት እና ውድመት መካከል “ሃይማኖትን፣ ስነ ጽሑፍን እና ባህልን” ወደ እራሱ ርእዮት መጠቀሚያ በማድረግ ሦስቱን ማሕበራዊ እሴቶችን እያጣመመ በማይገባ መለኩ የሚረግጥ ባለ ሶስት ራስ ጭራቅ ነው” ይለዋል።

የትግሬ ፋሺስቶች ከተፈጥሮ ሕግጋት ውጭ በዚህ የትምክህትና የዳግም ውልደት ቅዠት እየተመሩ ከ1967 ዓ.ም ውልደታቸው ጀምረው እስከ ዛሬ ድረስ የራሳቸው እና የሌሎች ኢትዮጵያዊያን ህይወት በማመሳቀል ከደም ወደ ደም እየተሸጋጋሩ ቢያንስ ከውልደታቸው ጀምረው እስከ ባድሜ ጦርነት እንዲሁም በዚህ ሁለት አመት ውስጥ በጠቅላላ የሞተ ሰው ቢቆጠር ከሚሊዮን ሕዝብ በላይ አስፈጅተዋል። በዚያ የፎኒክስዋ “አመድ ልሶ መነሳት” ትርክታቸው ክልላቸውንና አጎራባች ማሕበረሰቦችን አቃጥለው መጨረሻ የፎኒክሲዝም ቅዠት አፈታሪክነት እውን መሆን እንደማይችል ሲያውቁ ትጥቃቸው ለመፍታት ተስማምተው ለጊዜውም ቢሆን አረፍ ብለዋል። ፋሺዝም ጭራሽ ካልተደመሰሰ እሳት ከመጫር የማያርፍ ርዕዮት መሆኑን ብናምንም ለጊዘየው የተቃጠለው እሳቱን ለማጋገም እርፈት ወስዷል የሚል እምነት አለኝ።

ከዚህ እራስን በማቃጠል ወደ አመድነት የመለወጥ የፎኒክሲዝም አፈታሪክ እውን ለማድረግ የሄዱበት ጉዞ ቅዠት እንደሆነ ተምረውበት ይሆን? የሚለው አብረን የምናየው ይሆናል፡፡

ሌላኛው የሞት ፍርዱን እየተጠባበቀ ያለው ለ3000 አመት አንገዛችሗለን እያለን ያለው በሁሉም መአዝናት ተወጥሮ ያለው ዋርካ ዋርካ ፖለቲከኞች እና ጋዜጠኞችን በማሰርና እንዲሰደዱ በማድረግ እንዲሁም ከአስመራ ጀምሮ እስካሁን ድረስ በኦነግ አባልነቱ እያስታጠቀ እና ጽ/ቤት ከፍቶ ደሞዝ እየከፈላቸው አንዳንዶቹንም አምባሳደሮች እና አማካሪዎቹ በማድረግ በርካታዎቹ ወንጀለኞችም ፓርላማ አስገብቶ በፖሊስና በጦር ልፍሎች አስገብቶ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የአማራ፤የጋሞ ወዘተ…እናቶችና ህጻናት እያሳረደ ሥልጣን ላይ የተኮፈሰው “የአፓርታይዱ ንጉሥ የአብይ አሕመድ” ውድቀትም እንዲሁ መሳልሉ ሲከዳው ለአይቀሬው ዳግም ሞቱና ውርደቱ ለማየት በገጉት በመጠባበቅ ላይ እንገኛለን።

ጽሑፉን ብትቀባበሉት ሌላውን ታነቁበታላችሁ!

አመሰግናለሁ

ጌታቸው ረዳ

Wednesday, November 2, 2022

ከዚህ በኋላስ ወዴት? ከዚህ በኋላ ወያኔ ውስጥ ለውስጥ ተዋጊ አንጃ ይፈጥራል ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 11/2/22


ከዚህ በኋላስ ወዴት?  ከዚህ በኋላ ወያኔ ውስጥ ለውስጥ ተዋጊ አንጃ ይፈጥራል

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay

11/2/22

ወደ ትንታኔየ ከመግባት በፊት፡ የሁለቱ ፌርማ የሚነግረን በስምምነቱ መሰረት ስምምነቱ ዘላቂ ሰላም እንደማያመጣ አጭር መስመር ለማስመርአከራካሪ ቦታዎች (የወልቃይትና የራያ ማለቱ ነው) በሕገመንግሥቱ መሰረት ይፈታል ማለትወደ ቀድሞው ሁኔታ ይመለሳል፡ ማለት ነው፤ የቀድሞ ሁኔታ ማለት ደግሞበአማራና በትግራይ መካካል ያለው የመሬት ጥያቄና የዘር ማጥፋት ወንጀሎችይቀጥላል ማለት ነው። እዚህ ላይ ድሉ የማን ነው? የወያኔዎች /የትግሬዎች!! ማጠንጠኛው በዚህ ስምምነት ውስጥ ሆን ተብሎ የአማራ ማሕበረሰብ ተወካዮች እንዳይካተት የተደረገበት ዋናው ምክንያት ለዚህ የስምምነት ሴራ ነው። የአልጄሪስ ስምምነቱ እንደገና በወልቃይትና በራያ ስሙን ለውጦ ተከስቶ ይመጣል ስል የነበረው ለዚህ ነው።

አሁን ወደ ትንታኔየ ልግባ!!

ዛሬ በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ ውስጥ በወያኔ እና በኦሮሙማው መንግሥት ሲካሄድ የነበረው ድርድር ተቋጭቷል። ብዙ ሰው ደስታውን ገልጿል። የስሜት ህዋሳቶች ለመቆጣጠር አስቸጋሪዎች ናቸው። ደስ ብሎኛል፡ እልል፤ የዛሬ ቀን ልዩ የልደት በአሌ አድርጌ እቆጥረዋለሁ ..ወዘተ ..ወዘተየሚል ቡረቃ በየሚዲያው የፖለቲካ ተንታኞች ሳይቀሩ ሲቦርቁ ሰምተናል።

ሰላም ጥሩ ነው። ግን ይህ ሰላም የማን ነው? ይህ ስምምነት ወያኔ ያደረሰው የጦር ወንጀል እና ራሱም በተለያዩ ንግግሮቹ ያመነባቸው አብይ አሕመድ የፈጸማቸው ወንጀሎች ሁለቱ ፋሺስቶች የፈጸሙዋቸው አገራዊና ሰብአዊ የሕግ ጥሰቶች ማን ይጠይቃቸዋል? የሚለው ጥያቄ አልተመለሰም።

ሰዎች ለጊዜው መጀመሪያ ሰላም ይምጣ እና ከዚያ ተጠያቂነት ይመጣል የሚሉ ሊኖሩ ይችላሉ። ግን ሊሳካ አይችልም። ምክንያቱም በሁለት ተደራዳሪ ወንጀለኞች የሚካሄድ ማንኛውም ስምምነትና ውይይት የመጨረሻ ግቡሁለቱም ወንጀለኞችተጠያቂ የማያደርግ ስምምነት ነው የሚስማሙት። ዋናው ነገር ምን ስለሆነ ነው ወደ ድርድር የገቡት? “ሰውና ንብረት ስለወደመነው። ውድመት ደግሞ ከሰማይ አልመጣም በነዚህ ሁለት ተፋላሚዎች መካካል የመጣ ውድመት ነው። ውድመት ወንጀል ነው። ውድምት የፈጸሙ ወንጀለኞች ድግሞ የጦርነት ወንጀል የሚያጣራ ገለልተኛ ተቋም እስካልተመሰረተ ድረስ ይህ ሰላም የሁለቱ ወንጀለኞች ሰላም ብቻ ነው ሊሆን የሚችለው።

ከዚህ በኋላስ ወዴት? የሚለው ጥያቄ ካልተጠየቀ ውጤቱ ዞሮዞሮ በሌሎች ትንተናዎቼ እንደጻፍኩት የአልጀሪስ ስምምነት ሆኖ ይቋጫል (70 ሰው አልቆ ተጠያቂ አልባ ስምምነት) ማለት ነው።

ሁለቱም ፋሺስቶች መጨረሻ ሕዝብ አስፈጅተውና ፈጅተው አርስበርሳቸው ተቃቅፈው ያለ ምንም ተጠያቂነት ጦርነቱ ይቋጫል ብየ ደጋግሜ ከነሓሴ ጀምሮ ጽፌአለሁ፡ ስንት ሰው እንዳነበበው ባለውቅም እውነታው ይኼው ዛሬ ተፈራረሙ። ሆኖም ችግሩ እስካልተፈታ ድረስ የፋሺስት ሰላም እንጂ የማሕበረሰባችን ሰላም ሊፈታ አይችልም።

እንድታውቁልኝ የምፈልገው ወያኔ የሰላም ስምምነት ያድርግ እንጂ ትግራይ ውስጥየትግራይ ሪፑብሊክዓላማ ለማስቀጠል በውጭም በውስጥም ቁጥራቸው የማይናቅ የሚንቀሳቀሱ አክራሪ የትግራይ ብሔረተኞች አሉ። ወያኔ አሁን ይዋቀራል በሚባለው የትግራይ አዲስ አስተዳዳር ካልተካተተበት ወይንም ካልመራው፤ ውስጥ ለውስጥ አንጃዎችን መልምሎ ጦርነቱ እንዲቀጥል ያደርጋል (ተካትቶም ቢሆን ያንን ተንከሉን ይቀጥልበታል)

ምን መለቴ ነው? ትንሽ ዘርዘር ላድርገው። አሁን ያሉት የወያኔ ተዋጊዎች ትጥቃቸው ፈትተው ወደ ሰላማዊ ህይወት ይገባሉ የሚል ስምምነት ቢደረግም፤ በዚህ ስምምነት የማይስማማሙ በወንጀልና በሙስና የተጨማለቁ የወያኔ ወታደራዊ መሪዎች እና አክራሪ ብሄረተኞች አንጃ ፈጥረውአንገባምብለው (ከወያኔ ጋር ውስጥ ለውስጥ ምክክር በማድረግ) ታጣቂው ቡድን ትግሉ እንዲቀጥል ያደረጋሉ።

ይህ ደግሞ በኦነግ (አሁን በዳቦ ስሙሸኔእየተባለ የሚጠራው) ያየነው ታሪክ ትግራይ ውስጥ ይደገማል። ዞሮ ዞሮ ዋናው ጥያቄ ጦርነት ሲቆምየተፈጸመው ወንጀልመቋጫ ካልተሰጠውና በዚህ ድርድር እንዳይካተቱ የተደረጉየጦርነቱ ሰላባዎች የሆኑ ተወካዮችና ሌሎች ተዋናዮችድምጻቸው እስካልተደመጠ ድረስ የሰላም ትርጉሙ የወንጀለኞች ሰላም እንጂየተጠቂዎች (victims)” ሰላም አይደለም።

ወጣም ወረደ በተንኮል የተካነው ወያኔ ትግራይ ውስጥአንጃ ተዋጊትግራይ መፈጠሩአይቀሬነው! አንጃው ባለበትም ሆነ ዘግይቶ ጦርነት ሲቀጥልወያኔበለመደው ተንኮሉየኔ ስራ አይደለም እኔ የለሁበትምእያለ ልክ አብይ አሕመድ እና ኦነግሸኔአንጃ እንጂ የኔ ሰራዊት አይደለም ብሎእያታለለየምስኪን አማራ ገበሬዎችና ሰላማዊ ሰዎች ነብስ እየቀጠፈ እንደቀጠለው ሁሉወያኔምእንዲሁ አንጃውን አስቀድሞ በመመካከር የሽምቅ ተዋጊነቱን መቀጠሉ አይቀሬ ነው።

በዚህ አጋጣሚ አንዳንድ የሚዲያ ተንታኞች ሲሉ የምሰማው ያስገረመኝ ነገር፡እባካችሁ ጦርነቱ ይቁም ለድርድር እንዲቀመጡ ጦርነት አቁሙ ብለን እንግፋበት ስንል አምቢ ያለችሁ አሁን ይኼው ተደራደሩምን ይዋጣችሁ! እያሉ ሲናገሩ ሰምቼ ሁሌም የሚገርሙኝ ትንታኔዎች ናቸው።

የኔ ጥያቄጦርነቱን አቁሙ ፤ጦርነት እልቂት ነውብለን ብንጮህባቸውስ ወያኔዎች ጦርነቱን ያቆሙ ነበር ወይ? የሚለው ግን መልስ የላቸውም። ጦርነቱ ጀመሪዎች ወያኔዎች ወደ አማራ መሬቶች ገብተው ያሻቸው ሲያደርጉመልሱ ምን መሆን ነበረበት?” ጦርነት አይጠቅምም እባካችሁ አቁሙ ተብለው ሊሰሙ ይችሉ ነበር ወይ? አሁን ደግሞ ያለተጠያቂነትሰላም” (ጦርነቱ ቆሞ) ሰላም ተብሎ ሊጠራ ይቻላል ወይ?

ዞሮ ዞሮ ወደዳችሁም ጠላችሁም ትግራይ ውስጥ ወያኔ ውስጥ ለውስጥ አንጃ ተዋጊ ማዘጋጀቱን አይቀሬ ነው።

ጽሑፉን ተቀባባሉት፤ መረጃ የሕሊና መሳሪያ ነው

ጌታቻው ረዳ

Ethiopian Semay