Thursday, January 30, 2025

የሻዕቢያዎችን ፕሮፓጋንዳ የምታላምጥ ባንዳ ሚሰቱን አቅፎ ሲተኛ የነበረው የማይሙ የተፈራ ማሞ ቅሌት ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 1/31/25

 

የሻዕቢያዎችን ፕሮፓጋንዳ የምታላምጥ ባንዳ ሚሰቱን አቅፎ ሲተኛ የነበረው የማይሙ 

የተፈራ ማሞ ቅሌት

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay 1/31/25

አንዳንዱ በተፈጥሮ ወይንም በዘልማድ ሲያቀብጠው መቅለል የሚያምረው አመለ ክፉ ሰው አለ። ቅሌት ራስን ማዋረድ ማለት ነው። በዚህ የትግል ዘመኔ ብዙ ነገር ታዝቤአለሁ። እንደ ዛሬው 6 አመታት ያየሁት አስገራሚና አሳፋሪ ትግል አላየሁም። በተለይ ፋኖ የተባለው ሽምቅ ተዋጊ ሃይል ከተመሰረተ ወዲህ እያየሁ ያለሁት ጉድ ለመግለጽ ከገመትኩት በላይ ስለሆነ ለመግለጽ ያቅተኛል።

ፋኖ የተባለው ሽምቅ ተዋጊ ሃይልና በውጭ አገር እየኖረ በሞቀ ቤት ተቀምጦ ብዙ ሲጠበቅበት የነበረው ወጣት የአምሓራን ማሕበረሰብ ችግር ያስቆማል ብለን ስንጠብቅ በሚያሳፍር ሁኔታ ግማሹ በጠባብ አውራጂዊነት ተጠምዶ ሲጠዛጠዝ ይውላል፤ ግማሹ ደግሞ በሚያስቀን ሁኔታ እንግሊዝኛ የደበለቀ የወያኔን አፓርታይዳዊ የጎሳ ፌደራሊዝም አደረጃጀትን የሚናፍቅና የሚሰብክ አስቂኝ የሆነ የአምሐራ ሕዝብ ስቃይ ሜዳ ላይ ወጥቶ ብርዱንና ባሩዱን ለማሽተት ፈቃደኛ ያልሆነ “/ዋን አማራ/” ነፃ አውጪ በማለት እራሱን ሰይሞ በሞቀ ቤቱ የተቀምጦ <<አይስክሪም የሚልስ>> ዋሾ ትውልድ በአየር የሚጮኸውን ስናደምጥ ፦ ሐሜት ሱስ ሆኖበት በባዶ ቅዠት የሰው ስም ሲያጠለሽ መሽቶ የሚነጋለት የዲያስፖራው ወጣት ሐሜት ከየት ልፈልግ የሚልና እንቁራሪት አንድ ናቸው።

የስነ ፍልጠትና የስነ አካል ትምሕርት ያነባበችሁ ሰዎች ካላችሁ ስለ እንቁራሪትዋ ባሕሪ ልጥቀስላችሁ፤

የእንቁራሪት ዓይኖች የሚገኙት ከጭንቅላትዋ ራስ ላይ ነው። የምትቀልባቸው ሰለባዎችዋ የሚበሩትና የሚንሳፈፉት አብዛኛው አየር ላይ ናቸውና በሰማይ ላይ ትንሽ የሆነች ድፍን ነጥብ ካየች ወደ እሱ ዘልላ ትወጣለች፣ ለምግቧም ዝንብ ትይዛለች። የነዚህ አሉባልተኞችና የእንቁራሪት ባህሪ ምንም ልዩነት የለውም። ማንኛውንም ተንሳፋፊ ነገር ስታይ ትዘላለች። አንዳንድ ጊዜ በሰማይ ላይ የሚያልፍ ሁሉንም ተንሰፋፊዎችም አውሮፕላንም ወይም የአቧራ ቅንጣትም ይሁን ስታይ በስመ ተንሳፋፊ ዝንብ ነው እያለች እየዘለለች ምንም ነገር ሳትይዝ ፍለጋዋ በኪሰራ ይደመደማል።

 በዚህ አምሳያ የአርበኛ እስክንደርን ስም በማጠልሸት <<አዋቂ>> መስሎት የብአዴንና ኦሮሙማው ቡድን ተልዕኮ በማራመድ ቅሌት ውስጥ የገባ ብዙ ማፈሪያ አምሐራ ወጣት ሐሜት ሲቅምና ሲተፋ ይውላል። ተነስ ተብሎ በስንት መከራ ተወትውቶ “ይነቃል” ብለን ስንጠብቀው ረግረግ ውስጥ ገብቶ ራሱን የሚሰድብ አሉባልታ ነዢ ሆኖ አገኘነው።

አምሐራ የኔ እንጂ የማንም ኢትዮጵያዊ ዜጋ አይደለም የሚል ፤ <<አምሐራ ለአምሐራ ብቻ>> የሚል ናዚያዊና ፋሺስታዊ ወጣት ደንቆሮም በብዛት ተፈልፍሏል። እነኚህ አዳዲስ ናዚዎች ስመለከት እውቁ ኢትዮጵያዊው ሎሬታችን “የሎሬት ጸጋዬ ገ/መድህን” ንግግር ትዝ አለኝ።

እንዲህ ይላል፡

<<ሐይቅ ዳር ተሰብስበው እንቁራሪቶቹ አብዝተው ስለጮሁ ሐይቁ የእንቁራሪቶች ነው ማለት አይደለም። ለክብራቸው ሲሉ ዝም ያሉ ብዙ ዓሳዎች ሐይቁ ውስጥ አሉ>> (ሎቴት ጸጋዬ ገ/መድህን)

ውጭ አገር በሞቀ ቤታቸው ተቀምጠው በዩቱብና ቲከቶክ የሚንጫጩ ደናቁርት እንቁራሪቶች ማድመጥ እንዳይበቃን ዛሬ ደግሞ በፋኖ ስም ጫካ ውስጥ የገቡ የሽማግሌ ቅሌታሞች የሆኑ አንዱ ከጎንደር አንዱ ከወሎ ብቅ ብለው ራሳቸውን ሲያቀሉ አይተናል።

ከነዚህ አንዱ መሳፍንት የተባለው <<አስላምና ክርስትያን>> አብረው ሜዳ ላይ ዳቦ ቆርሰው ተካፍለው ሲዋጉ እያየ አስላምና አምሐራ “አንድ ዳቦ ቆርሰው እንዳይካፈሉ እያለ በጠላትነት የሚፈርጃቸው ፤ ትግራይን እንጨብጣታለን የሚል <<እልም ያለ ድንቁርና>> የጋረደው ጎንደሬው መሳፍንት ተስፉን ትተን ፤ ‘ወያነ ትግራይ’ እና ‘የሻዕቢያ ድብቅ ሰላዮች’ መንበረ ኢትዮጵያን ለመቆጣጠር  ጎንደር ፤ ወሎ፤ ጎጃም እና ሸዋ ጥሰው ወደ አዲስ አበባ ለመግባት እንዲያመቻቸው <<መንገድ ጠራጊ ባንዳዎች>> ከነበሩት መካከል ውስጥ እንደ እነ ተፈራ ማሞ (ብ/ጀኔራል) <<ጸረ አሳምነው ጽጌ>> የመሳሰሉ ማይማንን እየነዳ ወደ መሃል ኢትዮጵያ ገብቶ <<መንበረ ሥልጣን እንዲቆጣጠር>> ያደረጉ  <<መንገድ ጠራጊ ባንዳዎች>> ነበሩ።

ብአዴን ብሎ ወያኔ ያደራጀው ጸረ አምሐራ ድርጅት ውስጥ ዕድሜውን ሙሉ የወያኔን ጸረ አምሐራ ማኒፌስቶ ሲያስፈጽም የነበረው “ጀነራል” ብሎ ወያኔ የሾመው <<ማይሙ ተፈራ ማሞ>> እግሬ አመመኝ ብሎ ባለቤቱ ያመቻቸቺለትን ወደ ሻዕቢያዎቹ ከተማ ወደ አስመራ ለመሻገር እንዲያመቸው ከአገር ለመሸሽ ካገር ውጭ ሕክምና ሲጠይቅ “አፓርታይዳዊው ኦሮሙማው ቡድን ሲከለክለው” በመጨረሻ መደበቂያ ያደረገው አማራጭ “እነ እስክንደር ነጋ” የመሰረቱትን የፋኖ ትግል በመጠቀም ወደ ጫካ አመርቶ “ማይምነቱን” ያሻሽል ይሆን ተብሎ ሲጠበቅ አብይ አሕመድን ለማስደሰት ሲል <<አርበኛው አሳምነው ጽጌን “ሕሊናው የተቃወሰ ዕብድ”>> እያለ ሲያዋርደው የነበረው <<ሀሜተኛው አመሉ>> ሳይበቃ ፡-

ዛሬም በጀግኖች ላይ ስም የማጠልሸት “ክፉ አመል” ጫካ ላይም ገብቶ  ያንን መጥፎ ባሕሪው እንደገና አገርሽቶበት <<በታላቁ እስከንድር ነጋ>> ላይም  <<ስሙን በማጠልሸት>> <<በብልጽግና  ሰላይነት>> ሲከሰው መስማት እጅግ የሚገርም ወራዳ አመ ጫካ ውስጥም እንደገና ደግሞታል።

ብዙ ሰዎች በሻዕቢያ አጭብጫቢነትዋ የምናውቃት ሚሰቱ መነን ሃይሌ (የውሸት ስም) ባለቤቱ እንጂ ባልዋ ተፈራ ማሞ “ሻዕቢያ ጋር ንኪኪ የለውም” ሲሉ ይደመጣሉ። ደናቁርቶች በበዙባት አገር ውስብስብ ያልሆነውን ምስጢር ለማስረዳት ቢሞከርም ማይምነት ክፉ ነውና ‘ፈጣሪ ካልሆነ’ ሁኔታውን ለማሳመን ይከብዳል። ሆኖም ከኢትዮጵያ ወደ ኤርትራ በመሄድ ከኢሳያስ አፈወርቂ ጋር በመገናኘት፤ ከሻዕቢያው ፍሊፖስ (የሻዕቪያ ጦር አዛዥ ልብሱን አውልቆ አብሮ ከዚች ቅሌታም ጋር አብሮ በመውጣት የስቢል ልብስ ለብሶ እስዋም ፎቶ ላይ ዘንጣ የሚታየው ፎቶ) ጋር እና እንዲሁም.፦

 ከናት ጡት ነካሹ “እባቡ” ከበረከት መንግሥትአብ (ፎቶውን አልለጠፍኩትም) ፤ እንዲሁም አርበኞቻችን ኢትዮጵያዊያን ወታደሮቻችን ለናት አገራቸው ዳር ድምበር ብለው ከታንካቸው ጋር አብረው ከተቃጠሉበት አስከሬናቸው ላይ የሻቢያን ጀግንነት በማወደስ በሬሳቸው ላይ በተቃጠሉት ታንኮች ላይ ተቀምጣ ፎቶው ላይ የምናያት ፤ ምን ታመጡ ብላ በኢትዮጵያ ምድር እየኖረች የጸረ አምሐራውና <<በከሃዲውና በሻዕቢያው ወኪል በመለስ ዜናዊ ትብብርና ፈቃጅነት>> የባሕር በራችንን የዘጋን የኢሳያስ አፈወርቂን “ፎቶግራፍ አቅፋ” ለሕዝብ መታየት ብቻ ሳይሆን ፤ በሚገርም ሁኔታም ባልዋ ተፈራ ማሞ በሚኖርበት መኖርያ ግድግዳው ላይም ይዛው የምታዩት ትልቁ የኢሳያስ ፎቶ <<ተሰቅሎ ቤቱ እንዲያሸበርቅ የፈቀደ ፤-

ባልየዋም በሚሰቱ ቅሌት የማያፍር <<ከባንዳዋ>> ሚስቱ የማይሻል የሻዕቢያ አድናቂና ወዳጅ ነው ብንል አልተሳሳትንም።

እሰኪ አስቡት፡ ዘመናችን ከፋሺት ጣሊያኖች የባሱ “ጥቋቁር ጣሊያኖች” የሚገዙን ዘመን ነው። በ5ቱ አርበኞች ዘመን ከጣሊያን ሰላቶ ጋር የምትተቃቀፍና ዓላማቸውና ፕሮፓጋንዳቸውም የምትደግፍና ጥብቅና ቆማ የምታስፋፋ ሚሰት ጋር የሚኖር አንድ ኢትዮጵያዊ ቢኖር “የሰላቶዎች ተባባሪ” እንጂ እንዴት ያ ሰው “አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ” ተብሎ ሊወደስ ይቻላል? አንዳንዶቹ ደናቁርት ኦሮሙማው ስርዓት እስርቤት ሲከታት << አርበኛዋ ኢትዮጵያዊት ታሰረች>> እያለ ፎቶዋን ለጥፎ በየፌሰቡኩ ማየት እጅግ የሚገርም ደንቆሮ ማሕበረሰብ መኖሩን ስናይ፤ የምንለው ስናጣ በአግራሞት ከመታዘብ ምንስ ማለት ይቻላል?

 ስለ ዛቺው ሻዕቢያዊትዋ ባለቤቱ የባንዳነት ስራዋ እንዳይበቃ፤ ብላ ብላም ፤ የትግራይ ወላጆቻችንና ዘመዶቻችንን ቅማላም፤ አጋሜ እያለች የሻዕቢያ ተልዕኮ ለማስፈጸም <<የትግራይ ሕዝብ በሙሉ ከወሎ ውስጥ ተጠርጎ ወደ ትውልድ አገራቸው ወደ ትግሬያቸው ይባረሩ>> እያለችየዘር ማጥፋትኢንተርሃሙዌዊ ቅስቀሳ በማድረግ የታወቀቺው የጀኔራል ተፈራ ማሞ ባለቤትመነን ሃይለስለ ትውልድዋ ወሎ መሆንዋን ስትናገር ሰምቻት አፈርኩላት። ስለ እዚች ሻዕቢያዊትያልተገረዘ ቆሻሻ ምላስዋንምን ያህል ላንድ ጀኔራል ማዕርግ ላለው ሰው ባለቤትነት ውርደት መሆኑን ስንገምት እጅግ ከባድ ገመና እና አሰቃቂ ታሪክ ነው።

የአንድ ኢትዮጵያዊ ጀኔራል ሚሰት ሕዝብን የሚያክልኢትዮጵያዊ ዜጋከወሎ ተጠራርገው እንዲባረሩ ስትቀሰቅስጀኔራል ተፋራእንዴት ዝም ብሎ ይህንን የዘር ማጥፋት ዘመቻ ሰምቶ እንዳልሰማ ከዚች እብድ ጋር አብሮ ታቅፏት ይተኛ ነበር? እንዴትስ የወላጆቹን ምድር ኢትዮጵያንና ትግራይን ከድቶ60 አመት ዕደሜ ያላት ኢትዮጵያእያለ የሚያንኳስስ፤ ባንዳው ኢሳያስና ወያኔ በጣምራ ሆነው አርበኞች ወታደሮቻችንን አልጌና እና ምፅዋ ላይ ይህች የጠላት ባንዴራ እንዳትተከል መስዋእት ያደረጉትን አርበኞች ተረስተው እንዴት ሻዕቢያን የሚያክል ወንጀለኛ ድርጅት የጠላትን ባንዴራ ከሚተኛበት አልጋው ጎን ላይ ከገዛ አገሩ ሰንደቃላማ አብሮ ተሰቅሎ ሲያይ ጀኔራል ተፈራ እንዴት አቅል ሰጠው? ምን እሚሉት ዘመን ነው የደረስነው?!

የመሃል አገር ሰው በሴት እና በስጋ አያስችለውም (በዓሉ ግርማ ኦሮማይ መጽሐፍ)” በሚባለው በዚህ ባህሪ ተጠምዶ ይሆን ይህ ኢትዮጵያዊው ጀኔራል በኦሮማይ መጽሐፍ የተገለጸቺው ጫፍ ምፅዋ ላይአንዲት ልጅ ብቻዋን ካንድ ጠርብ ድንጋይ ላይ ቆማ ማዶ- ሰማዩንና ባሕሩን የሚሳሳሙበትን አድማስ ስትመለከት አየሁየተባለላትን የኦሮማይዋፍያሚታ ጊላይየሚያክል ቁንጅና የተላበሰቺው በመነን ሃይለተማርኮይሆን የጀኔራሉን ልብ አኖህልላ ይህ ሁሉ ኪሳራ ሊደርስበት የቻለው? የሚል ጥያቄ ሰንጠይቅ መልሱ እውነትምየመሃል አገር ሰው በሴት እና በስጋ አያስችለውምየሚለን አስመራ ላይ ሆኖ የታዘበውንና የነገረንን ደራሲው የበዓሉ ግርማ እውነታና ግጥምጥሞሽ እዚህ ላይ የታየ ይመስላል።

ፍያሜታን የተካነቺው ቁንጅናቆንጆዋ መነን ሃይሌጀኔራሉን እንዴትና ምኑን ወድዳለት ይሆን ያገባቺው? ኦሮማይን ማንበብ ነው! ሆኖም ሁላችንም ብንሆን (በኔ ላይ ልመስክር) በሴት ቁንጅና የማይማረክ ወንድ የለምና ቁንጅናዋ ያስገደደው ይመስለኛል።

ምክር!

አንዴ ፋኖን መቀላቀሉ ላልቀረ ፡ ተፈራ ማሞን የምክረው “ፖለቲካው ለተካኑት ፖለቲከኞች ትቶ በወታደራዊ ፍልሚያው ብቻ ቢያተኩር የተሻለ ውጤት ይኖረዋል” እያልኩ ሰለ ስም የማጠልሸት እና ሃመተኛ ባሕሪው ግን እግዚአሔር ይማረው!

ሰላሙን ለናንተ ይሁን!

ጌታቸው ረዳ