Sunday, February 9, 2020

የአባይ ሚዲያ ዜና በሻዕቢያና በወያኔዎቹ ቅኝት! ከጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ)

የአባይ ሚዲያ ዜና በሻቢያና በወያኔዎቹ ቅኝት!
ከጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ)
ፎሮግራፍ ላይ በኩራት ቆሞ የሚታየው የዋሺንግተኑ አገር ወዳዱ  ገብርኤል እና ምጽዋ ላይ ኤርትራ ላይ የተዋደቁ አርበኞቻችን ናቸው። ክብር ለተሰውትና በጀግንንት ዛሬም ለቆሙት ሁሉ ይሁን!

ዜና ሳጣ አለፍ ብየ የማደምጠው ‘አባይ ሚዲያ” ተብሎ የሚጠራው  በራዥ የድሮ የግንቦት 7 አለቅላቂ ሚዲያ፣ በትናንትናው ዜናው  “ከዘመነ አክሱም ጀምሮ የጀግኖች አጥንትና ደም የተከሰከሰበትን የኢትዮጵያ የባሕር ወደባቸን “ምጽዋ!!” በአሜሪካን የስለላ ሳተላይት አና በወያኔ ተዋጊ ባንዳዎች እየታገዘ ምፅዋን የያዘበትን “ፈንቅል” ብሎ የሚጠራው በየአመቱ የሚያከብረው የኢሳያስ ጉራ መንዣ በዓል፡ አባይ ሚዲያ ተብየው  ውዥምብራም ሚዲያ በቃለ አጋ’ኖ እየቀባባ በኢትዮጵያ የቀድሞ ሠራዊቶች ላይ ግልጽ ስድቡን አጣጥሞ በዜና መልክ ሰርቶለታል።

አንብቢ ተብላ በሚዲያው ደናቁርት የዜና አርታዎች የተሰጣትን ምሲኪንዋ የዜና አንባቢ እንዲህ ስትል በሚከተለው የአባይ ሚዲያ ድንቁርና የሚዲያው ድብቅ ማንነት ልጽ በማድረግ በድሮ የኢትዮጵያ ሠራዊት ላይ  የስድብ ውርጅብኝ በዜናው አስራጭቷል።

ከአዲስ አበባ የሚተላለፈው የዚህ አውታር ዜና አንባቢ እንዲህ ትላለች፡-

“ኤርትራ 30 መትዋን በድምቀት አከበረች። በማለት 150 ያክል ተሰብሳቢ የተገኘበትን ስብስብ “ድምቀት” እንዳለው አስመስላ አንብቢ የተባለቺውን እንዲህ ብላለች፡

“ኤርትራ 30 መትዋን በድምቀት አከበረች።   “ፈንቅል ለልማት” በሚል መሪ ቃል 30ኛው አመትዋን ስታከብር የአገሪቱን ፕረዚዳንት እና ሌሎች የስቪልና የወታደራዊ መሪዎች መገኘታቸውን ያገሪቱ የዜና አውታሮች ገልጸዋል። ፈንቅል ሻዕቢያ ምፅዋ የነበረው  ከባድ የደርግ ሠራዊት የደመሰሰችበትን 30ኛ አመት መሆኑን  ተዘግቧል። በባዓሉ ላይ የተገኙት ክቡር ፕረዚዳንት ኢሳያስ  አፈወርቅ ጉንጉን አበባ አስቀምጠዋል። የሰሜናዊ ባሕር የባሕር ሃይል ዋና አዛዥ የሆኑ ብ/ጀሜራል “ተኽለ ልብሱ” ሃገራዊ በዓሎቻችንን ‘ትግላችንን” ለማስታወስና ምዕራፎቻችንን የምንገመግምበት ነው’ ሲሉ ብ/ጄኔራል ተኽለ ልብሱ በዓሉን በማስመልከት ተናግረዋል”። ይላል የሻዕቢያው ቱልቱላ “አባይ ሚዲያ”።

እንግዲህ ወገኖቼ ይታያችሁ። የተደመሰሰበት በዓል” ብሎ ባልተገረዘ አንደበቱ የሚገልጽ ጠላት እንጂ ኢትዮጵያዊ ሚዲያ ነኝ የሚል የአገሬውን ሠራዊት “የተደመሰሰበት ዕለት” እያለ እንደጠላት አሳፋሪ ቃላት ሲጠቀም የብከላው እርከን ጣራ መድረሱን ያሳያል።

  ከዘመነ አክሱም ጀምሮ ከዚያም አምደጽዮን ከሸዋ ገስግሶ ምፅዋን ከቱርኮች ያስለቀቀ፤ቀጥሎም በገናናው ይለስላሴ ተክብሮ ቆይቶ በከሃዲውና ቅጥረኛው የትግሬ ባንዳዎቹ ፈቃጅ ሰጪነት የተነጠቅነውን ምፅዋን እያጋነነ ከሻዕያ የዜና አውታር በባሰ ምልኩ እያንዳንድዋን ቃል ከጠላቶች የተበደረውን የስድብ ቃል እየተዋሰ ለጠላቶቻችን በዓል ከማዳመቁ ባለፈ ጅግናውን ፡”የኢትዮጵያን ወታደር” የደርግ ሠራዊት” እያለ ባንዳዎቹ ወያኔና ሻዕቢያ የሚጠቀሙትን “አዋራጅ ቃል” በመጠም አባይ ሜዲያ የተባለው አዲሱ የሻዕቢያ ቱልቱላ መላው የድሮ የኢትዮጵያ ወታደር ዘልፏል።

ያ ሁሉ በሺዎች የሚቆጠረው ምጽዋ ላይ የተሰዋው ጀግና ሠራዊት “የኢትዮጵያ ሠራዊት እንጂ አባይ ሚዲያና ሻዕቢያ እንደሚሉት-“የደርግ ሠራዊት” አልነበረም።  ዘንግቶት የአፍና የብዕር ወልምታ እንኳ ቢሆን ግድ አልነበረም፤ ሆኖም እንዲህ ያለ የተጠናቀረ ዜና አስነዋሪ ቃላቶች (ወያኔና ሻዕቢያ የሚጠቀሙበትን የደርግ ሠራዊት፤ የተደመሰሰበትን እያለ) በመጠቀም ይቀር የማይባልብትን ወራዳ ና ሰርቶ ሠራዊቱን ማዋረድ ተገቢ ስላልሆነ ለዚህ ጣቢያ የቅሬታ ደብዳቤ እንዲጽፍና የሚዲያው ባለቤት “ይፋዊ ይቅርታ” እንዲጠይቅ መላው የድሮ ኢትዮጵያ ሠራዊት ማሕበርና ግለሰቦች ማሕበር ካላችሁ “በደብዳቤና በኢመይል እንዲወገዝ” እጠይቃለሁ።

ለዚህ ደግሞ ሃላፊነት የሚወስደው የጣቢያው ባለቤት ስዊድን አገር የነበረው የግንቦት የእነ ብርሃኑ ነጋ ፕሮፓጋንዳና ስብሰባ እያሰራጨ ፖለቲካ ሲሰራ የነበረ የዛሬ የሻዕያው ቱልቱላ የዛሬው የአባይ ሚዲያ ቲ/ቪ ባለቤት ነው። ስለዚህም ኢትዮጵያኖች በታቻላችሁ ሁሉ ይህንን አቃጣሪ ሚዲያ መቃወም ይኖርባች የምለው

ባንድ ወቅት ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም እንዳሉት- ላለፉት 30 አመታት የኤርትራ ታሪክ በሻዕቢያና በወያኔ ግምባር መሪነት አዲስና የማናውቀው መልክ እየያዘ መጥቶ አሁን ካለበት አሳዛኝ ደረጃ ደርሰናል። ትክክል ብለዋል። በ1970ዎች ውስጥ የኢትዮጵያን ታሪክ እኛ በማናውቀው በተወላገደና በሚያስፈራ ሁኔታ፤በተቀናጀ ስልት ታሪካችንን የሚያበላሹ በርካታ መጻሕፍት ተዘጋጅተው በዓለም ሙሉ ተሰራጭተዋል። ፕሮፌሰሩ ይህንን ሁኔታ አስመልክተው እንዲህ ይላሉ፡ “በዚያ ጊዜ የኢትዮጵያዊነት ስሜት  “እንደ አድሃሪነት” መቆጠር የተጀመረበት ጊዜ ስለነበር ከኢትዮጵያ በኩል መልስ ለመስጠት የሞከረ አልነበረም” በማለት  አሁን  ላለንበት ውርደት እኛ በተውነው ክፍት ቀዳዳ በመግባት ጠላቶች ዓላማቸውን እንዴት እንዳሳኩ ነግረውናል ።

 አውነት ነው። መቼም ቢሆን ጠላት የሚወጣው ከውስጥ ነውና ጠላት ብቻውን “ያለ የውስጥ ተባባሪና ፕሮፓጋንዳ አሰራጭ” መልዕከቱን፤የሚጠቀምባቸው ቃላቶችን፤ እንዲሁም ተክለሰውነቱን መቅረጽ ከቶ አይቻለውም። ላለፉት 30 አመታት በሠራዊታችን እና በሕዝባችን ሉዓላዊ ክብር የደረሰበትን የሻዕቢያና የወያኔ ትግሬዎች ስድብና ውርደት በውስጥ ሚዲያዎችና ተባባሪ ግለሰቦች እየታገዘ የሕዝቡንና የወጣቱን ንቃተ ሕሊና “4ቱን የክለሳ/ በሳብቨርዥን እርከኖች” ተጠቅሞ ሕሊናን እያጠበ “ኢትዮጵያን እንደ ወራሪ” እሰደቡ ‘ጸረ ኢትዮጵያ’  እንዲጓዝ መደረጉ የሚታውቁት ነው። ዛሬ ደግሞ ያንን የህሊና አጠባ እንዳይበቃ እንደ አዲስ የገባው “አባይ ሚዲያ” የተባለ የዜና አውታር “የሻዕቢያና የወያኔ” ቃላቶችና ፕሮፓጋንዳዎችን እየተዋሰ ለእናት አገራቸው የተዋደቁት የምጽዋ አርበኞችን “በሻዕቢያ ተዋጊ የተደመሰሰው የደርግ ሰራዊት” እያለ (እግዜር አባይ ሚዲያን ይደምስሰውና) የአርበኞቻችን እናቶች ፤ አባቶች፤ቤተሰቦችና መላው አገር ወዳድ ዜጋ አንጀት አሳርሯል።

ይህ ሚዲያ በታቸለ መጠን “ቦይኮት” እንዲደረግ እና ውግዘት እንዲደርሰው ቢያንስ የቀድሞ የኢትዮጵያ ሠራዊቶች ማሕበር ካላችሁ በማሕበራችሁ ደብዳቤ በመጻፍ የውግዘት ደብዳቤ ለዚህ “አሳፋሪና በራዥ ሚዲያ” በመጻፍ ተቃውሞኣችሁን እንድታስተላልፉለት እጠይቃለ ። እንደዚህ አይነት ግልጽ ፕሮፓጋንዳ ለ30 አመት ተቦክቶ ፍሬ አፍረቶ እሱን እየታገልን ባለንበት ወቅት አሁን እንደገና “አባይ ሚዲያ የተባለ” የሻዕቢያ አለቅላቂ” ምን ታመጡ ብሎ ባርበኞቻችን እና በሉዓላዊ አገራችን ኢትዮጵያ ላይ የጠላት ፕሮፓጋንዳ በማሰራጨት ተራራው ጫፍ ላይ ለመውጣት በምንሞክርበት የትግል ዘመን እንደገና እግራችንን እየጎተተ ወደታች አንድንንሸራተት እያደረገ ያለው የሚዲያ ፕሮፓጋንዳው በጥብቅ እንቃወማለን።

ተራራው ጫፍ ላይ ወጥተን የተዋረደቺውን የኢትዮጵያን ሰንደቅዓላማ አውለብልበን ተደመሰሰ እያሉ የሚያዋርዷትን የእምየ ኢትዮጵያ ሰንደቅዓላማና የሠራዊታችን የአልሞት ባይ ተጋዳይ ታሪክ በቆራጥ ልጆችዋ ክብር ይታደሳል። ‘የነፋስ አቅጣጫ ሁሌም ካንድ ከተወሰነ ቦታ ብቻ አይሆንም። ማጉረምረምና ቁጣም ካልታሰበ አቅጣጫ ነፍሶ ጀብደኞችና ጉረኞች መጠጊያን ያሳጣል። ለዚህም እንደ እነ አባይ ሚዲያ የመሳሰሉት “የብረዛ ሚዲያዎች” በአርበኞች ክብርና ሕይወት “የተደመሰሰበት ዓመት” እያላችሁ የምትሳለቁ የዜና አውታር ባለቤቶች ልንነግራችሁ የምንፈልገው እናንተ የምትሉት ምፅዋ ላይ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ተነቅሎ ሻዕቢያ ባንዴራ ተውለብልቦ የኢትዮጵያ ሠራዊት “ተደምስሰዋል” ብትሉዋቸውም አርበኞቻችን ከሕሊናችንና ከታሪክ ማሕደራችን በወርቅ ቀለም ተመዝግበው “ዛሬም አሉ!!!” ለወደፊትም ህያው ሆኖው ይኖራሉ!!  
የ28 አመት የጠላቶቻችን ቃላቶችን መጠቀም አቁሙ!  በቃ! ማለት በቃ ነው!
ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ)     


     

No comments: