መላ ዘመኔን ላገለግለዎት ቃል እገባለሁ ታማኝ በየነ
ጌታቸው ረዳ
ክፍል 1
4/15/2021
ወደ ትንታኔ ከመግባቴ በፊት
ሁሌም እንደማደርገው ስለ አንድ ሰው ትችት ከመጻፌ በፊት ስለ እምተቸው ሰው በከፊልም ቢሆን የጀርባ ታሪኩ ማቅረብ አንባቢ የሰውየውን
ማንነት ሙሉውን ስዕል እንዲያዩት ስለሚረዳ ለዛሬ ስለ ታማኝ የማሳያው ስለ አለፉት ትግላችን በማሳየት ነው። ይህ ክፍል አንድ ነው””
ከላይ ያለው ስዕላዊ ማስታወቂያ
ቀልቤ ከሳቡት አንዱ ነው። ሰሞኑን የርዕዮት ሚድያ አዘጋጅ ቴድሮስ ፀጋየ ለታማኝ ጥያቄየን አስተላልፉልኝ በሚል አንድ ግሩም ሐተታ
አዘጋጅቶ አስደምጦን ነበር። በተመሳሳይ እኔም ታማኝ ወደ ኡትዮጵያ ሄዶ በነበረበት ሁለት ወይንም ሦስት አመት በፊት ትችት አቅርቤለት
ነበር። ዛሬ ተመሳሳይ ትችቴ በቴዲ ስሰማ መልዕክቱ እኔንም ያሳሰበኝ ጥያቄ ስለነበር በዚህ መሰረት እኔም ለሁተኛ ጊዜ ትችቴን ላክልበት።
የህ ትችት ስተችም ታማኝ እራሱ በተናገረው ቃል መሰረት አድርጌ ነው።
ከሁለት አመት በፊት ይሁን
ከሦስት አመት በፊት (አመተ ምሕረቱ ትዝ አይለኝም) ወደ ኢትዮጵያ ሄዶ በነበረበት ወቅት ባሕርዳር ከተማ ወጣቶች በተሰበሰቡበት
አዳራሽ በድምጽ የቀዳሁት ንግግሩ እንዲህ ሲል በተናገረው መሰረት አድርጌ ለትችቴ ሙሉ መብት እንደሰጠኝ በማሰብ ነው።
እንዲህ ይላል፦
“(ጠ/ሚኒስትሩን) ከሥር ያሉ
አላነቃንቅ ያሉዋቸው ይመስለኛል። (ውጤት) ሂደት ይመስለኛል፡ “ሚራክል” (ተአምር) አንጠብቅም። (ትግሉ) የምናቀጣጥለው ወደ ቤታችን
እየገባን እየወጣን አይደለም የምናቀጣጥለው። “ኢትዮጵያዊ” ድርጅት ውስጥ ገብቶ ተደራጅቶ መብት ለማስከበር መታገል ያስፈልጋል።
(መብት) “ቁጭ ብለን የሚሰጠን የለም” ። እንዲህ ያለ መንገራገጭ ሲፈጠር የራሳችን ሃይል ማጠናከር አለብን።
“መተቸት ችግር የለውም በቂ መልስ መስጠት ይቻላል” (ታማኝ በየነ)። ይላል ታማኝ።
ስለዚህ ተከታዮቹን የምጠይቀው
በዚህ በቃሉ ተመርኩዤ ትችት የማድረግ መብቴን እንደምታከብሩልኝ አምናለሁ። የዛሬ ጥያቄየ የሚከተለው ነው። “መላ ዘመኔን ላገለግለዎት
ቃል እገባለሁ!” ሲልታማኝ በየነ በፈረንጅ 2018 (ወሩን አላስታወስኩትም) እዚህ ዋሺንግተን ዲሲ አብይ አሕመድ ለመጀሚሪያ ትውውቁ
በተደረገው ሕዝባዊ ስብሰባ የገባለት ቃል ነው። እንሚታወቀው “የማገልግል ቃል ኪዳን ብቻ ሳይሆን” ታማኝ በአብይ ጫማ ሥር ወድቆ
አክብሮቱን ገልፆለታል። (ያኔ አገር ወዳድነትና መልካም መሪን የመፈለግ ያመነጨው የስሜት ግፊት ነው፤ክፋት አልነበረውም ብለን እንለፈው እና) ያኔ የገባለትን
ቃል ኪዳን ዛሬስ መከራው በከፋ መልኩ እየቀጠለ ባለበት ወቅትስ ታማኝ በየነ ወያኔን ሲቃወም እንደነበረ መራራ ተቃውሞ አብይንም
እየተቃወመው ነው ወይስ አይደለም? ለማት ለሁለተኛ ጊዜ ለተመሳሳይ ጥያቄ ብዕሬን እንሆ አንስቻለሁ።
“ታማኝ በየነ በብዙ ኢትዮጵያውያን ዘንድ በተሰጠው የተፈጥሮ ጸጋ መስህብ ምክንያት
መንግሥትን፤ ሥርዓትን ድርጅትን የመገልበጥ፤የማስለወጥ፤የማስጠላት እና የማዳከም ሲፈልግም የማጠናከርና የማደራጀት፤ የማስጨፈር፤
የማስለቀስና የማ’ሳቅ አቅም አለው። ይህ ስጦታ በተፈጥሮ እንጂ በትምሕርት አይገኝም። ዘፋኝ ነው፤ ተነጋሪ ነው፤አስተዋዋቂ ነው፤ሙዚቀኛ
ነው፤ እምባ አቅራሪ፤አዛኝና ርህሩህ ነው፤ተንኮለኛም ነው፤ ስሜት የሚጋልበው ከፍተኛ ሃገራዊ ፍቅር የሚታይበት ዜጋ ነው። ሃገራዊ
ፍቅሩ መጠን ስለሌለው፤ በዚህ ሁሉ በጎ ባሕሪው ጥቂት ለሆኑ በራዥ
ከላሽ እና አደገኛ ቡድኖችና ግለሰቦች በትግል ስም ሲደግፋቸውና እያቆለጳጰሰ ሲያሞጋግሳቸው ብሎም “የተሸለመውን የአምበሳ” ሽልማት
ሲሸልምና ሲያሞካሻቸው የታየበት ጊዜም ጥቂት አይደለም። ለዚህም በራዦችና ጸረ አማራ ሃይላት እውነተኛ አገራዊያን ተመስለው እንዲታዩ
ረድቷቸዋል። በዚህ ምክንያት ማን ከማን መለየት በሚደረግ የመነፅር ፍለጋ ጉዳት አድርሷል።
ባለፉት ወቅቶች ታማኝ መንካት፤መውቀስ
ፈጣሪን መንካት መስሎ የሚታያቸው ብዙ ሰዎች በኔ ላይና በጥቂት ተቺዎች ላይ የስድብ ናዳ አውርደውብናል። ታማኝ ሰው ነውና ሲሳሳት
“ተመለስ” ብሎ ማለት እንደ ታቦት የሚመለከቱት በሚሊዮን የሚቆጠሩ አጃቢዎቹ ዘንድ አያስወድድም። በታማኝ በየነ ትችት ካነሱት ብዕርተኞች
ምናለባትም ለበርካታ አመታት ያለማቋረጥ ግምባር ቀደሙ እኔ ሳልሆን አልቅርም። ታማኝን መተቸት የጀመርኩት “በራዡና ዋሾው” ጸረ
አማራው ብርሃኑ ነጋና የዛሬው የአብይ አሕመድ አገልጋይ ከሆነቺው የያኔው የቅንጅት ከፍተኛ አመራር ከነበረቺው ብርቱካን መዲቅሳ
ከሚመሩት አፍራሽ ቡድን ጋር ወግኖ “አድማቂ” ሆኖ በነበረበት ወቅት ነበር ትችቴን የጀመርኩት።
የዛሬው የአብይ አሕመድ ተከታይ
የሕግ መምህር እና ጠበቃ ፕሮፌሰር አል ማርያም ጋር ከታማኝ በየነ ጋር “የጠበቀ” ትውውቅ የጀመሩት ያኔ ነው ብየ እገምታለሁ።
ሁለቱም ያገናኛቸው ደግሞ “ ቅንጅት” ለሁለት ሲከፈል በሰረኛው አንዳርጋቸው ጽጌ አቀነባባሪነት ለሚመራው ቡድን ድጋፍ በመስጥት
በተቃራኒ ለቆመው ለኢትዮጵያ ብዙ መስዋዕት የከፈለ ዛሬ ስሙ የማይነሳ የኢትዮጵያ መምህራን ማሕበር ሊቀመንበር የነበረው ደ/ር ታየ
ወልደሰማያት ቡድን ቅራኔ ውስጥ በተነሳበት ወቅት ነው።
በወቅቱ በውጭ አገር የቅንጅት ገንዘብ ያዥ ነበሩ የተባሉ አንድ የሻለቃ
ማዕረግ የነበራቸው የሃይሉ ሻውል ደጋፊን “ገለልተኛ አጣሪዎች ነን ብለው እነ ታማኝና አልማርያም በሰውየው እጅ ነበር የተባለው
ገንዘብ አጣሪ ኮሚቴዎች ሆነው ታማኝና አልማርያም ሆሆ! እያሉ ከነጭራሹ ገለልተኛነታቸውን አቁመው የእነ ብርቱካን እና አንዳርጋቸው
ደጋፊ ሆነው አረፉት። ታማኝና አልማርያም “የብርቱካን እና የአንዳርጋቸው” ጡሩምባ ሆነው ተደራጅቶ አንድ ሆኖ የነበረው ዲያስፖራው
ለሁለት ከፈሉት። ከዚያ ወቅት ጀምሮ “ዲያስፖራው ማሕበር” ጭራሽ እስካሁን ድረስ ሊያጋግም አልቻለም።
ታማኝ ከዚያ ወቀት ጀምሮ ኢሳት
የተባለው “የባንዳ ፕሮፓጋንዳ ሥራም ሆነ የሚመሰገኑ አገራዊ ሥራ አብሮ እየቀላቀለ ሲያናፍስ የነበረ ኢሳት የተባለ የብርሃኑ ነጋ
ሚዲያ (ቴ/ቪዥን) እርሱና መሰሎቹ መሰረቱ። “ተባለ”።
ቆየት ብሎም ኢሳት የብርሃኑ
ነጋ የግንቦት 7 ንብረት ነው ብለው ሰዎች ታማኝን ሲጠይቁት፤ ለምን ጠየቃችሁ በሚል ንዴት “አይደለም ግን ቢሆንስ!!ቢሆንስ!!!!
ኢሳት ሕዝብ የሚቆጧጠረው ሚዲያ ነው። ማንም የፈለገው ስም ሊሰጠው ይችላል፤ዛሬ ባለቤቱ ሕዝብ ነው።” በማለት ንዴቱን መቆጣጠር አቅቶት በጠየቁት ‘ላይ ምን ታመጡ’ ፤’ ምን አጋበችሁ’
በሚል ትዕቢት የቁጣ መልስ አወረደባቸው።
ታሪኩ ረዢም ስለሆነ አጠር
አጠር አድርጌ ታማኝ ላስተዋውቃችሁ። ከላይ በጎ ተግባሩ የገለጽኩት እንዳለ ሆኖ ፤ ቀስ እያለ ታማኝ የተዋጣለት አደራጅ እና ፖለቲከኛ ሆነ። ሚሊዮን ተከታዮች አፈራ።
የግንቦት 7 ዋናው ሰው ሆነ፤ የአንዳርጋቸው አድናቂ እና ሸላሚ ሆኖ አረፈው። አማራዎች እምነት ሊጥሉበት አልቻሉም። ቀስ ብሎም
“የኢሕአዴግ ሰይፍ ከሚበላኝ የእስላም ሰይፍ ይብላኝ” በማለት ብዙዎቻችን ያስደነገጠ ንግግር አደረገ። በወቅቱ ዋሃቢዎች ከፍተኛ
ስልት እና እንቅስቃሴ ሲያደርጉ በነበሩበት ወቅት ነው።
ለምን እንደዚያ አልክ ተብሎ
በፓልቶክ ሲጠየቅ፡ “የኢትዮጵያ ሙሰሊም አክራሪ ነው እያሉ የሚከሱት አላግባብ ነው” ብሎ መልስ ሰጠ።
ሲያብራራም ‘እንዲህ ይላል።
ካ1400 አመት በላይ ከክርስትያኑ
አብሮ የኖረ ነው። የገዛ አገሩን አያጠፋም። የኢትዮጵያ ሙስሊም አክራሪ ነው እያሉ የሚከሱት አለአግባብ ነው። 1400 አመት በላይ
የኖረ ሕዝብ ትናንት የተፈጠረው ህወሓት አክራሪ ነው ሲል ልክ አደለም። የኢትዮጵያ ሙሰሊም አክርሮ ጎራዴ የሚይዝ ከሆነ እኔ ከወያኔ
ጥይት ይልቅ የሙስሊሙ ጎራዴ እመርጣለሁ። ብያለሁ። እደግመዋለሁ “የኢትዮጵያ ሙሰሊም አክርሮ ጎራዴ የሚይዝ ከሆነ እኔ ከወያኔ ጥይት
ይልቅ የሙስሊሙ ጎራዴ እመርጣለሁ።” ይህንን አምንበታለሁ “የኢትዮጵ
ሙስሊም ሲከራከር ፤ሲደራደር አላየሁም። ኢትዮጵያዊ ሙስሊም ኢትዮጵያዊ መስሎ መኖር ነው የማውቀው “የመገንጠል ጥያቄ
አቅርቦ አያውቅም”። በማለት መልስ ሰጠ። ስሕተት ሀኜ ከተገኘሁ ተምበርክክ ይቅርታ እጠይቃለሁ የሚያርመኝ ሰው ካለ እና እውነት
ሆኖ ከተገኘ። ግን አስካሁንዋ ደቂቃ ድረሰ ትከክል ነኝ እላለሁ።” በማለት መስመሩን መከላከል ጀመረ።
እዛው ጃዋር መሓመድ በተገኘበትና
እና እስላሞች ስብሰባ በተደረገበት አዳራሽ ትክክለኛው ንግግሩን እዚህ ባጭሩ እንዲህ ይላል፡
“አላህ ወ አክበር! አላህ
ወ አከበር! ብየ ነው ንግግሬን የምጀረው!! በማለት ከእኛው ከክርስትያኖች ጋር እልክ የተገባ በሚያስመስልበት ከፍተኛ ጩኸት እየጮኸ
ተሰብሳቢው እስላም ማሕበርተኛውን በደስታ አስጮኸው።
“አሰላም አሊኩም ወ ሩሑመትላሂ
ወበረካቶ!! አላህ ወ አክበር! አላህ ወ አክበር! እኛ ትምህርት ቤት እያለን ‘የኢትዮጵያ ሙሰሊም የክርስትያን በዓል ሲከበር የናንተ
አይከበርላችሁም ነበር። ሙስሊሞች እንደ እኛ አኩል አልነበሩም። ይህ
በደል ሲደርስባችሁም አገር እንገንጥል የሚል ሙስሊም አይቼ ሰምቼ አላውቅም።
ሙስሊሙ አክራሪ ነው ሊያጠፉን ነው የሚል ከየአቅጣጨው ሰምቼዋለሁ፡ ““የኢትዮጵያ ሙሰሊም አክርሮ ጎራዴ የሚይዝ ከሆነ
እኔ ከወያኔ ጥይት ይልቅ የሙስሊሙ ጎራዴ እመርጣለሁ እኔ!!” “ተክቢር! አላህ ወ አክበር! ተክቢር አላህ ወ አክበር! እያለ በመጮህ
አዳራሹ “አላህ ወ አክበር!! እያለ በከፍተኛ አድናቆትና ድምጽ በመፈክሩን በመድገም አስተጋባ።
ይህ ንግግር ችግሩ የሚከተለው
ነው።
አላህ ወ አክበር ስላለው አንድ
ክርስትያን ወይንም ቄስ ወይንም ጳጳስ ወይንም ድያቆን (እስላሞቹ እንደሚጠሩን “አንድ ካፊር”) እንዲያ እስላሞች በተሰበሰቡበት
አዳራሽ ንግግር ሲጀምር እንዲያ እንዲል ይፈቀድለት ይሆን የሚለውን
ትችቴን ያኔ የተቃወምኩት በፈረንጅ
ዘመን አቆጣጠር በ2013 ማለትም ከ8 አመት በፊት “በፖለቲካና በሃይማኖት የማሻኮር ባሕሪ”
https://ethiopiansemay.blogspot.com/2013/05/blog-post.html
በሚል የታማኝ ንግግርን አስመልከቼ የጻፍኩትን አንዳንዶቹን ነጥቦች ላስታውሳችሁ።
“አላህ ወ አክበር እያለ ስላስተጋባ
አባባሉ መልስ ሰጥቼዋለሁ። መልሴም አንድ ክርስትያን ወይንም ቄስ
ወይንም ጳጳስ ወይንም ድያቆን (እስላሞቹ እንደሚጠሩን “አንድ ካፊር”) እንዲያ እስላሞች በተሰበሰቡበት አዳራሽ ‘አላህ ወ አክበር’
በማለት ንግግር ማድረግ አይፈቀድለትም።
ለምሳሌ የግብፅ ኦርቶዶክስ
አረቦች እና የግብፅ እስላሞች አላህ በሚለው ቃል ሁለቱም ላይ በቃላቱ አጠቃቀም ላይ ልዩነት አለ። አንድ ጻሐፊ እንዲህ ይላሉ፦
ለምሳሌ 95% ግብጻዊያን “ወላሂ” "Walahy" ሲሉ ኮፕቲክ ክርስትያኖቹ ግን "Tesdane"تصدقني በማለት በአላህ ላለመማል ይምላሉ። (as replacement,
just to avoid using the name Allah.)
ባጭሩ እስላሞቹ እኛ የምናመልከውን
ፈጣሪ እንደ አምላካቸው/ ፈጣሪያቸው አይቀበሉትም፡ እኛም የምናመልከው ፈጣሪ፤ እስላሞቹ ከሚያመልኩት ፈጣሪም ሆነ መልእክቶች፤ትርጉሞች፤ሕግጋቶች፤አምነቶችና
ሰበካዎች፤ ስለማይገናኙ አይቀበሉትም። ለዚህም ነው በእስልምና እና በክረስትያን መካካል ከተፈጠረ ጀምሮ እስካሁን ድረስ ጦርነቱ
እየጦፈ ያለው።ስለዚህም ነው የታማኝ “አሰላም አሊኩም ወበረካቶ! (ለምን
እንደሚጠቀሙበት ባይገባኝም ፤ ይህኛው ለዓረቦች እንጂ የራሳቸው ቋንቋ ላላቸው ለአበሾች የሚሰነዘር የሰላምታ ልውውጥ
አይደለም። ምክንያቱም እያንዳንዱ እስላም በየቤቱ ሲገባ ከሚስቶቻቸውና
ከወላጆች ጋር የሚነጋገሩባቸው ቋንቋዎች “ዓረብኛ” እንዳልሆነ ስለምናውቅ።
እስላሞቹ “ባላጡ ቋንቋ፡ ለምን
አዘውትረው እንደሚጠቀሙበት ባይገባኝም) “አላሁ አክበር! ተክቢር! ተክቢር! ተክቢር!” የሚለው የታማኝ አሻኳሪ ሃይመኖታዊ አዘል
ፖለቲካዊ ‘ምዝመዛ’፤ ካንድ “ኢትዮጵያዊ ኦርቶዶክስ ክርስትያን አማኝ”
ሃይማኖቱ ሳይለውጥ በአደባባይ “አላሁ አክበር/ተክቢር፤ተክቢር! ተክቢር!” የሚለው እስላማዊ የሃይማኖት መፈክር ሊደመጥ ከክርስትያናዊ
ደምብ የጣሰ ስነ ምግባር ነው። ብየ መልስ ሰጥቼዋለሁ። መልስ የሰጠኝ ሰው የለም ስለዚህ ትከክለኛ ነኝ ሲል ተደምጧል።
ለማጠቃለል ያህል፤ ከክርስትያን
እምነት ውጭ የቁርዓንን ሕግጋት የሚከተሉ እስላሞች ‘የመጽሐፍ ቅዱስ’ ሕግጋት ከሚከተሉ ከክርስትና የተከታዮች እምነት አንድ ስላላሆነ
ነው በሃይሞበት የምንለያየው። ለምሳሌ ቁርዓን/እስላሞች እኛን “ኩፋር” ከሚሉን እስላሞች ያልሆነን ሕብረተሰብ ወደ እስልምና ለማጥመቅ
ቢያንስ እስልምናን ለማስፋፋት 109 አንቀጸች “ሃይልን” የመጠቀም ትምህርት እንደሚያስተምር የሃይማኖት ተከራካሪዎች ይጠቁማሉ።
ታማኝ ይህንን ካላወቀ እንግዲህ
መልሱን ለማወቅ ግንቦት 7 እና እስላማዊ መሃበር ወክለው በየአገሩ (እሰተቶቹ) አብሮውት ሲዞሩ ከበሩት ቀሳውስት መካካል “አባ
እርስዎ “አላህ ወ አክበር” ብለው አዳራሽ ውስጥ ንግግር መክፈት ሃይማኖትዎ ይፈቅድለዎታል ወይ? ብሎ ቢጠይቅ እኔ ስሕተት ከሆንኩኝ
ከእነሱ መልስ ልያገኝ በቻለ ነበር። አንድ እስላምም “በስመ አብ ወ ወልድ ወ መንፈስ ቅዱስ አሓዱ አምላክ” ማለት ይችላሉ ወይ
ብሎ ቀዲው እና ሼኹ ወይንም ወዳጁን ‘አቡበከርን’ ወይንም “አሕመዲን ጀበልን” ወይንም “ሳዲቅ መሓመድን” ቢጠይቃቸው መልሱ ያገኘዋል።
በሃይማኖት እያሻኮሩ ፖለቲካ ፣መስራት አይፈቀድም ብየ የተቸሁትም ለዚህ ነው። ወደ ዋናው ርዕሴ ከመግባቴ በፊት የታማኝ የጀርባ
ታሪክ ላላወቃችሁ ወጣቶች በትግሉ ወቅት ያሳለፍነው ስዕል እያስተዋወቅኩዋችሁ ነው። ስለዚህ ታገሱኝ።
እስለሞች በሁለተኛ ዜጋ ይታዩ
ነበር ብሎ ታማኝ በምስክርንት ሲመጣ ለምሳሌ አንዲት እርጉዝ ‘እስላም
ስለሆንሽ በሆስፒታል ወሊድ ማካሄድ ላንቺ አይፈቀድም፤ አንቺም ልጅሺም ክትባት አትሰጡም፤ ትምህርት ቤት/በየደረጃው እስከ ዩኒቨርሲቲ
ድረስ ልጅሺን አስመዝግበሽ ማስተማር አትችይም/አትችልም….እስላም ስለሆንከ/ሽ ንግድ መነገድ አትችልም/ይም ፤በት መስራት አትችልም፤ማከራየት
አትችልም፤ ሳውዲ ሜካ ድረስ ሄደህ ጸሎት ለማድረስ ወይንም ‘ሃጅ’ ለማካሄድ አይፈቀድልህም…” የተባለበት ጊዜ አለ?
ተብሎ ከሆነስ እስላሞች ሲያስተዳድሩ
የደረሰው በደል ጋር ለምንድ ነው አነጻጽረው አቻችለው ታሪኩን የማይዘግቡትና የማይሰብኩት? ወንድሞቻችን ግን ተገቢ መብቶችን ከመጠየቅ
ይልቅ ጭራሽኑ “ክርስትያን ኢትዮጵያ ሲያስተዳድሩ እኛን በሁለተኛ ዜጋ አይተውናል” እያሉ እነ አቡበከር “ኦሪት ዘፍጥረት እየጠቀሱ
የክርስትያኖቹ አምላክ ጨፍጫፊ ነበር እያሉ ሲሰብኩ ነበር። ያውም ብዙ እስላም ወጣቶች “የአፄ ዮሐንስ ሀውልት ይፍረስ” እያሉ መፈክር
ያስተጋባሉ/ይከሳሉ። ይህ ምን ማለት ነው? ምንጩ ማን ነው? አሳባቂዎቻችውም ይህንኑ ያስተጋቡላቸዋል። አቡበከር የተባለው ለዚህ
ስብከት አንደኛ ሰባኪ ነበር። ለምን? በወቅቱ ጽፌበታለሁ።
ለምሳሌ እስላሞቹ አክሱም ውስጥ
እንደ የጭቆና ማስረጃ አድርገው የሚከራከሩበት (እኔም ደግፌው የነበረው
የእስላሞች መስጊድ አክሱም ውስጥ የመስራት መብት) የመስጊድ መስራት ጉዳይ ነው። ይህ ደግሞ ሕዝቡ እንጂ መንግሥት ውሳኔ ማሳለፍ
መብት የለውም (ይህንን ሳናውቀው ስንከራከር ነበር)። ይህ ከሆነ መንግሥት በሃይማኖት ጣልቃ መግባት ይሆናል። ስለዚህም ነው በዛሬው
ዘመን እስላሞቹ በሃይመኖታችን ጣልቃ አትግቡ እያሉ ወያኔዎችንም ሆኑ ሌሎችን የሚቃወሙት። አክሱሞቹ ክርስትያኖችም እንደዚያው
ስለዚህ አክሱም ውስጥ በባህል
የቆየ አንጂ በመንግሥት ወይንም በመጽሐፍ ቅዱስ በሕግ ተበይኖ የተደነገገ ሕግ የለም። ለእውነት አንነጋገር ከተባለ አክሱም ውስጥ እስላሙ ሕብረተሰብ ብቻ አይደለም
የሚጸልይበት ህንጻ ሰርቶ መጸለይ መብት የተነፈገው። የአክሱም ክርስትያን እናቶቻችንም እኩል እንደ እስላሞቹ መብታቸው ተነፍጓል።
እኔ ከእናቴ ጋር ጥዋት ወደ እንዳ ጽላት /ቤተክርስትያን ስሄድ ‘እሷ’ በተንጣለለው ግቢ ውስጥ ከደጅ እካቡ ላይ ባለው ሜዳ በበቀሉት
ዛፎችና ከመቃብር ድንጋዮቹ መካከል ጥላ ስር ሆና ለመጸለይ ወደ ኋላ ስትቀር ከማህጸንዋ የተገኘሁ እኔ ‘ወንድ’ ነኝ እና ወደ ቤተመቅደሱ
ውስጥ ገብቼ የቅዳሴው ስርዓት ተከታትየ፤አስቀድሼ፤ ቅብአ ሜሮኑን ተቀብቼ ስርዓቱ ተከናውኖ ሲያበቃ ወደ ደጅ ወጥቼ ፤ በግማበሬ
የተቀባውን ቅብ ሜሮንኑን በእጄ ወደ ግምባሯ ቀብቼ ፤እሷን አጅቤ ወደ ቤታችን አንሄዳለን። አንግዲህ የወለደቺኝ እናቴ “የቤተከርስትያኑን
ውስጣዊ ሰርዓት” ለማየት መብት ሳይኖራት እኔ በወንድነቴ ከማህጸኗ የወጣሁ ጮርቃ ህጻን ልጇ ግን ገብቼ ለማየት እና ለማስቀደስ
መብት አለኝ። ይህ የቆየ ‘ሰንሲቲቭ’/ወጣሪ/ ባህላዊ የመብት ሁኔታ ወንድሞቻችን እሳለሞች እና አሳባቂዎቻቸው ይህንን እያወቁ
“በእስላሙ” ብቻ የተደረገው የመብት ጥሰት እየመዘዙ ክርስትያኑ እና ስርዓቱ የእስላሙ መብት ተጋፊ እያደረጉ ዘመቻ ማካሄድ በሰማይም
በምደርም ቅንንት የተከተለ ክስ አይደለም። ነገሮችን ፤ታሪኮችና የቆዩ ባህሎች “በእርጋታና በጥንቃቄ” መመርመር ለአብሮነት አስፈላጊ
ነው። እውነቱን እና ውሸቱን በመረጃ መደገፍ አለብን። ብየ እነ ታማኝን እና መሰሎች ተከራክሬ አለሁ
ኦሮሞ መሬት እስላማዊ ስለነበር
ክርስትያኑ ሚኒሊክ መጥቶ ክርስትየን አደረገው እያሉ የሚዋሹ አሉ። እነ ታማኝ ይቀበሉ እና ያንን ለሃያ አንድ ዓመት ሲነዛ የነበረ
ውሸት አቁሙ የሚል ሰው በብዛት ስላልተገኘ ያንን ውንጀላ ለማወፈር እነ ታማኝ በእየ አዳራሹ “ምኒሊክ ግፍ እየፈጸሙ” ወደ ደቡብ
ሲስፋፉ” ከዛ በፊት የኢትዮጵያ ነገሥታት ዛሬ ኦሮሞዎች እየኖሩበት ያሉ ቦታዎች አላስተዳደሩትም፤ የሚለንን ውሸት ሲደመጥ ተጨብጭቦለታል።
የ እስላም ወንድሞቻችን ሁለተኛ ዜጎች ነበራችሁ የነ ታማኝ ስብከት ምንም በማያውቁ በእስላም ወጣቶች ብዙ ጉዳት አደርሷል። ስለዚህ
“አንደኛ እኛ ትምህርት ቤት እያለን ‘የኢትዮጵያ ሙሰሊም የክርስትያን በዓል ሲከበር የናንተ አይከበርላችሁም ነበር። ስለሚለው ውዥምብር
የእስላም ትምህርት ቤቶችም የክርስትያን በዓል ሲሆን አይዘጉም ነበር። “ሙስሊሞች” በኔ አባባል “እስላሞች” እንደ እኛ አኩል ዜጎች
ነበሩ። ሴት ክርስትያኖችም እኩል እንደ ወንዱ መብታቸው አይከበረላቸውም ነበር የሚለው አብሮ ማየት ጠቃሚ ነው። ስለዚህ እየለየህ
መሰንጠቅ ጠቃሚ አይደለም።
“እስላሞች፤ኦሮሞዎች፤ሶማሌዎች…”
በአማራው፤በነፍጠኛው፤በክረስትያኑ ተጨቁነው ነበር፤ ኢትዮጵያ የነሱ አገር አልነበረቺም፤ ያለፉት ኑሮ “መቻል አንጂ መቻቻል አልነበረም”
፤ እያሉ ስድቦቻቸውና ዘለፋዎቻቸው ሚዛን ባልጠበቀ ክስ ያስተጋቡላቸው በርካታ “ማሞ ቂሎቻቸውን” አድምጠናል። እስላሞችም ወቅት ሲፈቅድላቸው ግፍ ሰርተዋል።
ለምሳሌ የግዕዙን መረጃ ሰነድ
ከጠሉት ወይንም ታማኝ ካለወቀው እስላመዊው መንግሥት በኢትዮጵያ ክርስትያናዊ ሕብረተሰብ የተደረጉት ጸረ ክርስትያን ግፎች በ1535
ዓ.ም ገደማ (በፈረንጆች አቆጣጠር) ከጫፍ እስከ ጫፍ ከሐረር ጀምሮ
እስከ ሰራዬ (ኤርትራ-) ጐጃምና ጎንደር እስላም ወንድሞቻችን እስላሞች በክረስትያኖች ያደረሱት አሰቃቂ ሽብር በክርስተያን ጸሃፊዎች
ሳይሆን ከግራኝ ጋር አብሮ በጦርነቱ የዘመተውና ከግራኝ አህመድ ጋር ያልተለየው Sihab ad Din Ahmadin Abd
al-Qader bin Salem bin Utman ወይንም በሌላ የተጸውኦ ስሙ “ዓረብ ፋቒሕ” ( Arab Faqih) የተባለው የመናዊው
ዓረብ ጋዜጠኛ “ፉቱሕ አል ሐበሻ” ( Futuh Al- Habasa
– the Conquest of Abyssinia {16th
Century} በተባለው በዓረብኛ ቋንቋ በጻፈው መጽሐፉ ላይ እስላመዊው መንግሥት በኢትዮጵያ ክርስትያናዊ ሕብረተሰብ የተደረጉት
ጸረ ክርስትያን ግፎች በ1535 ዓ.ም ገደማ (በፈረንጆች አቆጣጠር)
ከጫፍ እስከ ጫፍ ከሐረር ጀምሮ እስከ ሰራዬ (ኤርትራ-) ጐጃምና ጎንደር ድረስ የዘለቀ በክርስትያኑ ሕብረተሰብ ላይ
የደረሰው ግፍ በግልጽ ለታሪክ አስፍሮ ትቶልናል።ለምንድነው ክረስትያኑ መንግሥት ብቻ ግፈኛ፤ጨቋኝ፤ገዳይ እና አድላዊ እየተደረገ
የሚዘመትበት? ይህ በክርስትያን መንግሥት እና በክርስትያኑ ሕብረተሰብ ላይ ሚዛኑን ያልጠበቀ የተቀነባበረ የክስ ዘመቻ ስንት ጊዜ
በቸልተኝነት ልናልፈው ትፈልጉናላችሁ? አንዲህ ያለ ክስ አላስፈላጊ ክርክር ውስጥ የሚያስገባ ብቻ ሳይሆን በክረስትያኑ ብቻ ያነጠጣረ
ክስ በመሆኑ፤ ጊዚያዊ ፖለቲካን ለመጠቀሚያ እንዲያመች የሚደረግ ምዝመዛ አደገኛ ነው፤ አንቃወመዋለን። በክርስትያኑ መንግስት ላይ
ወቀሳ እና ተጠያቂነትን መደርደርና የመረባረቡ ፖቲካ ልጓም ይበጀለት! ለዚህ ለዚህ ወያኔ ይበቃናል፤ ወያኔ ያለ ምንም ደገብ ያርከፈከፈብን
አሳባቂ ነዳጅ አንዳይበቃ ሌላ ተጨማሪ አሳባቂ ነዳጅ ከመረብረብ የተቃዋሚ መሪዎችና የሰብአዊ መብት ጠበቃዎች መቆጠብ ይኖርባቸዋል።
ብየ ተችት አቅርቤለት ነበር። ስለዚህ “የኢትዮጵያ ሙስሊም ‘አክርሮ’
ጐራዴ ይዞ ቢመጣ ከወያኔ ጥይት ይልቅ የሙሲሉን ጐራዴ እመርጣለሁ እኔ!” የሚለን ታማኝ ሙሰሊሙ አክርሮ ሲመጣ በዘመነ ግራኝ ምን
እንደተፈጸመ ቢያውቀው እንዲህ ባላለ ነበር።
“In the land of
infidels, nothing was to be seen but cut-off heads, spirits in the throats of
death, and palms of hands flying in the air. The Muslims cried out with a
mighty cry: ‘there is no God but Allah,’ and ‘God is the Greatest’ (( Futuh Al- Habasa – the Conquest of Abyssinia (16th Century) ገጽ (98)
ትርጉም ፡
(በከሃዲዎች ምድር ውስጥ የተቆረጡ
ጭንቅላቶች ፣ በሞት ጉሮሮ ውስጥ ያሉ መናፍስት እና በአየር ላይ ከሚበሩ የተቆረጡ የእጆች መዳፎች (እጆች) በስተቀር ምንም የሚታይ
ነገር አልነበረም። ሙስሊሞቹ “ከአላህ በቀር ሌላ አምላክ የለም”
እና “እግዚአብሔር ታላቁ ነው” የሚል ገጽ በታላቅ ጩኸት እየጮኹ ክርስትያኖቹን ሲቆርጡ ነበር፡፡” ( Sihab ad Din
Ahmadin Abd al-Qader bin Salem bin Utman ወይንም በሌላ የተጸውኦ ስሙ “ዓረብ ፋቒሕ” ( Arab
Faqih) የተባለው የመናዊው ዓረብ ጋዜጠኛ “ፉቱሕ አል ሐበሻ”
( Futuh Al- Habasa – the Conquest of
Abyssinia (16th Century) በተባለው በዓረብኛ ቋንቋ በጻፈው መጽሐፉ ገጽ (98)
ስል ተከራክሬ ነበር።
በማያያዝም ታማኝ በየነ፡
“ይህ በደል ሲደርስባችሁም አገር እንገንጥል የሚል ሙስሊም አይቼ ሰምቼ አላውቅም።
” ሚለውን እንመልከት፦
አገር ለማፍረስ የተነሱት ኦጋዴን
ነፃ አውጪዎች እስላሞች አልነበሩም እንዴ? እስላማዊ ኦሮሞ ነፃ አውጪ ግምባር እነ ዋቆ ጉቱ፤ እነ ጀኔራል ጃራ እነ ጃዋር መሓመድ ምን ሲያደራጁ ነበር
ብሎ ታማኝ ይነግረናል? ያውም እኮ እዛው አዳራሽ ታማኝ በተረናገረበት መድረክ “ጃዋር” “እኔ ባደግኩበት አካባቢ አንድ ክርሰትያን
አንገቱን ቀና ካደረገ አንገቱን በሜንጫ ነው የምንለው” ሲል አክራሪ እስላምነቱን እና ተከታዮቹ እንዴት አጋግሎ እንዳስጨበጨባቸው
በአሁኑ በጆሮው እየሰማ እና እያ ነው ታማኝ “ይህ በደል ሲደርስባችሁም አገር እንገንጥል የሚል ሙስሊም አይቼ ሰምቼ አላውቅም”
ብሎ ፖለቲካ ለመስራት ወይንም ደንቆሮነት ያስከተለው ዲስኩር መሆኑን ታማኝ ዛሬም አልተቀበለውም።
ክፍል 2 ይቀጥላል……………………
ጌታቸው ረዳ
No comments:
Post a Comment