Sunday, September 11, 2011

ዘመን ይለወጣል ዘረኞች ትተውት የሚሄዱ አሻራ ግን አይለወጥም!

መልካም አዲስ ዓመት!!!!

እንቅልፍና ምቾት የታደላችሁ ያለፈውን ዓመት በደስታም በምቾትም ያልታደሉትም በሰቀቀን እና በእስራት በግርፋት እና በስደት በሐሳብና በብስጭት ያሳለፋችሁ ወገኖች ሁሉ ሁላችሀም አንኳን ላዲሱ ዓመት አደረሳችሁ። ሃገሬ በታሪክ ማሕደር ልታኖረው የሚረዳት ማበርከት የምችለው ይኼው አዲስ መጽሃፍ አበርክቻለሁ። ከዳንኪራ ምሽት፤ ከቢራና ከጥብስ ቀንሶ መጽሐፍ ገዝቶ የሃገሩን የታሪክ መስተዋት ለማየት ማንበብ የሚፈልግ ሕሊና ካለ ይኼው ሌላው ጥሪ። የወያኔ ገባና ማህደር፡ ደራሲ ጌታቸው ረዳ getachre@aol.com(408) 561 4636 www.ethiopiansemay.blogspot.com
Getachew Reda
P. O.Box 2219
San Jsoe, CA 95109


ዘመን ይለወጣል ዘረኞች ትተውት የሚሄዱ አሻራ ግን አይለወጥም!



  ዘመን ይለወጣል ዘረኞች ትተውት የሚሄዱ አሻራ ግን አይለወጥም!
ኢትዮጵያዊነትን ጥላሸት ቀብተው የዘረኝነት አሻራ ለትውልድ ከተውት ዘመኑ ያፈራቸው እውቅ ዘረኞች የተውዋቸወ ጥቅሶችና መልዕክታቸው ዘመን የማይሽራቸው እድፎች ናቸው።
አስመራ ድረስ በመሄድ የሻዕቢያ በር እያንኳኳ የሻዕቢያ ወረበሎችን ደጅ የሚጠናው  በኦሮሞነቱ ተነሳስቶ አማራውን እንደጠላት የተመለከተ “አንዳርጋቸው ጽጌ” የተባለው የግንቦት 7 ዋና -ጸሓፊ ከጻፋው ዘረኛ መጽሐፍ የተወሰዱ የሕሊናው አድፎቹ እዚህ ሳህን ውስጥ አኑረን አረፋውን ስንመለከት፤ ይህ ዘረኛ ግለሰብ ለታሪክ የተወው አሻራ ሳያሳፍረውና ለኢትዮጵያ ሕዝብ ይቅርታ ሳይጠይቅ ዛሬም ሻዕቢያን  በመሞዳመድ በዓለም ዙርያ በሚገኙ የግንቦት 7 ተከታዮቹ እያሞኘ የአንድነት ሃይሎችን እየዘለፈ ስናዳምጥ ይህ ዘረኛ ግለስብ ቁም ነገር እናገኛለን ብለው ጊዜና ገንዘባቸው የሚለግሱለት ሰዎች ማግኘቱ የሚያመለክተው ፖለቲካን በሚመለከት ኢትዮጵያውያን እጅግ ወደ ሗላ የቀሩ ማሕበረሰቦች አንደሆንን አመላካች ነው። በውጭ አገር እና በውስ  አገር የሚገኙ ኢት ጵያውያን ዘረኞች ሲሰብኳቸው ለምን ዘረኞችን እንደሚያከብሩ መጠናት ያለበት አዲስ ክስተት ይመስለኛል።
ለማንኛውም ዘረኞች የተውልንን አሻራ አጠር ባለ መልኩ ክፍል 1 እነሆ።
የአማራው ሕዝብ ከየት ወዴት ?
አንዳርጋቸው ጽጌ
አዲስ አበባ
1985

ከመጸሀፉ የተቀነጨበ

*
በታሪካችን ውስጥ ሁሉንም ብሄሮች በጋራ ሰሜት የሚያስተባብሩ ታሪካዊ ክስተቶች አልነበሩንም ማለት ባይቻልም : ለምሳሌ የአድዋ ጦርነትና የአምስት ዓመት ጸረ ጣሊያን ተጋድሎ በዋነኛነት የመቶ ዓመት ታሪካችንን የሚገልጸው የተለያዩ ብሄር ብሄረሰቦችና ሕዝቦች በእሳትና በብረት ገብረው : በእሳትና በብረት ሲጠበሱ በመኖራቸው የሚሰማቸው ቁጭት ምሬት ሐዘንና ጸጸት ነው :: (ገጽ 11-12)

*
አንዳንዶቻቸን ብሄራችሁ ተብለን ስንጠየቅ ያለምንም ማመንታት አማራ ኦሮሞ አፋር ትግሬ ወዘተ ብለን ያለምንም ጭንቀት እንመልሳለን :: አንዳንዶቻቸን ተመሳሳይ ጥያቄ ሲቀርብልን ለምን ብሄር የሚባል ነገር ይነሳል ? ለምን ይህ ጥያቄ ያስፈልጋል ? ብለን የምንቆጣ አለን :: ለምን እንዲህ አይነት ጥያቄ ተጠይቅን በማለት ተናደን የሄድንበትን ጉዳይ ሳናሳካ የምንመለስም አለን :: ብሄር ሲባል ኢትዮጵያዊ ብለን የምንመልስም ሞልተናል :: (ገጽ 13)

*
ግር የሚያሰኘው ብሄሩን ሲጠየቅ ኢትዮጵያዊ የሚለው ወይም ለምን ተጠየኩኝ ብሎ የሚቆጣው ነው :: (ገጽ 14)

* ይህ መጋባት መዋለድ አልፎ አልፎ በአርሶደሮች መሀከል ያለ ቢሆንም ከመጀመሪያው ጀምሮ በነገስታቱና በመሳፍንቱ ኋላም በአንድ ማዕከል በመማርና በመስራት በተገናኙ የተለያዩ ብሄሮች ምሁራን መሀከል ሰፍቶና ጎልቶ ይታያል :: (ገጽ 15 )

*
የተጋቡ የተዋለዱ ሰዎች እንዳሉ በናስቀምጥም በኢትዮጵያ የሚታየው ተጨባጭ ሁኔታ እነዚህ ተዋልደናል ተጋብተናል የሚሉት ግለሰቦች እንድሚሉት ጋብቻና መዋለድ መላ አገሪቱን የቆላለፈ ጉዳይ አይደለም :: በአዲስ አበባና በአንዳንድ የደቡብ የአገሪቱ ከተሞች በመሳፍንቱና በባላባቱ በተለያዩ ብሔሮች መሀከል የሚታየውን ጋብቻ ብቻ ወስደን የሀገሪቱ ዋነኛ መግለጫ ማድረግ ሰህተት ነው :: (ገጽ 16 )

*
አንዱ የበላይ ሌላው ደግሞ የበታች ሆነው ሲታዩ ከመጡ ብሔሮች መወለዱ አማራነቱን መምረጥ ማለት በሌላ ጎኑ ባለው ብሔር ሲደርስበት ለነበረው የበታችነት ተጽዕኖ መገበር ሆኖ ይታየዋል :: እንዲህ ዓይነት ጭንቀት ውስጥ የሚገባ ግለሰብ ከጭንቀቱ መውጫ አድርጎ የሚከተለው መንገድ ሁሉንም ትቶ ኢትዮጵያዊ ነኝ ወይንም አልፎ ተርፎ አይደለሁም ወደሚለው የህልውና ክህደት መሄድ ነው :: (ገጽ 18 )

*
እኔ አማራ ነኝ ሚስቴ ኦሮሞ (ትግሬ ) ናት :: ልጆች አሉን : ምን እንሁን የሚል ጥያቄ ያቀረቡም አሉ :: (ገጽ 26 )

*
በዚሁ አኳያ የብሔር ጥያቄ ሲነሳ ከላይ ባስቀመጥናቸው ምክንያቶች ጭንቀት ወስጥ እየገቡ ለምን ጥያቄው ይነሳብናል : ወይም የሌለ ብሄር ብሔረሰብ የሚል ጣጣ አምጥታችሁ በማለት በምኞት ሊቀየር ከማይችል እውነታ ጋር የሚጋጩ ወገኖቻችን ጉዳዩ የደም የአጥንት አለመሆኑን ሊያውቁት ይገባል :: የየግል ወይንም የቤተሰብ ወሳኔያቸውን ያለምንም መሸማቀቅ ሊወስኑ እንደሚችሉ መረዳት አለባቸው :: በእንዲህ ዓይነቱ ነጻ ወሳኔ ለሚደረግበት የአማራነት ምርጫ የአማራው ህዝብ ታላቅ ከበሬታን እንድሚሰጠው አንጠራጠርም :: (ገጽ 31)
ከአንዳርጋቸው ጽጌ
የአማራው ሕዝብ ከየት ወዴት ?
ከሚለው መጽሀፍ የተወሰደ
ይቀጥላል.././…     
www.ethiopiansemay.blogspot.com              getachre@aol.com


6 comments:

Anonymous said...

እርስዎንም፡እንኳን፡በሰላም፡አስተ፡ቤት፡ሰወችዎ፡አደረሰዎ።"የወያኔ፡ ገበና፡ማኅደር"፡መጽሐፍዎን፡ዋጋ፡አልነገሩንምና፡ያስታውቁን።እንደ፡ እርስዎ፡ያሉ፡ብርቱ፡ጀግኖችን፡ኢትዮጵያ፡ደጋግማ፡ትውለድ።
በተረፈ፡ኢትዮጵያና፡ሕዝቧን፡አጠንክሮ፡እግዚአብሔር፡ይባርክ። ሃሌ፡ሉያ።አሜን።

Anonymous said...

ከደራሲው
በጣም አመሰግናለሁ ውድ ወገኔ ኢትዮጵያዊ። ስለ መጽሐፉ ዋጋ በቅርቡ ይፋ ይሆናል ፤የኔን ታጋይነት እና ኢትዮጵያዊነት በሚያከብሩ ውድ ኢትዮጵያውያን የህዋ ሰሌዳ አዘጋጆች ማስታወቂያዎች ይለጠፋሉ። በቅናት የበገኑ ተቃዋሚ ነን የሚሉ የትግራይ ተወላጅ ደካማና ጠባብ ሕሊና ያላቸው ግለሰቦችና አንዳንድ ተቃዋሚ ነን የሚሉ -ጸረ አንድነት የተቃዋሚ ፓርቲ አባላትና በቀይ ሽብር እጃቸው የተጨማለቁ አንዳንድ የፓልቶክ አዘጋጆችና የዋህ ተከታዮቻቸው ባለፈው መጽሐፌላይ የቻሉትን ውስጣዊ ዘመቻ በማካሄድ እንዳይዳረስ አድረገው አልተሳካለቸውም። እናንተ ብርቅየ ያንድነት ሃይሎች አልሞታችሁም እና መጽሐፉ በናንተ ጥረት ለትውልድ ይሸጋገራል። በመጽሐፉ ውስጥ የተካተቱ ቁም ነገሮች በዚህ ዘመን እየኖርን ላለነው ዜጎች አዲስ ላይሆንብን ኢችል ይሆናል፤፡ አስፈላጊነቱ መ-ጽሐፉን ገዝታችሁ በዚህ ዘመን ላልኖሩ መጪ ትውልዶች እንዲያውቁት ማድረግን ታሪኩን ማስተማር የያንዳንዳችሁ ሃላፊነት ነው። ወያኔዎች በመቶዎቹ መጽሐፍት እያሳተሙ በዚህ ዘመን ላልኖረው መጪው ትውልድ የውሸት ማህደር ሲያስነብቡት ያንን ውሸት የማጋለጥ ሃላፊነት በኛ ላይ የወደቀው ዜጎች ደግሞ እውነታውን እያሳተምን ለመጪው ትውልድ እያወዳደረ የራሱን ዳጅነት እንዲወስድማድረግ ይጠበቅብናል። አመሰግናለሁለሁ። ጌታቸው ረዳ

Anonymous said...

እርስዎም፡በ"ይድረስ፡ለጎጠኛው፡መምህር"፡መጽሐፍዎ፡ ገልጸውታል፣አሁን፡በሥልጣን፡ላይ፡ያሉት፡አጋንንቶች፡ ምንነታቸውን፡ደብቀው፡ዛሬ፡ፈነዳባቸው።በአባቶቻቸውና፡ አያቶቻቸው፡ከሃዲነት፡ፅንሰ፡ሐሣብ፡ታንፀውና፡ተኮትኩተው፡ እንድደጉ፡አላጠነውም።አንድ፡የኢትዮጵያ፡ልጆች፡ነን፡ በማለት፡ተታለናል።ኢትዮጵያ፡ለወደፊት፡ይጦሩኛል፡ብላ፡ አርቃ፡በማሰብ፡ያለ፡አቅሟ፡በነፃ፡አስተምራ፡ያጐረሰችበትን፡ እጇን፣ያጠባችበትን፡ጡቷን፡ነከሷት።እኛ፡ሰዎች፡ስለ፡ሆንን፡ እንጂ፣ለሁሉም፡እግዚአብሔር፡ያቀደውን፡ዕጣ፡ማለፍ፡ግድ፡ ይሏል።ይህ፡የመጀመሪያዋ፡አይደለና፡ያልፋል።"እኪያልፍ፡ ያለፋል"።ነውና፡በአድራጐትዎ፡ይቀጥሉ።ቀኝ፡ጌታ፡ዮፍታሔ፡ ንጉሤ፡ጨርሰውታል።"ኢትዮጵያ፡ሀገሬ፡ሞኝ፡ነሽ፡ተላላ፣ የሞተልሽ፡ቀርቶ፡የገደለሽ፡በላ"።ብለዋል።በመጨረሻ፡ እርስዎ፡ጠንቀቅ፡ይበሉ።ለክፍታም፡ወያነ፡ውሾች፡መርዛቸው፡ ከባድ፡ነው።

ዜናማርቆስ፤ said...

አክሱም፡ጽዮን፡ማርያም፡የተቀደስሽ፡ቦታ፣
እንደዚህ፡ሲያረክሱሽ፡በቀንና፡ማታ፤
ከጳጳስ፡ከጀሌ፡ዐድዋ፡ተወልደው፣
በውሸት፡ታንፀው፡ሆዳቸውን፡ነፍተው፣
ምድር፡ሰወችሽን፡በደም፡አጨማልቀው፣
ንሥሐም፡አያውቁ፡ጣዖት፡አሠርተው፣
ሲሰግዱም፡እያየሽ፡በእብሪት፡ተመክተው።
ካብራክሽ፡የወጣ፡እያለ፡ጌታቸው፣
አርኣያውን፡ዓይተው፡መሄድ፡አቅቷቸው፣
እያጉረጠረጡ፡በክፋት፡ዓይናቸው፣
እያዩት፡እያየሽ፡ዝም፡ትያለሽ፡ምነው።
እባክሽ፡ፍጠኝ፡ፍትሕ፡አሳያቸው፣
ሕዝብ፡ተሳቋልና፡ቶሎ፡ገስጫቸው።

እግዚአብሔር፡ሰላምን፡ያውርድልን።
ከዜናማርቆስ፣ካናዳ።

Anonymous said...

ወያኔዎች፡እናንተ፡የምታደርጉትን፡ጨናዊ፡ሕንፍሽፍሽ፡ሁሉ፡ ያሳበዳችሁ፡በመሆኑ፡ሳይታዎቃችሁ፡ሰውን፡ትሳደባላችሁ። ፅሉል።ወፈፌ፡ቆዳ፡ራስ፡አንተ፡ነህ።ርእሱ፡ስሒቱ።እንደ፡ ጌታቸው፡ያለ፡በግራይ፡አልተፈጠረም።አንተን፡መሰሎቹ፡ ሁሉ፡ውራጆች፡ናችሁ።

Anonymous said...

ጌታቸውን፡መስደብ፡ማለት፡በኢትዮጵያ፡አንድነት፡ለምትቀልዱ፡ ዲቃላዎች፡እጅ፡መስጠት፡ስለሚሆን፡እኛ፡እንመልስላችኋለን። ጌታቸው፡ምን፡አደረገህ?።ለምን፡የምትሠሩትን፡እኩይ፡አድራጐት፡ አትገነዘቡትም።እንደዚህ፡ቀልዳችሁ፡ዕድሜ፡ልካችሁን፡የምትኖሩ፡ አይምሰላችሁ።የባንዳ፡አባቶቻችሁ፡ዝላገብ፡ሕማም፡ሳይገድላችሁ፡
አይቀርምና፡እንገላገላለን።ንስሙ፡ጥርሕ፡ሰዎች፡ናችሁ፡እንጂ፡
የተለከፋችሁ፡ዐውሬዎች፡ናችሁ።