Sunday, May 25, 2014

ተቃዋሚዎች እና ሰንደቃላማችን

Note from the Editor;-
Dear Ladies and Gentlemen
I have a feed back that the font on my blog is too small to read for the eye. Here is the solution, what you can do if it is too small to read. On your keyboard, press 'Ctrl' key and hold it while holding that button press the + sign to magnify it. Or to downsize it- you can press the same key Ctrl and hold it and press the -sign situated before the - sign key. You can do this to all website pages.

ተቃዋሚዎች እና ሰንደቃላማችን

ጌታቸው ረዳ (የ Ethiopian Semay አዘጋጅ)

                                             ግንቦት 13/2006 ዓ.ም (May 21/2014)
አስቀድሜ አንዳስታወቅኩት፤ ከእንግዲህ ወዲህ የኔን ትችት ለማንበብ የምትፈልጉ በተቃዋሚዎች ድረገጽ ሳይሆን በእኔው ድረገጽ Ethiopian Semay ወይንም ፌስ ቡክ ብቻ አንደምታገኙኝ በድጋሚ አሳስባለሁ። የተቃዋሚ ድረገጽ አዘጋጆች ለሕዝቡ ይጠቅማል ለትግሉ አስፈላጊ ትችት ነው ብለው የሚያምኑትን ትችት በፈቃዳቸው ከድረገጼ ወስደው ከለጠፉት በስተቀር ካሁን ወዲህ በነሱ ድረገጽ ላይ አታገኙኝም።

የተቃዋሚው ችግር ብዙ ነው። አንዳንድ መሪዎች በፍርሃት የተሸበቡ ናቸው። አንዳንዶቹ ደግሞ አድርባዮች ናቸው። አንዳንዶቹም ግራ የተጋቡ ናቸው። በጠቅላላ ተቃዋሚው ስምረተ ሕልውናው በምን ላይ የተመረኰዘ አንደሆነ አያውቀውም። በትግራይ ባንቱስታኖቹ ግምባር ቀደም የተካሄደው ጸረ ኢትዮጵያ የሆነ የኢትዮጵያ ስም እና ዝና ማጉደፍ፤ የከተሞችን ስያሜ መለወጥ እንዲሁም ሰንደቃላማዋን በሕዝቧ ፊት ማጣጣል፤ እና ሕዝቡ በራሱ ማንነት ላይ አንዲዘምት በውጭ ጠላቶች ለዘመናት የተሞከረው የጥቃት ዘመቻ፤ በአሳሳቢ መልኩ በተቃዋሚውም ክፍል ሴራው እውን እየሆነ ወረርሽኙ እያጠቃቸው በግዝገዛ ዘመቻው ላይ እየተካፈሉ ናቸው።

አምና ‘ድምጻችን ይሰማ’ የሚለው በጂሃዳዊው ‘በግራኝ አህመድ’ “አሞጋሾች” የተሞላበት እስላማዊ እንቅሰቃሴ የጀመሩት የተለያዩ ቀለም ያሉባቸው መንዲሎች (ጨርቆች) በውስጣዊ እይታው የግራኝ አህምድ የተሰበጣጠሩ የቀለም ጨርቅ አርማዎች የሚያንጸባርቁ፤ ራስን ከብሔራዊ ሰንደቅ የነጠለ ስሜትን ያቀፈ የኢትዮጵያ አገራዊ ሰንደቃላማን የሚያጣጥል እርምጃ ከታየ ጀምሮ እነሱን ተከትሎለው የመጡት “በዩዲጀ” የሚታወቀው በራስ ስም በቅንጅት አባልነቱ መቀሌ ድረስ በመሄድ ‘የትግራይን ሕዝብ’ ቅንጅት ውስጥ ባልተደረገ እና ባልተፈጸመ የዘረኝነት ይቅርታ የጠየቀው በአድርባዩ በኢንጂነር ግዛቸው ሺፈራው የሚመራው፤ እና እንዲሁም ወደ መድረኩ አዲስ ሆኖ በወጣቶች ስብስብ የሚጠራው “ሰማያዊ ፓርቲ” ተብሎ በሚጠራው በይልቃል ጌትነት የሚመራው ተቃዋሚ፤ የወያኔን ስርዓት ለመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ በጠሩበት ጊዜያቶች ሁሉ ለክብራቸው እና ለማንነታቸው የሚያውለበልቡት መለያ የኢትዮጵያ ሰንደቃላማ ሳይሆን፤-የተለያዩ ቀለም የተቀቡ መንዲሎች/መሃረሞች/ጨርቆችን በማውለብለብ ነበር።

Our men with their yellow rag avoiding the Ethiopian flag

ይህ ባሕሪ የተቀዳው ኦራንጅ አብዮት፤ ቀይ አብዮት፤ሰማያዊ አብዮት ወዘተ ወዘተ በመባል የሚጠራው የቀድሞ የሶቭየት ግዛቶች የነበሩት ዛሬ ለቀውስ የተዳረጉ ትንንሽ “አገሮች” በሚያውለበልቧቸው የተለያዩ  ቀለሞች የያዙ ጨርቆች የተቀዳ ባሕሪ ነው። አረቦች እና እስላም አገሮች በዚህ በኩል ሰንደቃላማዎቻቸውን በማንገብ የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎችን አስንቀዋል።
UDJ and its white, red, yellow flags insinuating the Ethiopian flag in Addis Abeba protest

UDJ  building hoisting different colors of flags

Semayawi Party with its unknown circled code on its blue flag




በኢንጂነር ሃይሉ ሻውል ከሚመራው “መ ኢ አ ድ” በስተቀር የተቀሩት ሰላማዊ ሰልፍ ሲወጡ የአገራችን የማንነት ኩራት እና መለያ የሆነቺው ሰንደቃላማችንን በማስወገድ ላይ የተሞረኮዘ ነው። ይህ እርምጃ ከጣሊያን ጀምሮ የተጠነሰሰ ሴራ ዛሬ በዚህ ዘመን በማወቅም ሆነ ባለማወቅ በተቃዋሚውም በኩል እውን እየሆነ ለሴራው ተባባሪዎች ምቹ ሆነዋል። ስለሆነም አዲሱ ትውልድ የሚመካበትን ብሔራዊ ማንነት እያሳጡት ነው። ለጥቃቱ ግዝገዛ ሁሉም መጥረቢያቸውን ይዘው በመገዝገዝ ላይ ይገኛሉ ስንል፤ አዲሱ ትውልድ የኔ ነው የሚለው ብሔራዊ ማንነት በዛ ተከትሎ የሚታገልለት እሴት በዝግታ፤ቀስ በቀስ  እንዳያውቅ እየተደረገ ስለሆነ፤ የቅኝ ግዛት ወረርሺኝ ጥቃቶች ለመከላከል ‘ተረካቢው ትውልድ’ በራሱ ላይ እየተጐነጐነ ያለውን “ሴራ” እንዲያውቀው ያለመሰልቸት ለ22 ዓመታት እየጮህኩኝ ያለሁትበት ምክንያት ይህ ሴራ እውን እንዳይሆን ነው። ጥቂቶች ናቸው በሚል ማጃጃያ ሴራው እንድንንቀው እያደረጉ በዝግታ የተነሳው ሴራ፤ ዛሬ ባለንበት ሂደት የት ላይ እንደደረስን ባፈሩ/ግስገሳው በሩን ለመስበር የት ላይ ቆሞ እንዳለ መመለክቱ የሚከብድ አይመስለኝም።

MEAD protesting with its proud Ethiopian flag protesting in Sawula town few weeks a go

አስገራሚው የግዝገዛው ሴራ እና ተባባሪነት ሰንደቃላማችንን በማስወገድ ብቻ የተወሰነ ሳይሆን ፤ በሴራ ጠንሳሾች የታቀደው ኢሕጋዊ እና ተሪካዊ አልባ በሆነ መልክ የአገራችን፤የከተማችን፤ስሞችን በመቀየር ሁሉ ተባባሪዎች ሆነዋል።

ከወያኔ እና ከኦነግ ሚዲያዎች እየተቀበሉ ተቃዋሚ ነን የሚሉት የፖለቲካ ድርጅቶች እና ውጭ እና ውስጥ አገር ያሉ ሚዲያዎች ሁሉ (ኢሳት የስም ለውጥ አስተጋቢ ዋናው የግዝገዛው ተባባሪ ነው። ዘሃበሻ የተባለው ድረገጽ የኢትዮጵያን ኢሕጋዊ የሆነ የወያኔ የአገራችን መልክአ ምድር የለወጠ ካርታን በመለጠፍ፤ የግዝገዛው ሴራ መሪ ተዋናይ እና አስተዋዋቂ ሆኗል። እና የመሳሰሉ የተቃዋሚ ሚዲያዎች…..) አዲስ አበባን “በፍንፍኔ” ፤ ናዝሬትን “ በአዳማ” ወዘተ ወዘተ… የመሳሰሉ የስም ለውጦች ተባባሪነታቸው እያሳዩ ነው።

ፋሺስቱ እና ቅጥረኛው የወያነ ትግራይ ቡድንም ሆነ ቡቹላው የኦነግ ቡድን የሴራው ጠንሳሾች ናቸውና ከነዚህ ከቅጥረኞች የሚጠበቅ ባሕሪ ነው። ሆኖም የቅጥረኞቹ ሴራ ተባባሪ የሆኑት የተቃዋሚ ድርጅቶች እና ሚዲያዎች ግን የሴራው አዳማቂ ሆነው ሕዝቡ ይህንን ሕገ ወጥ የሆነ  ‘ወረርሺኝ እና ጥቃት” እንዲቀበለው የበኩላቸውን ግዝግዛ እያደረጉ ነው። ይህ የአናርኪዎች እና የአጥቂዎቻችን ስብከት እና ሴራ ተባባሪነታቸው እያሳዩ ሕዝባችን ማንነቱን እና ዳር ድምበሩን አንዲክድ እና አንዲጠራጠር በማድረጉ ዘመቻ ላይ አስተዋጽኦ እያደረጉ ናቸው።

ተቃዋሚው እና የታወቁ የህግ ባለሞያዎች እና የፖለቲካ ተንታኞች የሚባሉት ኢትዮጵያዊያን የአገራችን ችግር የሃይማኖት አክራሪነት አይደለም፤ የፖቲካ ተገንጣዮች ችግር አይደለም፤ ችግሩ “የዲሞክራሲ እጦት ነው” እያሉ ነባራዊውን እውነታ ሕዝቡ እንዳያየው በዲሞክራሲ ሕልም አንዲዘፈቅ በማጃጃል ላይ ናቸው። ቀደም ብየ በቃለ መጠይቄ በግልጽ አንዳስቀመጥኩት http://youtu.be/pXtJPLbbL48 ዲሞክራሲ የአንድ አገር ሁለንተናዊ መፍቻ ሊሆን አይችልም። ዲሞክራሲ ሲሰፍን፤ ኗሪ አይደለም። አገር ግን ኗሪ ነው እና በዲሞክራሲ ተመርኩዞ ሊፈርስና ሊጠብ አይገባም። ተገንጣዩም ቢሆን በዲሞክራሲ የተስፋ አንጀራ ተመርኩዞ ከዋናው አገር ቢነጠል፤ የተነገረው ተስፋ እውን ሊሆን አይችልም። ዲመክራሲ በማንም አድሃሪ ወይንም በታጠቀ ወታደር በማንኛውም ጊዜ የሚነጠቅ ዋስትና የሌለው የአስተዳዳር ሂደት ነው። ዲሞክራሲ ለፍትሕ አስፈላጊ ቢሆንም፤ ዲሞክራሲም የፍትሕ እና የሰውነት መብት (በተለይ ብዙሃን በአናሳው ላይ) ተጻራሪ የሚሆንበት ጊዜ አለ። ገፋ ሲልም፤ ዲሞክራሲ “ናዚዎችን፤ጨቋኞችን” በሕዝብ ጫንቃ ላይ እንዲወጡም የሚያግዝ “ነፃ የሕዝብ ጋሪ ” የሚሆንብት ወቅት እንዳለ እና እንደታየም ልብ ማለት ተገቢ ነው።

 ይህም ማለት ወሮበላዎችን ፤ነብሰገዳዮችን፤አክራሪዎችን እና  ሰላማዊውንም አሳፍሮ ባንድነት አጭቆ የሚጓዝ ሉጓም የሌለው ‘ልቅ ጋሪ’ ነው። ዲሞክራሲ ግምብ ያልተበጀለት፤የሚጠለፍ፤ በሕልም የሚጓዝ ሰው ሰራሽ ሞለጭላጫ ‘አርት’ ነው። ዲሞክራሲ በማንኛውም ጊዜ እና ሰዓት በጉልበተኛ አንደምትጠለፍ ውብ ሴት ማለት ነው። ስለዚህም ሴረኞች እና ተቃዋሚዎች ‘ዲሞክራሲ’ ከአገር አንድነት ጋር እያዘማዱ እሱ እና እሱ ብቻ እንደ ፈውስ አድርገው በማቅረብ ሰፊ የማጃጃል ስራዎች እያካሄዱብን ነው።

ዲሞክራሲ ገደቡ የት ላይ ነው? በዲሞክራሲ መብት አገርን በመስገንጠል? አክራሪዎች በስፋት እንዲራቡ በመርዳት? የት ላይ ነው የዲሞክራሲ በሩ እና ድምበሩ? ተቃወሚውም ሆነ የፖለቲካ ተንታኞች ጊዜያቸውን የሚያተኩረበት “ዲሞክራሲ” አጥር አልባ ነው። ወያኔ ሲወገድ የሚከተለው “የተቃዋሚዎች ዲሞክራሲ” አንድ ሕዝብ እገነጠላለሁ ካለ በጠምንጃ አንይዘውም፤ በሕዝብ ድምፅ መገንጠል ይችላል፡ ብለውናል (ውጭ አገር የሚገኙት የዋሆችን ኩፉኛ በማጃጃል ላይ የሚገኘው የግንቦት 7 መሪ ከሁለት አመታት በፊት በኢሳት የሰጠው ቃለ መጠይቅ ልብ ይለዋል። ውስጥ አገር  ያሉትም አንደዚሁ ከዛው የተለዩ አይደሉም።ለግንጠላ ዓላማ እንዲያመች የተቀናጀው “ራስን በራስ ማስተዳዳር” የሚባለው ‘ዲሞክራሲም’፤ ሞገደኛ እና ጨቋኝ እስከወዲያኛው የሚያስወግድ ተምስሎ የሚሰበከው ይህ ‘ለየዋሆች የተዘጋጀው አደንዛዥ እጽ’ ላይ ላዩን ከመዳሰስ በቀር በጥልቀት ከአገር አፍራሾች ከወያኔ እና ከኦነግ “ራስን በራስ አስተዳዳር’ አጀንዳ በምን መልኩ አንደሚለዩ ያብራሩት ነገር የለም።)፤  የተቃዋሚዎች ዲሞክራሲ አገርን በማፍረስ ላይ የሚያነጣጥር፤ አዲስ አበባን ወደ ፍንፍኔ ፤ ናዝሬትን ወደ ‘አዳማ’፤ ኢትዮጵያን ወደ “ብሔር ብሐየረሰቦች” ስያሜ የሚለውጡ ከሆኑ ከወያኔዎች በምን ራዕይ ነው የሚለዩት? ከእናት ከአባቶቻችን የፍስሐ ስሜት እና አንድነት የሚነጥለን ዲሞክራሲ የሚያመጡልን ከሆኑ ‘ዲሞክራሲ’ ጥንቱም የሕልም እንጀራ የሆነ በኢምፔሪያሊስቶች የተቀየሰ “ሞለጭላጫ አርት” ነውና በር ተበጅቶለት ሕዝቡ እንዲገለገልበት ካልተደረገ ‘ዲሞክራሲ’ ለባሕር ማዶ ባለቤቶቹ ተሰጥቶ፤ ነባሩ ባሕላችን ጉዱፉን ከመልካሙ ለይተን መልካሙን አዳብረን በመጓዝ ለ22 አመት አገር እንደ አገር ማስኖር ያቃተው ‘ሰነፉ ዲሞክራሲ’ ይልቅ አንደ መንግሥት እና እንደ አገር ሦስት ሺሕ አመት ከጠላት ጠብቆ ያስኖረንን ‘አገር በቀል’ ጠንካራ ባህላችንን ለመምረጥ እንገደዳለን።

የአውሮጳ ጸሐፊዎች፤ጣሊያኖች ታሪካችንን አጣመው ጽፈዋል። ሰንደቃላማችን የጉራቸው መጠን ልካቸውን ስላሳየቻቸው፤ በጠላትነት አይተዋታል። አማራው ለአገሪቱ ሕልውና ከፍተኛ መስዋእትነት ከፍሏል። ሰንደቃላማችን እንድትውብለበለብ እየተራበ፤በድርቅ እየተገረፈ፤በውስጥ  እና በውጭ ጠላቶች ተከብቦ ከነነብሱ ወደ ገደል እየተገፈተረ፤ እየተሰደበ እና በመርዝ እየተገደለም ቢሆን ከፍ አድርጎ ይዟታል። ይህ በማድረጉ ጠላቶች ከጣሊያኖች ጀምሮ “አማራን ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያንን እና ሰንደቃላማችንን” አንድ አድርጎ በመሳል፤ በሦስቱም ላይ ጠላት በማደራጀት አንዲዘመትባቸው ተደርጓል። ጠላቶቻችን ይኼው ተባባሪዎች አግኝተው ፍሬው እያየው ነው። ስለሆነም ነው በነዚህ “ተቋማት እና ዜጎች” ላይ ጠላት ዓይኑን በመጣል፤ ከስር እንዲሸረሸሩ ያደረገው።

በጠላት ወገን የተሰነዘረው በነዚህ ተቋማት ላይ ሴራው ከባድ ቢሆንም የተነበየው እና የተፈለገውን የሩዋንዳ እና የማንሮቪያ ዓይነት እልቂት ወዲያውኑ ባለመታየቱ ዛሬም ቢሆን ሴራው እውን እንዲሆን ከመጣር አልቦዘኑም።  ሕዝቡ “የኔ” የሚላቸውን ተቋማት፤አርማዎች እና ስሞችን እንዲጠላቸው፤ቸል አንዲላቸውና አንዲያስወግዳቸው የተለያዩ አዘናጊ ስዕሎች በዜጎች ሕሊና ላይ በመሳል በየሚዲያው እያሰራጩ ነው።

አንድ ምሳሌ ልግለጽ፦

ሲያትል የሚኖረው ወዳጄ ደራሲው አቶ አማረ አፈለ ቢሻው “የሁለት ሺህ ዓመታት ውጣ ውረድ በኢትዮጵያ’ በሚለው መጽሐፉ ላይ እንዲህ ይላል።

“ አንድ አርሶ አደር ሙክት ሊሸጥ ገበያ ሲሄድ ሽፍቶች አገኙት። ነገር ግን ሊቀሙት አልፈለጉም። ምክንያቱም  ደህና ጠንካራ ወንድም ስላለው ከገቡበት ገብቶ እንደሚቀማቸው ያውቃሉ። በሃይል ሳይሆን እውነቱን ‘ውሸት’ ብለው ራሱን እንዲጠራጠር ለማድረግ ተስማሙ።

ሽፍቶቹ ቁጥራቸው ወደ አስር ሲሆን አንድ በአንድ እየሆኑ ሰውየውን እንዲያገኙት ተስማሙ። ቃላቸው አንድ  ዓይነት ነው። በመጀመሪያ ያገኘው ሰው ሰላም እንደምን አደርክ ይለዋል። አርሶ አደሩም “እግዚአብሔር ይመስገን ደህና” ብሎ ሲመልስለት የት እየሄድክ ነው? ይለዋል። አርሶ አደሩም ይህንን ሙክት ልሸጥ ይለዋል። ሽፍታው የምትጐትተተው ‘ውሻ’ እንጂ መቼ ‘ሙክት’ ነው? ብሎት ይሄዳል።

ቆየት ብሎ እንዲሁ አንዱ ይመጣና ይህኑ ይለዋል። ከዚያም ሦስተኛ በዚሁ መልክ ከመለሰለት በሗላ ሁለት ሁነው ሲመጡ አንደኛው ለአንደኛው ውሻው እንዳይበላህ ተጠንቀቅ ብሎ ሲነግረው አርሶ አደር ይሰማል። ከዚህ በሗላ እርሱም እራሱን ተጠራጥሮ ሙክቱን ለቆ ወደ  ቤቱ ሲሄድ ሽፍቶች አርደው በሉበት። ይህም ሰው ያሳደገውን ሙክት ተጠራጠረ፤ ውሻ ነው ሲሉት ተወላቸው። እኛም ዛሬ የገጠመን ችግር የእኛን ታሪክ የእናንት አይደለም እያሉን ነው። ያንተ አይደለም ሲሉት “ለካ አውነት ነው” እያለ በመጠራጠር የሚቀበላቸው እራሱን የሚጠራጠር ብዙ የዋህ ሰው እያፈሩልን ነው።….. ስለዚህም ሴራውን ማክሸፍ ይጠበቅብናል።”

ኢትዮጵያን የሚያጠፏት አንደ ጠላት የመደብናቸው ‘ጣላቶቻችን’ ሳይሆኑ በጥቃቱ ግዝገዛ ላይ የጠላቶች ተባባሪዎች ናቸው ኢትዮጵያን የሚያጠፏት። ኢትዮጵያ የሚባል ስም ሲነሳ የሚበረግጉ “ተሸናፊዎች” የማንነቷን መገለጫ የሆነው ሰንደቃላማዋን ከዓለም እይታ እና ከዜጎቿ ዓይን እንዲሰወር፤ የክፍለሃገሮችን ሰፋፊ ለም መሬቶችን ወደ ትግራይ እንዲካተቱ፤ የከተሞቻችን እና ርዕሰከተማዋን ስም ሕግ ወጥ በሆነ መንገድ አንዲለወጥ፤ ሲደረግ፤ አንዳንድ የዜና አውታሮች፤ጋዜጠኞች እና የፖለቲካ ተቃዋሚዎች ተባባሪነታቸው በጉልህ እየነገሩን ነው።እነኚህ ክፍሎች ከሴረኞቹ ጥቃት በግዝገዛው ሴራ ለይ ከተባበሩ፤ የእናት ኢትዮጵያን መቀነት ከሚቀዳድዱ ወና ጠላቶች ለይተን ስለማናያቸው ከታቀፉበት ከሞቃቸው ደረቷ ላይ እባብ ሆነው ከመንደፍ አንዲታቀቡ ዛሬም መልእክቴ እንዲደርሳቸው ጥሪዬን አስተላልፋለሁ።

የሚቀጥለው ትችቴ የሚያተኩረው ሆን ተብሎ ወንጀል ፈጻሚዎች በዩቱብ የተለጠፉ ሕዝብን የፈጁባቸው ወይንም የተሳደቡባቸው ማህደሮች ወደ ዩ ቱብ ባለቤቶች አቤት በማለት እንዲነሱ እየተደረገ ስለሆነ፤ ይህ ወንጀላቸው እንዳይታወቅ የሚያደርጉት ሴራ ለዩቱብ ባለቤቶች አምቢታ ማስሰማት እንዲለምደን የሚያሳስብ ትችት አቀርባለሁ። ይህንንም ሆን ተብሎ ፈሪዎቹ አቤት ሲሉ የዩቱብ ባለቤቶች ““This video has been removed as a violation  of You Tubes policy on shocking and disgusting content.” በሚል  ያስነሱታል። ዩ ቱብ ይህ ፍርደገምድል በኢትዮጵያ ላይ ብቻ እንጂ ‘በአሜሪካኖች፤ በኢራቅ፤ ባፍጋኒስታን፤ በታሊባን፤ በሊቢያ፤ባሰውዲ….ወዘተ…ወዘተ… አገሮች የሚለጠፉ ዘግናኝ ወንጀሎች ግን አሁንም ተለጥፈው ለዓለም ይታያሉ። ኢትዮጵያዊያኖች ለምን ልዩ ፍርድ ተሰጠ ተብሎ የዩቱብ አስተዳዳሪዎች መጠየቅ አለብን። ወንጀለኞቹ ምንም አንኳ ስዕለ ድምፁ ከዩ ቱብ እንዲነሳ ቢያደርጉም “ድምፁ” ስለቀዳነው ወንጀላቸውን መደበቅ አይቻላቸውም። ሆኖም የወንጀለኞቹ ማህደር በዩቱብ አንዲታይ የለጠፉት ተቃዋሚዎች ከሆኑ ለምን አንዲነሳ እንደተደረገ ፈቃደኞች እና ተባባሪዎች እንደሆኑ ለኔ ግራ የገባ ነገር ነው። በዚህ ላይ በሚቀጥለው እንነጋገራለን። አመሰግናለሁ ጌታቸው ረዳ ካሊፎርኒያ አሜሪካ የEthiopian Semay ድረገጽ አዘጋጅ። getachre@aol.com


2 comments:

zienamarqos said...

ሊቀ፡ሊቃውንት፡ጌታቸው፡ርዳ፣እግዚአብሔር፡ዕድሜና፡ፀጋውን፡ያብዛልህ።ከ፡ሥነ፡ጽሁፎቻችን፡እስተ፡ሰንደቅ፡ዓላማችን፡አያሌ፡ኢትዮጵያዊ፡ንብረቶቻችንን፡እያጣን፡ስለ፡ሆነ፡ለምታደርገው፡ሁልሉ፡ታጋድሎ፡የኢትዮጵያ፡አምላክ፡ይጠብብቅህ።በበኩሌ፣ምን፡ግዜም፡የማደንቅህ፡የኢትዮጵያ፡ልጅ፡በመሆንህ፤የምኮራብብህ፡ወንድሜ፡ነህ።እግዚአብሔር፡ብርታቱን፡ይስጥህ።ኢትዮጵያና፡ሕዝቧን፡እግዚአብሔር፡አጠንክሮ፡ይባርክ።

Chisegnaw said...

This so called opposition parties, with the exception of AEUP, are TPLF created. Their mission is to keep TPLF in power for as long as it is able to finish off Ethiopia, or to take over and accomplish their western masters' mission of dismembering Ethiopia. This so called Semayawi party is definitely TPLF's creation. So is the so called UDJ. UDJ is filled with traitors that infiltrated and dismantled CUD. They are undercover TPLF agents. They rather collaborate with ethnic based parties than milti-ethnic, nationalist parties like AEUP. But they badly want to take over AEUP in the name of unity and hand it over to TPLF, as they tried many times before. Listen to their demands when they stage protests in the country. They call for the release of individuals like Eskindir Nega and Andwalem Arage, than call for the regime to STEP DOWN ! Their demands are so vague to threaten the stability of TPLF in power because they were created by TPLF, and work for TPLF. Those abroad, like the so called Ginbot 7 anarchists and their anarchist leader Dr. Birhanu Nega (I doubt the credibility of his Phd, given the guy's stupidity and lack of knowledge in many ways)are known obstructionists of the people's movement to savor their country. Dr. Birhanu is assisted by the Gondar bandits, such as Tamagn Beyene, Abebe Belew, and Abebe Gellaw, as well as the want to be White man Alemayehu Gebremariam, who confuse and mislead the already confused and grossly political illiterate diaspora into believing something other than the reality, as the author stated above. The solution is for those who are aware of the reality of Ethiopian politics, and are nationalists, to stand together in combating the numerous groups that are threatening the existence of our beloved Ethiopia. These anti-Ethiopian elements include, but are not limited to, TPLF/EPRDF, EPLF, OLF, Gimbot 7, UDJ, Semaiawi Party, ONLF, etc. God is with Ethiopia. As long as those of us who love Ethiopia and want to preserve it from her planned distraction from the bandits I mentioned above, God will use us to defeat these enemies once and for all. Long live Ethiopia !