ሊቀ ሣጥናኤል በቤተ መንግሥት
ዳግማዊ ጉዱ ካሣ
Ethiopian Semay
6/18/22
ሰሚ ኖረም አልኖረም ሊቀ ሣጥናኤል አቢይ አህመድ የተሠራው ከውሸት መሆኑን ደጋግመን ጽፈናል፤ ተናግረናል፡፡ በሰሞኑ የፓርላማ ስብሰባ ደግሞ ይህንኑ በሚገባ አረጋግጦልናል፡፡ እኔ እዚያ ፓርላማ ተብዬ ውስጥ እንደአንድ አባል ተቀምጬ ብሆን ኖሮ እንደወጣሁ ወደሚቀርበኝ ዛፍ ሄጄ እንጠለጠል ነበር፡፡ በዚያ ዓይነት ሰው መመራት እጅግ እጅግ አሳፋሪና ስብዕናን የሚነካ ነው፡፡
የውሸቱ ለከት ማጣት ሰው ለሆነ ሰው ክፉኛ ያስደነግጣል፡፡ ለሌሎች የማይታይን ዕድገትና ብልጽግና
ሲናገር “ለእናንተ አይደለም ለኔ ነው የሚታየው” በማለት እርሱ የተለዬ የማየት ችሎታ እንዳለው በተካነበት ሥራየ-ቤታዊ የሽሙጥ
አነጋገር ሲገልጽ ዞምቤ ሮቦቶቹ ከማጨብጨብ ባለፈ አልገረማቸውም፤ አልደነቃቸውም፡፡ ምክንያቱም እነዚህ የንክር ቤት አባላት በመጽሐፉ
“ዐይን አላቸው አያዩም፤ አፍንጫ አላቸው አያሸቱበትም፤ አፍም አላቸው አይናገሩበትም” ተብሎ እንደተነገራለቸው የጣዖት አማልክት
ናቸውና ከድጋፍ ጭብጨባ ባለፈ ምንም ነገር አያውቁም፡፡ ሲናገሩ እንደምንሰማቸው የተጻፈላቸውን እንኳን ለማንበብ የሚንተባተቡና የሚቸገሩ
ናቸው፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ በነዚህ ሲወከል ይታያችሁ፡፡ ደግነቱ እኛን ከቁም ነገር ቆጥሮ የሚያይ የለም እንጂ ቀሪው ዓለም በነዚህ
ተወካዮቻችን ጥርሱን በዘነዘና ተወቅሮ በሣቀብን ነበር፡፡ ከቃላት ጦርነት ባለፈ አሽትሬ እየተወራወሩ የሚጨቃጨቁና የሚከራከሩ የፓርላማ
አባላት ባሉባት ዓለማችን እነዚህን ጉዶች ማየትና በነዚህም እንደምንወከል ሲነገር መስማት በአቢይ አገላለጽ ያስደነግጣል፡፡
ከ500 በላይ የሚቆጠር በግ በአንድ አዳራሽ ሰብስቦ ይሄ አቢይ የሚባል ሊቀ ሣጥናኤል እንጨት እንጨት የሚል የቁጭ በሉ ድራማ ይተውንብናል፡፡ ለነገሩ በራሱ ላይ ነው ትያትሩን የሚጫወተው፡፡ ሒሣቡን የሚወራርደው ራሱ ነውና፡፡ የዚህን ሰውዬ መጨረሻ ሂትለርና ሣዳም ሁሴን ይቀኑበታል፡፡
በነገራችን ላይ የአቢይን ተፈጥሯዊ ጠባይ የሚገልጡ ሁለት አጫጭር ታሪኮችን ልናገር፡፡ ባትስቁም ፈገግ በሉ፡፡
አንዱ ዐይኖቹን ታሞ ከቅምብቢት ወደ አዲስ አበባ ዳግማዊ ምኒልክ ሆስፒታል ይመጣል፡፡ ዱሮ ነው ታዲያ፡፡
የህክምና ዶክተሩ የልጁን ዐይኖች ሲመረምር ወጥተው መታጠብና መጽዳት እንደሚኖርባቸው ይረዳል፡፡ ወዲያውኑም ውልቅ ያደርጋቸውና አጣጥቦ
መልሶ ሊከታቸው ሲል ጓደኛው ለሻይ ይጠራዋል፡፡ ከሻይ ሲመለስ ግን የልጁን ዐይኖች ካስቀመጠበት ያጣቸዋል፡፡ ያኔ ዘወር ሲል አንድ
የሆስፒታሉን ድመት ይመለከታል፤ ያም ድመት ኖሯል እነዚያን ዐይኖች ቀርጥፎ የበላቸው፡፡ ይሄኔ ዶክተሩ ምኑ ሞኝ ያንን ድመት ይይዝና
ዐይኖቹን በህክምና ዘዴ ጎልጉሎ አውጥቶ በጠፉት ምትክ በታማሚው የዐይኖች ጉድጓድ ይሰካቸዋል፡፡ ከዚያም ከ15 ቀናት በኋላ ለቼካፕ
እንዲመለስ ነግሮ ልጁን ወደቅምብቢቱ ይሸኘዋል፡፡
ዐይኖቹን ታክሞ አገር ቤት የሄደው ልጅ ዘመድ አዝማድና ጎረቤት ተሰብስቦ ጠበቀው፡፡ በልጃቸው መምጣት የተደሰቱት የአካባቢው ማኅረሰብ አባላት ልጁን ጥያቄ በጥያቄ ወጠሩት፡፡ “እንዴት ነው በደምብ ይታይሃል?” “አዎ፣ በደምብ ይታየኛል”፤ “አሁን በዙሪያ ምን ይታይሃል?” “አሁን በዙሪያየ ብዙ ዐይጥ ይታየኛል፡፡” ልጁ ልክ ነው - “ዶሮ ብታልም ጥሬዋን” እኮ ነው ነገሩ፡፡ የማያውቁት አገርስ ይናፍቃል?
እውነት ነው፣ የድመት ዐይን ከዐይጥ ሌላ አይታየውም፡፡ የአቢይም አንደበት ከውሸትና ከእብለት ሌላ ሊናገር ፈጽሞውን አይችልም፡፡ ችግሩ ያለው ከርሱ ሳይሆን ከኛው ከሀገሪቷ ሕዝብ ነው፡፡ ይህን የመሰለ እንኳንስ ሀገር ለመምራት ራሱንም መምራት የሚያስቸግር ዕብድና ወፈፌ ዜጋ ቁንጮ ላይ ማስቀመጥ ወይም እንዲቀመጥ መፍቀድ ነው ትልቁ ችግር፡፡ ኢዲያሚን ዳዳም፣ አፄ ቦካሣም እንደኛው ልጅ ዕብድ ነበሩ፡፡
ሁለተኛዋ ትንሽ ታስከፋለችና ብተዋት ደስ ባለኝ፡፡ ግን አልተዋትም፡፡ አንዱ ዲያቆን ሚስት ሊያገባ
ነው፡፡ ግን ልጃገረድ እገስሳለሁ ብሎ በራሱ አይተማመንም ነበር፡፡ በራስ ላይ እምነት ሲጠፋ ደግሞ አእምሮ አስቀድሞ ተቀይዷልና
ችግር መፈጠሩ አይቀርም፤ በራስ መተማመን ጥሩ ነው፡፡ አለመተማን ግን ብዙ ጣጣ አለው፡፡ ይህም ልጅ ታዲያ ሠርጉ ደርሶ የሙሽራ
ወጉን በማድረግ የደም ሸማው ሲጠበቅ እርሱ ግን ስላቃተው በፊቱን አዘጋጅቶት በነበረ ከእንጨት የተሠራ አርቲፊሻል የወንድ ብልት
ልጅቷን አበላሻት፡፡ ያንን የልጁን ነውረኛ ድርጊት የተረዳችው ሙሽራ በደረቅ ሌሊት ከጫጉላ ቤቱ አምልጣ ጠፋች፡፡ እውነተኛ ታሪክ
ነው - የፈጠራ አይደለም፡፡ አያድርስ በሉ፡፡ አንድ ማኅበረሰብ በብዙ አፈንጋጮች የተሞላ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡
ሊቀ
ሣጥናኤል አቢይ አህመድም ሀገራችንን ልክ እንደዚያ በራሱ የማይተማመን ሙሽራ እያደረጋት ነው፡፡ አቢይ ከልጁ የሚለየው የሰይጣናዊ
ተልእኮው ክብደት ነው፡፡ ማን ምን እንዳዞረብን ደግሞ አላውቅም፡፡
አሁን ሁሉም ሰው ስለዚህ የመርገምት ፍሬ ብዙ ነገር ያውቃል፡፡ ሀገር ለማፍረስ መምጣቱን እናውቃለን፤ ከኛ መራብና መጠማት ይልቅ ለወንበሩ እንደሚሳሳ እናውቃለን፡፡ ከኛ መፋጀት ይልቅ የርሱ ዝናና ክብር እንደሚበልጥበትና ለዚያም ተግቶ እንደሚሠራ እንገነዘባለን፡፡ እርሱ እያለ ኢትዮጵያ ለይቶላት ከዓለም ካርታ እንደምትፋቅ እናውቃለን፡፡ ችግሮቻችንን ብቻም ሳይሆን መፍትሔዎቻቸውንም እናውቃለን፡፡ ግን እንዴት እንተግብረው ነው ትልቁ ጥያቄ፡፡ አሁን ነው የዐይጦችን ጉባኤ ማስታወስ፡፡
አንድ ድመት ዐይጦችን እየበላ አስቸገረ፡፡ ዐይጦች ጉባኤ ጠሩና ስለመፍትሔው የጦፈ ውይይት ያዙ፡፡ ብዙ የመፍትሔ ሃሳቦች ላይም ተወያዩ፡፡ አንደኛው የመፍትሔ ሃሳብ ብቻ አሸነፈና የሁሉንም ቀልብና ድጋፍ አገኘ፡፡ እርሱም “በድመቱ አንገት ላይ ቃጭል እናድርግና ሲመጣ ሰምተን እንሽሽ” የሚለው ነው፡፡ ስብሰባው በጭብጨባ ሊበተን ሲል ግን አንድ ብልኅ ሽማግሌ ዐይጥ “ሃሳቡ ጥሩ ነው፡፡ ግን ቃጭሉን ወደ ድመቱ አንገት ወስዶ የሚያስረው ማን ነው?” የሚል ጥያቄ ደቀነባቸውና የጉባኤውን ልፋት ሁሉ መና አስቀረው፡፡
ይህ የአጋንንት ውላጅ፣ ይህ አስተዳደግ የበደለው ክፉና በሰዎች ስቃይ የሚደሰት ሀዘን አምላኪ፣ ይህ
አማራንና ኦሮሞን እያፋጀ ያለ የሣጥናኤል የበኩር ልጅ፣ ይህ በክፋት ሥራ መላ ሰውነቱ የተበከለ የሰንበት ጽንስ እንዴት ከአራት
ኪሎ ይውጣ ነው ጥያቄው፡፡ ይወጣል አይቀርም፡፡ እስኪወጣ ግን ጣጣው ብዙ ነው፡፡
…. ያቺ ጥቁር ክላሽ ግን አስቂኝ ናት፡፡ የመጣችው ከጦርነቱ በኋላ፡፡ ፋኖ የቆሰሉ አማሮችንና ኦሮሞዎችን እንዲሁም ወላይታዎችን የገደለውና ጥቁሪቷን ክላሽ ከቁስለኞች ማርኮ የታጠቀው ደግሞ ከጦርነቱ በፊት፡፡ ምን ዓይነት ውሸት ነው? ይሄ ሰውዬ የመዋሸት አማካሪም የለውም እንዴ? ደግሞስ ሰውን ከእስር ሲፈታ ደንግጦ፣ ሰውን ሲገድል ደንግጦ፣ ሰውን ሲያስር ደንግጦ፣ ሲሰድቡት ደንግጦ … እንዴት ይዘልቀዋል? ከኢዜማም ከቁዘማም ይህን ሰውዬ የከበባችሁ ሰዎች እባካችሁን አለቃችሁ እንዲህ ዓይነት ቅሌት ውስጥ እንዳይገባባችሁ የሚናገረው ውሸት ከቦታ ከጊዜና ከሁኔታ ጋር በመጠኑም ቢሆን እንዲመጣጠን እርዱት፡፡ ውሸት እኮ ልክና መጠን አለው፤ በትክክለኛው መንገድ ቢዋሽ ለሰሚም ግራ አይሆንም፡፡ መጥኔ ለሚስቶቹ ማለቴ ለሚስቱ፡፡ የቱቦ እንጂ የሰውነት ባሕርይ የሌለው የመጀመሪያው ፍጡር ይህ ሰውዬ ይመስለኛል፡፡ ወደፊት ሰዎች ስለውሸታም ሰው ሲናገሩ “እንደ እንደአቢይ ይቀረደዳል” ማለታቸው አይቀርም፡፡
ከርሱ አንደበት እንደተሰማው ከኢትዮጵያ መሪዎች እንደሱ የተሰደበ የለም፡፡ እኔም እላለሁ ከኢትዮጵያ
መሪዎች እንደሱ ኢትዮጵያን መቀመቅ የከተተ የለም፤ ወደፊትም አይኖርም፡፡ እናም ስድቡ መለማመጃ እንጂ ገና ብዙ ነገር ይጠብቀዋል፡፡
በእልህ ሥጋውን በልተው የማይረኩ እጅግ የተናደዱና የተከፉ ወጣቶች እንደሮማንያው ቻውቼስኮ ከሄሊኮፕተር አውርደው የመጨረሻውን ዋጋ ይከፍሉታል፡፡ ጠብቁ፤ እንጠብቅ፡፡
No comments:
Post a Comment