ኢትዮጰያዊያን ፈላሻዎችን በሚመለከት ቤተ እስራኤል የሚለው ቃል ምንም አይነት የነገድ ፍቺ የለውም! ይህ የኢትዮጰያን ማሕጸን መደፈር ነጋሪ ምልክት ነው!
ጌታቸው ረዳ
Ethiopian
Semay
12/30/25
ከፍል 1
መግቢያ፡
ይህ ትችት መነሻ የሆነኝ እግረኛ
ሚዲያ በመባል የሚጠራ ሚዲያ ጋዜጠኛ ወደ እስራኤል በመጓዝ የእስራኤል ከነሰት (ፓርላማ) ተወካይ የሆነች ጎንደር ተወልዳ ያደገች በ16
አመትዋ ከኢትዮጵያ (ወደ ሱዳን?)
ከዚያም ወደ ምደረ ምስር (ግብጽ) ወደ እስራኤል ወደ ፈረንጆች አገር (የራሰዋ ቃል ነው) በመሸጋገር እስከ ከፍተኛ የዲግሪ ትምሕርት ተምራ በአመድ አፋሸዋ እምየ ኢትዮጰያ ላይ ብዙ ወቀሳ (አለፍ ብሎ ሲነሽጣትም ባንዳንድ ሰዎች ላይ ዛቻ እና ቁጣ) የምታዘንብ ዶ/ር ጸጋ መላኩ የተባለች “እስራኤላዊት” ሰሞኑን የሰጠቺው ቃለ መጠይቅ በሚመለከት ነው።
እያንዳንዱ ቃላቶችዋን ለመቃወም ወይንም ለመተቸት ሳይሆን ከታሪክ ውጭ የሆኑ ከዕውነታ የሚዛቡ ንግግሮችዋን እና ክሶችዋን ብቻ አስመልከቸ እከራከራለሁ።
እንዲሁም እነዚህ «ቤተ-እስራኤል» ነን ይሚሉ ወግኖቻችን ለምን እንደካዱን ሳስበው ሁሌም የሚያቃጠለው አንጀቴን ለመግለጽ አጋጣሚውን ተጠቅሜ ለመግለጽ ነው።
እነዚህ ወገኖቻችን በዘር ከእናንተ ጋር አንገናኝም ፤ከናነተው ዘር አይደለንም ከሃብታሞቹ፤ ከኃያላኖቹ ከአምላክ ከተመረጡት ምርጦች የተገኘን ዘር ነን ብለው ክ3000 አመት በፊት የተውናትን ሃገራችን እስራል እንጂ ኢትዮጵያ አይደለችም ማለታቸው ለምንሰማ ወገኖች «በሃገራችን ላይ የተፈጸመው ሳብቨርዢን/ የባሕል እና የማንነት ወረራ» ሳስበው እጅግ ጥልቅ ደባ ተፈጽሞብናል።
በዚህ እነጋገራለን፡
ሆኖም
በዚህ አጋጣሚ ለመግለጽ የምፈልገው እንደማንኛችን “ዲያስፖራዎች(?)“ የፈለጉትን ዜግነት የመሆን መብታቸው እቀባላለሁ። ሆኖም «እኛ ከናንተ አልተወለድንም፤ እኛ እስራኤሎች እንጂ
ኢትዮጵያዊያን (ጥቁሮች አፍሪካዊያን አይደለንም) የሚሉበትን ክርክራቸው ግን “ለምን ሆኖ?” ብለን እንከራከራቸዋለን። ክርከሬ እና ቅሬታየ
በማስረጃ እነሆ ።
መልካም ንባብ፡
የ ዶ/ር ጸጋ መላኩ ቃለ መጠይቅ አንዱን ለግንዛቤ እንዲረዳን አንዳንዱን ልጥቀስና ከዚያ ወደ ትችት እገባለሁ።ጸጋ የተመረቀችበት ሙያ በፖለቲካል ሳይንስ እና ማሕብራዊ ጉዳይ ነው።
ጋዜጠኛው ኑሮ እንዴት ነው? ሲል ይጠይቃታል፦ ዶ/ር
ጸጋ መላኩም እንዲህ ትመልሳለች፦
« እኛ ቤተ እስራኤሎች ኢትዮጵያ ውስጥ ስንኖር ከመደበኛ ጽሎታችን በተጨማሪ መቸ ነው ወደ ሃገራችን የምንመለሰው እያልን እንጸልይ ነበር።»
ትልእና ጋዜጠኛው እንዲህ ያላታል፤
ቤተ እስራኤሎች ኢትዮጵያ ውስጥ እንደ ማንኛውም ዜጋ ተንደላቅቀው ይኖሩ ነበር ታዲያ ለምን እስራኤልን እንደ አገርኛ አስመኛችሁ? ሲል ለጠየቃት ጥያቄ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ለስንት አመት “በጥገኝነት” ይኖሩ እንደነበር ትንሽ ስቅጥጥ ሳይላት ስንት አመት እንደኖሩ እና ምን እንደገጠማችው እንዲህ ትነግረናለች፤
«ኢትዮጰያ ውስጥ 2500 አመት በኖርንባቸው ዘመኖች ጥሩ ዘመኖችም መጥፎ ዘምኖችም ነበሩ። መጠሪያ ስማችን እኛ ነን ራሳችንን ቤተ እስራኤሎች ብለን የምንጠራ እንጂ በሃገሬው አጠራር “ፈላሻዎች” ነን የምንባለው። ፈላሻ ማለት ፈልሶ የመጣ ፤
የቦታው ባለቤት ያልሆነ ማለት ነው። ስደተኞች ናቸው፤ ቡዳዎች፤ የቀን ጅቦች ናቸው፤ ካይላዎች እንባል ነበር፤ ይህ ደግሞ የተዘገበው መጥተው ያዩን የውጭ ጸሕፊዎች ነው በመጽሐፍ መልክ የተዘገበው፡ 2500 ስንኖር መጥፎ ነበር ልልህ አልችልም፤ ግን ደግሞ ቀላል አልነበረም። ከቤተ እስራኤሎች በጋብቻ ለመጋባት ክብር አልነበረም፤..............................»
እያለች ተልካሻ ምክንያትዋን ትዘከዝካለች።
ይህች በክሕደት ባሕር ውስጥ የምተዋኝ ሴትዮ ለማስተካከል ጋዜጠኛው እንዲህ ይላታል፤-
«መሰዳደብ እኮ የትም ዓለም ያለ የሰው አፈጣጠር ባሕሪ ነው: እንኳን በማሕበርሰብ ፤ በእህትና ወንድም ወይንም በባልና ሚስትም አለመጣጣምና መዘላለፍ ያለ ነው: እንደ እርሰዎ የመሰሉ በፓርላማ ተወካይ ደረጃ እና በምሁር ደረጃ ባለ ሰው እንዲህ ስንባል ነበር እያሉ ሲናገሩ ልዩነቱ አያሰፋውም ወይ? ወዘተ.... እያለ በጥሩ መረጃ እያስረዳ ቢሞክርም፤`
ብዙ ዝባዝንኬ እያመጣች ለማምለጥ ትሞክር ነበር።
በነገራችን ላይ እነዚህ እህቶች እና ወንድሞች ዛሬም እዛው ባሉብት ሃገር «ኩሺ» (“ባርያ ‘’ ኔገር’’) እያሉ የሰድቡዋቸዋል። ለጆቻቸው ጭምር ትምሕርት ቤት ሁሉ መገለል እንደሚደርስባቸው ራሳቸው ይናገራሉ። እንኳን ሲቪል ሆነው ደምብ ልብስ የለበሱ ወታደሮች ሆነው እንኳ በቀለማቸው ተለይተው በፖሊሶች እንደሚገደሉና ፤ልዩነት እንደሚፈጸምባቸው
በሚዲያ የምንሰማ ቢሆንም ሴትዋ ግን ልትነግረን አልፈለገችም።
ያም ሆነ ይህ በቃለ መጠይቁ ስፋት እያንዳንዱ ልሄድበት ሰለማልችል ማስፈንጠሪያውን እሰጣችኋለሁ እዛው አድምጡ እና ወደ መነሻ ነጥብ ልግባ፤ይህንን ቪዲዮ ንባቡን ሰትጨርሱ ቆይታችሁ ተመለክቱት።
እስራኤል የፈረንጆች (የነጮች አገር) እንጂ የጥቁሮች አገር አለመሆኑ እራሰዋ ዶ/ር
ጸጋ መላኩ የመትኖርበትና የፓርላማ አባል ሆና የተመረጠችበት እስራል «የፈረንጆች አገር» ትለዋለች፡
እንዲህ ትላለች ፤
«እኔ ወደ እዚህ አገር ስመጣ 16 አመት ነበርኩኝ ፤ በወቅቱ ከኢትዮጰያ ስንመጣ ፈረንጅ አገር እስራኤል መኖር ከባድ ነበር።» ስትል ሳታስበው “አገር የምትለውን እስራኤል የፈረንጆች (የነጮች) አገር መሆኑን ነግራናለች ።
ያም ሆኖ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ቤተ እስራኤሎቹ ራሳቸውን «አይሁዶች ነን» ብለው አይጠሩም ነበር። ኢትዮጰያዊያን ፈላሻዎችን በሚመለከት ቤተ እስራኤል የሚለው ቃል ምንም አይነት የነገድ ፍቺ የለውም ምክንያቱም እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ቤተ እስራኤላውያን ራሳቸውን አይሁዶች ብለው አይጠሩም ነበርና “ኢትዮጰያ ውስጥ የሚኖሩ የእስራኤል ዜጎች ወይንም “የኢትዮጵያ ቤተ እስራኤል” የሚባል ነገድ ኢትዮጰያ ውስጥ የኖሩ ወይንም አሁንም እየኖሩ ያሉ የሚለው ማስረጃ ለማመን አስቸጋሪ ነው።
Bete Israel has no meaning of any sort of
ethnic definition as many are tricked to believe it that the so called “the
house of Israel of Ethiopians”, because until fairly recently, the Bete-Israel
did not refer to themselves as Jews.
ማስረጃውን ላቅርብ፦«የኦፕሬሽን ሰሎሞን ዘመቻ» መጽሐፍ ደራሲ Stephen Spector እንዲህ ይላል፦
«Until fairly recently, the Bete Israel did
not refer to themselves as Jews. American Activists invented the term <<
Ethiopian Jews>> and by the mid-1970s the Bete-Israel had adopted it. In
Israel, they know universally use this designation. I employ it in discussing
events in 1988 and later, when the parties involved in arranging Operation
Solomon, the Western press, and often, the Bete-Israel themselves used it.
Similarly, I refer to ‘’Felashas’’ when presenting the views of people who used
that term at the time under discussion.
Despite the fact that their skin color can vary, the Ethiopian Jews did
not consider themselves to be black while in Africa. Allusions to the
Bete-Israel as “black Jew”’, also are problematic (Source -Operation Solomon –
author Stephen Spector).
በግርድፍ ሲተረጎም
« እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ቤተ እስራኤል ራሳቸውን «አይሁዶች» ብለው አይጠሩም ነበር። የአሜሪካ አይሁድ አክቲቪስቶች <<ኢትዮጵያውያን አይሁዶች>> የሚለውን ቃል ፈለሰፉላቸውና በ1970ዎቹ አጋማሽ ላይ ቤተ-እስራኤሎች ይህን ቃል ተቀበሉት። በእስራኤል ውስጥ፣ ይህንን ስያሜ በዓለም አቀፍ ደረጃ እንደሚጠቀሙ ያውቃሉ።
እ.ኤ.አ.
በ1988 እና በኋላ ላይ «በኦፕሬሽን ሰሎሞን ዘመቻ» ፣ የምዕራቡን ዓለም ፕሬስ በማደራጀት የተሳተፉ አካላት እና እራሳቸው ቤተ እስራኤሎችም <<ኢትዮጵያውያን አይሁዶች>> እያሉ መጥራት ስለጀመሩ እኔም ስለ ሁኔታው ስዘግብ እጠቀምበታለሁ። በተመሳሳይ፣ ‹ፈላሻ› የሚለውን ቃል ሰጠቀም በወቅቱ ቃሉን የሚጠቀሙ ሰዎች አስተያየት ሳቀርብም ተጠቅሜበታለሁ። ምንም እንኳን የቆዳ ቀለማቸው ሊለያይ ቢችልም ኢትዮጵያውያን አይሁዶች አፍሪካ ውስጥ እያሉ ራሳቸውን እንደ ጥቁር አድርገው አይቆጥሩም ነበር። ቤተ እስራኤልን እንደ “ጥቁር አይሁዳዊ” የሚሉ ጥቅሶችም አይወዱትም፡ ችግር አለባቸው። (ምንጭ - ኦፕሬሽን ሰሎሞን - ደራሲ Stephen Spector)።
ከላይ የጠቀስኩት ደራሲም እንዲህ ሲል ስለማንነታቸው እንዲህ ይላሉ፡
Who are the Bete-Israel? The Origin of the Bete Israel are obscure and
contested, and attempts to reconstruct, their
history have been based principally on inference. (Stephen
Spector)
ትርጉም፤
<<ቤተ-እስራኤል እነማን ናቸው? የቤተ እስራኤል አመጣጥ ግልጽ ያልሆነ እና አከራካሪ ነው። ስለሆነም የእነሱን ታሪክ እንደገና ለመገንባት የተደረገው ሙከራ በዋናነት መረጃዎቹ ጭልምልም ያሉ ግምቶች ነው።>> Stephen Spector) ።
James Quirin
These various beliefs about the Israelite
origin, all assume that a substantial number of Jews migrated to Ethiopia, but
there is no direct record that these ever happened. For that and other reasons,
most academic scholars argue that the Bete Israel are not the descendants of
Israelites, but are instead an indigenous Ethiopian people of Agaw stock who
adapted Judaism. The evolution of the Ethiopian Jews: - A History of Beta
Israel (Falasha) to 1920 p.8 James Quirin)
ስለ እስራኤላውያን አመጣጥ እነዚህ የተለያዩ እምነቶች፣ ሁሉም እጅግ ብዙ ቁጥር ያላቸው አይሁዶች ወደ ኢትዮጵያ እንደፈለሱ የሚገምቱ ናቸው፣ ነገር ግን እነዚህ እንደተከሰቱ ቀጥተኛ ዘገባ የለም። በዚህ እና በሌሎችም ምክንያቶች ቤተ እስራኤላውያን የእስራኤላውያን ዘር ሳይሆኑ ይልቁንስ የአይሁድ እምነትን የተቀበሉ የአገው ተወላጆች የኢትዮጵያ ተወላጆች ናቸው’’ በማለት አብዛኞቹ ምሁራን ይከራከራሉ። A History of Beta
Israel (Falasha) to 1920 p.8 -James Quirin)
<<Some scholars have contended that
they converted under the influence of Jews from Egypt. The more widely accepted
theory, though, is that Jews living in Southern Arabia crossed the Red Sea at
its narrowest point, then traveled to Axum>> (Ullendroff, Ethiopia and
the Bible, pp .16-17)
<<አንዳንድ ሊቃውንት ከግብፅ በመጡ አይሁዶች ተገፋፍተው ወደ ሃይማኖት የተመለሱ ናቸው ሲሉ ተከራክረዋል። በይበልጥ ተቀባይነት ያለው ጽንሰ ሃሳብ ግን በደቡብ አረቢያ የሚኖሩ አይሁዶች ቀይ ባህርን በጠባቡ ቦታ አቋርጠው ወደ አክሱም የመጡ ሰዎች ያስተማረዋችወ ናቸው።
Quirin notes the Jew of Southern Arabia
knew Hebrew and rabbinic Judaism, including the Talmud while the Bete Israel
did not. Still, a number of prominent scholars concluded that the Arabian
Peninsula probably was the earliest and most important source of biblical
Hebraic influence on Ethiopia (Notes on history and literature (Conti Rossini)
Ullendrof pp 17-23 and the Ethiopians, p.51
ኩዊን እንደሚለው «የደቡባዊ አረቢያ አይሁዶች ዕብራይስጥ ያውቃሉ። የነገረ-ራቢንም ይሁን የየታልሙድን (ሕጎች፤ደመቦች፤ ባሕሎች) ሲያውቁ ቤተ እስራኤሎች ግን እውቀቱ የላችውም። አያውቁም። አሁንም በርካታ ታዋቂ ምሁራ የፈላሻዎቹ ከአይሁድ ሃይማኖት እምነት ትውውቃቸው የመነጨው በዓረብ ባሕረ ሰላጤ አይሁዶች ምናልባትም ጥንታዊው እና ዋነኛው የመጽሐፍ ቅዱስ የዕብራይስጥ ተጽዕኖ ምንጭ ባላቸው ሰዎች ወደ አካባቢው በተለያዩ ምክንያቶች በመዝለቅ ነው ከአይሁድ ሃይማኖት እምነት የተዋወቁት። ብለው ደምድመዋል። Ullendrof pp 17-23
and the Ethiopians ,p.51
በገዘብ ተሽጥው (የሸጣቸው ደግሞ ወያነ መልስ ዝናዊ እና ደርግ መንግሥቱ ሃይለማርያም ናቸው) ወደ እስራል ከመጡት አንድ የፈላሻ ቄስ በክሕደት ባህር እየዋኙ እንዲህ ያሉትን ልጥቀስ፤
Are we really in Israel? I feel happy like a lamb; because now, all my wishes have been fulfilled. It is better to die as a free Jew than to continue living in exile in Ethiopia” (እውነት እስራኤል ውስጥ ነን ያለነው? እሰቲ ደስ እንዳላት በግ ልዝለል። እጅግ ተደስቻለሁ፡ ምክንያቱም አሁን ምኞቼ ሁሉ ተፈጽሞልኛል። ኢትዮጵያ ውስጥ በስደት ከመኖር እንደ ነጻ አይሁዳዊ መሞት ይሻላል” ። ይላሉ ከካሃዲዎቹ ቄስ ነኝ ባይ ፋላሻ።
እሺ ብለን እንቀበላቸውና የአይሁዶቹ የመጀመሪያ ፓትሪያሪክ የአብርሃም ዘሮች ናቸው እንበል እና ያም ከሆኑ የኔን ክርክር ደግሞ የኸው አድምጡ።
እነዚህ ወገኖቻችን ፈጥረት ከተፈጠረ ጀምሮ ሲኖሩባት የነበረቺው ሃገራቸው ኢትዮጵያ በአምሪካኖች እና በእስራኤል ቅንጅት (ሴራ) ከድተው እስራኤሎች ነን ለማለት ያበቃቸው እንዴት ወደ እስራኤል እንደሄዱ ቆይተን የምናየው ሲሆን በነገዳቸው ጥቁርነታቸውን ከድተው የፍረንጅ ነገዶች እስራኤል ነን ብለው ወደ አብርሃም የሚመዘዝ ነገድ አለን ሲሉ ነው የምንሰማቸው ፡ አብርሃም ደግሞ ማነው? ስንል ታሪኩ ሌላ ነው።
በዘፍጥረት 11 መጨረሻ ላይ የአይሁድ አባቶች ታሪክ ይጀምራል። አብርሃም ማን እንደሆነ ይነግረናል። አብርሃም በትውልድ የእስራል ነገድ አይሁድ አይደለም። የተወለደው በከለዳውያን ምድር (የአሁኗ ኢራቅ) ነው። መጽሐፉ እንደሚነግረን እግዚአብሔር አብርሃምን አገሩን ትቶ ወደ ከነዓን አዲስ ምድር እንዲሄድ ነግሮታል፣ ይህም እግዚአብሔር ለእርሱና ለዘሩ ወደሚሰጠው የእስራኤል ምድር ወደ ከነዓን በመስፈሩ ስሙም እስራኤል ተብሎ ተጠርቶ እንደ መጀመሪያው እስራኤላዊ ይቆጠራል።የላል መጽሐፉ። እንግዲህ እነዚህ የኛ ወግኖች ደግሞ ኢትዮጰያዊያን (በተለይ አማራው) “ፈላሻ” እያሉ ይሰድቡናል እያሉ ለስደታቸው መሸፈኛ ቃሉን ሲጠቀሙበት በዚህ ሴትዮ ቃለ-መጠይቅ ሰምተናል። የቃሉ ትርጉም ዶ/ር ጸጋ መላኩ በሐሰት ከምትከሰን ቃል የተለየ ትርጉም ቢኖሮውም “ከሌላ ሃገር የፈለሱ ናቸው” የሚል ከሆነም ትርጉሙ አባታችን የሚሉት ከለዳዊው ኢራቃዊው አብርሃም ጥንተ ትውልዱ እና ሃረጉ ኢራቃዊ እንጂ እስራላዊ አይደለም።
ስለዚህ ከያዕቆብ ትውልድ ካላቸው ያዕቆብ የተገኘው ከኢራቃዊው አብርሃም ዘር ስለሆነ ቅር ሊላቸው አይገባም። ለዚህ ነው እነኚህ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ፤እኛ ስንጠራቸው ስድተኞች ናቸው ሳይሆን የምንለው ኢትዮጵያዊያን ናቸው ነው የምንለው። አንጅቴ እያረረ የምታዩኝ ምክንያን አምሪካኖች እና እስራኤሎች ተባበረው ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ከጉያችን ፤ከምድራችን ሰለነጠቁን ነው እንዲህ የምበግነው። ይህም የኢትዮጰያን
ማሕጸን መደፈር ነጋሪ ምልክት ነው!
ነገዳቸው ፈላሻ ሙር ናቸው። እነሱም ፋላሽ ሙር ነን ይላሉ። ሙር የሚለው ቃል አገው ነው። ሃይማኖታቸው የለወጡ አገዎች ማለት ነው። ፈላሻ የሚለው ቃል የሂብሩ ቃል ነው፡፡ ፈለሰ የሚለው የኛው ቃል ወደ ፈላሻ ቀየሩትና የሂብሩ ቃል ‘’ፈላሻህ’ የሚለው ቃል ተጥቅመው ተሰደብን አሉ። ለምን ቅር ይላችዋል? ኢትዮጰያዊያን አይድለንም ከ3000 አመት በፊት ከእስራል ሃገር ወደ መላው ዓለም የተብተንን ሰደተኞች ነን ፤ ከእነሱም አንደኛው ቅርንጫፍ እኛ ወደ ኢትዮጰያ ተስድደን የመጣን ስደተኞች ነን ብለው አምኑ። አሁን ተሰደብንን ምን አመጣው?
ፈለሰ የሚለው ቃል "መከነ፤ ተገለለ ዓልም በቃኝ አለ፤ መነነ" ማለት ነው። የእኛ ግዕዛዊያን (አክሱማዊያን) በዘመነ ኢዛና ከጨረቃና ከፀሃይ አምላክ አምልኮ ወጥተው ኦርቶዶክስነት ሲያመልኩ እነዚህ አክሱም ውስጥ የነበሩ ሙራዎች (አገዎች) አሁንም የአይሁድ አምልኮ አንለቅም ሰላሉ፤ በዚህ የሃይማኖት አለመጣጣም ተነስቶ የበዙዎቹ ሕልውና አስጊ ሆኖ ሰላገኙት በአክሱም ሕዝብና ንጉሥ ኢዛና ተውግዘው «የመከነ ሃይማኖት ተከታዮች» ተብለው፤ አንዳንዶቹም በዚህ አለመስማማት ከአክሱም ተባረው በወገራ፣ ደምቢያ፣ ጭልጋ፣ ጣና ሀይቅ ዳር፣ እና በሰሜኑ ተራራማ ቦታ. ወደ እሚባሉት ገጠሮች... ሰፍረዋል ።
የፈለሰ/የመከነ ማለት ተቀባይ የሌለው ፤ተከታይ ያጣ ሃይማኖት እንደማለት እንጂ “እራሳቸውና አለቅላቂዎቻቸው እንድሚተረጉሙት ሰደተኛ” ማለት አይደለም።
ነገሩ ከቅርብ ሰዎች የማውቀው ሰለሆነ፤ በዙዎቹ ወደ ጎንደር በመጋዝ መኖርያ ቀየሩና የተቀሩትም እዛው ቀሩ። ከዚያ ወቅት ጀምሮ ብዙ ተከታይ የነበረው ሃይማኖት በጥቂቶቹ ተወሰኖ መከኖ በመቅረቱ (የፈለሰ - የመከነ) አሉት።
በአክሱም ብቻ ሳይሆን እዛም ከማሕበርሰብ የመገለል ችግር ሲገጥማቸው (ፖርቲጋል ወደ ጎንደር መጥተው ካቶሊክነት ለማስተማር ሲጥሩ እንደገጠማቸው ችግር ሁሉ) እነዚህም መገለሉን ሰለሰለቻቸው አንዳንዶቹም አምነውበት ሃይማኖታቸውን ትተው ወደ ተዋህዶነት ገቡ። ሃይምኖታቸው በጥቂቶች ተወስኖ ሲቀር የመከነ (የፈለሰ ሃይማኖት) ሆነ።
ፈላሲ የሚለው የ ግ ዕዝ እና የትግርኛ ቃልም የመከነ ማለት ነው (ፈላሲ አይወልድም አይራባም ፤ከዓለም እና አካባቢው ሕይውት የተገለለ ማለት ነው።) እነዚህም የተገለሉ ተባሉ እንጂ “ስደተኞች አልተባሉም።«እኛ ኢትዮጵያዊያን አይደለንም እስራኤላዊያን ሰደተኞች ነን» ፤ብለው በግልጽ አማርኛ እና እብራይስጥኛ እየነገሩን ያሉት ራሳቸው ናቸው። ከዚያ ወዲያ ጀምሮ በግልጽ አገላለጽ በብሉይ ኪዳን ተከታዮች (በኋላ ፈላሻ ተብሎ የሚጠራው ማሕበርሰብ) እና በአዲስ ኪዳን ክርስትና ተከታዮች (ተዋህዶ) መካከል የነበረው ሃይማኖታዊ የመለያ አጠራር ስም ሆነ እንጂ የነገድ ስም አይደለም። ፈላሻ ብሉይ ኪዳን የሚከተል አማኝ ማለት እንጂ ተንኮሎኞቹ (conspirators) እንድሚሉት “ስደተኛ” ማለት ወይንም የነገድ መለያ አይደለም።
ይህ የኔን ትርኋሜ ካላረካችሁ ወደ 5ኛው ክፍለ ዘመን ወደ ንጉሳችን ንጉሥ ይስሐቅ እና የፈላሻዎቹ ታሪክ ላቅርብላችሁ፤
ፈላሻዎች ናቸው (ስደተኞች ናቸው) ተብለን ኑሮአችን በእጀ ጥበብና በንግድ እንጂ አርሰን የምንኖርበት መሬት አልነብረንም ሲሉ የሚያቀርቡት ስሞታ አለ።(እሰላሞችም ባንዳንድ አውራጃ ለምሳሌ አከሱም ውስጥ ማሕበረ ዴጎይ (ከናዕዴር ወጣ ብሎ) ገጠር አካባቢ እስላም አራሾች አሉ (ዓዲ አስላም በሚባል ገጠር) ካልሆነ በቀር መተዳደሪያቸው ንግድ እና ልብስ በመስፋት ካልሆነ በቀር እስላሞችም ከኒሻዎችም ፤ካቶሊኮችም....(ፐሮተስታንት ታሪክ በዓድዋ የሚለው መጽሐፌን አንብቡ)። የሚያርሱበት መሬት የላቸውም ነበር (ትግራይ ውሰጥ ብቻ) (ምክንያቱም ልክ እንደ ፈላሻዎቹ የሃይማኖት አለመጣጣም ጉዳይ ነውና) ።ቆይተው ፈላሻዎቹ የሃገር ሎጆች ናቸው ተብሎ የሃያምኖት ጥሰት ተሰርዞላቸው እርሻ እያረሱ ይኖራሉ።
ስደተኞች ተባልን የሚሉ እነኚህ ወንደሞችና እህቶቻችን ስደተኞች ናችሁ ከመባላቸው በፊት እራሳቸው ነን በለዋል፡አደለም እንዴ? ስደተኞች ስለሆኑ ሳይሆን በአዲስ ኪዳን (የተዋህዶ ኦርቶዶክስ ክርስትና) አንጠመቅም ስላሉ ነው ክእርሻ ባለቤትነት የታገዱት። ጥሩ ምግባር የሚከተል ሃይማኖት ተከታዮች ነን የሚል ፈጣሪ ፊት መዋሸት ነውር ነው።
የአፄ ይስሐቅ አዋጅ እንዲህ ይላል፤
<<He who is baptized in the Christian religion, may inherit the land of
his father, otherwise, let him be Felasi>>
<<በክርስትና ሃይማኖት የተጠመቀ ሰው ፣ የአባቱን
መሬት ይወርሳል ፣ ካልሆነ ግን ፈላሲ ይሁን>> ይላል።
አዋጁ። ሃቁ ይህ ነው!!
መዋሸት ይብቃችሁ!! የመሬት ባለቤትነት የተነጠቁበት ምክንያት የሃያማኖት እንጂ ስደተኞች ናችሁ ሰለተባሉ አይደለም።
ፈላሲ የግዕዝ ቃል ሲሆን አማርኛው “መነኩሴ” ማለት ነው። ፋላሲ የሚያርሰው መሬት የለውም፤ ኑሮው ከፈጣሪው ጋር እየተነጋገረ ሕይወቱን በብቸኛነት ተገልሎ የሚያሳልፍ
ማለት ነው። ለዚህ ነው “ተገልለን ስንኖር ነበር የሚሉት”። ፈላሲ
የሚለው ቃል በራሳቸው ተረጎሙት እና “ፈላሻ” የሚል ቃል ፈልስፈው
ፈላሻ ተባልን ይላሉ። ፈለሰ ማለት መነኮሰ
ፈላሲ ሆነ ማለት ነው። ከስደተኛነት ጋር ምንም የሚገናኝበት ነገር የለም
እንደው መገልልን እና የሰውን ክብረ ማሳነስን የፈጣሪን ሕግ እና የፈጣሪ ፈጡር የሚጻረረ ሥራ ፤የሰው ልጅ መብት መግፍፍን ካነሱ እማ እነሱ (ፈላሻዎቹ) እኮ ይብሳሉ። ሃቅ ሃቁን እንነጋገር እንጂ!
ማስረጃይን ላቅርብ፤-
እናቶች የወር አበባ ሲከሰትባቸው ወይንም ከወሊድ መሃል ደማቸው እስኪጠራ የሚገለሉበት በድንጋይ ካብ ተከብቦ ከአካባቢው ወጣ ብሎ የታጠረ ጎጆ አለ። “የደም ጎጆ” ይባላል። እስኪነጽሁ ድረስ እዛ ይቆያሉ (እንዳይወጡ የታገዳሉ/ይገለላሉ)። እናቶች በዚህ ዓይነት ጨካኝ መገለል ይሰቃዩ ነበር።
ሌላም ጉዳችውን ልጨምርላችሁ፤-
የፖለቲካ ሳይንሰ እና ማሕበራዊ ኑሮ ትምሕርት ተመራቂዋ ዶ/ር ጸጋ መላኩ «እኛን ፈላሻዎች ናችሁ ሰለሚሉን ለጋብቻ
አይፈልጉንም» ስትል ከላይ የጠቀሰቺውን ከስ አንብባችኋል።
ያ ግን ወደ ራሷ ማሕብረሰብ ባሕል ገልብጠን እስኪ እንየው።
ፈላሻዎቹ (ቤተ እስራኤላውያን) ከዚህ በታች የሚከተሉትን ፍጡራን ከሰው በታች
እና ያልፀዱ ናቸው የሚባሉት ልክ እንደ ሕንድ “ዳሊቶች” ያይዋቸዋል (ሚስ ትሪት/isolate - mistreat ያደረጓቸዋል)።
ዘረኞች ሕንዶች እና እነዚህ
ቤተ እስራሎች የሚያመሳስላቸው ዘረኛ ባሕል/ሕግ አላቸው። ከጥቁር ሕንዶች በላይ አድርጎ ፈጣሪ ሰለፈጠረን ጥቁር ሕንዶች ከሰው በታች
ሰለሆኑ መነካካት ከነሱ ጋር መጋባትም ነውርና የቅዱስነት መርከስ ነው፤ ብለው ሰለሚሉ ፡ የፀዳን ነን የሚሉ ጨዋ ሕንዶች «ዳሊት» የሚባሉትን ጥቁር ሕንዶች
ድንገት ልብሳቸው ወይንም እጃቸው ከነኩዋቸው ሮጠው እጃችውን ይታጠባሉ (ልጅም አዋቂም)።
እነኚህ የኛ ቤተ እስራኤላውያን («የኛዎቹ ምርጥ ሕንዶች») ደግሞ ልክ እንደ “የሕንድ ዳሊቶች” ሰለሚያዩን
እኛም እነዚህ ንጹሃን ነን ብለው ለሚመጻደቁብን ቤተ እስራኤላውያን እኛ ኢትዮጰያዊያኖችም በመልስ ምት «አትንኩን» ብለን እንጠራቸዋለን።
ምክንያቱም አንድ ፈላሻ ያልሆነ እንግዳ ድንገት ከነካው ከሃያምኖታቸው ሕግ ውጭ የሆነ የአንስት ወርሃዊ አበባ ወይንም ደም
ነክቶ ሊኖር ስለሚችል በሚል ራሳቸው “እንደ
ተበከሉ” ስለሚቆጥሩት ይሸሻሉ/ያርቁሃል። በዚህ ምክንያት ራሳቸው ብጹአን አድርገው ስለሚቆጥሩ «አትንኩን» (Don’t touch me)
ይባላሉ።
አሁንም ሌላ ጉድ ልጨምርላችሁ-
ማንም ሰው በግርዘት/ግርዛት/ ሥራ የሚተዳደር (ሴትም
ይሁን ወንድ) የቆሸሸ ፈጡር ተበሎ ሰለሚታይ
፤ እጅ መንካትም ይሁን ትዳር መመስረት የተከለከለ ነው።
ሓቁ እንዲህ እያለ ፤ ዶ/ር
ጸጋ ግን ያንን የራሰዋን ወገኖች አግላይ ሕግ ደብቃ «እኛ በኢትዮጰያዊያን
“ፈላሻ- ስደተኞች ናቸው ፤ ካይላዎች ፤ ቡዳዎች.. ስለሚሉን ለጋብቻ አይፈልጉንም፤ ኢትዮጰያ ውስጥ ከፈላሻ ጋር ጋብቻ ክልከል
ነው» ። ስትል አድምጣችኋሃል። በሚገርም ግን እነሱ «ማንም ሰው በግርዘት/ግርዛት/ ሥራ የሚተዳደር (ሴትም ይሁን ወንድ) እንደ
“የሕንድ ዳሊቶች” የቆሸሸ ፈጡር ስለ ሆነ ከፈላሻ ጋር ለኢትዮጰያዊያን ጋብቻ አለመፍቀዳቸው ተቀባይ የሆነበት ምክንያት ምንድ ነው?
ይህም ልጨምርላችሁ፤
ሬሳ መያዝ/መንካት/መሸከም/
ቅድስናን ማርከስ/ መበከል ነው ብለው ስለሚያምኑ ማንም ሰው ሬሳን የነካ/የተሸከመ/ ቤተ እስራኤላዊ ለአንድ ሳምንት በአንድ የመገለያ ቦታ ታጉሮ ሳምንት
ከሰው ጋር ሳይነካካ እንዲቆይ ይደረጋል። እንዳይገለሉም ፤ የክርስትና ዕምነት ተከታዮችን ዕርዳታ በመጥራት ሬሳ እንዲሸከሙላቸው ትብብር ይጠይቃሉ።
ይህ ሁሉ ጉድ እያላቸው
ኢትዮጰያዊያን ሲያገሉን ነበር እያሉ መዘላበድና ክስ ማቅረብ ምን ይባላል? ሃይምኖታችን ሕግ ስለሆነ ነው ብለው ምክንያት ብያቀርቡም
አንድን ሰው በሃይማኖቱ በጾታው እና በሚሰራው የመተዳደሪያ ሙያው ማግልለ፤ ማውገዝ፤ መናቅ በፈጣሪም በሕግም ነውር ነው።
እነሱ ሲያገሉ እና በሙያ ዓይነቱ አንድን ሰው ጋብቻ ሲከለክሉ ሕጋዊና
ተቀባይ የሚሆንበት፤ነገር ግን በነበሩት ነገሥታት እና ባወጡት ሃይማኖታዊም ይሁን ሰው ሰራሽ (መንግሥታዊ) ደምብ የተፈጸመ አግላይ አዋጅ ልክ አይደለም፡ እያሉ ሲቃወሙ እነሱ
ጋር የተደረገ ድርጊት በመዘርዘር “አገለሉን” ብለው ማለቃቀስ ተቀባይነት የለውም (It works both ways)።
እነዚህ ቤተ እስራኤሎች ነን የሚሉ ሰዎች ኢትዮጵያዊነታቸውን ብቻ ሳይሆን የካዱት ጥቁርነታቸውንም ነው እኮ የካዱት። ያችን ኢትዮጵያዊነት የተፈጥሮ ቀለማቸው
ማጥራት አልሆን በሎአቸው እንጂ በተግባር እኮ የኩሪትዋ የጥቁር ሃገሮች መመኪያ የሆነች ጥቁሪትዋ አፍሪካዊትዋ ኢትዮጰያ ተውላጆች ሳንሆን የመካከለኛ
ምስራቅ የፈረንጆች አገር እስራኤላዊያን ነን እያሉ ነው።የገርማል!
ጥቁር ሰው መነሻውና አፈጣጠሩ በጥቁሮች ምድር «አፍሪካ» (በቅርቡ ፍንጮች እንደሚያሳዩት ያውም ኢትዮጵያ !!) እንጂ ባለ ነጭ ቆዳዎች (የፈረንጆች ምድር- የወ/ሮ ጸጋ መላኩ ቃል ልጠቀም እና) በተፈጠሩባት ምድር እስራኤል እና ፍልስጢኤም ውስጥ ጥቁር አልተፈጠረም።ሓቁን ማክበር መዋጥና መቀበል ያስፈልጋል።ልብ ወለድ ታሪክ እና ሳይንስ ለየቅል ናቸው።ልብ ወለድ ማንበበና መስማት የሚያረካቸው የተማሩም ያለተማሩም በሚሊዮኖች መናልባትም በቢልዮኖች የሚቆጠሩ «ቶፕሎሊኖዎች» (Toy) የኖራሉ ያንን ልብ-ወለድ ማንበብ ስለሚያረካቸው ስጥዋቸው።
እነኚህ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን (ምንም እንኳ ለሰርጋቸው ማሞቅያ ጭፈራዎቻችንን እየጨፈሩ ፤ ሙዚቃዎቻችንም እያቀነቀኑ ፤ እሰክስታዎቻችንም እያስኬዱ ‘እስራኤሎች’ እንጂ እኛ ወንድሞቻችሁ እና እህቶቻችሁ አይደለንም ቢሉንም እንኳ) ፈላሻዎችን በሚመለከት ቤተ-እስራኤል ማለት የነገድ ትርጉም የለውም። እነሱን አይመለከትም። ነን የሚሉትም ከላይ እንደገለጽኩት ዘራቸው ወደ አብርሃም የሚስቡት ከሆነ ፤ አብርሃም ኢራቃዊ ነው።
ከለዳውያን ነን የሚል ካልሆነ በቀር ቤተ-እስራኤልነት ለቃሉ አጠቃቀም ያመቻቸው እንድሆን እንጂ ወደ 3000 አመት ተጎትቶ የነገድ ትርጉም ሊሰጣቸው አይችልም (ከ7 ትውልዳቸው በላይ በስም ሊቆጥሩ አይችሉም። ምክንያቱም የዘር ቆጠራ ፍለጋ ሲኳትኑ ወደ ኋላ በተመለሱ ቁጥር ጨለማ ውስጥ ጎትቶ ያስገባቸውና ማየት ወደ እማይችሉበት ዕውር ዓለም ያስገባቸዋል!!!)።
ምክንያቱን የዘር ሐረጋቸው ከአብርሃም እንደገና ያዕቆብ ከሆን «ቤተ-ከለዳውያን» ማለት ይችላሉ።ያም ቢሆን እስራይል ውስጥ (አብርሃም በነበረበት ከናዓን ምድር ውስጥም ቢሆን ከ3000 (2500) አመት በፊት ‘እስራኤላዊያኖቹ” በዶ/ር ጸጋ መላኩ አነጋገር ከወሰድን «ፈረንጆቹ የምትለው ቃል ልጠቀምና» በንጉሥ ናብኮደናጾር (ባቢሎናዊ) ወይንም በሮማዊያን (ጣሊያኖች) እስራላዊያኖቹ ከምድራቸው ሲባረሩ ወደ ኢትዮጵያ የተሰደደ ጥቁር ኢትዮጰያዊ መልክ ያለው ሕዝብ የለም።
ፈላሻዎቹ የእስራኤል ተወላጆች ነን የሚለው የፈጠራ/ልብወለዳቸው ብዙ ጊዜ ሞግቻለሁ። ፈላሻዎች/ ቤተ--እስራኤሎች/ አማርኛ ተናጋሪ የአገው ዝርያ ቅርንጫፎች ናቸው። ራስን መካድ ያመጣው የብዙ ምክንያቶች ጫና ነው (በነበርው የሃገራችን
ርሃብ እና ድህነት፤ በዛው ላይ የፈረንጆቹ “የሰው ማዘዋውር” ደባ ጨምሮ)። እነዚህ ክ3000 አመት በፊት ከእስራኤል ወደ ኢትዮጵያ የተሰደድን ስድተኞች እንጂ ኢትዮጳያዊያን አይደለንም የሚሉን ሰዎች የጥንታዊ ታሪክ ተመራማሪ እና የፖለቲካ
ሳይንስቲስት ዶ/ር ዓለሜ እሸቴ እንዴት እንደሚገልጽዋቸው በከፍል 2 እናያለን።
እነዚህ ሰዎች እስከቅርብ ድረስ ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ እስከ ቅርብ ዘመናት ድረስ አገው ይናገሩ ነበር” ይላሉ ሊቀ ሊቃውንቱ ዶ/ር ዓለሜ እሸቴ እና ቅድም
የጠቅስኳቸው ሊቃውንት። እንደ ሰሜን ኢትዮጵያ ሃገዊያን ክርስትያኖች ሁሉ ፈላሻዎቹ ሃይማኖታቸው ኢትዮጵያ ውስጥ የቆየ መነሻው እስራኤል የሆነው እና የጥንታዊው የአይሁድ እምነት መሰረት የሆነው የብሉይ ኪዳን አማኞች ተከታዮች እንጂ ከባሕር ማዶ የመጡ ሰዎች አይደሉም ።
የሰሜን ኢትዮጵያ ሕዝብ እና ምናልባትም የጎንደር አገው ወዘተ መሃል ያሉ ኢትዮጵያውያን እንደሌሎች ቀይ ባህር፣ ሳባውያን የመን ወዘተ ሰዎች በቅድመ ክርስትና ብሉይ ኪዳን ያምኑ ነበር። ስለዚህ በ4ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የአክሱም ኢዛና ንጉስ ወደ አዲስ ኪዳን (ተዋህዶ ኦርቶዶክስ ክርስትና) ከተቀየረ በኋላ የብሉይ ኪዳን አማኞች በተፈጥሯቸው ደስተኛ አልነበሩም። ስለዚህም በብሉይ ኪዳን ተከታዮች (በኋላ ፈላሻ ተብሎ የሚጠራው) እና በአዲስ ኪዳን ክርስትና ተከታዮች (ተዋህዶ) መካከል የተፈጠረው ግጭት (960_1000 ዓ/ም) ዮዲት ጊድዖን (ዮዲት ጉዲት) የፍልሚያው መሪ ሆና የአክሱምን መንግስት (የተዋህዶ፣መንግሥትን) አፈራርሳ እንደ ኢትዮጵያዊነትዋ ለ40 አመት አስተዳድራለች። መነሻው ከፈላሻ ሃይማኖት እና ተዋህዶ የሃይማኖት ግጭት ውጤት ነበር። ከዚህ ውጭ ምንም ሌላ ትርጉም የለውም።እስዋ አገው ነች (ኦሪታዊት አክራሪ ይሁዲ ሃይማኖት ተከታይ)።
ይህች የአይሁድ ሃይማኖት አክራሪ ተከታይ ነበረች የሚባልላት የሓሓይለ (ዓድዋ) ተወላጅ ንግሥት ዮዲት (ጉዲት) ስደተኛ ነኝ በሚል ወይንም አገር በቅኝ ግዛት ለመያዝ
የተነሳች ሳትሆን፤ ሃያምኖት ግጭት ያመጣው ነው። ስደተኛ ነኝ የሚል አንድ ማሕበርሰብ ኢትዮጰያን ያክል ታላቅ አገር 40 አመት በንግሥነት ሊያስተዳድር አይችልም።
በራሳቸው ቃል 2500 አንዳንዴም
3000 አመት ይሉታል የኖረ ማሕበርሰብ DNAው ቢመረመር ወደ አብርሃም
ያመላክት ይሆን? ወይንስ ወደ አፍሪካዊትዋ ሃገር ወደ ኢትዮጵያ?
አሁን ወደ ሃይለኛው ሙግት እገባለሁ።
Slave Trade in Tens of Thousands of Ethiopians
Branded as “ Falasha” “Black Jews” Smuggled out of Ethiopia was the Direct Rape
of Our Dignity Recorded in History
Getachew Reda (Ethiopian Semay) የሚለው በጽዮናዊያኖች
እና በአመሪካኖች ኢትዮጵያን የማናጋት ደባ የሚለው ጽሑፍን አንብባችሁ ይሆናል። ያ ጽሑፍ መነሻ ያድረገኩት ዶ/ር ዓለሜ እሸቴ
በገንዘብ የተገዙት ወንድሞቻችን የደም እና የአጥንታችን ቁራጮች የሆኑ
ኢትዮጰያዊያኖች አስመልከተው እሳቸው ዘምናዊ ሕዝብን ማሸጋገር ባርነት ደባ
ይሉታል፡ እኔም ባያችሁት መልኩ የኢትዮጰያ ማሕጸን በፋሺስት ጣሊያኖች እና በጾናዊያን ለሁለተኛ ጊዜ መደፈር (The
second Rape of the Ethiopian womb) ብየዋለሁ።
መምህር እና ወዳጄ ከቡር ዶ/ር ዓለሜ እሸቴ ስለ ፈላሻዎቹ የጻፉልኝ ደብዳቤ በሚቀጥለው ወደ ከፈል 2 የሚያሸጋግረን ሰነድ ላቅርብና ልሰናበት፤
እንዲህ ይላል፤
Dear-Getachew
<Regarding Israel and the Agaw: This is an important subject which is not easy to understand. So, follow with great attention. When I wrote on the Falasha in EEDN, I challenged the Israeli fabrication with no historical basis that Falasha are Jewish migrants in Ethiopia. I explained with historical sources that the Falasha are like the Amharic speakers semitized Agaw, or Agaw under Geez superimposition or influence. The Falasha are Agaw Ethiopians and until recent centuries they spoke Agaw. Their religion like the Christianity of northern Ethiopia is largely taken from Old Testament. We know Tewahdo Orthodox New Testament Christianity was introduced in Ethiopia in the 4th century. It is possible that there were already in Ethiopia believers in the Old Testament which had its origin in Israel and which constitute the bases of ancient Judaism, before the modern additions (Talmud etc.).........
The slave
trade in Ethiopian so called “Falasha” has therefore intensified at an alarming
rate. The total so far exported to Israel under American Congress and
Presidential orders and pressure, and through the supervision of the CIA-Mossad
and international Zionism, is approaching 100,000. As the Intifada intensifies,
as Israel needs more and more settlers in the West Bank and Gaza, more and more
fodder, the slave trade in Ethiopians will redouble its rhythm and there will
be no point crying when the slave trade reaches the millions depopulating
further, and eradicating
the ancient peoples
of Ethiopia.
I will call you next week when posted. Follow me >>
Aleme.
በማለት የላኩልኝ ደብዳቤ
በማስታወስ በወያኔ እና በደርግ ዘመን ፈላሻዎችን አስመልክቶ ኢትዮጵያ ተከላካይ ባጣችበት ዘመን በኢትዮጵያ ላይ የተፈጸመው የውጭ
እና የወስጥ ደባ ከእነ ተዋናዮቹ ጭምር የተከሰተው አስደንጋጪውን
ክንዋኔ በክፍል 2 እንመለከታለን።
የዶ/ር ጸጋ መላኩ ቃለ
መጠይቅ ላላደመጣችሁ ማስፈምጠሪያው ይኸው፡
አነጋጋሪዋ የእስራኤል ፓርላማ
አባል | የዓለም ህዝብ ስልክ ላይ እስራኤል አለች | እኛን ያጥላሉ ኢትዮጵያ ቢሆኑ ይጠየቃሉ
https://youtu.be/YgI8DVmolwE?si=wb53VPEpFIF4TT40
እስከዛው ሰላም እንሰንብት
ጌታቸው ረዳ
Ethiopian
Semay
