Thursday, January 30, 2020

ጣምራ ዘመቻ፣ለአንድ ዓላማ ጥር 20 ቀን 2012 ዓም(29-01-2020) Semere Alemu Ethio Semay



ጣምራ ዘመቻ፣ለአንድ ዓላማ
ጥር 20 ቀን 2012 ዓም(29-01-2020)
 አገሬ አዲስ  
Ethio Semay

በተለያዬ አቅጣጫ ወይም በተለያዬ አሰላለፍ ሄዶ የሚፈልጉትን ለማግኘት ወይም የጋራ ዓላማን ለማሳካት የሚከተሉት ስልት የተለመደ ነው።በጦር ሜዳ ጠላቴ ነው የሚሉትን ወገን ለማንበርከክና ድል ለመምታት ከመሳሪያው አይነት ጀምሮ  በአሰላለፍ ከተለያዩ አቅጣጫዎች በሚዘምቱ ሃይሎች ጥቃት ማድረስ ወታደራዊ ስልት ነው። በፖለቲካም ትግል እንዲሁ የተለያዬ መፈክርና ስም ይዞ ግን ለአንድ ተመሳሳይ ዓላማ መቆምና መታገል የተለመደ ነው።የህብረተሰብ ክፍል አንድ አይነት ፍላጎትና አስተሳሰብ ስሌሌለው በፍላጎቱ አንጻር ለመሳብ የሚያስችሉ ስልቶችን በመንደፍ፣ድርጅታዊ ሰንሰለቶችን በመዘርጋት፣አነጋገሮችን፣ቅስቀሳዎችን በማካሄድ ከመጨረሻው የጋራ ዓላማ ላይ ለመድረስ የሚያስችል  ዘዴ የመጠቀሙ አሰራር በሌሎቹም አገሮች የተለመደለ ሲሆን አሁን በአገራችን የሚካሄደው የጎሳ ፖለቲካ አራማጆች እንቅስቃሴ የዚያው አካል እንደሆነ መረዳት  ይቻላል።ከነዚህ ውስጥ ጎላ ብሎ የሚታዬው በኦሮሞ ጎሳ ስም የተለያዩ የሚመስሉ  ግን ለአንድ የጋራ ዓላማ የሚንቀሳቀሱ ሃይሎች አካሄድ በቂ ምስክር ነው።

 ለብዙ ዓመታት ሲወድቅ ሲነሳ የኖረው የኦሮሞ ጎሳን መብት ለማስከበር በሚል ሽፋን ከኢትዮጵያ ለመገንጠል የሚንቀሳቀሰው ክፍል በተለያዩ ጊዚያት የተለያዩ ስሞች ይዞ መነሳቱ አይዘነጋም።በጣልያኖችና በእንግሊዞች ቅስቀሳ የተጀመረው ኢትዮጵያን የማፈራረስ ዘመቻ ኤርትራንና  ጅቡቲን በማስገንጠል ሌሎቹም እንዲነሳሱ አድርጉዋል።ላለፉት ሃምሳ ዓመታት እስከአሁን ድረስ የተለያዩ የሚመስሉ ግን አንድ ዓላማ ያላቸው  ቱሉና ሜጫ፣የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ)፣የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ(ኦፌኮ)፣፣የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራቲክ ድርጅት(ኦፒዲኦ)፣የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ግንባር(ኦዲግ) ፣የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ(ኦዴፓ)፣ኦነግ ሸኖወዘተ በሚሉ ስያሜዎች ስር በመደራጀት  አሁን ካሉበት ደረጃ ላይ ደርሰዋል።

የዚሁ ስብስብ አካል የሆነው ኦፒዲኦ አሁን ኦዴፓ በመባል በሥልጣኑ ላይ የተቀመጠው ቡድን መንግሥታዊ ሽፋን ተላብሶ የኦሮሞን የበላይነትና ጥቅም በማስከበር  ብሎም ለወደፊቱ የኦሮሞ አገር ምስረታ ሂደትን በማመቻቸት ላይ ይገኛል።የጎሰኞች ክለብ የሆነውን ኢህአዴግን ብልጽግና ፓርቲ የሚል ጭንብል አልብሶ በሚያደርገው የማጃጃል ፕሮፓጋንዳ ሌላው ኢትዮጵያዊ እንዲዘናጋ አድርጎታል።ሌሎቹም የኦሮሞ ጎሳ ድርጅቶች በስልጣን ላይ የተቀመጠውን ቡድን እነሱን የሚቃወምና  ለኢትዮጵያ አንድነት የቆመ በማስመሰል በስከጀርባ የሚያገኙትን መንግሥታዊ ድጋፍና ከለላ እዬተጠቀሙ በሌላው ላይ ጉዳት እያደረሱ እራሳቸውን በማጠናከር ላይ ናቸው። ሌላው ኢትዮጵያዊ ውስጣዊ ትስስራቸውን ካለመረዳት አንዱን ጠላት ሌላውን ወዳጅ አድርጎ እያጨበጨበ ከማጫፈር  በቀር ሊነቃ አልቻለም።ተፎካካሪ በሚል ስም ተጎታች ሆኖ አገሩን ለጥፋት አጋልጦ ለመስጠት ይረባረባል።

የነዚህ በተለያዬ ስም ጸረ ኢትዮጵያ ዘመቻ የሚያካሂዱት የኦሮሞ ድርጅቶች በመንፈስ የተሳሰሩ የኦነግ ቤተሰቦች መሆናቸውን ለማወቅ ጠንቋይ መሆን አይጠይቅም፤የሚሰሩት ሥራ አመላካች ነው።እንደኦዴፓ ያሉትን የኦሮሞ ድርጅቶች ለአንድነት የቆሙ ሃይሎች  ናቸው  እያሉ መጃጃልና እራስንና አገርን ለአደጋ ከማጋለጥ ይልቅ ሃይልን አሰባስቦ በመጡበት መንገድ መክቶ ለመመለስ መደራጀት ነገ የማይሉት ተግባር ነው።ትናንትና  ለኢትዮጵያ አንድነት ቆመናል የሚለው የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ  መሪ መረራ ጉዲና የተባለው ይሉኝታ ቢስ ግለሰብ  በድፍረት፣ ትግላችን ከአምስት መቶ ዓመት በፊት የተነጠቅነውን የኦሮሞ አገር ለማስመለስ ነው” ሲል በአደባባይ ተደምጥዋል። ትናንትና  ለይስሙላ ሲያወግዘው ከነበረው ጁዋር ሞሃመድ ከተባለ አሸባሪ ጋር ለብዙ ዓመታት አብሮ ሲሰራ እንደነበረ ዛሬ እጅ ለእጅ ተያይዞ የዓላማ አንድነቱን  ግልጽ አድርጉዋል።የጊዜ ጉዳይ ነው ሌሎቹም አንድነታቸውን ይፋ ያደርጋሉ።ወይም የምርጫው ውጤት አንድነታቸውን ያጋልጣል።

 ምርጫ የተባለው ዝግጅት የጉልበት መፈተኛ ከመሆንም ባለፈ የነገውን ሂደት የሚያበስር  ለመሆኑ አሁን መሬት ላይ ያለው  እውነታ ያረጋግጥልናል። ከሌሎቹ ድርጅቶች በላቀ ደረጃ እርስ በርሳቸው እዬተናበቡና እዬተጋገዙ፣ከውጭም አስፈላጊው ድጋፍ እዬተቸራቸው በሎጅስቲክስ፣በገንዘብ፣ በድርጅት መዋቅር የበለጠ ጥንካሬ ያላቸው እነዚሁ የኦሮሞ ነጻ አውጭ ግንባር (የኦነግ) የመንፈስ ልጆች የሆኑት የኦሮሞ ጎሳ ድርጅቶች ናቸው።የፈለጉትን ጥቃትና ወንጀል ሲፈጽሙ በሥልጣን ላይ የተቀመጠው አጋራቸው እርምጃ መውሰድ ቀርቶ እንደ መንግሥትነቱ ለማውገዝ እንኳን አልደፈረም።በዝምታ ተባብሩዋቸዋል።የምርጫ ጊዜ ሳይደርስ በፈለጉበት ቦታ ተዘዋውረው ቅስቀሳ እንዲያካሂዱ ብቻ ሳይሆን በአገር ወዳዱ ላይ ነጻ እርምጃ እንዲወስዱ የስነልቦና ስብራት እንዲያደርሱበት  ፈቅዶላቸዋል።መጠነ ሰፊ ወንጀል ሲፍጽሙ አይቶ እንዳላዬ፣ሰምቶ እንዳልሰማ ሆኑዋል።የሕግ የበላይነትን ማስከበር ተስኖታል።ወትሮስ ለሕዝብ ደህንነት የተነደፈ ሕግ መቼ አለና!ሕጻናት በአሸባሪዎች ታግደው ስቃይ ሲደርስባቸው አልደረሰላቸውም

    በጎሳ ያልተደራጁ ድርጅቶች በአገር ውስጥ ፣ከክፍለሃገር ክፍለሃገር በነጻነት ተዘዋውረው ቅስቀሳ ማካሄድ ቀርቶ በሚኖሩበት ከተማም በከፈሉበት አዳራሽ የመሰብሰብ ነጻነታቸውን ገፎ ለተገንጣዩ ኦነግ ግን በኢትዮጵያ ሕዝብ ገንዘብ በተሠራው የሚሊኒዬም አዳራሽ ውስጥ እንዲምነሸነሽ ፈቅዶለታል። ምርጫው እንዲካሄድ የሚወተውቱት እነዚሁ ድርጅቶች ሌላው ባልተዘጋጀበት ሁኔታ እንደሚያሸንፉ በመተማመን ነው።የውጭ ሃይሎችም ምርጫው እንዲካሄድ የሚወተውቱት ለዚያው ግብ ነው።

በዚህ መልክ ምርጫው ቢካሄድ በፓርላማ ተብዬው ውስጥ የሚጠቀጠቁት በልዩ ልዩ ስም ቅስቀሳ አድርገው የሚመረጡት ሙሉ ዝግጅት ያደረጉት የኦሮሞ ድርጅቶችና በነሱ መልክ በጎሳ የተደራጁ ድርጅቶች  ተወካዮች ይሆኑና   የጎላ ድምጽ ይኖራቸዋል።ያንን ዕድል ካገኙ ደግሞ ባለው መልክ ኢትዮጵያን በመቆጣጠር የበላይ ሆኖ ለመቀጠል ከፈለጉ ይቀጥሉበታል ፤አለያም የጋራ ዓላማቸው የሆነውን ኢትዮጵያን አፈራርሰው በታሪክ ያልነበረ ኦሮሚያ የሚባል አገር ፈጥረው አሁን የገነቡትን የጦር ሃይል ተጠቅመው  የእኛ ነው የሚሉትን አካባቢ ለምሳሌም ደቡብና ምስራቅ  ወሎን፣ግማሽ አፋርን፣ የኦጋዴን፣ደቡብና ምዕራብ ኢትዮጵያን፣ጋምቤላና ቤንሻንጉልን፣ሸዋን፣ጎጃምን በጉልበት  በመዋጥ ክልላቸውን  ያሰፋሉ።ይህን ካጠናቀቁ በዃላ ኦሮሚያ የሚል አገር መመስረታቸውን ይፋ ከማድረግ የሚያግዳቸው አይኖርም።የውጩም ተባባሪዎቻቸው ፈጥነው እውቅና ይሰጣሉ።በዚህ መልክ ኢትዮጵያን ካጠፉ በዃላ ወደ ቀጣዮቹ የአፍሪካ አገሮች ዘመቻቸውን ይቀጥላሉ። ይህንን አያደርጉትም ብሎ መጠራጠር  ከጅልነትም በላይ ጅልነት ነው።ለዚያ ማስረጃው በአዲስ አበባ የሚከናወነው የሥልጣንና የቦታ ቅርምት ብሎም በተለያዩ ቦታዎች ለምሳሌም በከሚሴ፣በድሬዳዋ፣በሓረር፣በጅማ፣ በወለጋ፣በባሌ፣በአዲስ አበባና በዙሪያዋ የሚያካሂዱት የማፈናቀልና  የሽብር ዘመቻ  በቂ አመላካች ነው።ይህ ስትራተጂ በኦሮሞ ነን ባዩቹ ብቻ ተወስኖ የሚቀር  ሳይሆን የሌሎቹም በጎሳ ማንነት የተደራጁት ቡድኖች ፍላጎት ነው።አሁን በዬጎሳው የሚነሳው ክልል የመሆን ጥያቄ ዓላማው  አገር የማፈራረሱ ሂደት ቢሳካ ሁሉም የእኔ ነው የሚለውን መሬት ቦጫጭቆ  ለመያዝ ያለውን ፍላጎት ያመላክታል።በሰላም እንደማይኖር ግን ዘንግቶታል።

ከዛም በተረፈ በኢትዮጵያ ዙሪያ ከበባ ያደረጉት የውጭ አገሮች የጦር ሃይሎች ግብግብ አፍሪካን ለመቀራመት ለሚያደርጉት ዘመቻ መሰናዶ እንጂ ለከባቢው ሰላም ብለው አይደለም። ይህ  ኢትዮጵያን የማፈራረስ ፍላጎት  ጸረ ኢትዮጵያ የሆኑት አገር በቀሎቹ ብቻ ሳይሆን  ታሪካዊ ጠላቶች የሆኑት የውጭ አገር መንግሥታትና የፖለቲካ ሃይሎችም ጭምር ነው።ከወረራ እራሱዋን ተከላክላ በመቆዬት እንኳንስ ለራስዋ ለአፍሪካ ነጻነት ቀናኢ የሆነችው አገር በዚህ መልኩ እንድትጠፋ በልዩ ልዩ መልክ  ሰርገው በመግባት ያላደረጉት ተንኮል የለም ።ታሪካዊ ወደቦቹዋንና በግዛት ድንበሩዋ ውስጥ የነበሩትን  ኤርትራና ጅቡቲን እንድታጣ አድርገዋታል።አሁንም ተገንጣዮቹ በተለይም የኦሮሞ ጎሳ ድርጅቶች እንዲጠናከሩ አንዱ የሆነውን ኦፒዲኦን ለሥልጣን እንዲበቃ ከማድረጋቸውም በተጨማሪ ለወደፊቱ አገር ምሥረታ ብቃት እንዲኖራቸው አስፈላጊውን  የገንዘብ፣የፖለቲካ ድጋፍ እንዲሁም፣ስልጠና በመስጠት ላይ ናቸው።ለዚያ መንደርደሪያ እንዲሆን ኢዴሞክራሲያዊ መሆኑን ቢረዱም ምርጫው እንዲካሄድ አጥብቀው ይሻሉ።በሚሊዬን የሚቆጠር ገንዘብም እያፈሰሱ ነው። ሕጻናት፣ አዛውንት ወጣትና ሴቶች ሲታገቱ፣ሲረሸኑ፣ሲፈናቀሉ ግን ድምጻቸውን አላሰሙም፤ምንም እንዳልተደረገ በዝምታ አልፈዋል።ዓለም አቀፍ ግዴታቸውን አልተወጡም።ይባስ ብሎ ተጠያቂ የሆነውን የመንግሥት መሪ የዓለም  የሰላም ምልክት አድርገው የኖቤል ተሸላሚ አድርገውታል።  

ለኢትዮጵያ አንድነት ብሎም ለራሱ የመኖር ህልውና የሚቆረቆረው ወገን ያለው አማራጭ አንድ ብቻ ነው።ያም በልዩ ልዩ ስም ተነጣጥሎ የተበታተነ ደካማ ትግል ከማካሄድ እንደ አያት ቅድመአያቶቹ በአንድ የአገር አድን የአርበኞች ጣራ ስር ፣ሃይሉንና እውቀቱን አሰባስቦ ትግሉን ማካሄድ ነው። ኢፍትሃዊ በሆነው በምርጫው ዙሪያ መረባረብ ሳይሆን ሁሉንም ያካተተ ግን ኢትዮጵያዊነትንና የኢትዮጵያን አንድነት የተቀበሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣የሲቪክ ማህበራትና የህብረተሰብ ክፍሎች፣የእምነት ተቋማት፣የሙያ፣የሴቶችና የወጣት ድርጅቶች የሚሳተፉበት የሽግግር መንግሥት እንዲቋቋም፣ሕዝብ የተሳተፈበትና የተቀበለው ሕገመንግሥት እንዲረቅና በሥራ ላይ እንዲውል በሚያበቃው ትግል  ላይ መረባረብ መሆን ይገባዋል።ይህንን ካረጋገጡ በዃላ ምርጫ ቢካሄድ አስተማማኝ ይሆናል። አሁን በተወጠነው የምርጫ ዝግጅት መሳተፍና ያለውንም ሕገመንግሥት” ተሸክሞ መጉዋዝ እራስንና አገርን ለጥፋት አሳልፎ መስጠት ነው።ለእርድ የሚነዳ ከብት መሆን ማለት ነው።

ምርጫ ቦርድ ተብዬው የመንግሥት ተቋም ለምርጫ ብቃት መመዘኛው ኢትዮጵያዊነትና የኢትዮጵያን አንድነት መቀበል መሆን እንደሚገባውም አብስሮ መጠዬቅ ይገባል።በኢትዮጵያዊነቱና በኢትዮጵያ አንድነት የማያምን ጸረ ኢትዮጵያ የሆነ ድርጅትም ሆነ ግለሰብ እንኳንስ በአገራዊ ምርጫ የመካፈል በአገር ውስጥ የመኖር መብት ሊኖረው አይገባም።ሰላምና አንድነትን በሚያናጋ በግልጽና ድብቅ ሴራ የተሰማራ በሥልጣንም ላይ ያለ ቢሆን ለፍርድ እንዲቀርብ ማድረግ የሁሉም አገር ወዳድ ዜጋ ግዴታ ነው።

የዶክተር አብይ መንግሥት እውነት ለኢትዮጵያ አንድነት የቆመ ከሆነ ያለው ምርጫ ሥልጣኑን ለተውጣጣ ሕዝባዊ ጊዜያዊ መንግሥት ማስረከብ ነው።እንዳለፉት መንግሥታት ይህንን አልቀበልም ብሎ በያዘው መንገድ መጉዋዝ ከመረጠ የእሱም ያገራችንም አወዳደቅ አያምርም።በአገር ውስጥ ከሃይለሥላሴ፣ከመንግሥቱ ሃይለማርያም፣ከመለስ ዜናዊ፣ከሃይለማርያም ደሳለኝ ከውጭ አገር አምባገነን መሪዎችም አወዳደቅ ጭምር ትምህርት ቢወስድ ይጠቅመዋል። ሥልጣኑን ያስረክብ ሲባልም በእልህና አላፊነት በጎደለው መልክ አዝረክርኮ መሄድ አይደለም።ወይም ሥልጣኑን ለነውጠኞች በሚያመች መንገድ አሳልፎ መስጠት ማለት አይደለም።እሱም አካል ለሚሆንበት የሽግግር መንግሥት አላፊነቱን ይስጥ ማለት ነው።   

  የአንድነት ጎራው ልብ ይግዛ! በአንድ የጋራ ግንባር ጣራ ስር ተሰባስቦ እራሱንና አገሩን ከጥፋት ያድን!!አገር ሳይኖር ሥልጣን እንደማይኖር ይገንዘብ!!ጎሰኝነት የሰው ልጆች ጸር የሆነ ቫይረስ ነው።ያለፉት ሁለት የዓለም ጦርነቶችና ከዚያም በዃላ ለተከናወኑት ግጭቶችና አገር የመበታተን ውጤት ለሆኑት የእርስ በርስ ጦርነቶች፣ለህዝብ መፈናቀልና መሰደድ ምክንያቱ ዘረኝነትና የዘራፊዎች  እራስ ወዳድነት ነው።ከዚያ አደጋ ለመዳን ያለው አማራጭ  የጋራ አመራር ፈጥሮ መሰለፍ ብቻ ነው። መከፋፈል ምን እንደሚያስከትል ከየመን፣ከሶማሊያ፣ከሊቢያ፣ከሶሪያ፣ከሩዋንዳ፣ከዩጎዝላቪያ ተመክሮዎች መማር አለብን።አሁን ያለንበትንም ሁኔታ እናጢን።

ከሁለት መቶ ዓመታት  በፊት በጎሰኞች ተበታትና የነበረችውን አገር በማሰባሰብና ከውጭ ገፍቶ የመጣን ወራሪ አሳፍረው የመለሱትን ጀግና ኢትዮጵያውያን ገድል ከመዘከር አልፈን አሁን የገጠመንን ተመሳሳይ ሁኔታ ለማሶገድ ቆርጠን መነሳት ይኖርብናል።የአድዋን ጀግኖች ስንዘክርና ስንኮራባቸው የዘመናችንን አድዋ ግዳጅ መዘንጋት የለብንም።ጎሰኞች ለአንድ አገር የማፈራረስ ዓላማ በመተባበር ሲነሱ እኛ አገራችንን ለማዳን በጋራ የማንነሳበት ምክንያት  ሊኖር አይገባም።የግልና የቡድን ጥቅም ሊከበር የሚችለው አገር ሲኖር ነው።ትልቁ ጥቅም ደግሞ እንደልብ ተንቀሳቅሰው በሰላም የሚኖሩበት፣ከአያት ቅድመ አያት የወረሱት የሚከበሩበት ነጻ አገር ባለቤት መሆን ነው። ለዚያ የጋራ ዓላማ እጅ ለእጅ ተያይዘን እንነሳ!!     
      አገሬ አዲስ  


Tuesday, January 28, 2020

ይቺ ልጅ ግን ጤነኛ ናት? ዳግማዊ ጉዱ ካሣ Ethiopian Semay


ይቺ ልጅ ግን ጤነኛ ናት?

ዳግማዊ ጉዱ ካሣ
Ethiopian Semay

ሆ! “ወደው አይስቁት” አሉ? ኤል ቲቪ የማን ነው ግን? ከጊዜ ዕጥረት የተነሣ ሁሉንም ቲቪዎች ማየት ለማንም ከባድ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ አንድ ሰው አንድ ነው፡፡ አንዳንዴ በአንዴ ዘጠኝ ሰው መሆን እንደሚችል ይናገር እንደነበረው የቲቤቱ ባለሦስት ዐይን ቲዩስደይ ሎብሳንግ ራምፓ መሆን ያምረኛል፡፡ የሚዲያ መብዛት አማራጭን እንደማብዛቱ ጥሩ ሆኖ ሳለ ችግሩ አንድ ሰው በአንድ ጊዜ ብዙ መሆን አለመቻሉ ነው፡፡ በሾርኒ የብዙዎቻችንን አንገብጋቢ ችግር መጥቀሴ ነው፡፡


ወደተነሳሁበት ጉዳይ ከመግባቴ በፊት የዛሬ ደስታየን ልግለጽ፡፡ በአማራው አካባቢ የነበረው የዛሬው ሰላማዊ ሠልፍ ልዩ ነበር፤ ተስፋን ያለመልማል፡፡ እውነትም አማራው ላይመለስ አምርሮ ተነስቷል፡፡ ዱሮም አበያ በሬ ሲነሳ አይጣል ነው፡፡ መመለሻ የለውም፡፡ ልግመኛም ሰው ሲነሳበት እንደዚሁ ነው፡፡ እንግዲህ እነእንቶኔም ይወቁት፡፡ ምርጫቸውን ያስተካክሉ፡፡ ከረፈደ በኋላ ማቄን ጨርቄን አይሠራም፡፡ የዛሬው ምልክት ነው፡፡ ምኑ ታየና! በነገራችን ላይ በጎንደርና በደሴ እንዲሁም በአንዳንድ የአማራው አካባቢዎች ሰልፍ የተካሄደ አልመሰለኝም፡፡ለምን እንደሆነ ቢታወቅ ደስ ባለኝ፡፡ መለያየት ለጠላት በር ይከፍታልና አማሮች ሳትነጋገሩ እንኳን መግባባት አለባችሁ፡፡ ብዙ ስለተገፋችሁና ስለተበደላችሁ መጪው ጊዜ የእናንተም ነው፤መጪው ጊዜ ችላ ለተባሉ የሌሎች ዘውጎችም ጭምር ነው፡፡ እናም ተናበቡ፤ መለያየትና ቸልተኝነት ብዙ ዋጋ አስከፍሏችኋልና ከአሁን በኋላ ተጠንቀቁ፡፡ ትልቁ ትንሹን፣ ምሁሩ ማይሙን፣ ሀብታሙ ድሃውን፣ የደጋው የቆላውን፣ ታችኛው ላይኛውን …ያቅርበው፣ ያፍቅረው፣ አይናቀው፣ ያወያየው፣ ልባዊና ሥሙር ግንኙነት ይመሥርትና ሁሉም ለጋራ ነፃነት በጋራ ይታገል - ከሌሎቹ ተማሩ -ከእስራኤላውያን ተማሩ - ከተጋሩ ተማሩ፤ ንፋስ አይገባባቸውም፡፡ የግል ብልጽግናና ምንም ዓይነት ትምክህት ከስደትና ከውርደት አላዳናችሁም፤ የግል ኩራታችሁና ትዕቢታችሁ እትብታችሁ የተቀበረባትን አገራችሁን እንደናፈቃችሁ ልጆቻችሁም የሁለት አገር ሰዎች እንደሆኑ ከመኖር አላተረፋችሁም፤ አሁን እንኳን ተማሩ፡፡ ትልቅ ሆናችሁ ሳለ ለምን ለዚህ መሰል ሕይወት እንደተጋለጣችሁ ታውቃላችሁና ካሁን በኋላ አስተዋይነትንና የቀደመ የአያት የቅድመ አያት ጥበባችሁን መልሱ፡፡ መናናቅና በተናጠል መጓዝ ለበለጠ ጭቆናና ዕልቂት ይጋብዛልና ሁሉም በሞረሽ እየተጠራራ ጎጃም ሳይል፣ ወሎ ሳይል፣. ሸዋ ሳይል፣ ጎንደር ሳይል፣ ባሌ ሳይል… የጠነከረ የትግል ትስስር ይፍጠር፡፡ ድል ሳይገኝ የድል ባለቤትነት ክፍፍል ውስጥ መግባት፣ በጋራ እየተጨቆኑ ሳለ በሌለ የማንነት ልዩነት መኩራራትና እርስ በርስ መነቃቀፍ ለጠላት በርን በርግዶ መክፈት ነውና እንጠንቀቅ፡፡ የሚመከር አይደለም እንጂ መናናቅ ራሱ እንኳን የሚያምረው ሀገር ሲኖርና የናቂ ተናቂ ድርብ ናቂ በሌለበት ሁኔታ ነው፡፡ የምለው ይግባችሁ፡፡ “ቂጥ ከፍቶ ክንንብ ይቅርባችሁ” እያልኳችሁ ነው፡፡ በብኣዴንም ሆነ በአብን በኩል ጠላት ሠርጎ ሊገባ ስለሚችል ጠንቀቅ ማለት ተገቢ ነው፡፡ አማራ የቋንቋም ሆነ የሥነ ልቦና አጥር የሌለው በመሆኑ ለዚህ ዓይነቱ ጥቃት የተመቻቸ ነው፡፡ በነበረከትና በነጥንቅሹ ይብቃ፡፡ አማርኛ የተናገረና በዘዬህ ወግ የሚጠርቅ ሁሉ ወገንህ እየመሰለህ የሆድህን ስታዋየው ጠላት ሆኖና ለጠላት ወግኖ ሲያስበላህ ኖሯል - ሰውን ማመን በድርበቡ ነው፡፡ ባህልህን ባህሉ አድርጎ፣ ወግ ልማድህን ተላብሶ፣ በአምቻ ጋብቻ ተጣልፎ፣ በአበ ልጅነት ተጋምዶ፣ በዕቁቡና በፅዋ ማኅበሩ ተሳስሮ … እንደመዥገር ጉያህ ውስጥ ከተሰነቀረ በኋላ ጉድ ሲሰራህ የቆየውን አሰለጥ ሁላ አሁን ንቃበት፡፡

በሌላም በኩል ወያኔዎች የዘሩት እሾህና አሜከላ በደምብ ማፍራቱን ዛሬ ተረዳን፡፡ ከካናዳና ከስዊድን ስንዴና ሳልቫጅ እየተላከ ነጩ ጥቁሩን ከርሀብና ከርዛት እንዳላዳነ የከበደ ልጅ በጉርሜሣ ልጅ ታግታ የስንሻው ባለቤት ወ/ሮ ብርጣሉ ፊቷን ስትነጭና የአለምነሽ ጓዴ ባል አቶ አገሩ አበረ አለወጉ ሙሾ ሲያወርድ የባጫ ወርዶፋ ሚስት ሻሽቱ ጫልጪሣ ከነቤተሰቧ ማዘኗን በሰልፍ አለመግለጹዋ፣ የሸዋርካብሽና የሞላልኝ ልጅ ለአብረኸትና ለሐጎስ ባዕድ ሆና እነማንጠግቦሽና ጓንጉል “ልጆቻችንን አምጡ!” ብለው ሲጮሁ ለድጋፍ አለመውጣታቸው… ምክንያቱ ምንም ይሁን ምን አያቀባብርም፡፡ በሰውነታችን ብቻ መተዛዘን ነበረብን፡፡ ኢትዮያዊነቱ ቀርቶ የአንድ አምላክ ልጆች መሆናችን ብቻውን ለመተዛዘን በቂያችን ነበር፡፡ ትልቅ መረግምት በኢትዮጵያ ላይ መውረዱን ዛሬ ከምንጊዜውም በላይ ተረድቻለሁ፡፡ ደግነቱ ይህም ሁሉ ያልፋል፡፡ ወያኔን ለጊዜውም ቢሆን ደስ ይበላት! የርሷ የቤት ሥራ በደምብ ሠርቷል፡፡ ይህን ነቀርሣ ከሥሩ ነቅሎ ለመጣል ብዘዙ መስዋዕትነት ይጠብቀናል፡፡ አይዞን! ለአንድዬ ቀላል ነው፡፡

“ንግባኢኬ ሃበ ጥንተ ነገር” ይላል ቅዳሤ ማርያም - እኔም ወደ ቀደመው ነገሬ ተመለስኩ፡፡ አልፎ አልፎ ግሩም ዝግጅቶች እንዳሉት ባልክድም ከኦ ኤም ኤን ቀጥሎ ከሚያስጨንቁኝ ጣቢያዎች አንዱ ኤል ቲቪ ነው፡፡ የአንዲት ጦጣ ትሁን ዝንጀሮ ሴት ልጅ ዝግጅት ግን እጅግ ያሳስበኛል፡፡ ጦጣ ያልኳት ወልጄ ስለጨረስኩ ነውና ይቅርታችሁን፡፡ ወልዶ የጨረሰ ሰው እውነትን ነው መናገር ያለበት፡፡ እርግጥ ነው እርሷ ስለውበቷ የምትለው ከኔና ከብዙዎች ዕይታ በተቃራኒ ነው፡፡ “የልብን ተናግሮ የምን ጨዋታ” እንዳትሉኝ እንጂ እንዲህ የምለው እንኳን ለጨዋታ ያህል ነው፡፡ ነገሩ ያለው ከውጫዊው የሰውነት ውበት አይደለም፡፡ እርሱ እንዲያውም ምንም ማለት አይደለም፡፡ የሚበልጠው ውስጣዊው ውበት ነው፡፡ እንጂ የዚያች ልጅ ፀጉር ምን ሆነ ምን፣ የዚያች ልጅ ፊት የፈረስ መሰለ የቀጭኔ ታጥቦ አይጠጣምና ስለርሱ ማውራት እኔን ጨምሮ ጊዜን በከንቱ ማባከንና ንዴትን ባልተገባ መንገድ ለማስተንፈስ መሞከር ነው፡፡ አዎ፣ ለወደፊት ከመልክና ከሰውነት ሳይሆን ከሃሳብና ከአስተሳሰብ መንገድ ጋር ብቻ እንጋፈጥ፡፡ በሃሳብ ማሸነፍ ሲያቅተን ከመነሻችን ጋር ከማይያያዙ ነገሮች ጋር በመታገል ኃይላችንንና ጊዜያችንን ገንዘባችንንም በከንቱ አንጨርስ፡፡ እኔን ጨምሮ፡፡ ምክር ከየትም ይምጣ ጥቅሙ ለሁሉም ነውና፡፡

ያቺ ልጅ ሁለት ዝግጅቶች አሏት፡፡ አንዱ የምትሽቆጠቆለት የአክራሪ ኦሮሞዎች ዝግጅት ነው - የቆመችለት ዓላማ ይመስላል፡፡ ሁለተኛው ከርሷ ብሶ በዐይኗ መቀመጫ (በዐይኗ ቂጥ ለማለት አፍሬ ነው) አዎ፣ በዐይኗ ቂጥ የጎሪጥ እያየች የምትጠይቃቸው የአማራ እንግዶችን ወይም አፍቃሬ አማራዎችን የምታቀርብበት ዝግጅት ነው፡፡ ይህች ልጅ የጋዜጠኝነት ሥነ ምግባርም ሆነ ዕውቀት፣ ልምድም ሆነ ችሎታ የላትም፡፡ መጠየቅ የቻለ ሁሉ፣ አንዳች ደካማ ጎን ያገኘ ሲመስለው ተጠያቂን ማፋጠጥ የቻለ ሁሉ ጋዜጠኛ ነው ማለት እንዳልሆነ መረዳት ተገቢ ነው፡፡

ጋዜጠኝነት ሙያ እንጂ ማንም እየገባ እንደዚያች ልጅ የሚጨመላለቅበት የስዶች መድረክ አይደለም፡፡ እርግጥ ነው - አንድ ሰው ኮሌጅ ወይም ዩኒቨርስቲ ሳይገባ በግሉ በማንበብና ሰውን በመጠየቅ፣ ሚዲያዎችን በመከታተልና ለሙያው ልዩ ትኩረት በመስጠት የጋዜጠኝነትን ሙያና ክሂሎት ከመደበኛ ትምህርት ቤት ውጪ በኢ-መደበኛ ትምህርት ሊያገኝና አንቱ የተባለ ጋዜጠኛ ሊሆን ይችላል፡፡ ሁሉ ነገር በግድ በትምህርት ቤት ይገኝ ማለት ስህተትና የመደበኛ ትምህርትን አባትና እናት መካድ ነው፤ ዲግሪ ሳይጀመር እኮ ማኅበረሰብ ነበር፡፡ ዋናው ጉዳይ መስሎ ሳይሆን ሆኖ መገኘት ነው፡፡ እንዲህም ሲሆን የሙያውን ሥነ ምግባርም በዋናነት ማስታወስ ይገባል፡፡ ምሣሌ ልሰጥህ እችላለሁ - በሥነ ጽሑፍ ሙያ ስንትና ስንት ዲግሪ ይዘው አንድም አጭር ልቦለድ ያልጻፉ ምሁራን የመኖራቸውን ያህል አንድም የሥነ ጽሑፍ ትምህርት ቤት ደጃፍ ሳይረግጡ በግል ጥረታቸውና ተፈጥሯዊ ተሰጥዖዋቸው ብቻ እጅግ የሚመስጥና ሁሉንም የሥነ ጽሑፍ መሥፈርት የሚያሟላ ዘመን ተሻጋሪ ረጂም ልቦለድ የሚጽፉ የሌላ ሙያ ባለቤቶች አሉ - ለአብነት ዶክተር ምሕረት ደበበ፤ ጓደኛየና አብሮ አደጌ ጎበና ዳንኤል፡፡ ካልጻፉት ደግሞ እኔ ራሴ፡፡ እ… ጓደኞቼ እነ እንትና - ስማቸውን ምን አስጠራኝ፡፡
ጋዜጠኝነት እንደማንኛውም የዕውቀትና የሙያ ዘርፍ ሁሉ ክብር አለው፡፡ ማንም በልጣጣና የዘረኝነት ልምሻ ያሽመደመደው ወልጋዳ ሁላ ዘው ብሎ እየገባ የሚያንቧችርበት የከተማ አውቶቡስ አይደለም፡፡ ከልካይ የሌለባቸው ሙያዎች በጣም ያሳዝኑኛል፡፡ ተቆጣጣሪ የሌለባቸው ሙያዎች አንጀቴን ይበሉታል፡፡ በህክምናው ቢሆን ይህን ያህል ልቅ ባልሆነ - የአሁኑን እንጃ እንጂ ቀደም ሲል ጥብቅ ቁጥጥር ነበር፡፡ ጋዜጠኝነት እንደልመናና ሴተኛ አዳሪነት ሁሉ እንደዚያች ልጅ ያለ በሁሉም ረገድ አስቀያሚ ሰው እየገባ አንዱን በመሽቆጥቆጥና በመለማመጥ ሌላውን ግን በመሳደብና በማላገጥ ሲቀርብበት ማየት የቲቪውን ባለቤት አልባነትና የሙያ ሥነ ምግባርን መውደቅ በግልጽ ያመለክታል፡፡ ቲቪው እርግጥ ነው የማን እንደሆነና ለነማን እንደሚያሸረግድ አውቃለሁ፡፡ ይህ ቲቪ የዝምባብዌውን ሚሌ-ኮሊንስ ሬዲዮና ቴሌቪዥን በኢትዮጵያ ተክቶ እንደሚንቀሳቀሰው የጃዋሩ ኦኤምኤን የሚቆጠር በተለይ በአማራና በኦሮሞ መካከል እንክርዳድ እየዘራ የሚገኝ አደገኛ ቲቪ ነው፡፡ መንግሥት ቢኖር ኖሮ መከልከል ካለባቸው ቲቪዎች ሁለቱ እነዚህ ናቸው - የጃዋር ኦኤምኤንና የዚያችን የመርገምት ፍሬ ቀጫጫ ሴት ልጅ መርዝ የሚረጭ ቲቪ፡፡

በአንድ በኩል ችግሩ ያለው ከነእስክንድርም ነው፡፡ ምን ሊያተርፉ ወደዚያ ጣቢያ ሄደው ለውርደትና ለትዝብት እንደሚዳረጉ አይገባኝም፡፡ ባለጌን ባለጌ ብሎ ጅባት ብሎ እንደመተው አጉል ዴሞክራሲያዊነት ዋጋ እንደሚያስከፍል እየተረዳን ነው፡፡ እንዴ! አማራ ነኝ እንዲላት የማታደርገው ጥረት እኮ የላትም፡፡ የአማራን ብሔርተኝነት አምኖ እንዲቀበላት ያልወጣችበት ቆጥ አልነበረም፡፡ አንዴ በፀጉሩ፣ አንዴ በብሔሩ... በዚያ ሾጣጣ ነገረኛ አገጯ እያሸሞረች ስትጎነትለው ሳይ እኔ ራሴም ተናደድኩ፡፡ በነገራችን ላይ ጥሎብኝ ከሰውነት ቅርጽ ተነስቼ ሰውን ማንበብ እችላለሁ - የፈለግኸውን በለኝ፡፡ ግዴለኝም፡፡ እናም ስለዚያች ልጅ ጠባይ ልንገርህ - ስማ፤ ልጂቱ እጅግ ሲበዛ ነገረኛ ናት፡፡ ነገርን ማዞርና በተንኮል መረዳት ዋና ሥራዋ ነው፡፡ ከንፈረ ስስና አገጨ-ሾጣጣን ሰው ተጠንቀቁ! የፊት ቅርጹዋ በአጠቃላይ የሚናገረው ክፉ ሰው መሆኗን ነው - በርሷ ሰበብ ሌሎችም እንደሚነኩ ይገባኛል፤ ግን እውነትን መናገር ኃጢኣትም ሆነ ወንጀል አይደለምና በተቻለ መጠን ይህን የተፈጥሮ ዝማሜ በጥበብና በአስተውሎት ለማረቅ ከመሞከር ውጪ መካድ አያዋጣም፡፡ ማሻሻል ይቻላል፤ የኮከብን ጥመት፣ የክፍልን ጽላሎት በዕውቀትና በጥበብ ለማስተካከል መሞከር ብዙ ከባድ አይደለም፡፡ ዋናው ነገር ችግርን በቶሎና ሰውን ሳይጎዱ መረዳት ነው፡፡ እነዚህ ነገሮች ቀልድ የሚመስላቸው ብዙዎች ናቸው - ግን ወሳኝ ናቸው፡፡ ስንትና ስንት ጓደኝነቶች፣ ትዳሮች፣ መልካም ግንኙነቶች፣የሃይማኖትና የፖለቲካ አመራሮች፣ ወዘተ. አምረው ተጀምረው ሲያበቁ ብዙም ሳይጓዙ የሚጨነግፉት በነዚህ ምክንያቶች ጭምርም ነው፡፡ “ያንን ሰው ሳየው ይቀፈኛል!” “ይቸን ሴት ሳያት ውስጤን አንዳች ነገር ይወረኛል!” ብለህ አታውቅም? አዎ፣ ነገሩ እንደዚያ ነው፡፡ የአንድ ሰው ስድስተኛ ስሜት እያጎነቆለ ሲመጣ ብዙ የማንጠብቃቸው ክስተቶች ብቅ ብቅ ማለት ይጀምራሉ፡፡

ያች ዐውሬ ልጅ ሰውን በማናደድ የምትደሰት፣ ጭራ በማስበቀል እንደጌታዋ እንደጃዋር ሃሤትን የምታደርግ ደምበኛ የሴት ጋንኤል ናት፡፡ ስለዚህ እባካችሁ የወዲህኛዎቹ ወገኖች ወደዚያ ቤት መሄድን ለጊዜው ተውት፤ መሣቂያና መሣለቂያ አትሁኑ፡፡ “ያልወለድኩት ልጅ ቢለኝ አባባ አለኝ አፌን ዳባ ዳባ” ሲባል አልሰማችሁም? እናሳ! ዘመድ የማይሆንህን ሰው ብትለማመጠው ልቡ አንዴውኑ ሸፍቷልና ላትመልሰው ምን አለፋህ?

ተናድጄ ስለጻፍኩ ውድ የዘወትር አንበቢዎቼን ይቅርታ መጠየቅ አለብኝና ይቅርታ፡፡ በብሂላችን “ስትናደድ ልጅህን አትቅጣ፤ አንደበትህንም ቆልፋት” ይባል ነበር ዱሮ - ያቺ ድውይ ዘረኛ ተሳስታ አሳሳተችኝ፡፡ ግን ግን ማን ትሆን እንዲህ የወረድኩባት? ስሟን ረሳሁት፡፡ “ባለጌና ዋንጫ ከወዳፉ ይሰፋል” የሚባለው እውነት እኮ ነው እናንተዬ፡፡ በነገራችን ላይ ባለጌና ዋልጌ ሰዎች በዚህ መልክ የሰው መነጋገሪያ ሲሆኑ ከመናደድ ይልቅ ደስ እንደሚላቸው ታውቃላችሁ? ለምን መሰላችሁ - በመልካም ነገር ሊታወቁ እንደማይችሉ ውስጣቸው ይነግራቸዋል፤ ተፈጥሯቸው ከX እና Y ጋር የተያያዘ Chromosomatic የDNA ጥመት እንዳለበት እኛም እነሱም አሣምረን እናውቃለን፡፡ የሚገርማችሁ የተፈጥሮ ችግር ያለባቸው ጎደሎ ሰዎች የላይኞቹን ወንበሮች እየያዙ ነው ክፉኛ የተቸገርነው፤ እንደነዚህ ያለ ብልሹ ሰው ሥልጣን ላይ ሲወጣ ደግሞ ደህነኞቹ ይፈሩና ይደበቃሉ፡፡ ያኔ እነሱ ሁሉን ዐዋቂ፣ ሁሉን አድራጊ ይሆኑና በምሥኪኑ ሕዝብ ላይ እንደልባቸው ይዘባነናሉ (አትክልተኛ ሞልቶ አትክልተኛ የሚሆኑት፣ ፓይለት ሞልቶ ፓይለት የሚሆኑት፣ ሹፌር ሳይጠፋ ዘዋሪ የሚሆኑት፣ ሀኪም እያለ ሀኪም የሚሆኑት … ይሄው ሁሉን የመሆን አባዜያቸው ስለሚያንቀዠቅዣቸው እንጂ አርአያ ሆነው ሰውን ለማነቃቃት ባላቸው ስሜት እንዳይመስላችሁ - ይሄ አቢይ የሚሉት ከውካዋ ልጅ ግን እንዴት ይቀየመኝ!)፡፡ ስለዚህ ለነጃዋርና እህቱ ቀጮ ዋናው ነገር በሰዎች መታወቁና የቡና ማጣጫ መሆኑ እንጂ የሚነሱበት ጉዳይ ክፉ ሆነ ደግ አያሳስባቸውም፡፡ ኧረ እንዲያውም በክፉ ሥራቸው ይኮሩበታል! አንዳንድ ጥያቄ ሲጠየቅ የተገረመ ወይም ቀድሞ የሚያውቀው ተራ ነገር እንደሆነ ለማስመሰል የትከሻና የፊት እንቅስቃሴው ሥልት እያጣበት  እንዴት እንደሚፍነከነክ ጃዋርን ታዩት የለም እንዴ? - መፍነክነክ ራሱ እስኪከዳው ድረስ ማለት ነው፤ በሉ ቻው፡፡ ዛሬስ ብዙ ጨቀጨቅኋችሁ መሰለኝ፡፡ ይቅርታ፡፡

Saturday, January 25, 2020

የአማራ ወጣቶች ከዕንቅልፋችሁ የምትነሱት መቸ ነው? ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ)


ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ)
                                          
እንዴት ሰነበታችሁ? ለተወሰነ ሳምንት ለሥራ ጉዳይ ከምኖርበት ክ/ሃገር በርሬ ወደ ሌላ አገር ሰንብቼ በሠላም መጥቻለሁ። በተለየሁዋቸው ሳምነታት እምየ ኢትዮጵያ ውስጥ በርካታ አሳዛኝ ክንዋኔዎች መከሰታቸውን ይህ  ለምን  ሆነ አልልም ምክንቱም  መንግሥት ሥልጣን በጫካ ሰዎችና በነብሰ ገዳዮች እስከተያዘ ድረስ አሳዛኝ የሕዝብ ዕምባና ጉስቁና ሊቆም አይችልም።

 “ወጣቱ ትውልድ” ሥልጣን የተቆጣጠሩትን ‘ዘመናይ ሽፍቶች’ በጉልበትም ሆነ በማዕቀብ ካልተጋፈጡት እና ዕረፍት  ካልነሱት አማራውንና የጋሞ ተወላጆችን በማጥፋት ላይ የተጠመደ “አብይ” የተባለው የቀን ጅብ ሕዝብን ከማጥፋት ሥራው ቀይታቀብም።    

በግዕዙ ልሳን ልጀምርና ወደ ትንታኔው እንግባ። “ጽልው እዝነክሙ ሃበ ቃለ አፍየ (ጀሮአችሁን ወደ አፌ ቃል አዘንብሉ)። አዎ ከስሜት ውጡና ጀሮአችሁን ወደ እምጠይቃችሁ ጥያቄ አዘንብሉ።

አማራ ወጣቶች ከዕንቅልፋችሁ የምትነሱት መቸ ነው?
 ነቅተናል አትበሉኝ። ከነበራችሁ ዕንቅልፍ ባነናችሁ እንጂ አልነቃችሁም። አንድ ከትግሬ የሚወለድ የቅርብ ወዳጄ ስለ አማራዎች ሁሌም የሚለው ነገር አለው። አማራ በጣም አከብራለሁ፡ ዘረኛ ነህ አትበለኝና እውነቱን ልንገርህ፡ አውነታው ‘አማራ’ ጉረኛ ነው ሲሉ ስሰማ  እከላከልላቸው ነበር፡ አሁን፤አሁን ስታዘባቸው ግን 27 አመት ሙሉ ግፍ ሲፈጸምባቸው ፤ዛሬም ነቅተዋል በተባለበት ወቅት አብን የተበላ የወጣት ምሁራን ድርጅት መስርተውም ቢሆን የሕዝባቸው ግፍ ከቀኝ ወደ ቀን እየከፋ መሄዱ ስመለከት “ይህ በየ ዩቱብ” ላይ የሚለቀቀው ጠምንጃና ዝናር ታጥቀው በመቶዎቹ ታትመው  የሚለቀቁ “የሽለላ የሙዚቃ ሸክላዎች”   
ለመታየት፤ለጉራ ወይስ ለምን? የሚል ጥያቄ ይጭርበኛል”፤ ብሎ አውርቶኛል።

ይህ ትዝብት  አንዳንዶቻችሁ እንደ ዘለፋ  ትወስዱት  ይሆናል። አማራ እየደረሰበት ካለው ግፍና የዘር ማጥፋት ጋር ሲነጻጸር ይህ የሙዚቃ ሽለላና ቅስቀሳ ዛሬውኑ ካልሰራ ለመቸ ይሆን የሚል እኔም እጠይቃችሗለሁ። አማራ  እራሱ  ካልሆነ  ማንም ሊያድነው  እንደማይችል  አወቁ።  ጊዜው  በጣም  እየከነፈ  ነው።

  በሳምንትታ ተለይቼ ወደ ስፍራየ  ስመለስ የሰማሁዋቸው ዜናዎች እጅግ አስከፊ ናቸው። የአማራ ወጣት ሴት ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በመንግሥት ዝምታ (አንድ ወላጅ እንዳሉት “በመንግሥት ጠላፋ/ትብብር” ህላዌአቸው የት እንዳሉ አይታወቅም። ለጥምቀት  በዓል የወጡ የተዋህዶ ክርትና አማኞች በሐረር/ሐረሪ/ ፖሊስ ጥይት እየተደበደቡና ወደ ታቦቱ ጭምር ጥይት እየተተኮሰ የሃይማኖት ጥቃት መፈጸሙ ስሰማ፡ “ፖለቲካ እንመራለን” የሚሉት “የፋሺስቱ የኮሎኔል አብይ አሕመድ” ወደ ገብ አጫፋሪዎች ስለሆኑ ከነሱ ምንም  አልጠብቅም፡ እኔ የጠበቅኩት “አብን” የተባለው ድርጅት የት አለ? ይህንን ጥያቄ ስጠይቅ አብሬም የሽለላ ሙዚቃ የሚለቁት ጠምንጃና ዝናር የታጠቁት ሸላዮች ይህ ሁሉ ጉድና ጥቃት ሲፈጸም “እምቢታቸውን  ለምን አላሳዩም”?

ብአዴን የተባለው የወያኔ ሎሌ የነበረው ዛሬ የምዕራባውያኖቹና የዓረቦች ቅጥረኛ ለሆነው “ለኦነጉ የኮለኔል አብይ አሕመድ” እግር አጣቢ ሆነው ስላየናቸው የገዛ ወላጆቹ  “ሸታታ እግር፤ ልሓጭ እና  ትምክሕተኛ”  ብሎ የሚዘልፍ  ብአዴን የተባለ ማፈሪያ ስብስብ ለአማራ መሕበረሰብ እና  በተለይም ለተጠለፉት ልጃገረዶች ይከላከላሉ ተብሎ ተስፋ የሚጣልባቸው የጠላት ሎሌዎች ስለሆኑ ትኩረት አልሰጣቸውም። ትኩረቴ “አብን”  የተባለው  ድርጅት መሪያቸውን አሳስረው፤ በርካታ  አንስት  የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች “በኦሮኦሞ ሽብርተኞች” ተጠልፈው፤ ብዙ አማራዎች  እየተገደሉ ባሉበት ባሁኑ ወቅት ድምፃቸው የት ተሰወረ ?

እውነት ለመናገር አብን  ከተባለ ድርጅት ይልቅ የሌሊት ወፍ ይሻላል። የሌሊት ወፎች የዋሻ ጥግ ጥግ ላይ ይዘው የሌሊት ወፍ እንደሚጮህ ሁሉ መጮህ አልቻሉም። ከሌሊት ወፎቹ አንዳቸውም ከተጠለሉበት የጣራ ሰገነት ላይ ወደ መሬት ከወደቀ  ነፍሳቸው ይናደዳል። እጅግ ይጮሃሉ። አማራው ከመጮህና ከመናደድ አልፎ ተግባራዊ እምቢተኝነቱን መቸ ነው የሚያሳየው? ይህ ጥያቄ ወያኔ አዲስ አበባ ከተቆጣጠረበት ወቅት ጀምሮ አማራ ምሁራንን ስጠይቃቸው የነበረ ጥያቄ ነው። አብን ሆነ አማራ ወጣቶች ከስሜት ወጥታችሁ ሕዝባችሁን ከመጠለፍና  ከመገደል ለመከላከል ከነፍጥ እስከ ማዕቀብና “መሬት አርዕድ” የሆነ “ሰላማዊ ሰልፍ” አሁኑኑ “ነገ ጥዋት” መጀመር አለባችሁ።

 ሽለላው ፉከራው የፌስ ቡክ ንትርኩና ጉራውን አቁሙና ጠላቶቻችሁን መክቱ። ለመሆኑ የውርደት ትርጉም ታውቃላችሁ? ወላጆቻችሁ ውርደት የሚባል በላያቸው ላይ እንዲያንዣብብ አይፈቅዱም። ጣሊያንን አፈር ድሜ ያስጋጡ  እምቢተኞች ነበሩ፤ እናንተ ግን የየትኛው ችግኝ ዲቃላዎች እንደሆናችሁ ሊገባኝ አልቻለም።

አብይ አሕመድ የሚመራው ድርጅትም  ሆነ በዙርያው የተኮለኮሉ ጎስታፖ ፋሺሰቶች ለ27 አመት በወንጀል የተጨማለቁ በአሕዛብ ላይ የዘመቱ፤ምጥ በያዛት አርጉዝ የሚሳለቁ “ክራባት እና ሱፍ” ያጠለቁ የሰው  ልጅ ቀርጽ ያላቸው “የበረሃ ጭራቆች” ናቸው። ከወያኔና ከኦነግ/ኦፒዲኦ/ኦፌኮ “ፍትሕ” የምትጠብቁ ከሆነ ሕክምና ያስፈልጋችሗል። ለዚህ ነው “የአማራ ወጣቶች ከዕንቅልፋችሁ የምትነሱት መቸ ነው? ስል የምጠይቃችሁ።
አመሰግናለሁ።
ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ)

Monday, January 13, 2020

ኤርትራ? ኤርትራ? ኤርትራ ደግሞ ማናት? ኤርትራ የደፈረሰች፤ ያለቀላት፤ የተበላሸች መንደር ! ድጋፍ ለጋዜጠኛ ታምራት ነገራ ጌታቸው ረዳ (Ethio Semay) ጥር 3/2012 ዓ.ም (ጃንወሪ 12/2020)


ኤርትራ? ኤርትራ? ኤርትራ ደግሞ ማናት? ኤርትራ የደፈረሰች፤ ያለቀላት፤ የተበላሸች መንደር !
ድጋፍ ለጋዜጠኛ ታምራት ነገራ

ጌታቸው ረዳ (Ethio  Semay)

ጥር 3/2012 ዓ.ም  (ጃንወሪ 12/2020)

“Eritrea Licks its wounds” (quoted BBC Focus on Africa) - during the Badime war between Eritrea bandits and Ethiopia gallants) ትርጉም ኤርትራ ቁስሏን ላሰች (ቢቢሲ ትኩረት በአፍሪካ- ዘገባ “ኢትዮ- ኤርትራ ዋር” ተብሎ በሚጠራው ስለ የባድሜ ጦርነት ሲዘግብ ኤርትራኖች 3/4ኛውን መሬታቸውን ጥለው ተሸንፈው “ፈርጥጠው ወደ አስመራ እና ወደ ሱዳን” እየሸሹ በነበሩበት ለታሪክ የተዘገበ ርዕስ ነው፤ “Eritrea Licks its wounds”
ከአዘጋጁ ማስታወሻ
ለኢትዮ ሰማይ ድረገጽ አንባቢዎቼ መልካም ንባብ እያልኩ ላልተወሰ ጊዜ ከምኖርበት ካሊፎረኒያ ለህጸጽ ጉዳይ ወደ ሌላ ስለምጓዝ፤ እስክመለስ ድረስ “ጭር” አንዳይላችሁ ይህንን ረዢም ሰነድ ያቆዩያችኋል።  መልካም ሰሞን ያድርግልን።  

አሁን ወደ ታሪካዊ ክርክራችን ትንታኔ ልግባ።
ወያኔና ሻዕቢያ በውጭ ሃይላት ተደግፈው በሕገ ወጥ መንገድ መንግሥትነት ተቆጣጥረው አንድ አገር ለሁለት ከፍለው፤ 1998 ተጠያቂነት በሌለው ጦርነት ውስጥ 70 ሺሕ ሕዝብ ህይወት አጥፍተው አንዳቸውም ተጠያቂ አልሆኑም። የድሃ ልጅ ሞቶ ቆስሎ እነሱ አሁንም ሥልጣን ላይ አሉ።


ትግሬዎችን የተካው በኮለኔል አብይ አሕመድ የሚመራው ተረኛው ዘረኛው የኦሮሞዎች አፓርታይድ መንግሥት ከመጣ ወዲህ የጄዳ ስምምነት ተብሎ ሳውዲ ውስጥ የተፈረመው አንቀጽ 4 በጠቅላላ አወዛጋቢው የ1200 ኪ.ሜ የድምበር መስመር ባድሜን ጨምሮ ሕገወጡ “የአልጄሪሱ ስምምነት” መሰረት አድርጉ ለኤርትራ ሊሰጥ በምዕራባውያን አለቆቻቸው የሚመሩት የተባበሩት መንግሥታት ሊቀመንበሩ አንቶንዮ ጉተሬዝና ቻዳዊው የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ኮሚሽነር ‘ሙሳ ፋቂ ሞሃመት” አፈራራሚነት ፈርሟል። ይህ ሴራ  በሕግም በታሪክም ዉሃ ባይቋጥርም፤ ሊጎዳን የተሴረ ሴራ ነውና ይጎዳናል። አንዳንድ ጅል ኢትዮጵያውያን ጦርነቱን ለማቆም ሰላም ለማምጣት ስለሚረዳ  ባድሜ ለኤርትራ ያለ ቅድመ ኩነት/ሁኔታ መሰጠት አብይ የገባበትን ውል እንደግፋለን በማለት  የመለስ ዜናዊን ሴራ እውን እንዲሆን በቀጥታም በተዘዋዋሪም ሲጪሁ እየሰማን ነው ።

 ኢትዮጵያን በመጉዳት የሚመጣ የሴረኞች ሰላም ከተጨባጩ ሃቅ የራቀ ስለሆነ፤ መነሻውና ማቆሚያው በቅጡ ካላወቅነው፤ ሰላም ፤ሰላም፤ሰላም ብቻ ስለተመኘን ሰላም ሊመጣ አይችልም። ሰላም ያመጣል ተብሎ መለስና ኢሳያስ በበረሃ ስምምነታቸው መሠረት ኤርትራን ካስገነጠሉ በኋላ እስከ 70ሺ የሰው ህይትን በርካታ ንብተረትና መፈናቀል ደርሻል። ምክንያቱም ግልጽ ነው። በሴራ የተፈጸመ  የድብብቆሽ ፌርማ ቀን ጠብቆ ይፈራርስና ጸቡ ያገረሻል።

ሰላም እንዲመጣ ከተፈለገ፤ ኤርትራኖችም ሆኑ ወያኔዎችና ዛሬም ያለው አደገኛው የመለስ ዜናዊ ኮቴ የተከተለው “ኦነጉ” አብይ አሕመድ ኢትዮጵያንም ሆነ ሕጋዊ ውክልና ያላቸው መሪዎች ስላልሆኑ ከሥልጣን ተወግደው፤ ኤርትራን የሚረከብ ቡድንኢትዮጵያዊነትንአክብሮ አንድ አገር የሚያደርግ፤(ሕዝባችን አካላችን ናቸው ብንልም እነሱ ስለማይፈልጉን እስካሁን ድረስ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉት ኤርትራኖችም ሆኑ ኤርትራ ውስጥ ያሉ ኤርትራውያኖች አገራችን የምትሰጣቸው አቅርቦትና ጠቀሜታ ትተው የፈለጋቸው ይሁኑና) ወይንም ያለ ሕግ የተነጠቅነውን የባሕር ወደባችንን በፈቃዱ ለኢትዮጵያ እንዲያስረክብ የሚፈቅድ ቡድን ወይንም የሚገደድ ቡድን ሲፈጠር ያኔ ወሳኙና የሰላም ምንጩና መፍተሄው ይህ ይሆናል።

አናደርግም የሚሉ ከሆነ እና የኢሳያስና የሻዕቢያ  መንገድ እንከተላለን የሚሉ ከሆነ፤ ጊዜ ይፈጃል እንጂ በመጪውየነቃ ትውልድከባንዳነት የጸዳ አንድ አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ወደ ሥልጣን እንዲወጣ ሲደረግ፤ ወይንም የኢትዮጵያ አምላክ በአስገራሚና አስደንጋጭ ተአምራቱባንዳውመለስ ዜናዊናአበ ነብሱየነበሩት አባ ጳውሎስን በተአምር እንዳስወገዳቸው ሁሉ፤  አብይ አሕመድም” በተመሳሳይ ጥሪ ወደ ሌላኛው ዓለም “ከተጠራ”  አንድ አገር ወዳድ አርበኛ ኢትዮጵያዊ ወታደር ወይንም ሲቪል ወደ ስልጣን ሲቆጣጠር፤ ባንዳዎች የወሰኑት ውሳኔ ሽሮ ከላይ የጠቀስኩትን የሰላም አማራጭ መንገድ አንወስድም ብለው የሚያንገራግሩ ኤርትራ ቡድኖች ከተከሰቱ፤ የናፈቁትን ጦርነት ከፍቶ፤ ዓሰብን 30 አመት የተኮናተሩትን ዓረቦችን እንደለመዱት ማራወጥ እና ባሕሮችንን መለስን መቆጣጠር፤ የአሉላ አባ ነጋ፤ የአምደፅዮንን ታሪክ መድገም የመጨረሻው አማራጩ የመፍትሔ ሃሳብ ሲፈጸም ብቻ ነውሰላም እያልን የምንኳትተው ሕልም እውን የሚሆነው”። የኤርትራኖች አቅምም ያው ባድሜ ላይ ያያችዩት ነው። “Eritrea Licks its wounds” (quoted BBC Focus on Africa “ኤርትራ ቁስሏን ላሰች” (ቢ ቢ ሲ)

ካልሆነ ሰላም ስለተፈለገ፤ መነሻውና ምክንያቱ ሳንዳስስሰላምበገዛ ፈቃዱ በነዚህ ወረበሎች ጊዜ ሊመጣ አይችልም።ሁለቱም ወረበሎች የሚሰጡት መልስ ለጦርነቱ መነሻ እና ለሰላም ጠንቅ በመሆኑ፤ ያለ ሕግ የተነጠቅነውን የኤርትራ መሬታችንና በባርነት የያዙትን ሕዝባችንን በድርድር ያስረክቡን። ካልሆነ ጦርነቱ መቼም ቢሆን አይቀሬ ነው።  ደርግን በሴራ አስወግደው ኤርትራን ሲገነጥሉ “ጦርነት አይቀሬ ነው” ብየ ጽፌ ተናግሬ ነበር (ብዙ ወገኖቼ ይህንን ይመሰክራሉ) እንዳልኩትም በ1989 በኢሳያስ ፀብ ጫሪነት ዘግናኝ ጦርነት ተደረገ። አሁንም ይደገማል~~~~!!!  ባንዳዎችም ሆኑ የተቀራችሁ አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊን ኢትዮጵያ አገራችን እንዴት እና ለምን እንደተበደለች ምክንያት አለኝ፤ ምክንያቴን አንብቡ።

          ኤርትራኖችና የ እንእኒምናባዊ ሕልም
                    
 በዚህ-ጽሑፍ ሻዕቢና ወያኔዎች (ዛሬም አብይ አሕመድ) 27 አመት-መልስ ያጡበትና ያሳፈራቸው አንድ አጭር እና ግልጽ ጥያቄ እንመለከታለን። ድሮ በልጅነታችንእንእኒ” (ሲነበብ ይጥበቅ) የሚባል ዘመን ነበር ሲሉ ወላጆቻችን ያጫውቱናል።  እኛም ያንኑ ትረካ ተቀብለንዝናብ ሲዘንብጓደኛሞች የሆንን ሁሉ ሁሌም በምንጫወትበት ሞቃታ ስፍራ ሰብሰብ ብለን ተጠጋግተን በብርዱ ላለመጠቃት ተኮማትረን ተቃቅፈን  ስለዘመኑ እውነተኛነት በዓይናችን ያየን ይመስል የራሳችንን ቅጥያ ጨማምረን አጣፍጠን ከፊት ለፊታችን የሚታዩ የድንጋይ ኮረቶች ሁሉ የዛው ዘመን የአምቧሻ ቅሪት መሆኑን በእርግጠኝነት እናወራ ነበር። ዘመኑምዘመን እንእኒይባል ነበር።

 በዛ ዘመን ምን ነበር? ብለን ስንጠይቅ ድንጋዩ ሁሉ አምቧሻ ነበር ማረስ መዝራት፤ መውጣት መውረድ አያስፈልግም ነበር።ብዘመን እንእኒ ሕምባሻ እንተሎ እምኒድንጋይ ሁሉ አምቧሻ የነበረበትየእንእኒ ዘመንአጣፍጠው ወላጆቻችን የነገሩንን እና እኛም ጨማምረን ስለ ዘመኑ መልካምነት እናወራ ነበር።ታዲያ እግዚሃር በሰው ልጆች ስነ ምግባር ተቆጣና አምቧሻው ወደ ድንጋይ ለወጠው ይባላል። ኤርትራኖችምድሪ ባሕሪነፃ ስትወጣ ወደዘመን እንእኒተመልሳ ድንጋዩ ሁሉ አምቧሻ ሆኖ አንደሚቀየር ለእናቷ ኢትዮጵያም ከሚትረፈረፈው አምቧሻዋ አንደምታጎርሳት ኢትዮጵያ ያስተማረቻቸው የኤርትራ ኢኮኖሚስቶች ያልቀባጠሩት ዲስኩር አልነበረም።

አንድ እውቅ የጦቦያ ጸሐፊ (ማን መሆኑን አላስታወስኩትም) ኤርትራ ነፃ ስትወጣ፤ድሮ በጥንት ጊዜ ራሴን ችዬኤርትራስባል የነበርኩኝ  አገርነኝ  ታዲያኢትዮጵያየምትባል ከኋላየ የተፈጠረች 60 አመት ዕድሜ ያላት አገር በጉልበት አጠቃልላኝ ነው እንጂ አገር ነበርኩኝ፤ አሁን  ግን ነፃ አውጡኝ፡ እያለች እረፍት ስለነሳችን ነፃነቷን ለመስጠት ተዘጋጅተናል እና ኤርትራ የምትባል አገር በፈጠርካት በዚች ዓለም-ምድር ተዘግባ ታውቃት ነበር? ብለው እግዚሐርን ሲጠይቁት ኤርትራ? ኤርትራ? ኤርትራ ደግሞ ማናት? ብሎ መዝገቡን ሲፈትሽ ማግኘት አልቻለም። አንዲህ የምትባል አገር አላውቅም! ምነው ጊዜን ባታባክኑብኝብሎ እግዚሓርም ራሱ ተገርሞ ነበር ይባላል። ትክክለኛ አባባሉ ባይሆንም በራሴው ማጠጋጋት (ፓራፍሬዚንግ) እንዲያ ብሎ ጽፎ ነበር።ኤርትራ ዛሬ 22 አመቷ ነው ነፃ ከወጣች። እገምጠዋለሁ ያለቺውየዘመን እንእኒ ቅዠትድንጋይ ብቻ ሆኖባት ፈዝዛ ቀረች።

ኤርትራ ሁሉም ሞክራዋለች። ግድያ፤ ዘር ማጥፋት፤ ሕዝብን ወደ ባርነት መለወጥ፤ ጥቁር ገባያ፤ ሌብነት፤ ስም ማጥፋት፤ ውሸት፤ጉራ፤ ወንጀል፤ ጦርነት፤ሽብር፤ስደትና ዕብደት፤ ሁሉንም ሞክራዋለች። ከዚህ ወዲያ የሚቀራት መደምደሚያዋ ወደ አመድነት መጓዝ ነው።ከዚያ ጣረ ሞት መዳን ከፈለገችየቀራት አማራጭኢትዮጵያዊነትዋንበቁርባንተቀብላ ከዘላለማዊው ቅዠት (ደሉዥን) እና ሞት መዳን ነው። ካልሆነ ግን እንደምታስታውሱት “የኢሳያስ ኤርትራ” ከባድመ ጦርነት በኋላ “እጅግ ከፍቷት ስለነበር የአለም ጤና ጥበቃ ድርጅት እንዲቃጠሉ የወሰነባቸው በሽታ የለከፋቸው የአውስትራሊያ በጎችን በምጽዋት ተመጽውታ መሳቂያና መሳለቂያ እንደሆነቺው ሁሉ  በውንብድና የፖለቲካ በሽታ የተለከፈች መንድር በመሆንዋ የመጨረሻ ዕድልዋመበላሸት፤ ስደት፤ ጦርነት፤ሞት፤ውርደትይሆናል።በውንብድና እና በውሸት በዘር ፖለቲካ ተለክፈው ለሚሰቃዩ ኤርትራኖች እና የወያኔ ትግሬዎች ፈውስ አለን። ኢትዮጵያነት!! የተሰኘ መድሃኒት።
ኢትዮጵያዊነት ለምን? የሚሉ የኢሳያስ አለቅላቂዎችና ጀብሃዎች መሪዎች እና የትግራይ ወያኔዎች የታሪክ አተላዎች ክቡር ፕሮፌሰር አስራት የተናገሩትን ልጥስላቸውና ልሸጋገር። ጥቅሱን ያገኘሁት ከፕሮፌሰር ንጉሳይ አየለ ነው።

... 1991 (...) ሐምሌ 1-5 (...). “ቻርተርበተሰኘው ስብሰባ ላይ ሰማዕቱ ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ ቃላቸው እንዲመዘገብላቸው እንዲህ ሲሉ ተናገሩ


 ይህ ኮንፈረንስ በኢትዮጵያ ሕዝብ ስም የመወሰን የመተው ወይም የመሰረዝ ስልጣን የለውም ፡፡ ሆኖም አንድ ሰው በሀገሪቱ ውስጥ ያለውን የወቅታዊ ሁኔታ ሁኔታ ይገነዘባል ይህም በወንድማማቾች መካከል የደም ጠብ መቋረጡን እንዲሁም የአሁኑን የሰላም እና የዴሞክራሲን ፍጥነት ይጨምራል ፡፡ ኢሕአዴግና ሕዝባዊ ግምባርም በወንድማማች እና እህትማማች (በኢትዮጵያ-ኤርትራዊ) ህዝቦች መካከል ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን በአፋጣኝ ለመስራት የኢትዮጵያን እና የይቅርታ መንፈስ እንዲመጣ ለማድረግ ልዩ የቅርብ ግንኙነታቸውን ሊጠቀሙበት ይገባል፡፡..” በማለት ጠቃሚ ምክርና ተቃውሞ አቅርበው ነበር።

ሆኖም ጀሮ ስላልነበረ፤ ፕሮፌሰሩ የሰጉትን ነገር ተፈጸመ የባድመ ጦርነት ተከሰተ። አሁንም የሚያምነን የለም። አንዴ በክሕደት የተቀረጸ ሕሊና ጩቤው እስኪነካው ድረስ አይነቃም።

አትዮጵያዊነት!!!” የዘላቂ ሰላም መፍቻውና ቁልፉ እሱ ብቻ ስለሆነ በዛው ፈውስ ተዳኙ ነው ያሉት። ይኼ ፈወስ በትዕቢት ንቃችሁ ወርውራችሁት እንደወትሮው በመንገዳች ግን፤ ዘላቂ ሰላም ሳይሆን ዘላቂ ጦርነት ብቻ ነው የሚከተለው እውንኢትዮጵያዊነትእየተናቀ፤ ባንዳነት እየጎለበተ ከሄደ፤ ሰላም የሚባለው የነ ሻዕቢያ እና ወያኔ እንዲሁም አዲሶቹ  ኦሮሞ ባንዳዎች የሚዋሹትየሰላም መንገድ አጭበርባሪዎች የቀየሱት የባንዳዎች መንገድ ስለሆነ ሕዝባችን ለሁለተኛ ጥፋት እንዳትራመድ እነዚህን በጠራ ዓይን እና ሕሊና መርምሩት።

ታሪክ አለን! ታሪካችን ባንዳዎችም ሆኑየተባባሩት ግሳንግስ መንግስታት ማሕብር”  ሊጠመዝዙት አንፈቅድም። ቢሞጅሩም ምንም አያደርጉም የድምበር ተመራማሪው እንግሊዛዊው አስተያየት አድምጡ” ኢትዮጵያ ካልተስማማች ማንም ሃይል ሊያስገድዳት አይቻለውም ብሎ ነበር’። አገር ወዳድ ወይንም ባንዳ የሚያስብለን ታሪካችን እና መልህቃችበጊዜአዊ አስቸጋሪ ማዕበል ስንለቅ ወይንም አጥብቀን ስነይዝ ብቻ በዚያው ስያሜ እንጠራለን ሁለታችን የሚለየን ታሪክ በማጉደፍ እና ታረክ አጥብቆ በመያዝ ነው። የወላጆቻችን አደራ አናስበላም። አርበኞች ነበሩን፤ ታሪክና ታሪካቸው አለን;፡ታሪካችን እና ጭብጨጣችንም እነሆ አንብቡ። ኢትዮጵያ አለቀላት ብለው ከጠላቶች ጋር የሚደባለቁ ከሃዲዎችኢትዮጵያ እንዳላለቀች  ዛሬም ነገም አለን! አለን! አለን! እንላቸዋለን።፡ታሪካችን እነሆ። መልካም ንባብ….

ጣሊያኖች ወደ አዲስ አበባ ሲገቡ Ethiopia E Finita !!!! (ኢትዮጵያ አለቀላት) የሚል መፈክር የያዙ ትሬንታ ኳትሮዎች አዲስ አበባን ወርረዋት እንደነበር ጆን ስፔንሰር Unity and territorial integrity (የግዛት ውሁድነት) በሚለው መጽሐፉ ጠቅሰው እንደነበር አንድ የዛሬው የቅርብ ወዳጄ የሆኑ በጦቢያ መጽሄት ላይ ጠቅሰው ነበር። የተጠቀሰው መፈክር፤ ዛሬ ያለምን ጥርጥር ኤርትራ ካለ ኢትዮጵያ መኖር የማትችል በጉራ ብቻ የተነዳች፤ ኗሪዎቿ ወደ ኢትዮጵያና ወደ ሰሓራ የሚሰደዱባት፤ደካማ አውራጃዎችን የያዘች፤ ያለቀላት የተበላሸች መንደር ነች። ሰርጓም ሞትዋም 25 አመት ውስጥ ተጠናቀቀ። ዕጣ ፈንታዋነፃነት” (የኤርትራ ባርነት) ብላ የገለጸቺውን ነፃነቷንከአመዳም ሕይወት ለመውጣት’ ስትል እንደገናእራስዋን መፈተሽአለባት።ለ25 አመት የተሰጣትየኦክሲጅን ስሊንደርአልቋል! ከዚያ ወዲያ መቀጠል full of difficulties/ ነው። ብልሽት! ነው የምለው ዛሬ አይደለም። ቆይቷል።


ኤርትራዊው አማረ ተኽለ ዴንቨር ዩኒቨርሲቲ ለዶክተሬት ዲግሪው መመረቂያ የጻፈው የምርምር ወረቀት The creation of the Ethio-Eritrean Federation; a case study in post-war international relations, 1945-1950. ላይ እንዲህ ይላል፤-

ኤርትራ የኢትዮጵያ አካል አልነበረችም ብለው የሚከራከሩት የአካባቢው ታሪክ የማያውቁ ወይም ሊቀለብሱት የሚፈልጉ የሙሶሎኒ ፋሺስታዊ ፖለቲካ የሚጋሩ ብቻ ናቸው።ይላል።

 አማረ በድሮ ጊዜ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ውስጥ ኢትዮጵያዊነቱን አምኖ ተቀጥሮ ሲሰራ የነበረ፤ በኋላ ታስሮ ሲፈታ ወደ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ስራ ለመመለስ ሲሞክርይህ ሰውዬ አባርሩልኝብሎ / ጐሹ ወልዴ አንዳይቀጠር የከለከለው ሰው እንደነበር ኤርትራኖች ፅፈውበታል። አማረ ተኽለ የዛሬ አያድርገው እና ያኔ ሕሊናው ሲከተል በነበረበት ወቅት ኢትዮጵያ የኤርትራ አካል አልነበረችም ብለው የሚከራከሩ ሰዎችን “/Neo Fascist ፋሺስትናቸው ብሎ ለዲዘርተሼን በጻፈው የመመረቂያው የጥናት ጽሑፍ የነገረን ረስቶት ጊዜ መስተዋቱ! ዛሬ እራሱ ወደ ኒዮ ፋሺስቶቹ በመቀላቀል፤የኤርትራ ርዕሰ ውሳኔ ኮሚሽነር/አስመራጭበመሆን የውስጥ እና የውጭ የወረበሎች ስብስብ ያዘጋጁትን የወያኔና የሻዕቢያ ሬፈረንደም ባዘጋጁት ሴራ ውስጥ በመሳተፍ እንድትገነጠል ከጣሩት ቀዳሚ ኤርትራዊያኖች አንደኛው / አማረ ተኽለ ነበር።
ባለ ሁለት ምላሱ አማረ ተኽለ ወንበዴዎቹ ያዘጋጁትን የግንጣላ ሴራ ስለ ሪፈረንደሙ እንዲህ ይላል፤

 “the referendum process as one of the fairest and freest of referendums ever.” የድምፀ ውሳኔው ሂደት የተካሄደው በቅንነትና በነፃነት ከተካሄደባቸው ሂደት አንዱ ነው።”
 ሲል ዘረኛው እና ኢፍትሃዊው ሬፈረንደም ከማድነቁ በላይ፡ የሻዕቢያ ተቀጣሪ ሆኖ ቱልቱላውን በመንዛት Eritrea is in the stage of democratic transition በሚል ንኡስ ርዕስ በዲሞክራሲያዊ ሽግግር ድልድይ እንድትራመድ እየመራት ያለው መሪ ኢሳያስ አፈወርቂ አፍሪካ በታሪኳ ያላየቺው ጠንካራ መሪ በማለት።

 There is, as is almost universally agreed by African social scientists, the need for a strong leadership to guide this process. Eritrea is blessed with such a strong leadership whose source of legitimacy is a Rousseauean General will of the population has shaped and shares the vision of the government. It is this leadership that you demonize as authoritarian either out of ignorance or political malice.

ሲል የምሁርሊጥ”-ነቱን አይ ኤውየወያኔ አፈ ቃላጤ ለነበረው ፖል ሄንዝ March 21 /1999 በባድሜ ጦርነት ጊዜ በጻፈው ጽሑፉ ነግሮናል። አሁን አለማፈር ጠንካራ መሪ ብሎ ሲያሞግሰው የነበረው ኢሳያስን በመቃወም፤የኤርትራ ነፃነትበኢሳያስ ዲክታቶሪያል ባሕሪ እየተረገጠ ነው፤ ሲል ተቃዋሚ ሆኗል። ዛሬ ኤርትራ ያለቀላት የተበላሸችበረዶ ውስጥ ተቀብራ መውጫ ቀዳዳው ጠፍቶባት ያለች መንደርእንደሆነች እኔ ብቻ ሳልሆን፤ ደጋፊዎቿ የሆኑ የውጭ አገር ሰላዮች እና ጸረ ኢትየጵያ ሃይላትም ይህንን እየደገሙት ነው።
ለምሳሌ’- December 2013, Herman Cohen አንዲህ ብሏል።
“bringing “Eritrea in from the cold” was overdue.” ኤርትራ “ከሠጠመችበት በረዶማ ብርድ የማስወጣቱን ሂደት አሁን ነው” ይላሉ በሺወቹ ዶላር እየተከፈለው በጥብቅና ለኤርትራ የሚሰራው አማካሪያቸው ኮኸን ሄረመን እና መሰሪው ጸረ ኢትዮጵያ የመለስ ዜናዊ ቅርብ ወዳጅና
የ ኦጋዴን ነፃ አውጪዎች አማካሪ አምባሳደር ዴቪድ ሺን-David Shinn’። ይህ መሰሪ ደግሞ “The idea that Assab belongs to Ethiopia is outdated” ሲል ይከራከራል።

 ልብ በሉ። አገራችን ምን ያህል የባንዳዎች ብዛት እና የውጭ ጣላት እየተረባረቡባት እንዳሉ ጥልቅ ግንዛቤ ይኑራችሁ።ለዚህ ነው ይህነን ሰፊ ትንታኔ አንድታነቡ በትዕግስት የምጠይቀው። የኦጋዴን እና ኤርትራ ተገንጣዮችን የሚያበረታታው የዴቪድ ሺንንአናርኪንግግር ወደ ጎን እንተው እና ኤርትራ ያለ ኢትዮጵያብርድልብስመኖር እንደማትችል ካወቁ በኋላ Ambassadors Princeton Lyman, Herman Cohen, David Shinn’ ኤርትራን ከቀዝቃዛው በረዶ እናወጣት ብለው አዲስ ዘመቻ ማድረጋቸው የሚታወስ ነው። የፈረንጆቹ ኰቴ ተከትለውም አዳዲሶዩ የግንቦት 7 ባንዳዎችምኢሳያስን ወደ ፍርድ አታቅርቡት” “ኢትዮጵያን ይወዳል” “አማራዎችን ጠልቶ ወይንም ገድሎ አያውቅም” “አይገድልም’ ‘አይሰርቅምዜጎች አያንገላታም፤ አይገርፍም፤በተጨማደደ ሸሚዝ፤ በበርባሳ ጫማ በጨረጨሰ መኪና የሚጓዝ፤ ካለ ውሃዊስኪ የማይቀምስ” ፤ ምርጥ ሕክምና ፤ምርጥ ትምህርት በነፃ የሚሰጥ፤ ለአፍሪካ ተምሳሌት የሚሆን መሪ ነው” (ይህንን ያለው አንዳርጋቸው ጽጌ) ሲሆን እነ ብርሃኑ ነጋ፤ እነ ንአምን ዘለቀም ተመሳሳይ የባንዳ ጥብቅና ሲናገሩና ሲቆሙ ወደ ተባባሩት መንግሥታት “ፐቲሽን” (ለኢሳያስ ድጋፍ) ሲያመለክቱ አድመጠናል/አንብበናል። እነዚህ የኛዎቹ ባንዳዎችም በነ ሄርምን ኮኸን መንገድ እየተጓዙ ነው። ያውም ዓይን ባፈጠጠ ጥብቅና እና በሚያሳፍር  መልኩ። 

ፈረንጅም ሆነ ባንዳ ኢትዮጵያውያን ለኤርትራ መሰረታዊ ስቃይ መነሾግንጠላው መሆኑን ሊገባቸው አልቻለም”።  የኤርትራ ጥያቄ እና ትግሉ ከጅምሩ የተወላገደ መነሾ መሆኑን መረዳት አቅቷቸዋል። ዛሬም ሊሂቃኖቹ ካፈርኩ አይመልሰኝ በሚል ጉዞ፤- ለሃፍረታቸው መሸሺያ ሲሉ ከኢትዮጵያ ጋር ከመወሃድ ኤርትራትሙትብለው ኤርትራኖች ራሳቸው ፈርደውባታል። ሞታለችም። ይህንን ሁኔታ ያሳሰበው በጀርመን የብረይመን ዩኒቨርሲቲ የሕግ መምህር (የፕሮፌሰር ተስፋጽዮን መደሃኔ “ይኼውና ኤርትራ ሞታለች! ትግል ለሀገር ትንሳኤ!!” በማለት ጥር 2007 ዓ.ም (ጃኒዋሪ 2015) የፃፈው ባለ 58 ገጽ ዝርዝር ማሕደር ማንበብ ጠቃሚ ነው። ፕሮፌሰሩ በሌላ ጽሑፉ ‘ብዙ ኤርትራውያን በቅኝ ግዛት፤ በፈደረሽንና በኮንፈደረሽን መሃል ያለውን ልዩነት ፍጹም አያውቁም፡፡” ሲል የምሁራኖቹ ግብዝነት በመገርም ሰፊ ዝርዝርም እንደሰራበት አስታውሳለሁ።

ሞት የውርደት መሸሻ ዋሻ ነውና፤ ከውርደታቸው ለመሸሽ ሲሉ ሞቷን እያቀላጠፉላት ይገኛሉ።
 ከኢትዮጵያ ተገንጥሎ መኖርም ሆነ በፌደረሽን መኖር እንደሚጎዳቸው የድሮ የባሕር ነጋሽ ተወላጆች በፌደረሸን ጉዳይ አጣሪ ኮሚቴ ሆነው የመጡ የተባበሩት መንግሥታት መልዕክተኞች አስመራ ተገኝተው በነበሩበት ወቅት በአቤቱታ መልክ ገልጸዉ እንደነበረ ታሪክ ዘግቦታል። ኤርትራ እስከ 1889 . (..) ድረስ፤ መረብ ምላሽ/ምድሪ ባሕሪ/ባሕረ ምድር/ባሕሪ ነጋሲ/ባሕረ ነጋሽ እየተባለች ስትጠቀስ የነበረቺው የጥንቷ ኢትዮጵያ አካል ‘ሓንቲ ኢትዮጵያ/አንድ ኢትዮጵያ’ “ኢትዮጵያ ወይም ሞት!” ብለው በመነሳትማሕበር ፍቕሪ ሀገርድርጅትን የመሰረቱ ወላጆቻቸው መገንጠሉ ኤርትራን እንደሚጎዳ እና ኤርትራ ከኢትዮጵያ ተነጥሎ ራሷን ችላ መኖር የማትችልበት ምክንያት ለሕብረቱ ጥያቄ  ምክንያቶቹ ካቀረቡዋቸው ነጥቦች ውስጥ በምጣኔ ሀብቱ እና በቤተሰባዊ ግንኙነት በሚመለከት ከክረስትያኖቹ እና ከእስላም ማሕበረሰብ ተወክለው አቤቱታ አቅራቢዎች በሁለት ነጥቦች የሚከተለውን አቤት ያሉበትን አቤቱታቸውን ታሪክ ዘጋቢዎች በጦቢያ መጽሄት ላይ ያኔ ኤርትራ ነፃ ወጣህ ባለችበት ወር ከዘገቡት ሰነድ ልጥቀስ።
 እጅግ አስፈላጊ ስለሆነ ረዢሙን አቤቱታ ባጭሩ ላስቀምጥ ያንብቡት፡፡

                  ከሁሉ አስቀድሞ መርማሪው ኮሚሲዮን ባቀረበው ውስጥ እንደተገለጸው እኛ የኤርትራ ሕዝብ ለኑሮአችን በቂ የሆነ እህል በደጋው አገር ለማብቀል የማንችል መሆናችንን አረጋግጠናል። ይህም በመሆኑ ስንዴ ጤፍ እነዚህን የመሳሰሉትን ለኤርትራ ሕዝብ ምግብ የሚያገለግሉት ከኢትዮጵያ መግዛት አለብን።..”  ብለው ነበር። ዛሬ፤ እውን ሆኖ ጤፍ፤በርበሬ፤ ቡና የመሳሰሉ ምግብ ቅመሞች ወደ ኤርትራ የሚገባው በጥቁር ገበያ በትግራይ መንደሮች፤በጁቡቲ፤በየመን፤በሱዳን ዞሮ እየገባ ነው፤፡

 እንደዚሁም ደግሞ የእስላሞች ሊግ ቃል አቀባይ ባደረገው መግለጫ የሚከተለውን ተናገረ፦
              
 የኤርትራ መሬታችን ጤፍ የማያፈራ መሆኑን በኢትዮጵያ ሰሜን የሚገኘው የትግራይ ክፍል እንደዚሁ በመሬት በኩል ድሀ ሆኖ ለኤርትራ ምንም ዓይነት ጥቅም የማይሰጥ በመሆኑ በየአመቱ በብዙ ሺሕ ሕዝብ የሚቆጠሩት ሕዝባችን ከብቶቻቸውን እየያዙ ኢትዮጵያ ውስጥ ወደ ጐንደር አውራጃዎች ተሻግረው ከብቶቻቸውን ያበላሉ። በዚህ ሁኔታ የትግራይ መሬት በምሥራቅ ኤርትራ ክፍል ላሉት በቆላ ውስጥ ለሚኖሩት ሕዝቦች ከብት የሚያግጡበት ሥፍራ ሲሆን፤ ጐንደር ደግሞ በምዕራብ አውራጃ ለሚኖሩት የሚበዙት እስላሞች ለሆኑት ሕዝቦች ከብት ማሰማርያ ሆኖ ይገኛል። ስለዚህም በምሥራቅና በምዕራብ ኤርትራ (በምፅዋ እና እሱንም በመሳሰለው አውራጃ) ላሉት ክርስትያኖች እስላሞች ለኑሮአቸውን ከኢትዮጵያ ውስጥ አድርገዋል። እነሱም ከኤርትራ ውስጥ ለመኖር ቢፈልጉ ኖሮ በረሃብ ባለቁ ነበር።ይል እና በመቀጠልም፤-……

ለሕዝቧ ኑሮ አስፈላጊ የሆነውን ማንኛውንም ዓይነት ምግብና እህል ከኢትዮጵያ በመግዛት ብቻ የምትደገፈው ኤርትራ ከጥቂት ጨው በስተቀር ወደ ውጭ የምትሸጣቸው ሌላ ዕቃ የላትም። ይህም በመሆኑ ያገር ውስጥና የውጭ አገር ንግዳችን የሚበዛው ክፍል በትራንዚት ወደ ኢትዮጵያ የሚተላለፍ የንግድ ዕቃና ለኤርትራ ሕይወት የሚያስፈልግ ምግብ ብቻ ሆኖ ይገኛል። ይህን የመሰለው ከኢትዮጵያ ጋር የሚያደርገው ንግድ ቢቋረጥ የምፅዋ ወደብና መላውም ኤርትራ ንግዶች ሥራቸውን ያቆማሉ። ከእነዚህም ከኤኮኖሚ ማስረጃዎች በስተቀር ይበልጥ ጠቃሚነት ያለውና ከአእምሮአችንም ምንጊዜም የማይለየው ከሦስት ሺሕ ዘመን በፊት ጀምሮ ቅድመ አያቶቻችን አንድ የኢትጵያ ሕዝብ ክፍል ሆነው የነበሩበት መሰረተታዊ ጉዳይ ቀርቦ ይገኛል። የጋራ ጥንታዊነታችን የልምዶቻችን የቋንቋዎቻችን ፤የሃይማኖቶቻችንና የጥቅማጥቅሞቻችን መተሳሰር በጣም ጥልቅ ከመሆናቸው የተነሳ ግልጽና ተገቢ በሆነ አኳሗን በሚያጠግቡ ለመግለጽ ምቹዎች ናቸው።

በማለት በምጣኔ ሃብቱ ረገድ የሚደረስባቸው መከራ ከላይ የተነበዩት ፍራቻ ትክክል ሆኖ ይኼው በዓይናችን እያየነው ነው (ድበቁ የኤርትራ ርሃብ በሚል የተዘገበ ቪዲዮ፤ ወይንም እኔ በአንድ ዘገባ ባቀረብኩት ውስጥ ኤርትራኖች መንገድ መውጣት እያፈሩ ቤት እያንኳኩ  ህጻናት ይዘው ቁራሽ እንጀራ እንዴት እንደሚለምኑ፤ ያቀረብኩትን አስታውሱ)

ቀጥሎ ኤርትራ ከኢትዮጵያ የመዋሃድ ጉዳይ ዋል እደር ማይባልበት መሆኑን እና ተሎ እንዲፋጠን ሁለት መቶ ሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያ ውስጥ ሲኖሩ የነበሩ ኤርትራኖች በተመሳሳይ መልክ ጥያቄአቸውን አቅርበዋል። ያካተቱት ዝርዝር ሐተታ ረዢም በመሆኑ፤ የመጀመሪያዋን ብቻ ልጥቀስ፦ አንዲህ ይላል፤-

 እኛ በኢትዮጵያ ውስጥ የምንኖር ሁለት መቶ ሺህ የምንሆን ኤርትራውያን በኤርትራ ውስጥ የሚኖር ወንድሞችና ዘመዶች አሉን። የእነሱንም ችግር ብዙ ከመሆኑ በስተቀር በዚያ ክፍል በሚገኘው ባልተረጋገጠ ሁኔታ ውስጥ አለመጠን ተጨቁነው ይኖራሉ። የሚበዙት የተማሩት ኤርትራውያን ከኤርትራ እየተሰደዱ ባሁኑ ጊዜ በእናት አገራቸው (ኢትዮጵያ) ውስጥ በነፃነትና በመልካም የኑሮ ደረጃ ተደስተው የሚኖሩ መሆናቸውን እዚህ ላይ ማንሳት አስፈላጊ ነው። በጣም የሚያሳዝነው ካገራችን መለየታችን ብቻ ሳይሆን ከወሰን ባሻገር ያሉት ወንድሞቻችንና ዘመዶቻችን በችግርና በጭቆና ውስጥ እንዲኖሩ ማወቃችን ነው። ስለዚህ የኤርትራ ወደ ኢትዮጵያ መቀላቀል ጉዳይ በተቻለ ፍጥነት አንድ ውሳኔ አንዲያገኝ ልመናችንን እናቀርባለን።
ሲሉ እነሱም በበኩላቸው ጥያቄአቸው ለኰሚሽኑ በደብዳቤ ገልጸዋል።

የወያኔ ትግራይ ባንዳው መለስ ዜናዊና ኢሳያስ አፈወርቅ ሴራ በኢትዮጵያ

የትግሬ ባንዳዎች ኢትዮጵያን የባሕር ወደብ አልባ ለማድረግ ለኤርትራኖች ወግነው የተጠቀሙባቸው የቅን ግዛት ካርታዎች እና ውሎች በዛሬው ዘመን ውድቅ መሆናቸውን ለማየት የተለያዩ ካርታዎችን እንመልከት እና ውይይታችንን እንደምድም። ድርጎቹ እነ ሻለቃ ዳዊት /ጊዮርጊስ እና ካሳ ከበደ እንዲሁም ንአመን ዘለቀ የመሳሰሉ የኤርትራ ነፃነት በሕግ የታወቀ ነው፤ ያለቀለት ነው፤ ኤርትራ፤ ዓሰብ፤ ወዘተወደ እሚለው ዝባዝንኬና ጥያቄ አንመለስም  (ሻለቃ ዳዊት ወ/ጊዮርጊስ) የሚሉን ጨለምተኞች ወይንም የወያኔ ትግሬ ባንዳዎችዓሰብ! ዓሰብ! የሚሉ የአማራዎች ጥያቄ ነውየሚሉን ባንዳዎች ሁሉ እነዚህ ካርታዎች እንዲያጤንዋቸው እንጠይቃቸዋለን።

ሦስት ካርታዎችን እንመልት

 የሚከተሉት 3 ታሪካዊ የተለያዩ የኢትዮጵያ መልክአ ምድሮችን እንመለከታለን። ይህ መልክአ ምደር/ማፕ የፕሮፌሰር ንጉሳይ አየለ የምርምር ውጤቶች ስለሆኑ አስቀድሜ ለሳቸው ምስጋናዬን አቀርባለሁ። በእነዚህ መልክዓ ምድሮች የምንመለከተው ቁም ነገር ጣሊያን ከአፄ  ምንሊክ ጋር ያደረገው የድምበር ውል በማፍረስ እራሱ ያዘጋጀው 1888 እስከ1928  ኢትዮጵያን ያዋሃደ የመጀመሪያው የኮሎኒ/የወረራ መልክዓ ምድር /ካርቶግራፊን እንመለከታለን። ከዚያ 5 አመት ግራ እና ቀኝ በጀግኖች እየተዋከ ቆይቶ 1933 . ከኢትዮጵያ እና ከኤርትራ ተባረረ።

ግርማዊ ቀዳማዊ ሃይለስላሴ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ ጣሊያን በሠራው ካርቶግራፊ እና እራሱ ኤርትራ እና ኢትዮጵያ አንድ ግዛት መሆናቸውን የሰራውን እና ውሉን አፍርሶ የሰራውን መልክዓ ምድር ተከትለው ሕዝቡን በማማከር እና ከላይ ባስነበብኳችሁ የኤርትራ ጥያቄና ፍላጎት እሳቸውም ጠቅልለው ሕጋዊ መልክዓ መሬታቸውን እስከ 1966 . ድረስ አስተዳደሩ።

 ከዚያ ደረግ 1966 እስከ 1991 . ድረስ የተረከበውን ሕጋዊ መልክዓ ምድር ሲያስተዳድር ቆይቶ በዚያ 17 አመት ውስጥ ውስጣዊ የድምበር አስተዳዳር ለውጥ አደረጎ ዓሰብን እና ሌሎችን በራስ ገዝጀሪ መንደሪ’ (ሪዲሰትሪክቲንግ) ሕግ በመከተል አስተዳደሩ ወደ ወሎ አዛውሮታል።

 የመረብን ወንዝ ጥሼ ወደ ኢትዮጵያ ወደ ትግራይ ድምበር ከገባሁ በጣሊያን እና በምንልክ የተደረገው ዉል አይጸናም ብሎ የፈረመበትን ዉል ድምበር ጥሶ 1928 . ኢትዮጵያን ለሁለተኛ ጊዜ በሁለት አቅጣጫዎች ኢትዮጵያን ወርሮ የኮሎኒ አዲስ መልክዓ ምድር የሰራበትን ብቻ ሳይሆን፤ እኔ በሆነ ምክንያት ኤርትራን ለቅቄ ስወጣ፤ ኤርትራ ለሕጋዊ ባለቤቷ ለኢትዮጵያ አስረክባለሁ፡ ያለውን ዉል ሁሉ ማጤን ያስፈልጋል።

 ከአክሱም ዘመነ መንግስት ጀምሮ እስከ ደርግ ጊዜ በወላጆቻቸው አስተዳዳር ሥር በአጥንታቸውና በደማቸው ተከብሮ የቆየው የባሕር ነጋሽ ምድር ዛሬራሳቸውንወያኔብለው የሚጠሩ ትግራይ ውስጥ የበቀሉ ባንዳዎቹ የኤርትራ ጉዳይ የኮሎኒ ጥያቄ ነው፡ በቅኝ ግዛት የያዘቻት ደግሞ ኢትዮጵያ ነች፡ ስለሆነም መለክዓ ምድሩን ለማካለል በኮሎኒ/በቅኝ ግዛት ደምብ እና ካርታ ተደራድረን ኤርትራን ጉዳይ እንፈታለን ያሉትንም ቢሆንየኮሎኒሕግም ቢሆን አልተከተሉም። አሁን አሁን ከአልጄሪስ ስምምነት ወዲህ ብዙ የወያኔ መሪዎች እና ደጋፊዎቻቸው የነበሩ ስምምነቱ የወያኔ መሪዎች እንጂ የሕዝብ ውሳኔ እንዳልነበረ ሁለት ያታወቁ የትግራይ ተወላጆች እንዲህ ይገልጹታል፡-

 “Before anything else, the people living in the region called “Eritrea” are, Tigreans. The idea of “Tigreans” and “Eritreans” as separate peoples, was never ours. See editorial (December 1993) Ethiopian Commentator, Haile Mariam Abebe.).
ሻዕቢያዎች እየነገሩን ያሉት ኤርትራ ነፃ የወጣቺው በሕግ ሳይሆን በጉልበታችን ነው። ብለዋል። በትግሬ ምሁራን የሚገለጸው እውነታው ግን እንዲህ ነው፦

“When the EPLF was pinned down by Mengistu’s army in Nakfa, the Tigrean fighters arrived for its rescue twice. During the “Red Star Campaign” of 1982, for instance, Tigreans fought in Nakfa on the Eritrean side, for nine months. Furthermore, without the supreme sacrifice of the Tigreans, the demand for Eritrean independence would have been little more than a bargaining chip for a negotiated settlement.”  ( Alem Abbay (1993) “An Unappreciated Gift Horse in the Mouth”, The Ethiopian Times, March/April 1,No. 2) 
አለም ዓባይ ከላይ የነገረን፤ “….ሻዕቢያ በመንግስቱ (ኢትዮጵያ) ወታደር ናቕፋ ላይ ተገፍቶ ትንፋሽ አጥሮት ከተራሮቹ ግድግዳ ተጣብቆ ሞቱን ሲያጣጥር  የወያኔ ትግሬ ተዋጊዎች ወደ ናቕፎ ገስግሰው ቶሎ ደርሰውለት ከፍተኛ መስዋዕት ከፍለው ከደርግ ሃይለኛ ብትር ባያድኑት ኖሮ የሻዕቢያ መጨረሻ ዕድል ከኢትዮጵያ ጋር በደርድር ይቋጨው ነበር።እንዳለው ሁሉ እውነትም ሻዕቢያ ዓሰብን ለመስጠት ዝግጅነቱን ለደርግ መግለጹ ይታወሳል።

ወያኔዎች የኰሎኒ የግዛት ማፕ ብለው ወደ ዓለም መድረክ ለድርድር (ለሴረው) ሲቀርቡ ይዘውት የመጡት ማፕየኰሎያሊስትዋ ጣሊያን እንጂ” “የኰሎኒያሊስትዋ ኢትዮጵያአይደለም። ምክንያቱ ምንድ ነው? ቢባል፤ የመጨረሻዋ ኢትዮጵያ ኮሎኒያሊስት ነች ሲሉ የደሰኮሩበትን ሁለቱወንበዴዎችበግብር ለመተርጎም የኢትዮጵያን ኮሎኒያል ካርታ ይዘው ከሄዱ ከታች የሚታየው 3ኛው ካርታ ሕጋዊ ሊሆን ነው። ደግሞ ዓሰብን ወደ ኢትዮጵያ የሚያስገባ መሆኑን በደምብ ስለሚያውቁ እና ስጋት ስላደረባቸው፤ በለመዱት ዓመጽ እና ቅጥፈት ከውጭ ኢትዮጵያ ጠላቶች ጋር ተመካክረውኢትዮጵያየት ትደርሳለችኢትዮጵያን አምበርክከናታልስለዚህ የበሰበሰ ጣሊያን ማፕ ብቻ ይዘን አንቅረብ ብለው ኤርትራን አስገነጠሉ።

 በጣም የሚገርመው ደግሞ ከጣሊያን ካርታዎችም ቢሆን መርጠው (ፒክ ኤንድ ቹዝ) ነው ለግንጠላ የሚያመቻቸውን የበሰበሰውን የድሮ ማፕ የተጠቀሙበት።እንደነገርኳችሁ በማፕ የሚገዙ ቢሆኑ ኖሮ ጣሊያን የሰራው ኤርትራን ከኢትዮጵያ ጋር ያዋሃደው 1928 እስከ 1933 . የመጨረሻውን ውሉን አፍርሶ የሰራውን አዲሱን የጣሊን ቅኝ ማፕ ሊጠቀሙበት በቻሉ ነበር። ሆኖም ገብሩ አስራት በመጽሐፉ አንደገለጸው በባንዳው ወየኔ አመራር ውስጥ ከኤርትራኖች በላይ ኤርትራኖች ሆነው ኤርትራኖችን ለመጥቀም ከነሱ ጋር ወግነው አገራቸውን ኢትዮጵያ ፍትሕ በተጻረረ ሁኔታ ኤርትራን አስገንጥለው 90 ሚሊዮን ሕዝብ ያለ ባሕር ወደብ አስቀርተው በጠላት አንደትከበብ አድርገው የፈርንሳይ ጥገኛ የሆነቺውን ከጅቡቲ እና ስርዓት ከፈረሰባት (ፈይልድ ስቴት) ከሶማሊዋ የሐርጌሳ የወደብ ተከራይ ቴናንት/ጥገኛ አደርገዋታል።

ሦስቱ ካርታዎች ወያኔዎች ለኤርትራ ጥብቅና ቆመው የባሕር በር ለኢትዮጵያ ሲዘጉ፤ የተጠቀሙባቸው ወጋ ቢስ የሆኑየፈረሱ የቅኝ ግዛት መከራከሪያ ውሎችብለው የሚሞጉቱባቸው በምኒልክ እና በጣሊያን ፋሺስት መካካል ተደረጉ የተባሉ ሦስቱ ዉሎች 1900/19002/1908(እኤአ) ውሎች ናቸው። እነዚህ ውሎች ዋጋ ቢስ ናቸው አንቀበላቸውም ብልን የምንሞግትባቸው ምክንያቶች በሚከተሉት ነጥቦች ምክንያቶች ነው። በቀላሉ አንዲገባችሁ ባጭሩ ላስረዳ፤-

1)    May, 1889 (ኤዘአ)ውጫሌ ውል እየተባለ የሚጠቀሰው ምኒሊክ ለመሳሪያ እና ለገንዘብ ልውጥ ኤርትራን ለጣሊያን ሸጧት የሚባለው ውል የያዘ እና ኢትዮጵያ የጣሊያን ቅኝ ነች የሚለው በጣሊያን ቋንቋ የተጻፈው ከአማርኛው ትርጉም እና ውል የሚጻረር በመሆኑ ምኒልክ ውሉ እንዲስተካከል በትዕግስት እየጠየቁ አንዲስተካከል ቢጠይቁም ጣሊያን አልለውጠውም በማለቱ ምንሊክ 1893 ( ) በግልጽ አወጁ፡ ዋጋ አንዴሌለው ለጣሊያን እና ለዓለም አስታወቁ። ጣሊያን ኢትዮጵያን ካልገዛሁ ብሎ 1888 ድምበር ጥሶ ( አቆጣጠር) ዓድዋ ላይ ጦርነት ከፍቶ ውርደቱን ተከናንቦ እጁን ሰጠ። ከዚያ በፊት የነበሩት ውሎች በሙሉ ፈረሱ።ለጊዜው ለሁለቱ ተዋጊዎች ደምበር ሆነው የሚያገለግሉ ሦስት ወንዞችን መረብ፤በለሳ እና ሙና እንደ ድምብር አጥር ሆነው ተወሰኑ።


2)  ምኒሊክ ሰራዊታቸው ይዘው ወደ ኤርትራ መዝለቁ ፤ጣሊያን ተዋጊ ትኩስ ሃይል፤ስንቅና መሳሪያ በባሕር እየተላከለት አንደሆነ እና በተጨማሪም እዚህ ለመጥቀስ የማያመቹ ሰፊ የሆኑ የመሃል፤የደቡብ እና የምስራቅ ኢትዮጵያ ግዛት ክፍሎች ዝርዝር ትንተናዎች የሚሹ ሰፋፊ ያልተጠቀሱ ምክንያቶችም ጭምር ጦርነቱን መግፋት አደጋ አንዳለው በመገመታቸው ሰራዊታቸው ከድሉ በሗላ በደስታ ወደ እየ መንደራችን አንመለሳለን ብሎ መፍረስ በመጀመሩ እና በከብትና በሰውሕይወት ረሃብ እና በሽታ ትግራይ ውስጥ ግብቶ ብዙ ሰው ስላለቀ (የስንቅ ችግር) እና በመሳሰሉ ሁኔታው አመች ስላልነበረ ኤርትራ በጣሊያን እጅ ልትቆይ ወሰኑ። ኤርትራ ሲቆይ ድምብር እንዳያልፍ ተፈራረመ።ኤርትራ ለቆ ሲወጣምኤርትራለባለቤቷ ለኢትዮጵያ አንደምታስረክብ 1896 እና 1900 (ኤአ) ውል ገባ። ኤርትራ ለማንም መንግሰት /ሃይል/ተዋዋይ አሳልፋ ለመስጠት ወይንም መሸጥ አንደማትችል ፈርማለች። (በሗላ ቃሉን አጥፎ ኤርትራ ለእንግሊዝ ሰጥቶ ወጣ፤ ወይንም አንግሊዝ በጉልቷ ነጠቀች)


የተጠቀሱት ስመምነቶች አስመልክተው አሜሪካ ውስጥ የሚኖሩት ታላቁ የታሪክ ምሁር / ሃይሌ ላሬቦ እንዲህ ይላሉ።

 “It should be emphasized that the treaties of 1902 and 1908 under which Eritrea claims the disputed territories are essentially flawed. These territories belong indisputably to Ethiopia and until Italy, in its attempt to provoke another war with Ethiopia annexed them in 1929 by force, they were administered by Ethiopia. What makes even more difficult the settlement of conflict between the two countries according to the colonial treaties is the fact that the geographical map of Eritrea has constantly changed during and after those treaties as the following instances highlight:

Even under Italian rule, considerable part of Eritrea was under the sovereignty of Ethiopia. This includes the huge expanse of land under the control of Dabre Bizen and its dependencies (daughter monasteries) that were directly administered by the imperial Ethiopian government. If Eritrea insists that the border should be marked according to the above-mentioned colonial treaties, it is within Ethiopia's power to claim back these territories and those forcibly annexed by Zolli in 1928 and 1929. In both ways, Eritrea is bound to lose substantial mass of its land. Moreover, the control of Dabre Bizen and its dependencies will give Ethiopia a safe gateway to the important port of Massawa. Understandably, this will have serious consequences for Eritrea as an independent state.
ጣሊያን ኤርትራን እያስተዳደራት እያለም ቢሆን ኤርትራ ውስጥ የሚገኘው ደብረቢዘን ገዳም ሳይቀር በኢትዮጵያ ኣስተዳደርና ንብረት ነበር (በውጫሌ ውስጥ ተጠቅሷል)


http://www.ethiopianreview.com/2001/Article_HaileMLareboAPRJUN_2001.html

3)   ጣሊያን ለሁለተኛ ጊዜ አልደፍርም ያለበትን የድምበር ውል እንደገና ጥሶ በመረብ እና በኦጋዴን ገብቶ 1928 (ኢዘአ) ኢትዮጵያን ወረረ። 5 አመት ሲዋከብ ቆይቶ ተሸንፎ ወጣ። ከዚህ በፊት የነበሩ ውሎች ሁሉ ፈረሱ።

4)  ከዚያ በኋላ በእንግሊዝ ተንኮል ኤርትራ ወደ ኢትዮጵያ መዋሃድ ሲኖርባት ከሃያላኑ አንዱ በመኖሩ ኤርትራን እና ትግራይን ገንጥሎ ለማስተዳዳር እንዲመቸው ፍላጎት ስላደረበት  ኤርትራ ውስጥ እቆያለሁ ብሎ ተንኮል ሰራ። በዚህ ጭቅጭቅ ተነሳ። ከሁለተኛ ዓለም ጦርነት በኋላ 4 ሐያላን መንግስታት ሲባሉ የነበሩት የመሰረቱት የኤርትራ እና ኢትዮጵያ ጉዳይ መርማሪ አካል በደረሰበት ጥናት መሰረት፤ የተባበሩት መንግሥታት ማሕበር ጉባኤ ኤርትራ በንጉሡ የዘውድ አስተዳደር ሥር ሆና ፤የራስ ገዝመብት ተሰጥቷት 10 አመት ከቆየች በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ትዋሃድ ብሎ ውሳኔ ሰጠ። 1900/1902/1908 የነበሩ ዉሎች እንደገናለሦስተኛ ጊዜበዚህ ባዲሱ ሕይወት እና አስተዳደራዊ ለውጥ ተሻረ።

5)  1944 . (ኢዘ ) ኤርትራ እላይ እንደተመለከታችሁት መሰረት በሕዝቡ ተወካዮች ኤርትራ ከኢትዮጵያ ሙሉ ውሕደት አደረገች። በዚህ ለአራተኛ ጊዜ የቆዩ ዉሎች በሙሉ ፈረሱ።

6)  ዓሰብ ከዋነኛው የኤርትራ ማሕበረሰብ 400 .ሜትር ርቀት ርቃ ትገኛለች። ለብዙ አመታት መላትም እስከ ደርግ ፍጻሜ ድረስ ከኤርትራ ይልቅ ምጣኔ ሐብታዊ (ንግድ) እና ማሕበራዊ ግንኙነት ከኤርትራ ይልቅ ከኢትዮጵያ ጋር ነበር። ዓሰብ ለደሴ 70/ ትርቃለች። የወደብ መጠቀሙ መብት እና ሂሳቡን በሕግ ምረኩዝ ስታሰሉትወያኔዎችባሕር ወደብ ለኛ መከልከላቸው ትግራይ ትግርኚ መደብ ሊጠብቁት የፈለጉት ሴራ አለ (ዓሰብ ወደብና አካባቢ አስቀድመው ወደ ትግሬ አጠቃልለውት እንደነበር በረሃ ውስጥ ያዘጋጁት ካርታ ይመሰክራል) ወይንም በሥልጣን ያሉ ትግሬዎች ወደ ኤርትራ የሚያደሉት፤ ሙሉ በሙሉ ወይንም የሁለት ደም ዲቃላዎች ሆነው ይበልጥ ለኤርትራ በማዳላታቸው ነው። ከሁለቱ አንዱ።

7)   ወያኔዎች አልጀሪስ ሄደው ባቋቋሙት ፈራጅ አካል 1902/1905/1908/ ጠሊያን የሰራው ካርታ እና ስምምነት አንፈረዳለን ሲሉ በሚሰጠው የመጨረሻ ውሳኔይግባኝማለት እንደማይቻል የተፈራረሙበት ምክንያትም ከዚያ በኋላ የተሰሩ ካርታዎች እና ውሎች ካቀረቡይዘውት የሄዱት ውሉየበሰበሰ፤የማይሰራ መሆኑን አስቀድመው ስላወቁ፤ይግባኝየሚያግድ ስምምነት ሆን ብለው መፈራረማቸውለ፤ግልፅ ሴራ መሆኑን ያሳየናልነ። ለወደፊቱም በሕጉ መሰረትአንድ የመንግስት ተወካይ/አካል/ ሆን ብሎ የአገሩን ጥቅም የሚጎዳ ስምምነት ከፈረመ ስምምነቱ እንደገና እንደሚመረመር የተባበሩት /ሕግ ይጠቅሳል። እነ ሻለቃ ዳዊትና ካሳ ከበደ ግን ይህንን ሊደብቋችሁ ይፈልጋሉ።

     አሁን፤ ለማስረጃ ያቀረብኳቸው 3 የተለያዩ መልክዓ ምድሮችን እነሆ ተመልከቱ::

  ኢትዮጵያ የቅኝ ገዢ ነበረች “ከተባለ” በ1964 የካይሮ አፍሪካ ውል መሠረት በማድረግ ኤርትራ “የመጨረሻዋ” የቅኝ ገዢዋ የአሰመረችላትን የመልክኣ መሬት አስተዳደር ይዛ መገንጠል ነበረባት። ሆኖም የወያኔ ትግሬዎች ኢትዮጵያን ለመጉዳት በሕግ የተጣሰውን የኢጣሊያ ቅኝ ገዢ መስምርን  በመጠቀም በሴራ እንዴት እንደጐዱን ተመልከቱ። ለዚህም ነው  በሴራ የተፈጸመ ውል ነው ስለዚም አንቀበልም የምልበት ምክንያት።ይኼው ተመልከቱ። ካርታውን በትልቁ ለማየት በኪ-ቦርዳችሁ ላይ Ctr + የሚለውን ሁለቱን ቁልፎች አብሮ መጫን ነው። (Ethio Semay)
Ethio Semay


   እንደገና ልድገመው፡ በዚህ መረጃ መሰረት ኮሎኒዎች ነን ከተባልን የመጨረሻው የኮሎኒካርታ” የቀረጸው እና የመጨረሻው ኮሎኒያሊስት ማን ነው? የሚለው ጥያቄ እናቅርብ። ኢትዮጵያ የቅኝ ገዥ ባዕድ ነች በለውናል። በኮሎኒያሊሰት ካርታ/ማፕ እንዳኛለን ካሉ እኛ የሰጠናቸውን የመጨረሻዎቹ ቅኝ ገዢዎች የምንባለው የሰራንላቸው የኮሎኒ ማፕ ለምን ይዘው ለድርድሩ አልተጠቀሙበትም? 1964 የካይሮ ውሳኔም ተገንጣዩ የመጨረሻው ቅኝ ገዢ የሰጠው መሬት/ቅርጽ ይዞ ይሄዳል ይላል። መጨረሻ ቅኝ ብለው ወያኔዎች የሰየሙንም እኛ ከሆንን፤ ኢትዮጵያዊያን ቢሆኑ ኖሮ የኛን ካርታ ይዘው መከራከር ነበረባቸው። መልስ የሚያሻው ጥያቄ ነው።

ባንዳዎቹ በእውነተኛ ክርክር ጎሮራቸው ስለታነቁ ለዚህ ጥያቄ እስካሁን ድረስ መልስ ሲሰጡበት የሰማነው መልሳቸውኢትዮጵያ ያለ ወደብ 27 አመት ኖራለች ስለዚህ አያስፈልገንምወይንም በስብሐት ነጋ መልስ መሰረትዓሰብ ሳይሆን ጅቡቲ ነው ለኛ ለኢትዮጵያ የሚረባው” (ዓሰብን አትጠይቁ ወደ ትግራይ- ለትግራይ ትግርኛ መርሃ ግብሩ ስለሚጠቃለል ማለቱ ነው)። ወያኔዓሰብበትግራይ ክልል ያካተተ ካርታ ሰርቶ እንደነበረም ታውቃላችሁ):: ኤርትራኖችም ሆኑ የወያኔ ትግሬዎች  ለጥያቄአችን ቀጥተኛ መልስ ሊመለሱልን አልቻሉም። 27 አመት ያለወደብ ከጅቡቲ፤ከሶማሊ ወደብ እየተከራዬን ኑረናል፤ ስለዚህ ያለ ወደብ መኖር ይቻላል፤ የሚለውመልስ ሲያጡ የሚመልሱት መልስ ነው።  ለነገሩ ኑሮ አይባልም እንጂ ኤርትራም  እኮ 27 አመት ወደቧ ባዶ ሆኖ ኖራለች። ጥያቄአችን አጭር፤ቀጥተኛና ግልጽ ነው!!!  27 አመት ዳክረው መልስ ያጡበት ጥያቄ አሁንም እንዲመልሱልን እንጠይቃቸዋለን።

ዛሬ የፈራነው እና የተነበይነው አውን ሆኖ  የየመን ሁቲ ተዋጊዎችን ለመጨፍለቅና የቀይ ባሕር ወሽመጥ ለመቆጣጠር የነበራቸው የዘመናት  ሕልም ዓሰብ እና ምጽዋ “አሜሪካኖች፤ኤኢሁዶች፣ኢራኒያኖች እና ዓረቦች (UAE…) ተከፋፍለው ይዘውታል።፡ይህንን ስንል፤ ውሸታሞች ሲሉን የነበሩት ዛሬውሸታሞቹእኛ ወይንስ እነሱ?  The UAE is scrumbling to controle posrt in Africa ወይንም Eritrea: Another Venue for the Iran-Israel Rivalry.


(ሳውዝ ፍሮንት በመባል የሚታወቀው ‹‹ፎረይን ፖሊሲ ዲያሪ›› በሚባል ፕሮግራሙ የቀረበው አጭር ግን ጥልቅ መረጃ የያዘ ዘጋቢ ፊልም ነው፡፡ “Arab Coalition Expands into the Horn of Africa” በሚል ርዕስ ባሰራጨው ዘጋቢ ፊልም፣ ‹‹ይኼ ለኤርትራ ከፍተኛ የገንዘብ ምንጭ ብቻ ሳይሆን፣ እስካሁን የገጠማትን የመነጠል ችግር የሚፈታ ነው፤›› ብሎታል፡፡ በአፍሪካ ኅብረት የደረሰባትን ‹‹የሥርዓተ አልበኝነት›› ፍረጃም ነፃ ያወጣል ብሏል፡፡ ‹‹በእርግጥ ኤርትራ ማንም ቢሆን ገንዘብ የሚሰጣት ከሆነ ከመደገፍ ወደኋላ አትልም፤›› ይላል በዘጋቢ ፊልሙ ላይ የቀረበው ሐተታ፡፡ በአሰብ እየተገነባ ያለው ወታደራዊ ኃይል በአፍሪካ ቀንድ ከዚህ በፊት ያልነበረና የመጀመሪያው መሆኑንም ጠቅሷል፡፡ ‹‹ለአካባቢው (ለአፍሪካ ቀንድ) አደገኛ እንቅስቃሴ›› በማለት የአፍሪካ ቀንድ የዓለም አቀፉ የግጭት እንቅስቃሴ መናኸሪያ ሊሆን እንደሚችል ግምቱን ያስቀምጣል፡፡

ይህ ሃቅ እውን ሆኖ ከተገኘ በኋላ ያለ ወደብ መኖር ይቻላል ሲሉን የነበሩ የወያኔ አለቅላቂ አሽከሮች (አይጋ ድረገፆች፤ ትግራይ ኦን ላይን እና የወያኔ ሎሌዎች ሁሉ) ባለፈው 6 አመት በፊት ዓረቦች  ዓሰብን ተቆጣጥረውታል ሲባልመንግሥታችን፤ እባካችሁ ወሳኝ የሆነ አርምጃ በመውሰድ ኢሳያስን አስወግዳችሁ  ስጋት የሆኑብንን ዓረቦችን ኣባርሩልንብለው ሲጮሁ ሰምተናል። ዛሬ ደግሞ ወያኔ ከሥልጣኑያለ ጥይት ተባርሮ  ወደ መቀሌ ሲሸሽ ትግራይ ኦን ላይን የተባለ የትግራይ ትግርኚ አቀንቃኝ ድረገጽ ሰሞኑ ታምራት ነገራ ስለ ኤርትራ ጉዳይ ኢ-ሕጋዊነት አስመልክቶ በሰጠው አስተያጥ  ኤርትራነውያኑን ወግነው እንደ ለማዳቸው አንደ ውሻ ሲጮሁ አንብበናቸዋል።

እንግዲህ ወደ ቁም ነገሩ ልመልሳችሁ እና ወያኔዎች የኤርትራን ጉዳይ መፍትሄ ለማግኘት በኮሎኒያሊሰት ማፕ እንዳኛለን ካሉ ለምን እኛ የሰጠናቸውን የመጨረሻዎቹ ቅኝ ገዢዎች የምንባለው የሰራንላቸው የኮሎኒ ማፕ ይዘው ለድርድሩ አልተጠቀሙበትም? ጥያቄአችን አጭር እና ቀጥተኛ ነው። ለመረዳት አያስቸግርም።
ይህንን ለመመለስ 27 አመት ፈጀባቸው- አሁንም መልስ የላቸውም፤ ዛሬም ለጥያቄችን መለስ እየጠበቅን ነው። ወይ ኢትዮጵያ የኤርትራ ቅኝ ገዢ አልነበረችም በሉን ወይንምመነበረች” ካላችሁ ደግሞ ጥያቄአችንን መልሱ። ካልሆነ ክርክራችሁ አንጅት የሚያሳርርየፖለቲካ ጨዋታ ነው ፕሮፈሰር / ሃይሌ ላሬቦ አንዳሉት

“…the time gap that exists between these treaties and the Eritrean independence is so vast, and the change in status that Eritrea underwent during this same period is so intricate as to make any appeal to colonial treaties and OAU charter of no use beyond political gimmickry.”
(Colonial Treaties in the Context of the Current Ethio-Eritrean Border Dispute and Settlement 4th International Conference of Ethiopian Studies, November 6-10, 2000, at the Institute of Ethiopian Studies, Addis Abeba University. Ethiopian Review Ethiopian Review, April 2001)  

ኤርትራ የደፈረሰች፤ ያለቀላት፤ የተበላሸች መንደር ጉራዋን እና ዕብደቷን ካላቆመች መጪው ዘመን የኢትዮጵያውያን ብርቱ ክንድ እየጠበቃት ነው። ምርጫው የራሷ ነው።
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር።
ጌታቸው ረዳ (ኢትዮፕያን ሰማይ)