ሶስቱ የአማራ
ነቀርሳዎች !!!
አቻምየለህ
ታምሩ
ኦዴፓ በአማራው
ህዝብ ላይ እየተገበረው
ያለው አይን ያወጣ
አድሏዊ አሰራርና የብአዴኖቹ
አፋሽ አጎምባሽነት!—
(Posted
at Ethio Semay)
እነዚህ
ከላይ የምትመለክቷቸው ሶስት የዐቢይ አሕመድ የአፓርታይድ አገዛዝ ቤተኞች መላው አማራ አልቆ ቢያድር የማይበርዳቸውና የማይሞቃቸው የአማራ ነቀርሳዎች ናቸው። ሶስቱም የዐቢይ አሕመድን ተልዕኮ ለመፈጸም እንወክለዋለን የሚሉትን አማራ ሸጠው የበሉ ይሁዳዎች ናቸው።
ዳግማዊት
ሞገስ
ዳግማዊት
ሞገስ ፦ የታከለ ኡማ የስልጣን ተጋሪ ሆና ምክትል ከንቲባ ተደርጋ ተሹማ ነበር። ታከለ ኡማ ኦሕዴድን ወክሎ በአዲሱ አረጋ ቋንቋ «የኦሮምያን ልዩ ተጠቃሚነት በአዲስ አበባ ለማስጠበቅ» የከተማውን ከፍተኛ የሥልጣን እርከን ከሕወሓት ዘመን በከፋና በፈጠነ መልኩ በአንድ ዘውግ ሰዎች ሲሞላው፣ ከአዲስ አበባ ኗሪዎች መካከል የአማራ ማንነት ያላቸው እየታዬ ቤታቸው ሲፈርስ፣ ስራ አጥ የአዲስ አበባ ወጣቶች ተቀምጠው የኦሮሞን ጥቅም ለማስጠበቅ ሲባል ከከተማ አስተዳደሩ ውጪ የመጡ ወጣቶች መታወቂያ እየታደላቸው በጥቃቅንና አነስተኛ ሲደራጁና ሌሎች ወንጀሎች በከተማ አስተዳደሩ ሲሰሩ ብአዴንን ወክላ ምክትል ከንቲባ የሆነችው ዳግማዊት ግን በእነ ታከለ ልክ እወክለዋለሁ ለምትለው አማራ ልትሰራ ይቅርና እነ ታከለ የሚፈጽሙትን ወንጀል «ሚስጥር ነው» እያለች ደብቃ መያዝን ዋና ስራዋ ያደረገች ጉድ ነበረች።
በአለም
ባንክ
ጥናት
መሰረት ከኢትዮጵያ ክልሎች ውስጥ የመጨረሻ ድሀና በመንገድ፣ በውሀ፣ በኤሌክትሪክና በሌሎች የኢኮኖሚና ማኅበራዊት መሰረተ ልማቶች ጭራ መሆኑ የተነገረለት ብአዴን የሚገዘግዘው የአማራ ክልል የሚባለው የሕወሓት የጠላት ቀጠና ነው። ዳግማዊት ሞገስ የትራንስፖርት ሚኒስቴር ከመሆኗ በፊት በመጨረሻው የፋሽስት ወያኔ የአገዛዝ ዘመን በአገዛዙ ሊተገበሩ ከተያዙ 41 የመንገድ ልማት ፕሮጀክቶች መካከል ሁለቱ ብቻ አማራ ክልል ለሚባለው እንደተመደበለት ተነግሮን ነበር። በዳግማዊት ሞገስ የትራንስፖር ሚኒስቴርነት ዘመን ዘንድሮ ደግሞ በአገር አቀፍ ደረጃ ከተያዙ የመንገድ ፕሮጀክቶች መካከል ዝቅተኛ የመንገድ ሽፋን ላለው የአማራ ክልል ለሚባለው አካባቢ የተያዘለት አንድ ፕሮጀክት ብቻ ነው።
ለማ መገርሳ በየትም
እርከን ላይ
ብንመደብ የምንሰራው
ኦሮሞን ወክለን
ነው ብሎ
ነበር።
በኦሕዴድ/ኦነግ ዘመን አማራን ወክላ የትራንስፖርት ሚኒስትር የሆነችዋ ዳግማዊት ሞገስ ግን ሚኒስቴር ሆና በተሾመችበት ዘመን በመንገድ መሰረተ ልማት ጭራ ለሆነው የአማራ ክልል ለሚባለው አካባቢ ፋሽስት ወያኔ እንኳ ይመድብለት ከነበረው ሁለት ፕሮጀክቶች አንዱን ቀንሳ ኦሮምያ ክልል ወደሚባለው የኦሕዴድ ኦነግ ግዛት አዛውራዋለች። የብአዴን አማሮች አማራን ጠላት ያደረጉት ኃይሎች ለፍላጎታቸው ማስፈጸሚያ ይሆን ዘንድ አማራ ክልል በሚባለው አካባቢ የተከሏቸውን የልማት አውታሮች ሳይቀር ሎሌ ላደረጋቸው የአማራ ጠላት ነቅለው የሚሰጡ ጉዶች ናቸው።
አዲሱ ለገሰ የሚባለው
የአማራ ባለደም «አማራ ክልል» የሚባለው አካባቢ ፕሬዝደንት ሳለ የነበሩ የልማት መዋቅሮችን አስነቅሎ ወደ ትግራይ እንዲጓዙ ያደረገው በኢትዮጵያ መንግሥት የተሰሩትን ብቻ ሳይሆን የፋሽስት ወያኔ የመንፈስ አባት የሆነው ፋሽስት ጥሊያን በጎንደር፣ ጎጃም፣ ሸዋና ጎንደር የሰራቸውን የልማት መዋቅሮች ጭምር ነው። የአዲሱ የመንፈስ ልጅ ዳግማዊትም እነሆ የአማራን ጠላት ያደረገው ፋሽስት ወያኔ የአማራ ክልል ለሚባለው አካባቢ ይፈቅድለት ከነበራቸው ሁለት የመንገድ ፕሮጀክቶች መካከል አንዱን ቀንሳ ጌቶቿ ለሚገዙት የኦሕዴድ/ኦነግ ክልል ሰጥታለች። የብአዴን አማሮች እንዲህ ናቸው! የብአዴን ወኪሎች እንወክለዋለን ከሚሉት ከአማራ ጉዳይ ይልቅ ሎሌ ላደረጋቸው ጌቶቻቸው ማደር ይበልጥባቸዋል።
ንጉሡ
ጥላሁን
ሌለኛው
የአማራ ነቀርሳ ንጉሡ
ጥላሁን የዐቢይ አሕመድ
አፈቀላጤ ነው።
ስለዚህ
ጉድ
ባለፉት ዓመታት የጻፍሁትን ወደኋላ መለስ ብሎ ማየት ይቻላል።
ብናልፍ
አንዷለም
ሶስተኛው
የአማራ ነቀርሳ ብናልፍ
አንዷለም
በሚኒስትር
ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ዋና አስተባባሪ ተደርጎ የተጎለተው ጉድ ነው። የብአዴን የማዕከላዊ ኮምቴ አባል የሆነው ብናልፍ አንዷለም «ነጻ ያወጡን ሕወሓቶች አይደለም ወልቃይትና ጠገዴን የተወለድሁበትን ጎጃም ደጋ ዳሞትን እንኳ ቢወስዱ ሲያንሳቸው ነው» ብሎ የሚያምንና «ሕወሓት በሕዝባዊ አመጽም ሆነ ሆነ በትጥቅ ትግል ከስልጣኑ ቢወገድ፤ ሕወሓትን መልሼ ወደ ሥልጣን ለማምጣት አብሬያቸው ደደቢት እንደገና እወርዳለሁ» የሚል ወደር የማይገኝለት ባንዳ ነው።
የብናልፍ
አንዷለም የሙሉ ጊዜ ስራ ወይም በዐቢይ አሕመድ የተሰጠው ተልዕኮ የአማራውን እንቅስቃሴ ማክሰምና የኦሕዴድ/ኦነግ ቅጣ ያጣ የበላይነት ማንበር ነው። ብናልፍ ከሁለት ሳምንት በፊት ባሕር ዳር ውስጥ በሚስጥር ያሰለጥናቸው ለነበሩ የብአዴን ካድሬዎች «ፌዴራል መንግሥት ከብአዴን የሚጠብቀው የፖለቲካ ተግባር ከምርጫው በኋላ እንደ ኢሕአዴግ መንግሥት ለመሆን አብንን ከጥቅም ውጭ አድርገን ማጥፋትና በአማራ ሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት እንዳይኖረው መስራት ነው» ሲል ስምሪት ሰጥቷል።
ኦሮምያ
በሚባለው ክልል ኦነግ ማደፋፈሪያ ስለተሰጠውና የዐቢይ ፓርቲ ምናልባትም ሊሸነፍ ስለሚችል ኦሕዴድ መንግሥት መሆን የሚችለው ብአዴን የአማራን ድርሻ ከአብን እንዲጫረት በማድረግ ብቻ ነው። ብናልፍ በአሁኑ ወቅት እየሰራ ያለው ይህንን የዐቢይ አሕመድ ፕሮጀክት ነው። አድልዎ እንደወረደ የመንገዶች
ባለሥልጣን ስምምነት ሲጋለጥ! የመንገዶች ባለሥልጣን ሲገነባው የኖረው መንገድ ከትግራይ ወደ ኦሮሚያ በማዞር ባለ ተራዎችን ይፋ አድርግ ውል ይህ አይን ያወጣ አድልዎ ሊያስገነባቸው ስምምነት ከፈረመባቸው ከአገሪቱ ካዝና እና ከዓለም ባንክ እና ሌሎች አበዳሪዎች በኢትዮጵያ ሕዝብ የሚመጣ ብድር እና እርዳታ እንደ ትላንት ለአንድ ወገን ያደላ ነውና ሊሰሩ ከታሰቡት 15 የመንገድ ፕሮጀክቶች 14ቱ አንድ ክልል ኦሮሚያ ማድረግ ስንቃወመው ይኖር ነውን አሳፋሪ አድልዎ መድገም ነው።
ኦዴፓ
በአማራው ህዝብ ላይ
እየተገበረው ያለው አይን
ያወጣ አድሏዊ አሰራርና
የብአዴኖቹ አጎምባሽነት!
ላለፉት
15 አመታት ሲሰራ የነበረው ነገር የአማራ ክልልን በመሰረተ ልማት አውታር ማዳከምና ማድቀቅ እንደሆነ ግልፅ ነው። በመሆኑም በክልሉ የመብራት፣ ቴሌኮሙኒኬሽን፣ ውሃ፣ ትምህርት እና የመንገድ መሰረተ ልማት አውታሮች እንዳይገቡ ተደርጓል። ይህን ደግሞ በዓለም ባንክ የተሰራ ጥናት አረጋግጧል። በጥናቱ መሠረት ኢትዮጵያ ውስጥ ዝቅተኛ የመሠረተ ልማት ተደራሽነት ያለው የአማራ ክልል እንደሆነ በሳተላይት መረጃ የታገዘ ተጨባጭ ማስረጃ አቅርቧል። የዶ/ር አብይ አመራር ሆነ አዲሱ የክልሉ ፕሬዜዳንት ከመሠረተ ልማት ግንባታ እና መስፋፋት ጋር በተያያዘ የሚወስዷቸው እርምጃዎች ላለፉት አመታት በአማራ ህዝብ ላይ ሲፈፀም የነበረውን በደልና ጭቆና፣ በተለይ ደግሞ ከላይ የተጠቀሰውን አድሏዊ አሰራር ከግምት ባስገባ መልኩ መሆን አለበት።
ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ
መንገዶች ባለስልጣን የመንገድ ግንባታን አስመልክቶ ያወጣው ሪፖርት የህወሓት አፓርታይድ ስርዓት እንዲቀጥል መደረጉን ያሳያል። ከዚህ ቀደም የመሠረተ ልማት ግንባታ እና የካፒታል ፕሮጀክቶች አመዳደብ ፍትሃዊ እንደነበረ ሁሉ ባለስልጣኑ ከዚህ ቀደም የተጀመሩ የመንገድ ፕሮጀክቶችን ለመጨረስ ቅድሚያ እሰጣለሁ ማለቱ የህወሓትን አድሏዊ አሰራር ከማስቀጠል የዘለለ ትርጉም የለውም። የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን የቀድሞውን
አድሏዊ
አሰራር እያስቀጠለ ነው ማለት ይቻላል። በመሆኑም የአዴፓ አመራሮች ከጠ/ሚኒስትሩ እና ከመንገዶች ባለስልጣን መስሪያ ቤት ጋር በመነጋገር አስቸኳይ መፍትሄ መስጠት አለባቸው። ይህ ካልሆነ ግን ፍፁም ያልተጠበቀና የከፋ ፖለቲካዊ ጉዳት ያስከትላል።
Achamyeleh Tamiru (Posted at Ethio Semay)
No comments:
Post a Comment