Tuesday, June 30, 2020

ሓጫሉ እጅግ ሲበዛ ሞገደኛ እና በባለተራነት ስሜት ተሰፍጦ የጥጋበኛነት ግሳት ሲያገሳ የነበረ፤ ምላሱ በልኩ የማይቆጣጠር “ግዙፋን ዋርካዎቻችንን” ሲያረክስ የነበረ ወጣት ነበር፡ ነብስ ይማር! ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ Ethio Semay) June 30/2020


ሓጫሉ እጅግ ሲበዛ ሞገደኛ እና በባለተራነት ስሜት ተሰፍጦ የጥጋበኛነት ግሳት ሲያገሳ የነበረ፤ ምላሱ በልኩ የማይቆጣጠር “ግዙፋን ዋርካዎቻችንን” ሲያረክስ የነበረ ወጣት ነበር፡ ነብስ ይማር!
ጌታቸው   ረዳ (ኢትዮ ሰማይ Ethio Semay)
June 30/2020
 ሓጫሉ ለምን ሞተ? ማንስ ገደለው? እንዴት ሞተ? ብዙ ሰዎች መላምታቸው ሲነታረኩበት አንብቤ ገርሞኛል። አበበች አደነም ገዳዮቹ ትግርኛ ተናጋሪዎች ናቸው በላ በይፋ አወጃለች (ኣግዚኦ የሚባልላት  ሕግ የምትጥስ ሕገ ወጥ ወንጃሊት!!)ልጁ ከሰማይ በታዘዘለት ቀነ ቀጠሮ በተጠራበት ወቅት ሄዷል (ሁላችንም የየራሳችነን መጥሪያ ቀኖች አሉን)። ኦነጎች እና በወያኔዎች በነፍጠኛነት እየተወገዙ፤ በሓሰት ተወንጅለው ባጭር የተቀጩ ብዙ ኢትዮጵያውያን እናስታውሳለን። አንደኛውና ቀዳሚው ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ ፤ ጋዜጠኛ ደምስ በለጠ እና ሚሊዮኖች ተቀጥቅጠው ተረሽነው፤ተሰቅለው፤አንገታቸው ታርደው፤ብልታቸው የተኮላሹ፤ በመርዝ የተገደሉ ሚሊዮኖች ናቸው።ዛሬ ሓጫሉ በጥይት ተገደለ የሚል ዜና ሰምተናል።

ኢትዮጵያውያንና የኮርያ ሕዝቦች ልዩ አልቃሾች ናቸው። ይንሰቀሰቃሉ። ሰው በግፈኞች ሲገረፍና ብልቱ ሲኮላሽ፤ እናቶችና ባለትዳሮች ሲደፈሩ፤ ወጣት ሴቶች ሲያለቅሱ፤ተጠልፈው ደብዛቸው ሲጠፋ፤ ግን ምንም የማይሰማቸው፤ ዛሬም ለግፈኛ መሪዎች የሚያጎበድዱ ኢትዮጵያውን ሁሉ ዛሬም ለመከራችን ዋናው ተጠያቂዎች ናቸው። ለመከራችን ዋናው ተጠያቂ የነበረው ‘መለስ ዜናዊ’ ሲሞት “ከላይ እንደገለጥኩት “መሬት ትዋጠን” ብለው ስቅስቅ ብለው ያለቀሱ ተቃዋሚ ፖለቲከኞችን እናስታውሳለን።

“አንተም ክፉ ነበርክ ክፉ ሰደደልህ..” ሲሉ የነበሩ ጥንታዊ አያቶቻችን ዛሬ የነሱ ልጆች የሆንን የሐበሻ ልጆች በተቃራኒ ቆመን “ሰው ሲያፈናቅሉ የነበሩ፤ በተሰጣቸው መድረክ ተጠቅመው አገር የሚያፈርስ ቅስቀሳ ሲያደርጉና ከተማው ገጠሩ ሲያውኩ ሰላም ሲያደፈርሱ የነበሩ “ጋኔሎች በሞት ሲሰናበቱ ” ወደ እርግብነት ለውጠው “የሚያለቃቅሱ” ኢትዮጵያውያን የመለያ ባሕሪቸው ሆኖ ዛሬም አለ። ቤተክርስትያኖቻቸው እና መስጊዶቻቸውን ሲያቀጥሉላቸው ፤ሰንደቃላማቸው እና ማተባቸው በመንግሥት ወኪሎችና ታጣቂዎች እንዲያወልቁ ሲደረግ “እነሱን የሚቆጣጠረው” መንግሥት ማሞካሸትና ማሽቃበጥ የኢትዮጵያውን ባሕሪ ሆኖ ቀጥሏል።

ዛሬም በሕይወት ቆመው በሚሊዮኖች ኢትዮጵያውያን ደም እጃቸው በደም የጨቀየው እነ ኢሳያስ አፈወርቂ የመሳሰሉ ዓለም አቀፍ ወንጀለኞችን “በወኪሎቻቸው ጋባዥነት” ወደ ኢትዮጵያ እንዲመጡ ተደርጎ “በገደልዋቸው ሰዎች አገር ተንፈላስፈው ባንዴራቸው እየተውለበለበላቸው “ወላጆቻችን ወንድሞቻችን እህቶቻችን ጥርሳቸውን እየነቀልክ ስላባረርክልን፤ በሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮች የሳህል ተራራ በውሃ ጥም እያቃጠልክ ምሽግና አስፋልት ቆፋሪዎች አድርገህ በባርነት ስለገደልካቸው ፤ ወደብ አልባ እንድንሆን የዓረቦች ሙርከኞች ስላደረግኸን “እንወድሃለን” የሚሉ የሙታን ልጆች በገፍ ተፈጥሯል። ወንጀለኞች የሚንቀባረሩበት አገር ብቸኛው የአበሾች አገር “ኢትዮጵያ” ነች። “ጋኔሎች” ሲሞቱም አይጠየቁም፤ አይወቀሱም፤ ሲኖሩም አይጠየቁም አይወቀሱም፡በቃ!

ተጠቂ ሙታኖች የሚጮሁባት ኢትዮጵያ!

በሚገርም ክስተት አንዳንድ ሰዎች ፈስ-ቡክ ላይ ሲጽፉ ያነበብኩት “ሓጫሉ ስለሞተ አማራዎች እንዳይገደሉ፤ ሕዝብ እንዳይገዳደል እርስ በርስ ጦርነት አንዳይነሳ ዝም በሉ ይላሉ” ፤ ሓጫሉ ስለተገደለ ሳይሆን አገር የሚደፈርሰው ፤ወንጀለኛው ስርዓት በሕዝባዊ ስርዓት ተለውጦ ወንጀለኞች ከሥልጣን ካልተወገዱ ስርዓቱ እስካለ ድረስ የሞገደኞች መገዳደል ቀጣይ ነው። ባሕሪው ነው፡ (28 አመት ያየነው ይህ ነበር) አሁን ብሶበታል ።ለዚህ ነው ይህ ሥርዓት ተሎ መወገድ አለበት ብለን የምንቀሰቅሰው።

አንድ ሰው “በሕይወት እያለ ሲያሳየው የነበረው የተረኛነት ግሳት ከሞተ በሗላ በምንዘግብ ሰዎች ውርጅብኝ ሲያወርዱብን የሕሊናቸው ጩጬነት ነው ብለን ብናልፈውም” ይሕ ባሕሪ እስከ መቸ ይቀጥላል? የሚለው ግን መልስ አልተገኘለትም። “ሓጫሉ” እጅግ ሲበዛ የተወጣጠረ ባለጊዜነትን ሽቅብ ያወጣው፤ መኪና ሲነዳ ሕዝብ በተሰበሰበበትና በመተላለፊያ ጎዳና ላይ “ሽጉጥ” መሳርያ ከኪሱ እያወጣ ሰላማዊን ሰው ሲቃጣ እና ሲያስፈራራ የነበረ ጥጋቡን መቆጣጠር ያልቻለ ፤ የተረኛነትን ስሜት በአፍንጫው የወጣ እጅግ ሞገደኛ ሰው ነበር።

መለስ ሲሞት ብዙ ሰዎች ፡እንደሰው ሰውነኝና ማዘን አለብኝ” እያሉ ሲያለቅሱ ልባቸው የተሰበረ አንጋፋ ሰዎች አይቻለሁ (እንደ እነ ታማኝ በየነ አይነቶቹ ልባቸው ወለል ብሎኣቸው አይሮፕላን ሲወርዱ “በቴክስት መልእክት” መርዶውን ሰምተው መራመድ እስኪያቅታቸው የተሰናከሉ አዛኝ ፍጡራን አይተናል) በእነ በቀለ ገርባ ፤በነ ጃዋር፤ በእነ ዳውድ ኢብሳ፤ በእነ ተስፋየ ግበረአብ ፖለቲካ ሕሊናው በአክራሪ ፖቲካ ተወጥሮ አማራውን ሲያወግዝ፤ ምኒሊክን እርኩስ አድርጎ ሲኮንን የነበረ፤ የትላልቅ ዋርካዎቻችን መልካም ዝናን ያቈሸሸ፤ ልጓም የበጠሰ ሞገደኛ “ፀብ የሚዘራ” አዝማሪ ነበር።

ሓጫሉ እንደተመኘውም “ተረኛ ኦሮሞዎች ፈረሳችሁን እየጋለባችሁ ምኒሊክ ቤተመንግሥት ተቆጣጠሩት “ ብሎ እንደዘፈነላቸው ሁሉ ፤ ያለው አልቀረም “ተረኞቹ ኦነግንና ኢሳያስ አፈወርቂን በውስጥ አርበኛነት ሲያገለግሉ የነበሩ እነ “ኮለኔል “አብይ አሕመድ” የመላውን የኢትዮጵያ ሕዝብ ተቃውሞ እና “ደም” ምርኩዝ አደርገው ምንሊክ በተመንግሥት ቁጢጥ ብለው በሁለት አመት ውስጥ ለመስማት፤ለማየት የሚሰቀጥጥ ዘግናኝ ወንጀል ሲደርግ “አልሰማንም አላየንም” እያሉ “ንጸሐን አስረው ፤መግረፍ፤ማሰቃየት፤ነብሰጡሮችን በግፍ አስረው ያስወርዱ ካለፉት ያልተሻሉ “የባሱ ጋኔሎች” ሆነው በንጹሓን ደም ቀለዱ። =

ሓጫሉ ምላሱ በልኩ የማይቆጣጠር “አማራን በጡት ቆራጭነት እያወገዘ በአኖሌ ሃውልት ቆሞ በኩራት ተኮፍሶ ፎቶ መነሳትን የሚወድ” እጅግ ሲበዛ “አግረሲቭ” የነበረ እሱን በሚመስሉ መጎደኞች ተገደለ፡ በቃ! ።ከሥርዓተ አልባ መሪ እና “አናርኮ ፋሺስት” የሆነ ሥርዓት የሚከሰተው ክስተት “ሞገደኞች” እርስ በርሳቸው የሚገዳደሉበት ክስተት ውጤት ነው።

ባለ ተረኞቹ ከሥልጣን ካልወረዱና መሰርያቸውን ለሕዝባዊ ስርዓት ካለስረከቡት መገዳደሉና ግድያው የስርዓቱ ባሕሪ ነውና አገሪቱ በመገዳደል ማዕበል ውስጥ እየተናጠች ትቀጥላለች። ወንጀለኞችን በየቦታው እየሾመ አገሪቱ የሚያምሳት እራሱ አብይ አሕመድም አብይ እራሱ እንደተናገረው መገዳደሉ ይቀጥላል ብሏል። አይደለም እንዴ? ስለሆነም ነብስ የመጠፋፋቱ አሳዛኝ ክስተት ሓጨሉን “በድንገት በላው”፤ ታሪኩ ይኼው ነው፤ በቃ! ማን ገደለው?ተገደለ? የሚለው መላምት ውስጥ መግባቱ “ድካም ነው”። ጥያቄው ከዚህ በኋላስ ባለተራው ማን ይሆን? ሁ ኢዝ ኔክሰት?
ጌታቸው ረዳ (Ethio Semay)

Friday, June 26, 2020

መቀሌ ውስጥ የገዳ ስርዓት የኦሮሙማው የመደመር ብልጽግና ፓርቲ ሹም ሆኖ የተሰየመው በምኒሊክ ሸዋ ጥላቻ የሰከረው ትግራዋዩ የሃተታ 70 እንደርታ መጽሐፍ ደራሲ ነብዩ ስሑል ሚካኤልን ላስቃኛችሁ! (ጌታቸው ረዳ) (Ethiopian Semay ድረገጽ አዘጋጅ)


መቀሌ ውስጥ የገዳ ስርዓት የኦሮሙማው የመደመር ብልጽግና ፓርቲ ሹም ሆኖ የተሰየመው  በምኒሊክ ሸዋ ጥላቻ የሰከረው ትግራዋዩ  የሃተታ 70 እንደርታ መጽሐፍ ደራሲ ነብዩ ስሑል ሚካኤልን ላስቃኛችሁ!
(ጌታቸው ረዳ)
(Ethiopian Semay ድረገጽ አዘጋጅ)

በፎቶ ላይ የሚታየው ደራሲው ነብዩ ስሑል መጽሐፉን ሲያስመርቅ የተሰጠው የካባ ሽልማት ለብሶ ምርቃቱ ሲከናወን የሚያሳይ ፎቶግራፍ ነው። 

እንደምን ሰነበታችሁ!  
ባለፈው ሰሞን የመጀመርያው ወያኔ መስራች የብላታ ሃይለማርያም ረዳ ልጅ የሆነው ‘ካሳ ሃይለማርያም’ አክራሪ የሸዋ ጥላቻው ምን እንደሚመስል በመጠኑ ለማሳየት ሞክሬአለሁ። በጣም በበርካታ አንባቢዎች ተነቧል። የምጽፋቸው ሰነዶች ለኢትዮጵያ ወገኖቼ ለሕዝብ እንዲዳረሱ ላደረጋችሁ ወገኖች ሁሉ አመሰግናለሁ።

ዛሬ ደግሞ አዲስ አባባን “ፍንፍኔ” እያለ በመጽሐፉ የሚጠቅሰው የብልጽግና ፓርቲ የነብዩ ስሑል ማንነት ላጫውታችሁ ነው። በቂ ጊዜ ባላገኝም በማገኛት ክፍት ደቂቃም ቢሆን ‘አረፈ እያልኩ’ ማንበብ የጀመርኩት የዚህ ልጅ መጽሐፍ የታዘብኩት ነገር መጽሐፉ በእንደርታ ታላቅነት እና በወያኔዎች የ“አሽዓ” ጥንታዊ የንግሥና  የበላይነት “ፉክክር” ያነሳሳው ውስጣዊ ቁጣ ይመስላል። 


ያም ካልሆነም የታላቅዋ እንደርታነት የንግሥና መሰረት ነን ባይነት ያመነጨው እልክነት በተለይ እንደርታዎች በወያኔ አሽዓዎች (አክሱም  ዓድዋ ሽሬዎች- በተለይ  በዓድዋዎች የመተዳደሩ እንቆቁልሽ የሚያበሳጭ እውነታ እንዳለው ቢገባኝም) ባጭሩ “ዓድዋዎች እጃችሁን ከእንደርታ አንሱ” - ራሳችን በራሳችን እንተዳደር የሚለው ድብቅ ሕጋዊ መልእከቱ እንዳለ ብቀበለከውም ጥያቀው አስታኮ የሄደበት እጅግ አክራሪ ጸረ ሸዋነቱ ለማንበብ ይጎመዝዛል።



 ዓድዋዎች ወይንም እንደርታን ትግርኛ የሚያንኳስሱ መሰል አውራጃ የወያኔ ትምክሕተኞች እቅጩን ሲነግራቸው (1ኛ) ትግርኛ ቋንቋ የተመሰረተው “እንደርታ ውስጥ መሆኑን” በመጽሐፉ በገጽ 22 ይናገራል። ሆኖም ነብዩ ይህን ሲል- እንደርታ ውስጥ ትግርኛ ሲፈጠር በስንተኛው ክ/ዘመን መሆኑንም አይገልጽም፡ የሚገልጸው ፣ማስረጃ “እዛው ለመጀመሪያ ጊዜ ትግርኛ መነገሩንም “እንደሆነ ይታመናል” ከማለት ውጭ ማስረጃ አልጠቀሰም። አማርኛም ቢሆን ከተለያዩ ነገዶች የተወጣጡ  ላስታ ውስጥ የነበሩ የንጉሥ ወታደሮች እንደተፈጠረ እንጂ እንሌሎቹ ማሕበረሰቦች “አማራ የተባለ ማሕበረሰብ” ራሱ ችሎ የተከሰተ ማሕበረሰብ እንዳልነበረ እነ ‘ ዶ/ር ላጲሶ ደሊቦን’ የጻፉትን እንደ ማስረጃ ይጠቅሳል።ወቅቱም ወሎ ላስታ ውስጥ አማርኛ በተፈጠረበት ወቅት ትግርኛም እንደርታ ውስጥ ባንድ ወቅት መፈጠሩን ይገልጻል።



ያንን እንዲህ እንዳለ፤ ልጁ በአጼ ምንሊክና በሸዋ ላይ ያለው ጥላቻ ከወያኔ ጸሐፍቶች እና ፖለቲከኞች ያልተሻለ እንደውም ንጉሡ በከፋ መልኩ በትግራይ ሕዝብ ላይ ክፉ የሆነ ውስጣዊ የጠለቀ ጥላቻ እንዳላቸው ይገልጻቸዋል። “የእንደርታ ታዳጊ ወጣቶች የወያኔ የቂም እና ጥላቻ ትምህርት እንዳይበቃቸው ዛሬ ደግሞ እንደ አዲስ ወያኔን ይቃወማሉ ተብሎ የተነገረላቸው ወጣቶቹ እነ ነብዩ ስሑል የጥላቻ ማስተማርያ መጽሐፍ ተጨምሮበት ሌላ የ29 አመት ንትርክና ቂም ብቻ ሳይሆን የሺ መጪው ዘመን ጥላቻ እየተከለ የመሄዱን እድሳት ስመለከት ማቆሚያው የት ይሆን? እላለሁ።



ለውግዘቱ መነሻ ነው ብሎ የሚጠቅሰው ማስረጃ “ንጉሡ ጎረምሳ የሆነውን “የእንደርታን ወንድ” እየለዩ እንዲሰለብ በማድረግ የእንደርታ ልጃገረዶች እና ሴቶች የሚያገባቸው ወንድ አጥተው ቁም ቀር ሆነው “የትግርኛ  ግጥም” ተገጥሞ በእንደርታ ሕዝብ ላይ “የዲሞግራፊክ መናግት (እራሱ የተጠቀመበት ቃል ነው) “የተዋልዶ መናጋት” ሆን ተብሎ  የተደረገ በእንደርታ (ትግራይ) የዘር ማጽዳት ጭፍጨፋ ምኒልክ ፈጽመዋል እያለ ይከሳቸዋል።


ለዚህም እንደማስረጃ የሚጠቅሰው ደብተራ ፍስሃ አብየዝጊ የተባሉ በጣሊያን ጊዜ የራስ ስብሓት ተከታይ ሆነው ራስ መኮንን ከጣሊያን አገር ኖርው በኤርትራ በኩል ወደ ትግራይ ሲሻገሩ ምኒሊክ መቀሌ ከተማ ሲገቡ ራስ መኮንን *ን) አጅበው ወደ መቀሌ ከተማ የገቡ የትግራይ ሰው ናቸው። 


ሰውየው በጣሊያን ጊዜ ኤርትራ ውስጥ የኖሩ የጣሊያን ሃይማኖታዊነት/ ዘመናዊነት/ንክኪ የነበራቸው፤ እጅግ አድርገው ሸዋን የሚጠሉ፤ ጎንደር አማራ እና የሸዋ አማራ እየለዩ (በባድሜ ጦርነት ወቅት ልክ አቶ አብርሃም ያየህ መቀሌ ውስጥ የመቀሌ ህጻናት የጨፈጨፈው ኤርትራዊ ፓይለት ሳይሆን የሸዋ ሰው የሆነ እንጂ ጎንደሬ ቢሆን እንዲህ አያደርግም ብለው በሕዝብ ፊት እንደተናገሩት ማለት ነው። በሗላ ግን ኤርትራዊው ፓይለት ጅቡቲ ውስጥ ጥገኝነት ጠይቆ እንደገባ በወቅቱ እኔም መዘገቤ ትዝ ይለኛል) ፡ ሰውየው (ደብተራ ፍስሐ አብየዝጊ)  ጎንደሬው የዋህ እና የትግሬዎች ወዳጅ “ሸዌው” ግን የትግሬ ጠላት እያደረጉ በማነጻጻር አማራን ከሌላው አማራ በባህሪ እንደሚለያዩ እያነጻጸሩ የሚገልጹ እጅግ አክራሪ የትግራይ ብሔረተኛ የነበሩ መጨረሻ የጣሊያን አገር ሆነው በእጅ ጽሑፍ በትግርኛ የጻፉትን መጽፍ ነው የጠቀሰው።


እኔ የገረመኝ ግን ነብዩ ምኒልክን ያለ አግባብ ንጉሡ ትዕዛዝ እንዳስተላለፉ አድርጎ በመዋሸት ፡ “የእንደርታ ወንድ እንዲሰለብ ትዕዛዝ አስተላልፈዋል እያለ ንጉሡን በውሸት ይከሳቸዋል። ደብተራ አብየዝጊ ግን የምኒሊክ ወታደሮች ናቸው የፈጸሙት እያሉ ነበር በታጣቂ ወታደሮች ላይ ብዕራቸው የጻፉት እንጂ ነብዩ እና መሰሎቹ እንደሚሉት እንደርታን/የትግሬ ወንድን እየለያችሁ ስለቡት ብለው ምኒሊክ ትዕዛዝ አላስተላለፉም።  ያውም ደብተራ ፍስሓ የጻፉት  “ምኒሊክ የዋህ ነበሩ ሰውን አትስለቡ ሲሉ ነበሩ፤ ተራራ ላይ መሽገው እየወጉን ያሉትን የመድፍ ጥይት አትተኩሱባቸው ተው! ሲሉ ነበር” ብለው ጽፈዋል። ነብዩ ግን ምኒልክን ከግራኝ አህመድ የባሰ አረመኔ ነው ይላቸዋል።



አርግጥ ደብተራ ፍስሓ አክራሪ ብሔረተኛ ትግራይ ትግርኚ ነበሩ። ‘አማራዎች በትግራይ ደጋማ ለምለምነት ይደነቁ ነበር፡ ሆኖም የትግርኛን ቋንቋ ሲሰሙ ትግርኛን እጅግ የሚጠሉ ነበሩ ይላሉ። ዘማቾቹ በሙሉ አማርኛ በመናገራቸው አማራዎች አድርገው ስለዋቸዋል።  እንዲህ ይላሉ፡ አክራሪነታቸውን ተመልከቱልኝ፡ “ትግራይ ለምና ያመጣቻቸው ይመስል ይንገጫገጫሉ፤ ፡ እንኳን እነሱ አብረው የመጡት አጥንታቸው የወጡ የከሱ ከብቶቻቸው ሳይቀር አይተውት የማያውቁት “የትግራይ ለም ግጦሽ መሬት” እየጋጡ ሰውነታቸው ደልቶአቸው ነበር”።  እያሉ የሚጽፉ ከትግራይ ወዲያ ያለው መሬት ደረቃማ ምድረበዳ ለከብት እንደማይመች አስመሰልው በሚገርም ሁኔታ የሚገልጹ አሰገራሚ ሰው ነበሩ።


እንደውም “ትግሬ ሲጠግብ እስክስታ ያምረዋል ፤አማራ ሲጠግብ ጦር አውርድ የሚል ሕዝብ ነው” ይላሉ። በዚህ ጦር አውርድ ብለው  እግዚሓርን ሲለምኑትና መሬት እየደበደቡ ሲጸልዩ፤ አህመድ ግራኝን ላከላቸውና ከቀያቸው ፈረጠጡ’፡ ብለው የጻፉ  የፋሺስቶቹ የወያኔዎቹ የነ መምህር ገበርኪዳን ደስታ የጥላቻ የጡት አባት ነበሩ።  ዛሬም የነ ነብዩ ስሑል ሚካኤል የጡት አባት ሆነው ‘ምኒልክን” የትግራይ ሴት ወንድ እንዳትወልድ “ወንድ እንዲሰለብ አድርገው፤ ሴቶች እንዲበዙ አደረጉ” እያለ መጽሐፍ ጽፎ በትግራይ መቀሌ ውስጥ የአብይ አሕመድ የብልጽግና ወኪል ሹም “ወጣት ነብዩ ስሑል ምኒልክን ይከሳል”።


ምኒሊክ ይላል ነብዩ ‘ ከግራይ አህመድ የከፋ ጭፍጨፋ በትግራይ/እንደርታ ሕዝብ ላይ የፈጸመ ንጉሥ ነው” “..፣ “የትግራይ የፖለቲካ ማዕከል ሆና በቆየቺው ‘በታላቅዋ’ እንደርታ ውስጥ ወንድ የተባለ እየለየ በመግደል ትግራይን ለማዳከም እንዲህ ያለ የጭፍጨፋ ትዕዛዝ ያስተላለፈ ንጉሥ (ምኒሊክ) ‘ክርስትያን ወይንም ኢትዮጵያዊ ነው’ ለማለት አያስደፍርም”


በማለት የነብዩ ስሑል አያቶች ከጣሊያን መገዛት ነጻ ያወጣቸውን እምየ ምኒልክን ክፉኛ  በሆነ ቃላት በመጠቀም “የትግራይ ዘር አጥፊ እያለ” ያወግዛቸዋል።


በዚያ ሳይወሰን ጣሊያን ተምቤን ላይ መሽገው የነበሩት የትግራይ ተዋጊዎች ከብቦ እንዲወጋቸው ተመሳጥሮ ነበር እያለ ምኒሊክን ይከሳቸዋል። እኔ ደግሞ ምን አለበት እኛ ትግሬዎች ከኤርትራ ወንድሞቻችን ጋር ሆነን የጣሊያን እግር አጣቢ እንድንሆን ለምን አልፈቀዱልንም ነበር እላለሁ?  አዎ! ምክንያቴን አድምጡኝ፡  “ምኒልክ ወደ ትግራይ ለምን እንደሄዱ እወቅሳቸዋለሁ” የሐርር ፤ የጎንደር፤ የሸዋ፤ የወሎ፤ የወላይታ… እምቡጥ  ወጣት አበቦች - ትግሬን ነፃ ለማውጣት “መቀሌ እንዳየሱስ ተራራ” እና  “ዓድዋ ሰሎዳ ተራራ” ረግፈው ሲቀሩ እንዲያ ነፃ ባወጡት ሕዝብ “ሲዘለፉና ክብራቸው ስደፈር መስማት እጅግ ያመኛል”። ትግራይ ያፈራቻቸው የ28 አመት የወያኔ ፍሬዎች እንዲህ ይመስላሉ። ነጻ አውጪውን ምኒሊክን ሲከስሱ መስማት ይዘገንናል።

እስኪ አንድ ልጨምርላችሁና ልጨርስ፦

 መቀሌ እንዳየሱስ ተራራ ላይ የመሸገው የጣሊያን ሰላቶ በውሃ ጥም ተይዞ እጁ እንዲሰጥ የመጀመሪያው ምክር ለጋሽ የሆነው የፊተውራሪ ተክለሐዋርያት ተክለ ማርያም ወንድም የሆነው “የሸዋው  አርበኛ ዋጊ ወጣት የአብዩን” ምክር ፡ ደብቆ እንዲህ ያለውን ዘዴ ያመጡት “ራስ አሉላ ናቸው ለጣይቱ አማክሮአቸው ነው ጣሊያኖች በውሃ ጥም እንዲከበቡ ያደረጉት”፡ እያለ በጀሮአቸው የሰሙ የዓይን ምስክር የነበሩ እራሳቸው የጦርነቱ ተካፋይ የነበሩት ሎጋ (ወጣት ዘማች) ፊታውራሪ ተክለሃዋርያት እያሉ ፈረንጅ የጻፈውን ማስረጃ በማቅረብ አቶ ነበዩ ስሑል ብልሃቱን የፈጠሩት የትግሬው ራስ አሉላ ናቸው እያለ መጽሐፉ ላይ ጽፎ ለታሪክ ማስተላለፍ  ስመለከት፤ የኔ ዘመዶች ብዙ እንደሚቀራቸው ግልጽ ነው።አብዩ ይንን ሓሳብ በማቅረቡ ከራስ መኮንን የስብሰባ ምሽግ ተሰብስቦ ከስብሰባው የጉርስም ጦር ዘማች ዋና አዛዥ በነበሩት በቀኛዝማች በሻህ ቁጣ ከስብሰባው እንዴት እንዲወጣ እንደተደረገ ፊታውራሪ የጻፉትን በሗላ “አብዩ” በዚህ እልክ ወደ ጣሊያን ምሽጉ ገብቶ ተዋግቶ እንዴት እንደሞተ አሳዛኝ ታሪክ በገጽ 61 በወንድማቸው በፊታውራሪ ተክለ ሐዋርያት ተክለ ማርያም የተጻፈ “የሕይወቴ ታሪክ” በሚለው መጽሐፋቸው ውስጥ  “ወደ ትግራይ ዘመትን” በሚል ንኡስ ምዕራፍ በገጽ 61 ሲያነቡ እንባዎ ይተናነቀዎታል።
                          
                ማጠቃለያ-

    አዲስ አበባን በምጸሐፍ ውስጥ በገጽ 146 “ፍንፍኔ እያለ በመጥራት ለታሪክ ትቶ   የሚያልፈው የኦሮሞዎቹ የመደመር  ፖለቲካ “ነገረ ፈጂ”  ሆኖ የተሾመው ትግራይ የብልጽግና ወኪል “እንደርታዊው ወጣት ነብዩ ስሑል” አብይ አሕመድን ደግፎ አንድ ያደረጋቸው ርዕዮት “የምንሊክ ጥላቻ እና ኦሮሙማ ፖለቲካ እምነታቸው የሚመሳሰል እንደሆነ በግልጽ ማየት የቻላል”። “ሓየሎም” ምናምን እያሉ ምጽዋ ወደብ ሄደው የኢትዮጵን ወታደር የጨፈጨፉና ያስጨፈጨፉ፤ ያዋረዱና ያስገነጠሉ’ የወያኔ ጀኔራሎች/ታጋዮች/ አድናቂዎች ሁላ “ወያኔን እቃወማለሁ እያለ” በዩቱብ ሲንጫጫ ማድመጥ ዛሬም የሚገርም ነው።  ትግራይ ከወ ኔ እስቴች እና ስተሳሰቦች ነፃ ለመውጣት አዲስ አስተሳሰብ ይዞ ለመውጣት አዲስ ትውልድ (ጀኔረሽን) መጠበቅ አለብን። ይህ በሳብቨርሺን የተጠናቀቀ ሳይንሳዊ የሳብቨርዢን ሕግጋት ነው። በመጽሐፌ የትግራይ ብሔረተኞች በአማራ ላይ ያላቸው ጥላቻ ከምን የመነጨ ነው” በሚለው መጽሐፌ  የጠቀስኩት “ሳብቨርዢን ምንድነው?” በሚለው ርዕስ ውስጥ ይመልከቱ።
       አመሰግናለሁ።  
       ጌታቸው ረዳ  (ኢትዮ ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ Ethiopian Semay)   
             

Sunday, June 21, 2020

ኢትዮጵያ ከአማራ ከርሰ ምድር ከፈለቀው ከጫካው አምበሳ ከአሳምነው ጽጌ በኋላ ሌላ ወንድ ታገኝ ይሆን? ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ Ethio Semay) June 21, 2020


ኢትዮጵያ  ከአማራ ከርሰ ምድር ከፈለቀው ከጫካው አምበሳ ከአሳምነው ጽጌ በላ ሌላ ወንድ ታገኝ ይሆን?
ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ Ethio Semay)
June 21, 2020

የኢትዮጵያን ሃቀኛ ጀግኖች እያጣጣላችሁ ከባለተራዎች ጋር ሆናችሁ ነፋስ ወደ ነፈሰው የምትነፍሱ ትንንሽ ጭንቅላቶች ሆይ! ወላጆቻችሁ በመንደር ጋጠወጥ ፖለቲከኞች እየተገፈተሩ ውርደት እንዲቀበሉ ለምን ትፈቅዳላችሁ? መልዕክቴ ከ17 አመት ጀምሮ እስከ 48 አመት ዕድሜ ላለው ለአማራ ወጣት ነው። ለ28 አመት ወላጆቻችሁ ግፍ ተፈጽሞባቸዋል። አማራ ማሕበረስብ በትግሬዎች እና ኦሮሞዎች እንዲሁም በሶማሌ በሲዳማ እና በመሳሰሉ አክራሪ ቡድኖች ምክንያት “ክብር ከሚነካ ስድብ ጀምሮ እስከ የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ ተካሂዶበታል፤ በመርዝ ግድያም ጭምር”!!!ከሰሜን ኢትዮጵያ ከምድር ባሕር (ኤርትራ) ጀምሮ እስከ ጫፍ ደቡብ ኦጋዴን ድረስ ካጫፍ እስከጫፍ ግፍ ተፈጽሞበታል። ግፉ ዛሬም ቀጥሏል”። አማራ ወጣት ከመለፍለፍ አልፎ መሬት አርዕድ ነውጥና ተቃውሞ ማሰማት አልቻለም። ለምን? ዛሬስ ምንድነው ችግራችሁ?

ለዚህ እንቅስቃሴ ባይተዋር አይደለሁም፤ ከጥዋቱ እስከ ማታው ነበርኩበት አሁንም አለሁ።  ይህ ሁሉ ግፍ ሲፈጸም እኔም ሆንክ በጣም እጅግ በጣት የምንቆጠር ኢትዮጵያውያን ለአማራ ሕዝብ ልሳን ሆነን ስንጮህ ጥቂት ነበርን። እንዲያ ሲሆን ብዙ ዘለፋ ተቀብለናል።ሚዲያዎች አፍነውን ነበር (ኢትዮ ሚዲያ፤ ኢሳት፤ ዘሓበሻ፤ ኢትዮ-ፎረም፤ አባይ ሚዲያ…..ወዘተ….)። ልክ እንደ አማራው ማሕበረሰብ እኛም ላይ በ4 መአዝኖች ተከብበን  ድምጻችን ሲታፈን ነበር። 

ግራ በሚያጋባ ሁኔታ “አማራ ነን የሚሉ እራሳቸው በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የጥቃቱ ተዋናይ ሲሆኑ፤ አንዳንዶቹም “ነገር አታባብሱ ውሸት ነው እንዲህ አልተፈጸመም እያሉ” ጥቃቱ እንዳይገለጽ ሚና ሲኖራቸው፤ ይባስ ብሎ እኔም በትግሬነቴ እየዘለፉ “ከአማራ በላይ አማራ ለመሆን የሚፈልግ” እያሉ እዚህ አሜሪካ ያለው  በሕዝብ ሕሊና በበጎ የማይነሱት ላንዴና ለመጨረሻ ጠውልገው የሟሸሹ፤ አማራ ሆነው ጸረ አማራ የሆኑት የኢሕአፓ ድርጅት ጀሌዎች እና የግንቦት 7 ጀሌዎች ሲዘልፉኝ የነበረውን እስከመቸውም አልረሳውም። 

ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ እንዳሉት ለአማራው ጥቃት ዋናው ተላላኪ የሆነው እራሱ የአማራ ምሁር ሲሆን በስም ሲጠሩት “ሆዳም አማራ” ነበር ያሉት።  አማራ ንኝ የሚለው ምሁር የወላጆቹን ታሪክ ሲረገጥ አብሮ ሲጨፍር ነበር። ኤርትራን ያልጨመረ በሴራ የተቀነሰው ሉኣላዊ  የኢትዮጵያ መልክአምድር የታተመ ካርታ የአማራ ወጣቶች እንዲቀበሉት ተደርጎ በከናቲራቸው እና በየፌስቡኩ እንዲሁም በየሱቁ በስፖርት በዓላት ቀን በደረታቸው የሚለጥፉት ካርታ ዛሬም ቅቡልነት አግኝቶ ስመለከት እጅግ ሐዘኔታ ይሰማኛል። 

ያ አልበቃ ሲላቸው አዲስ አባባ ውስጥ “ባንዲራው ይኼ ነው!!” እያሉ የሻዕቢያን ባንዴራ እያውለበለቡ አዲስ አባባ እስፖርት በዓላት ላይ በሰላማዊ ሰልፍ እና የጥምቀትና ቅዱስ ዮሐንስ በዓል ክንውን ላይ ሲያውለበልቡ አይተናል።  

እንዲያ እየቆሰልንም እዚህ አሜሪካ የሚኖሩ በየፌስ ቡኩ የተጣዱ አማራ ነን የሚሉ  የኤርትራ ነፃንት እውቅና አልሰጥም ብሎ የተሟገተው አዲስ አበባ የሚኖር አገራዊው ጀግናው “ጋዜጠኛ ታምራት ነገራን” ስብዕናው የሚነካ ስድብ ሳይቀር እየሰደቡ ለሻዕቢያ ወግነው የቆሙ አማራ ነን የሚሉ ወጣቶችም እያየን ነው። የወጣቱ የሕሊና ዝቅጠት እያሽቆለቆለ ሄዶ፤ የአገሩን ታሪክ ጠንቅቆ ባለማወቁ ሄዶ፤ ሄዶ መጨረሻ ላይ “የኢሳያስ አፈውርቅ ፎቶግራፍ” ከመኖርያ ቤቶቻቸው ግድግዳ ላይ ለጥፈው በፌስ ቡክ በቪዲዮ የሚታዩ ትንንሽ ሕሊናዎች ብዛት ባለው ቁጥር በዚህ ትውልድ ለማየት በቅተናል። 

ባጭሩ ለአማራ ውርደት የመጀመሪያው ተጠያቄ አጥቂዎቹ ሳይሆኑ ከአጥቂዎች ጋር ቆመው የሰቆቃው ገመድ አጥባቂ የሆነው ዛሬም ከበሽታው ያልተፈወሰው በኔው አባባል “አለቅላቂ አማራ” በፕሮፌሰር አስራት አባባል ደግሞ  “ሆዳም አማራው” ነው።

ዛሬ  ለ28 አመት የአማራ ወንድ ስንፈልግና ስናፈላልግ በ2012 ዓ.ም  አንድ ብርቱ በላይ ዘለቀና ቴዎድሮስ የሚመስል፤ የወንድ ሚዛን ልክ የለበሰ፤ የአማራ ጠላቶችን ያስደነበረ  እንደ መስቀል ወፍ ብቅ ብሎ ድንገት ስለተሰወረው ትንግርተኛው ብ/ጀኔራል አሳምነው ጽጌን ለምን ተገደለ? አምና ስለ አሳምነው ጽጌ ሰፊ ማብራርያ ጽፌ አሳትሜአቸዋለሁ። ዛሬ ከዚህ ቀጥሎ የማቀርብላችሁ ማስረጃዎች አሳምነው ጽጌ ከመሞቱ በፊት በዘሓበሻ ቀርበው የነበሩ በአሳምነው ጽጌ አንደበት የተነገሩ እውነተኛ አውደዮ/ድምጸ ቃል/ እና በአሳምነው ላይ ሲፈጸሙ የነበሩት ሴራዎችን አቀርብላችኋ  ለሁ።

የአሳምነው ሞት አማራ ካሁን ወዲህ ያያል ተብሎ የማይገመት እጅግ ክብርና በጣም ደፋር የሰው አምበሳ ማጣቱ ሳስበው ድሮ አማራን በሚጠሉ በአክራሪ ትግሬዎች፤ አሁን ደግሞ አማራን በሚጠሉ አክራሪ የኦሮሞዎች መንግሥት እጅ መውደቁን ስመለከት አሳምነውን የሚተካ ወንድ በታጣበት ወቅት የአማራ ዕጣ ፈንታ ምን እንደሚሆን እጅግ ያሳስበኛል።  

አሳምነው በህይወት እያለ ለምን በአምባቸው ተገመገመ?  ገዱ አንዳርጋቸው ወደ አዲስ አባባ ሄዶ “ቀነኒሳ ሆቴል ለ15 ቀን ተቀምጦ የሥራ ስንብት ለምንስ ጠየቀ”? የሚሉት አስፈላጊ አንኳር ጥያቄዎችን እንመልከት።

የአሳምነውን ቃል እንደዋዛ ለረሳችሁት ሁሉ በድጋሚ ላስታውሳችሁ። እያንዳንዷን ቃል ሕጋዊነትዋን ጠንቅቃችሁ ተረድዋት። እንዲህ ይላል፤

ለመረጋጋት እና እንደ አማራ ለመቆም በምናደርገው ትግል  ውስጥ የሃይማኖት አባቶች ወጣቶች ሴቶች የፀጥታ ሃይሎች አንድነታችንን የሚፈታተን ነገር ሲመጣ በንቃት መታገል አለብን፡ መሞት አለብን! ።” (አሳምነው ጽጌ)

ይህ ንግግር ሕጋዊ ነው። ተግባራዊም አድርጎታል።፡በምንም መለኪያ ሕግን ሞራልን የሚጻረር ንግግር አይደለም። ይህ ሕጋዊ ንግግር ያስደነበራቸው በአብይ አሕመድ የሚመራው የኦሮሞ መንግሥት እና በትግሬዎች መንግሥት የተቀናጀ “ገዳይ ቡድን” አሰማርቶ አሳምነውን ለማሰር ወደ ባሕርዳር ሲከንፍ በአልሞት ባይ ተጋዳዩ አሳምነው ጽጌ እጅ የወደቁ ወላዋዮችን ጨምሮ እራሱንም ወደ የማይቀረው ዓለም ይዞ የሄደ ክስተት ተከሰተ።

እንግዲህ አስታውሱ፡ “ለአፓርታይዱ ክልል” አዲስ አስተዳዳሪ ሆኖ የተሾመው “ዶ/ር አምባቸው መኮንን” እና አሳምነው ጽጌ መግባባት እንዳልነበራቸው በወቅቱ ሲወራ እንደነበር እናስታውሳለን። ጀኔራሉ (አሳምነው) ከመሞቱ በፊት የዘሓበሻው ሽክሹክታው ፕሮግራም እንዲህ ብሎ ዜናውን አስደምጦን ነበር።ነበረ የተበሰለውም እዚህ ልግለጽ፡

"በውስጥ አዋቂዎች አነጋግረን እንዳገኘነው መረጃ በዶ/ር አምባቸው እና በብ/ጄ አሳምነው ጽጌ መካከል ምንም ችግር ባይኖርም ዶ/ር አምባቸው ግን ብ/ጄ/አሳምነው ጽጌን ከሰሜን ሸዋ እና ከከሚሴው ጥቃት በሗላ ቁጭ አድርገው ገምግመዋቸዋል፤ ተብሏል። ለምን ገመገሙዋቸው? ይላል ዘሐበሻ (ግምገማ የተባለው በዘሓበሻ ዘገባ በተቃራኒው ወደ መደምደሚያ አቀርባለሁ)

…ነገሩን ከሥር እንመልከተው፡ ብ/ጄ አሳምነው ጽጌ የደህንነትና የሰላም ግንባታ ቢሮ ሓላፊ ሆነው እንደተሾሙ በርካታ አመርቂ ሥራዎችን መስራታቸው እሙን ነው።በተለይ በተሾሙበት ወቅት በሰሜን ጎንደር እና ዓፋር ክልል ባቲ አካባቢ ታጣቂዎች ችግር በፈጠሩበት ወቅት፤ ከነዚህ ሁሉ በስተጀርባ በተለይም የህወሓት እጅ እንዳለበት በግልጽ በሚዲያ (በዜና የማሰራጫዎ ማእከሎች) በመናገር ይታወቃሉ። በተለይም በሰሜን ጎንደር ገንዳ ውሃ በነበረው ግጭት ታጣቂዎቹ በገበሬዎች ላይ ሲቶኩሱ “ፀረ አየር” መቃወሚያ መሳሪያ ታጥቀው እንደነበር መግለጻቸው ይታወሳል። “በወቅቱ በሰሜን ጎንደር በነበረው ግጭት ከመከላከያ ጋር በቅርበት እየሰራችሁ ነው ወይ?” ተብለው በጋዜጠኞች ሲጠየቁ “ከመከላከያው ጋር በላይኛው ደረጃ እየተሰራ መሆኑን አላውቅም” ማለታቸውን በወቅቱ ፓርቲያቸው ውስጥ ያሉ ወገኖች እና እንዲሁም መከላከያዎችን አስደንግጦ ነበር።
አሳምነው እንዲህ ብለው ነበር”

“በማንኛውም ቦታ እና ጊዜ ይህንን ክልል የጦርነት አውድማ እና የችግር ቀጠና አድርጎ እኛ እንደ አማራ አንድ ላይ ቆመን እንደ አማራ አስበን፤ለኢትዮጵያ ወይንም ለአገር የምናበረክተው አስተዋጽኦ እንዳናደርግ እንደሆነ መታወቅ አለበት። ይህንን አስቡበት።” ሲል ተናግረው ነበር፡

አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በሥልጣን ለይ በነበሩበት ጊዜ ብ/ጄ አሳምነው ጽጌ ለጋዜጠኞች ሲሰጥዋቸው በነበሩ ምላሾች ደስተኛ አልነበሩም። በዚህ ጉዳይም ብ/ጄ አሳምነው ንግግራቸውን እንድያስተካክሉ ተነግሯቸው ነበር ። በሚፈጠሩ ግጭቶች ላይም ምንም ማጣረት ሳይደደረግ በሌሎች ላይ በጋዜጣ መግለጫም ሆነ በጋዜጣዊ ቃለ መጠይቅ ጣት መቀሰር እንዲያቆሙ እና ፖለቲካዊ በሆነ መንገድ ብቻ መግለጫዎች እንዲሰጡ ተነገሮአቸው እንደነበር ሹክ ብለውናል።” ብሎ ነበር የዘሓበሻ ዜና።
ልብ በሉ፤ ገዱ አንዳርጋቸው የተባለው የአብይ አሽከር አሳምነው ጋር የነበረው አለመጣጣም አንድ በሉ። ከዚህ በታች ያለውን ተመልከቱ።

በወቅቱ በተለይም  በጎንደር ግጭት ሲፈጠር አሳምነው ጽጌ መግለጫ ሲሰጡ የነበረውን ቀርቶ የአማራ ፖሊስ ኮሞሽነር ዘላለም ልጃለም መግለጫ እንዲሰጡ በእነ ገዱ አንዳርጋቸው ተደርጎ እንደነበርና በዚህ የተነሳ ገዱ አንዳርጋቸው ከነ አሳምነው ጋር አለመስማማት ተፈጥሮ ነበር። በኋላ ግን የአሳምነው ሃይል  እያየለ መጣ። ገዱ ሥልጣናቸውን ለመልቀቅ ወደ አዲስ አባባ በመጡበት ወቅት በቀነኒሳ ሆቴል ሲቀመጡ የሥልጣን መልቀቂያቸው ምክንያቶች አንዱ “የጎበዝ አለቆች አስቸገሩኝ ፤ እነ አሳምነው ጽጌ አላሰራም አሉኝ” የሚል ነበር።
ገዱ ይህንን ሃሳባቸውን እንዲቀይሩ 15 ቀን ቢሰጣቸውም አሻፈረኝ ብለው ሥልጣናቸውን ለቀዋል። 

ገዱ ሥልጣን ከለቀቁ በኋላና ዶ/ር አምባቸው ክልሉን መምራት ከጀመሩ በኋላ አሳምነው ጽጌን ተክቶ በአሳምነው ቦታ መግለጫ እንዲሰጡ በእነ ገዱ አንዳርጋቸው ተሰይመው የነበሩት የፖሊስ ኮሚሽነር ዘላለም ልጃለምን ተክተው በምትካቸው የግንቦት 7 አመራር አባል የነበሩት የመቶአለቃ አበረ አዳሙ ከስዊድን አገር መጥተው የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር  ሆነው ተሾሙ። እሳቸው ከተሾሙ ወዲህ በክልሉ ስለሚከሰቱ ግጭቶች ጋዜጣዊ መግለጫ የሚሰጡ የሰላም እና የመረጋጋት ም/ሃላፉ የሆኑት ኮ/ል አለበል አማረ ናቸው።” ይላል ዘሓበሻ።

የኔን አስተያት ልጨምርበት፡ ወሬ አፈንፋኞቹ ከሚሴ ላይ ጥቃት ከመፈጸሙ በፊት  የተሳሳቱት አሉባልታ ነገር አለ። አሳምነውን የሚወነጅሉበት ፤ በእነ ጌታቸው አሰፋ እየሰለጠነ የነበረው ሰሜን ሸዋ አካባቢዎች በኦነግ እስላማዊና “ኢንተርሃሙዌ’ አክራሪ ኦሮሞዎች ከ5 ወራት በፊት ከሚሴ ላይ ጥቃት ከመድረሱ በፊት የአማራ ክልል አካባቢዎች በተለይ የሰሜን አማራ ክልል አካባቢ፤ በኦነግ ስም የሚንቀሳቀሰው በወያኔው ጌታቸው አሰፋ የኋላ ድጋፍ ሰጪ የሚያንቀሳቅሰው ሃይል አሰማርቶ እስከ ላውንቸር ተኳሾች ድረስ እያሰለጠነ እንደሚገኝ እና አሰልጣኞቹም የትግርኛ ተናጋሪዎች እንደሆኑ የሚያሳይ በሰነድ በአንድ የደህንነትና የሰላም መረጋጋት ቡድን የቀረበው ለደህንንቱ ሃላፊዎች ቀርቦ “ተቃጥሎ ቆሻሻ መጣያ ተጥሏል”  ብሎ አምባቸው መኮንን አሳምነውን ገምግሞት ነበር እያሉ በውሸት ያልሆነውን ወሬ “እንደ ውሻ አፍንጫ” እያፈናፈኑ (ምናልባትም እንደ ማፈሪያው ብ/ጄ/ል ተፈራ ማሞ የመሳሰሉ ሴረኞች ሲያፈንፈኑት የነበረውን ውሸት ሊሆን ይችላል) ሲነገር እንደነበር ይታወሳል። እንደምታውቁት አሳምነው ከማንኛቸውም የክልሉ ባለሥልጣን ከታች እስከ ላይ ድረስ እና እንዲሁም የደህንነትና የሰላም መረጋጋት አባሎች በበለጠ የአማራ ጥቃት የማይፈልግ እና “ጸረ ኦነግና ጸረ ወያኔ” መኖሩን እየታወቀ እንዲህ ያለ ዘገባ አሳምነውን ለማሳጣት፤ አሳምነው ሆን ብሎ “ዘገባውን አፍኖት ነበር” ብለው እየዋሹ ስትሰሙ እንዲህ ብለው የሚዋሹት እነማን ቡድኖች እንደሆኑ በቀላሉ  የአሳምነው ጽናት እና የሌሎቹ ጽናት ገምግማችሁ በቀላሉ ልትደርሱበት ትችላላችሁ። ጀግና ሁሌም ምሳር ይበዛበታል። እኛ ሁሉ 28 አመት ወያኔን ስንታገል የወያኔ አርበኞች ሲሉን አልነበረም? አሳምነውም ላይ የደረሰው እንደዚያ ነው።

እኔ የጨነቀኝ ‘ኢትዮጵያ ከአማራ ከርሰ ምድር ከፈለቀው ከጫካው አምበሳ ከአሳምነው ጽጌ በኋላ ሌላ ወንድ ታገኝ ይሆን? የሚለው ጥያቄ ሳቀርብ “አሳ ነባሪ” ተብሎ የውስጥ አርበኛ መጠሪያ ስም በኢሳያስ  አፈወርቅ ዕውቅና የስለላ ስም ተሰጥቶት የነበረው አብይ አሕመድ ያኔ አስመራ ውስጥ ከነበረው የኦነግ አመራር  ከኮለኔል ገመቹ ጋር ምስጢሮችን በስልክ ወደ አስመራ እየደወለ (እራሱ ኮ/ል ገመቹ  እንነጋገር ነበር ብሎ ተናግሯል- ኦነግን በገንዘብም ጭምር ይረዳቸው ነበር) ምስጢሮችን ሲያስተላልፍ የነበረው “ባንዳው አብይ አሕመድ” (አሳ ነባሪ) ዛሬ ሥልጣን ላይ ወጥቶ አብን የተባለው የወጣት ቡድን መሪዎችን እየተጎተቱ ወደ እስር ሲገቡ ባሕርዳርም መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤ የመሳሰሉ እየተገፉ ወደ እስር ሲገቡ ወጣቱ ይህንን እያየ ምንም አመጽ ባለማስናሳቱ ስታዘብ አሁን ያለው ወጣት እውን የአማራ “ከርሰ ምድር” የወለደቺው ከጫካው አምበሳ ከአሳምነው ጽጌ በኋላ ሌላ ወንድ ታገኝ ይሆን? የሚል ጥያቄ ጭሮብኛል። ዝም! በቃ ዝም! በቃ እንዲህ መቀለጃ ሆናችሁ ልትቀጥሉ ነው?፡የተረጨባችሁ አደንዛዥ ውሃ ምን ይሆን? ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ Ethiopian Semay)

Wednesday, June 17, 2020

የቀዳማይ ወያኔ መስራች የብላታ ሃይለማርያም ረዳ ልጅ የሆነው ካሳ ሃይለማርያም አባቱ ያስተማሩት የሸዋ አማራ ጥላቻው ከትግርኛ ወደ አማርኛ ልተርጉምላችሁ እነሆ! ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay) June 17/2020



የቀዳማይ ወያኔ መስራች የብላታ ሃይለማርያም ረዳ ልጅ የሆነው ካሳ ሃይለማርያም አባቱ ያስተማሩት የሸዋ አማራ ጥላቻው ከትግርኛ ወደ አማርኛ ልተርጉምላችሁ እነሆ!
ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)
June 17/2020
ጉዳዩ ሽምግልና ተልዕኮ ይዘው ወደ ትግራይ/መቀሌ ሄደዋል ስለተባለው ጉዳይ በፌስ-ቡክ የጻፈው ነውረኛ ጽሑፉን ይመለከታል። 

ወደ ትርጉም ከመሄዴ በፊት ስለ አባት እና ልጅ ትንሽ ልበል። ብላታ ሃይለማርያም ማናቸው ለምትሉ ባጭሩ ከርዕሱ እንደምትመለከቱት የቀዳማይ ወያኔ መሪ የነበሩ ናቸው። የብላታነት ማዕረግ ከጣሊያን የተሰጡት ሃይለማርያም ረዳ ብዙ ተመራማሪዎች እንደጻፉት በዘመነ አፄ ሃይለስላሴ ከሽፍታነት እስከ የጉልተኛው ሥርዓት ተሿሚና አስፈጻሚ ሆነው ገበሬውን እንዳላስከፉት ሁሉ በሗላ ትግራይ ውስጥ የተነሳው የገበሬዎች አቤቱታን “ውሻ በቀደደው ጀብ ይገባበታል” በሚለው በሚገርም ብልጣብልጥ ስልት ተጠቅመው “እነዚህ ሽዌዎች ምን አድርጉ ነው የሚሉን?!” በሚል ብሔረተኛነት ባጀበው ስሜት በመነሳሳት “ሥልጣን ከትግራይ እጅ ለምን ወጣች” በሚል ማንኛውም አክራሪ የሆነ ብሄረተኛ እንደሚከተለው ሁሉ እሳቸውም “ወደ አጼ ምኒሊክ ዘመን ወደ ኋላ ተመልሰው ስልጣን ከትግራይ እጅ ለምን ወጣች፤ በሚል ቀደም ብሎ በነበራቸው የአማራ (ሽዋ) ጥላቻቸውን በማጠናከር ብጤዎቻቸውን በማስተባባር የድሃውን እውነተኛ ብሶት ‘ጠልፈው’ ወደ “አማራ እና ትግሬ” ቅራኔ በማሳደግ የቀዳማይ ወያኔን አመፅ በመምራት ቀዳሚ ስፍራ የያዙ ናቸው።

ብላታ ሃይለማርያም ቀዳማይ ወያኔን በመሩበት ወቅት የተከተሉት ማኒፌስቶ (አዋጅ) እጅግ ከከረረ አምባገነናዊነት አልፈው ከአንድ ‘የተዋህዶ ክርስትያን አማኝ’ የማይጠበቅ ማኒፌሰቶ አውጥው እውን ያደረጉ ናቸው። ምናልባትም ለማታውቁት አዋጁ እዚህ ልጥቀስላችሁ እና ወደ ልጃቸው እንሻገራለን፡
ያወጁትን የጊዜያዊ መንግሥት መተዳደሪያቸውን ስንመረምር ከ6 አመት በፊት ያቀረብኩላችሁ ዛሬም ደግሜ ላቅርብላችሁ። እንዲህ ይላል፤

የምንከተለው ሃይማኖት (የቀዳማይ ወያኔ ጊዜአዊ መንግስት) ሃይማኖታችን (የአፄ ዮሐንስ)፤ገዢያችን (እየሱስ ክርስቶስ) ፤ ጠባቂያችን (ሃይለማርያም ረዳ)፤ባንዴራችን (የኢትዮጵያ) ነበር ያሉት። እንዲህ ይላል። (ገረብ ማለት ጅረት/አካባቢ ማለት ነው) (ከ12 ፈለግ/ጀረቶች ከሚዋሰነው ሕዝብ የተውጣጣ የጊዜያዊ መንግሥት ተወካዮች ማለት ነው።)፤

(አዋጅ ስማ! አዋጅ ስማ!
በትግርኛ፤ ከታች በአማርኛ ትርጉም ይከተላል።
“…ስምዑ፤ስምዑ!
አዋጅ ሃይለማርያም አዋጅ ገረብ እዩ
ገዛኢና _ እየሱስ ክርስቶስ፤
ሓላዊና _ ሃይለማርያም፤
ዳኝነትና _ ናይ ዓሰርተ ክልተ ገረብ፤
ባንዴራና _ ባንዴራ ኢትዮጵያ፤
ሃይማኖትና _ ናይ ሃፀይ ዮውሃንስ
ህዝቢ ትግራይ ወያነ ተኸተል!
ገረብ መንግሥቲ ተቐበል!”
አዋጅ! አዋጅ!
ይህ አዋጅ የሃይለማርያም እና የገረብ አዋጅ ነው።
ገዢያችን_ እየሱስ ክርስቶስ፤
ጠባቂያችን_ ሃይለማርያም፤
ዳኝነታችንም_ ከ12 ገረብ ተወጣጥተው የወሰኑት የፍትሕ ዳጅነት ይሆናል።
ባንዴራችን_ የኢትዮጵያ ባንዴራ ነው።
ሃይማኖታችንም _ የአፄ ዮሐንስ ነው።
የትግራይ ሕዝብ ሆይ! ወያኔን ተከተል!
የትግራይ ሕዝብ ብቸኛ የሆነው የገረብን መንግሥት ተከተል!

በማለት ‘በአንድ እየሱስ፤ አንድ ሕዝብ፤ አንድ ድርጅት፤ አንድ ሃይማኖት፤ አንድ መሪ፤” የሚከተል “የገረብ መንግሥት” ተከተል ሲል አውጇል።

የዛሬ የወያኔ ትግሬዎች “ሸዌዎች አንድ መንግሥት፤አንድ ቋንቋ፤ አንድ ድርጅት፤አንድ ሕዝብ፤አንድ ሃይማኖት” ይላሉ ሲል “በፀረ ሸዋነት ሕሊና የተቀረጸው” የብላታ ልጅ ደግሞ ሸዌዎች ሊገዙን ፈልገው አፈር አስበላናቸው፤አሸንፈውን ነበር ዛሬ አሸንፍናቸው፤ ዲሞክራሲ ከትግራይ ሕዝብ አልፎ ለሌሎቹ ተርፎ መብታቸው ተከብሮ በልማት ጎዳና እየተጓዘ ይገኛል” ይላል ልጃቸው። እሱ አጥብቆ በሚጠላት በሸዋ አገር ገበሬዎች ታርሶና ተፈጭቶ የበቀለ የሸዋ ምግብ እየተመገበ “ቀዳማዊ ኃይለስላሴ ዩኒቨርሲቲ አካውንታንት” የተማረው ልጃቸው። እኔ ይህንን ስታዘብ ‘ኢትዮጵያ አገሬ ሆይ ይህንን እየሰማሽ ምን ብታደርጊ ይሻልሽ ይሆን?” እላለሁ።

በብላታ መሪነት የጸደቀው አዋጅ ከላይ ያለው አልበቃ ብሎ’ የሚለተለውን አዋጅ ተግባሪ እንዲሆን ምክር ቤቱ (ገረብ ዓረና) ተጨማሪ አዋጅ አከለበት፤ -

ድሮ በሃይለስለሴ ዘመን አንድ ሞገደኛም ሆነ አንድ ሰው ወደ ሕግ ለማቅረብ አንሂድ ስትለው “በሃይለስላሴ በሕግ አምላክ” ሲባል ነበር። የመሳፍንቶች እና የነገሥታት ዘሮች የሚበዙበት እና የሚወለዱበት አካባቢ እንደርታ አውራጃ በቀዳማይ ወያኔ ለንጉሥ ሃይለስላሴ አንገዛም በማለት “12 ገረብ” (አስራ ሁለት ጅረት) በሚል ስም ጊዜያዊ የአማጽያን መንግሥት ሕዝባዊ ባይቶ/ጉባኤ/አሰምብሊ) መስርቶ በነበረበት ወቅት “ዝባን ገረብ” (በገረብ ሕግ አምላክ) በማለት አንድ ሰው እንድትቆም ተማጽኖህ ካልቆምክ፤ ወይንም “በገረብ ሕግ ዳጅነት ላለመዳኘት አምቢ ካለ” የገረብ ሕግ ረግጦ እንደሄደ ተቆጥሮ የሚከተሉት በሕግ የጸደቀ የገረብ አዋጅ ይፈረድበታል።
እንዲህ ይላል፤-

የቀዳማይ ወያኔ የእርምጃዎች መግለጫ፤

(1ኛ)-የገረብ ሕግ ያላከበረ ታምሞ የአልጋ ቁራኛ በሆነበት ወቅት አግዚአብሔር ይማርህ ተብሎ በማንኛውም ጐብኚ እንዳይጎበኝ፤

(2ኛ)- በሐዘን ጊዜ ጥናቱን ይስጥህ ተብሎ እንዳይጠየቅ/ለልቅሶ እንዳትደርሱት

(3ኛ)-ከሕዝብ እና ማሕበራዊ ግንኙነት እንዲገለል። የሚሉ ነበሩ።

በዚህ አጋጣሚ

አፄ ዮሃንስም አንድ ሃይሞኖት ለማድረግ ሞክረዋል። ፕሮተስታንት ወይንም እስላም የተባለ ወደ ኦርቶዶክስ ካልተጠመቀ ከትግራይ ግዛቴ ለቃችሁ ወደ ሌላ አገር ሂዱ ብለው አውጀዋል። መረጃየን ላቅርብ፡
“Internal Rivalries and Foreign Threats (1869-1879) Edited by Sven Rubenson page 6 ስንመለከት አሰገኸይ የተባሉ የቤተክሕነት ምሁር የሆኑ ትግሬ ሰው “የአንቶይን ዲ አባዲ” የተባለ አውሮጳዊ ወዳጅ/አስተርጓሚ/ዜና ነጋሪ/አገር አስተዋዋቂ የነበሩ በAssegehen to Antoine d’ Abadie, 12,Feb, 1869 በሚል ርዕስ አሰገኸኝ ለ ‘ዲ አባዲ’ በግዕዝ ርዕስ የጻፉትን ደብዳቤ እንዲህ ይላል።

“ትብጻሕ ሃበ አቶ አንደጦንዮስ ዘአባዲያ ሙሑረ ጥበባት…….” እያሉ ሰፋ ያለ በግዕዝ ሰላምታቸውን ካቀረቡ በኋላ፤ ወደ አማርኛ በመግባት፤

“ታሪክ ዘደጃዝማች ካሳ አባ በዝብዝ የትግሬ ንጉሥ እንዲህ ነው። አባ ተክለ አልፋ የሚባሉ መነኩሴ ዘደብረ በርበሬ ነበሩ፡ ቅባት ናቸው፡ ያባ በዝብዝ የንስሐ አባት ወደ ተዋህዶ ሃይማኖት ግቡ ብሎ ተማጠናቸው። አባ ተክለ አልፋም፤ በስመ አብ ወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ አምላክ ትርጓሜው እንዴት ነው፡ ብለው ጠየቁት። አላውቅም አለ። ደጃዝማች ካሳም ደንቆሮ ነህ፡ብለው .. የነብስ አባታቸውን ገረፉት።

፪ኛ ታሪክ፤

ደጃዝማች ካሳ አባ በዝብዝ በትግሬ ያለ ቅባት ሁሉ ወደ ሃይማኖቱ ይግባ። እምቢ የሚል ሁሉ በምገዛው አገር አይኑር አሉ። በትግሬ ያሉ ቅባቶች ሁሉ ወደ አባ በዝብዝ ሃይማኖት ገቡ፡ አባ ተክለ አልፋ ግን ገዝተው ወደ ታላቅ ገደል ወጡ፡ ያባ በዝብዝ አጎት ደጃዝማች አርአያ ከብዙ ጦር ጋር ተከተለው፡ከገደል አወረዱዋቸው፤በነፍጥም እንደመቱዋቸው፤ፈርተው ከገደል ወረዱ፡ ግዝታቸውንም ፈቱ፡ ወደ ሌላ አገርም አባ ተክለ አልፋ ተሰደዱ።” (( Internal Rivalries and Foreign Threats (1869-1879) Edited by Sven Rubenson page 6 ምንጭ ከላይ የጠቀስኩት መጽሐፍ ገጽ 6 )

የብላታ ሃይለማርያም ኮቴ የተከተሉ ወያኔዎችና ልጃቸው የሸዋ ነገሥታት ጸረ ትግሬ ስለሆኑ ፤ኢትዮጵያን በአሃዳዊ ስርዓት ገዝተዋታል፤ እያሉ አማራ የሚሏቸውን ነገሥታት ሚዛን ባልጠበቀ ዘለፋ እና ውንጀላ ሲወነጅሏቸው፤የራሳቸው የትግራይ መሳፍንት እና ነገሥታት እና ቀዳማይ እና ዳግማይ ወያኔ ግን ከላይ በማስረጃ እንዳቀረብኩላችሁ ታሪካቸውን እየሸሸጉ በየሚዲያቸው ሲያብዱ ሌላውን ሲወነጅሉ እያዳመጧችኋቸው ነው። እነሆ አሁን የትግራይ መሳፍንቶች እና ነገሥታት ሥርዓት እውነታው በመረጃ ይዛችሁታል። ሌላም ስትፈልጉ “ደቂቀ ተወልደ መድህን” የሚለው በ2005 ዓ.ም ያሳተምኩትን የአማርኛ መጽሐፌን አንብቡ እና ትግሬዎች የተለየ ሃይማኖት ለያዘ የትግራይ ሰው ምን ዓይነት ፍዳ ያደርሱበት እንደነበረ ዓድዋ ላይ የታየው ፍዳ አንብቡ።
እንቀጥል።

ካሳ ሃይለማርያም የብላታ ሃይለማርያም ልጅ ነው። አማርኛ ከትግርኛ በበለጠ አሳምሮ ይናገራል (አማርኛ የመጀመሪያ ቋንቋው ነው በሚያሰብል ሁኔታ ይናገራል)። የተኮላተፈ ትግርኛ ተናጋሪ ሲሆን፤ አማርኛ በሚነገርበት አገር ተሞላቅቆ ያደገ ፤ ወላጆቹ ከእንደርታ አካባቢ ቢሆኑም እንደ ብዙዎቹ የእንደርታ ተወላጆች ልሳናቸውን እየተው አንዳንድ ትግሬዎች “አስማሪኖ/አስመርኛ/ ብለው በሚጠሩት ኤርትርኛ እና የትግሬ “አሽዓ” ኛ በሚመስል የትግርኛ ልሳን ለመናገር የሚሞክር፤ ከዚያም አልፎ የወላጅ አባቱን መጽሐፍ በዚህ ልሳነ ቅኝት እንዲጻፍ የፈቀደ ነው”።

ስለ ልጁ ከንቱ የሸዋ ጥላቻው ለወደፊቱ በግምገማ ስለማቀርበው ለጊዜው እናቆየውና አባትየው ብላታ ሃይለማርያም ረዳ ከሞቱ በኋላ ብላታ የጻፉት ሰነድ እና አደረጉት የተባለው ቃለመጠይቅ አሜሪካ አገር በዋሺንግተን ዲሲ ኗሪ በሆነው በኩር ልጃቸው (በመጀመሪያ ልጃቸው) በሆነው በካሳ ሃይለማርያም ረዳ የበላይ ሃላፊነት አገር ውስጥ የታተመ “ገረብ ዓረና ወያነ ትግራይ 1933-1939 ዓ.ም” የሚል ባለ 502 ገጽ የያዘ የትግርኛ መጽሐፍ ከሁለት አመት በፊት (በ2010 ዓ.ም) መቀሌ ከተማ ተመርቆ ለትግራይ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች የታሪክ ጥናት መማርያ (ካሪከለም) እንዲሆን እራሱ መቀሌ ድረስ በመሄድ በስጦታ ተሰጥቶ የትግራይ ታዳጊ ወጣት ተማሪዎች በሸዋ ጥላቻ ታንጸው እንዲቅፁበት የተበረከተ መጽሐፍ ነው።

ይህ መጽሐፍ በግዥ መልክ እንዲልክልኝ ካሳን አነጋግሬው “እሺ ብሎ የኔን አስፈላጊውን አድራሻ ከወሰደ በኋላ” ብደውል ብደውል መልእክትም ብልክለት “ውሃ ውስጥ እንደገባች ዓይጥ ድምፅ ሊሰጠኝ አልፈለገም” ከዚያም ዘመዶቼ ከትግራይ እንዲልኩልኝ አድርጌ መጽሐፉ ያገኘሁት በቅርብ ሲሆን በመጽሐፉ ዙርያ የምሰጠው ግምገማ እስክሰጥበት ድረስ እስከዛው ድረስ ለዛሬ መነሻ የሆነኝን ይህ የብላታ ልጅ በፌስቡኩ የለጠፈው አንድ ወዳጄ እንድመለከተው የላከልኝን ከአባት ወደ ልጅ ተላልፎ አላባራ ያለው በሸዋ ያጠነጠነ ጥላቻውን “ድሮ አሸንፈውን ነበር ዛሬ እኛ አሸንፈናቸዋል እነሆ አንድ ባንድ ሆነናል!” የሚለውን የካሳ ሃይለማርያም ቂም ቋጣሪነት ከትግርኛ ወደ አማርኛ የተረጎምኩላችሁን እንድታነቡት እነሆ። መጀመሪያ አማርኛው ከዚያም ለሰነዱ ተያያዢነት እንዲመች ወደ መጨረሻ የካሳ ሃይለማርያም የትግርኛውን ጽሑፍ አያይዤዋለሁ።

ይህ ጽሑፍ የጻፈበት መነሻው፤ ሰሞኑ ወደ መቀሌ ተጉዘዋል የተባሉት “ሽማግሌዎችን” አስመልክቶ ከሸዋ ጋር እያያዘ እየተቸበት ጽሑፉ የእንደርታዎቹ የወላጆቹ የትግርኛ አጻጻፍ ዘይቤ ሳይሆን ኤትርኛም፤ ዓረብኛ ቃልም የተቀላቀለበት “የዓድዋ ፤ አክሱም ፤ ሽረ” ኗሪዎች የሚናገሩትና የሚጽፉት “መለስ ዜናዊና ጓዶቹ ያስተማሯቸው” ወያኔዎች ከበረሃ ጀምረው በበላይነት የተጠቀሙበት የትግርኛ አጻጻፍ ዘይቤ ነው የተጻፈው ፡ ስለዚህ ለአማርኛ አንባቢ እነሆ ተርጉሜዋለሁ።


እርቅና ሽምግልናን አስመልክቶ እኛ እና ሸዋ ባለፉት 130 ዓመታት እኩል አንድ ባንድ ነበርን ፤የዛሬው ሽምግልናስ ምን ይሆን?

የሸዋ ነገሥታት መፈናፈኛ ሲያጡ እኛን (ትግሬዎችን) ለማጥፋት ተንኮል ሲጠነጥኑ ሁሌም የሚሮጡት “ወደ ሽምግልና ነው”። ሁሉም የሽምግልና ጥያቄዎች የሚቀርቡት መነሻቸው ከሸዋ ነው። በ1881 ዓ.ም ንጉሠነገሥት አፄ ዮሐንስ የማህዲን ወረራን ለመመከት ሲዘጋጁ ፤ ምኒልክና አምሳያዎቹ በአፄ ዮሐንስ ላይ ተንኮል እየሰሩባቸው መሆኑን ሲያውቁ ምኒልክን ሊቀጡት ወደ ሸዋ ለመሄድ ተዘጋጅተው ነበር። ምኒልክ ይህንን ሲያውቅ ተሎ ተሯሩጦ “ጌታዮ ሆይ ይማሩኝ” ብሎ በጥር 10/ 1881 ዓ.ም ከእንጦጦ የጻፈው ደብዳቤ አጎቱን ደጃዝማች ዳርጌ ሽምግልና አስልኮ (እንዳይቀጡት) አጃጃላቸው።በዚህ ተጃጅለው ምኒልክን ከመቅጣት ይልቅ ፊታቸውን ወደ መተማ ዘመቻ አዞሩ።

ተንኮለኛው ምኒልክ ግን ሴራው እያጠነጠነ መነኮሳት ያልሆኑ ግን “መነኮሳት” አስመስሎ ዕርቅ እያለ አስሰርጎ በማስገባት በሁለተኛው ወር ንጉሳችንን አስገደለብን። “በሽምግልና ስም አሸነፉን!”

ከ100 አመት በኋላ በ1983 ዓ.ም የደርግ ስርዓት ወደ መቃብሩ ሊወርድ ሲቃረብ በሁለት መንገዶች ወደ ዕርቅ ተሯሯጠ። ባንድ በኩል መንግሥቱ ሃይለማርያም እራሱ አሜሪካኖችን “አስታርቁኝ” ብሎ ጠየቀ። ከዚየም መስፍን ወልደማርያም የሚመራው “የሽማግሌዎች” ቡድን ጊዮን ሆቴል ውስጥ “የሰላም አማራጭ” የሚል ሰነድ አዘጋጅተው ታችና ላይ ይሯሯጡ ነበር።

ሽምግልናውን በሚመለከት እስከ ጣሊያን ድረስ በመሄድ የዳግማይ ወያኔ መሪዎች ተወያይተውበታል። ሲወያዩም ላንድ አፍታም ቢሆን ዘመቻችን (ትግላችንን) ሳናቆም ቀጠልን። ከዚያም ለመቶ አመታት በጫንቃችን ላይ ዝጎ (ሻግቶ) የነበረው ሰርዓት ከስሩ ነቅለን ጣልነው። እኛ አሸነፍናቸው! አንድ በአንድ ሆንን!

በ1881 እነሱ በተንኮል በለጡንና ንጉሣችንን ነጠቁን። በ1983 ዓ.ም ግን ከገራገርነታችን ተምረን ልባም ሆን እና እኛ አሸነፍናቸው።መሪያቸውም እንደ “አያቶቹ” አገር ጥሎ ፈረጠጠ። የዛሬዋ ሽምግልናስ ማን ይሆን ዘዴኛ/ በመሆን በጥበብ እንዳለፈው ሕዝባችንን የሚያሻግር!?

የሆኖ ሆኖ ሽማግሌዎቹ 14 ቀን በለይቶ ማቆያ እንዲቆዩ ሳይደረግ ወደ ቤታችን (ወደ አገራችን) እንዳይገቡ ፡ ሲገቡም የሚከተሉት ሁኔታዎችን ማጣራት አለባቸው፦

• እነዚህ ሽማግከሌዎች እነማን ናቸው? ማን ነውስ ያሰማራቸው? የሚሉ የመመካከሪያ ሃሳቦችን ማንሳትና ይፋ እንዲሆን መደረግ አለበት!


• የራስን በራስ የመወሰን መብት ወደ ድረድር የሚቀርብ አይደለም። የዚህ ሽምግልና መነሾ ሰላም ከሆነ ግን ባለቤቶቹ የትግራይ ሕዝብ እና የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው ማለት ነው። ስለሆነም ግልጽነት፤ተጠያቂነት እንዲኖሮው ለማድረግ በሽምግልናው ወቅት የተደረጉ ሁሉም ክንዋኔዎች በስዕለ-ድምፅ (በቪዲዮ) ተቀርፆ ለሕዝባችን እና ለመላው ዓለምም እንዲያየው መደረግ አለበት። (ካሳ) "

በማለት የብላታ ሃይለማርያም ልጅ ካሳ ሃይለማርያም በጥላቻ ሕሊና የቀጨጨው ጩጬ ሕሊናው፤ ዛሬም ዘመን ሰለጠነ በተባለበት ዘመን ንጉሳችን ተነጠቅን እያለ ባለፉት የነገሥታት የሥልጣን መነጣጠቅ ዘመን የተደረገውን እንደሕልም ሆኖበት አክራሪ ፋሲሰቶች በመቃዠት የሚሰቃዩበት ወደ ኋላ ዞሮ የማስተንተን ቀውስ ነው ዛሬ በዚህ ጽሑፍ ካሳ ወደ 130 አመት ዞሮ እየጋለበ ያለው።

የኢትዮ ሰማይ ተከታታዮች እንደምታውቁት በ28 አመት ትግራይ ምን ዓነት ማፈሪያ አዲስ ትውልድ እንዳፈራችና በቂም በቀል የተበከለ ትውልድ እንደተከሰተ እንድታውቁትና እንድትወያዩበት የተቸሁበትን ትችትና ትርጉም እዚህ አበቃሁ። "ሼር" አድርጉት፡ ሃሳብ ስጡበት!

ትግርኛውም ከታች አያይዤዋለሁ።

አመሰግናለሁ። ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay ድረገጽ አዘጋጅ) June 16, 2020

ኣብ ታሪኽ ሽምግልና ኣብ ዝሓለፈ 130 ዓመታት ትግራይን ሸዋን ሓደ ብሓደ ኢና! እዛ ናይ ሎሚኸ?

መንግስትታት ሸዋ ዓቕሎም እንትፀቦምን ከጥፍኡና እንትሽርሑን ኩልግዘ ናብ ሽምግልና እዮም ዝጓየዩ፡፡ ኣብ ታሪኽ እውን ኩሎም ሽምግልናታት ዝነቐሉ ካብ ሸዋ እዩ፡፡ ብ1881 ዓ.ም ንጉሰ ነገስት ሃፀይ ዮሃንስ ንመኸተ ወራር ማህዲስት እናተዳለው እንተለው፤ ምኒልክ ኣንፃሮም ምስ ጥልያንን ካልኦትን ብድሕሪት ውሽጣውሽጡ እናሸርሐ ምዃኑ ምስፈለጡ፤ ክቐፅዑዎ ናብ ሸዋ ነቒሎም ነይሮም፡፡ ሽዑ ምኒልክ ተጓይዩ 10 ጥሪ 1881 ካብ እንጦጦ ደብዳበ ፅሒፉ፤ ጎይታይ መሓሩኒ ኢሉ ንኣኩኡ ደገዝማች ዳርጌ ሽምግልና ልኢኹ ንንጉሰ ነገስትና ኣዘናግኦም፡፡ ገፆም ካብ ምኒልክ መሊሶም እውን ናብ መተማ ወፈሩ፡፡ ምኒልክ ግና ሰሩ ዘይሓደገ ፈለስቲ ኣምሲሉ እናለኣኸ፤ ዕርቂ ምስ በለ ኣብ ካልኣይ ወርሑ ንንጉሰ ነገስትና ኣቕተሎም፡፡ ብስም ሽምግልና ስዒሮምና!

ድሕሪ 100 ዓመት ብ1983 ዓ.ም ስርዓተ ደርጊ ናብ ኣፈዕርበቱ ምስተቓረበ፤ ብክልተ ኣንፈት ናብ ዕርቂ እዩ ዝተጓየየ፡፡ ብሓደ ወገን መንግስቱ ሃይለማርያም ባዕሉ ንኣሜሪካ ሸምግሉኒ ኢሉ ብዕሊ ሓተተ፡፡ መስፍን ወልደማርያም ዝመርሖ ጉጅለ “ሽማግለታት” ድማ ኣብ ግዮን ሆቴል ናይ ሰላም መማረፂ ዝብል ሰነድ ኣዳልዮም ላዕልን ታሕትን ይጓየዩ ነይሮም፡፡ ንቱ ሽምግልና ተቐቢልና መራሕቲ ዳግማይ ወያነ ክሳብ ጥልያን ከይዶም ዘትዮም ግን ወፍርና ንፃት እውን እንተየሞንገና ቀፀልና፡፡ ብምዃኑ እውን ንሚኢቲ ዓመት ኣብ ልዕሌና መሪቱ ዝነበረ ስርዓት ካብ ሱሩ መሃውናዮ፡፡ ንሕና ሰዓርናዮም፤ ሓደ ብሓደ ኮንና፡፡

ብ1881 ንሳቶም ጎሪሖም ንንጉስና መንጠሉና፤ ብ1983 ግና ንሕና ለቢምና ተዓወትናሎም፤ መራሒኦም ከም ኣያታቱ ዓዲ ሓዲጉ ሃደመ፡፡ እዛ ናይ ሎሚ ሽምግልናኸ? መን እዩ ለባምን ንህዝቡ ዘሻግርን!?

ብዝኾነ እዛ ሽምግልና ዘይትተርፍ እንተኾይና 14 ማዕልቲ እንተይተወሸቡ ናብ ገዛና ከይኣትዉና! ምስ ኣተዉ እውን፤
       እዞም ሸምገልቲ እንመን እዮም? መን እዩ ኣዋፊሩዎም? መበገሲኦምን ሽቶ እዙ ሽምግልናን? ወዘተ… ዝብሉ ዝርዝር መመያየጢ ነጥብታቱ (terms) ክንፅርን ዕላዊ ክኸውንን ኣለዎ!
       መሰል ዓርሰ ውሳነ ናብ ዘተ እውን ክቐርብ የብሉን!! መንቀሊ እዙ ሽምግልና ሰላም እንተኾይኑ ግና፤ ብዓልዋና እዙ ሽምግልና ህዝቢ ትግራይን ህዝቢ ኢትዮጵያን እዩ ማለት እዩ፡፡ ብምዃኑ እውን ግልፅነትን ተሓታትነትን ምእንታን ክህልዎ፤ ኩሉ ከይዱ ብቪድዮ ተቐሪፁ ብዕሊ ብሚዲያታት ንህዝብናን ንዓለምን ክመሓላለፍ ኣለዎ!  #ካሳ )
ከትግርኛ ወደ አማርኛ ትርጉም ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵን  ሰማይ)


Saturday, June 13, 2020

ሳሞራ! ሳሞራ! ወደ አብይ መጣ! ትግራይ ውስጥ መሬት አርዕድ ተቃውሞ ተነሳ! ቃለአጋኖዊ ጊዜኣዊ የስቃይ መስታገሻ! Saturday, June 12, 2020 ጌታቸው ረዳ ( Ethiopian Semay - ኢትዮ ሰማይ)



ሳሞራ! ሳሞራ! ወደ አብይ መጣ! ትግራይ ውስጥ መሬት አርዕድ ተቃውሞ ተነሳ! ቃለአጋኖዊ ጊዜኣዊ የስቃይ መስታገሻ!
Saturday, June 12, 2020
ጌታቸው ረዳ ( Ethiopian Semay - ኢትዮ ሰማይ)

እንደምን ሰነበታችሁ?  በኢትዮጵያዊያን ጀሮ ገብተው ሲያስደልቁ የሰነበቱት የዚህ ወር ሁለት ትኩስ ዜናዎች (1) የወያኔው ወታደራዊ አዛዥመሓመድ የኑስ” (ሳሞራ) ወደ አዲስ አበባ መምጠቱና ከፋሺሰቱ ኦሮሙማው መሪአብዮት መሐመድ” (አብይ) በመልካም ወዳጅነት ስለመገናኘቱ (2) ለኤርትራውያን ዘመዶቹ ወግኖ ምፅዋ ወደብና ሳሕል በረሃዎች ድረስ በመሄድ የወያኔ ተዋጊ ሃይሎችን ለውግያ በማሰማራት በሺዎቹ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ጀግኖች ወታደሮችና ሰለማዊ ዜጎቻችንን የጨፈጨፈና ያስፈጀ፤ የተማረኩ ኢትዮጵያውያን ወታደሮች ለሻዕቢያ አሳልፎ በመስጠት ለስቃይ የዳረጋቸው፡ ከጠላት ጋር የተባበረ፤ አረመኔው ጸረ አማራው በሟቹሓዲሽ ኣርአያ” (ሓየሎም አርአያ ) ስም የተሰየመፈንቅልየተባለ (አክራሪ የትግራይ ብሔተኛነትን አውቀውም ሳያውቁትም በኩራት የለበሱት መጠሪያፌስ ቡክ ላይ እየጨፈሩ ሲያስጨፍሯችሁ የሰነበቱትየተለያዩ የቃለ አጋ” (Exclamation) ቡድኖችትግራይ ውስጥ ድንገት ፈነዳ የተባለለትን መሬት አርዕድ ተቃዉሞእንዳጋጋልዋችሁ ታዝቤአለሁ።

በፈጠራቪዲዮውም በፎቶውምእየተደገፈ የስንቶቻችሁ ጀሮ እንደበጠበጠ ባላውቅም ከሚገባው በላይ ተለጥጦ ወያኔ አለቀላት እስከሚባል ድረስ ከተቃዋሚ የዜና ማሰራጫዎች እስከ የአብይ አሕመድኦሮሙማው እና መሰል ማሕበራዊ መገናኛ ድረገጾች ምራቃችሁ እስኪንጠበጠብ ድረስ ሲያስግቱዋችሁ ሰንበተዋል።
እነዚህ ሁለት ዜናዎች የሳምንቱ ዋና ርዕስ ሆነው ቆይተዋል።

ፈንቅል የተባለው የአብይ አሕመድ ደጋፊዎች የሚወራጩበት የቃለ አጋኖው ቡድን ዋና መዘውሩ ውጭ አገር ሲሆን፡ ትግራይ ውስጥ ተነሳ የተባለውመሬት አርዕድየተባለለት አብዮት፤ ካሁን በፊት የአማራ እና የኦሮሞ ቄሬዎች በዓለም ፊት በድምፅ ማጉልያ ይዘውወያኔይውደም የሚልመፈክርሳይሆን ለበርካታ አመታት የቆዩ የአስተዳደር ጥያቄዎችን የሚመለከት ነበር። እናነተ ጸረ ወያኔ ነው ማለት መብታችሁ ነው። ለመጃጃል ዲሞክራሲም ተዋናይ ነው።

ይህ ቃለ አጋኖ፤ እኔ የምለው ሳይሆን አዲስ አባባ ውስጥየዚህ እንቅስቃሴአማራር አባል የሆነ ከአጋር ወገኑ የቲ-- ተጠሪ ግለሰብ ጋር በቲ/ ለውይይት ተጋብዘው ስለ ጉዳዩ ሲያብራራ እንዲህ ነበር ያለው፡-

የሕዝቡ ጥያቄ በጣም ቀላል ነው። በቀላሉ የሚፈቱ እነዚህ ጥያቄዎች ወዲያውኑ መፈታት ሲገባቸው እየተጓተተ መዘግየቱ እንጂ በቀላሉ መፈታት የሚቻሉ ቀላል ጥያቄዎች ነበሩነበር ያለው።

የዜና ማሰራጫዎች ሲገልጹት ግን በተለይእኔ የምወደውኢትዮ 360 የተባለው ሚዲያ እነ ኤርሚያስ ለገሰና ሃብታሙ አያሌው እጅግ በሚያስገርም ሁኔታ ሁኔታው ሲገመግሙድሮም የትግራይ ሕዝብ እና ወያኔ አንድ አይደሉም ስንል ብዙ የተሰደብንበት አቋማችን ነው፤ ይኼው ዛሬ ማስረጃችን ይህ ነውእያሉ አጉል የቦተለኩበት መናኛ አቋማቸው አስደምጠውናል። በዚህ ወደ ሗላ እመለስበታለሁ።

አሁን ወደ ሳሞራ የኑስ ወደ አብይ መምጣት ጉዳይ እንመልከት።

በወያኔ ትግራይ ፖሊሲ ተቀርጾ በልኩ ተሰፍቶ እንዲለብሰው የተሰጠው የወያኔ ጨርቅ ለባሹአብይ አሕመድለቀድሞ አለቃው ሳሞራ የኑስን ከትግራይ አስጠርቶ በማይታወቅ ጉዳይ እንዲያማክረው ወደ አዲስ አባባ እንደመጣ እራሱ ሳሞራ ተናግሯል። ለምን እንደጋበዘው እስካሁን ድረስ ግልጽ ባይሆንም፤ በዜና ተንታኞች እንዳሉት ከሆነስለ ግብፅ እና አባይ ግድብእንደሆነ ይገልጻሉ።

እዚህ ላይ ብዙ ሰዎች ሲገረሙ አድመጬአለሁ። አብይን ሳሞራን በመጋበዙ ሲያደንቁት አደምጬአለሁ። ሁለት ነገሮችን እንመለክት ስለ ተባለው ግድብ እና የጸጥታ ጉዳይ ከሆነ፤ ሳሞራ ግብዣውን ለምን እንደተቀበለ ሊገርማችሁ አይገባም። ሁለት ነገሮች አሉ፡

አባይ ግድብ ሲመሰረት የአብይ አሕመድ ምላስ አስታውሱ። ምን ድነው ያለው? “ወያኔ ለፖለቲካ ፍጆታ ሲል ነበር የገነባውሲል አብይ ገና ወደ ሥልጣን ሲመጣ መናገሩን ታስታውሳላችሁ። ያንን የለመድነው እስስታዊ ምላሱን እራሱ ቀርጥሞ የግድቡ ተቆርቋሪ ሆኖ ቀረበ። ሳሞራን ያማከረበት ምከንያት አንደኛው ምክንያት፤ አባይ ግድብ የተመሰረተው በወያኔዎች ነው፡(በመለስ ዜናዊ) ወያኔዎች ከማንኛውም ኢትዮጵያዊ አጀንዳ ይልቅ ያንን ግድብ ለማስቀጥለና ለማስፈጸም የማይተኙበት ምክንያት በመሪያቸው በመለስ ዜናዊ ስለተጠነሰሰ ነው። አባይ ግድብ ሲነሳ የወያኔን ስም አብሮ ከግድቡ ጋር የተያያዘ ነው። ስለሆነም ሳሞራ ፈቃደኛነቱን ገለጸለት። የሚገርም አይደለም።

ሁለተኛው ምክንያት አብይ እና ሳሞራ የሚጣሉበት ምክንያት የለም።

የሚከተሉትም የሚያራምዱትምፋሺስታዊ አክራሪ ብሔረተኛነት ነው ስለዚህም አይጣሉም። የሚጣሉበት ወቅትአብይ እስካልነካቸው ድረስ ብቻ ነው” (ቀይ መስመራቸውን ካላለፈ!!!)።እስከዛሬ ድረስ ብዙዎቹ ወያኔዎችና ጋሻ ጃግሬዎቻቸው አልተነኩም (ስልጣን ላይ አሉ፤ ደሞዝም ይከፈላቸዋል) የሚሰጣቸው ባጀትበጉቦ እና ቁጣን ለማስታገሻመልክ ከአማራ ሕዝብ በላይ ከጋምቤላ ከሶማሊ ከወዘተ.. በላይ ለትግሬዎች አዳልቶ አለቆቹና ወዳጆቹ ለሆኑት የወያኔ ትግራይ መሪዎች ለሚያስተዳድሩት ለትግራይክልልለልማት ዘርፍ ከፍተኛ ሥራ ማስኬጃ እንደመደበላቸው አብይ እራሱ ኢፍትሃዊነቱን ሳያስበው ኑዛዜውን በፓርላማው ሳያፍር፤ሳይደብቅ አድላዊ መሆኑን ነግሮናል። (ትግሬዎች ድሮም ዛሬም ተጠቃሚዎች ናቸው የምንለው ለዚህ ነው)

በርዕዮተ ሓሳብም አንድ ናቸው። ሁለቱም ብልጽግናም ወያኔም አክራሪ ብሔረተኞች እና በአክራሪ ብሔረተኛነት የተቃኘው ፋሺስታዊው ሕገመንግሥት ተንከባካቢዎችና አስቀጣይ ናቸው። ስለዚህ ሳሞራ አብይ ጋር ወዳጅነት አለው፤ ወይንምአብይ ላይ መፈንቅለ መንግሥት እንዳካሂድ ተጠይቄ አላካሂድም አልኩኝአለ እየታበለ በአድናቆት እየተሞካሸ በዜና ማሰራጫዎች በተለይአለምነህ ዋሴየተባለው በዘሓበሻ ሚዲያ በጎረናው ድምጹ የቀረበው ቃለ አጋኖ ብታደምጡትእንዴት እያሳመረ በድምጽ ቅላጼ እንዳቀረበውስታደምጡ መስማት እጅግ የሚያሳምም፤በኢትዮጵያ ሉኣለዊነት እና ኢትዮጵያውን ነብስ የተጫወቱ የወያኔ አራዊቶችን ሰብኣዊ ባሕሪ ለማልበስየሚደረገው የዜና ማሰራጫዎች ትያትራዊ ቃለ አጋኖነት እጅግ ይገርማል። የእኛን (ኢትዮጵያን ያጠቁ/ያንበረከኩ/ለውርደት የዳረጉ/ወደባችንን የዘጉብን) ተሎ የመርሳት አባዜ ስንት ግዜ እየተጠቃን እንደምንኖር ለኔ ግራ ገብቶኛል።

አሁን መቸ ነው ሳሞራ (ወያኔዎች) እና አብይ የሚጣሉት? የሚል ጥያቄ ብታቀርቡ መልሱአብይ ወያኔን እንደናዚ ድርጅት ፈርጆ ከፖለቲካው ተሳትፎነትና ለሰሩት ወንጀል በሕግ እንዲጠየቁ ለማድግ ሲሞክር” (አያደርገውም ግን እንዲጥማችሁ ብየ ነው) ያኔ የአብይ አሕመድ መጨረሻ ይሆናል። ያንን ለማድረግ ወያኔዎች ወደ ደደቢት መሄድ አያስፈልጋቸውም! አብይን በደቂቃ ከብበው ማሰር የሚችሉ የወያኔ ታጋይ ወታደሮች ትጥቃቸውም ልብሳቸውም፤ የማዘዣ (የኮማንድ) ቀዳሚ መምርያዎች ሳይነጠቁ ከነማዕረጋቸው በወታደራዊ ስብሰባዎች የምታይዋቸው መኮንኖችና ወታደሮች ዛሬም የወያኔ ታጋዮች ናቸው። ለመለስ ዜናዊ ተንሰቅስቀው ከነመለዮቻቸውና ማዕረጎቻቸው አለም እያየ በቀብሩ ሰርዓትመሬት ላይ እየተንከባለሉ ያለቀሱወታደሮች ዛሬም አብይን እየወደዱት እንዳይመስላችሁ። የወያኔ ትግሬ ታጋዮች ተንኮል ማወቅ ብዙ መንገድና አመት ይጠይቃል።ወያኔነት ሃይማኖት ነው!! እንኳን ለትግሬዎችአባ ዱላ ገመዳእንዳለው ከኦነግ ይልቅ ወያኔዎች ለኦሮሞ ይቀርቡታልብሏል።

ስለዚህም አብይ አሕመድም ሆነ አማራን እንወክላለን የሚሉት 26 አመት ለትግሬዎች ያደሩዛሬም 2 አመት ደግሞለኦሮሞዎቹ በሎሌነት ያደሩት አማራ ነን የሚሉ (ብኣዴንም) ሆነ ወያኔዎችውስጣቸውን ደፍረው ማየት የሚያስችል ሓሞት ስለሌላቸው ሊለወጡ አይችሉም።፡አርከበ. ዕቁባይ .ወዘተ..እያላችሁ ቁጠሩ አብይ ጉያ ውስጥ ገብተው ወሬና እስትራተጂ የሚቀርጹ ሁሉም የተመደቡ የወያኔ ሰላዮች ናቸው። ወየኔን ለማታውቁ ሰዎች ይገርማችሁ ይሆናል።
ወያኔዎች በባህሪ ሊለወጡ ስለማይችሉመሸኘትከመጣ የሚለያቸው ሁኔታ ካለወያኔም፤አብይምአብረው ይሞታሉ። ሥብሓት ነጋ- “የኢሕአዴግ የቁልቁለት ጉዞበሚል የወያኔ አምላኪ የነበረው ባለሹመት ብርሃነ ፅጋብየተባለ በጻፈው መጽሐፉ እንዲህ ይላል።

ስብሓት ባንድ ስብሰባ ውስጥ እንዲህ አለ ይላል፡

ህወሓትምሆነኢሕአዴግእንደገና መፈጠር አለባቸው። ሕዝቡ በሚገባ አውቆናል። ሕዝቡ እያለን ያለውበዚህ ተሃድሶ ስብሰባቸውም ቢሆን ራሳቸውን ማየት ድፍረት ስለሌላቸው፤ ተቻችለውና የስቃይ መድሃኒት ውጠው ማቆያ አድርገውት ሊወጡ ይችላሉ፤ እያለን ይገኛል። እራሳቸው የምር ማየት ከጀመሩ እራሳቸው ይሞታሉ፤ እራሳቸውን ይገድላሉ እያለን ይገኛል።ሲል ስብሓት ይናገራል።

ደብረጽዮን እኮ አብይን ተአምራዊ ከሰማይ የመጣ ሙሴ አድርጎ ነበር ሲያሞግሰው የነበረው? የተለቀቀው ቪዲዮውን አድምጣችሗል አደለም? ወያኔዎች እስስቶች ናቸው፡ መያዣ የላቸውም። ስብሓትም ሆነ ሌሎቹ ወያኔ እና ኢሕአዴግ እንደገና መፈጠር እንዳለባቸው በተሃድሶ ስብሰባቸው ላይ ቢያሳስቡም እውን ወያኔ እና ኢሕአዴግ እንደገና ራሱን ፈጥሮ መሻሻል የሚያስችል ቁመናም ሆነ ድፍረቱ አለው ወይ? የሚለው መልስ ማግኘት ቀላል ነው። ሁሉም የወያኔ መሪዎች ለውጥ ያስፈልጋል ይበሉ እንጂ ራሳቸውን ማየት ከጀመሩ እራሳቸው እንደሚያከስሙ ስለሚያውቁ፤ ይኼው አብይ አሕመድ እራሱ መቀየር የማይችል ማስረጃ ነው።
አብይ እራሴን እቀይራለሁ ብሎ ቢነሳምእራሱን ማየት ሲጀምር አስፈሪ ሕዝባዊው ጥያቄ ከፊት ድቅን ሲልበትየሕገመንግሥቱ ጠበቃና አሞጋሽሆኖ በግልጽ በመናገርበስንት ታጋይ ደም የመጣ ሕገመንግሥታችንእያለ ባለፈው ሰሞንየወያኔና የኦነግ የፋሺቶች ሕገ መንግሥትንጥብቅና ቆሜ እሞታለሁ ሲል ፓርላማው ተቀምጦ ሲለፈልፍ መኖሩን ታስታውሳላችሁ።

ይህ የሚነገረን ነገር፤ ፋሺሰቶች በዲሞክራሲ የማጃጃያ ዘዴ የሚያታልሉ፤ እራሳቸውን መለወጥ እንደማይቸሉ ማስረጃ ነው። ስለዚህ ሳሞራ መጣ፤ ወዲ ወረደ (ታደሰ ወረደ) አብይ ጋር አብረውምሳ በሉወዘተ…. ለቃለ አጋኖዊ ቡድኖች ግን እርካታ ነው።

አሁን የትግራይ እና የወያኔ ድርጅት አንድ ነው አይደሉም ክርክር፤ በሚቀጥለው በሰፊው ባቀርብ ለዛሬ ግን እነዚህን ጥያቄዎች ላቅርብላችሁ_ እነሆ፤-

ወያኔ እና ህወሓት አንድ ነበሩ? አንድ ከነበሩስ መቸ አመተምሕረት ተለያዩ? የትግራይ ሕዝብ ወያኔን ሲከተል የፈቀደበት (አስገዳጅነት ከሚለው ሌላው ምክንያት) የተቀበለው ምን ነበር? የድርጅቱ መነሻ ጥያቄ ምን ነበር? የትግራይ ሕዝብ ጥያቄ ዲሞክራሲ ነበር? ዛሬም ዲሞክራሲ ነው ለምትሉ ሰዎችዛሬም ትግሬዎችበጎሳ ፌዴራሊዝምያምናሉ፤ይቀበላሉ። አይደለም እንዴ? ታዲያእውን ፌደራሊዝም፤ በዲሞክራሲ ያምናል? የትግራይ ሕዝብ ቋንቋን መሰረት ያደረገ ፌደራሊዝምን ያምናል ወይስ አያምንም? አዎ የምንል ከሆነ፤ የማንን ርዕዮት እየተከተለ ነው ልንል ነው? የወያኔ!! አይደለም እንዴ? በቋንቋ መተዳደር ያመጡት ጣሊያኖች ናቸው- ታዲያ ትግሬዎችና ወያኔ አንድ ካልሆኑ ወያኔ ጣሊያንን የሚያመልክ ወያኔ ያስተማራቸውን በቋንቋ የመስተዳደር ትግሬዎች ለምን ዛሬም አፓርታይዱን ተቀብለውት እስከመጨረሻ እንታገልለታለን ይላሉ?

ይህንን ልጨምርላችሁ___-

አጅግ አምርሮ ኢትዮጵያዊነት የሚጠላ የትግራይ አዲስ ትውልድ ተፈጠሯል ወይስ አልተፈጠረም? ብዛቱስ ስንት ይሆናል? ወያኔ ኢትዮጵያን ሰንደቃላማ እያወረደ የወያኔ ባንዴራ እንዲይዙ ሲደረጉ ዛሬም ያንን ተቀብለው በዓለም ፊት ይታያሉ፤ በየገጠሩ በክብር ተውለብልቦ በሙዚቃ ስትታጀብ ይታያል፡ ታዲያ ትግሬዎች እና ወያኔዎች አንድ አይደሉም? 42 አመት ሙሉ የትግራይ ሰው ኢትዮጵያዊነቱ ጸንቶ ቆይቷል ለምትሉ ከዶ/አሰፋ ነጋሽ የቀረበላችሁ ጥያቄ ልጠይቃችሁ፡

1967 . ወያኔዎች የካቲት ወደ ደደቢት በረሃ ከሄዱበት ጀምሮ የተወለደ ትውልድ ስንመለከት በአማካኙ 1- 12 አመት ዕድሜ ጀምሮ ያላቸውን ህጻናት በወቅቱ የነበሩትን ስንመለከት ጸረ ኢትዮጵያነት እና ጸረ አማራነትን (ጎቦታት ትግራይ መቓብር አምሓራይ! (የትግሬ ተራሮች የአማራ መቀበሪያዎች) እያሉኣምሓራይ ፤አድጊ፤ ዑዎሽ በሎ እዚ ኣምሓራይ) በሚል ጥላቻ እየተመረዘ ካስተማራቸው ከዚያ አመት ማለትም ዕድሜአቸው 12 ጀምረው የነበሩ ታጋዮችም ሆኑ ሰላማዊ የትግራይ ህጻናት ወጣቶች ዛሬ ዕድሜአቸው 46 ሲሆን በጠቅላላ የኢትዮጵያ ሕዝብ በአማካኝ 92% (ዘጠና ሁለት ከሞቶ) ዕድሜአቸው 52 እስከ 56 ዕድሜ በታች ሆኖአቸዋል ማለት ነው (ትግራይን የሚጨምር ማለት ነው) ይህ 92% በወያኔ አስተሳሰብተላቅጦ፤ተቦክቶ የተፈጠረ ትውልድ ነው ባጭሩ ጸረ ኢትዮጵያ እና ጸረ አማራ አመለካካት ተሸካሚ ነው። አሁን ጥያቄው፤ ባንዴ ሊፈወስ የቻለ ከወያኔ እሴቶች/በረከቶች/አስተሳቦች/ ጋር እንዴት ተላቀቀ የሚል ልትነግሩኝ ትችላላችሁ?

ስለዚህ በዚህ ሃይል ድጋፍ ነው ወያኔ ይወድቃል ስንባል የነበርነው። ደርግን የሚያክል ስርዓት ታግሎ ከጣለ፤ ዛሬ ከወያኔ እራሱን ማውጣት ለምን አልቻለም?
ካናዳ ውስጥ ኗሪ የስደተኞች የሕግ ጠበቃ ባለሞያ የሆነው ተክሌ የተባለው (ኢሳት ውስጥ እንደ ጋዜጠኛ ሆኖ የነበረ)- ጌታቸው፤ ማሰረሻ፤ ወዘተ የሚሉ ስሞች በሓጎስ፤ በዲሳሳ በነገዎ.. ስም ተተክተው በሥልጣን ፊት ለፊት መግባት አለባቸው፡ጌታቸው ..ማስረሻ..” የሚሉ አማራ ስም ያለቸው አማራዎች ስልጣን ይበቃቸዋል፤ በመንበረ ሥልጣን አመራር ከሗላ እንጂ ከፊት መቀመጥ የለባቸውም ሲል አማራን አጥብቆ የሚጠላማፈሪያየሆነ ግለሰብ ይህንኑ በትግራይ ተሸንፈናል ፤በትግሬዎች እንድናለን ሲል ነበር። ዛሬ የትግራይ ምሁራን እና ወጣቶች ራሳቸውን ነጻ ማውጥት አልቻሉም። የወያኔ ተቃዋሚ የሚባሉትም ግማሹ ትግራይ ለማስገንጠል የቆሙ ግማሹ ደግሞ የአብይ አሕመድ የርዕዮተአለም አስፈጻሚኩሊዎችሆነዋል። ወየኔ ሄደ በወያኔ ተተካ!!

ታዲያ በማአከላዊ መቶኛ ማለትም 92% የሆነው ትግራይ ውስጥ 42 እስከ 54 ዕድሜ ያለው ከላይ የተዘረዘሩትን የወያኔእሴቶች በሙሉይቃወማል ወይስ ይቀበላል? አይቀበልም ካልን ማስረጃችሁን ንገሩኝ።የወያኔ ትግራይ መመስረትስ ዛሬም ህያው ሆኖ ያከብረዋል ወይስ አያከብረውም? አዎ ከሆነ ለምን? ወያኔነት ኢትዮጵያን ሉአላዊነት ያስደፈረ ኢትዮጵያን ያለ ወደብ ያስቀረ፤ አማርኛን በላቲን ፊደል እንዲተካ በሕግ የደነገገ (ትግራይም ጭምር (ኩናማም ዓፋሮችም..ወዘተ..) የመከራችን ፈጣሪ ከሆነ- ከወያኔ ትግሬ ጋርብዙዎቹ ትግሬዎችዛሬም ግንቦት በመጣ ቁጥር ለምን ትግሉን ያከብሩታል?
አመሰግናለሁ

ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)