ግንቦት 7 የአማራዎችን ተጋድሎ የሰረቀ የመጀመሪያው “የአውደ ውግያ ፕላጊያሪስት/ሌባ”
ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay ድረገጽ አዘጋጅ)
የግንቦት 7 ውሸት በአማራ
ሕብረተሰብ ላይ የትግሬ ፋሺስቶች እያደረሱበት ያለው የዘር ጥቃት እራሱን ለመከላከል ግንዛቤው እንዲዳብር መረጃን በመመገብ ወደ
አገር ቤት በሚሰራጭ “የአማራ ድምፅ” በመባል የታወቀው ራዲዮ ጣቢያ
ተጋልጧል። እኔ ግን ውሸት ብቻ ሳይሆን ድርጊቱ “የአውደ ውግያ ፕላጊያሪዝም/ስርቆት” ብየዋለሁ።
እንዲህ ያለ የውጊያ ፕላጊያሪዝም/ስርቆት/ በዓለም ውስጥ ሲፈጸም ግንቦት 7 የመጀመሪያ ሳይሆን
ሁለተኛ ነው። ካሁን በፊት የወያኔ ትግራይ ፋሺስቶች ምንሊክ እና ባለቤታቸው የመሩት የዓድዋው ጦርነት ድል
የትግሬዎች የጅግንነት ሥራ ነበር ሲል የመላው ኢትዮጵያ ዜጎች የተካፈሉበትን ጦርነት ሰርቆ ፕላጊያዚዝም
ፈጽሟል። በዚህ ርዕስ ካሁን በፊት ባሳተምኩት “ይድረስ ለጎጠኛው መምህር” መጽሐፌ ውስጥ ትግሬዎች እዚህ ድረስ የተባለ አመርቂ
የጦር ተዋጊ ብዛት እንዳልነበራቸው እና በተደጋጋሚ የትግራይን ጦር የመሩት ራስ መንገሻ ጣሊያን እያባረራቸው እስከ ማይጨው ድረስ
እየተከተለ እንዳስቸገራቸው ገልጫለሁ። መላው ትግራይ በጣሊያኖች ተይዞ የትግራይ ሕዝብ የመከላከል አቅም እንዳልነበረው ገልጫለሁ። የትግራይን ጦር የመሩት ራስ መንግሻ ጦርነቱን አልቻልነውም እና እባክዎትን
ከዚህ ውርደት ያድኑን ብለው የተማጸኑበት ደብዳቤ በታሪክ መዛግብት ተዘግበዋል። የምኒሊክ ተዋጊዎች መንገሻን እና ትግራይን ከጣሊያን
ውርደት በማዳናቸው ራስ መንገሻ የምስጋና እና አድናቆት ደብዳቤ ጽፈዋል።
እነ ሃጋይ ሄርሊክም ሌሎችም ስለ የወቅቱ የአሉላ ጦርም/የትግሬ ጦረኛም በቁጥር
ጥቂት እንደነበርና እሳቸውም መንገሻን እየተከተሉ ሲሸሹ እንደነበር ዘግቦታል። እምየ ምንሊክ መላውን ሕዝብ አሰባስበው ሸዋን ወሎን
ለወራት በእግር እያቋረጡ ተጉዘው ያ ሁሉ ጦረኛ አስከትለው ትግራይ
ድረስ ሄደው፤አስገራሚ ድል በመጐናጸፍ፤ እኛ ትግሬዎች “የጣሊያን ክልሶች” ከማድረግ አድነውን፤ እናቶቻችን በሰላቶ የሲሲሊ ሥራ
አጥ የጣሊያን ቦዘኔ ዱርዬ ወራሪ ጦር ከመደፈር እንዳዳንዋቸው እየታወቀ፤ የትግራይ ፋሺስቶች “የዓድዋ ድል የትግሬዎች ድል
ነው” ሲሉ የትግሬ ፋሺስት ሊህቃን “ፕላጊያሪዝም”
ፈጽመዋል ስል በመጽሐፌ ውስጥ መጻፌ ይታወሳል።
የባድሜ “ፕላጊያሪዝም
የትግራይ ፋሺሰት ብሔረተኞች በዛው
ውሸት ብቻ ሳይወሰኑ፤ ሁለት ዓመት ሙሉ ዱርዬው ሻዕቢያ የትግራይን መሬት ይዞ ገበሬዎችና ኗሪዎችን አባርሮ ከ1000 ርዝምት በላይ
ያለው ድምበር በቁጥጥሩ አድርጎ ድፍን ሁለት ዓመት ወያኔ ሞክሮ፤ ሞክሮ ስላለቻለው፤ “ማፍረያው ወያኔ” ተማጽኖው (ልመናው) ወደ
ኢትዮጵያዊያን በማዞር የ100 አመት ዕድሜ ያላት አገር ሲላት የነበራትን ኢትዮጵያ “የ3000 አመት ዕድሜ ባለታሪክ ነች” ማንም
አይደፍራትም እያለ ልቅሶውን ወደ ኢትዮጵያዊያን በማዞር እባካችሁ የድሮ ወታደሮም ብትሆኑ ኑ እና የትግራይን ሕዝብ እርዱት ሲል
ልመና በማቅረብ ፤ከሶማሌ እስከ ጫፍ ለጫፍ አገር ያለው ሕዝባችን “ሖ!!” ብሎ በመነሳት፤ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ወደ ባድሜ እና
ዓይጋ ተራሮች በመዝመት (ያልተዋጋ ሕዝብም ፤ገንዘብ፤ ፍየል፤በሬ፤ ከብት፤ሱካር… ለተዋጊ ዜጎቻችን እየለገሰ) ሻዕቢያን አፈር ድቤ
በማስጋጥ፤ የትግሬን ሕዝብ እና የትግራይን ድምበር በማስመለስ ለሁለት አመት ከፍተኛ ብዛት ያለው ዙርያ መለሽ (1000 ኪ.ሜትር)
የፈንጂ ቀበራ ተደርጎበት እሱን እየረገጠ እና እያፈነዳ ሻዕቢያን እስከ ሱዳን ድረስ ሲያባርር የአካልና እና የሞት መስዋዕት ከከፈለ
በኋላ፤ ሓፍርት የሌለው ወያኔ ተመልሶ “ባድሜን” እንሰጣችኋላን ብቻ ቁጭ ብለን እንነጋገር እያለ ባድሜን ለማስረከብ ከመፍቀዱ ሌላ፤ ያ ሁሉ የኢትዮጵያዊያኖችና የድሮ ወታደሮች ጀግንነት እና መስዋእትነት በመርሳት “ድሉ በወያኔ ትግሬ ተዋጊ ሃይሎች” የተከናወነ
ጦርነት ነበር በማለት ልክ እንደ አድዋው ጦርነት ያደረገው “ፕላጊያሪዝም”
እንደገና ዓይኑን ሳያሽ የባድሜና የዓይጋ ወዘተ.. አውደ-ውጊያዎች ድል “ፕላጊያሪዝም” ፈጽሟል።
ዛሬ የጦርነት ውግያና ገድል እንደገና በወያኔ ትግሬ ያየነው አሳፋሪ “የጀግንነት ስርቆት”
ግንቦት 7 የተባለ “ውሸት በመጋጋር” የተካነ ድርጅት በጎጃም በጎንደር
አካባቢ እየተደረጉ ያሉትን አማራዎች በራሳቸው ትጥቅ እና ጅግንነት እያስመዘገቡት ያለውን ጅብዱ “የኔ ነው” ሲል የአማራዎችን ገደል
በመስረቅ “የነፃነት ሃይሎች” ሲል የጦርነቱን ታጋዮች ስም ለውጦ ፕላጊያሪዝም በመፈጸም በታሪካችን ውስጥ ከወያኔ ቀጥሎ ሁለተኛው “ፕላጊያሪስት” ሆኗል። እንዲህ ያለ የጀግንንት የውጊያ ስርቆት
የማጭበርብር ባሕሪ የሚመጣው መረን የለቀቀ “የሞራል ዝቅጠት” ከምን የመንጨ ነው? ለሚለው በራስ ያለመተማመን ያስከተለው የመጋለጥ
ጭንቀት፤ ወይንም በሰነፍነት መከሰስ አጅግ ያሳፈረው ድርጅት የሚፈጸም አጭበርባሪዎች የሚሄዱበት መንገድ ነው (ብቻ ስለዚህ ዝቅጠት
ሳይኪያትሪስቱ ደ/ር አሰፋ ነጋሽ ወይንም ሳይኮሎጂሰትዋ ዶ/ር አባባ ፈቃደ እንዲያስረዱን ለባለሞያዎቹ ልተወው)።
“አንድነት” እና “ኢትዮጵያ”
የሚባል ስም ሲነሳ “ያንገሸግሸኛል” (ያስጠላኛል፤ ያስታውከኛል) በማለት ሳያፍር በስብሰባ አዳራሽ ለመላው ኢትዮጵያ
አድማጮች እራሱን በመግለጽ የታወቀው ንአምን ዘለቀ የተባለው የግንቦት 7 እና ሻዕቢያን በማገልገል የታወቀው አንዳርጋቸው ጽጌን
የተካው “የሻዕቢያው ጡሩምባ” ንአምን ዘለቀ፤ ለውግያ ኤርትራ የሄደ መስሎን ከሸወደን በኋላ
ተመልሶ ወደ መኖርያው መጥቶ በየአደራሹ እየዞረ ኮሎኔል መንግሥቱ ሃይለማርያም ይመስል ገና ሥልጣን ሳይዝ ጠረጴዛን እየመታ
አድማጮቹን “ኢንቲሚዴት/ለማሸማቀቅ” የአማራ ታጋዮችን ሲዘልፍ በዩቱብ ተለጥፎ አንድ ወዳጄ ልኮልኝ አይቸው ገርሞኛል።
የአማራ ድምፅ የተባለው ራዲዮ ጣቢያ “ካልቶቹን” ለማጃጃል ወደ ውግያ ሄጃለሁ በማለት መኖርያው
አስመራ ከተማ እና ሲያሻው አሜሪካና አውሮጳ ያደረገው የውጭ ሃይሎች ቅጥረኛ ለ“ፕላጊያሪሰቱ” ብርሃኑ ነጋ እንዲህ ሲል
በጥያቄ ተችቶታል።
“በሰሜን ጎንደር ያለው የአማራ
ማንነት ተጋድሎ “የነፃነት ታጋዮች” ትግል እያልን እንዲነገር እንጂ እየታገልን ያለነው እኛ ነን” ማለቱን ዘ-ሓበሻ የተባለው ድረገጽ
ዘግቦታል። ‘የአማራ ማንነት ተጋድሎ’ እንዴት፤እንዴት ሆኖ ነው ከአርበኞች ግምባር ጋር የተገናኘው? ብለን ጠየቅን። ይላል ። ይህ
መጠየቅ ያለበት ግሩም ጥያቄ መልስ አላገኘም። ራዲዮኑ ብዙ ቁም ነገሮችን የያዘ ትችት አስተላልፏል። መደመጥ ያለበት ነው። ራዲዮኑ
ትክክል ብሏል። ፕላግያሪሰቱ የግንቦት7 መሪው በሰላሳ ከተሞች ‘ለካልቶቹ እና የዋህ አጨብጫቢዎቹ’ በስካይ-ፒ ያስተላለፈው መላውን
‘የውግያ ባለቤትነት ስርቆት’ ንግግሩ (ሙሉውን) እንዳያስተላልፍ ለዘሓበሻ ድረገጽ አስገንዝቦታል። በዚህም ምክንያት ሙሉውን የፕላጊያሪዝም
ስርቆት ለሕዝብ ይፋ እንዳይሆን ሆኗል። ምክንያቱን ስንገምት ደግሞ የነፃነት ሃይሎች እያለ የሚጠራቸው ታጋዮች ገድል ” የግንቦት
7” ሳይሆን “የአማራ ማንነት ተጋዮች” መሆኑን ስለሚያውቅ ዝርዝሩን ከገለጸ ‘የአማራ ራጋዮች’ በማስረጃ እንደሚያጋልጡት ስለሚያውቅ
“አጫብጫቢዎቹን” ለመጋለብ እንደተለመደው እንዲያመቸው በዝግ ችሎት ብቻ እንዲደመጥ እንጂ መላው ኢትዮጵያ አንዲያዳምጠው አልፈቀደም።
አማራን “ነፍጠኛ” እያለ የሚሳደብ ከአለቆቹ ወያኔዎች የተማረው አጭበርባሪ ቡድን ሁሉንም ሞክሮ ሲከሽፍበት “ፕላግያሪዝም” “የውግያ
ስርቆት ውስጥ ገባ”።
አማራና ኦሮሞን ደም ያቃባው “የቡርቃ ዝምታ” በዘር ወንጀል የሚፈለገው ወንጀለኛው ኤርትራዊው
ደራሲ ተስፋዬ ገብረአብ የመጽሐፍ መቅድም የጻፈለት ዶ/ር ተብየው ማፈሪያ ስለ አማራና ኢትዮጵያ አንድነት
ደንታ የሌለው ብርሃኑ ነጋ “እዚህ ትግል ውስጥ የገባነው ትግሉን ዳር ለማድረስ እንጂ ጫጫታ ፈጥረን እቤታችን ልንቀመጥ አይደለም”
ሲል የተለመደው “ወያኔን በሦስት ወር ውስጥ ታግለን “እመኑኝ” አዲስ አባባ ለፋሲካ እንገባለን” ዓይነቱ የውሸት አንጀራ
ጋግሮ ጅሎችን ከማጉረስ ወደ ኋላ
ከማለት ዛሬም አልቦዘም።
ይህ ሰው በሲኣይ ኤ እና ባውሮጳ
ሃይላት የተወደሰ በመሆኑ ቪዛና ፓስፖርት ተፈቅዶለት ሲያሰኘው ከተስፋዬ ገብረ አብ ጋር ምጽዋ/ጉርጉስም፤ ሲያሰኘው ሽምሩክ
እና ኒያላ ሆቴል፤ ሲያሰኘው አውሮጳ፤ አሜሪካ፤ እየተዘዋወረ ባለቤቱን እያቀፈ ሲሄድ፤ ‘ሃረና በረሃ’ ውስጥ ታግተው አውሮጳም ሆነ
አሜሪካ እየመጡ ሚስቶቻቸውም ሆነ ቤተሰቦቻቸውን እንዳያዩ ተከልክለው “መውጪያ አጥተው” እንዳይንጫጩ “ጠረጴዛ በሚደበድቡ”
አስፈሪ “ፕላጊያሪሰት” አምባገነኖች ታግደው ኤርትራ ውስጥ ያሉትን ምስኪኖችን አፍኖ ይዞ “እንዳትንጫጩ” እያለ በሻዕቢያ
ወረበላ ገራፊዎች እንዲሰቃዩ ማድረግ ነው የብርኦት 7 “ትግል ዳር ማድረስ ማለት”።
ትንሽ ሳያፍር ‘የአማራ ማንነት ተጋድሎ ታጋዮች’ እያደረጉት ያለውን “በቆብቃቀው”
የትግሬ ፋሺስት ሥርዓት ተደናግጦ “የጎስታፖ ኮማንድ ፖስት” እስከማወጅ ድረስ ያደረሱትን የጀግኖች ገድል የኔ ነው ብሎ
ባደባባይ ሲዋሽ የሕዝቡ ሕሊና ምን ዓይነት የግንዛቤ ዝቅጠት ውስጥ እንዳለ በቂ ግንዛቤ ያየንበት ነው። ሕዝቡ ዛሬም
ውሸት ሲነገረው “ከማንጨብጨብ በሽታው” አልተፈወሰም።
ግንቦት 7 ልክ እንደ የድሮ አለቆቹ ወያኔዎች ታሪክን/ገድልን/ “መከለስ” የጦርንትና የውጊያ
ድሎችን እና እንቅስቃሴዎችን እንደ መጽሐፍ ስርቆት ፤ የሌላውን ገድል እና ታሪክ ወደ እራሱ በማዞር ተክኖበታል።ኦነጎች/የኦነግ
ጀሌዎች በየድረገጾቻቸው ኢትዮጵያዊያን ነን ብለው በኢትዮጵያ ዜግነታቸው ኮርተው በመላው ዓለም አትሌት ውድድር ተሳትፈው ሲያሸንፉ
“ሯጮቹ” የለበሱትን የኢትዮጵያ ሰንደቃላማ ‘በስልታዊ ጥበብ/ኣርት’ በመፋቅ ያልልበሱትን “የኦነግ ባንዴራ” በላያቸው ላይ በማልበስ
ከፍተኛ የሆነ “የፕላግያሪዝም” ወንጀል በስፖርት ዓለም ሲፈጽሙ አይተናል።
በላይ ዘለቀም ኦሮሞ ነው ሲሉ ኦሮሞ ጀግኖች ያጡ ይመስል በአማራው በላይ ዘለቀ ለመመካት “አሮሞ” ነው ሲሉ በአማራ ጸሐፊዎች ተጋልጠዋል።
ግበረኪዳን ደስታ ቴድሮስ ትግሬ ነው፤ ብሎ ታሪክ ለመስረቅ እንደሞከረው ማለት ነው።
ወያኔዎች እና ሕሊናቸው በጎሳ ፖቲካ የሰከሩ የትግራይ ልሂቃንም “ምንሊክና ጣይቱ” የመሩትን
የዓድዋው የጅግንነት ጦርነት “የትግሬዎች ድልና ጀግንነት ነው” ብሎ የመላውን ኢትዮጵያዊያን ዜጎች ድል ወደ ጎሳቸው የቀየሩትን
ሲያስገርመን፤ ዛሬ ደግሞ ግንቦት 7 አሁን እየተደረገ ያለው አማራዎች እየተጋፈጡት ያለውን ተአምራታዊ ገድል የኔ የግንቦት 7 ነው
ብሎ “የጣሪያ ሽፋኑን” ስም (የአማራ
ማንነት ተጋድሎ)
የሚለውን ርዕስ ቀይሮ “የነፃነት ሃይሎች ገደል”
በማለት ፕላጊያሪዝም/ስርቆት መፈጸሙን የጊዚያችን አጅግ አስገራሚ እርቃኑ የወጣ የታሪክ ሽምያ ፈጽሟል። ወያኔ እና ግንቦት 7 የመጀመሪያዎቹ
“የጦርነት ፕላጊያሪስቶች” ናቸው። ይላል ጌታቸው ረዳ ኢትዮጵያን ሰማይ አዘጋጅ:: በመጨረሻ
“We are please to announce Ethiopian Semay vistors are now reaching upto 20,000
daily last month vistors number reached 135,000 Thanks. (Ethiopian seamy) getachre@aol.com
No comments:
Post a Comment