Sunday, June 26, 2022

ለኢትዮ 360ው ኤርሚያስ ለገሠ አፍን መቆጠብ ያስፈልጋል! አዎ የኦሮሞ ሕዝብ አማራን በመገደልና በማባረር ተባበሪም ተጠያቂም ነው! ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay) 6/25/2022

 

ለኢትዮ 360ው ኤርሚያስ ለገሠ

አፍን መቆጠብ ያስፈልጋል!

አዎ የኦሮሞ ሕዝብ አማራን በመገደልና በማባረር ተባበሪም ተጠያቂም ነው!

ጌታቸው ረዳ

(Ethiopian Semay)

6/25/2022

“አገሬው ነው እጃችን እየያዘ ያስገደለን ያስበላን” ይላሉ ተጠቂዎቹ። እነሆ ማስረጃው! ቪዲዮውን ለማየት እዚህ ድረገጽ ላይ የተለጠፈውን ወደ ቀኝ የቪዲዮ ማከማቻ ያለውን ፎዶራ ይመልከቱ ወይንም የተያያዘ መስኮት በመክፈት ቪዲዮውን ይመልከቱ፡

ኢትዮ 360ው በጎንደር ... ወቅቱን የዋጀ ጥሪ!" Friday June 24, 2022 በሚል ርዕስ የተላለፈው የውይይት ርዕስ ላይ ኤርሚያስ ለገሰ እንዲህ ይላል፦

 “በተለይ በተለይ አማራ የሆናችሁ ሰዎች ብትጠነቀቁ ይሻልል! ሌለው ላይ ጀኖሳይድ እያወጃችሁ ነው! Sure አማራው ሲጨፈጨፍ ኦሮሞውም አብሮ ነው የተጨፈጨፈው፤ “ፓርቲን እና ሕዝብን ማስተሳሰር ነው። በጣም በጣም አደገኛ ነው። አንዳንዶቹ እሰማቸዋለሁ ፡የኦሮሞ ሕዝብ ፣…ሊያደርግ ነው..ይሉኛል” የኦሮሞ ሕዝብ አልገደለም!!” “ኦሮሞ ሕዝብ ገደለ ብየ የምናገርበት ሞራልም የለኝም” “እንደዚያ ከሆነ ብ አ ዴ ን ሲገድል አማራ ገደለ ልል ነው? “Yes ኦ ሕ ዴ ድ ኦሮሞ ናቸው ግን ኦሮሞ ሕዝብ ይወክላሉ ማለት ስሕተት ነው።ማን ጨፈጨፈ ለሚለው እኮ እያየን ነው ‘አብይ አሕመድ እኮ ነው እየጨፈጨፈ ያለው” ኢትዮጵያ ውስጥ ሕዝብ ለሕዝብ ቅራኔ ተፈጥሮ አያውቅም አብይ የፈጠረው ቅራኔ ነው”……….. ወዘተ እያለ አማራና ኦሮሞ የተዛባ ግንኙነት ኖሮ አያውቅም አሁን ነው አብይ የተዛባ ቁርሾ እየፈጠረ ያለው…….ወዘተ እያለ እሳት የጎረሰ ቁጣው በማስጠንቀቂያ “ብትጠነቀቁ ይሻልል” በማለት ይዘባበታል። በመጨረሻም አማራ እና ኦሮሞ ጥቅም መሃከል መቸውም የጥቅም ፍላጎት ተቃርኖ የለም። የሚገርም ደግሞ “በትግራይና በአማራ ሕዝብ መካከል የጥቅም ፍላጎት ተቃርኖ የለም”

 እያለ ቁጣውን በድንፋታ ሲቀጥል ያኔ ጣቢያውን መከታተል አላስችል ብሎኝ ዘጋሁት።ትችቱን ካደመጥኩ በላ ንዴትየን መቆጣጠር ስላልቻልኩ  የተቀረውን ውይይታቸው ምን እንዳሉ አላዳመጥኩም ዘግቼ መልስ ለመስጠጥ አመራሁ።

ኤርሚያስ

 ወደ መጨረሻ የሰጠውን  “በአማራ እና ኦሮሞ ጥቅም መሃከል መቸውም የጥቅም ፍላጎት ተቃርኖ የለም። በትግራይና በአማራ ሕዝብ መካከል የጥቅም ፍላጎት ተቃርኖ የለም”… በሚለው ላይ ልጀምርና “ብትጠነቀቁ ይሻልል” ወደ እሚለው ዛቻውን ልመለስ ነው።

 

እንዴት ሲሆን በአማራ እና ኦሮሞ ጥቅም መሃከል መቸውም የጥቅም ፍላጎት ተቃርኖ ፤ በትግራይና በአማራ ሕዝብ መካከል የጥቅም ፍላጎት ተቃርኖ የለም ማለት ይቻላል? ኦሮሞው 3/4ኛ የማይገባውን መሬት ነጥቆ (ዕድሜ ለወያኔ) ወደ ራሱ ባለቤትነት አድርጎ የኔ ነው ብሎ አማራውን ከቦታው እያስወጣ እየገደለ ነው (31 አመት)። ኬኛ የሚለው ፖለቲከኛው ጀመረው ሕዝቡ አክብሮ ተቀበለው። ላቲን ነው ፊደልህ ተባለ አርሱም አዎ ብሎ አክብሮ ይኸው መላቅጡ የማይታወቅ ለማንበብም እርስ በርሳቸው የማይደማመጡ Latine Spelling እየተጠቀሙ የራሳቸው አድርገውታል። የቋንቋ ተቃርኖ፤ የመሬት ይዞታ ተቃርኖ አለ። ሕዝብ ካልደገፈው ኦሮሞማው እንዴት ዕድሜ ኖሮት ከወጭ አገር እስከ ውስጥ አገር ደረስ በጥላቻ የታጠበ ማሕበረሰብ ሊወጣ ቻለ? ለማ መገርሳ ምን ብሎ ነገረን? ሕዝቡ ኢትዮጵያዊ  አይመስልም፤ በጭካኔ በጥላቻ በትምክሕት የተበከለ ነው። ከታች ማስረጃ አቀርባለሁ፡

ወያኔ የወልቃይትን ለም መሬት በጠምንጃ ነጥቆ አማራውን ሕዝብ ጨፍጭፎ ለወገኖቹ ትግሬዎች በሚሊዮኖች ሲያስፍርበት፤ “ትግሬዎች” መሬታችን ነው ብለው ሰፍረው ይኸየው እየተዋጉ ነው፡ አይደለም እንዴ?  የመሬት ይዞታ ተቃርኖ ካልሆነ ጦርነቱ እና ጭፍጨፋው የምን ተቃርኖ ነው ሊባል ነው?

ለማ መገርሰ እንዲህ ይላል። ከኤርሚያስ ለገሰ በተሻለ ለማ መገርሳ እውነታወን ግልጽ ያደረገልን እውነታውን እነሆ፤

“ የኢትዮጵያ ሕዝብ እውነቱን ማወቅ ይገባዋል፡ፍርሃት አለኝ! እዚህ አገር ውስጥ፤ ባሕር ደር ፤ አባ ገዳዎችን ይዤ የሄድኩት ለሴራ ለተንኮል ኣይደለም፡ ተውት ሌለውን ነገር! ስጋት አለኝ፤ ያውም የዚህ ሕዝብ መሪ ሆኜ እኔ ባለሁበት ዘመን ደም እንዲፈስ አልፈልግም። ታሪኬን ማቆሸሽ አልፈልግም፤ ፍርሃት ነበረኝ ፤ስጋት ነበረኝ። እዚህ አገር ውስጥ እስካፍንጫው ድረስ ጥላቻ ነበረ! ጥግ የደረሰ ጥላቻ! እነኚህ መፈናቀል ፤ ‘ምን አምንላቸው’ (ግድያ ማለቱ ነው ለማ) የምንላቸው ዝምብለው እኮ የመጡ አይደሉም። ለዘመናት በጠላቻ ላይ የጥላቻ “ድሪቶ” ስንምግበው የኖርነው ትውልድ ነው ይኼ ትውልድ። ጠላትህ፤ የገደለህ፤የበዘበዘህ ጡትህን የቆረጠ፤ዘርህን ያጠፋ፤እየተባለ የተሰበከ በዚህ እየተሞላ የኖረ  ትውልድ ነው፤ ይህ ትውልድ ። ተራ ድሃ ሰው እንኳ ተራ ድሃ እንኳ በሰውነቱ ሰው መሆኑን እስኪክድ ድረስ ‘ገዳይ አስገዳይ” ሆኖ እንዲታይ፤ ጠላት ሆኖ እንዲታይ ነው ሲጫንበት የኖሮው። ፍርሃት ነበረኝ፡ አምና በነበርንበት ዳመና ብንቀጥል ኖሮ እዚህ አገር ላይ ሊከሰት የሚኖሮው ጥጋት ቀላል አልነበረም። አውቀዋለሁ፤ አይቸዋለሁ። በተለይ በአማራ እና ኦሮሞ መካከል አንዱ ያንዱ ጠላት ሆኖ እንዲተያይ የተተከለው ተክል ቀላል አይደለም። መርዙ  ቀላል አይደለም፡ አኔ አሱ አስፈርቶኛል። አሳስቦኛል! ይኼ ጉዳይ መልኩን ካልቀየርን፤ ኢንቫይሮንመንቱን ካልቀየርን፤ እንደዋዛ የሺዎችን ህይወት ይጠፋ ነበር፡ ደም ይፈስ ነበር፤ ሌላ ሩዋንዳ እዚህ ይከሰት ነበር! እኔ እሱ ነው ባሕርዳር ተሎ እንድሄድ የወሰደኝ ምንክያት።…” (የለማ መገርሳ ንግግር)

ሲል ከላይ የጠቀስኩትን የሕዝቡን የትውልዱን በጥላቻ መመረዝ በግልጽ የነገረንን አንባቢዎቼን ላስታውሳችሁ እፈልጋለሁ።

(የለማ “በሺዎች ይጠፋ ነበር” የሚለው “ነበር” የሚለው  ስሕተቱን ላርመውና ይኸየው ትናንት በሺዎች ኦሮሞ “አገር” ውስጥ ታርደዋል) አገራችን ወደ ሩዋንዳ የተለወጠቺው ኦሮሞ “አገር” ውስጥ ነው። አማራ ግን ለማ መገርሳ በሄደበት የባሕር ዳር ተማጽኖ አማራው ቃሉን አክብሮ አንድንም ኦሮሞ ሳይነካ በሰላም ኦሮሞዎች አማራ “ክልል” ውስጥ እየኖረ ነው። አማራው ኢትዮጵያም ሆነች “አማራ ክልል ኦሮሞዎችን እያረዱና እያባረሩ “ሩዋንዳ” ከመሆን አድነዋታል (አማራው እግዚሓር ይታደገውና እሱ እየታረደም ቢሆን ከጥላቻ የጸዳ ሰላሙን አያሳይቷቸዋል)። አማራ በነሱ ፈለግ ቢሄድ በእርግጠኛነት አገር ይፈርስ ነበር!

ስለዚህ ኦሮሞ ሕዝብ ስንል በኤርሚያስ የቁጥር ስሌት ስንት እንደሆነ ባይነግረንም፤ ለማ መገርሳ ግን አዲሱ ትውልድ በጥላቻ የታወረ በመርዝ ጥላቻ የሰከረ ፤አማራ የወላጆችህን ጡት ሲቆርጥ የነበረ ነው ብለን ሰብከነው ‘ተራ ድሃ አማራው እንኳ’ እንደ ‘ገዳይና አስገዳይ’ ሆኖ ባዲሱ የኦሮሞ ሕዝብ ትውልድ እንዲታይ ሆኗል፡ እያለ ለማ መገርሳ ስጋቱን የነገረን ዛሬ ኦሮሞዎች አማራን በማፈናቀልና በማረድ ኦሮሞ ምድር ልክ እንደ የ “ሁቱዎች” መንደር ሆና እንደ “ሩዋንዳ” ይኼው አማራዎች ወደ አገራችሁ ሂዱ እየተባሉ  በሺዎች እታረዱና እየተባረሩ ነው።

ኤርሚያስም ሆኑ ባልደረቦቹ የኦሮሞና ይትግሬ ፖለቲካና ፖሊሲ አያውቁትም ሆነው አይደለም። ይህ አጉል መለሳለስ የባሰውን ፖለቲካው እንዳይገለጥ እንዲደበቅ የሚረዳ ነው። ትግሬ ተጠቃሚ ነበር ስንል “አትበሉ ሲሉን ነበር” (ያንን በማስረጃ አቅርብን ሊያፈርሰው ማንም ሰው እስካሁን አላየሁም።) ፖለቲካቸው ኦሮሙማ ነው የትግሬውም ፋሺዝም ነው ብለናል።

ሁለቱ በናዚ እና ሙሶሊኒ ርዕዮት የሚመራ ከ40 አመት በላይ ያስቈጠረ ፖለቲካቸው ነው። የናዚ ፓርቲ፤ የፒፒ ኦነግ የወያነ፤የሻዕቢያ የአ ዴ ፓ በሕዝብ አልተወከሉም፤ ሆኖም በነዚህ ስብከት ሕዝቡ አሜን ብሎ ፖለቲካቸው ሰንደቃላማቸው አቅፎ ቋንቋቸው መፈክራቸው ትምህርታቸው፤ያነጋገር ዘይቤአቸው ተቀብሎ በዛው በቀየሱለት በመንገዳቸው ጎርፎ የተበከለ ማሕበረሰብ /ሕዝብ ሆኖ አሁን ያለበትን ሁኔታ ደርሷል።

ሙሶሎኒ በወቅቱ ሕዝቡን አስጨፍሯል፡ መጨረሻ ዘቅዝቀው ሰቀሉት; ሂትለር ጀርመንን አሳበደው (ጥቂት ተቃውሞ ቢሮውም)  መጨረሻ እራሱን ገደለ። ኢሳያስ አፈወርቂ ኤርትራ ሕዝብን አሳበደው አስጨፈረው፤ ጨርቁን አስጥሎ ከቦ አስደለቀው፤ እስክስታው በየተራራው ምግብ እየቀረበ አንድ ወር ሙሉ ነፃነት መጣ ብሎ  ሙዚቃው በማይክሮፎን እየተስተጋባ በየመንደሩና አስመራ ጎዳናዎች ፤ እንዲሁም አስመራ ዙርያ ኮረብታዎች እስኪደነቁሩ ድረስ እረፍት አጥተው የዛፍ ቅጠሎች እየረገፉ እየተዋዛወዙ “ለረፍት ሲማጸኑ” ሕዝቡ  አብዶ ሲጨፍር አይተናል፤ መጨረሻ የሆነውን አየን።

 ኦሮሞዎችም ትግሬዎችም በጥላቻ የታጠበ ማሕበረሰብ እንደሆነ የሚከተሉትን የፖለቲካው አይነት ማየት ነው (ሁለቱ ማሕበረሶበች ባንድ ዘር ላይ ያነጣጠረ ጥቃት የሚከተሉ ናቸው)። ከለማ መገርሳ ምስክርነት ሌላ የተያየዛው የተፈናቀሉ አማራዎች ምስክርነታቸው  በራሳቸው አንደበት ከኤርሚያስ እንዴት እንደሚለይ ማስረጃ ላቀርብ ነው ‘ወደ መጨረሻ’።

“በተለይ በተለይ አማራ የሆናችሁ ሰዎች ብትጠነቀቁ ይሻላል! የሚለው ኤርሚያስ የማደንቀውን ትንተናው ዛሬ ምን እንደደገጠመው አላወቅኩም። አሮሞው አማራ ክልል መብቱ ተጠብቆለት እየኖረ ነው፤ ይባስ ብሎ በገዛ ክልሉ ኦሮሞዎች የአጣየን እና የመሳሰሉትን ከተሞች እንዲቃጠሉ ያደረጉት እራሳቸው የክልሉ ኗሪዎች የሆኑት ኦሮሞዎች ናቸው (ቪዲየዎች ምስክር አለን)። ስለዚህ አማራው ኦሮሞ በጎንደርም ፤በጎጃምም፤ በወሎም በሸዋም በሰላም እየኖረ ነው። ይሉቁኑ “በተለይ በተለይ ኦሮሞዎች የሆናችሁ ሰዎች ብትጠነቀቁ ይሻልል!” ብለህ ማስጠንቀቂያህን ኦሮዎቹን ዘንድ ላክ።

“በተለይ በተለይ አማራ የሆናችሁ ሰዎች ብትጠነቀቁ ይሻልል! ሌለው ላይ ጀኖሳይድ እያወጃችሁ ነው! Sure አማራው ሲጨፈጨፍ ኦሮሞውም አብሮ ነው የተጨፈጨፈው” ብሏል አርሚያስ።

መቸ ነው ደግሞ አማራ በተጨፈጨፈ ቁጥር ኦሮሞ የተጨፈጨፈው፤ ቁጥሩ ስንት ነው፡ አብይ የነገረህን ኦሮሞ በብዛት ሞተ ያለውን ነው? ጀርመኖች እኮ አይሁድ ጀርመናዊ ነው አይገደል ብለው ስለተናገሩ በሂትለር ናዚ ተገድለዋል። ምን አዲስ ነገር አለ!? ቤትም መልካም ሰው አይታጣም፤ ተፈጥሮ ነው! አነጋጋሪ የሆነው የደጋፊውና የዝምታው ብዛት ሰንት ነው? ነው አነጋጋሪው ጥያቄ!

እስኪ በመጨረሻ በዚህ በለጠፍኩት ቪዲዮ “አገሬው ነው እጃችን እየያዘ ያስገደለን ያስበላን” ብለው የነገሩን የተባረሩት እና በቆጨራ አንገታቸው ተወግተው ደማቸው በወጊዎች “ሲጠጣ” ያዩ  የአማራ ተፈናቃዮች ምን እንደሚሉ አንባቢም ኤርሚያሰም ፍረዱ።

ይሕ  ቪዲዮ ብቻ ሳይሆን ከዚህ በተሻለ በግልጽ የሚናገሩ በርካታ ተፈናቃዮች የኦሮሞ ሕዝብ ከገዳየቹ ጋር አብሮ የጨፈጨፈን ሕዝቡ ነው የሚሉ ማስረጃዎች በተከታታይ አቀርባለሁ።

“አገሬው ነው እጃችን እየያዘ ያስገደለን ያስበላን” ይላሉ ተጠቂዎቹ። እነሆ ማስረጃው! ቪዲዮውን ለማየት እዚህ ድረገጽ ላይ የተለጠፈውን ወደ ቀኝ የቪዲዮ ማከማቻ ያለውን ፎዶራ ይመልከቱ ወይንም የተያያዘ መስኮት በመክፈት ቪዲዮውን ይመልከቱ፡

ሕዝብ እንደ ሕዝብ በጅምላ በፖለቲካ ተብክሎ ያብዳል፤ ወንጀል ውስጥ እጁን ያስገባል (ሩዋንዳ ውስጥ አይተናል፤ ጀርመን እና የሌሎች ሕዝቦች የጋራ ዕብደት አይተናል.. ሕዝብ ወረበላ መሪዎችን በመከተል ጥፋት ውስጥ ይገባል፤ ካጠፋም ይወቀሳል!!ሕዝብ አይወቀስም አያጠፋም የሚል ብሂል በኔ ዘንድ ቦታ የለውም!!)። እንደ ትግሬነቴ ለእውነት ስል ብዙ ዋጋ ከፍያለሁ፤ትናንትም ዛሬም ለወደፊትም እውነት ምርኩዜ ናት።

Amhara Genocide by the Oromo Testimony of victims interview Cannibalism involved in the attack አገሬው

https://youtu.be/Eh7h0YgsZp0

አመሰግናለሁ

ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)

No comments: