Friday, February 28, 2020

የካቲት 11 የትግራይ ሕዝብ በዓል ነው እናከብረዋለን ብሎናል የድሮው የኢንሳ የዛሬ የቴክ ሚኒስትር እና የትግራይ ብልጽግና ፓርቲ ሓላፊ! ከጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ) መልስ ለሚኒሰተር ለዶክተር አብርሃም በላይ (ክፍል 1) 2/28/2020 (በፈረንጅ አቆጣጠር)


የካቲት 11 የትግራይ ሕዝብ በዓል ነው እናከብረዋለን ብሎናል የድሮው የኢንሳ የዛሬ የቴክ ሚኒስትር እና የትግራይ ብልጽግና ፓርቲ ሓላፊ!
ከጌታቸው ረዳ  (ኢትዮ ሰማይ)
መልስ ለሚኒሰተር ለዶክተር አብርሃም በላይ
(ክፍል 1)
2/28/2020 (በፈረንጅ አቆጣጠር)

ዶ/ር አብርሃም በላይ ይባላል። ደናቁርት የወያኔ ተቃዋሚ ትግሬዎች ህ.ወ.ሓ፣ትን የሚጋፈጥ አንድ ሰው አገኘን እያሉ የሚቦርቁበት የትግራይ ሰው ነው። ከዚያም ተሻግረው አንዳንድ የፌስ ቡክ ደናቁርት ትግሬዎች መቀሌ ውስጥ ከሚኖሩት የዓረና ትግራይ ብሔረተኞች ደምረው “ቲም አብርሃም” በማለት እያቆለጳፐሱት የሚገኙ “ትኩስ” የትግሬዎች ታጋይ ነው።


ይህ ወጣት ከኮሎኔል አብይ አሕመድ ጋር የስለላ ማለትም “የደህንነት ስጋትና የፖለቲካዊ ምስጢሮች ጠለፋ ክንውን ክፍል” ሰራተኛ የነበረ የዛሬው የትግራይ ብልጽግና ተጠሪ እና በፋሺስቱ የአብይ አሕመድ መንግሥት “የሳይንስ እና ኢኖቬሽን” ሚኒስተር ባለሥልጣን ነው። ይህ ወጣት በዕድሜው ወጣት ነው። ቃለ መጠይቁን ያደመጥኩት  “ትግራይ ሃውስ ሚዲያ” በሚባል የወያኔ ድምፅ አስተጋቢ ቴ/ቪዥን ጣቢያ ቀርቦ ባደረገው ቃለ መጠይቅ ስለተገረምኩ መጀመሪያ የማቀርበው (ጽሑፉ እንዳይረዝምብችሁ) ክፍል 1 የራሱን (የዶክተሩን) መከራከሪያዎቹን ብቻ አቀርባለሁ (ከራሴ ትንሽ ማብራሪያ ጋር)።

በክፍል ሁለት ደግሞ የሂትለር ናዚ ፓርቲ፤ የሙሶሎኒ የፋሺሰት ፓርቲ የጀርመን እና የጣሊያን ሕዝቦች እንደ ሕዝባዊ በዓል ካላከበሩዋቸው የትገሬዎቹ የህ.ወ.ሓ.ት ፋሺሰት ፓርቲ የትግራይም ሆነ የኢትዮጵያ ሕዝብ በዓል ሆኖ መከበር እንደሌለበት መከራከሪያየን በክፍል 2 አቀርባለሁ። አሁን ዶ/ር አብርሃም መከራከሪያ ነጥቦቹን እንመልከት፡=-እንዲህ ይላል በቀረበለት ጥያቄ ቃለ መጠይቅ

“በየአመቱ የምናከብረው የየካቲት 11 በዓል የሕዝብ እንጂ የፖለቲካ ፓርቲ በዓል አይደለም። የካቲት 11 የትግራይ ሕዝብ በዓል ነው እናከብረዋለን፡ ይህንን የሚቃወሙ እንታገላቸዋለን።” በማለት ያደረገው ቃለ መጠይቅ የተወሰደ ነው። ይህ አቋም የራሱ ብቻ ሳይሆን የብልጽግና (የብልግና ፓርቲ/ ‘ሩድ’ ፓረቴ ብየ የሰየምኩት) የፓርቲው አቋም እና በዓሉን አስመለክቶ ትግራይ ውስጥ ሲከበር ድርጅቱ በ ኢ ቲ ቪ የድጋፍና የደስታ መግለጫ ያስተላለፈበት ልሳንም እንደሆነ ገልጿል።

ዶ/ር አብርሃም በላይ በሰፊው ሲያብራራ በትግርኛ እንዲህ ይላል።

“ ከውጭም ሆነው አገር ውስጥ ይህንን ሕዝባዊ በዓል ጥላሸት ለመቀባት የጣሩ ሁሉ ከተግባራቸው እንዲቆጠቡ ነው የኛ ፓርቲ  በተከበረው  የካቲት 11 አስመልክቶ ያስተላለፈው መልዕክት።አናቆምም ካሉ ለዚህ እንታገላቸዋለን። የካቲት 11 (ይህ በዓል) የሁሉም ሰላም ፈላጊ በዓል ስለሆነ ማንም ኢትዮጵያዊ ፕሮቴክት (መንከባከብ) እንዳለበት የሚል መልዕክት ነው ያስተላለፍነው።” ካለ በ

ሚኒሰተር ዶ/ር አብርሃም ይቀጥልና እንዲህ ይላል፦

“ሌላው ያስተላለፍነው መልዕክት የካቲት 11 የሕዝብ እንጂ ለፖለቲካ መጠቀሚያ ታስቦ የተወሰነ ቡድን በባለቤትነት የሚመዘምዘው አዝማምያ ስህተት ስለሆነ ይህ ባህሪ መቆም አለበት ብለናል። የአንድ ቡድን ባለቤትንት ነው ማለት የጥፋት መንገድ ስለሆነ ያ መታረም አለበት የሚል መልዕክት አስተላልፈናል።

ጋዜጠኛው ንግግሩን በማስቆም እንዲህ ሲል ጠይቆታል፦

ህወሓቶች ምን አገባችሁ ድርጅቱ የኛ ነው የካቲት 11 ቀን ወደ ደደቢት ወርደን ፍትሕ ለማምጣት የመሰረትነው ስለሆነ 45ኛ የልደት በዓላችን የማክበር መብት ባለቤትነት እና የታገልንለት ድርጅታችን ስለሆነ መብት አለን ቢሉህሳ? (ለምሳሌ እንደ እነ ስብሓተ ናጋ የመሳሰሉ ቢለህስ?)?

መልስ፦    
“በዓሉ እንደ የትግራይ ሕዝብ በዓል ሆኖ እየተከበረ ስለሆነ እነሱም የሕዝቡ አካል ስለሆኑ የሁላችን ስለሆነ እነሱም የማክብር መብታቸው መነፈግ አለበት አላልንም። የሁላችን ባዓላችን እንጂ የፓርቲ/የድርጅት/ ብቻ በዓል ስላልሆነ አብረን እናክብረው ነው የምንለው። ድርጅቱ ማለትም ‘ህወሓት የትግራይ ሕዝብ አካል እንጂ ሕዝብ የድርጅት አካል አይደለም”። በዓሉ ሕዝባዊ ስለሆነ በኢትዮጵያውያኖች ጭምር “ሪኮግናይዝ” መደረግ አለበት። ይህ ሕዝባ በዓል የጠላት በዓል ነው እያሉ የሚያጠለሹት አካሎች አሉ። የኛም በዓል ስለሆነ ይህ መስተካከል አለበት በሚል መነሻ ነው መልዕክት ለሕዝብ ለማስተላለፈው የፈለግነው። ይላል።


ባጭሩ  ድርጅቱ ከሕዝብ የተገኘ እንጂ ሕዝቡ ከድርጅቱ የተገኘ አይደለም። የድርጅቱ ፈጣሪ ሕዝብ ነው፡ እያለን ነው። ህወሓት በሕዝቡ የተፈጠረና የተገነባ ከሆነ ህወሓትና የትግራይ ሕዝብ አንድም ሁለትም ሦስትም ናቸው ማለት ነው። ይሄ ብዙ የሚያነጋግረን ስለሆነ በሰፊው እንመለከተዋለን። ያም ሆነ ይህ በኒቶ ሙሶሎኒ በ1911 ዓ.ም (በእኛ ዘመን አቆጣጠር) ‘ፋሺዝሞ’ በሚል ስም ሰይሞ የመሰረተው ብሔረተኛ ድርጅት እና በ1967 ዓ.ም ደደቢት በረሃ መሽጎ የመሰረተው የትግራይ ህ.ወ.ሓ.ት በባሕሪያቸው አንድ ናቸው። የፋሺዝሞ ዓላማ የድሮ ጥንታዊቷ ሃያልዋን የሮም ገናናነትን መልሶ ለመፍጠር ሲያቅድ፤ የትግሬዎቹ ህ.ወ.ሓ.ት ድርጅትም የጥንት የአክሱም ገናናነት መልሶ በማደስ ሃያል ትግራይን መስርቶ በዙርያዋ ያሉ ጎሳዎች/ “ብሔሮች” የበላይነትዋን በማረጋገጥ የተመሰረቱ ሁለቱ የፋሽት ድርጅቶች ናቸው።


የትግራይ ፋሺስታዊነት በትግራዋይነት ጥምር ማፊያዊ ብሔራዊ (ሲንዲካሊዝም) ስሜት፤ በአብዮታዊ ብሔረተኝነትና በትግራይ ግዛት (ኢምፓየር) የበላይነትና ጥንካሬ በማረጋገጥ ቅኝት ነበር የተመሰረተው። ጣሊያን ሙሶሎኒ  የተጠቀመበት ምልክትም የጥንታዊትዋ (ሮም) ኃያልነት የሚወክል ተምሳሌነት ለመግለጽ  በአንድነት የተጠመሩ ጥቅል እንጨቶች የታሰረ መጥረቢያ ሲሆን የትግሬ የህ.ወ.ሓ.ት ምልክትም በጥንታዊትዋ ሃያልዋ ኣክሱም የቆመ ሃውልት እና የአክሱም ነገሥታት ገንዘብ ላይ ታትሞ የሚታየው የሰንዴና የዘምባባ ምስል በተምሳሌነት ወስዶ ምልክቱ አድርጎ ተጠቅሞበታል።

ዶ/ር አብርሃም በላይም ሆነ ህ.ወ.ሓ.ት የተመሰረተበት የካቲት 11 ቀን የኢትዮጵያ ሕዝብ ማክበር አለበት ብሎ የሚለን እና የሱን መስመር የሚከተሉ ሚሊዮኖች ትግሬዎች ልነግራቸው የምፈልገው፤ ህ.ወ.ሓ.ት ማለት ብሐረተኛ ማለት ነው። ለትግሬ ፋሺስቶችኢትዮጵያማለት በነገድ ተከፋፍላ በግንጣላ ታርጌት/ /ቀለበት/ የገባች እንደባዕድአገር ነች። በትግሬ ፋሺስቶች ዓይን፤ የአገሪቱ ታሪክ፤ አገር፤ ሃይማኖት፤ አማራ እና አማርኛ ቋንቋ፤ እግዚአብሔር እና ሉኣላዊነት  ሃገራዊ ሰንደቃላማችን እና አፄ ምኒሊክ በጥላቻ የተፈረጁ፤ በውጭ አገር ታዛቢዎች ፊት በፓርላማ የሚዘለፉ የሚብጠለጠሉ እሴቶችና ሊፈርሱ የተነደፉ ኢላማዎች ናቸው። ይህ ትዕይንት ብዙዎቻችን ያስገረመ፤ ብሔራዊ እሴቶቻችንን እንደ የባዕድ ዕቃ የሚንቋሸሹና የሚብጠለጠሉ ሆነው የተነጣተረባቸው ናቸው። ይህ ሊሆን የቻለው የካቲት 11 የተመሰረተው ህ ወ ሐ ት የትግሬዎች ፋሺዝም የሚመራው ቡድን እና ድርጅቱታሪክ በማይፈሩእኔ Intellectual Lampoons የምላቸውበዱርየነት ባሕሪ የሚመሩ፤ ማአከላዊነትን የሚያጠብቁ ምሁራንእና ከድርጅቱ ውጭ ላሉሆድ አደርምሁራንን ለመምራትየሚደፍሩነፍጥ ባነገቡባልተማሩ ዱርየዎችየተመራ ዘመናዊመስፍንቶችንያፈራ፤ በሲንዲካሊሰት የገንዘብ ማግበስበስ የተካነ፤ በነብሰገዳዮች የሚታዘዝ፤ ቀኝ አክራሪናበፓራኖይድ ፐርሶናሊቲ ዲስኦርደርየተጠቁ ሰዎች የሚንከባከቡት፤የድሮ ግሎሪ (ልዕልነት) የሚዘክርመስያኒክድርጅት ነው። የካቲት 11 ለኢትዮጵያ ሕዝብ የባሕር ወደቦችዋን ያስነጠቀ፤በተለይ ደግም የካቲት 11 ለአማራ ሕብረተሰብ የምጽኣት ዘመን ያመጣ በጣም አደገኛ የፋሺሰቶች ቀን በዓል ስለሆነ ዛሬ የአብይ አሕመድ ወኪል ሆኖ  በትግራይ የብልጽግና ፓርቲ ተጠሪ ነው የሚባልለት በብዙ ወያኔ በሚቃወሙ በብዙ ደናቁርት ትግሬዎች የሚወደስ አዲስ አብዮተኛ እየተባለ የሚወደሰው ዶ/ር አብርሃም በላይ ልነግረው የምፈልገው የካቲት 11 ቀን ማለት የትግሬዎች የግዛት ማስፋፋት እና በትግሬዎች የሥልጣን ጠቅላይነት እና ሃያልንት ስሜት የተቃኘ በዓል ነው።

 ወያኔ የተጠቀመው የጎሳ ፋሺዝም፤ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ደጋፊ ትግሬዎች አፍርቷል።  ተካተዮቹ በትግሬነታቸው እንደተጠቁ በማሳመን፤ ጠንካራ ድርጅት መስርቶ አማራን በጠላትነት መድቦ፤ ለትግራይ ድህነት አማራ ተጠያቂ በማድረግ፤ አማራን ጨፍጭፎ፤ አማራዎች የሚኖሩባቸው ብዙ ቦታዎች ወደ ትግሬ መሬት በመከለል፤ (የተቀሩትም በሉሎች ጎሳዎች ክልል ሥር እንዲጠቃለሉ በማድረግ) የፋሺዝም ዋናው የመሬት መስፋፋት መለኪያው በተግባር አሳይቶናል። የካቲት 11 ቀን የተመሰረተው ይህ ድርጅት የአካባቢውን የጥንትን ሥልጣኔ ባሕል ታሪክ ማንነት፤ጀግንነት (መስያኒክ) ተከታዮቹን እያስታወሰ፡ ሁሉ ኩራት በአማራዎች እንደተደመሰሰና እንደተነጠቀ በማስተማር፤ ያንን ተነጠቅን የሚለው ኩራት ፤ መሬትና ታሪክ ፤ መመለስቀዳሚ ትግላችን ነው” ብሎ በማስተማሩ ዘመቻ ውስጥ የትግሬ ምሁራን የትግራይን ሕዝብ በማሳሳት፤በተለይ ወጣቱን ትውልድ አክራሪ የተግራዋይነት የነገድ ፍቅር አንዲከተል በማስተማር ታሪክ የማይፍቀው ወንጀል ሠርተዋል።
ክፍል ሁለት ይቀጥላል…………..
አመሰግናለሁ። ጌታቸው ረዳ (ኢትዮፕያን ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ)




Wednesday, February 26, 2020

ግንቦት 7 ጸረ አማራ ብቻ ሳይሆን ጸረ ኢትዮጵያም ነው ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ)


ግንቦት 7 ጸረ አማራ ብቻ ሳይሆን ጸረ ኢትዮጵያም ነው
ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ)
ድጋፍ ለሰዐሊ አምሳሉ ገብረኪዳን አርጋው ስለ ግንቦት 7 በጻፈው ላይ ተጨማሪ እኔም ላክልበት።
ይህ ጽሑፌ የግንቦት 7 ደናቁርት ደጋፊዎች ግንቦት 7ን *ብርሃኑ ነጋ እና አንዳርጋቸው ጽጌን) በመቃወሜ እኔ በመስደብ ላይ ተጠምደው በነበረበት ወቅት የሞረሽ ፓልቶክ ስለ ሁኔታው አንዳብራራ ጋብዘውኝ ካደረጉት ቃለ መጠይቅና ክርክር ያቀረብኩት መከራከሩያ ነጥብ። ዛሬ የፋሺስት ሥርዓት አስፋፊ ተረኛ የጂማው ኦሮሞ “የኮሎኔል አብይ አሕመድ” ወዳጅ ብርሃኑ ነጋ (ኢዜማ) “.ዛሬ አማራ ክልል እንዳንንቀሳቀስ ተደርገናል!!”  ብሎ ሲያጉረመርም፤ ለምን እንደሆነ ያለፈው ታሪኩና ገመናው ምን እንደሚመስል ማወቅ ነበረበት። ገመናውም ይሄው በጥቂቱ ላስታውሳችሁ፡
Efrem Masebo in Oakland EPLF Seminar
ጌታቸው ረዳ (ሞረሽ ቃለ መጠይቅ ከተወሰደ ቅንጫቢ ሰነድ)
ስለ ኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች ተጠይቄ ስመልስ እንዲህ ነበር ያልኩት

“፤…….ፖለቲከኞቻቸውስ ምን ይመስለሉ? እነሱ ደግሞ የባሱ ናቸው። ለምሳሌ፤ የግንቦት 7 ደርጅት ሚከተለው የፖለቲካ ጎዳና ፤ እጅግ “ፌክ” የሆነ ነው። “ኮስሞስ” ይሁን “አባስ” ማን አንደሆነ ትዝ አይለኝም “ ከግንቦት 7 ሸሽተው የመጡ” ታጋዮች “ግንቦት 7ን” “አስመራ ውስጥ የተቋቋመው የአንዳራገቸው እና የብርሃኑ ነጋ ሱቅ” ይሉታል “ግንቦት 7ን በፖለቲካ መልኩ ሲገልጹት። ይህ ድርጅት የበሰበሰ በጸረ- ኢትዮጵያ ሃይሎች የሚመራ አደገኛ ቅጥረኛ አይነት ድርጅት ነው (ማስረጃውን እሰጣችሗለሁ)። ግንቦት 7 ጸረ አማራ ነው። የግንቦት 7ዲሞክራሲ ታጋዮችም ይህንኑ ነግረውናል። በግንቦት 7 ጋዜጣ ርዕሰ አንቀፁ ላይ “አማራና ትግሬ ለዘመናት ገዝተውናል ዛሬ የደቡብና ኦሮሞዎች ተራ ስለሆነ ሥለልጣን የመያዝ ተረኛነቱ የኛ ነው.. የሚል ጽፏል።

ሦስተኛው ሰው የሆነው “ፓስተር ኤፍሬም ማዴቦ” የተባለው የሻዕቢያ ቅጥረኛ ስትመለከቱ፤ ከአንደበቱ የሚወጡ ንግግሮች ‘ጸረ ኢትዮጵያ” የሆነ የሻዕቢያ ነገረ ፈጅ ነው። ካሁን በፊት “እንሰት” በተባለው በወቅቱ እሱ እና “ፍቅሩ ሄሌቦ” የተባለው ጓደኛው በኤዲትረነት ሲመሩት በነበረው “ድረ ገጽ” ላይም  The First and the Last Ethiopian Millennium በሚል የኤዲቶሪያል ጽሑፍ “ዋጋ ቢስ የሆነ የኢትዮጵያ የዘመን መቁጠርያ” ሗላ ቀር የሆነ “ኮፕቲካዊ” ስለሆነ፤ ወደ “ግሪጎሪያን” የዘመን አቆጣጠር መለወጥ አለበት የሚል የኤዲቶሪያል “ጽሁፍ” አቅርቧል።”

እንዲህ ይላል፦


 In a little over two weeks time Ethiopians all over the world (except for some like me) will celebrate the first and the last Ethiopian millennium. Yes, this is the first millennium which is uniquely Ethiopian and, hopefully, if it is left up to people like me, it will be the last uniquely Ethiopian millennium. I am of the opinion that the current calendar should be discarded in favor of the Gregorian calendar which serves as the de facto world calendar”.


“ፕሮተስታንቶቹ” የግንቦት 7ቱ “ፓስተር” አፍሬም ማዴቦ እና አቶ ፍቅሩ ሃሌቦ” የሚቆጣጠሩት “እንሰት” የተባለ በርከት ያሉ ከኦነግ ማይሻሉ “የደቡብ ባንዳዎች እና ጸረ ኦርቶዶክስ የሆኑ ”ምኒሊክን” “ኮሎኒያሊስት” እያሉ የሚዘልፉ አንዳንድ ፕሮተስታነት ነን የሚሉ አንዳንድ የደቡብ ሊሂቃን  የተሰባሰቡበት “ጸረ ኢትዮጵያ” ቅስቀሳ የሚጻፍበት ድረገጽ በመላ ዓለም የምንገኘው ኢትዮጵያዊያን በ2000 ዓ.ም “አዲስ ሚሊዮኔም” ስናከብር “ፕሮተስታንት የሆኑት “ፍቅሩ እና ፓስተር ኤፍሬም ማዴቦ” ካላንደራችን “ዓረባዊ” ስለሆነ “የኛ ዘመን መቁጠሪያ ስላልሆነ” እንደ አውሮጳዊያን እንቁጠር በማለት በመቁጠሪያችን ያለው ከግብፅ ዓረቦች ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸው የወራት መቁጠሪያ ስሞችም “መወገድ” እንዳለበት እና “ሴፕተምበር” “ጁን” “ጁላይ” እያልን እንድንቆጥር ከሰበኩት “አደገኛ ባንዳዎች” ከምላቸው የደቡብ አካባቢ ግለሰቦች አንዱ እሱ ነው። እንደህ ሲሉ፤ የትኛው ሃይማኖት ለመንካት እንደሆነ ከናንተ የሚሰወር አይደለም፡፤ በዓሎቻችንን በሙሉ ለመሰረዝ እንደሆነ የታለመ ነው። ኤርትራኖችም በግድ ቢጫንባቸውም፤ በምንም መልኩ ከጥንቱ የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር እና በዓላት መራቅ አልቻሉም።


በርከት ያሉ ወገኖች ስለተበሳጩ፤ አንድ ወዳጄ ወደ ኤዲተርያሉ እንዲሀ ሲል ሰፊ “ትችት” ጽፎላቸው ነበረ ፡-

“Why don't we keep our own Calander ?
Dear Enset: I will like to join the world for democarty, and Humanbiengs value.You advocate today to use the european calander, as it is used by rest of the world. Will you then also advocate to have the same relgion, while most of the people. believe in it.”
ሲል ባንዳዎች ሊሰሙት ሚገባቸው መልስ ሰጠው።


 የግንቦት 7 Public Relation Officer- (የሕዝብ ግንኙነት) የሆነው “ፓስተር ኤፍሬም ማዴቦ” አደገኛ ጸረ ኢትዮጵያ ነው የምላችሁ ምክንያት እነዚህ፡ሚመሩት ግንቦት7 የተባለው ጸረ ኢትዮጵያ “ድርጅት”፤ መጪው ስርዓትም ከወያኔ አንደማይሻሉ ለማሳየት ቀላል ነው። ግምት ሳይሆን በተጨባጭ ነው የምላችሁ። አንድ ማስረጃ ላቅርብ (በኮሎኒ ተይዘው እንደነበሩት እንደተቀሩት አፈሪቃኖች የካላንደር ለውጥ እንድናደርግ ከከፈቱት ጸረ ኢትዮጵያ ዘመቻው ሌላ)፡ ስለ ኤርትራ በሚመለከት የተናገረውን “በሬከርድ” እንዲያዝልኝ ቃል በቃሉ የተናገረውን ላንብብላችሁ። ይህንን ሪከርድ እንድትይዙልኝ እያንዳንዳቸሁ እጠይቃለሁ።


በ2012 ኦክላንድ ካሊፎረኒያ የሻዕቢያ “ፌስቲቫል”ግንቦት 7 ን ወክሎ  ከተናጋሪዎቹ አንግዶች አንዱ ሆኖ በተገኘበት ጊዜ የተናገረው “ንግግር” ልብ ብላቸሁ እንድትከታተሉኝ ነው የምጠይቀው። ከኤርትራዊያኑ አድማጮቹ ኣንዱ ተነስቶ ግንቦት 7 ለወደፊቱ  መንግስት ሲሆን “በኤርትራ” ላይ ያለው “ፖሊሲ” አንዲያብራራለት የጠየቀውን ልንገራችሁ።
እንዲህ ይላል፦(
Question. I believe you are Public Relation Officer for Ginbot 7. I want to know what is your position as Ginbot 7 officer on the Sovereignty of Eritrea.    “Secondly”, What is your position as far as the border issue is concerned? I ask you this, because when Ethiopia declare war on Eritrea- it did it so, with the permission of the Ethiopian parliament. As far as I know that declaration is not been official repeal. So will your organization repeal, If your organization has that opportunity to leadership?

Answer ;- Efrem Madebo’s response:- “It is a very nice question. Especially on the sovereignty of Eritrea; as far as I am concerned, as far as I my organization is concerned “Eritrea is a sovereign regime. It is a country,  It is a Nation now, it is a country by itself. (We are working) , so that countries sovereignty and territorial integrity is respected and fully accepted by my organization. ( Eritrean audiences stood up and clap their hands for Efrem’s conformation of Eritrea accepted now and for the future as a country by Ginbot 7 ) Everything we do comes out of that respect!.....”

Efrem continues on and on. Finally said፤-  “ I went to Eritrea. When I was a young boy going to Eritrea at 20 years of age~ I was a product of Mengistu. A lot of propaganda in me. “The Arab Delala/የዓረብ ደላላ”, “ ሊሸጥዋት ነው” (I think it would make sense if I explained it in Amharaic said Efrem Madebo to his Eritrean Audience). The audience laughed loudly.), I am a product of that propaganda. Only these two flags will stand together when only the two people and the two government “especially the people) stand together (ጭብጨባ). So if we want to live together, we have to respect each of us territory and integrity of each other’s country. There are extremely, extremely, extreme elements in Ethiopia- especially in the Diaspora. Who still declare war on Eritrea, especially some radio stations. There are some radio station in my part of Diaspora that starts its program with the musical introduction declaring the “Ethiopia-the 14 Provinces”. Do you know what 14 provinces mean? (audience response….) Yea, yea, “elements like that!” said Efrem “belittling the patriotic and nationalist demand and assertion as war mongers and anti Eritrean people.” These are very, very extremist elements ነፍጠኛ.  We do have those extremist elements still in our community. In our Ginbot 7, we have toned down the very, very extremists; we cooled down the extremist elements, which are negative elements, who do not respect the Eritrean sovereignty. Those are people who live in the 60’s or before that era. Let me give you one example in the world that resemblance to Eritrea. Israel. Israel is a small country in size, but very strong country. Size in bigness is irrelevant. Ethiopia and Eritrea are different in size. Ethiopia, even though big in size Ethiopia needs Eritrea. My son is born from Eritrean mother. I do not want my son to fight against his own country “Eritrea” because he is 50% Eritrea and 50% Ethiopia. Let us tell our kids, that “these are Nations that can live together respected each other living separately on their own sovereignty”. We as Ginbot 7 , we are working together to get this “cancer” (Woyane), so we can live together healthy life.”  (Efrem Madebo- Panel discussion Western USA region August 10,11 and 12 … 2012 Oakland California)

እነዚህ ናቸው “ግንቦት 7ን የሚመሩ”። ምኒሊክ እና መለስ ዜናዊ አገር የወረሩ ኮሎኒያሊስቶቸ ናቸው። ብሎ Negotiation, nation building, and the naysayers) March 2012 ብሎ፡ ኤፈሬም መአዴቦ የጻፈው “አቡጊዳ” በተባለወ የተለጠፈውን ጸረ ምኒሊክን መጣጥፍ አንበቡ። የኔ ወገኖች ፡ ግንቦት 7 ይህንን ይመስላል። “ኢክስትሪሚሰት ስትባሉ”  ምን ተሰማችሁ? “ኤርትራ እስራኤላዊቷ “ዳዊት” ስትባል ፤ ኢትዮጵያ ደግሞ “ያረጀች “ጐልያድ” ስትባል? የኢትዮጵያ ግዙፍነት “Irelevant” (ዋጋ ቢስ) ነው፡ “ዋጋ የሌላት አገር” ስትባሉ ምን ተሰማችሁ? ይህ ክህደት አንጀት አያቃጥልም? ከዚህ ወዲያ ምን የከፋ የባንዳ ድርጅት ሊኖር ይችላል? ግንቦት 7 የከፋ ባንዳ ከመባል ምን ሥም ልትሰጡት ትችላላችሁ? የአርበኛችሁ የአንዳርጋቸው ግንቦት 7 ይህንን ይመስላል!!! የግንቦት 7 ማንዴላዎች እና የቀራኒዮው ክረስቶሶቻችሁ “ድርጅት” መሪዎቻቸሁ ይህንን ይመስላሉ። ግንቦት 7 መሪዎች ለኢትዮጵያ ጥብቅና የቆሙ ናቸው ስትሉ አታፍሩም? “እኔም አንዳርጋቸው ነኝ” “እኔም ግንቦት 7 ነኝ” ስትሉ አታፍሩም?

ይህ እና የመሳሰሉ የግንቦት 7 ሰዎች ናቸው ፖለቲካውን የሚያሾሩት። ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉትም “ከእጅ ማይሻሉ ዶማዎች ናቸው”። የታሰሩ ጋዜጠኞችም ሆኑ ኣሁን ያሉት “የሚሽከረከሩት “በኦነግ እና በመሳሰሉ” ሙገሳ እና ግዙፍነት አስፈሪነት ሚሰብኩ “ሸክስፔር ዎናቢ”  “አማርኛ አሳማሪ” እና “በተምበርካኪ” ወጣት ጋዜጠኛ የተሞላ ነው። ከተመስገን እስከ እስክንደር!፡

አይስክሪም እና ጫት ሲልሱ እና ሲቅሙ የሚውል የፓል ቶክ ወጣቶችም በነዚህ መሰሪዎች ሕሊናው ተቦውዞ “አንዳርጋቸው ማንዴላ፡ እኛም አንዳርጋቸው፤ ቪቫ ግንቦት 7” እያለ ላንቃው እስከኪያብጥ ሲጮህ የነ በርሃኑ ተክለሰውነት ሲክብ ይውላል። ይህ ሁሉ ወጣት “ወደ ኤርትራ ሂድ ብትለው አይሄድም”። በአፉ ግን ማይክ ይዞ “ወያኔ ሊወድቅ 6 ወር ቀርቶታል” ይላል። በቅርቡ የወያኔ ገበና በማጋላጡ ምስጋና የቸርኩትን “ወያኔ ነበር” የወያኔው X-ሚኒሰትር የነበረው “ኤርሚያስ ለገሰ” የተባለውም፡ “ጐሽ፤ ጐሽ” ሲሉት ሰከረ እና ወደ ኢሳት እና ጉንበቴዎች ተጠግቶ “ስለ አንዳርጋቸው ስብእና” ሲገልጽ እና “አንዳርጋቸው ማንዴላ”እያለ ሊያቃዠን ጀምሯል።

ከአሲምባ ጋር ባለፈው ቃለ መጠይቄ አንደገለጽኩት “ትግሉን” እያበላሹት ያሉት “የወያኔ አገልጋዮች የነበሩ፤ ተጣልተው የወጡ፡ ለወደፊቱም አገሪቷን ልክ በወያኔ አምሳያ የሚመሯት ያው “አንዳርጋቸው እና ኤፍሬም መዴቦ አይነቶቹ ናቸው” ብዬ ገልጫለሁ። አሁን ድሮ ኤርሚያስ የተባለው ደግሞ ስለ አንዳርጋቸው ማንዴላነት ሊሰብከን ሲሞክር “”ወጊድ በሉት”። ለነሱ “ሁሉም ነገር” አሳፈሪ አይደለም። ሁሉም ወያኔ ስላገለገሉ፤ እርስ በርስ ይሞጋገሳሉ። ኤርሚያስ የተባለው ሰው “የፍስሃ እሸቱን” ዕጣ ፈንታ ሳይገጥመው “ረጋ ብሎ” ግራ ቀኝ እያስተዋለ “ሌላ መጽሐፍ” ቢጠርዝ ይሻለዋል እላለሁ( ወንድማዊ የመጀመሪያ ምክር!)። ከወያኔ ወጥተው ደህና ትግሉ ያካሂዳሉ ሲባሉ ተመልሰው ጭቃ ይረግጣሉ። ምን ማድረግ ይሻላል? ስዬ ሆሆ ሲሉለት ፤ የነበሩትን ጀሌዎቹ ‘በሗላ’ መለስ ዜናዊ ሲሞት ሊሰሙት ያልፈለጉትን ነግሮ “አንጀታቸውን አሳረረው”። ጉደኛ ዘመን ነው!

ውጭም ይሁኑ አገር ውስጥ ያሉት ተቃዋሚዎች፤ አንድም ሁለትም ናቸው። ፖለቲከኞቻቸሁ በጣም ይገርሙኛል። ግንቦት 7 ም ይሁኑ የመሳሰሉት ስለ ዲሞክረሲ እና ስለ መጪው “የስርዓት ሕዳሴ” ሲናገሩ ይገርሙኛል። ለምሳሌ “ብርሃኑ ነጋ” ምንድ ነው ሲል የነበረው? ። ሕዝብ እስከወሰነ ድረስ “ማንኛውንም ውሳኔ እናከብራለን”፡ የምንታገለው ይህንን ለማስከበር ነው ይላል። ማንኛውንም ውሳኔ የሚለው “የመገንጠልም ጭምር ነው። አማራ ይገደል የሚል ውሳኔ ህዝብ ካጸደቀ “የሕዝብ ውሳኔ ነውና አንዲጨፈጨፍ ያከብራል” ማለት ነው። ጋምብሌ፤ ጉራጌ፤ኦጋዴን፤ኦሮሞ ትግሬ፤ እገነጠላለሁ ካለ “የሕዝብ ድምጽ ነውና ፤ ውሳኔውን ያከብራል። በምንም ታምር በጠምንጃ አንይዘውም  እንደ ወያኔ” ብሏል”። ትግሬዎች ሥልጣናቸው ካጡ ወደ መገንጠል ስለሚሄዱ እንደብርሃኑ አባባል “ሕዘብ ከወሰነ” ትግሬዎች አገር የማፍረስ እና ለመገንጠል መብታቸው ይከበራል ማለት ነው?

 ይህ ንግግር በኢሳት እና ጥምረት በጠራው ስብሰባ ነግሮናል። እነዚህ ናቸው የወያኔ ገጽታ እና ባሕሪ ስርዓት የሚደግሙት።
አመሰግናለሁ ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ)

Thursday, February 20, 2020

አብዛኛው ትግሬ ጸረ አማራ ነበር የምንለው ከዚህ በመነሳት ነው ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ) 02/20/20



አብዛኛው ትግሬ ጸረ አማራ ነበር የምንለው ከዚህ በመነሳት ነው
ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ)
02/20/20

ይህ በየ ማሕበራዊ መገልገያ ድረገጾች እየተዘዋረ የምታዩት ይህ ቪዲዮ፤ ትግሬዎች በጸረ አማራነት ተቃኝተው ነበር ስንል በማስረጃ ነበር። ብዙ ማስረጃዎች በመጻህፍቶቼ ሰጥቻለሁ። ዛሬ ደግሞ ይህ ቪዲዮ ስታደምጡ ክርክራችን ትክክል መኖሩን ያረጋግጣል። ለዚህ ነው ህወሓት ፕሮግራሙም ሆነ ሕገምነግሥቱና ታጋዮቹ በጸረ አማራነት ቅኝት የተቃኙ ናቸው የምንለው። እኚህ አዛውንት እናት እንዲህ ይላሉ፤

ትግርኛው እንዲህ ይላል፡

ወዲ ትግራይ ናዓ በሎ
እዚ ኣድጊ ኣምሓራይ ክኸድ ነቒሉ ኣሎ፡

የትግራይ ልጅ ና በለው
አህያ አማራ እንዲቀብረው”

አርስዎ ከዘፋኞቹ አንዱ ነበሩ? ብሎ ጋዜጠኛው ሲጠይቃቸው፤ የመለሱት መልስ “አዎ”። እንግዲህ ባጭሩ ሴትዮዋ የምትለው፤ አህያ አማራ መሞቻው ተቃርቧልና ና ተሎ አሰናብተው (ቅበረው) ነው የምትለው። እርኩሱ ወያኔ እነዚህ የዋሆችን በመጠቀም ነው የትግራይ ሕዝብ በማወቅም ባለማወቅም ጸረ አማራ እንዲሄድ አድርጓል የምንለው። (ጌታቸው ረዳ -ኢት ሰማይ)

Wednesday, February 19, 2020

ንምስረታ ሪፑብሊክ ትግራይ ማእቶት (ቅያዕ) (በአማርኛ እና በትግርኛ) ጌታቸው ረዳ (ኢትይ ሰማይ)


ንምስረታ ሪፑብሊክ ትግራይ ማእቶት
(ቅያዕ)
(በአማርኛ እና በትግርኛ)
ጌታቸው ረዳ (ኢትይ ሰማይ)

“ንምስረታ ሪፑብሊክ ትግራይ ዝረድእ መቃላጠፊ ማእቶት ኣብ ቀረባን ኣብ ርሑቕን ግምት ዘእተወ ምጣነ ሃብታዊ መጽናዕቲ ተባሂሉ ዝግመት ኣብ ውሽጢ ትግራይ ንዝኸፍቱ ሓደሽቲ ቤት መብልዕ ንቻይናውያን ተባሂሎም ንማሕረድቲ ዝተዳለው መቕተሊኦም ዘገልግል ሸጓጉጥ ዝተዓጥቁ ብህወሓት ዝውነኑ ኣኽልብቲ ህወሓት።”

እወ፡ ወያነ ብ80 ሚሊዮን ብር ዝውድእ “የአህያ ቄራ” ዝባሃል “መሕረዲ ኣእዱግ” (ሉኳንዳ) መስሪቱ “ሥጋ አድጊ” ንቻይናውያን ምሻጥ ዘየሕፈሮ’ዶ፤ ነኽላብ ንድሕሪት ክብል። ወይ’ት ጉዱ!
    
አማርኛ ትርጉም
በቅርቡ ለትግራይ ሪፑብሊክ ምስረታ ገቢ ማሰባሰቢያ የሚውሉ ለወደፊቱ ትግራይ ውስጥ በቻይናውያን ለሚከፈቱ ምግብ ቤቶች የሚያገለግሉ ለእርድ የተዘጋጁ የህወሓት ውሾች!



Friday, February 14, 2020

ምርጫ ወቅት ኮሮጆ ቢሰረቅ ብጥብጥ ያስነሳል ማለት ቅዠት ነው ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ)

ይህን ማሃይም ወጣት ይዘህ በምርጫ ወቅት ኮሮጆ ቢሰረቅ ብጥብጥ ያስነሳል ማለት ቅዠት ነው

ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ)


የጣሊያን ፋሺስቶም ሆኑ የጀርመን ናዚዎች የመጀመሪያ ትኩረታቸው የወጣቱን ሕሊና መበረዝ ነበር። “ኦፔራ ናዚዮናለ ባሊላ” የተባለው የመጀመሪያው የጣሊያን ፋሺሰቶች ወጣት ብቅል ነበር። በአገራችን የመጀመሪያው የፋሺስቶች አገር በቀል ወጣት ብቅል (ጥንስሱ) የተመሰረተው ትግራይ ውስጥ ትግራይ ‘ደደቢት’ እና ኦሮሞ “ባሌ” ውስጥ ነበር።

ከዚያም ፋሺሰት ድርጅቶቹ አድገው ቀስ በቀስ ወደ መንግሥትነት ሲሸጋገሩ የ28 አመት የፋሺዝም መንግሥታዊ ትምህርት በየትምህርት ተቋማት እና አብያተ ጸለቶች በማስፈራረትም፤ በገንዘብም ይሁን በቅስቀሳም ሁሉ ወጠቱን በመበረዝ “ሳብቨርዢን” ተብሎ በሚታወቀው የሕብረተሰብ የብከላ መረብ አስጠምደው አሁን ላለንብት የፋሺስቶች የሥልጣን ሽግግር ውስጥ ወጣቱ በፋሺዝም ርዕዮት ተጠምቆ አገር ከሚያፈርስ አብይ አሕመድ የተባለው ከ28 አመቶቹ ባሊላ ፋሺስቶች የተገኘ ሌላ የፋሺስቶቹ አሸጋጋሪ ግለሰብ ወደ መደገፍ ደርሰዋል።

በ28 አመት ውስጥ በፋሺዝም ትምህርት የተበከሉ ወጣቶች ጉዳቸው የሚከተለው ነው።  ‘ወጣት ልጃገረዶችን ከየትምህርት ተቋማቶች አፍኖ ከመጥለፍ እስከ የሴቶች ጡት ቆረጣ እና ሰው ዘቅዝቆ በአደባባይ መስቀል፤እንዲሁም አማራ ተማሪዎችን እየለዩ ከየትምህርት ገበታቸው ከፎቅ እየገፈተሩ መግደል፤ቤተ ጸሎት ማቃጠል የሰው አንገት አርዶ ሬሳን በመኪና መጎተት ተሸጋግረዋል።

ወጣት ይንገስ፤ አዛውንት ይወገድ ሰትሉ የነበራችሁ ግራ ተጋቢዎች ይኼው ዛሬ ወጣት ነግሶ ዛሬ ይኼው ለ28 አመት በተለያዩ ወንጀሎች ተሰማርተው ዜጎች ሲያሰቃዩና ሲገድሉ ሲሰውሩ የነበሩት ወጣቶች እስከ ጠ/ሚኒስቴርነት ድረስ ወደ ሥልጣን በመውጣት ለነሱ አጨብጫቢ የሆኑ የፋሺሰት “ባሊላ“ ወጠቶችን በየከተማው በማሰማራት “ወያነ ትግራይ” ሲሰራው የነበረው ወንጀል እንደገና በመፈጸም “ሌላ 28 አመት” ተጨማሪ ብሔራዊ ወንጀል  እንዲፈጽሙ  “ይንገሡልን” በማለት “በዓረብ አገር በዱባይ” እና “በኢትዮጵያም በናዝሬት” ያሉ በዚህ ፎቶግራፉ ላይ የምታይዋቸው የተበከሉ የፋሺሰት “ባሊላዎች” ለሁለተኛ ዙር የፋሽስቶች ሽግግር መንግሥት እንዲመሰረት ድጋፋቸው እየሰጡ ነው።

ታዲያ እኔ የገረመኝ እንደዚህ የመሳሰሉ በፋሺስቶች ርዕዮት የተበከሉ ወጣቶች ተይዞ ነው ገና ይመጣል እየተባለለት ያለው የምርጫ ተብየው” ሽር ጉድ” ኮረጆ ቢሰረቅ አገር አንቀጥቅጥ ብጥብጥ አስነስቶ ፋሺስቶችን ያስወግዳሉ የሚባልላቸው?

ለመሆኑ ይህንን አብይ አሕመድ የተባለው የስለላ መረብ በመዘርጋትና በመቆጣጠር የአገር ምስጢሮችን ለኦነግና ለሻዕቢያ አሳልፎ በመስጠት የታወቀው በብዙ ብሔራዊ ወንጀል ተጨማለቀው (እራሱም ወንጀል መፈጸሙ ፓርላማ ውስጥ ያመነ) የሥልጣን ጥም ያሰከረው “ጂሃዳዊ ወንጀለኛ” ሰው ከያዘው ኢሕጋዊ-ሥልጣን ማስነሳትና እሱንም ማሰር የሚያስችል ብዙ ብሔራዊ ወንጀሎች ተፈጽሞ ባለበት “አሁን! አሁን! አሁን ዛሬ!” እንኳ ሕዝቡ መነሳት ያልቻለ፤(ያውም “አግዚአብሔር ሃይላችን ነው” እያለ በአቡነ ዘበሰማያት መዘዝ የተጠመደ “ጥፊ እና መንገላታት እራቱ ያደረገ” ማሕበረሰብ ተይዞ) በመናኛና ማጃጃያ ምርጫ ተብየው “ኮሮጆ” ተጭበረበረ ቢባል ይህንን “ጂሃዳዊ የሥልጣን ጥመኛ” ሰው የሚያስወግድ ሰላማዊም ሆነ የብርት ትግልና ብጥብጥ ይነሳል ብለው የሚቃዡ እና ተስፋ የሚያደርጉ ሰዎች ሳደምጥ እጅግ ይገርሙኛል። እስካሁን ድረስ የተፈጸመው ግፍ ይበዛል ወይስ ስለ ትንቢት የምርጫ ወቅት በብጥብጥ ተስፋ አብይን ማስወገድ? የትኛው ግፍ ይበረታል?

ፍራሽ አዳሽ የሚባለው ቀልድ የሚጫወተው ትምህርት ሰጪው ቀልድ ሰሪው “ተስፋሁን ከበደ” እንዲህ ብሎ ነበር፡
“አያ ጅቦ አንድ ቀን ባለቤቱ አርፋበት አህዮች መርዶውን ሰምተው “አይ ምንም ጠላት ብንሆን ‘ሓዘን ነውና’ ብለው ሰብሰብ ብለው ለቅሶ ጋ ይሄዳሉ ። አንድ ሞሾ አውራጅም ፊት ለፊቱ ቆማ “ሙሾዋን መውረድ ጀመረች”፡ አህዮቹ ልክ ዱንኳኑ በር ሲደርሱ
“ምንም እሩቅ ቢሆኑም ይሰማል ድምጸዎ
አስገራሚ ነው ግርማ ሞገስዎ
እንደምነሽ ምን ነካ አበዎ..”
እያለች ሙሾ ስታወርድ
አያ ጅቦም ወደ ድንኳኑ እንዲገቡ እየጋበዛቸው ‘ግቡ ግቡ’ እንኳን ደህና መጣችሁ እያለ እንዲህ ሲል ለሙሾ አውራጅዋን መለሰላት፡
“እውነት ተናግረሻል እውነትም ብለሻል
ይህ ሁሉ ሐዘንተኛ ምን ይብላ ብለሻል!” አላት ይባላል።

እንዲህ ያለ ወደ ጅቦች ድንኳን የሚንጋጋ የጅቦች ሙሾ አውራጅ ባለበት የወጣት መንጋ ፋሺሰቶችን ስርዓት ይጥላል ብሎ ተስፋ ማድረግ ውሃ መዝገን ነው። አሳዛኙ ክስተት ግን “ሁሌም ራስጌና እግርጌ መለየት የማይችል ወጣት በማጎብደድ ይጀምርና በመጨረሻ እራሱን ማንገላቻ እስርቤት ውስጥ ገብቶ ራስጌም እግርጌም በማይለይበት ማሰርያ ቤት ተኝቶ የገዛ እራሱ ያገኘዋል።
አመሰግናለሁ
ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ)



Sunday, February 9, 2020

የአባይ ሚዲያ ዜና በሻዕቢያና በወያኔዎቹ ቅኝት! ከጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ)

የአባይ ሚዲያ ዜና በሻቢያና በወያኔዎቹ ቅኝት!
ከጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ)
ፎሮግራፍ ላይ በኩራት ቆሞ የሚታየው የዋሺንግተኑ አገር ወዳዱ  ገብርኤል እና ምጽዋ ላይ ኤርትራ ላይ የተዋደቁ አርበኞቻችን ናቸው። ክብር ለተሰውትና በጀግንንት ዛሬም ለቆሙት ሁሉ ይሁን!

ዜና ሳጣ አለፍ ብየ የማደምጠው ‘አባይ ሚዲያ” ተብሎ የሚጠራው  በራዥ የድሮ የግንቦት 7 አለቅላቂ ሚዲያ፣ በትናንትናው ዜናው  “ከዘመነ አክሱም ጀምሮ የጀግኖች አጥንትና ደም የተከሰከሰበትን የኢትዮጵያ የባሕር ወደባቸን “ምጽዋ!!” በአሜሪካን የስለላ ሳተላይት አና በወያኔ ተዋጊ ባንዳዎች እየታገዘ ምፅዋን የያዘበትን “ፈንቅል” ብሎ የሚጠራው በየአመቱ የሚያከብረው የኢሳያስ ጉራ መንዣ በዓል፡ አባይ ሚዲያ ተብየው  ውዥምብራም ሚዲያ በቃለ አጋ’ኖ እየቀባባ በኢትዮጵያ የቀድሞ ሠራዊቶች ላይ ግልጽ ስድቡን አጣጥሞ በዜና መልክ ሰርቶለታል።

አንብቢ ተብላ በሚዲያው ደናቁርት የዜና አርታዎች የተሰጣትን ምሲኪንዋ የዜና አንባቢ እንዲህ ስትል በሚከተለው የአባይ ሚዲያ ድንቁርና የሚዲያው ድብቅ ማንነት ልጽ በማድረግ በድሮ የኢትዮጵያ ሠራዊት ላይ  የስድብ ውርጅብኝ በዜናው አስራጭቷል።

ከአዲስ አበባ የሚተላለፈው የዚህ አውታር ዜና አንባቢ እንዲህ ትላለች፡-

“ኤርትራ 30 መትዋን በድምቀት አከበረች። በማለት 150 ያክል ተሰብሳቢ የተገኘበትን ስብስብ “ድምቀት” እንዳለው አስመስላ አንብቢ የተባለቺውን እንዲህ ብላለች፡

“ኤርትራ 30 መትዋን በድምቀት አከበረች።   “ፈንቅል ለልማት” በሚል መሪ ቃል 30ኛው አመትዋን ስታከብር የአገሪቱን ፕረዚዳንት እና ሌሎች የስቪልና የወታደራዊ መሪዎች መገኘታቸውን ያገሪቱ የዜና አውታሮች ገልጸዋል። ፈንቅል ሻዕቢያ ምፅዋ የነበረው  ከባድ የደርግ ሠራዊት የደመሰሰችበትን 30ኛ አመት መሆኑን  ተዘግቧል። በባዓሉ ላይ የተገኙት ክቡር ፕረዚዳንት ኢሳያስ  አፈወርቅ ጉንጉን አበባ አስቀምጠዋል። የሰሜናዊ ባሕር የባሕር ሃይል ዋና አዛዥ የሆኑ ብ/ጀሜራል “ተኽለ ልብሱ” ሃገራዊ በዓሎቻችንን ‘ትግላችንን” ለማስታወስና ምዕራፎቻችንን የምንገመግምበት ነው’ ሲሉ ብ/ጄኔራል ተኽለ ልብሱ በዓሉን በማስመልከት ተናግረዋል”። ይላል የሻዕቢያው ቱልቱላ “አባይ ሚዲያ”።

እንግዲህ ወገኖቼ ይታያችሁ። የተደመሰሰበት በዓል” ብሎ ባልተገረዘ አንደበቱ የሚገልጽ ጠላት እንጂ ኢትዮጵያዊ ሚዲያ ነኝ የሚል የአገሬውን ሠራዊት “የተደመሰሰበት ዕለት” እያለ እንደጠላት አሳፋሪ ቃላት ሲጠቀም የብከላው እርከን ጣራ መድረሱን ያሳያል።

  ከዘመነ አክሱም ጀምሮ ከዚያም አምደጽዮን ከሸዋ ገስግሶ ምፅዋን ከቱርኮች ያስለቀቀ፤ቀጥሎም በገናናው ይለስላሴ ተክብሮ ቆይቶ በከሃዲውና ቅጥረኛው የትግሬ ባንዳዎቹ ፈቃጅ ሰጪነት የተነጠቅነውን ምፅዋን እያጋነነ ከሻዕያ የዜና አውታር በባሰ ምልኩ እያንዳንድዋን ቃል ከጠላቶች የተበደረውን የስድብ ቃል እየተዋሰ ለጠላቶቻችን በዓል ከማዳመቁ ባለፈ ጅግናውን ፡”የኢትዮጵያን ወታደር” የደርግ ሠራዊት” እያለ ባንዳዎቹ ወያኔና ሻዕቢያ የሚጠቀሙትን “አዋራጅ ቃል” በመጠም አባይ ሜዲያ የተባለው አዲሱ የሻዕቢያ ቱልቱላ መላው የድሮ የኢትዮጵያ ወታደር ዘልፏል።

ያ ሁሉ በሺዎች የሚቆጠረው ምጽዋ ላይ የተሰዋው ጀግና ሠራዊት “የኢትዮጵያ ሠራዊት እንጂ አባይ ሚዲያና ሻዕቢያ እንደሚሉት-“የደርግ ሠራዊት” አልነበረም።  ዘንግቶት የአፍና የብዕር ወልምታ እንኳ ቢሆን ግድ አልነበረም፤ ሆኖም እንዲህ ያለ የተጠናቀረ ዜና አስነዋሪ ቃላቶች (ወያኔና ሻዕቢያ የሚጠቀሙበትን የደርግ ሠራዊት፤ የተደመሰሰበትን እያለ) በመጠቀም ይቀር የማይባልብትን ወራዳ ና ሰርቶ ሠራዊቱን ማዋረድ ተገቢ ስላልሆነ ለዚህ ጣቢያ የቅሬታ ደብዳቤ እንዲጽፍና የሚዲያው ባለቤት “ይፋዊ ይቅርታ” እንዲጠይቅ መላው የድሮ ኢትዮጵያ ሠራዊት ማሕበርና ግለሰቦች ማሕበር ካላችሁ “በደብዳቤና በኢመይል እንዲወገዝ” እጠይቃለሁ።

ለዚህ ደግሞ ሃላፊነት የሚወስደው የጣቢያው ባለቤት ስዊድን አገር የነበረው የግንቦት የእነ ብርሃኑ ነጋ ፕሮፓጋንዳና ስብሰባ እያሰራጨ ፖለቲካ ሲሰራ የነበረ የዛሬ የሻዕያው ቱልቱላ የዛሬው የአባይ ሚዲያ ቲ/ቪ ባለቤት ነው። ስለዚህም ኢትዮጵያኖች በታቻላችሁ ሁሉ ይህንን አቃጣሪ ሚዲያ መቃወም ይኖርባች የምለው

ባንድ ወቅት ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም እንዳሉት- ላለፉት 30 አመታት የኤርትራ ታሪክ በሻዕቢያና በወያኔ ግምባር መሪነት አዲስና የማናውቀው መልክ እየያዘ መጥቶ አሁን ካለበት አሳዛኝ ደረጃ ደርሰናል። ትክክል ብለዋል። በ1970ዎች ውስጥ የኢትዮጵያን ታሪክ እኛ በማናውቀው በተወላገደና በሚያስፈራ ሁኔታ፤በተቀናጀ ስልት ታሪካችንን የሚያበላሹ በርካታ መጻሕፍት ተዘጋጅተው በዓለም ሙሉ ተሰራጭተዋል። ፕሮፌሰሩ ይህንን ሁኔታ አስመልክተው እንዲህ ይላሉ፡ “በዚያ ጊዜ የኢትዮጵያዊነት ስሜት  “እንደ አድሃሪነት” መቆጠር የተጀመረበት ጊዜ ስለነበር ከኢትዮጵያ በኩል መልስ ለመስጠት የሞከረ አልነበረም” በማለት  አሁን  ላለንበት ውርደት እኛ በተውነው ክፍት ቀዳዳ በመግባት ጠላቶች ዓላማቸውን እንዴት እንዳሳኩ ነግረውናል ።

 አውነት ነው። መቼም ቢሆን ጠላት የሚወጣው ከውስጥ ነውና ጠላት ብቻውን “ያለ የውስጥ ተባባሪና ፕሮፓጋንዳ አሰራጭ” መልዕከቱን፤የሚጠቀምባቸው ቃላቶችን፤ እንዲሁም ተክለሰውነቱን መቅረጽ ከቶ አይቻለውም። ላለፉት 30 አመታት በሠራዊታችን እና በሕዝባችን ሉዓላዊ ክብር የደረሰበትን የሻዕቢያና የወያኔ ትግሬዎች ስድብና ውርደት በውስጥ ሚዲያዎችና ተባባሪ ግለሰቦች እየታገዘ የሕዝቡንና የወጣቱን ንቃተ ሕሊና “4ቱን የክለሳ/ በሳብቨርዥን እርከኖች” ተጠቅሞ ሕሊናን እያጠበ “ኢትዮጵያን እንደ ወራሪ” እሰደቡ ‘ጸረ ኢትዮጵያ’  እንዲጓዝ መደረጉ የሚታውቁት ነው። ዛሬ ደግሞ ያንን የህሊና አጠባ እንዳይበቃ እንደ አዲስ የገባው “አባይ ሚዲያ” የተባለ የዜና አውታር “የሻዕቢያና የወያኔ” ቃላቶችና ፕሮፓጋንዳዎችን እየተዋሰ ለእናት አገራቸው የተዋደቁት የምጽዋ አርበኞችን “በሻዕቢያ ተዋጊ የተደመሰሰው የደርግ ሰራዊት” እያለ (እግዜር አባይ ሚዲያን ይደምስሰውና) የአርበኞቻችን እናቶች ፤ አባቶች፤ቤተሰቦችና መላው አገር ወዳድ ዜጋ አንጀት አሳርሯል።

ይህ ሚዲያ በታቸለ መጠን “ቦይኮት” እንዲደረግ እና ውግዘት እንዲደርሰው ቢያንስ የቀድሞ የኢትዮጵያ ሠራዊቶች ማሕበር ካላችሁ በማሕበራችሁ ደብዳቤ በመጻፍ የውግዘት ደብዳቤ ለዚህ “አሳፋሪና በራዥ ሚዲያ” በመጻፍ ተቃውሞኣችሁን እንድታስተላልፉለት እጠይቃለ ። እንደዚህ አይነት ግልጽ ፕሮፓጋንዳ ለ30 አመት ተቦክቶ ፍሬ አፍረቶ እሱን እየታገልን ባለንበት ወቅት አሁን እንደገና “አባይ ሚዲያ የተባለ” የሻዕቢያ አለቅላቂ” ምን ታመጡ ብሎ ባርበኞቻችን እና በሉዓላዊ አገራችን ኢትዮጵያ ላይ የጠላት ፕሮፓጋንዳ በማሰራጨት ተራራው ጫፍ ላይ ለመውጣት በምንሞክርበት የትግል ዘመን እንደገና እግራችንን እየጎተተ ወደታች አንድንንሸራተት እያደረገ ያለው የሚዲያ ፕሮፓጋንዳው በጥብቅ እንቃወማለን።

ተራራው ጫፍ ላይ ወጥተን የተዋረደቺውን የኢትዮጵያን ሰንደቅዓላማ አውለብልበን ተደመሰሰ እያሉ የሚያዋርዷትን የእምየ ኢትዮጵያ ሰንደቅዓላማና የሠራዊታችን የአልሞት ባይ ተጋዳይ ታሪክ በቆራጥ ልጆችዋ ክብር ይታደሳል። ‘የነፋስ አቅጣጫ ሁሌም ካንድ ከተወሰነ ቦታ ብቻ አይሆንም። ማጉረምረምና ቁጣም ካልታሰበ አቅጣጫ ነፍሶ ጀብደኞችና ጉረኞች መጠጊያን ያሳጣል። ለዚህም እንደ እነ አባይ ሚዲያ የመሳሰሉት “የብረዛ ሚዲያዎች” በአርበኞች ክብርና ሕይወት “የተደመሰሰበት ዓመት” እያላችሁ የምትሳለቁ የዜና አውታር ባለቤቶች ልንነግራችሁ የምንፈልገው እናንተ የምትሉት ምፅዋ ላይ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ተነቅሎ ሻዕቢያ ባንዴራ ተውለብልቦ የኢትዮጵያ ሠራዊት “ተደምስሰዋል” ብትሉዋቸውም አርበኞቻችን ከሕሊናችንና ከታሪክ ማሕደራችን በወርቅ ቀለም ተመዝግበው “ዛሬም አሉ!!!” ለወደፊትም ህያው ሆኖው ይኖራሉ!!  
የ28 አመት የጠላቶቻችን ቃላቶችን መጠቀም አቁሙ!  በቃ! ማለት በቃ ነው!
ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ)