Wednesday, July 27, 2022

የአብይ ፕሮተስታንት መንግሥት እና የሂትለር ፕሮተስታንት መንግሥት ተመሳሳይነት ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 7/27/2022

 

የአብይ ፕሮተስታንት መንግሥት እና የሂትለር ፕሮተስታንት መንግሥት ተመሳሳይነት 

ጌታቸው ረዳ 

Ethiopian Semay 7/27/2022

watch this video also

 

Dr Abiy Ahmed surprise to Yonatan Aklilu

https://youtu.be/M0h6MPQyUtc

ከእስልምና ወደ ፕሮተስታንት ከፕሮተስታንት ወደ ገዳነት እምነት ወደ ..እስላም መሳይነት (የራሱ ቃል ነው) እየተገለባበጠ የሰውየው እምነት ምን እንደሆነ በቅጡ ለማወቅ ቢያስቸግርም። ለዛሬው ፕሮተስታንትነቱ እንውሰደው እና በዚያው እንውሰደው።

እንግዲህ ፕሮተስታንቱ ኦሮሙማው መሪ አብይ አሕመድ ሥርዓቱ እየተጠላ በመጣ ቁጥር እና ስጋት በያዘው ቁጥር፤ የሚያደርጋቸው አስገራሚ ባሕሪዎች አሉት።  የመተቃቀፍ እና የአባባ መለዋወጥ ቀን፤የምስጋና ቀን…. እያለ ሕዝቡን “ሰለማዊ መንግሥት ነኝ” በሚል “ለማጃጃል” የሚያደረግው አሳፋሪ ባሕሪው እንደገና ዛሬ “የፀሎት ቀን፤የምስጋና ቀን ለፈጣሪያችን እንድታቀርቡ ይሁን” የሚል “በአፉ ለይስሙላ” ካንድ የፖለቲካ መንግሥት ነኝ ከሚል “ሃይማኖታዊ መንግሥት” ትዕዛዝ በማስተላለፍ  በአሽከሮቹ በኩል በየመስርያቤቶች በግዳጅ እንዲከበር እያስጻፈ ነው።

ይህ የምስጋና ቀን የሚባለው በአብይ አሕመድ ዘመን አዲስ አይደለም። ለምሳሌ የEthiopian News Agency በ2020 (ፈረንጅ ዘመን) 2012 ኢትዮጵያ አቆጣጠር) ኩለት አመት በፊት ማለት ነው፡ "የምስጋና ቀን" በአዲስ አበባ እየተከበረ ነው፤ በሚል ርዕስ እንዲህ ይላል።

"የምናመሰግናችሁ ስለሚገባችሁ ነው" በሚል መሪ ሃሳብ የጳጉሜ 4 "የምስጋና ቀን" በተለያየ መርሃ ግብር በአዲስ አበባ እየተከበረ ይገኛል።” በማለት የዘገበውን ታስታውሳላችሁ። ምስጋና የሚጋበችሁ ነው የሚላቸውን በማግስቱ ምስጋና ትርጉም የማያውቀው አብይ አሕመድ ተቃዋሚ ናቸው የሚላቸውን የብዕር ጀግኖችን ወደ እስር ቤት ጭለማ በመግፍተር ሽማግሌ፤ ወጣት፤እመጫት፤ህጻናት የሚጠለሉበት መኖርያ ቤቶቻቸውን እያፈረሰ በከረምት ወራት በዝናብ ጎዳና ላይ እንዲሰቃዩ አደረገ።

ዛሬ ደግሞ ወደ አምላክ ፀሎት እናቅርብ እያለ ንጸሃንን አስሮ፤ አምላክ ላላቸውም አምላክ ለሌላቸውም ቀኝ እጃቸው ወደ ደረታቸው (ከፈረንጆች የተኮረጀ/ የተቀዳ/ ማለት ነው) በማድረግ ፀሎት አድርጉ እያለ በባለሥልጣኖቹ በኩል ትዕዛዙ እንዲከበር እያደረገ ነው።

ይህ እጃችሁን ወደ ደረታችሁ በማድረግ ጸልዩ የሚለው ጸረ አገራዊ ባህል፤ እስላሞች እና ክርስትያኖች በፓርላማም ይሂን በፍርድቤት በመጽሐፍ ቅዱስ ወይንም በቁርአን መጽሐፍ ከመማል ይልቅ የፈረንጅ ባህል አምጥቶ የሃይማኖት ምሃላቸውንና ፀሎታቸው አግባብ አስቀርቶታል።

አብይ በኦርቶዶክስ ሃይማኖት እና በነባሩ/አገራዊ እስላምና ሃይማኖት ላይ ከወያኔዎች በባሰ  እጅግ ጥላቻ አለው። ሰውየው የውጭ ቅጥረኛ በመሆኑ እስልምናውን ትቶ ወደ ፕሮተስታንት በመዞር እዛም የወላጆችዋን ሃይማኖት ባራከሰቺዋ ማፈሪያዋ በሚስቱ በኩል ፕሮተስታንት ተከታይ አፈርቶ ኦርቶዶክስን የማፍረስ ተልእኮው ለማሳካት ያላደረገው ሴራ የለም። ሌላ ቀርቶ ህጻናት ልጃገረዶችን እየሳመ በመሃል አዳራሽ የሚማግጠው ወንጀለኛው ዮናታን የተባለው አደገኛ የፕሮተስናት ፓስተር ነኝ ባዩ አብይ አሕመድ የመንግሥትን መሬት በነፃ እየሸለመ ፕሮተስታንት ወንጀለኞችን የፈለጉት ወንጀል እንዲሰሩ ልቅ በመስደድ የሚያበረታታ አደገኛ ሰው ነው፤፡

አገራችን ውስጥ ፕሮተስታንት እንደሚታወቀው በኦሮሞዎች ልሂቃን የሚቀነቀን ሃይማኖት ነው።ኦሮሞ ልሂቃን ደግሞ ጸረ ኦርቶዶክስ እና ጸረ አማራ ፤ጸረ ኢትዮጵያ ናቸው። ኦርቶዶክስ በመክሰስ የፕሮተስታንትን መንግሥት በመትከል አሁን ደስተኞች ናቸው።ከዚህ አልፎ ኦርቶዶክስ ውስጥ የተሰገሰጉ ከእስላሞች ጋር አብረው ስጋ የሚበሉ ፤የኦነግ ፕሮተስታንት የውስጥ ልዑካን የሆኑ ኦሮሞ ኦርቶዶክስ መሳይ ቀሳውስትም እንደሚታስውሱት ከፍተኛ የማፍረስ ስራ ሰርተዋል። (ቀሲስ በላይ የታበለው ፈጣጣ ሴረኛን ታስታውሱታላችሁ)

 

እንደ አብይ አሕመድ የብልጽግና (ፒፒ) ወረበላዋ የናዚ ጀርምንም እንዲሁ የናዚ ቡድኑ ወደ ሥርዓተ መንግሥት በምርጫ ሲወጣ ከልቡ አልሞት የነበረውን ጸረ ካቶሊክ ሴራው እውን አድርጓል።

የጀርመን የፕሮቴስታንት ቀሳውስት የመጀመሪያውን የዓለም ጦርነት በካቶሊካዊትዋ ፈረንሳይ፤ቤልጂየም እና በኦርቶዶክስ ሩሲያውያዊቷ ጸረ ጀርመን ሃይማኖታዊ ጦርነት (ክሩሴድ) ነው የተካሄደብን እያሉ “ፕሮተስንታኖችን” ሲሰብኩ ስለነበር “ብሔርተኝነት እና ፕሮቴስታንት” የአንድ ርዕዮተ ዓለም / ያንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች እንደነበራቸው ግልጽ ነበር።

 ልብ በሉ ኦሮሞዎች የ “ፒፒን” መንግሥት እንደ የኦሮሙማ ስርዓትም፤ እንደ አባገዳም እንደ ፕሮተስታንት እና እንደ ‘’የእስላማዊ ብራዘር ሁድ”  አቀንቃኝ መንግሥት አድርገው ያዩታል (የአባ ገዳ መሪ አቶ “በየነ ሰንበቶ” አብይ ባይመረጥ ኖሮ ሁሉ ኦሮሞ በየቤቱ ዘግቶ ‘ቢላዋ፤ቆንጨራ እና ጠመንጃ ስራ ላይ እንዲያውለው ይጠባበቅ ነበር!’ ያሉትን ልብ በሉ)።

 ጀርመን ውስጥም ይህ “ያንድ ስዕል ሁለት ገጽታ ያለው” እምነት ኢትዮጵያ ውስጥም በአብይ አሕመድ ዘመን እያየን ነው።

ስለዚህ የምስጋና ፀሎት እናድርግ እያለ ፖለቲካ እና ሃይማኖት በየወቅቱ የሚዘበራርቀው “አብይ አሕመድ” በፕሮተስታነቱ እና እስላማዊው ውሃብያው ‘ብራዘር ሁድ” ማሕበረሰብ  የሱን ስም እየተነሳ ውዳሴ እንዲደረግለት እየተማጸ ነው።

 ለመሆኑ ንፁሃንን እያሰረ ለማን ነው ምስጋና ን እናቅርብ እያለ ያለው? እሱን ለሚያመልከው ለሰይጠኑ ከሆነ የራሱ ጉዳይ ነው፡ ኢትዮጵያዊያን ግን የምናደርሰውና የምንጸልየው አገር ሙሉ ንጹሃንን እየለቀመ እስር በማስገባት የሚያንገላታ “እስላም መሳይ ነኝ እያለ የሚያታልል የዲያብሎስ አማኝ” እንደ መለስ ዜናዊ ተሎ እንዲያሰናብልን ነው ጸሎታችን።

 

ሰላም ቆዩ

ጌታቸው ረዳ      Ethiopian Semay

 

  


Sunday, July 24, 2022

ወንጀለኞች ከወንጀለኞች አቻቸው ጋር መደራደር ወንጀለኞችን ከተጠያቂነት ነጻ የማድረግ ሴራ ነው! ጌታቸው ረዳ ETHIOPIAN SEMAY 7/23/22


 

ወንጀለኞች ከወንጀለኞች አቻቸው ጋር መደራደር ወንጀለኞችን ከተጠያቂነት ነጻ

የማድረግ ሴራ ነው!

ጌታቸው  ረዳ

ETHIOPIAN SEMAY 7/23/22



በሺዎች የሰው ሕይወት ጨፍጭፈው ያለምን ምንም ስጋት  በነጻ የሚኖርባት አገር ኢትዮጵያ ብቻ ነች። ያውም በገደሉና በዘረፉ ቁጥር ሥልጣን የሚያገኙበት አገር ብቸኛዋ አገር ኢትዮጵያ ብቻ ነች።አሳዛኝ!

 ታስታውሱ እንደሆነ ከባድሜ ጦርነት በሗላ ሁለቱም ወንጀለኞች (ወያኔ እና ሻዕቢያ) በመደራደር 70 ሺ የሚገመት ሕዝብ በሁለቱም ወገን ህይወቱ እንደተቀጠፈ ይታወሳል። ታዲያ በወቅቱ ከድርድሩ በፊት እኔ  “የሁለት ወንጀለኞች ድርድር ተጠያቂነትን የሚሸሽግ ተንኮል” በሚል ርዕስ በጋዜጣ (ሓዋርያ ይመስለኛል) አሳትሜ ለሕዝብ አስነብቤ ነበር። ታዲያ በወቅቱ ሰሚ ታጣ እና “ከባድሜ መልስ ወደ መለስ” እያሉ ተቃዋሚዎች ነን ባዮች ሕዝብን ሲያታልሉት ባጁና እንደገመትኩት በዛው ወቅት የተፈጸመ የጦርንትና የሕግ መጣስ አንድም ሰው ተጠያቂ ሳይሆን- ተቃዋሚው የፈከረው መፈክር እውን ሳይሆን ለመለስ የተባለው ብትር መለስ ዜናዊ  መልሶ ወደ ተቃዋሚው አዞረውና የተቃዋሚውን ብልት ማኮላሸት ተያያዘው። በሚገርም ተመሳሳይነት “ወያኔ ከደብረሲና ተመትቶ ካፈገፈገ በሗላ” አብይ አሕመድም ልክ እንደ መለስ ተቃዋሚውን ወደ እስር በመክተትና በመደብደብ ያንን ደገመው። ተመሳሳይነቱን አልገረማችሁም?

በወቅቱ በጦርነቱ ለደረሰው ጉዳት አንድም ሰው ሳይጠየቅ እንደገና እደግመለሁ “አንድም ሰው ተጠያቂ ሳይሆን” ባድሜንም አስረከበው ወንጀለኞችም ይኸየው እስካሁን ሥልጣን ላይ አሉ፡ ይባስ ብሎ  እነኛ ወንጀለኞች ዛሬም አዲስ ጦርነት ከፍተው ሕዝብን አሳለቁት፤ንግድ፤ቤተጸሎት አፈረሱ ፤ ሰቶች መነኮሳት ደፈሩ። ተጠያቂነት አልቦ! ጭጭ!

አሁን ደግሞ ያንን ተመሳሳይ የባድሜን የኪሳራ ድርድር ለመድገም ኬኒያ እንዲገናኙ እየተሸባሸቡ ነው።

 እኔ በሁለቱም  በኩል የሚደረገው ድርድር እቃዋማለሁ። ሁለቱም ወደ ዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት ቀርበው እንዲጠየቁና “የዘር ማጥፋት ወንጀል ሕግ አዋቂዎች፤ ሰብኣዊ ድርጅቶች፤ሲቪልና ወታደራዊ የሕግ ባለሞያዎች፤የሃይሞኖት እና የሞያ፤የሴቶች መብት ተወካዮች፤ ከሁለቱም ሕዝብ በኩል ለድርድር እንዲቀርቡና አለም አቀፍ የድርድር ባለሞያዎች፤ ተወጣጥተው ሁለቱም ወንጀለኞች ያገለለ ድርድሩ መካሄድ አለበት እላለሁ። ካልሆነ እያንዳንዱ ወገን ወንጀል ስለፈጸመ እራሱን “ኢንክሪመንት” የሚወነጅል ድርደር ስለማያደርግ ሁለቱም ከጠያቂነት ነፃ የሚያደርግ ድርግ አድርገው ሕዝቡን ሌላ ጦርነት ውስጥ ያስገቡታል።

ድርድሩ አይሰምርም እንጂ (ምክንያቱም ጦርነት ለወያኔም ለኦሮሙማውም የሥልጣን ምንጭ በመሆኑ) ድርድሩ (ከኖረ) ከላይ በጠቀስኩት ምክንያት የህግ የበላይነትን መሰረታዊ መርሆ ይጎዳል።

ጦርነት ከፍተው ወንጀለኞች ወንጀል ፈጽመው ለድርድር ከቀረቡ ወንጀለኞቹ እራስ በራስ እንዲደራደሩ ከተፈቀደ ሕግን በጣሰ መልኩ ራሳቸውን ነፃ በሚያደርግ መብት እንዲያገኙ መደረግ የለበትም።  ሁላችንም በሕግ  እንድንገዛ ለራሳችን ካስገዛን እነሱም እንዲሁ መገዛት ነበረባቸው፡  ይሁን እንጂ በተግባር ግን ወንጀለኞቹ  ባለሥልጣኖችና ተደራዳሪዎች ስለሆኑ  በተለመደው አተገባበር ላይ  ሕዝብን ባገለለ መልኩ ውሳኔዎችን ወስነው ከተፈራራሙ ድርድሩና ውጤቱ በባድሜ ጦርነት ያየነው ኣይነት ሴራና ውጤት እናያለን።

በሚሊዮን የሞቆጠር የወያኔ ታጣቂ አብይ በድርድሩ እንዲፈታ ይጠይቃል ወይ ብለን አንገምትም። ለይስሙላ ሊጠይቅ ይሆናል፤ እምቢ ካሉ ግን አብይ በምን ከሃዲው አንጀቱ (አንጀቱ ውስጥ የኢትዮጵያዊነት ደም ስለሌላው) አሻፈረኝ ብሎ  የወያኔን ወንጀለኛን ታጣቂ ያስፈታዋል? የሚል ነው ጥያቄው።

 ድርድር ሲካሄድ በሌሎች አፍሪካና እንዲሁም እንደ ኮሎምቢያ ውስጥ ዲሞቢላይዜሽን፣ ትጥቅ መፍታት እና እንደገና መቀላቀል (DDR) የሚባሉት በአብይ አጀንዳ የሚጠበቅ አይሆንም። መጀመሪያ ላይ የሽምቅ ተዋጊ ቡድኖችን ወደ ሲቪል ህይወት ለመቀላቀል እንደ ዘዴ  ወደ ፖለቲካ ፓርቲ ማዋቀር እንዲቀላቀሉ ማድረግ አንድ  ስኬት ነው። ይህ ግን በወያኔም ሆነ በኦሮሙማው መሪ አይታሰብም።

ወንጀለኞች እርስ በርሳቸው ሲደራደሩ ሕዝቡ ተመልካች ሆኖ መጨረሻ በጫማቸው ሥር ይወድቃል ማለት ነው።መጨረሻው ሁለቱም ወንጀለኞች የሥልጣን መቀራመት በስምምነት ተቀራምተው የፈሰሰው ደም፤የጎደለው አካል፤ የታመጹት መነኮሳትና የድንግል ልጃገረዶች ዕምባ ሳይጠረግ “ተረስቶ እንደ ጮኸ ይቀራል” ማለት ነው። ሁሌም የተለመደው አሳዛኝ ክሰተት!

አመሰግናለሁ።

 

 

 

Sunday, July 17, 2022

እያነባሁ ያነበብኩት የተከዳው የሰሜን ዕዝ መጽሐፍ ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 7/17/2022


እያነባሁ ያነበብኩት የተከዳው የሰሜን ዕዝ መጽሐፍ

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay

7/17/2022

በሕግ የተጠበቀውን የደራሲው መብት ላለመጋፋት በጣም እጅግ በጣም አንድ ገጽ ብቻ ቀንጭቤ እንዴት ይህን ሁሉ ሰራዊት ትጥቅ ሊፈታ ቻለ? በሚል ደራሲው ያቀረበው ጥያቄ ጦሩ አምበጣ ሲያባርር እና የትግራይ ድሃ ተማሪዎች ደብተር መግዣ ሲያዋጣ ውሎ ደክሞት በተኛበት ወቅት አዘናግተው በድንገት በጭካኔ እንዴት እንደጨፈጨፉት እና በዚህ ጭፍጨፋ የትግራይ ሕዝብ ሱታፌ ምን እንደነበር ከጭፍጨፋው በተአምር የዳነው የዓይን ምስክር ደራሲ የአምሳ አለቃ ጋሻዬ ጤናው (ቻቻው) ከጻፈው መጽሐፍ አጋራችሗለሁ።

የመጽሐፉ ገጽ 393 ሲሆን ገጽ 101 ብቻ አንብቤአለሁ። ከደረስኩበት ገጽ ወደፊት ብዙ አሳዛኝ፤የሚያበሳጭ እና አስለቃሽ ታሪክ እንዳለ ተነግሮኛል። ለዛሬ ግን ደራሰውን እያመሰገንኩ ይህ መጽሐፍ እንዳነበው ከአገርቤት ሰው አስልኮ በማሰመጣት  በስጦታ ያበረከተኝ የልብ ወዳጄና ወንድሜ የሳንሆዜው ደ/ር ግርማ በቀለ ከልብ አመሰግናለሁ።              

አሁን ወደ ታሪኩ ልግባ፤-

ከዚህ ጽሑፍ በታች “ልዩ ኃይል” እያለ የሚተርከው ወያኔ ያሰለጠነው “የትግራይ ልዩ ኃይልን” ነው፦

“….. ልዩ ኃይሉ ከተተኮሰበት የሚደነብር፤ በልምምድም ሆነ በስልጣና ያልበቃ በመሳሪያና በፕሮፓጋንዳ ብቻ ማሸነፉን አልሞ የተነሳ ፈሪ ኃይል ነው።ሚሊሽያው ግን የዋዛ አይደለም። ምሽጉን ከያዘ መድፍ ቢተኮስበት ይሞታታል እንጂ ከምሽጉ ንቅንቅ አይልም።

በዋነኛነት ሠራዊቱ እጅ እንዲሰጥ ያደረገ ይኼ ያሰለጠኑት ብዙ ቁጥር ያለው ታጣቂ ነው። ታጣቂው ብዙ ቁጥር ያለው ስለሆነ የተሟላ ትጥቅ ሳይኖራትና 2 መቶ የማይሞላ የሰው ኃይል ላላት ሻለቃ 8 መቶ እና 1 ሺ ታጣቂ ይከባታል። ከሠራዊቱ በቁጥር ሦስት አራት ጊዜ የሚበልጥ ታጣቂ ጁንታው ያሰማራል። አንድ ሰው በሞተበት ቁጥር አንድ መኪና ሰው አምጥቶ ይደፋል።

ሌላው ጉዳይ የጁንታው ደጋፉዎች ሠራዊቱን በእጅጉ ያስደነገጡ ነበሩ። እንዴት መቶ ለማይሞላ አንድ ሻምበል ሠራዊት ከተሰለፈው ሚሊሽያና ከልዩ ኃይል በተጨማሪ ሦስት አራት ተሳቢ መኪና ድምፅ አልባ መሳሪያ የታጠቀ ሲቪል ሰው ይመጣል? የሚመጣው ሰው ደግሞ መጥረቢያ፤ USA ጩቤ፤ ካራ፤ገጀራ፤ሚስማር የተመታበት ጣውላ፤ ሠራዊቱ ዓይን ላይ የሚበተን በርበሬ… የያዘ ነው። ድንጋይ መሬቱን ሞልቶታል። ብሔርን መሰረት ያደረገ ስድባቸው አጥንት ይሰብራል። ሕሊና ያደማል።

በእርግጥ በወቅቱ የነበረ የትግራይ ሕዝብ ሦስት አራት አይነት ነው። ግማሹ የጁንታው ደጋፊ ሆኖ ሠራዊቱ እንደ አባቱ ገዳይ በክፉ ዓይኑ የሚያይ ነው። ዕድል ሲያገኝ  በገጀራና በመጥረቢያ እየቆረጠና እየፈለጠ፤በካራ እየባረከ፤ በድንጋይ እየወገረ እና በጩቤ እየወጋ፤በርበሬ ዓይኑ ላይ እየበተነ፤ጣውላ ላይ በተመታ ሚስማር ጭንቅላቱን እየሰነጠቀ ገድሏል፤ አቁስሏል።

በጣም ጥቂት ሕዝብ የሠራዊቱ ደጋፊ ነው። የጁንታው ደጋፊዎች ሠራዊቱን እንደ ጉንዳን ሲወሩት በግልጽ ይቃወማል።ተቃውሞ መከላከል ሳይችል ሲቀር ይለምናቸዋል። “ለዚህ ሠራዊት ይኼ አይገባውም ፤ አረ እባካችሁ የታሪክ ተወቃሽ አታድርጉን…?!” ይላል። ልመናው አላዋጣ ሲለው ያለቅሳል። ደረቱን እየደቃ “ወዮ”ይላል።  

ሌላው ሕዝብ ደግሞ ከማንም ያልሆነ መሀል ሰፋሪ ነው።ሠታዊቱን የሚቀጠቅጠውንም ፤ ለሠራዊቱ የሚያለቅሰውንም ዝም ብሎ ያያል። እንዲህ አይነት ሰው ግን አያበሽቅም? ይኼ እኮ የፖለቲካ ጉዳይ አይደለም። ይኼ እኮ የብሔር ወይንም የክልል ጉዳይ አይደለም። የሰብአዊነት ጉዳይ ነው። ሰው እንዴት በሰብአዊነት ጉዳይ መሀል ሰፋሪ ይሆናል?

የሆነው ሆኖ በኛ ሠራዊት ላይ ጥቃት  እንዲፈጸም ያዘዙና የመሩ የጁንታው ባለሥልጣናት ቢሆኑም፤ ሠራዊቱን እጅግ ዘግናኝና አሰቃቂ በሆነ መንገድ የገደሉ ግን ልዩ ኃይል ወይም ሚሊሽያ ሳይሆን የጁንታው ደጋፊ ሕዝብ እና እኛን የከዱ የሠራዊቱ አባሎች ናቸው።

ልዩ ኃይሉና ሚሊሽያው የያዘው መሳሪያ  ብቻ ነው፤የሚገድለውም በጥይት ነው። በካራ ያረዱ፤በጩቤ የወጉ፤ በገጀራ የቆረጡ ፤ በመጥረቢያ የፈለጡ፤  በድንጋይ የቀጠቀጡ አብዛኛዎቹ የጁንታው ደጋፊዎች ናቸው።ሌላኛው አስከሬንን በመኪና የረገጡ፤ ቁስለኛን በታንክ የጨፈለቁ የፍጥኝ አስረው ገደል የለቀቁ…ከኛ የከዱ የትግራይ ተወለጆች የሠራዊቱ አባላት ናቸው።

ይህ የጁንታ ኃይል ነው እንግዲህ የሠራዊቱን የግንኙነት መረቦች ቆራርጦና መንገድ ዘግቶ ካምፑን የከበበ። ሠራዊቱ ከአቅም በላይ ተዋግቷል (ሁሉም አንድ ባይሆንም ዘጠኝ ቀን ሙሉ ርሀብና ውኃ ጥሙ ሳያሸንፈው የተዋጋ አለ። አምስት ቀን ሌሊትም ቀንም ከምሽጉ ሳይወጣ ጥይቱ እስከሚያልቅ የተዋጋ አለ። ሰባት ቀን ሙሉ ያለምንም ዳቦና ውኃ የተዋጋ አለ።አምስት ቀን ሌሊትም ቀንም ከምሽጉ ሳይወጣ ጥይት እስከሚያልቅ የተዋጋ አለ። ለሦስት ቀን በእልህና ወኔ ከጁንታው ኃይል የተፋለመ አለ። ማንም የሚደርስለት አልነበረም።

ሠራዊቱ ምግብና ውኃ የለውም። የጁንታው ኃይል እንደፈለገ ምግብና መጠጥ ይቀርብለታል። ሠራዊቱ ጥይት እየቆጠበ ካልሆነ ካለቀበት ዕጣው በጁንታው እጅ መውደቅ ነው። ለጁንታው ኃይል ጥይት እንደ አፈርና ጭቃ ነው። ሁለት መቶእና ሦስት መቶ የሚሆን ሠራዊት 1 ሺ 5 መቶ እና ከዚያ በላይ የታጠቀ ኃይል ያሰልፋል። ከ    ደግሞ ተራራ የሚሸፍን ሕዝብ አለ።

ሠራዊቱ አንድ ሰው ሲቆስልበትና ሲሞትበት የሰው ኃይሉ ይቀንሳል። ጁንታው ስለሰው አይጨነቅም። አምስት ታጣቂ ቢሞትበት አምሰት አውቶብስ ሰው አምጥቶ ይደፋል። ታዲያ እንዴት ይሄ ሠራዊት ትጥቅ አይፈታም?

እያለ ወያኔ መጀመሪያ በሰሜን ዕዝ ሠራዊት ላይ ጥቃት ሲፈጽም ደራሲው በግል ማስታወሻው በምስጢር እየመዘገበ ያየውን የተፈጸመው አገራዊና ሰብአዊ ወንጀል ባስጨናቂ ሁኔታ በነበረበት ወቅት  ብርታትን የተሞላበት  የእልህ ግብግብ ያየውን ለኛ አቅርቦልናል።

ይህ የሚያሳየን የትግሬዎች ፋሺስዝም ብሎ ብሎ ወደ እዚህ ወንጀል እንዴት እንደተሻገረና ሕዝቡ ወደ ጭለማ እየተጓዘ እንደሆነ የምናይበት መስተዋት ነው። ይህ ሁሉ ወንጀል ፈጽመው ሲያበቁ ፤ በድርጊታቸው ሳይጸጸቱና ሳያፍሩ ፤ይህ አረመኔ ወንጀላቸው ደብቀው አሁን ደግሞ  “ትግራይ ሪፑብሊክ አንመሰርታለን” እየተባለ እየተፎከረ በሌላ መልኩ ደግሞ “ባንክ ክፈቱልን፤ ጤፍ ላኩልን፤ስልክ ጀምሩልን” እየተባለ እየተጮኸ ያለው። ከአማራ ሕዝብ ላይ ጠብ የለንም ይላሉ በሌላ በኩል ደግሞ የአማራን ልጆች ከጦሩ እየለዩ ሲረሽኑ ነበር። አምሳለቃ ጋሻዬ አንኳን ተረፍክና ይህንን ጉድ ነገርከን! ወጣም ወረደ ግን አብይ አሕመድና ወያኔ ሁለቱም ለዚህ ሁሉ ወንጀል ተጠያቂዎች ናቸው!!

መጽሐፉ ስጨርስ ለግምገማ እመለሳለሁ። እስከዚያው ድረስ ግን እንደተለመዳችሁት እንለምናችሀና ይህ ጽሑፍ ሕዝብ እንዲያውቀው ተቀባበሉት።

አመሰግናለሁ

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay

 

 

Saturday, July 16, 2022

ለአንባቢዎቼ ከአዘጋጁ ስለ ፍራሽ አዳሽ (ተስፋሁን ከበደ) የተሳሳተ ትችቴ ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay) 7/16/22

 

ለአንባቢዎቼ ከአዘጋጁ

ስለ ፍራሽ አዳሽ (ተስፋሁን ከበደ) የተሳሳተ ትችቴ

ጌታቸው ረዳ

(Ethiopian Semay)

7/16/22

 ማሕበረሰብ ሲበሰብስ የጨዋ ሰው ምስልና ማንነት እየወሰደ በስሙ ሲነግድ ማየት የበሰበሰ ማሕበረሰብ ይባላል። እዚህ የምታዩት የተቀምኩበት ፎሮግራፈም ያንኑ ያሳያል።

ከጥቂት ሰዓታት በፊት ስለ ተወዳጁ ባለቁም ነገሩ ቀልድ ነጋሪው ተዋናይ ተስፋሁን ከበደ (ፍራሽ አዳሽ) ትችት መሰንዘሬ ይታወሳል። ትችቴም በድረገጼና በፌስቡኬ ለጥፌው የነበረውን ታስታውሳላችሁ። ሆኖም ተወዳጁ ተስፋሁን የተመለከትኩት ፌስቡክ የራሱ ፌስቡክ እንዳልሆነ እና ብዙ ፌስቡኮች የራሱ እያስመሰሉ መጠቀማቸውን ስለጠቆመኝ፤ እኔም ከልቤ በማዘን ጥቅርታ ጠይቄው የለጠፍኩትን ከድረገጼ እንዲወገድ አድርጌዋለሁ።

ተሳስቼ ላሳሳችችሁ ወገኖቼም ይርታ እጠይቃለሁ።

የሚገርመው ነገር እንዲህ ያሉ ስነ ምግባር የጎደላቸው አጭበርባሪዎች ከእንደዚያ  ዓይነት ጨዋ ማሕበረሰብ ኢትዮጵያ እንዴት እንዳበቀለቻቸው ሳስበው መልስ ለማግኘት እጅግ ይከብዳል።

አመሰግናለሁ

ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)

Thursday, July 14, 2022

የወያኔ ስትራተጂካዊ መጥቃዕቲና የዛሬው ሰበቡ ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 7/14/22

 

የወያኔ ስትራተጂካዊ መጥቃዕቲና የዛሬው ሰበቡ

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay 7/14/22

ስትራተጂካዊ መጥቃዕቲ” የሚል በተከታታይ ስለምታገኙ ስትራተጂካዊ መጥቃዕቲ ምን እንደሆነ ልግለጽና በቀጥታ ወደ ሰነዱ እንገባለን። ስትራተጂካዊ መጥቃዕቲ ለወሳኝ ምዕራፍ የሚያደርስ የመጨረሻ የውግያ ዝግጅት ነው። ”ስትራተጂካዊ መጥቃዕቲ” ተብሎ የሚታቀው የወያነ ትግራይ የጦርነት ዕቅድ ብዙ ሃላፊዎችን በየዘርፉ ያካተተ ሲሆን ሰዎቹ በተለያዩ የሥራ ዘርፎች ሃላፊነት ወስደዋል።

ስንቅ፤ነዳጅ፤መጓጓዧ፤ትጥቅ፤ሕክምና የመሳሰሉት በተቀናጀ አሰራር እንዲቀነባበር የተደረገ ጥናት ነው። በዚህ ዘመቻ ወሳኝ ሆኖ የተገኘው ደግሞ የተዋጊው ሃይል ቁጥር በብዛት መኖር ወሳኝነት ስለነበረው፤በወቅቱ ወያነ ትግራይ የሻዕቢያ ባርያ ስለነበረ ጌታውን ሻዕቢያን ከኢትዮጵያ ሠራዊት ለማዳን ሲል በብዙ ሺሕ ትግራይ ታጋዮች ወደ ኤርትራ በመላክ እንዲያልቁ በማድረጉ፤ ”ስተራተጂካዊ መጥቃዕቲ” ስለተባለው ዝግጅት ከመደረጉ በፊት ከቀረው እጅግ አድካሚ እና ወሳኝ ፍልሚያ ሲነፃፀር በሰው ሃይል እጅግ ቀንሶ እና ተመናምኖ ነበር።

ለዚህ አንድ ሁለት ምክንያቶች ነበሩት። አንዱ ቀደም ብየ እንደገለጽኩት ወደ ኤርትራ እንዲሄድ ተደርጎ በሺዎች ተሰውተዋል።ሌላው ታጋዮቹ ከደርግ ሰራዊት ይዘት ትግራይን ነፃ እንዳወጡ ወዲያውኑ እንዲተገብረው የተማረው ጠባብነት በተግባር በማዋል ”ትግራይን ነፃ አውጥተናል፤ አማራው ነፃ ለመውጣት ከፈለገ እራሱ ነፃ ያውጣ፤ እኛ ለአማራዎች ስንል የምንሰዋበት ምክንያት የለንም፤ ስለዚህ ከአለውሃ ምላሽ ወዲያ እንዲሁም ከደብረታቦር ወዲያ አናልፍም በማለት ከነ ትጥቃቸው ምሽጋቸውን እየለቀቁ ወደየ መንደራቸው ስለሄዱ የወያኔ ታጋይ በቁጥር የተመናመነ ስለነበር የግድ እሱን ለመተካት ሲል የትግራይ ገበሬ ወጣት በግድ ወደ ማስልጠኛ ጣቢያ በመትመም ወታደራዊ ስልጠና ተገድዶ እንዲወስድ ተደርጓል። ከየመንደሩ በገፍ እየታፈሰ ሲሄድ እምቢ ያለ ደግሞ ከዚህ በታች ያለውን ድርጊት ተፈጽሞበታል። ባንድ ወቅት በግድ እየተገፋ አፅቢ በተባለው ማሰልጠኛ ውስጥ 79 ሺህ አዲስ ምልምል ታጋዮች እንደነበር አስገደ ይገልፃል።

ይኸ አሃዝ እንድ ቦታ የነበረ እንጂ በየገጠሩ ማስለጠኛ የያዘዘቸው ብዛቶች በርካታ ናቸው።ከዚህ ቀጥሎ የምታነቡት አስገደ የዘገበው ታሪክ አምቢ አልታገልም ያለ ሰው በአሳዛኝ ሁኔታ የትግራይ ገበሬ እና የከተማ ኗሪ ሕዝብ በወያነ ክፍሊ ሕዝቢ (ካድሬዎች/የህዝብ ግንኙነት ሓለፊዎች) እየተጎተተ ወደ ማጎርያ (ኮንሰንትረሺን ካምፕ) እስርቤቶቸ ተወስዶ የደረሰበት ስቃይ ትመለከታላችሁ። ወደ ታሪኩ ልውሰዳችሁ። አስፈገደ ገ/ሥላሴ እንዲህ ይላል። ”የአዲስ ምልምሎች ሥልጠና ጉዳይ በበላይነት የሚመሩ ከማዕከላዊ የደጀን አስተዳደር ክፍል የህወሓት ፖሊት ቢሮ አባላት ስምዝርዝር የሚከተሉት ናቸው።

 1 ገብሩ አስራት

2 አረጋሽ አዳነ

3 ተወልደ ወልደማርያም

4 ቢተው በላይ የምልመላው የህዝብ ግንኙነት (ክፍሊ ሕዝቢ 08)ሃላፊው ተወልደ ወልደማርያም ሲሆን ከተወልደ ሥር በትግራይ ውስጥ በየአውራጃው ለምሳሌ በወልቃይት፤ ፀገደ፤ አርማጭሆ፤ ፀለምቲ፤ ላሬ፤ በየዳ፤ ጃን አሞራ፤ በለሳ ሰቆጣ፤ ወሎ ሰሜን ሸዋ 500 የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ነበሩ።

በስትራተጂካዊ የማጥቃት ዘመቻ ዕቅድ ለማሳካት አዲስ ሰልጣኝ ለማብዛት ሁለቱም ማለትም የሕዝብ ግንኙነትና የደጀን አስተዳደር ክፍል ከፍተኛ ሓለፊነት ተጥሎባታፀቸዋል። ምክንያቱም ተመልማይ ብብዛትና በወቅቱ ሰልጥነው ወደ ጦር ግምባሩ ካልዘመቱ ስትራተጂካዊ መጥቃዕቲ ሚባለው ወሳኝ ፍልሚያ ግቡ አይመታም። የታሰበው ግብ ካልመታ ”ሙሽራ ሳይዙ ሚዜ ፍለጋ ዓይነት” እንዳይሆንበት በማሰብ ካሁን በፊት በግድም ሆነ በውዴታ ልጆቹን ወደ ጦር ሜዳ አስልኮ አታግሎ የነበረ ወላጅ ወይንም ቤተሰብ ልጆቻቸውን ወደ ታጋይ ምልመላ ያልላኩ ቤተሰቦች/ጎረቤቶች ካሉ ልጆቻቸው እንዲያታግሉ ”ዛሬ ያልከተተ በቁሙ የበከተ” የሚል መፈክር እንዲያሰሙዋቸው በመገፋፋት በሁለቱም ላይ ቅራኔ እንዲፈጠር አድርገው ለጆቻቸው ያልላኩ ሰዎች በግድ እንዲሄዱ በመጫን በርካታ ምልምሎች ወደ ማሰልጠኛ ቦታ ጎረፉ።

በተለይም በ1981 ዓ.ም ደርግ የለቀቃቸው በሗላ ነፃ የወጡ ቦታዎች ያልተነካ ወጣት ስለነበር መጀመርያው ዙር ላይ 30,000 ወጣት በግድ ተመልምሎ ሰልጥኖ ታጋይ ሆነ። ያ በ1982 ዓ.ም በጠባብነት ስሜት (ፀረ ኢትዮጵያዊነት /ፀረ አማራነት) የተማረውን ትምህርት ተግባራዊ ለማድረግ ምሽጉን እየጣለ ወደ የቤቱ የሄደው ታጋይ ከነ ብረቱ ተመልሶ ወደ ጦር ሜዳ መመለስ ጀመረ።

የመጀመርያው ዙር በእንዲህ ቢከናወንም የተጠበቀው ቁጥር ከተገመተው በታች ስለሆነ እና የመታገል ስሜት ስለቀዘቀዘ ሰሜቱን ለማነሳሳት የኪነት ቡድኖች እነ እያሱ በርሐ እና እነ ገብረመድህን ስቡሕ (ጠርጣራው) ወደየ ገጠሩ ወደየ አውራጃው ተሠማሩ። የኪነት ትርዒት ባሳዩ ቁጥር ባንድ መድረክ ውስጥ ወደ 300 ሰዎች ለትግል ዝግጁነታቸው ይገልፁ ነበር። ያም ሆኖ አሁንም የተፈለገው ሃይል ማግኘት አልተቻለም። በቂ የታጋይ ቁጥር ስላልተገኘ የሚከተለው ውሳኔ ተላለፈ።

ወደ ትግል ለመሄድ ዝግጁነቱ ያላሳየ ሁሉ በታጋዮችና በሚሊሺያ ወያኔዎች እየተጎተተ ወደ ማሰልጠኛ ጣቢያ እንዲወሰድ። አልታገልም ብሎ አሻፈረኝ ያለ ወጣት ደግሞ ሚሰቱ፤ወላጆቹ፤እህት ወንድም ዘመድ አዝማድ እየተገደዱ እስር ቤት እንዲገቡ፤ንበረታቸው፤በግ፤ፍየል ላም በሬ ደሮ እንሰሳት በሙሉ ተወርሰው ለድርጅቱ ገቢና ጥቅማጥቅም ይውላል።

 በነፃ በወጡት ገጠሮችም ሆነ ከተማዎች እምቢ እያሉ የሚያንገራግሩ፤የሚያውኩ፤የሚሰብኩ በማንቁርታቸው እያታነቁ ወደ 06 እስር ቤት ተወርውረው እንዲቀጡ። ቅጣቱም ወደ አፅቢ ማሰልጠኛ ቦታ በመሄድ ሠልጣኙ የሚወስንላቸው የቅጣት ውሳኔ ተግባራዊ እንዲሆን ሙሉ ስልጣን ተሰጣቸው። የዚህ ምልመላ ቅጣት ውሳኔ አመንጪዎች፤ፈፃሚዎችና አስፈፃሚ አካላት ሥም ዝርዝር የሚከተሉት ናቸው።

ተወልደ ወልደማርያም-የሕዝብ ግንኙነት አስተዳደር ሐላፊና አደራጅ

 ገብሩ አስራት- የትግራይ ደጀን አስተዳዳሪ

 አረጋሽ አዳነ -ትግራይ ደጀን ምክትል አስተዳዳሪት

ቢተው በላይ -ሕዝብ ድርጅትና አስተዳደር (ምክትል)

ሃለቃ ፀጋይ በርሀ- ሕዝብ ግንኙነት ሃላፊ

 ሐሰን ሽፋ - ደጀን ትግራይ የፀጥታ ጉዳይ ሐላፊ

ቁዱሳን ነጋ -የምዕራብ ትግራይ የሕዝብ ጉዳይ

ሐላፊ ትርፉ ኪዳነማርያም - የትግራይ ማዕከላዊ አስተዳደር የሕዝብ ክፍል አደራጅ ሓላፊት

አብርሃ ማንጁስ -የድርጅት ጉዳይ ፀሐፊ

ዘርአይ አስገዶም - መቀሌ የሕዝብ ጉዳይ ሐላፊ

 ዓለምሰገድ ውረታ - ውቅሮ የህዝብ ጉዳይ ሃላፊ እና የውቅሮ አስተዳዳሪ

 ምሩፅ - የዛላምበሳ እና አካባቢዋ ሕዝብ ጉዳይ ሓላፊ

 ሃረያ ስባጋድስ - ዓድዋ የሕዝብ ጉዳይ ሓለፊት (ልጅቷ በህይወት የለችም፡ አብራኝ ስትማር የነበረች፡(12ኛ ክፍል) የተወልደ ወ/ማ ባለቤት የነበረች ነች (ከተርጓሚው ጌታቸው ረዳ)

አቶ ሙሉ ሰንደቕ - የህዝብ ጉዳይ

 ሸዊት ገብረክርስቶስ -የሕዝብ ጉዳይ

ዓባዲ ወልዱ - የሕዝብ ጉዳይ

ካሕሳይ ቆራይ - የእስርቤቶች (06) ጉዳይ ሓላፊ

 እና በመቶዎች የሚቆጠሩ እነዚህና እነዚህን የመሳሰሉ የሕዝብ ጉዳይ ሓላፊዎችና ካድሬዎች ሲካሄድ በነበረው የሕዝብ ዓፈና ተጠያቂዎች ብቻ ሳይሆኑ ዓፈናውን በግምባር ቀደምትንት ፈፃሚዎችና አስፈፃሚዎች የነበሩ ናቸው።

ለዛ ዓፋኝ እና አስገዳጅ የምልመላ መርሃ ግብርና ዓፈናውንም ግብር ላይ መዋሉን የሚከታተል ፖሊት ቢሮ ማአከላዊ አባላት ሲሆን በተለይም ደግሞ የማአከላዊው አመራር ኣባል (ሰንትራል ኮማንድ) በቀጥታ ምልመላውን በምን ሁኔታ መካሄድ እንዳለበት ይቆጣጠረው ነበር።

ከላይ ተጠቀሱት ሰዎች ምድብ ሥራቸው ተሰማርተው ዓፈናውን ማጧጧፍ ከጀመሩ በሗላ በጣም በርካታ የከተማና የገጠር ወጣቶች ካአፈናው ለማምለጥ ሲሉ ወደ ሱዳን (ጂዛን) እና ወደ ደርግ መሸሽ ጀመሩ።

 በተላለፈው መመርያ መሠረት ከዚያ በሗላ የሸሹትን ወጣቶች ቤተሰቦች ንብረታቸው እየተቀሙ/እየተወረሰ ሚሰት፤ ባለቤት፤ አባት፤ እናት፤ ወንድም፤ አጎት....ሁሉ እየተለቀሙ ፅዳት በጎደላቸው፤ምግብ በሌለበት፤ሕክምና በሌለበት ትናንሽ እስር ቤቶች እና የእስረኛ ማጎርያ ስፍራዎች ታጉረው እንዲሰቃዩ በመደረጉ ለታይፎይድና ልዩ ልዩ ለተላላፊ በሽታዎች እና ለተቅማጥ በሽታ ተጋለጡ

 ከገጠር የተወረሰ የቤተሰብ እህልም ወደ ከተማ እየተጫነ የአሳሪዎቻቸው ባለሥልጣኖች መሽሞንሞንያ ሆነ። ክፍሊ ህዝቢ (የሕዝብ ጉዳይ) የሚሉዋቸው እነዚህ ክፍሎች ባለ ሙሉ ሥልጣን ሆነው ያለ ተቆጣጣሪ ሕዝቡን አበሻቀጡት።

17 ዓመት ሸሽጎ፤ አዝሎ ወደ ሰሜን ሸዋ ያሸጋገረን እሽርሩ ብሎ ተንከባክቦ ያሳደገን ሕዝብ ካሳው/ወረታው/ ዓፈና ሆነ! አሳዛኝ! በአስገዳጅ እየታፈነ ወደ ህወሓት ትግል እንዲገባ የተደረገው ይህ አሳዛኝ ድርጊትና ግፍ ለማስረጃ እንድትሆናችሁ እኔ የማውቀው በዓይኔ ያየሁዋት አንዲት ማስረጃ በማቅረብ ልመስክር።

ሃቁን ገልጬ ለናንተው ለፍረድ ልተወው። በወቅቱ ምድብ የሥራ ቦታየ ሽሬ ውስጥ ነበር። አዲስ መመርያ ስለሚተላለፍ ወደ ሃገረሰላምና (ተምቤን) ባስቸኳይ እንድትመጣ ተብየ ትዛዝ ተላልፎልኝ በመመርያው መሠረት ከሽሬ ተንቀሳቅሼ መንገድ ስጀምር መውጫ በር ላይ በሺሕ የሚቆጠሩ ፍየሎች፤ በጎች፤ላሞች፤በቅሎና ደሮዎች በወያኔ ታጋዮችና ሚሊሽያዎች እየተገሩ ወደ ከተማው ሲገቡ አገኘሗቸው።

ግራዝማች በላይ ሃይሉ የተባሉ አንድ አዛውንት አባት ከከብቶቹ ኋላ ኋላ በአዝግሞት ሩጫ እየተከተሉ ንብረቴ ዘረፉኝ እያሉ እየጮኹ ሰማኋቸው። እንዴ! ምን ጉድ ነው ብየ፤ ምን የሆኑ አባት ናቸው? ብየ ታጋዮቹን ስጠይቅ ”አይ ተዋቸው ሕሊናቸው ተቃውሶባቸው ነው” አሉኝ።

 አብረውኝ ከኔው ጋር በመኪና ሲጓዙ የነበሩ 8 ታጋዮች ነበሩኝ። መኪናዋን አስቁመን ”አቦ! (አባባ) ምንድነው ችግሩ? ብለን ጠየቅናቸው። ”ንብረቴ ተወረርኩኝ! ወያኔ ፀባይዋ ቀይራለች! አዲስ ጠባይ አምጥታለች!” አሉን። እኚህ አባት ታጋይ ዘነበ በላይ የሚባል ልጃቸው በ1968 ዓ.ም ተጋይ ሆኖ እስከ የሃይል መሪነት እና አዋጊ ሆኖ ውጊያ ላይ ተሰውቷል።ሌሎች ሁለት ልጆቻቸውም እንደዚሁ ታጋዮች ሆነው በክብር ተሰውተዋባቸዋል። ይህ ሁሉ አስተዋፅኦ አድርገው ልጆቻቸውን ያጡ አዛውንት አባት መሆናቸውን እየታወቀ አንድ የቀራቸው ልጃቸውን ታገል ተብሎ አልታገልም ብሎ ስለተሰወረ፡ የኚህ አባት ንብረት የሆነ 30 ፍየሎች 42 ከብቶች አንድ በቅሎ6 አህዮች 10 ኩንታል እህል ወረሷቸው።

እኛም ታሪካቸውን ሰምተን በማዘናችን የሳቸውና የሌሎች ሰዎች ፍየሎችና ከብቶች በጎች ቀላቅለው ሲነዷቸው የነበሩ እነኛ 3 ታጋዮችና 10 የሚሆኑ ጀሌዎች (ሚሊሽያዎች) ጠርተን የሚመለከታቸው ክፍሎች እስክናነጋገር ድረስ እየነዳችኋቸው ያሉትን እንሰሳት በሙሉ ካመጣችኋቸው መልሳችሁ ውሰዷቸው፡ ብለን አዘዝናቸው። ትዛዙን ላለመቀበል ብያጉረመሩሙም ሳይወዱ መለሷቸው።

ጉዟችንን ቀጠልን። በለስ ከተባለች ትንሽ ከተማ ደረስን። በዛች ትንሽ ከተማ ውስጥ ከላይ ቆራሮ እና ከታች ቆራሮ የተለቀሙ በሺዎቹ የሚቆጠሩ ዜጎች ህፃናት ሽማግሌዎች ሳይቀሩ ልጆቻችሁ/ቤተሰቦቻችሁ ከተሸሸጉበት ቦታ አምጧቸው ተብለው መጠለያ በሌለው አውላላ ሜዳ ላይ ልክ እንደ አውጫጭ በጥበቃ ተከብበው ታጉረው ታስረው አየን። ራቅ ብለህ በሺ የሚቆጠሩ የታሳሪዎቹ ንብረት የሆኑ ላሞች፤ከብቶች የቤት እንሳሰት ጠባቂ አልባ ሆነው የሌባ ቀለብና እና የጅብ እራት ሆነው ለአደጋ ተጋልጠው ይቀራመቷቸዋል።

ያ አልበቃ ብሎ በሌሎች ቦታዎችም በሰለኽለኻ በኩል ስናልፍ የታዘብናቸውም ቢሆን በለስ ውስጥ ካየነው የባሰ በየጠባብ ማጎርያ እስር ቤት ክፍል ውስጥ በብዛት ታጭቀው፤ምግብ ውሃ ተከልክለው፤ንፅህና በጎደላቸው ክፍሎቸ ታጉረው በቅማል በላብ በእድፍ ምክንያት በታይፎይድ (በተላላፊ በሽታ በአር ኤፍ) በወባ በሽታና በተቅማጥ እየተሰቃዩ ጠረኑ ለህዋሳት የሚዘገንን ሽታው የማያስጠጋ ማጎርያ እስር ቤት ታጉረው አየን። ይህን ስመለከት በስልጣኔ እንድፈታቸው ፈልጌ ነበር፡የሰለኽለኻ ሕዝብም እርምጃው በጣም ስለተቃወመው እንዲፈቱ ግፊት ያደርግ ስለነበር ድርጊቱ በውስጤ እጅግ አስቆጣኝ። ይሕ ግፍ የተመከተ ሰብአዊነት የተላበሰ ሰውም ምን እንደሚሰማው የታወቀ ነው። እኔም የተወለድኩባት መንደሬ በመሆኗ ለመንደሩ ተቆርቁሮ ነው ፤አድልዎ በማድረግ ነው የፈታቸው እንዳልባል ”ነብሴ ላዘሬ ብለሽ ታገሺ” ብየ ውስጤ እሳት እየነደደበት ወደ ውቅሮ ማራይ (አክሱም አጠገብ) ተጓዝን።

 ውቅሮ ማራይም በሺ የሚቆጠሩ እንሰሳት እና ሰዎች የታሰሩ ገጠመኝ። አክሱም ከተማም አንደዚሁ በሺዎቹ የሚቆጠሩ እስረኞች አንዳሉ ተገነዘብኩ። ዓድዋ/ዓዲ አቡን እንደደረስንም ባካባቢውና ከተማው ውስጥ የነበረው የእህል ማከማቻ ጎተራ በሺዎቹ የሚገመቱ እስረኞች ታጉረውበት እንዳሉ ካገኘናቸው ገበሬዎችና ታጋዮች በኩል እንዲህ ያለ አሳዛኝ የእስራት አስገዳጅ ዘመቻ በመላ ትግራይ ውስጥ በሰፊው እየተጧጧፍን እንደሆነ እና በተለይም አልታገልም ወይም ልጄ የት እንደሸሸ/ሸሸች አላውቅም ያለ ሁሉ ንብረቱ እየተቀማ እየተጎተተ ፍዳውን አየ።

ኩፍኛ የተጧጧፉባቸው ማጎርያ እስር ቤቶች የተባሉት በዓድዋ፤አክሱምና ሽሬና ተምቤን ውስጥ የከፋ እንደሆነ ነገሩን። ጉዟችን ወደ ሃገርሰላም ነው። ያ ከሽሬ ጀምሮ አክሱም እስከ ዓድዋ ድረስ ያየነውና የሰማነው በሕዝብ ላይ የደረሰው ግፍ ጉዟችን የከፋና በሃሳብ እንድንዋጥ አድርጎት ነበር። ጉዟችን ወደ ሀገረሰላም ከማቅናታችን በፊት የተመለከትነው አሳዛኝ ድርጊት ዓድዋ ውስጥ ለነበሩ ማዕከላዊ ኮሚቴ ባለሥልጣኖች ስለ ሁኔታው አሳሳቢነት መንገር እንዳለብኝ ወሰንኩ።

ስለሆነም ሁኔታውን ለመንገር የማአከላዊ ኮሚቴ አባላት ወደ ሆኑት ወደ አረጋሽ አዳነ፤ቢተው በላይ፤ሓሰን ሽፋ፤ አብርሃ ማንጁስ፤ካሕሳይ ቆራይ ወደ ሚተኙበት ቤት አመራን።

እነኚህ የደጀን መሪዎች ቤት ዘግተው በኮንትሮባንድ የመጣ መጠጥና ከውጭ አገር የመጣ የቆርቆሮ ቢራ እየተጎነጩ በውጭ አገር ቪዲዮ ካሴቶች እየተዝናኑ ሲመለከቱ ደረስንባቸው። መጀመርያ በሩን ስናንኳኳ እኛ መሆናችንን ካወቁ በሗላ ግቡ፤አረፍ በሉ እንኳን ደህና መጣችሁ ቤት ለእንግዳ ከማለት እና እንደታጋይ ጓዶቻቸው ከማስተናገድ ይልቅ ”ጉዳቸውን” እንዳናይባቸው በማለት በሩን ከፍተው ሐሰን ሽፋና ቢተው በላይ ወደ ደጅ በመውጣት እንደማንም ሰው ከደጅ አነጋግረው ሊመልሱን ዳዳቸው።

 ዘግናኙ ሁኔታ በዝርዝር ነገርናቸው። በማይገባ ውሳኔ ወላጆቻችን ፤ሕዝባችን በቁር በበሽታ በረሃብ በሙቀት በጠባብ ክፍል ታጉሮ ለተላላፊ በሽታ ለስቃይ ተዳርጎ ንብረቱና ከብቱ በድርጅታችን እየተወረሰ ታስረው ተሰቃይተው እየሞቱ፤ እህሉ ከብት፤በግ ፍየሉ ንብረቱ ሁሉ ወርሳችሁ ለስቃይ ዳርጋችሁት በወረሳችሀት ገንዘብ በመፈንጨት ትጠጣላችሁ ትበላላችሁ። ጭራሽኑ ይህ የተበደለ ሕዝብ ልጅ ከወላጁ ተሰብስቦ አንድ ቀን ይበላችሗል፡ጭራሽኑ ለምናካሂደው ትግል እንቅፋት ነው። እያልን ስንነግራቸው፤ ሓሰን ሽፋ በማሾፍ ገጽታ ተመለከተን፡ ቢተው በላይም ”ተደፈርን” ብሎ ተቆጣ።

ቆየት ብላ አረጋሽ አዳነ መጣች። እየነገርናቸው ያለውን ጉዳይ አዳመጠች። ብዙ ከተጨቃጨቅን በሗላ ወደ ነበሩበት ክፍላቸው ተመልሰው በመግባት ስብሰባ ካደረጉ በሗላ ”ሁሉም ይፈቱ ነገር ግን 150 ብር እየተቀጡ ይውጡ” የሚል ውሳኔ አሳለፉ። አሁንም ጭቅጭቅ ገባን። ገንዘብ እየከፈሉ ይፈቱ አሉ እንጂ መቸ መፈታት እንዳለባቸው ላቀረብነው ጥያቄ አልመለሱትም። መጨረሻ አክርረን ስናጠብቅባቸው እስረኛ በሙሉ ከዛሬ ጀምሮ እንዲፈታ፤ የታመሙትንም ሕክምና እንዲያገኙ ሓኪሞች እንዲሰማሩ እናደርጋለን አሉ። እኛም ከምድብ ቦታችን ተነስተን ለአስቸኳይ ስብሰባ ለመሄድ አስበነው የነበረውን ጉዞ ሠርዘን ወደ ሗላ በመመለስ ያስተላለፋችሁትን ማዘዣ መልዕክት ይዘን እንድንመለስ የመፍቻ ወረቀት ትእዛዝ ስጡን አልናቸው። እነሱም በስምምነታችን መሠረት ወረቀት ሰጥተውን የወደፊት ጉዟችን ሰርዘን ወደ ሗላ በመመለስ በሌሊት ገስግሰን ወደ አክሱም፤ሰለኽለኻ፤ሽሬ አድያቦ ወረዳዎች ውስጥ ላሉ እስር ቤቶች እንዲዳረሱ አደረግን።

እኛ ባሰማነው ተቃዉሞ በመላይቱ ትግራይ ውስጥ ታጉሮ በግፍ ታስሮ ሲሰቃይ የነበረ በሺዎች የሚገመት እስረኛ እንዲፈቱ ተደረገ። የተወረሰው ንብረትም ሆነ ላም ከብት ፍየል በግ እንዲመለስለት ትዕዛዝ ይተላለፍ እንጂ ብዙ እንሰሳ እና ንብረት የክፍሊ ሕዝቢ (በየገጠሩና በየከተማው የተመደቡ የሕዝብ ድርጅት ጉዳይ ሓላፊዎች) ሓላፊዎችና የወያኔ ሚሊሺያዎች ምግብ ሆነው የተቀሩትም ያለ እንክብካቤ በዘራፊና በአራዊት እየተበሉ የትም ቀርተዋል። እኛም ውሳኔውን እንዲፈፀም ካደረግን በሗላ ወደ መድረሺያችን ወደ ሃገረሰላም (ተምቤን) ጉዟችን በቀን ቀጠልን።

ሃገረሰላምም በሰላም ገብተን ጉዳየችንን እንደፈፀምን ወደ ምድብ ቦታችን ከመመለሳችን በፊት ወዲያውኑ አከታትለን በሕዝብ ላይ እየደረሰ ያለው ግፍ ለተወልደ ወልደማርያም፤ለመለስ ዜናዊ፤ለዓባይ ፀሃየ፤ለስየ አብርሃ እና ለስብሐት ነጋ ነገርናቸው። በጣም አሳዛኝና አሳሳቢ ሁኔታ እንደሆነም በሰፊው አስረዳናቸው።

 እነሱም ወደ የሕዝብ ጉዳይ ክፍል ሓላፊዎችና የትግራይ ደጀን ሓላፊዎች በመጻፍ የታሰረው ሕዝብ እንዲፈታ ተጨማሪ ትእዛዝ በጽሑፍ ጽፈው ሰጡን። ቀደም ብየ እንደገለጽኩት ሰዎቹ በኛ አቤቱታ በማዘዣ እንዲፈቱ ይደረግ እንጂ የቤት ንብረታቸው ላምና ፈየል ደሮ እና በግ ተወርሰው አብዛኛው የትም ባክኖ ቀረቷል።

ይህ በ1983 ዓ.ም ከሽሬ እስከ ዓድዋ ድረስ ባጋጣሚ ስጓዝ ድንገት ያየሁት በሕዝብ ላይ የደረሰ ግፍ እንጂ በሌሎች ወረዳ ጣቢያዎች ከተሞች ገጠሮች በሰው ልጆች ሲፈፀም የነበረ ኢሰብአዊ ግፍ ቢገለጥ ተጽፎም አያልቅ፤ ብዙ መጻሕፍቶችም በወጡት ነበር።በዚህ መጽሐፍ ላይ በጨረፍታ እንደማስረጃ የጠቀስኩት ባይኔ ያጋጠመኝ በሕብ በጅምላ በድርጅታችን የተፈጸመ ግፍ ለታሪክ ፃሐፍት መነሻ እንደሚሆናቸው በማሰብ ነው።” (አስገደ ገብረስላሴ -ጋህዲ ቁ 3 የትግርኛው ቅፅ 289-293) ከትግርኛ ወደ አማርኛ ትርጉም ጌታቸው ረዳ (የወያነ ገበና ማሕደር መጽሐፍ ደራሲ ጌታቸው ረዳ ኢትዮ- ሰማይ- የትርጉም ስሕተት የጻሐፊው ሳይሆን የእኔ የተርጓሚው ሓላፊነት መሆኑን አሳውቃለሁ)

አንግዲህ ከላይ እንዳነበብነው የወያኔ ትግራይ የገበና ማሕደር መሠረት ድርጅቱ እጅግ የከፋ አረመኔ ቡድን ሲመራው በትግራይ ኗሪ ላይ ያደረሰው አሰቃቂ ግፍ ነበር።

 ስትራቴጂካዊ መጥቃዕቲ (ወሳኝ/ዘላቂ የማጥቃት ዘመቻ) በሚል የጦርነት ትልም ሲያቅዱ የጠበቁትን የሰው ሃይል ጌቶቻቸው ሻዕቢያን ለማዳን ወደ ኤርትራ በመላክ ብዙ ሺሕ የትግራይ ታጋይ በማለቁ ምክንያት ስለተማናመኑ፤ በግድም በውድም 80,000 አዲስ ወጣት ታጋይ ያስፈልገናል ስላሉ ለወታደራዊ ስልጣና በማንቁርቱ እየታነቀ ወደ ማሰልጠኛ ጣቢያ ሲወረወር፤ የሸሸውም የቤተሰቡን ንብረትና የቤት እንሰሳ እየተወረሰ እየታጎረ በተላላፊ በሽታ በተቅማጥ በወባ በቅማል በመሳሰሉት ለስቃይ ተዳርጎ በኮንሰንትሬሽን ካምፕ/በማጎርያ እስርቤቶችና አውላላ ሜዳ ላይ ተከብቦ የደረሰበት ግፍ ፤-አሳሪዎቹና አድራጊ ፈጣሪ የወያኔ ማአከላዊ ኮሚቴዎቹ ግን ቢራና ዊስኪ እየጎነጩ፤በውጭ አገር ፊልሞች እየተዝናኑ ዓለማቸው ሲቀጩ እንደነበር ከውስጥ አዋቂ በይፋ ሲገለጥ የሚሰማችሁ ስሜት ለናንተው ለሰው ልጆች መብት የቆማችሁ ዜጎች ሁሉ ለሕሊና ፍርድ ልተውና ልሰናበታችሁ።

ዛሬም እነሆ ያንን የሕዝብ ማስጨፍጨፍ አስገድዶ ወደ ጦርነት ማስገባት ሳይጠየቁበት እነሆ አሁንም ከሥልጣን ተፈነቀልን ብለው ያንን በመድገም የትግራይ ማሕበረሰብ ወደ ባሰው ሲኦል ከትተውታል። የትግራይ ምሁራን የዚህ ወንጀል ተካፋዮች እና ተጠያቂዎች ናቸው። የገዛ ወንድሞቼና ዘመዶቼ በ17 አመቱ የጫካ ትግላቸው አንዳንዶቹ እስካሁን ድረስ ለ44 አመት አመት አካል ጉዳተኞች የሁኑ አሉ።

“ትግራይ ከዚህስ ወዴት?” እያሉ የትግራይ ምሁራን በነ ፕሮፌሰር ጌታቸው አሰፋ UMD የድረገጽና የፌስቡክ ሓላፊ እየተጋበዙ ያንን የድሮ ወንጀል ሲደግሙና “ግፋ በለው” ሲሉ መስማት እጅግ ያሳዝናል።

ፈጣሪ ይቅር ይበላችሁ!

  ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay

 

Sunday, July 10, 2022

Translation By Assefa Negash, M. D. Amsterdam, the Netherlands - 10th of July 2022 Ethiopian Semay 7/10/22

                                                                         Translation

                                                            By

Assefa Negash, M. D.

Amsterdam, the Netherlands - 10th of July 2022

Ethiopian Semay

7/10/22

I have Buried 61 People Including 22 of My Own Children and Grandchildren – Personal Testimony of an Amhara Father Who Survived the Massacre at Gimbi (Western Ethiopia) on Saturday the 18th of June 2022

 

Readers of this translated report can forward any comment they may have with regard to the translation via Debesso@gmail.com

 

On Saturday the 18th of June 2022 many Amhara inhabitants and their family members have been killed in the massacre perpetrated at the locality known as Tole which is located in Gimbi, Western Wellega zone of Ethiopia.  

Among the Amhara inhabitants of this locality who survived this gruesome massacre figure Mr. Mohammed Yusuf. Mr. Mohammed Yusuf, aged 64 told (BBC reporters) that he moved from his birth place Harbu which is located in Wello of the Amhara region to his present place of residence Wellega in 1990. He moved from his birth place to Wellega in order to escape the deleterious effect of the drought that affected his birth place at that time.

Mr. Mohammed moved to Wellega, along with his wife he married at a young age and their six children. After he moved to Wellega, he was legally given land to till and was engaged in farming thereby paying the appropriate tax due to the government. After he moved to Wellega, he got more children and has also been able to be a grandparent.

Mr. Mohammed who said that “Before this time, there was no such worry. We used to live by working very hard on our farm”. But what transpired or happened on Saturday the 18th of June 2022 was unprecedented and has left behind an indelible memory of grief which he cannot ever forget. On this fateful date the 18th of June 2022 when the locality he lives in was invaded by armed men, “assuming that they do not kill women and children, my children, grandchildren gathered at my home and sat behind closed door. I hid myself in within a maze farm” said Mr. Mohammed recollecting what happened.  

Mr. Mohammed said that he returned to his home after the shooting which lasted more than half a day has subsided. But when he arrived at his home, the door of his house was left wide open. When he entered his house, his family members whom he left behind were not inside his house. Mr. Mohammed said “I moved here and there and everywhere in search of my family members”. In the process of searching for his family members, he met his wife and the mother of his children, with whom he has lived since his youth walking on the road. His wife has sustained wounds on her side (flank) and her palms. His wife who was soaked in blood was heading to her house.

Mr. Mohammed said “we were overwhelmed by shock”. And added that “I asked my wife where are the children?”. Mr. Mohammed’s wife told him that they were killed near the Mosque. Mr. Mohammed hurriedly ran towards the Mosque. But when he arrived at the Mosque, there was no one survivor left alive. “He found bodies of massacred members of his family piled upon each other. And that included a newly born child”. As he was relating this story, Mr. Mohammed was sobbing.

According to Mr. Mohammed, his family members were taken away from their village and taken to another village known as Chekorsa Selsaw and killed next to the Mosque located there. Mr. Mohammed said that “at this place 42 individuals, including my family members, have been massacred”. Mr. Mohammed was still crying while relating the following about the loss he sustained.

“My eldest daughter Semira Mohammed was killed along with her five children (6 family members); my daughter Aminat Mohammed was killed along with her four children (5 family members); my daughter Amet Mohammed (1 family member); Saada Mohammed (1 family member), Fatima Mohammed was killed with her five children (6 family members) and my daughter Mereyma Mohammed was killed along with her two children (3 family members) thereby making the total number of family members of Mr. Mohammed massacred soar to a staggering figure of 22 persons)”. According to Mr. Mohammed children of his sister had been killed and six other members of his family members who sustained injury are undergoing medical treatment at the Nekemt and Gimbi hospitals.

Among his children who had been killed figure his eldest daughter Mrs. Samira Mohammed who was 40 years of age and the youngest victim of massacre is the daughter of his sister who was just four days-old (newly born baby). In the grave I dug on my own to bury my children and grandchildren, sixty-one (61) people were buried. Mr. Mohammed said that there are many Amharas who have lost all their family members and remain alone now.

Mr. Mohammed said that “we have not done any harm to anyone except tilling our land in order to earn our living. We have been killed because we are Amharas” thereby underscoring the fact that the attack (the massacre) was specifically directed against members of the Amhara ethnic group.  The house, store and property of Mr. Mohammed had been set on fire and destroyed. Mr. Mohammed told the BBC reporters saying that he is staying with the remaining family members who survived the massacre in the part of the house that has survived the fire attack.

Mr. Mohammed said “I am spitting out blood in grief and my brain is not functioning anymore”. He added “No government authority or functionary has come towards them (the survivors) to even ask what happened to them”. He said “This neglect by the government has compounded or amplified the grief of the survivors”.

According to Mr.  Mohammed, the area in which he lives is not yet free from security risks and worries linger on or persist for the surviving inhabitants of the area. Mr. Mohammed said “They have held us back from leaving the area but what we want the government to do is help us get out of here”. He added “How can we live in the place where we have buried our beloved children and family members in our own backyards?” Mr. Mohammed added that “The surviving women and children are leaving the area on foot”.

A local official, who chose to remain anonymous, told to the BBC journalist saying that “most of the people massacred on the 18th of June 2022 were pregnant women, children and women”. This local official has confirmed to the BBC the fact that “Mr. Mohammed Yusuf has lost twenty-two (22 family members) of his children and grand-children”. The local official who was present at the funeral confirmed to the BBC the fact that among members of Mr. Mohammed Yusuf’s family members figured children who were 2 ½ years old, seven years old and 10 years old.

The local official told the BBC that he did not have prior knowledge in regard to the security risks/problems obtaining in the area and said that the members of the armed group (the Oromo Liberation Army) have been living in the adjoining desert for more than three years.   

“For more than a month, we have witnessed the movement of many armed men (members of the Oromo Liberation Army otherwise dubbed Shene by the government). It was reported that these armed men were traveling to Dembidolo (a region located in Western Wellega). But as of May 2022, we do not have any information about them” added the unnamed official.

The official said “We do not have contact with the district administrators. As the roads are closed, we cannot travel to the administrative office of the district even when we are called to come there and participate in meetings. It is only when government security forces come to our areas that we can move about to conduct our work” thereby underscoring the security risks and problems obtaining in the area.     

“On Friday the 17th of June 2022, security forces (belonging to the Oromo Regional government administering the Oromo region) left the area, just a day before the massacre was perpetrated. When we asked why the government security forces were withdrawn from the area, we were not told the exact reason for their pull out or withdrawal. Subsequent to their withdrawal, we were in a state of fear (apprehension) and suspicion” told the local official to the BBC.

The Amhara association, based in USA, has stated that many Amhara inhabitants have lost all or most of their family members and added that Mr. Mohammed who lives in the Chekorsa locality of Wellega (Western Ethiopia) has lost 31 family members. With regard to the number of victims of the massacre, the Ethiopian government has put the number of those killed just to 338 individuals whereas the Amhara Association, based in USA, has put the number of those massacred so far as being close to 600 individuals.

Eye witnesses, survivors of the massacre and the Ethiopian government whom BBC has talked to, have blamed the Oromo Liberation Army (belonging to the Oromo Liberation Front) otherwise dubbed Shene by the government as being responsible for the massacre. The Oromo Liberation Army on its part has blamed the Ethiopian government as being the culprit or the perpetrator of the massacre.

The Human Rights Commission of the United Nations (UN) has stated that many houses were burned down and more than 2000 people have been uprooted and displaced following the killings of hundreds of people, most of those killed being women and children. Following the attack (massacre), the UN Commission for Human Rights and other political organizations have demanded a speedy, independent and a detailed inquiry into the massacre. The Ethiopian parliament has instructed the Ethiopian Human Rights Commission (which is a governmental body) to conduct an investigation about the horrendous human rights violations perpetrated on innocent citizens in Western Wellega and Gambela and report back to the parliament. It has also been reported that United Nation’s Human Rights Commission would investigate the massacre perpetrated in Western Wellega.

----------------------End of the Translated Text -------------------------

Note from the translator:

This report was compiled by BBC’s Amharic Service. It has bearing on the recent massacre perpetrated against innocent Amhara civilians living in Western Wellega (Western Ethiopia). In order to reach a wider public, I have translated it into English. Please help in spreading the word about this horrendous genocide which is still unfolding with increased intensity and fervor as witness the genocide that followed at Kelem (Western Wellega) on the 3rd of July 2022 claiming at least 400 lives of innocent Amhara civilians, just two weeks after the massacre at Tole on the 18th of June 2022. Since Abiy Ahmed has been ensconced into power, Wellega has been the frequent site of Amhara carnage. The massacre has all the hallmarks of genocide as it has targeted members of a particular ethnic group (Amharas) who have been subjected to a barrage of systematic and incessant campaign of state-sponsored demonization, dehumanization thereby singling out members of the Amhara ethnic group dispersed in all nooks and corners of Ethiopia, particularly in the newly carved ethnic homelands of Oromia, Benishangul, Metekel, Southern region, etc for a gruesome massacre on account of their ethnic identity. This has been unfolding during the past 31 years. Bedeno, Arba Gugu, Metekel, Grua Ferda, Benishangul, Tepi, Guliso, Eastern & Western Wellega, etc bear witness to the horrendous atrocities committed against Amharas with the abatement, connivance and authorship of the Ethiopian state be it the one led by the Tigrean People’s Liberation Front (TPLF) from 1991 to 2018 or the one led by the Orommuma ultra-nationalist/fascist party of Abiy Ahmed (from 2018 till now) donned and masquerading as the “prosperity” party.

The words or statements in parenthesis in this translated report have been added by me the translator to highlight some of the texts that need more elaboration for readers who may not be conversant with the reality of Ethiopia.