Sunday, January 28, 2024

የሰላም ሐዋርያት ወደሚኮነኑበት አገር እንኳን ደህና መጡ! ሓወርያው ሉቃስ ግራኝ አሕመዱ አብይ አሕመድ ይሰቀል ስላሉ ሓጢያታቸው ምኑ ላይ ነው? ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 1/28/2024

 

የሰላም ሐዋርያት ወደሚኮነኑበት አገር እንን ደህና መጡ!

ርያው ሉቃስ ግራኝ አሕመዱ አብይ አሕመድ ይሰቀል ስላሉ ሓጢያታቸው ምኑ ላይ ነው?

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay

1/28/2024

ሰሞኑን የሰማሁት ዜና አቡነ ሉቃስ የተበሉ አርበኛ ኢትዮጵያዊ አቡን ቀደም ብለው የአፓርታይድ መሪ አብይ አሕመድ ‘እየፈጸመብን ካለው መከራ  የሚያላቅቀን አንድ ጥይት ያለው ወታደር እንዴት ይታጣል’ በማለታቸው ፤ ቀን ቆጥረው ሰሞኑን አዛውንቱን አቡነ ሉቃስ ፍርድቤት እንደሚከሰሱ ሰምቼ ገረመኝ።

በአፓርታይዶቹና በፋሺሰቶቹ ትግሬዎች ስትረገጥ የነበረቺዋ ኢትዮጵያ እንዳይበቃ እነሱን የተኩ አፓርታይድና ፋሺሰት ኦሮሞዎች እየገዝዋት ያሉዋት አገር ግራኝ አሕመድ ካደረሰው ጉዳት እኩል የፈጸመው ወንጀለኛው “የኩሽ ኦሮሙማ ማኒፌስቶ” መሪው አብይ አሕመድ ይሰቀል ማለት ፍትሓዊ ነው። ግራኝና ጣሊያኖችን ይሰቀሉ ማለት  እንደሚያስገድል ዛሬ የተጀመረ ሳይሆን በጣሊያንም፤በ27 አመት የትግሬዎች አስተዳደርም ምሁራን ፤ጋዜጠኞች፤ ሰብአዊ መብት ተሟጋቾች፤ ሥርዓቱን የተቃወሙ የፓርላማ አባላት፤ አክቲቪስቶች ፤ የስነ ጥበብ ባለሞያዎች፤ ሠራተኞች፤ ወጣቶች፤ዕርጉዞችና እመጫቶች ፤ ጠበቆች፤ ነጋዴዎችና የሕክምና ባለሞያዎች እንዲሁም አስተማሪዎች ብዙ የሰላም ሓዋርያቶች፤ቀሳውስቶች ድያቆናት፤አቡኖች ሲረሸኑና ሲጋዙ የነበረበት ሁኔታ ነው። ዛሬ ያንኑ የቀጠለ ሆኖ ሳየው ቢገርመኝም፤ ኦርቶዶክስ መሪዎችም ሆኑ ተቃዋሚ ነን የሚሉ ቡድኖች ሐዋርያውን መኮነናቸው ስሰማ ቅር የሚያሰኝ ነው። ለግራኝ ሕይወት የሚስገበገቡ ግራኝ አሕመዶችና ሽብርተኞች ብቻ እንጂ “ፍትሕን” የሚጠይቅ፤ አድልዎና ግፍ እንዲያጥር ጥሪ የሚያቀርቡ ጸረ ግራኝ የሆኑ ሐዋርያት የዘመናችን አፓርታይድ መሪ ባጭር እንዲቀጭ መጸለይም ሆነ መቀስቀስ እንዴት እንደሚያስኮንን የሚያስረዳኝን ሰው እጠብቃለሁ።

 አብይ አሕመድ የተቀመጠባት አዲስ አበባ መዲና የሚጠራት “ፍንፍኔ” በሚል ይጠራታል። ይህ ሰው “የኦነግ ጥራጊ ፖለቲካ” ተሸክሞ ዛሬም ተባባሪዎቹን ሲያነጋግራቸው አዲስ አበባን “ፍንፍኔ” እያለ ነው።  እኛ ደግሞ አዲስ አበባ በፍንፍኔ መጠራትዋ ብቻ ሳይሆን የሰላም ሐዋርያት የሚኮነኑባት መዲና ከሆነች ወደ 33 አመትዋ ተጠግቷታል እንላለን።

 እስኪ የህችን ከኛ በተለዩን ኢትዮጵያዊ ሐዋርያ ጻሐፊ የጻፍዋትን ማስታወቂያ አብረን እናንብባት።

የሰላም ሐዋርያት ወደሚኮነኑበት አገር እንን ደህና መጡ!

    <<የሰላም ሐዋርያት ወደሚኮነኑበት አገር እንን ደህና መጡ! ነቢያት ዛሬም ወደ ሚወገሩበት መዲና ጥሩ እግር ጥለዎታል።ከዓለም አካባቢ በጥራጊ መልክ የወጣዉ አፓርታይድና ፋሺዝም ሥር እየሰደዱ ሚገኙበት አሮጌ አገር አዳዲስ ጋንግስተሮችን ያገኛሉ።ማስታወሻ ደብተርዎን ይቆጥቡ።ብዙ የሚያስጽፍ ድርጊት አለና! ለማንኛዉም እንኳን ወደ ማፊያዎች አገር መጡ! ስለ ሕግና ስለ ሕጋዊነት ብዙ ይሰማሉ! እንኳን ደህና መጡ ብቻ!>…..<ስለ ንግድና እንቅስቃሴ የሚአስተምረውን ሥነ ኣእምሮ አወቃለሁ ባልልም ቱሪስት ድርጅት (እሱም ስሙን ቀይሮ ካልሆነ) የተነሳሁበትን ዓይነት ማስታወቂያ ገና ከቦሌ እላይ እና ቀጥሎም የአራዳነት ማእከል በሆነዉ ከጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ወረድ ብሎ ቢለጠፍ ከ24ቱ የዓለም ድንቅ ነገሮች አንደኛዉ እንደሚሆን እገምታለሁ።>> (ጸጋየ ገ/መድህን አርአያ ጦቢያ ቁጥር 10/1993 (ጦቢያ መጽሔት)

አዎን ከዓለም አካባቢ በጥራጊ መልክ የመጣዉ አፓርታይድና ፋሺዝም አንደ ዱባ ሥር ሰድዶ/ተንሰራፍቶ/ የሚገኝባት ጥንታዊቷ አገር፤ ዛሬ ባለ ብሔሮቹ  <ዘረቢሶች> ናችሁ ቢሉንም ከስርዓቱ ባሕሪይ የተያያዘ በመሆኑ ለመነጋገርያ አና ሌሎች ማስገንዘቢያ ይረባ እንደሆን እንጂ ሰዎቹ ቢወቀሱም ቢመከሩምተፈጥሮን ተመክሮሊያድነውና ሊመልሰዉ እንደማይችል ከነ “በኒቶ” እና ከነ “ሂትለር” የወል ባሕሪይ ተገንዝበናል፡ ትግሉ ይቀጥላል።

ለሐዋርያቶቻችን ድምፅ እንሁን።

ኢትዮጵያ የነጠቀቺው ነጻነትዋ እስኪመለስ ድረስ ፤ የተዋረደቺው ሰንደቅዓላማችን ከተጣለቺበት እስክትነሳ ድረስ ሐዋርያቶች ድማጻቸው እንዲቀጥል እንጠይቃለን!

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay

Sunday, January 14, 2024

በትግሬዎች የበቀል እርምጃ ምክንያት መቶ ሚሊዮን ሕዝብ ታፍኖ እንዲሞት የተወሰነበት ሕዝብ ወደብ ፍለጋ ሲኳትት ምን ተሰማችሁ?! ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 1/14/2024


በትግሬዎች የበቀል እርምጃ ምክንያት መቶ ሚሊዮን ሕዝብ ታፍኖ እንዲሞት የተወሰነበት ሕዝብ ወደብ ፍለጋ ሲኳትት ምን ተሰማችሁ?!

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay        1/14/2024

በዚህ ቪዲዮ የምታደምጡት ለትውስታ እንዲሆናችሁ “በጣም በጣት የምንቆጠር ተቃዋሚዎች በነበርንበት ወቅት” የሰጠሁት ቃለ መጠይቅ ነው።አሁን ወደ ርዕሴ ልግባ።

ካሁን በፊት ደጋግሜ ነግሬአችሁ ነበር፤ ዛሬም ልድገመው፤ << ከትግሬዎች መወለዴ በሐዘኔታ ነው የማየው>> ለምን እያላችሁ ባታስቸግሩኝ እመርጣለሁ። ለብዙ ዘመን ትግሬዎች የተከተሉት ፖለቲካ እጅግ ቀፋፊና ዕብሪት የተሞላበት ጸረ አገር ነው። ስመ-ጥር የሆኑት  <ራስ አሉላ አባ ነጋ> የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚያውቃቸው በአርበኛነታቸው ነው፤ ነገር ግን አሉላም “ጸረ አማራ አክራሪ ትግሬ ብሔረተኛ እና ባንድ ወቅት የባንዳ ውል አድርገዋል”። ይህንን ስል በማስረጃ ነው።

ብዙ ትግሬ ሊበግን የችላል፤ ሊጨስ ይችላል፤ በመጨስ ታሪክ አይፋቅምና ትግሬዎች ሁሌም ከሃገር ግምባታና አብሮም እነሱ ካልገዙ ወደ ክሕደት ጋር የማይላቀቅ ገበና አላቸው ።

ትግሬዎች በጀግንነት አገር ጠባቂነት ሲወራላቸው ዘመናት አልፏል።  በተደጋጋሚ የፈጸሙዋቸው አገራዊ ወንጀሎች ግን ሲወራ አልሰማሁም። የትግሬዎች ብሔራዊ ክሕደት ከጣሊያን፤ከቱርክ፤ከግብፅም በላይ ነው።

ክሕደት ብቻ ሳይሆን ጥላቻቸውም በዚያው ልክ ነው። እስካሁን ድረስ ብዙ ሃገራዊ በደሎች ፈጽመዋል ፤ሆኖም አውርጄ አውጥቼ ምክንያ ካሰብኩት በላይ የፈጸሙት የበቀል እርምጃ የባሕር ወደባችንን ማሳጣት ነበር።

አንድ የሚያበሳጭ ነገር ሲከሰት ሁላችንም ለዚህ ተጠያቂ ወደሆነው << ሰው ፤ቡድን፤ሕዝብ>> ፊታችንን  ለመመለስ እንገደዳለን። የሚያበሳጭ ነገር ሲከሰት ከቁጥጥር ውጪ የሆኑ ስሜቶች ድቅን ይሉብናል።  ትግሬዎች የፈጸሙት ወንጀል- ልንረዳው አንችልም። አብዛኞቻችን በጭንቅላታችን ውስጥ እንዴት ያንድ አገር ዜጋ አገሩን በዚህ ደረካጃ ይጎዳል የሚል ሙግት ይመጣብናል።

አሁን የገጠመን የባሕር ወደብ ችግር አደገኛ ነው። እንኳን ወደብ ባንዳንድ ትላላቅ ከተሞች እንኳ  መኪና ማቆሚያ መፈለግን የሚመስል አበሳጭ ነገር የለም። ለግማሽ ወይንም ለሰዓት ማቆሚያ ፍለጋ ስትኳትር ውለህ መጨረሻ ሲጨንቅህ ሌሎች ባቆሙበት ጎን ከመስመር ውጭ በእጥፍ ተደርበህ እንድታቆም ትገደዳለህ።ይህ ኢ-ሕጋዊ ነው፤  ባለመኪኖችን ስለዘጋህባቸው ይበሳጫሉ፤ ሆኖም የጨነቀው ዕርጉዝ ያገባል ነውና ያንን የሚያደርጉ ብዙ ሰዎች አሉ። አሁን ኢትዮጵያ የገጠማት ይህንኑ ነው። የባሕር ወደብ እንዳይኖረን ትግሬዎች ዘግተውን ወደ መሄጃቸው ሄዱ!

የትግሬዎች መሪ “መለስ ዜናዊ” በፈቃዱ ከውጭ ሃይል ጋር መመሳጠር ያንን በቀል ፈጸመብን።

እንደ አለም ተምሳሌት ስትቆጠር የነበረቺው የሀገሮች ሰላምና መረጋጋትን ማስፈን፣ ለአለም አቀፍ ልማት እና ሰብአዊ ጥረቶች የበኩሉዋን አስተዋፅኦ ማድረግ የታወቀቺው የሃይለሥላሴ የተፈሪ አገር  “የተበረዙ ቅዠታም ተማሪዎች ባስነሱት ሁከት የወታደሮች ስብስብ ገባና የተፈሪን አገር ኢትዮጵያን  ወደ ደም መፋሰስ መራት”። ከዚያም ሁለቱ ትግሬዎች በአሜሪካን በእንግሊዝና በዓረቦች እየታገዙ “ባቢሎን” አደረግዋት። ዛሬ ከሞቱት በታች ዕጥፍ ሞት ሞተን ሬሳችንና አገራችን ለአራዊቶች ተጣለ።   

በትግሬዎች የበቀል እርምጃ ምክንያት መቶ ሚሊዮን ሕዝብ ታፍኖ እንዲሞት የተወሰነበት ሕዝብ ወደብ ፍለጋ ሲኳትት ሳይ ዕንቅልፍ ያሳጣል!

መልካም ሳምንት!

ጌታቸው ረዳ

Getachew Reda Interview Ethiopian Semay Editor 82 % የትግራይ ህዝብ አማራን በተለይ የሸዋ አማራን ይጠላሉ , በጥናት የተረ

https://youtu.be/uLDBFyDsMjI?si=PvpSsKDBQ5yHhJys

 

 

Saturday, January 6, 2024

ትግሬዎች በኢትዮጵያ አንገት ያጠለቁላትን የመታነቂያዋ ገመድ ለማስለቀቅ በሚደረገው ትግል የምትቃወም ሶማሌም ሆነች ኤርትራ እንዲሁም የአብይ አሕመድ ታቃወሚዎች ከፈለጉ በገመድ መታነቅ ምርጫቸው ነው! ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 1/6/2024

 

ትግሬዎች በኢትዮጵያ አንገት ያጠለቁላትን የመታነቂያዋ ገመድ ለማስለቀቅ በሚደረገው ትግል የምትቃወም ሶማሌም ሆነች ኤርትራ እንዲሁም የአብይ አሕመድ ታቃወሚዎች ከፈለጉ በገመድ መታነቅ ምርጫቸው ነው!

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay 

1/6/2024

ካሁን በፊት ትግሬዎች በዘመነ ሥልጣናቸው የሚያስመሰግናቸው ያስቀመጡት “የአባይ ግድብ” ‘መሰረተ ድንጋይ’ ተቃዋሚው ገደብ የለሽ መንጫጫት ሲያስማ፤ ዘግየት ብልም <<መንጫጫት አያስፈልግም>> ስል ጌታቸው ረዳ “ወያኔ ሆነ” እንዳላችሁኝ ሁሉ፤ ዛሬም እንደልማዳችሁ ጌታቸው ረዳ “ኦሮሙማ ሆነ” ማለታችሁ ስለማይቀር ረጋ በሉ። Check the Video at the end of this article. 

የዛሬ ቀን ወጋችን የወደብ ጉዳይ ነው። ከተቃዋሚው ጋር የተለየ አቋም ይዤ ይህ ለሁለተኛ ጊዜ እየተነተንኩ ነው። አንደኛው በቀደም ስለ ዓሰብና ጁቡቲ ወደብ  ባለቤትነት ልመና የነበረው አድካሚ ሙከራ እና  ቀጥሎ ዛሬ ደግሞ  በሶማሊ ላንድ እተደረገ ያለው የ50 አመት የ20 ኪ.ሜ የባሕር ወደብ ባለቤትነት ስምምነት በኢትዮጵያ ስምና ለኢትዮጵያ ህልውና ስለሆነ የወደብ ፍለጋ ጉዳይ እየተደረገ ያለው በአብይ አሕመድ የሚመራው ፋሺሰቱ የኦሮሙማው መንግሥት ካለው የአገሪቱ የወደብ ችግር “ከሰይጣንም” ጋር ተፈራርሞ ወደብ ለማግኘት መሞከሩ የሚመሰገን እንጂ የሚያስኮንነው መሆን የለበትም የሚል  ድጋፍ እያስሰማሁኝ ነኝ።

ዓለም በምቾት አትንቀሰቀስም። ሞተናልና መሞታችን ላይቀር ፤ ሞት ተፈርቶ ሳይተኛ አይታደርም። አገርም እንዲሁ ለህልውና ሲባል መሞትና መነሳት ያለ ነውና ትግሬዎችና ኤርትራኖች ተስማምተው 1983 (1991 ፈረንጅ ዘመን) ባንገታችን  ላይ ያጠለቁልንን የ36 አመት ገመድ ለማውለቅ የፈለገው የሥልጣን ብልግና የሚፈጽም መንግሥትም ይሁን  “የተንጠለጠለብንን ያንገታችን ገመድ” ላማውለቅ የሚጥር መሪ <<ማውለቅ ከቻለ>> በዝምታ መመልከት እንጂ መንጫጫት ተገቢ አይደለም።

ያው የተቃዋሚው ጀሌ እንደለመደው ሊንጫጫ ይችላል፤ እርሱም በመንጋነት መነዳቱ ሱስ ካደረገው አመታት ያስቆጠረ ስለሆነ እርሱም እንደ ሶማሊያዎቹና እንደ ኤርትራኖቹ ሲፍልግ ትግሬዎች ባንገታችን ያጠለቁልንን ገመድ ተጠቅሞ መታነቅ ይችላል።

ኤርትራዊው መለስ ዜናዊ ግድብ ለማነፅ ሲያቅድ መንጫጫታችን ትክክል እንዳልሆነ ሁሉ ኦሮሙማውም ወደብ ፍለጋ መራኮቱ መንጫጫት አያስፍልግም። ቢቻል ቢቻል እንኳ መደገፍ ካልፈለጋችሁ “ዝምታን” እንጂ ከሶማሊያኖችን ኤርትራኖች እንዲሁም ከግብፆችና እንዲሁም ከዓረቦች ብሳችሁ መንጫጫት ያስተዛዝባልና ሰከን ማለት አለባችሁ።ለነገ በይደር የሚደረግ አርምጃ ሁሉ “ነገን ከነገ ወዲያ” ምን ውልዳ እንደምትመጣ ስለማይታወቅ ነገር ባደረ ቁጥር ገመዱ እየጠበቀ መሄዱንም ማስተዋል ያስፈልጋል። ፖለቲካና አገር መለየት ልባምነት ነው።

አንዳንድ ተቃዋሚ ሚዲያዎች የሚያስሰሙትና የሚዝቱት ድምፀት፤ ጠላትን እያጎለበቱ ኢትዮጵያን የሚያንኳስስ ፕሮፓጋንዳና ውይይት ስሰማ “ጠመንጃ ይዘው” ከሶማሊያ እና ከዓረቦች ጋር ሆነው ኢትዮጵያን ለመውጋት የፈቀዱ እስከሚመስል <<የሚያስሰሙት ድምፀት>> እጅግ የሚገርም ዕብደት ነው።

ይባስ ብሎም የሶማሊያ ተወላጆችም ሆኑ ኤርትራኖችና አክራሪ ሶማሊ እና ኦሮሞዎችን ወደ ሚዲያቸው እየጋበዙ ተቃውሞ እንዲያስሰሙ በመጋበዝ እያደረጉት ያለው አስገራሚ ፕሮፓጋንዳ “ሶማሊያዎች ወይስ ኢትዮጵያኖች” ናቸው የሚል ጥያቄ ያስጭራል።

በጥር 1991 የሲያድ ባሬ መንግስት መውደቅ እና በ1998 ዓ.ም የሽግግር ብሄራዊ መንግስት ተመስርቶ ከዚያም  ሶማሊያ  በ6ቱ የነገድ ጎሳ (ክላን) መሪዎች ተከፋፍላ ወደ ስብርባሪ “አገርና መንደር” ተለውጣ <<የዘላን ምንግሥታት የሚያስተዳድርዋት ‘ሥርዓተ አልባ’ ሆና የዘመናችን “የወደቀች የተበላሸች አገር” ተብላ “አክራሪ እስላማዊ ሽብርተኞች” ሶማሊያን ሰላም ነስዋት። ከዚያ <<ምፅአተ ሶማሊያ>> ለማላቀቅ ኢትዮጵያ ልጆችዋን ወደ ሶማሊያ በመላክ መስዋእት ከፍላ ሶማሊያ አሁን ወዳለችበት መረጋጋት ካደረስዋት አገሮች ግምባር ቀደም ሚና የተጫወተቺው ኢትዮጵያ ነበረች።

 ስለ ሁሉም ጎረቤት ሕዝብ የምትጨነቅ፤ ሁሉንም አስተናግዳ የምትንከባከብ ኢትዮጵያ ዛሬ <<እጇ አመድ አፋሽ ሆኖ>> የወለደቻቸውም ሆኑ የውጭ ዜጎችና ጎረቤቶችዋ ሁሉም ተዛበቱባት (ዕድሜ ለትግሬዎችና ለኤርትራኖች ባንገትዋ ገመድ አጠለቁባት)

ሶማሊያ ማእከላዊ መንግሥት አልነበራትም ፤አሁንም የሚንገዳገድ ነው። ሶማሊያ አገር የሆነቺው በቅርቡ ነው። በ1960 ዓ.ም <<ፑንትላንድ እና ጋልሙድ>> ያሉ ትላልቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች በአለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ያልተሰጣቸው እና የሶማሊያ የራስ ገዝ ክልሎች ሆነው ይተዳደሩ የነበረ ሲሆን በሰሜናዊ ምዕራብ የሚገኙ ኃይሎች የሶማሌላንድ አሁን ካለቺው ሶማሊያ በቋንቋ እንጂ በአገራዊ አመሰራራት ዕድሜአቸው ሁሉም ለየብቻ የጣሊያንና እንግሊዝ ተገዢዎች ስለነበሩ ዛሬ ሶማሊ ላንድም ሆነች ፑንት ውሎው አድረው ሪፐብሊክን አወጁ።

ሶማሊ ስትወድቅ አጋጣሚውን አገኙና ዋና ከተማዋን ሞቃዲሾን ጨምሮ ቀሪዎቹ አካባቢዎች በተፎካካሪ አንጃ መሪዎች የሚተዳደሩ ትንንሽ ግዛቶች ሲካፋፈሉ <<ሶማሊ-ላንድም ልክ እንደ “ከሃዲዋ” ኤርትራ የጣሊያን ገዢ ነበርኩ ብላ አርስዋም ከኤርትራ እንዴት አንሳለሁ ብላ ነፃነቷን አወጀት። ኤርትራ ነፃ መውጣት ከቻለች (ሕጋዊ ባይሆንም) ያውም ሶማሊ-ላንድዋ “ይልቅኑም” ከኤርትራ በበለጠ አገርነት ለማወጅ ሕጋዊነት አላት። ሶማሊያ ዘላን እንጂ የተሰባሰበ አገርነት አልነበራትም። ይልቁኑ የጥንትዋ ኢትዮጵያ አካልም ነበረች።

በዚህ ወቅት ሶማሊያ አገር አልባ የሆነች ማህበረሰብ እና መደበኛ የህግ ሥርዓት የሌላት ሀገር የገሃዱ ዓለም ምሳሌ ተደርጋ የምትጠቀስ አገር በሌላት አቅሟ ኢትዮጵያን ለማጥፋት ስትዝት ተቃዋሚው ድጋፍ ሰጥቶ “አብይ አሕመድን ለመዘባበት” ሲል ኢትዮጵያ ላይ ሰይፉን ሲመዝ ማየት ያበሳጫል።

አሁን በመንጫጫት የባሰ ደምፅ እያስተጋባ ያለው ተቃዋሚው ሆኖ ከሚያስደምጠን አስገራሚ ተቃውሞና “ትያትራዊ ፌዝ” ወግንተኛነቱ ከኢስላሚክ ፍርድ ቤቶች ህብረትና አልሸባብ ጋር እስኪያስመስለው ድረስ እየጮኸ ስለሆነ፤ ተቃዋሚ ሚዲያዎች “አደብ” እንዲያደረጉ እጠቁማለሁ።

 አሁን ሶማሊያ በምትፎክረው  ፉከራ ‘‘እስላማዊ ሃይሎችንም ሆኑ ተገንጣይ ኢትዮጵያ ቡድኖች እደግፋለሁ ካለች’’ “እያሳከካት ያለው ወደ ነበረቺበት “ሥርኣተ አልባነት ለመመለስ ስለሆነ ያ እንዳይመለስባት መጸለይ ያስፈልጋታል”።

ሶማሊያ ሕልውናዋ በኢትዮጵያ ወታደሮች ጥበቃ ስር ስለሆነ 6 ሚሊዮን ሶማሊ-ላንድ እና 100 ሚሊዮን ኢትዮጵያን እገጥማለሁ ካለች (አብይ አሕመድ ወለዋይና አቋመ ቢስ የሆነ ስለሆነ እንጂ ቃሉን ከጠበቀ) ሞቃዲሾን እና አብዛኛውን የሶማሊያን ክፍል በአማፂያን እጅ እንደምትወድቅ ሶማሊያ ልብ ያለቺው አትመስልም።

ሶማሊያ በእግሯ ለማስቆም ሕግና ስርዓትን ለማስፈን የታገለቺላትን ኢትዮጵያ የታሪክ  ወንጀለኛ ትግሬዎች ያስገቡላት ገመድ ለማጥበቅ መዛትዋ ለኛም ለእርሷም ለማንም አይበጅምና <<በትግሬዎች የታነቅንበትን ገመድ>> ለማውለቅ ስንሞክር የሚታገልንን ማንኛውም ፖለቲካ እናወግዘዋለን። ኢትዮጵያ ስትጨነቅ አብሮ ከጠላት ጋር ጭንቋን የሚያባብስ በታሪክ ነበር ፤ዛሬም አለ፡ ለወደፊቱም ይኖራል።

ጽሑፉን “ሼር” ብታደርጉም ባታደርጉም የራሳችሁ ጉዳይ፤ እኔ የዜግንት ድርሻየን ወርውሬአለሁ። check the video at the bottom of this page. video credit to Futurology. If you cant open the video,  just copy and paste the title given to Google (you tube)

አመሰግናለሁ!

ጌታቸው ረዳ