Friday, August 26, 2011

አፋቸው በጣም የሚከፍቱ የሻዕቢያ ኦይሰተሮች


አፋቸው በጣም የሚከፍቱ የሻዕቢያ ኦይሰተሮች

ከጌታቸው ረዳ


በዚህ ልጀምር መሰለኝ። “Oysters የተባለ እንሰሳት በጠፌ ጨረቃ ጊዜ ሙሉ በሙሉ ይከታል ይባላል። Crab የተባለው እንሰሳ (አብዛኛው ዓለም ይበላዋል) ኦይስተሩን ሲያይ ትንሽ ድንጋይ  ወይም የባሕር አረም (አራሙቻ) ይወረውርበታል። ኦይሰተሩ እንደገና ራሱን መዝጋት ያቅተዋል። የክራቡ ምግብም ይሆናል። አፉን በጣም በመክፈት ራሱ ላይ ከፍተኛ ችግር ሚያደርስ ሰውም ዕጣ ይኸው ነው።>> {ጸጋዬ ገብረመድህን አርአያ- ጦቢያ መጽሄት-ቅጽ8-ቁጥ-12/1993-“ከኢትዮጵያና ከኢትዮጵያውያን ጋር የተፈራረሙት ውል (ኮንትራት) የላቸውም”}
አፋቸው ከመጠን በላይ የሚከፍቱ የሰው ኦይሰተሮችም አሉ። በዚህ ሁለት ወር ውስጥ ኢትዮጵያውያን ነን የሚሉ የሻዕቢያ ኦይሰተሮች አስቀያሚ አፋቸውን ከፍተው አሳይተውናል። እነዚህ ኦኢሰተሮች ኦነግን በመደገፍ የአገር ክብርና የአርበኞች ተጋድሎ የሚያንኳስስ ንግግር በማድረግ በየአገሩ እየዞሩ ምን አይነት ዘለፋ እና የጸረ ኢትዮጵያ ቡድኖች የፕሮፓጋንዳዊ ውክልና እያካሂዱ እንደነበር (አሁንም እንዳሉ) ተደጋግሞ የተገለጸ እና እያንዳንዱ ንግግራቸው በዝርዝር እየጠቀስን አጋልጠናቸዋል። ከላይ የጠቀስኳቸው አንጋፋ ጋዜጠኛ እንደሚሉት “በሥልጣን ወንበር ላይ የተቀመጡ ወይም ሕዝብን እንወክላለን የሚሉ ለወደፊቱም  የሚቀመጡ ሰዎች ግሞ የቃላት ሃብታቸው ሲያባክኑ እንዳይውሉ ሃገርን፤ሕዝብንና ታሪክን ከሚዘልፉ ንግግሮች ይቆጠቡ፤የታሪክ ርፍን ይፍሩ” ተብሏል፤ ሰሚ ግን የለም። ግንቦት 7 እያለ ራሱን የሚጠራ የሻዕቢያ ኦይስተር እና “እኔ አርጅቻለሁ፤የዘመኑም ፖለቲካ አላውቅበትም” እያለ ከፖለቲካ ተወካዮቹ በላይ ውሸት የተሞላበት የፖለቲካ ውክልና ንግግር የሚያሰራጨው ዶ/ር ጌታቸው በጋሻው እና መሰሎቹ ግን የሚሰማ ጀሮ የላቸውም። በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የሻዕቢያ ራዕይ እያናፈሱ ከመጠን በላይ አፋቸው የሚከፍቱ  እነኚህ ኦይሰተሮች በሚወረውሩት መርዘኛ ጸረ አገር እና ጸረ አርበኞች ፕሮፓጋንዳቸው አድማጭ አጸፋ ሲመልላቸው እና በጣም የበገነውም ሲሰድባቸው “ተሰደብን” ብለው ተሰምተው በማይታወቁ ሰዎች ስም በእልፍ አስከልካዮቻቸው በኩል ኡኡታውን ያቀልጡታል። አለማፈራቸው ደግሞ አእላፍ ወንጀል የፈጸመውን ወያኔን ሳይከሱ ግለሰቦች ሰደቡን ምንትስ እያሉ ያሜሪካ ሕግ እንዲህ ነው፤ ብልቱ፤ ማንቁርቱ፤መውጪያው መግቢያው አንቀጹ ቁጥሩ፤ገጹ… ወዘተ…ወዘተ… እናውቀዋለን ወደ ማለት የህጻን ጨዋታ ውስጥ ሲገቡ ወያኔ ምን ይለን ይሆን ብለው እንኳ ትንሽ አላፈሩም።
ለመሆኑ እነዚህ ተሰደቡ እየተባሉ በእልፍ አስከልካዮቻቸው የሚጮህላቸው ሰዎች እነማን ናቸው? የማይጨው አርበኞችን በሃፍረተኛነት ሲዘልፉ፤ አገርን ሲያዋርዱ፤ የተለየ ሃሳብ ያላውን በንፍጥ የተሞላ ጭንቅላት እያሉ ባደባባይ የሚንዘላዘሉት (የትግርኛ ቃላት ነው) እንደ ኦይስተር ራሳቸው ከመጠን በላይ በመክፈት አፋቸው እንዲዘጉ አራሙቻ በሚወረውሩባቸው ላይ ኡ ኡታ ማቅለጥ አስተዋይነት የጎደለው ነው።

ከመጠን በላይ የተከፈተን አፍቸውን አደብ ግዛ ሳይሉት በየፓልቶኩ እና በየኢንተርኔቱ ኡኡታ ማቅለጥ ኦይስተሩ አፉ እንደከፈተ ለረዢም ጊዜ የሰው መሳቂያ እንዲሆን ተጨማሪ እይታን መጋበዝ መሆኑን አልገባቸውም።
 በዚህ ጥቂት ቀናት ያስደመመኝ የሰማሁት መረጃ ደግሞ “አንድ ወዳጄ እንዳጫወተኝ ልክ ከሆነ” ዶ\ር ጌታቸው በጋሻው የተባለው አዲሱ የኦኖጎች አፈቀላጤ “ጌታቸው ረዳ” ሚባለው ሳንሖዜ ያለው ማን ነው? ሲል ጠይቆ ነበር አሉኝ።
 ለመሆኑ ጌታቸው በጋሻው ጌታቸው ረዳ ማን መሆኑ እስከዛሬ ድረስ አያውቀውም ማለት ነው? ዕድሜየ በሙሉ ለሕዝብ ስል ስታገል ማንነቴን ሳልደብቅ ነው የታገልኩት፤ ፎቶግራፎቼ ሁሉ በግልጽ የሚታዩ ናቸው። ፍርሃት እንደሌለኝ ወያኔዎችም ኦነጎችም ያውቃሉ። በጉልበት እንደማላሸንፋቸው ቢያውቁም የእውነት ብእር ይዤ እንደምታገላቸው ስለሚያውቁ ዛሬ ሰልችቷቸው የኔነት መረጃ ማወቁን ለጌታቸው በጋሻው ትተውለታል።
 የሻዕቢያ ኦይስተሮች ግን በፖለቲካው ሲወድቁ ወያኔን በሕግም በጉልበትም መቋቋም ሲፈሩ ግለሰቦች እየለዩ አፍ ለማስያዝ ሎውየር! ሎውየር! “ተሰድብን ‘ተሰደብን!’ እያሉ ያስፈራራሉ። እነኚህ የሻዕቢያ ኦይስተሮች ፈሪ ሰው ቢያገኙ “ፍርድ ቤት ፍርድ ቤት’ እያሉ አፉን አንዲዘጋ ያደርጉ ነበር (መድረኩ ለሻዕቢያ እና ለኦነጐች ሰጥተው በሕዝቡ ዓይን ላይ እንደ ዶልፊን ዓሳ ዓይናችን ላይ ውሃ እንዲረጩብን ማለት ነው)። ይሄ ስልት ደግሞ በነኚህ የሻዕቢያ ኦይስተሮች አልተጀመረም፤ ወየነ ትግራይ ሞክሮታል (ሁላችሁም የምታውቁት ዜና ነው) የማያዋጣው መሆኑን ሆኖ ሲያየው ተወው። ጌታቸው በጋሻው ‘ወያነ ትግራይ’ ሊሆንብኝ ሲሞክር እንዲህ ያሉትን ሞኞች በተፈጥሮዬ ስቄ ባልፋቸውም አንዳንዴ ተምረው እንዳልተማሩ የሚዘቅጡትን ሲያጋጥሙኝ የዛች አገር ዕጣ ፈንታ የሕዝቡ መከራ እጅግ አድርጎ ያሳዝነኛል። ለመሆኑ የኔን ማንነት ፍለጋ የኳተነበት ምክንያት በኦነግ ኤየር ላይን ወይስ በግንቦት 7 ኤየር ፎርስ  አስመራ ወስዶ ለ “ወዲ አፎም” ሊያስረክበኝ ነበር ፍለጋው? ወይ ትጉዱ!
 ለምሳሌ ከትላንት በስቲያ ሰሙን ሰምተነው በማናውቀው ‘በቀለ ንጋቱ’ በሚል ጸሐፊ በሦስት ድረገጾች ተለጥፎ የነበረው “ዛቻና ስድብ የኢሕአፓ ፖለቲካ”

(ሁለት ድረገ ጾች ወዲያውኑ አንስተውታል) ኢትዮሚዲያው ብቻ ነው ኢሕአፓን የሚዘልፍ ጽሐፍ መሆነን ሲያይ የወደደለት እና አሁን ተለጥፎ ያለው ምናልባትም ንአምን ዘለቀ  ከአብርሃ በላይ ጋር የድረገጸ አንደኛው አርታኢ ስለሆነ ይመስለኛል (ብቻ ለነገሩ ዌብ ሳይቱን ብትመለከቱት እኮ አሲምባ ዌብሳይትን “ብሎግ” ብሎታል ዛሬ (ዛሬም እልኩ አለ)፤  ድሮ ከመተቸቴ በፊት “አሲምባ ውብሳይትን “በፖለቲካ ፓርቲ” ከሚለው መስኮት/ሊንክ አስገብቶት ነበር። )

ስልክ ተደውሎ በዶክተሩ ስልክ የመልእክት መቀበያ ሳጥን ዛቻና ስድብ ተልኮበታል ሲል “ዓለም” ቀውጢ እንደሆነች ሁሉ “ንገሡ’ ተሰድበዋል” አለን።በስልክ መሰደብ በጌታቸው በጋሻው አልተጀመረም። ዛሬ ዛሬ ሰልችቷቸው ተውኝ እንጂ በስልክ እየተደወለ ሳዳምጠው የነበረው ዛቻው በገፍ ነበር። ሲደርሰኝ የነበሩ ጽሁፎች ስልኮች እና የዛቻው ብዛት እና ቃናው በትግል ያላደገ ሰው ቢያደምጠውና ቢያነበው ወደ ጫጩትንት ይለውጠዋል። ለምሳሌ ከጥቂት አመታት በፊት ትዝ ይላችሗል ካናዳ ሃዋርያ ጋዜጣ ላይ የታተመ ከኦክላንድ ካሊፎርኒያ ከወያኔ የተላከልኝ ማስፈራሪያ (ኦክላንድ ውስጥ ስዩም መስፍናቸውን ስለተቃወምኩ በሰለማዊ ሰልፍ ) ስታነቡት በጣም ይገርማል። የላኪው አድራሻ የት እና ማን እንደሆነ አውቀነው ነበር፤ ግን እያንዳንዱ ስድብ እየተከተልኩ ሎውየር፤ሎውየር ብል ኖሮ የትግል ትርጉም ባልገባኝ ነበር። መጀመሪያ ትግል አለመግባት፤ ትግል ውስጥ ከገባህ ከምትናገራቸው ፍሬ ነገሮች የሚያበሳጫቸው ሰዎች ስለሚኖሩሪአክሽንእንደሚኖር አስቀድመህ መረዳት አለብህ (it is part of the package)። ግፋ ቢል ባለ ኢንተርኔት ባለቤቶችን የተለጠፈ ስድብ ካለ እንዲሰርዙት አቤት ማለት ተገቢ ነው፤ ካልሆነ ግን ጌታቸው በጋሻውአንዲት የስድብ ስልክከቺካጎ ኗሪ ለመጀመሪያ ጊዜ ተደወለብኝ ብሎ ስሙን ሰምተነው በማናውቀው ሰው ጌታቸው በጋሻውን ተንተርሶ ኢሕአፓን መዝለፍ  አስፈላጊ አይደለም።የመልእክቱ ፍሬ ነገር መልእክቱ ተሳደ ለታበለው የማይታወቅ ግለሰብ ሳይሆን ያልዋለበት እና ባካባቢው የማይኖር የድርጅቱን መሪ ለመዝለፍ መክንያት ማድረግ ነበር።ይገርማል!

እውነት ስድብ ከተቃወመ ለምን ብርሃኑ ነጋ “ከዚህም ከዚያም የተከማቹትን ቆሻሾች እንጠርጋቸዋለን” ያለውን “ የጠየቀውን ሃያሲ “በንፍጥ የተሞላ አእምሮ” እያለ ሲሳደብ ምነዋ እንደ ዛቻ እና ስድብ አልተቆጠረም? ካንዳርጋቸው በላይ ሕዝብን የዘለፈ ዘረኛ ከቶ አለ? ምነዋ አቶ በቀለ ንጋቱ የት ነበሩ እስከዛሬ ድረስ?
 ደግሞ ሰውየው “ኢህአፓዎች ወንጀል ለመፈጸም እያቆበቆቡ ናቸው” ሲል ያለ መረጃ እና ወንጀል ለመፈጸም የታቀደው የወንጀሉ ዓይነት እና በላያቸው ላይ ወንጀል እየተሸረበባቸው ያሉትን (የሚፈጸምባቸው ሰዎች) እንኳ እነማን እንደሆኑ አልነገረንም። እውነትም ጌታቸው በጋሻው እንዳለው ፖለቲካው ካላወቀበት በስሙ ተንተርሶ  የሚጮኩለት ሰዎች ፖለቲካ ደካማነቱ አውቀውበታልና እየተጠቀሙበት ነው ማለት ነው። ስድብ ማለት ድንቁርና ነው የሚለውን ሳነበው “ስድብ ድንቁርና ነው ብሎ ያስተማረው መምህር እራሱ ‘የስድብ ትርጉም” ለምን እንደሚጠቅም አላወቀውም። ስድብ የቋንቋ ተፈጥሮአዊ ተገቢ የመግለጫ መገልገያ ባይሆን ኖሮ “ደንቆሮ” “ድኩማን” የሚለው ቃል ባልታወቀ ነበር እሱን የማይመለከት ከሆነ “የተሰጠው ስድብ” እሱን እንደማይገልጸው መልስ መስጠት ነው። ካልሆነ ግን ስድብ ደካሞች የሚገለገሉበት በትር ነው የሚለው እራሳቸውን መግለጽ ያቃታቸው ድኩማን ናቸው። አንጎላቸው እስኪታይ ድረስ ከመጠን በላይ አፋቸው የሚከፍቱ ኦይሰተሮች በተከፈተው ክፍት አፋቸው የሚደመጠው ነገር አስቀያሚ ነውና አራሙቻ እንዳይወርባቸው ከፈለጉ የአፋቸው ክፍተት መጠን እንዲኖረው መለካት የክፍትአፎቹ ሃላፊነት ነው። ጌታቸው ረዳ ኢትዮፕያን ሰማይ አዘጋጅ።www.ethiopiansemay.blogspot.com




No comments: