Sunday, July 24, 2022

ወንጀለኞች ከወንጀለኞች አቻቸው ጋር መደራደር ወንጀለኞችን ከተጠያቂነት ነጻ የማድረግ ሴራ ነው! ጌታቸው ረዳ ETHIOPIAN SEMAY 7/23/22


 

ወንጀለኞች ከወንጀለኞች አቻቸው ጋር መደራደር ወንጀለኞችን ከተጠያቂነት ነጻ

የማድረግ ሴራ ነው!

ጌታቸው  ረዳ

ETHIOPIAN SEMAY 7/23/22



በሺዎች የሰው ሕይወት ጨፍጭፈው ያለምን ምንም ስጋት  በነጻ የሚኖርባት አገር ኢትዮጵያ ብቻ ነች። ያውም በገደሉና በዘረፉ ቁጥር ሥልጣን የሚያገኙበት አገር ብቸኛዋ አገር ኢትዮጵያ ብቻ ነች።አሳዛኝ!

 ታስታውሱ እንደሆነ ከባድሜ ጦርነት በሗላ ሁለቱም ወንጀለኞች (ወያኔ እና ሻዕቢያ) በመደራደር 70 ሺ የሚገመት ሕዝብ በሁለቱም ወገን ህይወቱ እንደተቀጠፈ ይታወሳል። ታዲያ በወቅቱ ከድርድሩ በፊት እኔ  “የሁለት ወንጀለኞች ድርድር ተጠያቂነትን የሚሸሽግ ተንኮል” በሚል ርዕስ በጋዜጣ (ሓዋርያ ይመስለኛል) አሳትሜ ለሕዝብ አስነብቤ ነበር። ታዲያ በወቅቱ ሰሚ ታጣ እና “ከባድሜ መልስ ወደ መለስ” እያሉ ተቃዋሚዎች ነን ባዮች ሕዝብን ሲያታልሉት ባጁና እንደገመትኩት በዛው ወቅት የተፈጸመ የጦርንትና የሕግ መጣስ አንድም ሰው ተጠያቂ ሳይሆን- ተቃዋሚው የፈከረው መፈክር እውን ሳይሆን ለመለስ የተባለው ብትር መለስ ዜናዊ  መልሶ ወደ ተቃዋሚው አዞረውና የተቃዋሚውን ብልት ማኮላሸት ተያያዘው። በሚገርም ተመሳሳይነት “ወያኔ ከደብረሲና ተመትቶ ካፈገፈገ በሗላ” አብይ አሕመድም ልክ እንደ መለስ ተቃዋሚውን ወደ እስር በመክተትና በመደብደብ ያንን ደገመው። ተመሳሳይነቱን አልገረማችሁም?

በወቅቱ በጦርነቱ ለደረሰው ጉዳት አንድም ሰው ሳይጠየቅ እንደገና እደግመለሁ “አንድም ሰው ተጠያቂ ሳይሆን” ባድሜንም አስረከበው ወንጀለኞችም ይኸየው እስካሁን ሥልጣን ላይ አሉ፡ ይባስ ብሎ  እነኛ ወንጀለኞች ዛሬም አዲስ ጦርነት ከፍተው ሕዝብን አሳለቁት፤ንግድ፤ቤተጸሎት አፈረሱ ፤ ሰቶች መነኮሳት ደፈሩ። ተጠያቂነት አልቦ! ጭጭ!

አሁን ደግሞ ያንን ተመሳሳይ የባድሜን የኪሳራ ድርድር ለመድገም ኬኒያ እንዲገናኙ እየተሸባሸቡ ነው።

 እኔ በሁለቱም  በኩል የሚደረገው ድርድር እቃዋማለሁ። ሁለቱም ወደ ዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት ቀርበው እንዲጠየቁና “የዘር ማጥፋት ወንጀል ሕግ አዋቂዎች፤ ሰብኣዊ ድርጅቶች፤ሲቪልና ወታደራዊ የሕግ ባለሞያዎች፤የሃይሞኖት እና የሞያ፤የሴቶች መብት ተወካዮች፤ ከሁለቱም ሕዝብ በኩል ለድርድር እንዲቀርቡና አለም አቀፍ የድርድር ባለሞያዎች፤ ተወጣጥተው ሁለቱም ወንጀለኞች ያገለለ ድርድሩ መካሄድ አለበት እላለሁ። ካልሆነ እያንዳንዱ ወገን ወንጀል ስለፈጸመ እራሱን “ኢንክሪመንት” የሚወነጅል ድርደር ስለማያደርግ ሁለቱም ከጠያቂነት ነፃ የሚያደርግ ድርግ አድርገው ሕዝቡን ሌላ ጦርነት ውስጥ ያስገቡታል።

ድርድሩ አይሰምርም እንጂ (ምክንያቱም ጦርነት ለወያኔም ለኦሮሙማውም የሥልጣን ምንጭ በመሆኑ) ድርድሩ (ከኖረ) ከላይ በጠቀስኩት ምክንያት የህግ የበላይነትን መሰረታዊ መርሆ ይጎዳል።

ጦርነት ከፍተው ወንጀለኞች ወንጀል ፈጽመው ለድርድር ከቀረቡ ወንጀለኞቹ እራስ በራስ እንዲደራደሩ ከተፈቀደ ሕግን በጣሰ መልኩ ራሳቸውን ነፃ በሚያደርግ መብት እንዲያገኙ መደረግ የለበትም።  ሁላችንም በሕግ  እንድንገዛ ለራሳችን ካስገዛን እነሱም እንዲሁ መገዛት ነበረባቸው፡  ይሁን እንጂ በተግባር ግን ወንጀለኞቹ  ባለሥልጣኖችና ተደራዳሪዎች ስለሆኑ  በተለመደው አተገባበር ላይ  ሕዝብን ባገለለ መልኩ ውሳኔዎችን ወስነው ከተፈራራሙ ድርድሩና ውጤቱ በባድሜ ጦርነት ያየነው ኣይነት ሴራና ውጤት እናያለን።

በሚሊዮን የሞቆጠር የወያኔ ታጣቂ አብይ በድርድሩ እንዲፈታ ይጠይቃል ወይ ብለን አንገምትም። ለይስሙላ ሊጠይቅ ይሆናል፤ እምቢ ካሉ ግን አብይ በምን ከሃዲው አንጀቱ (አንጀቱ ውስጥ የኢትዮጵያዊነት ደም ስለሌላው) አሻፈረኝ ብሎ  የወያኔን ወንጀለኛን ታጣቂ ያስፈታዋል? የሚል ነው ጥያቄው።

 ድርድር ሲካሄድ በሌሎች አፍሪካና እንዲሁም እንደ ኮሎምቢያ ውስጥ ዲሞቢላይዜሽን፣ ትጥቅ መፍታት እና እንደገና መቀላቀል (DDR) የሚባሉት በአብይ አጀንዳ የሚጠበቅ አይሆንም። መጀመሪያ ላይ የሽምቅ ተዋጊ ቡድኖችን ወደ ሲቪል ህይወት ለመቀላቀል እንደ ዘዴ  ወደ ፖለቲካ ፓርቲ ማዋቀር እንዲቀላቀሉ ማድረግ አንድ  ስኬት ነው። ይህ ግን በወያኔም ሆነ በኦሮሙማው መሪ አይታሰብም።

ወንጀለኞች እርስ በርሳቸው ሲደራደሩ ሕዝቡ ተመልካች ሆኖ መጨረሻ በጫማቸው ሥር ይወድቃል ማለት ነው።መጨረሻው ሁለቱም ወንጀለኞች የሥልጣን መቀራመት በስምምነት ተቀራምተው የፈሰሰው ደም፤የጎደለው አካል፤ የታመጹት መነኮሳትና የድንግል ልጃገረዶች ዕምባ ሳይጠረግ “ተረስቶ እንደ ጮኸ ይቀራል” ማለት ነው። ሁሌም የተለመደው አሳዛኝ ክሰተት!

አመሰግናለሁ።

 

 

 

No comments: