Friday, February 14, 2020

ምርጫ ወቅት ኮሮጆ ቢሰረቅ ብጥብጥ ያስነሳል ማለት ቅዠት ነው ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ)

ይህን ማሃይም ወጣት ይዘህ በምርጫ ወቅት ኮሮጆ ቢሰረቅ ብጥብጥ ያስነሳል ማለት ቅዠት ነው

ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ)


የጣሊያን ፋሺስቶም ሆኑ የጀርመን ናዚዎች የመጀመሪያ ትኩረታቸው የወጣቱን ሕሊና መበረዝ ነበር። “ኦፔራ ናዚዮናለ ባሊላ” የተባለው የመጀመሪያው የጣሊያን ፋሺሰቶች ወጣት ብቅል ነበር። በአገራችን የመጀመሪያው የፋሺስቶች አገር በቀል ወጣት ብቅል (ጥንስሱ) የተመሰረተው ትግራይ ውስጥ ትግራይ ‘ደደቢት’ እና ኦሮሞ “ባሌ” ውስጥ ነበር።

ከዚያም ፋሺሰት ድርጅቶቹ አድገው ቀስ በቀስ ወደ መንግሥትነት ሲሸጋገሩ የ28 አመት የፋሺዝም መንግሥታዊ ትምህርት በየትምህርት ተቋማት እና አብያተ ጸለቶች በማስፈራረትም፤ በገንዘብም ይሁን በቅስቀሳም ሁሉ ወጠቱን በመበረዝ “ሳብቨርዢን” ተብሎ በሚታወቀው የሕብረተሰብ የብከላ መረብ አስጠምደው አሁን ላለንብት የፋሺስቶች የሥልጣን ሽግግር ውስጥ ወጣቱ በፋሺዝም ርዕዮት ተጠምቆ አገር ከሚያፈርስ አብይ አሕመድ የተባለው ከ28 አመቶቹ ባሊላ ፋሺስቶች የተገኘ ሌላ የፋሺስቶቹ አሸጋጋሪ ግለሰብ ወደ መደገፍ ደርሰዋል።

በ28 አመት ውስጥ በፋሺዝም ትምህርት የተበከሉ ወጣቶች ጉዳቸው የሚከተለው ነው።  ‘ወጣት ልጃገረዶችን ከየትምህርት ተቋማቶች አፍኖ ከመጥለፍ እስከ የሴቶች ጡት ቆረጣ እና ሰው ዘቅዝቆ በአደባባይ መስቀል፤እንዲሁም አማራ ተማሪዎችን እየለዩ ከየትምህርት ገበታቸው ከፎቅ እየገፈተሩ መግደል፤ቤተ ጸሎት ማቃጠል የሰው አንገት አርዶ ሬሳን በመኪና መጎተት ተሸጋግረዋል።

ወጣት ይንገስ፤ አዛውንት ይወገድ ሰትሉ የነበራችሁ ግራ ተጋቢዎች ይኼው ዛሬ ወጣት ነግሶ ዛሬ ይኼው ለ28 አመት በተለያዩ ወንጀሎች ተሰማርተው ዜጎች ሲያሰቃዩና ሲገድሉ ሲሰውሩ የነበሩት ወጣቶች እስከ ጠ/ሚኒስቴርነት ድረስ ወደ ሥልጣን በመውጣት ለነሱ አጨብጫቢ የሆኑ የፋሺሰት “ባሊላ“ ወጠቶችን በየከተማው በማሰማራት “ወያነ ትግራይ” ሲሰራው የነበረው ወንጀል እንደገና በመፈጸም “ሌላ 28 አመት” ተጨማሪ ብሔራዊ ወንጀል  እንዲፈጽሙ  “ይንገሡልን” በማለት “በዓረብ አገር በዱባይ” እና “በኢትዮጵያም በናዝሬት” ያሉ በዚህ ፎቶግራፉ ላይ የምታይዋቸው የተበከሉ የፋሺሰት “ባሊላዎች” ለሁለተኛ ዙር የፋሽስቶች ሽግግር መንግሥት እንዲመሰረት ድጋፋቸው እየሰጡ ነው።

ታዲያ እኔ የገረመኝ እንደዚህ የመሳሰሉ በፋሺስቶች ርዕዮት የተበከሉ ወጣቶች ተይዞ ነው ገና ይመጣል እየተባለለት ያለው የምርጫ ተብየው” ሽር ጉድ” ኮረጆ ቢሰረቅ አገር አንቀጥቅጥ ብጥብጥ አስነስቶ ፋሺስቶችን ያስወግዳሉ የሚባልላቸው?

ለመሆኑ ይህንን አብይ አሕመድ የተባለው የስለላ መረብ በመዘርጋትና በመቆጣጠር የአገር ምስጢሮችን ለኦነግና ለሻዕቢያ አሳልፎ በመስጠት የታወቀው በብዙ ብሔራዊ ወንጀል ተጨማለቀው (እራሱም ወንጀል መፈጸሙ ፓርላማ ውስጥ ያመነ) የሥልጣን ጥም ያሰከረው “ጂሃዳዊ ወንጀለኛ” ሰው ከያዘው ኢሕጋዊ-ሥልጣን ማስነሳትና እሱንም ማሰር የሚያስችል ብዙ ብሔራዊ ወንጀሎች ተፈጽሞ ባለበት “አሁን! አሁን! አሁን ዛሬ!” እንኳ ሕዝቡ መነሳት ያልቻለ፤(ያውም “አግዚአብሔር ሃይላችን ነው” እያለ በአቡነ ዘበሰማያት መዘዝ የተጠመደ “ጥፊ እና መንገላታት እራቱ ያደረገ” ማሕበረሰብ ተይዞ) በመናኛና ማጃጃያ ምርጫ ተብየው “ኮሮጆ” ተጭበረበረ ቢባል ይህንን “ጂሃዳዊ የሥልጣን ጥመኛ” ሰው የሚያስወግድ ሰላማዊም ሆነ የብርት ትግልና ብጥብጥ ይነሳል ብለው የሚቃዡ እና ተስፋ የሚያደርጉ ሰዎች ሳደምጥ እጅግ ይገርሙኛል። እስካሁን ድረስ የተፈጸመው ግፍ ይበዛል ወይስ ስለ ትንቢት የምርጫ ወቅት በብጥብጥ ተስፋ አብይን ማስወገድ? የትኛው ግፍ ይበረታል?

ፍራሽ አዳሽ የሚባለው ቀልድ የሚጫወተው ትምህርት ሰጪው ቀልድ ሰሪው “ተስፋሁን ከበደ” እንዲህ ብሎ ነበር፡
“አያ ጅቦ አንድ ቀን ባለቤቱ አርፋበት አህዮች መርዶውን ሰምተው “አይ ምንም ጠላት ብንሆን ‘ሓዘን ነውና’ ብለው ሰብሰብ ብለው ለቅሶ ጋ ይሄዳሉ ። አንድ ሞሾ አውራጅም ፊት ለፊቱ ቆማ “ሙሾዋን መውረድ ጀመረች”፡ አህዮቹ ልክ ዱንኳኑ በር ሲደርሱ
“ምንም እሩቅ ቢሆኑም ይሰማል ድምጸዎ
አስገራሚ ነው ግርማ ሞገስዎ
እንደምነሽ ምን ነካ አበዎ..”
እያለች ሙሾ ስታወርድ
አያ ጅቦም ወደ ድንኳኑ እንዲገቡ እየጋበዛቸው ‘ግቡ ግቡ’ እንኳን ደህና መጣችሁ እያለ እንዲህ ሲል ለሙሾ አውራጅዋን መለሰላት፡
“እውነት ተናግረሻል እውነትም ብለሻል
ይህ ሁሉ ሐዘንተኛ ምን ይብላ ብለሻል!” አላት ይባላል።

እንዲህ ያለ ወደ ጅቦች ድንኳን የሚንጋጋ የጅቦች ሙሾ አውራጅ ባለበት የወጣት መንጋ ፋሺሰቶችን ስርዓት ይጥላል ብሎ ተስፋ ማድረግ ውሃ መዝገን ነው። አሳዛኙ ክስተት ግን “ሁሌም ራስጌና እግርጌ መለየት የማይችል ወጣት በማጎብደድ ይጀምርና በመጨረሻ እራሱን ማንገላቻ እስርቤት ውስጥ ገብቶ ራስጌም እግርጌም በማይለይበት ማሰርያ ቤት ተኝቶ የገዛ እራሱ ያገኘዋል።
አመሰግናለሁ
ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ)



No comments: