ለአንባቢዎቼ
ከአዘጋጁ
ስለ
ፍራሽ አዳሽ (ተስፋሁን ከበደ) የተሳሳተ ትችቴ
ጌታቸው
ረዳ
(Ethiopian
Semay)
7/16/22
ማሕበረሰብ ሲበሰብስ የጨዋ ሰው ምስልና ማንነት እየወሰደ በስሙ ሲነግድ ማየት የበሰበሰ ማሕበረሰብ ይባላል። እዚህ የምታዩት የተቀምኩበት ፎሮግራፈም ያንኑ ያሳያል።
ከጥቂት ሰዓታት በፊት ስለ ተወዳጁ ባለቁም ነገሩ ቀልድ ነጋሪው ተዋናይ ተስፋሁን ከበደ (ፍራሽ አዳሽ) ትችት መሰንዘሬ ይታወሳል። ትችቴም በድረገጼና በፌስቡኬ ለጥፌው የነበረውን ታስታውሳላችሁ። ሆኖም ተወዳጁ ተስፋሁን የተመለከትኩት ፌስቡክ የራሱ ፌስቡክ እንዳልሆነ እና ብዙ ፌስቡኮች የራሱ እያስመሰሉ መጠቀማቸውን ስለጠቆመኝ፤ እኔም ከልቤ በማዘን ጥቅርታ ጠይቄው የለጠፍኩትን ከድረገጼ እንዲወገድ አድርጌዋለሁ።
ተሳስቼ ላሳሳችኋችሁ ወገኖቼም ይርታ እጠይቃለሁ።
የሚገርመው ነገር እንዲህ ያሉ ስነ ምግባር የጎደላቸው አጭበርባሪዎች ከእንደዚያ ዓይነት ጨዋ ማሕበረሰብ ኢትዮጵያ እንዴት እንዳበቀለቻቸው ሳስበው መልስ ለማግኘት
እጅግ ይከብዳል።
አመሰግናለሁ
ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)
No comments:
Post a Comment