ትችቴ ለማርያመዊት ሃይለ
ጌታቸው ረዳ
Ethiopian Semay
9/22/22
ሴትዮዋ ማርያማዊት ትባላላች። በግል አላውቃትም 27 አመት
ፖለቲካ ውስጥ ገብታ አይቻት አላውቅም (ከተሳሳትኩ ልታረም)። ብዙ የወያኔ ቱልቱላዎች በየማሕበራዊ ድረገጾች ሲያንጨበጭቡላትና
ሲያንቆላጵስዋት ሰምቼ፤ “ሴትየዋ እንዲህ ዓይነት ድምቀት ስታገኝ ምን እንደሆነች ገርሞኝ” በየማሕበራዊ ድረገፆች ስፈትሽ
በርካታ ቃለ መጠይቅዋና ክርክሮችዋን አደመጥኩና እንደ መሳቅም ቃጣኝ እንደ አግራሞትም አደረገኝ። ለማንኛውም እስኪ
ኢትዮጵያዊያንስ እንዴት ያያትዋል ብየ ይህንን ትችት ለናንተው አድርሻለሁ። አብረን እንየው።
ብዙዎቹን ንግግሮችዋን አደመጥኩ፡ ማኅበራዊ ፖላራይዜሽን ውስጥ ራስዋን በመዘፈቅ ‘የትግራይ ሕዝብ በኢትዮጵያ ሕዝብ
የተከዳ ሕዝብ ነው’ እያለች ስታወራ ትንሽ ስቅጥጥ የማይላት ሴት ይህች የመጀመሪያ ሳትሆን አትቀርም። የትግሬዎች መንግሥት
በስልጣን ዘመናቸው ውስጥ “አንዱ መብረቅ አንደኛው ነጎድጓድ” የሚል ዘፈን እየተዘፈነላቸው “መሬት አልበቃቸው ብላ ኤርትራኖች
ጋር አብረው ዳንኪራ እየረገጡ” ሕዝቡን ምን ያደርጉት እንደነበር በታሪክ የተዘገበ ቢሆንም ኢትዮጵያዊያንን በተለይ አማራውን
እስኪበቃቸው ድረስ ቅጥቅጥ አድርገው፤ ጨፍጨፈው፤ ከደቡብ ከምስራቅ ከምዕራብና ከየጣሻ ገጠሮች እንዲፈናቀል በመለስ ዜናዊ
ስላቅና ትዕዛዝ ሲባረር፤ እስርቤት አስገብተው አካላቱን አኮላሽተው፤ ሸንተውበት፤ ግብረሰዶም ፈጽመውበት፤ የሕሊና ቁስል
ፈጽመውበት 27 አመት ያስለቀሱትን ኢትዮጵያዊ ሕዝብ ወያኔ ከሠልጣን ሲነቀል በበቀል እና በቁጣ ሳይነሳሳ ትግሬ የሚባል በመላ
አገሪቱ እየተለቀመ በገጀራና በጥይት፤ በእሳትን በድንጋይ
የርዋንዳ ሁቱዎቹ እንዳደረጉት እንዲጨፈጨፍ ያላደረገ ጨዋው ኢትዮጵያዊ ማሕበረሰብ ትግሬ ጠሊታ እና ከዳተኛ አደርጋ ስትወነጅለው
ሕዝቡ ምን ይታዘበኛል አላለችም። የጭንቅላትዋ ንዝረት የሚገርምና አሳሳቢ ደረጃ የደረሰ ይመስላል።
ሴትዋ በብዙ ሚዲያዎች ስትጮህ አድመጫታለሁ። በትግራይ ያለው ሁኔታ
ለመግለጽ ከሚገባት በላይ ስትርቅና ስትወጠር ታዝቤአለሁ። ኢትዮ 360 በሚባለው ሚዲያ ቀርባ ወያኔዎችዎች በፖሊሲ ደረጃ
ያጸደቁት ኢሚፔሪያሊዝምን፤ ፊውዳሊዝምን፤ ቢሮክራሲ ካፒታሊዝምን እና የአማራን ማሕበረሰብን (ሁለት ጊዜ በድርጅታቸው ያጸደቁትና
የሳተሙትን በፖሊሲያቸው የተጻፈው “ያቺ የአማራ ብሔር” ብለው የጻፉላትን)
ቀንደኛ ጠላትና ‘’ማሕበራዊ ዕረፍት ማግኘት እንደሌለባት ዝተው’’ ያስተላለፉትን ድርጅታዊ ፖሊሲ፤ ሕዝቡም ተቀብሎት ጸረ አማራ
መንፈስ እንደያዘ ሲነገራት (በኔው መጽሐፍ እና ወደ ደደቢት በረሃ ከወረዱት 11 ወያኔዎች አንዱ የነበረው አስገደ ገብረስላሴ
በጻፈው መጽሐፍ ላይ ለማስረጃ ይመልከቱ) አይንዋን በጨው አጥባ
“ፍፁም ውሸት” ነው ብላ ስትከራከር አደምጫታለሁ።
በሚገርም ሆኔታ አዘጋጆቹ በማስረጃ ብስዕለ ድምፅ
ሲያቀርቡላት ደግሞ ጎንደር ውስጥ ስታድግ ግላዊ የዘረኝነት ገጠመኝዋን በማስረጃ በማቅረብ ግለሰባዊ “ነጠላ ምሳሌን” አቀርባ
ስትከራከር ገርሞኛል። በመላዋ ትግራይ ከጫፍ እስከ ጫፍ እንደ እሳት ሰደድ የተቀጣጠለው ጸረ አማራ ዘረኛ እንቅስቃሴ
(የአስገደን ቃል ልዋስና) የወያኔ ድርጅታዊ መመሪያን አልፎ አልፎ በግለሰቦች ብቻ የተንጸባረቀ አድርጋ በመሳል “ግማሽ ትግሬ
በመሆኔ ዘረኝነት ጎንደርም ሳድግ በኔ ላይ የደረሰና ምን ይሉኝ እንደነበረ ስለማውቅ “ሁሉም ቦታ የነበረ ክስተት ነው’፡
በማለት ስታጣጥለው መስማት ለወያኔ ያላት ፍቅር ከምታስደምጠን ንዝረት በቀላሉ ማድመጥ ይቻላል።
በሚገርም አስደማሚ ስላቅ ደግሞ እንዲህ በማለት የአማረውና
የትግሬው “ኬዝ” ዳኛ ላይ ቢቀርብ “ዳኛው” ይስቅ ነበር” በማለት አማራው ከትግሬው ያነሰ የጨለማ ዘመን አሳልፏል ስትል
ይቃጣታል። ይህች የሃይማኖት ሰባኪት ሴትዮ 27 አመት ምን ስትሰብክ እንደነበር ወይንም ለማን ጥብቅና ቆማ ትከራከር እንደነበር
እውቀቱ ባይኖረኝም ድፍን 30 አመት (እስካሁን ድረስ) በማን ምክንያት አማራው የግፍ ፅዋ እንዲጎነጭ እየተደረገ እንደሆነ
የሁለቱን ማሕበረሰብ ህይወት በማበላላጥ እንጭጭ ዕውቀትዋን ለማሳየት “የአማራውና የትግሬው “ኬዝ” ዳኛ ላይ ቢቀርብ “ዳኛው”
ይስቅ ነበር” ስትል አማራውን የዳኛ መሳለቂያ እንደሚሆን ትናገራለች።
አለፍ ብላም “አማራው አዎ ተጎድቷል” ግን ተላላኪ መሪዎች
ስላሉት ነው ትላለች። ለ27 አመት የአማራው የጭለማው ዘመን ተላላኪዎቹን የሚልካቸው “አውራው ላኪ” ማን ነበር? የሚል ጥያቄ
ቢቀርብላት ግን በትክክል ልትንገርን አትችልም።
ይባስ ብሎም፤ “አማራው እኮ ነው ትግራይን ለምኖ ከትግራይ
ጋር መጣበቅ የነበረበት ትላለች” *እባካችሁ ፈገግ አትበሉ፤ ፈገግ የሚያሰኝ አይደለም። ሊለመኑ የሚገባቸው የትግራይ መሪዎች
የሚባሉት እነማን ናቸው? የሚል ጥያቄ ቢቀርብላት ደግሞ “በግምት ወያኔዎች የሚል ይሆናል ብየ እገምታለሁ”። ወያኔዎች ለአማራው
ምንና ምን ነበሩ? ተላላኪዎችን ልከው “የአማራ ብሔር ማሕበራዊ
ዕረፍት እንዳታገኝ እናደርጋታለን ብለው በፖሊሲ ዝተው በተግባር 27 አመት ማሕበራ ዕረፍት የነሰዋትን ነው “ውቢትዋ ማርያማዊት
“አማራው እኮ ነው ትግራይን ለምኖ ከትግራይ ጋር መጣበቅ የነበረበት” ትላለች። ይህ ትምክሕትዋም ከፍ ስታደርገውም እንዲህ
ትላለች፡
“ትግራይ እኮ ነች ዌል አርምድ ሠራዊት ያላት እና ትግራይ እኮ ነች ጀኔራሎች ያልዋት፤ትግራይ እኮ ነች
የፖለቲካ መሪዎች ያልዋት፤ወያኔዎች እኮ ናቸው ከዓለም መሪዎች ጋር ለውይይት የሚቀርቡት ….” ትላለች።
የትግራይ ፖለቲካ ምንድ ነው ብላ ብትጠየቅ የምታውቀው
አይመለስለኝም። “ፍርድቤት ብንሄድ ዳኛው ይስቅባችኋል ካላለችን በቀር በደረቅና በብሔራዊ ወንጀል በዝርፍያና ሴትን በመድፈር
እንዲሁም በዘር ማጥፋት በግድያና ተቛማትን በማፍረስ የተካፈሉትን ንበሰገዳይ የወያኔ ወንጀለኞች የሚከተሉት ፖለቲካ “ፋሺዝም”
እንደሆነ የምታውቀው አልመሰለኝም። ደግሞ ወያኔዎች እኮ ናቸው ከዓለም መሪዎች ጋር ለውይይት የሚቀርቡት ብላን ዕርፍ!!!
ታሊባኖችም አልቃይዳኖችም፤ አል ዳወላሕ እና ዳዓሽም የኛው
ሶማሊ አልሸባባም እኮ ከዓለም መሪዎችና ወኪሎች ጋር ተደራድረዋል። የትግሬ ታሊባኖች ከ1977 ዓ.ም ጀምረው ከአማካሪዎቻቸው
እና አሰሪዎቻቸው ጋር ውይይት ማድረጋቸው ምን ብርቅ አግኝታበት አዲስ ነገር እንዳገኘችበት የሚገርም ነው።
“የሴትዮዋ የፖላራይዘሺን ንዝረት” ርኅራኄ ጋር ላስማማው ብትልም የሚስማማ አይሆንም። የስሜታዊነት አሳሳቢነቱ ከፍ እያለ ደረጃው እየዘለለ
በሄደ ቁጥር ፖላራይዜሽን ጋር የተቆራኘ ይሔድና አድማጩንም ሳይሆን ስሜተኛውንም የጤና ዕክል ውስጥ ይከተዋል። ሰዎች
በገራ-ገርነት ርኅራኄና ተቆርቋሪነት ለማሳየት ሲባል ግለሰቦች አጨቃጫቂ የፖለቲካ ታምቡሩን አድመቀው ድንገት ሳያስቡት ቀስ
በቀስ እየተሳቡ “በትልቅ የወገንተኝነት ገመድ ውስጥ ይተበተቡና ብሔረተኞች ዳንኪራ ውስጥ ይገባሉ”። ከዚች ሴትዮ የማየው
ይህንኑ ክስተት ነው።
ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay
No comments:
Post a Comment