Friday, April 9, 2021

የብርሃኑ ነጋ ሱቆች በግንቦት 7 እና በኢዜማ የሚሸጡ ሁለት ሸቐጦች ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ) ክፍል 1 3/9/21

 

የብርሃኑ ነጋ ሱቆች በግንቦት 7 እና በኢዜማ የሚሸጡ ሁለት ሸቐጦች

ጌታቸው ረዳ

 (ኢትዮ ሰማይ)

ክፍል 1

3/9/21



ነጋዴው ብርሃኑ ነጋ የመሰረታቸው ሁለት የፖለቲካ ሱቆች “ውሸት” እና “አማራ ጠልነት” የሚታወቁበት የንግድ መላያ (ትሬድ ማርክ) ሆነው ለበርካታ አመታት ያለማቋረጥ ሲሸጡ ነበር።

ታስታውሱ እንደሆነ ለውጥ ተብሎ የተከሰተው “የባለተረኞች ለውጥ” አስመልክቶ ብርሃኑ ከሮይተር ጋር ያደረገው ቃለ መጠይቅ ትችት ጽፌ ነበር። ብርሃኑ ስለ ለውጡ ለሮየተር ምን ብሎ ዋሸ? በፈረንጅ ዘመን ኖቨምበር (ሕዳር ወር) 2018 በለመደበት ዋሾ ምላሱ ከሮይተርስ የዜና ማእከል ያደረገው ቃለ መጠይቅ እንዲህ በማለት የዋሸውን በድጋሚ ላስታውሳቸሁ።:

“አዲሱ ለውጥ የመጣው የኤርትራ መንግሥት ባደረገልን ወታደራዊ፤ ዲፕሎማሲያዊ እና የገንዘብ ዕርዳታ ባደረገልን ድጋፍ ኢትዮጵያ ውስጥ አዲስ ምዕራፍ ለማምጣት ችለናል።

የኤርትራ መንግሥት የምንዋጋበት ቦታ እና ማሰልጠኛ ስፍራ ባይፈሰጠን ኖሮ አሁን ዛሬ ኢትዮጵያ ውስጥ የታየው ድል ባልመጣ ነበር።

እኔ ዕድሜ ለኤርትራ መንግሥት ባደረገልኝ ድጋፍ በርከት ያሉ የድል ውጤቶችን አስመዝግቤአለሁ።

 

የምንቀሳቀስበት የዲፕሎማቲክ ፓስፖርቴ በኤርትራ መንግስቲ የተሰጠኝ ነው። ዕድሜ ለእርሱ እንደ ልቤ ልንቀሳቀስ ችያለሁ።ኢትዮጵያውያን ባሉበት ሁሉ ሄጄ እንድቀሰቅስ ለትግሉ እንዳነሳሳ አስችሎኛል።” (ብርሃኑ ነጋ)

ሲል የሚገርም ውሸቱ ለዓለም አቀፍ የሮይተርስ ዜና ማሰራጫ ዋሽቷል። ፓስፖርቱ “ኤርትራዊ” ይል እንደሆነ ማን ያውቃል። የፓስፖርቱ ቁጥሩ ቅጂ ግን ከአራት አመት በፊት አግኝቼ ኮፒው አቅርቤው ነበር፡

መለስ ዜናዊ “ሶማሌ” የሚለው ዜግነት ሳይለውጥ 20 ምናምን አመት ገዛን አሁን ድግሞ ብርሃኑ ነጋ “ኤርትራዊ” የሚል ዜግነት መኖሩን አለመኖሩን የመረመረ ሰው የለም።  ምን እርሱ ብቻ! አማራ ጠሉ “ ኤፍሬም ማዴቦ” ዜግነቱ አሜሪካዊ እንደሆነ ነግሮናል፡፡ ታዲያ ስለ ኢትዮጵያ ምን አገባው? በማለት የፖለቲካ ተንታኙ ወዳጄ “ሰርፀ ደስታ” አምርሮ ኤፍሬም ማዴቦን እዚህ አዲስ አባባ መጥቶ እየፈተፈተ ስላለው የኤፍሬም ማዴቦ ማንነት ጠይቋል።

 የግንቦት 7 ሦስተኛው ሰው፤የዛሬው ኢዜማ የበላይ አመራር ፓስተር ኤፍሬም ማዴቦ “ምኒሊክ እና መለስ ዜናዊ አገር የወረሩ ኮሎኒያሊስቶቸ ናቸው። በማለት በእንግሊዝኛው “Negotiation, nation building, and the naysayers” March 2012 ፡የጻፈው “አቡጊዳ” በተባለወ የተለጠፈውን ጸረ ምኒሊክ የጻፈ ስም አጥፊ ነው።  ኤፍሬም ቆይተን ከታች ማን እንደሆነ እመለስበታለሁ። የግንቦት ሰባት ባሕሪ ኢዜማ ውስጥ በጎ ድርጅት ሆኖ ሊለወጥ አይቻለውም።

ብቅርቡ በርሃኑ በዙ ሰው ያስገረመ ንግግሩ እንመልክት ( ለአሃዱ ተ/ቪዥን የሰጠው ቃለ ምልልስ)

 

"የአማራ ብሄርተኞች ወለጋ እና አሩሲ የሰፈረ አማራ ሲገደል አማራ ሞተ ማለታቸው ስህተት ነው" -

 

"ባለፉት 3 አመታት ህዝብ በማንነቱ ሲገደልና ሲፈናቀል ዝም ያልነው ሀገር እንዳትፈርስ ብለን ነው። ሽግግሩ መስመሩን የሳተው ባህርዳር ውስጥ የተደራጁ ወጣቶች እኛን ስብሰባ እንዳናደርግ የከለከሉን ጊዜ ነው።"

የአማራ ብሄርተኞች ወለጋ እና አሩሲ የሰፈረ አማራ ሲገደል አማራ ሞተ ማለታቸው ስህተት ነው። በዚህ አካባቢ የሰፈሩ አማሮችም መንግስት ህግ አላስከበረልኝምና ራሴን መከላከል አለብኝ ወደሚል አመለካከት ከገቡ ህገወጥ ተግባር ነው። በዚህ መንገድ ሀገር ትፈርሳለች። ወደ ሲቭል ዋርም ይከተናል።"(ብርሃኑ ነጋ)

ንአምን ዘለቀንም አንርሳ፤ ንአምን እንዲህ ይላል፡-

 

‘“አንድነት” እና “ኢትዮጵያ” የሚባል ስም ሲነሳ “ያንገሸግሸኛል” (ያስጠላኛል፤ ያስታውከኛል) በማለት ሳያፍር በስብሰባ አዳራሽ ለመላው ኢትዮጵያ አድማጮች እራሱን በመግለጽ የታወቀው ንአምን ዘለቀ የተባለው የግንቦት 7 እና ሻዕቢያን በማገልገል የታወቀው አንዳርጋቸው ጽጌን የተካው “የሻዕቢያው ጡሩምባ” ንአምን ዘለቀ፤ ለውግያ ኤርትራ የሄደ መስሎን ከሸወደን በኋላ ተመልሶ ወደ መኖርያው መጥቶ በየአደራሹ እየዞረ ኮሎኔል መንግሥቱ ሃይለማርያም ይመስል ገና ሥልጣን ሳይዝ ጠረጴዛን እየመታ የተናገረው ንግገሩን ጽፌ ለተከታታዮቼ አቅርቤው እንደነበር ያኔ ምታስታውሱት ነው።

እነኚህ ግለሰቦችም ሆኑ በተለይ መሪያቸው ‘ብረሃኑ ነጋን’ መተቸት ለኢትዮጵያ ፖለቲካ ወሳኝ ነው። ሰውየው ከፖለቲካ ካልተገለለ ፖለቲካውን ሆን ብሎ በማመስ ጸረ አማራ ድርጅቶች እንዲበረቱና አገሪቱ እንድትታመስ የማድረግ ተልዕኮ ስላለው እንደ አንዱአለም አራጌ የመሳሰሉ የዋህ ፖለቲከኞች እና ቅን ሰዎችን በመንጠቆ ሰልቦ ሕሊናቸውን የማበላሸት ባሕሪ ስላላው አገር ውስጥ የሚገኙ የኢትዮጵያ ወጣቶች “ቆሎ በሚቆላው ምላሱ” ተታልለው መሳሪያ እንዳይሆኑ ካሁኑኑ እንዲያውቁት ማድረግ ጠቃሚ ነው። ምክንያቱም ሰውየው ዛሬ የተከሰተ ፖለቲከኛ ሳይሆን በወዳጄ በጸሐፊው “ሰርፀ ደስታ” አገላለጽ “ብርሀኑ ነጋ ከ60ዎቹ ጀምሮ በፖለቲካ ድራማ ውስጥ የነበረና ያለ ሰው ነው፡፡” 

ብርሃኑ በኔው አገላለጽ “እጅግ ሞለጭላጫ የሆነ አምታታው በከተማ” እና “ጸረ አማራ ፖለቲከኛ” መሆኑን ከብዙ አማታት ጀምሮ በተቸሁባቸው በሁለት ገላጭ ርዕሶች የሚገለጽ የፖለቲካ ነጋዴ ሲሆን ፡ ሌሎችም እንዲሁ አምርረው ስለ ብርሃኑ ነጋ መሰሪነት ብዙ ጽፈውበታል።

የኔን ገላጭ ርዕሶች ልተውና ሳንሆዘ በሚኖሮው በወጣቱ ገጣሚ ሄኖክ የሺጥላ ጽሑፍ ብርሃኑ እና አብረው የሚፖለቲኩ አጋሮቹን በእንዲህ ይገልጻቸዋል፤

 

“እነ ኢንጅነር ሃይሉ ሻውልን ፥ እነ ዶ/ር ታዬ ወ/ሰማያትን እና ሌሎችንም የአማራ (ኢትዮጵያዊ) ሊህቃንን አዋርደው ፥ ፈርጀው ፥ ሰድበው ፥ ዘልፈው ፥ ከትግሉ ሜዳ ባስወጡበት መንገድ የአማራ ታጋዮችን ማጣጣል እና ማናናቅ ጀምረዋል።” ሲል የብርሃኑ ነጋ እና ጀሌዎቹ አማራን በማጥላላት ብዙ ምሁራንን ከትግሉ እንዲርቁ ያደረገ እጅግ አደገኛ ሰው የመሆኑን እውነታ ገልፆታል። 

ህዝባዊ ሓርነት ትግራይ ጫካ እያለ ብርሃኑ ነጋ እዚህ ፈረንጅ አገር ሲኖር ከተወሰኑ አድርባዮች ጋር ሆኖ የሆነ መጽሔት መስርቶ ከሽምቅ ተዋጊውም ሆነ ከመሰል ጸረ አገር ድርጅቶች ሲሞደዳሞድ ኖሮ አጋጣሚ ሽምቅ ተዋጊዎቹ አዲስ አባባ ሲቆጣጠሩ ሮጦ አገር ገብቶ ከመለስ ዜናዊና ከነ ታምራት ላይኔ ዊስኪ ሲያንቃርር አገር ወዳዶች ግን በጠራራ ጸሐይ አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በሻዕቢያ፤ ወያኔና በኦነግ ነብሰገዳዮች በጥይት እየተቆሉ ሬሳቸው ጎዳና ላይ ተጥለው ሲገኝ ነበር።

ቆየት ብሎ፤ “አማራው ሶማሌውን ሽርጣም እያለ ሲንቀው ነበር” ፤ እያሉ ሶማሌው በአማራው ላይ እንዲያምጽ ለማድረግ “አማራ መኖሩን” ከነገሩን በሗላ ቆየት ብለው ‘አማራ የሚባል ነገድ የለም” ብለው ችክ ካሉት ነብሳቸው ይማረውና “ከሊቀሊቃውንቱ መስፍን ወ/ማርያም” ጋር አብሮ ወደ ቅንጅት ተቀላቅሎ ቅንጅትም አፍርሶ ወደ አሜሪካ ሮጦ በመምጣት፤ “ሳትሰራ፤ ሳታስተምር፤ ተራራ ላይ ቁጭ ብለህ አስብ” ብለው አሜሪካኖቹ ገንዘብ ስለሰጡኝ ሕዝቡ ለምን እንደሚያስቆጣው አልገባኝም” ብሎ አሜሪካኖች እንዴት በፍቅር እንደወደቁለት “በማያሻማ ቃል ነገረን” ።

በፍቅር እንደወደቁለትም ማሳያው “እራሳቸው የደነገጉት የራሳቸውን ሕግ” በመጣስ የአንድ ሌላ አገር መንግሥት ጠመንጃ በማንሳት አመጽ አስነስቶ ለመጣል የሰለጠነ የሽምቅ ተዋጊ መሪ መሆኑን እያወቁ እንደልቡ አሜሪካ አገር ያለምንም እገዳ እንዲመላለስ “ቪዛና ፓስፖርት” ይፈቅዱለት እንደነበር ስናስታውስ እውነትም የፍቅራቸው መጠን ምን ተልዕኮ እንደሰጡት እጅግ አሳሳቢ ነበር። ዛሬም አሜሪካኖች ለብርሃኑ ነጋ ያላቸው ፍቅር እጅግ ያሳስበናል። መጨረሻ አገሪቷን በትኖ ተቃዋሚውን አቃቅሮ ወደ ሚሮጥባት አሜሪካ ሮጦ እንደማይመጣ መከራከር የሚችል ሰው የለም።

ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም እንዳሉት “ብርሃኑ ነጋ ቅንጅት ለማፍረስ ያቀደው ስልጣን ለኔ ካልተሰጠኝ ሲል ነው” ብለው መስክረዋል (ቪ ኦ ኤ አማርኛ ክፍል ተጠየቀው፤ሕንድ ለሕክምና/ለውስብስብ የጭንቅላት/የማጅራት ለቀዶ ጥገና  ሄደው ሳለ። ሳልናገር እንዳልሞት ብየ ይህችን መናገር አለብኝ። ብለው ነበር።  

ከብርቱካን መዲቅሳ ጋር አብሮ በየእስቴቱ እየዞረ “የድሮ ቆሻሾችን ጠራርገን እናስወግዳቸዋለን” በማለት አሜሪካ የቆዩትን ፖለቲከኞች በመወረፍ “በገፍ ደጋፊ አገኘ፤ ተንጨበጨበለት” ።  ብርሃኑ ቆየት ብሎ “መለስ የተባለውን ትግሬ አስወግጄ ፤ ሃይሉ ሻውል የተባለው አማራ ሥልጣን ላይ ለመስወጣት ነው የምታገለው? ያ አላደርገውም” ብሎ አረፈው “፡፡ እንዲህ ካለ በሗላ “አማራና ትግሬ ለዘመናት ገዝተውናል ዛሬ የደቡብና የኦሮሞዎች ተራ ስለሆነ ሥለልጣን የመያዝ ተረኛነቱ የኛ ነው... ። በማለት በግንቦት 7 ጋዜጣው አስነብቦናል።

ታስታውሱ እንደሆነ ከማንም ሰው አስቀድሜ በፈረንጆች 2013 ከ8 አመት በፊት አሲምባ ድረገጽ ባደረገልኝ ቃለመጠይቄ ላይ አሁን ያለው ቀውጢ የተነበይኩት እውነት ሆኖ ሳየው እራሴን አመሰገንኩ፡

እንዲህ ብየ ነበር፤

 

ዛሬ “ትግሉን” እያበላሹት ያሉት “የወያኔ አገልጋዮች የነበሩ፤ ተጣልተው ወደ ውጭ አገር የመጡ፡ ለወደፊቱም አገሪቷን ልክ በወያኔ አምሳያ የሚመሯት ወይንም ግጭት ውስጥ ገብተን ጸር የሚሆኑብንና የምንታጋቸው ከነዚህ አሁን ተቃወሚ ነን ከሚሉት ጋር ነው። ኦሮሞ ድርጅቶች ቀዳሚዎቹ ሆነው እንደ “አንዳርጋቸው እና ኤፍሬም መዴቦ አይነቶቹ ለውጥ ከመጣ ቅርአኔ ውስጥ የምንገባው ከነዚህ ቡድኖች ጋር ነው” ብዬ የገለጽኩት ቃለ መጠይቅ አሁን ሳየው ልክ ነበርኩ። ይህንንም እንደገና በድጋሚ Feb 21, 2017 በድረገጼ እንደገና አስታውሼአለሁ።

እነ ብርሃኑ ነጋንና እነ አንዳርጋቸውን ሰማይ ሲሰቅሉና ተከታይ እንዲያገኙ ሲያደርጉ ከነበሩት አንዱ የዛሬው ኢትዮ 360 ጋዜጠኛ (ዛሬ ሚመሰገን አስተዋጽኦ እያደረገ ቢሆንም) ድሮ ኢሳት ላይ እያለ “ኤርሚያስ ለገሰ” “ስለ አንዳርጋቸው ስብእና” ሲገልጽ “አንዳርጋቸው ማንዴላ” እያለ ሲሰብክ ነበር። መቸም ታሪክ እያጣመመ አማራን በማጥላላት መጽሐፍት የጻፈ አንዳርጋቸው በዚህ ስዕል መሳል እውነቱ ዛሬ አንዳርጋቸው በቅርብ ከጻፋቸው ጽሑፎቹ እንኳ ብትመለከቱ ሰውየው የአገራችን ታሪክ የሚመለከትብት ቆሻሻ ሕሊና መምዘን ትችላላችሁ።

የአንዳርጋቸው “የአማራ ሕዝብ ከየት ወዴት” “የኦሮሞ ሕዝብ ከየት ወዴት” በአባ ዱላ ገመዳ “ የኤርትራ ሕዝብ ከየት ወዴት” በመለስ ዜናዊ የተጻፉ ተመሳሳይ ዘረኛ መጽሐፉቶች ያተኮሩት አማራው ላይ ነበር። ያንን ያነበባችሁ አንዳርጋቸው ማን መሆን ለማወቅ አያዳግትም። የግንቦት 7 ሱቆች የሚሸጡት ሸቀጥ ውሸት ነው የምለው ለምሳሌ አንዳርጋቸው መለስን አስመልክቶ “መለስ ሚባል ሰው፤ከተቀበረበት ሥላሴ ቤተክርስትያን ወጥቶ፤መንገድ ላይ እንዲወረወር ነው ያደረገው የኢትዮጵያ ሕዝብ” በማለት ኢትዮጵያዊያን ያላደረጉት የስነ ሞራል ድርጊት አድርገዋል ሲል የፖለቲካ መሪ ነኝ ከሚል ሰው እንዲህ ያለ ጸያፍ ንግግርና ፈጠራ ሲናገር ድርጅቱ የመዋሸት ባህሉ የዳበረ ነው።

አሁን ኢዜማ እንመራለን ብለው የተቀመጡ ሰዎች ዋና መዘውሩ በብርሃኑ ነጋ የተያዘ ነው። ብርሃኑ ነጋ ደግሞ ኢዘማ ብሎ ይምጣ እንጂ ሰብኣዊ መብት ሲጥስ የነበረ ሰው ነው። ይህንን ለማረጋገጥ “የግንቦት 7 የግፍ ተግባር እና የመገናኛ ብዙሃን ዝምታ – ያሬድ ኃይለማርያም” የሚል ሰብኣዊ መብት ጠበቃው ያሬድ የጻፈውን አንብቡ።

ኢዘማ ብሎ ዛሬ ብርሃኑ ሌላ ሰው መስሎ ወጣቶችን ስለ አንድነት ሰባኪ መስሎ ሊያምታታ ቢሞክርም ፤ ኢዜማ ብርሃኑ ስለ አንድነት ደንታ ቢስ ነው። ማሕደሩን መፈተሽ ነው። “ብርሃኑ ነጋ” ምንድ ነው ሲል የነበረው? ። ሕዝብ እስከወሰነ ድረስ “ማንኛውንም ውሳኔ እናከብራለን” ፡ የምንታገለው ይህንን ለማስከበር ነው ይላል። ማንኛውንም ውሳኔ የሚለው “የመገንጠልም ጭምርም ነው” ። አማራ ይገደል የሚል ውሳኔ ህዝብ ካጸደቀ “የሕዝብ ውሳኔ ነውና እንዲጨፈጨፍ ያከብራል” ማለት ነው። አብይ እና ብርሃኑ አንድ ናቸው የምለው ለዚህ ነው። ጋምብሌ፤ ጉራጌ፤ኦጋዴን፤ኦሮሞ ትግሬ፤ እገነጠላለሁ ካለ “የሕዝብ ድምጽ ነውና ፤ ውሳኔውን ያከብራል። በምንም ታምር በጠምንጃ አንይዘውም እንደ ወያኔ” ብሏል”። ትግሬዎች ሥልጣናቸው ካጡ ወደ መገንጠል ስለሚሄዱ እንደብርሃኑ አባባል “ሕዝብ ከወሰነ” ትግሬዎች አገር የማፍረስ እና ለመገንጠል መብታቸው ይከበራል ማለት ነው? ፖለቲከኞች ተብለው ከ60 ዎቹ ጀምሮ የሚጠሩት ፖለቲከኞቻችን እነዚህ ናቸው።

 ይህ ንግግር “ኢሳት እና ጥምረት” በጠሩት ስብሰባ ነግሮናል። እነዚህ ናቸው የወያኔ ገጽታ እና ባሕሪ ስርዓት የሚደግሙት የምለው።

 

የግንቦት 7 Public Relation Officer- (የሕዝብ ግንኙነት) የሆነው “ፓስተር ኤፍሬም ማዴቦ” ዛሬም ከአስመራ ወደ አዲስ አበባ ገብቶ ከፍተኛ ተዋናይ የሆነው የኢዛማ አመራር በ2012 ኦክላንድ ካሊፎረኒያ የሻዕቢያ “ፌስቲቫል” ግንቦት 7 ን ወክሎ  ከተናጋሪዎቹ እንግዶች አንዱ ሆኖ በተገኘበት ጊዜ የተናገረው “ንግግር” ኤፍሬም ማዴቦ ምን ብሎ ነበር? Efrem Madebo in Oakland EPLF Seminar የሚለውን ዩ ቱብ ላይ ጉጉል አድርጋችጉ ብታደምጡ “ነፍጠኛ” እያለ ጸረ አማራነቱን በግልጽ ሲናገር ታደምጡታላችሁ።

 

“ኤርትራ እስራኤላዊቷ “ዳዊት” ስትባል ፤ ኢትዮጵያ ደግሞ “ያረጀች፤የጃጃች” “ጐልያድ” ስትባል፤ የኢትዮጵያ ግዙፍነት “Irrelevant” (ዋጋ ቢስ) ነው፡ “ዋጋ የሌላት አገር” ስትባሉ እንደ አንድ ዜጋ ካንድ የፖለቲካ ሰው ነኝ ከሚል ይህ ዘለፋና ይህ ክህደት ስትሰሙ “አንጀት አያቃጥልም ወይ ?” ከዚህ ወዲያ ኢዜማ ብለው መጡ አልመጡ ከዚህ ባሕሪ ሊለወጡ እንዴት ይቻላቸዋል?

ግንቦት 7 ጸረ አማራ ነው። የግንቦት 7ዲሞክራሲ ታጋዮችም ይህንኑ ነግረውናል። በግንቦት 7 ጋዜጣ ርዕሰ አንቀፁ ላይ “አማራና ትግሬ ለዘመናት ገዝተውናል ዛሬ የደቡብና ኦሮሞዎች ተራ ስለሆነ ሥለልጣን የመያዝ ተረኛነቱ የኛ ነው... የሚል ጽፏል።

 

ግንቦት 7 ዛሬ ኢዜማ የከፋ ባንዳ ሆኖ መምጣቱን በቅርብ ኢዜማ ከተመሰረተ ወዲህ የተቀላቀላቸው ውስጥ አንዱአለም አራጌ ላስነብባችሁ እና ልደምድም:-

 

“አሁን እየታየ ያለው ሞት እና መፈናቀሉን ያመጣው ኢህአዴግ ሳይሆን የኢትዮጵያ ህዝብ ለዘመናት ታፍኖ እና ተጨቁኖ በመኖሩ ዛሬ ነጻነት ስለተቀዳጀ ነፃነት በግባቡ ያለመጠቀም ነው፡፡” ሲል አፈናቃዩ ኦሕአዴግ ሳይሆን ሕዝቡ እራሱ ነው። ሲል ተፈናቃዩን የወነጀለ አንዱአለም አራጌ በክፍል 2 እንመለከታለን።

 

 አስከዚያው ግን ወደ ኢዜማ የተለወጠው ግንቦት 7 ነፃ አምጪ ሳይሆን ሌሎች ሃይሎች ያመጡትን ነፃነትን የሚሰርቅ ነው። ይህንን ለማረጋገጥ

በሰሜን ጎንደር ጫካዎች፤ከተማዎችና በገጠሮች አማራዎች ከትግራይ ፋሺስቶች ጥቃት ራሳቸውን ለመከላከል እያደረጉት የነበረው መራራ የሞት ሽርት ውግያ “የአማራ ማንነት ተጋድሎ” የሚለው “የነፃነት ሃይሎች” ብሎ ስሙን በመቀየር የግንቦት 7 ተዋጊዎች ናቸው ሲል ‘አማራዎች እያደረጉት ጀግንነት የተሞላው አስደናቂ የመከላከልና የማጥቃት ውጊያ በመስረቅ፤ የኔ ተዋጊዎች ናቸው ሲል በአደባባይ በመዋሸት “የአውደ ውግያ ፕላጊያሪዝም” ፈጽሟል። ይህንን እኔ Feb 21, 2017 “ግንቦት 7 የአማራዎችን ተጋድሎ የሰረቀ የመጀመሪያው “የአውደ ውግያ ፕላጊያሪስት/ሌባ” በሚል የጻፍኩትን ማንበብ ይቻላል።

እኔ ጨርሻሉ እናንተ ሼር አድርጉ!

አመሰግናለሁ ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ)

No comments: