Thursday, September 15, 2022

መቀሌ ቢገባስ ምን ትርጉም አለው? ጌታቸው ረዳ የ Ethiopian Semay ድረገጽ አዘጋጅ 9/15/2022

 

መቀሌ ቢገባስ ምን ትርጉም አለው?

ጌታቸው ረዳ

የ Ethiopian Semay ድረገጽ አዘጋጅ

9/15/2022

አብይ አሕመድ ታስሮ ለስቅላት ይቅረብ ልለው ነበር የመወያያ ትችት ርዕሴ፤ ሆኖም ታስሮ ይሰቀል ብልስ  የተኛን ደንቆሮ ሕዝብ  እና አለቅላቂ ምሁር ተይዞ ተግባራዊ እንደማይሆን ስላወቅኩኝ እሱን “መቀሌ ቢገባስ ምን ትርጉም አለው? በሚል ለወጥኩት።

መሕመት የተባለው ፈላስፋ እንዲህ ይላል፤

የሥልጣን ጥመኛው መሪ ሥልጣን ላይ ለመቆየት ሁለት ምርኩዞች አሉት።

“አንደኛው ምርኩዙ ‘የሥልጣን ጥማተኛው ‘እራሱ’ ሲሆን ፤ ሁለተኛው ምርኩዙ ደግሞ ምንም ባለማወላውል አመጽ ሳያነሳ ‘እንደከብት መንጋ’ የሚነዳለት ደንቆሮ ሕዝብ (ኢግኖራንት ማስ) ሲኖረው ሥልጣን ላይ ይቆያል።” ይላል።

አብይ ለስቅላት እንዲቀርብ ስል፤እየታሰረ፤እየተረሸነ፤እየተደበደበ፤እየተዋረደና እየተራበ የተኛ ሕዝብ ባለበት ኢትዮጵያ ምድር ውስጥ ‘ተግባራዊ ባይሆን’ እንኳ ፤ ካሁን በፊት መለስ ዜናዊን ለሞት እንደተመኘሁለት በሚገርም ትንቢትና እርግማን ምኞቴ ሰምሮ እግዚሃር ወሰደው። አብይም በዚያ የመለስ ዕጣ አንዲሸኝ ዛሬም ጸሎቴ እና አቤቱታዬን ወደ እዚህ መሬት የላከው ዲያብሎስ መልሶ እንዲወስደው ምኞቴ ዛሬም ህያው ነው።

ጦርነቱ ከተነሳ በዚህ ሦስተኛው ጦርነት ሆን ብየ ጦርነቱን በሚመለከት ምንም አልጻፍኩም (ከዚያ በፊት በነበረው ጦርነት አብይ በደረገው ማጭበርብርና በፈጸመው ሴራ አስተምሮኛል እና፤ ተቆጥቤ ነበር፤ ይህ የመጀመሪያ ትችቴ ነው።እኔ ብቻ ሳልሆን ብዙዎቹ እንደኔ ታዛቢ ሆነዋል።) በሁለተኛው ጦርነት ወያኔ እስከ ደብረብርሃን አጠገብ ደርሶ ብዙ ችግር ፈጥሮ ልጃገረዶችን፤ መነኮሳትን እና ባለትዳሮችን ደፍሮ ፤ ንብረት ዘርፎ፤ ተቋማት አውድሞ ወደ አዲስ አባባ ሲገሰግስ፤አብይ አሕመድ ዓሊ (አብዮት በላይነህ ካሳሁን) ፓርክ ውስጥ የልጆች መጫወቻ ብስክሌት ሲነዳና ችግኝ ሲተክል ነበር፤ፎቶ ሲነሳ ነበር። አይቀሬው የወያኔው ግስጋሴ ወደ አዲስ አባባ ቤተመንግሥት መሆኑን ሲያወቅ፤ የአማራን ሕዝብ በመማጸን “የኢትዮጵያ ወታደር ብቻውን ወያኔ መዋጋት አልቻለም እና በመሸነፉ እናንተ ገብታችሁ አድኑኝ” ብሎ ሲማጸን ሕዝቡ በውጭም በውስጥ አገርም ተረባርቦ ወያኔን ድባቅ መትቶ እንዲሸሽ አድርጎ ሲያበቃ በሸሽቱ ወቅት ተከታትሎ መቀሌ ገብቶ የመጨረሻ ምት ከመምታት ይልቅ ፤ ሆን ብሎ አብይ አሕመድ ግማሽ መንገድ አማራ መሬት ከተሞች ላይ አንዲመሽግ አድርጎ ጦርነቱን አስቁሞ “መለስ ኤርትራ ባድመ ጦርነት” ያደረገው ዓይነት ታሪክ ደገመው።

ከዚያ ወያኔ በያዛቸው አማራዊ ቦታዎች ብዙ ስቃይ እያደረሰ እንድ አመት ሙሉ እራሱን አደራጅቶ እንደገና አሁን ለሦስተኛ ጊዚ ጦርነት ከፍቶ ሌላ ጥፋት አስከተለ።

ትዝ ይላችሁ እንደሆነ አሁን ያለው ጦርነት (ሦስተኛው ጦርነት) ከተጀመረ አንድ ቀን ውስጥ የሚከተለው ጥያቄ ጠይቄ ነበር።

አብይ አሕመድና ብርሃኑ ጁላ ወደ አራዊትነት የተለወጠው የትግራይ ተዋጊ ሃይል እንደ በፊቱ እነኚህን መነኮሳት እናቶች ዳግም ያስደፍሯቸው ይሆን?

ጌታቸው ረዳ” 8/25/22 Ethiopian Semay”

ብየ ጠይቄ ነበር። ሓተታ ውስጥ አልገባሁም ይህችን ርዕስ ብቻ ነበር የጻፍኩት።  ከዚያ በላ ምንም አልጻፍኩም። የጠየቅኩት ጥያቄ እውነትም እውን ሆነና ብዙ እመቤቶች ተደፈሩ ተቋማት መድሃኒቶች ሁሉ ተዘርፈው ወደሙ።

በዚህ በለጠፍኩት ወያኔዎች በለጠፉት ቪዲዮ የምትመለከቱት የመንግሥት የሕዝብ ንብረት ኪሳራ ስትመለከቱ፤ በሺዎቹ ህይወት ተቀጥፎ መቀሌ ቢገባስ “ድል” ተብሎ ዳንኪራ ሊመታ በምን ሞራል ያስችላል?

መቀሌ ቢገባስ እንደገና የትግራይ ገበሬ የሰብል መሰብሰቢያ ወቅት ስለሆነ፤ ሰብሉ እስኪሰበስብ ድረስ ከትግራይ ወጥተናል ቢልስ” አብይ ማን ጠያቂ አለው? ማንም! ካሁን በፊት ግማሽ መንገድ ጦርነቱን አስቁሞ ላሁኑ ውድመት ሲዳርገን ያኔ ማን ጠየቀው? ማንም? ይባስ በሎ ጦርነቱን ያበላሹት ደካማ ኦሮሙማ የጦር መሪዎች “ተሰምቶ የማያወቅ የወታደራዊ ማዕረግ ሲሰጣቸው፤ ተቃውሞ ተሰማ? ምንም! ይባስ ብሎ ከ10,000 ፋኖዎች አስሮ አንዳንዱችንም እያሳደደ ገድሎ የሕዝባዊ ሠራዊት መሪዎችን ሲያስር ፤ጋዜጠኞችና የሰብኣዊ መብት ጠበቃዎችን ሲያስር ሕዝቡ ምን እርምጃ ወሰደ? ምንም!

ይባስ በሎ “እምነተ ቢሱ” እና አጭበርባሪው አብይ አሕመድ ፓርላማ አዳራሽ ተገኝቶ የፓርላማ አሽከሮቹን ሲያፋጥጥባቸው “የትግራይ ሕዝብ ምግብና ነዳጅ እንዳያገኝ የምትፈልጉ ጸረ የትግራይ ሕዝብ ናችሁ? ምግብ በመከለክላችሁ ‘ትግራይ እንድትገነጠል እያደረጋችሁ ነው” እያለ ፓርላማ ተብየው ሲዘልፋቸውና ሲወነጅላቸው ፓርላማዎቹም ሆነ ሕዝቡ ምን መልስሰጠ? ምንም?

አሁን መቀሌ ለመግባት ብዙ እየጣረ ነው፤ እስካሁን ድረስ አልተሳካለትም። እንደለመደበት ምላሱ “መቀሌ ከመግባቱ በፊት ጦርነቱን አቁሜአለሁ አቁሙ” ቢላቸው ወታደሮቹ ምን ይላሉ? ምንም! ሕዝቡስ ምን ሊል ነው? ምንም!  ለዚህ ሁሉ ኪሳራ አማራውና  አፋሩ ከደረሰበት በላ፤ ብዙ ነብረት፤ህይወት፤ መድሃኒት፤ ሆስፒታል፤ ሕዝባዊ ተቋማት ተዘርፈው፤ ፈራርሰው፤ መቀሌ ቢገባስ ምን ትርጉም አለው?

አብይ ለዚህ ሐላፊነት እንዲወስድና ታስሮ በስቅላት እንዲፈረድበት አቤት ብንልስ የትኛው ብርቱ ህዝባዊ አመጽ፤በየትኛው ዳኛ፤በየትኛው ፍርድቤት ተከስሶ ማስቀጣት ይቻላል? ወያኔንም አብይንም ተከስሰው በስቅላት ካልተቀጡ መቀሌ ቢገባስ ትርጉሙ ምንድ ነው? 

የለጠፍኩት ወያኔ ያሰራጩት ቪዲዮ ስትመለከቱት አንድ መንግሥት አይሮፕላን እና ድሮን ያለው ምንግሥት ምንም አይሮፕላን በሌላቸው ተራ ተዋጊ ወጣቶች በሚመርኩት መሳርያ እንዲህ የአማራን እና ዓፋርን ከተሞች አቆሽሸው ሲያወድሙ ማየት አብይ ለስቅላት መቅረብ የለበትም ትላልቸሁ? 

በአብይ አሕመድ ደካማ መሪነት ምክንያት ወያኔዎች የአማራን ከተሞችና የመንግሥት ወታደራዊ መኪኖች ዶግ አመድ ያደረጉበት አሳዛኘ ማስረጃ Ethiopian Semay

https://youtu.be/VXjYFz6TTAw

“በአጭበርባሪው ወረበላው” አብይ አሕመድ እና በአሽቃባጭ አሽከሮቹ እንዲሁም በፋሺሰቱ ወያኔ እና “ከብቶች” አሽከሮቹ ላይ ጥይት መተኮስ ካልቻላችሁ፤አመጽ ማስነሳት ካልቻላችሁ ፤ ይህ ጽሑፍ ያንቀላፋውን ሕዝብ እንዲባንን ድጋሚ ቀስቃሽ መንገድ ነውና  በጥይት ተክታችሁ ተቀባበሉት።

ጌታቸው ረዳ

 የ Ethiopian Semay ድረገጽ አዘጋጅ

No comments: