Friday, June 30, 2023

አፈንጋጮች የፈጠሩት ባለ አዲሱ “ዲ ኤን ኤው” ትውልድ መልስ ለፊልም ሰሪና መምህር ለፕሮፌሰር ሃይሌ ገሪማ በኢትዮጵያን ሰማይ አዘጋጅ ዕይታ ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 6/30/2023Haile

                             አፈንጋጮች የፈጠሩት ባለ አዲሱዲ ኤን ኤው” ትውልድ

መልስ ለፊልም ሰሪና መምህር ለፕሮፌሰር ሃይሌ ገሪማ

በኢትዮጵያን ሰማይ አዘጋጅ ዕይታ

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay

6/30/2023Haile

 

Haile Gerima film imperfect journey 

ትናንት እስታሊን የተባለ “ኢትዮጵያ ፈርሳ ሳልሞት በህይወቴ ማየቴ እጅግ ደስተኛ ነኝ” በማለት የታወቀው ጸረ ኢትዮጵያው ድዋዊው የወያኔ ሚዲያ ቱልቱላ ለፕሮፓጋንዳው እንዲመቸው የአንዳንድ እውቅ ኢትዮጵያዉያን ምሁራን ቃለ መጠይቅ እየዳሰሰ ይጠቀምባቸዋል። ትናት ድንገት ፌስቡክ ቪዲዮ ላይ የዚህ ልጅ ሚዲያ “በቲክ ቶክ ቨርዢን” ያየሁት የፊልም መምህርና ፊልም ሰሪ የሆኑት ታዋቂው  የሃርቨርድ መምህር ፕሮፌሰር ሃይሌ ገሪማ እያሞካሸ ንግግራቸው ሲያደንቅ ድንገት አደመጥኩና የሰጡትን አስተያየት ከኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ ጋር የማይገናኝ  ስሜተኛ ወቃሽ (unrelated blame) ሆነው ስላገኘሁዋቸው አልተመቹኝም።

 ቪዲዮው የቆየ ቢሆንም ንግግራቸው ግን አሁንም ስራ ላይ ነው (አክቲቭ ነው)። ምሁር ናቸው፤ የፖለቲካ ምጥቀታቸው ግን ጠንካራ አይደለም። ስለ ኢትዮጵያ ያላቸው ፍቅር ግን ሞልቶ የፈሰሰ ፍቅር እንዳለቸው አጠራጣሪ አይደለም። ችግሩ የሚከተለው አባባላቸውን እንምለክት፡

ባንድ በዛው በቀረበው ቃለ መጠይቃቸው እንዲህ ይላሉ፡             

<<ከኢትዮጵያ ማፈንገጥ የተጀመረው ማፈንገጥ ፈልጎ ሳይሆንና ፈረንጆች ቆርቁረውት ሳይሆን፤ “ኢትዮጵያ” የሚለው ነው “እንድታፈነግጥ” የሚያደርግህ። የኢትዮጵያን ትርጉም ሳይገባው፤ታሪኩን ሳያውቅ “ሴንትራሊቲውን ይዞ” ቪዛህን ይጠይቅሃል፡ ያኔ አፈንግጠህ ትሄዳለህ፤ ይሰለችሃል።  ኢትዮጵያዊም ሆነ ኤርትራዊ አንድ ላይ ለመሆን የሰለቸው “ለወደፊቱም ብዙ ሊሰለቻቸው ይመጣሉ)፤ ይህችን መሃሉን ይዞ እኔ እኮ ኢትዮጵያዊ ነኝ ብሎ የሚያሰቃይህ ነው ችግሩ”>>፡ ይላሉ

መሃሉን ይዞ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ባይገባኝም (እንደ ወያኔዎች አባባል ወይንም እንደ ተኮላ ሓጎስ አባባል “ሸዋ” (መሃለኛው አገር?) ማለት ይሆን? ወይስ ሌላ ትርጉም?

ይሁን እና ፕሮፌሰሩ በደፋና ከመናገር ይልቅ በስም ቢገልጹልን ይቀለን ነበር ፤ ሆኖም በደፈና ለገለጹት ትንታኔአቸው መልስ ያሸዋል።

ይህ አባባለቸው የወያኔና ኦሮሙማ ሚዲያዎች በደምብ ወድደውት “ለማፈንገጣችሁ” ምክንያት “ኢትዮጵያ” የሚለው ሃይል ነው ብለው ጥሩ “የመሸሸጊያ ሽፋን” ስለሆኑላቸው በየሚዲያቸው እንደ ምሳሌ እየጠቀሱ ቪዲዮውን እየደጋገሙ ሲጠቅስዋቸው እያደምጥን ነው። የፕሮፌሰሩ አባባል በስነልቦና እሳቤ (ትምህርት) ከውስጣቸው የሚከነክናቸው ባንድ ቡድን የተገፉበት በግሃድ ሊነግሩን ያልፈለጉ የተዳፈነ ቁጣ እየገፋቸው እንደሆነ እገምታለሁ። ያም ሆነ ይህ ምክንያታቸው ከፖለቲካ ዐውቀት ደካማነት የተነሳ ነው ብየ እገምታለሁ።

ባጭሩ ያም ሆነ ይህ፤ አባባላቸው ለቃላቴ አጠቃቀም ይቅርታ እየጠየቅኩ ይህንን ታላቅ አትዮጵያ ሰው መዳፈር እንደሆነ ሳይወሰድብኝ “የፖለቲካ ድንቁርና” ይመስለኛል። አንድ ቡድን/በራሳቸው ቃላት “ትውልድ” አፈጋጭ የሆነበት ምክንያት አንድ ሰው “እኔ ብቻ ነኝ ኢትዮጵያዊ” ስላለው እንዲህ ለምን ትለኛለህ ብሎ “ያፈነገጠ አፈንጋጭ” ከ1960 ጀምሮ እስካሁን ድረስ አልሰማሁም። እሳቸው እንሚነግሩን ኤርትራኖችና አንዳንድ ኢትዮጵያዉያን (ኦነግ ፤ወያኔ ወዘተ…) ተገንጣይ ክፍሎች ለፍንገጣቸው ምክንያት እሳቸው ከሚሉት ጭራሽ አይገናኝም።

የዛሬ ትውልድ ከ60ዎቹ ጀምሮ እስካሁን ድረስ ያለው ማለቴ ነው አዲስ DNA (መለ-ዘር) በጭንቅላቱ ተተክሎበታል። አፈንጋጭም ሆኗል፤ ሌባም አጭበርባሪም ገዳይ የሰው ስጋ የሚበላ (ካኒባሊሰት) ዕርጉዝ የሚያርድ የሰው ደም ጨው ጭምሮበት የሚጠጣ ትውልድ ቢያነስ ወደ ላ ትተን በዚህ 5 አመት ውስጥ እንኳ በተጎጂ እማኞች ምስክርነት ሰምተናል በምስልም አይተናል። ለዚህ አፈንጋጭነትም ሆነ አጭበርባሪ ባሕል የመለውጥ ምክንያት እውን ፕሮፌሰሩ እንደሚሉት ነው? አይደለም።

ይህንን በተመለከተ አንድ  የኔን የብዙ አመታት የትግል ልፋት ኣይቶ ሁሉንም በየመልኩ እየታገልኩና እየተበሳጨሁ መምጣቴን ኣይቶ አንድ ወዳጄ በኢመይል የጻፈልኝን የቆየ መልዕከቱ ላጋራችሁ ፡

እንዲህ ይላል፡-

 ይህ ትውልድ የወላጆቹና የድሮ ቅድመ ኣያቶቹ DNA ከውስጡ አለ ለማስተማር ከጣርክ ድካምህ ከንቱ ነው፡ ጤንነትህም ላይ ቀውስ ያመጣብሃል። አገሪቱ ትኖራለች; ትውልዱ ግን የተለወጠእርኩስ ፤ ለብቻየ የሚል ግለኛ፤ ስሜተኛ፤ዘራፊ፤ መሃይም፤ ወላጆቹን የሚዳፈር ብሎም የሚገድል፤ ሃይትን የግንዘብና የዝሙት መጠቀሚያ የሚያፈደርግ አጭበርባሪ፤ ደፍሮ በማይገባበት ትግል ጨፋሪና ባሕል አልባ የሆነ ባለ አዲስ DNA በምድሪቱ ላይ መኖሩ ላንዳች ደቂቃም ቢሆን አትጠራጠር

ሲል ጽፎልኝ ነበር።

ይህ ባለ አዲስ DNA ትውልድ ፕሮፌሰሩ እንደሚሉት “ኢትዮጵያ” የሚለው ሃይል ነው እንዲለወጥ ያደረገው ወይስ በአገራችን አዲስ የባህል ወረራ ስለተፈጸመ ነው? መልሱ ለገንጣዩ (ላፈንጋጩ) ምክንያት “አዲስ የባሕል ወረራ” በመከናወኑ ምክንያት ነው።

ይህ እንዲፈጸም የብዙ መቶ አመታት በውስጥ ቅጥረኞቻቻው እና በውጭ ሃይላት የተከናወነ አዝጋሚ ሂደት ተከናውኗል። በኢትዮጵያ ታሪክ ሁለት ክስተቶች ተከስተዋል። ገንጣይና እና የግንጠላ ቀስቃሽ (አስፈንጋጭ እና አፈንጋጭ)።

ኢትዮጵያ ከዘመነ አክሱም ጀምሮ የሃይማኖት፤የመልክአ-ምድር እና የባህል ወረራ ተፈጽሞባታል። አጥቂዎቹ ከዘመነ አክሱም ጀምረው ያው እነሱ ናቸው አልተለወጡም (ትንሽ አዳዲሶች ተጨመሩባቸው እንጂ የጥነቶቹ ናቸው፡)  አንዴ ይሳካላቸዋል፤ አንዴ አልተሳካለቸውም። ለዘመናት ሲሸምኑት የነበረው ሴራ በ1983 ዓ.ም በትግሬዎች በኩል በመጨረሻ  ተሳካለቸው። ከላይ ወዳጄ የጠቀሰውን የባህልና የፖለቲካ እንዲሁም የመልክአ-መሬት *ግንጣላ/ማፈንገጥ” ለውጥ በኢትዮጵያ ተከናውኗል። ኤርትራም ተገንጥላለች ትግሬዎችም ግንጠላው እውን ሊያደርጉት ሞክረዋል፤ አልተሳካም ፤ አሁንም ቢሆን አልተኙም።

 ኦሮሞዎችም የመልክአ-ምድር፤ የባህል የጽሑፍ ቋንቋ ለውጥ አድርገው የመሬትም የባህልም ወረራ ፈጽመዋል፤ ብዙ ጉዳት አድርሰዋል፤ እያደረሱም ነው። ይህ ሁሉ የተከሰተው ፕሮፌሰሩ እንደሚሉት አፈንጋጮቹ “ኢትዮጵያ” የሚለው ሃይል ስላስገደዳቸው ሳይሆን በደምብ የተጠና ሴራ በአገራችን ለዘመናት በሂደት ስለተከናወነ ነው። እነዚህ ሴራዎች ምንድናቸው?፡ፕሮፌሰሩ አያውቁዋቸውም ሳይሆን አንባቢን ለማስገንዘብ ነው፡

ከራሴ መጽሐፍ የተገኘው “የትግራይ ብሔረተኞች በአማራ ላይ ያላቸው ጥላቻ ከምን የመነጨ ነው?” ከሚለው  ‘የብከላ ሂደት በኢትዮጵያ *ሳብቨርዥን” ከሚለው ንኡስ ርዕስ ልጥቀ

 (ለ) አራቱ የግዝገዛ ደረጃዎ……..91

   1-የሞራል ዝቅጠት Demoralization ………………ገጽ91           

   2-አገርን ማናጋት   Destabilization………………ገጽ93

   3-በቀውስ ቀለበት ውሰጥ መግባት  Crisis…….  ገጽ104

   4-የውሸት እርጋታ    Normalization………….  ገጽ104

ብታነቡት አፈንጋጮችም ሆኑ አሁን ላላው ባለ DNA አዲሱ ትውልድ ልናይ የበቃንበት ምክንያት ከላይ የተጠቀሱ በውጭ ጠላቶች ቁርቆራ (ሽፍን ወረራ) አራቱ ዋና ዋና ርዕሶች ተግባራዊ ስለሆኑ ምክንያት እንጂ ፕሮፌሰሩ እንደሚሉት “ኢትዮጵያ” የሚለው ተናጋሪ ወይንም ቪዛ ሰጪና ከልካይ ምክንያት የተጫወተው ጨዋታ ከኖረ “ኢሚንት” ነው። ከኖረም ጉዳቱ (ኢፌክቱ) ፈረንጆቹ “ኢነሲግኒፊካት” የሚሉት “ኢምንት” ነው።

ጋዜጠኛና ደራሲ መስፍን ማሞ ስለ ሟቹ ጋዜጠኛ ኢብራሂም ሹፋ አንስቶ ባንድ ጽሑፉ ኢብራሒም የከተበውን አንዲህይ ጠቅሳል፤ (ባጭሩ አሳጥሬ እጠቅሳለሁ)፤

“ታሪክ ያለቀ ነው፤ የተፈፀመ። ስለዚህም ስህተት ከነበር ለይተን ልናርመው፤ በጎውን አውጥተን የበለጠ ልናጎለብተው እንጂ። ‘ቴዎድሮስ ካሳሁን አፄዎቹን ያወድሳል። አፄዎቹ ደግሞ ሙስሊሙን ጨቁነዋል…ሙስሊም እንደ መሆንህ መጠን ልትቃወመው ይገባል’ የሚል ‘ምሁር መካሪን’ ራሴው ዓቃቤ ህግ ሆኜ፣ ክስ መስርቼ፣ ጥፋተኛ አስብዬ፤ ራሴው ደግሞ ዳኛ ሆኜ እስር ቤት ብወረውረው ደስ ይለኛል…ምኞቴ ነው። ይሄንን ‘ምክር’ እንኳን ለዕድሜ አቻዎቼ ለመጠቆም አደባባይ ልወጣ አይደለም አብረውኝ ላደጉት በጣም ለምወዳቸው በዕድሜ እጅግ ታናናሾቼ ለእህቶቼ ልጆች ዘኪዬ እና ኢብሮዬ አይመጥንም። ሳት ብሎኝ ይኽን ስል ቢሰሙ እንኳን (ፍፁም አልልም እንጂ) በእነርሱ የግንዛቤ አቅም እንኳን እየነሆለልኩኝ መሆኔን ልብ ብለው የሚስቁብኝ ይመስለኛል…አጎቴ ምን ነካው?

ይልና

…..ኢትዮጵያ የብዙ ሺህ ዓመታት ውጤት ነች። በጣም በርካታ መጽሐፍትም ስለ ኢትዮጵያ ተጽፏል። ከተለያዩ አቅጣጫዎች እና ፍላጎት ጋር’ ሲሉን ነበር። አዎን ኢትዮጵያ ብዙ ነች። ያለፍንበት ዘመንም ረጅም ነው። ያለፍንበት ዘመንን የሚገልፁልን ብዙ መጽሐፍትም አሉን። እነዚያን መጽሐፍት የምናነበው፣ የምንመረምረው እና የምናጠናው አሁን እኔ ቂም ወርሼ፣ ጥላቻን በልቤ አርግዤ፣ በቀልን በመሻት ከወንድሜ ጋር ልጋደልባቸው አይደለም…ዘኪዬ እና ኢብሮዬም ጊዜያቸው ሲደርስ ከወንድሞቻቸው ጋር እንዲፋጁ አይደልም… አንድ የሚያደርጉንን ነጥቦች ነቅሼ፣ የሚያስማማንን አበጥሬ እና በጋራ የሚያኮሩንን ለይቼ ብላቴናው የሚመኛትን በፍቅር የተሞላች ምርጥ ሀገር ለማየት እንጂ…!!! ለማንኛውም ወደ ፍቅር ጉዞ እያላችሁ ደግሞ ዛሬ………..!!!” >>  (ኢብራሂም ሺፋ)

ብሎ ጽፎ ወደ እማይቀረው ዓለም ተሰናብቶናል ሲል ብዕረኛው አውትራሊያ የሚኖር ጋዜጠኛና ደራሲ መሰፍን ማሞ ጠቅሶታል።

ከሟቹ ጋዜጠኛ ኢብራሂም ሹፋ የምንይዘው ነጥብ ፡

<ያለፍንበት ዘመንም ረጅም ነው። ያለፍንበት ዘመንን የሚገልፁልን ብዙ መጽሐፍትም አሉን። እነዚያን መጽሐፍት የምናነበው፣ የምንመረምረው እና የምናጠናው አሁን እኔ ቂም ወርሼ፣ ጥላቻን በልቤ አርግዤ፣ በቀልን በመሻት ከወንድሜ ጋር ልጋደልባቸው አይደለም…ዘኪዬ እና ኢብሮዬም ጊዜያቸው ሲደርስ ከወንድሞቻቸው ጋር እንዲፋጁ አይደልም…>>

 የሚለው ምክር የሚያሳየን ፕሮፌሰሩ የሚለትን ሳይሆን ለቂምና ለአፈንጋጭነቱ መነሻ ያለፈውን እየነቀሱበቀልን በመሻት አርስ በርሳችን እንድንጋደል በውጭ ሃይላት የተጻፉት መጻሕፍቶች  እንደ እነ 1) Marxism and Leninism; Stalin 2) Abyssinia The Powder Barrel  A Book the most burning question of the day;(Author- Baron Roman Prochazka 1935) በጣሊያን ጊዜ ሙሶሊኒ አስተዳዳር ኢትዮጵያነ ሲያስተዳድር የተከለው አስተዳዳር ምን እንደሚመስልና (ትግሬዎችና ኦሮሞዎች እንዲሁም ኤርትራኖች) የተከተሉት አሁን ላላው የርስ በርስ መገዳደልና ማፈንገጥ መነሻ እንደሆነ በግሩም አቀራረብ ሰነዱን አስደግፎ የጻፈ ጣሊያናዊው ፕሮፌሰር አልቤርቶ ሳባኪን መጽሐፍ ማንበብ ነው፡ (3) Ethiopia: The Last Two Frontiers (Eastern Africa Series, 10) Paperback – August 15, 2013 by John Markakis (Author) (4) Ethiopia: Anatomy of a Traditional Polity - by John Markakis 1974) እና የመሳሰሉ መጽሐፍቶችን ማንበብና  እና አሜሪካኖችነ አንግሊዞች በኢትዮጵያ ምሁራን ታዋቂ ሰዎችና ወታደራዊ ክፍሎች “ሲ አይ ኤ” እና “ኤም አይ” እንዲሁም እስላሙ ክፍልም አረቦች የመለመልዋቸው “ዋሃቢዎች” የተለያዩ የጴንጤ፤ የ666፤ ወዘተ….ሃይመኖት የውስጥ ተቀጣሪዎች ለፍንገጣው ዋና ተዋናዮች ናቸው።

ፕሮፌሰሩን ላስታውስ የምፈልገው “ጯሂ ያጣ ጩኸት” የሚለው የፕሮፌሰር የመጨረሻ መጽሐፍ ላይ በምርጫ 97 (በወያኔ ጊዜ) አንዲት የአሜሪካ ዲፕሎማት “የታሰሩ የፖለቲካ መሪዎች” እስርና መፈታት ጣሊቃ በመግባት (ድብቅ ስራዋን ለመስራት) ለማስፈታትና ለማስታረቅ ላይ ታች ስትል የነበረች አሜሪካዊት ባንድ ስብሰባ ላይ “ኢትዮጵያ ለአራት ትከፈላለች፤ ይህ የማይቀር ነው” ስትል ጩሆታችሁ ፋይዳ አያመጣም ማለትዋን ጽፈውታል። ይህ እንግዲህ ኢትዮጵያ ውስጥ አፈንጋጭ የበዛበት ምክንያት ከውጭ ሃይላት የተጠናቀረ የባህልና የፖለቲካ ሴራ ሥራው በደምብ ሰርቶ እሸት ሆኖ አፍርቶ ሴራው ስለተሳካ እንጂ “ኢትዮጵያ” የሚለው ምክንያት ሰውን እየገፈተረ ስላስፈነገጣቸው አይደለም (በምርጫ 97 አሜሪካን ኤምባሲ የተጨወተው የጣልቃ ገብነት ሚና ከትዝታችን ውስጥ አሁንም አለ፤ ዛሬም እየተጨወቱ ነው) ።

 ወያኔዎችና ኦነጎች የፕሮፌሰሩን ንግግር እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ማታም ጥዋትም በየሚዲያቸው ሲሰብኩበት ማየታችን የሚያስገርም ባይሆንም ፕሮፌሰሩ ግን አገሪቱ በውጭ ሴራና በአገር ቅጥረኞች ሴራ “በአፓርታይድ ፋሺዝም” እየተነዳች መሆንዋን ማየት ተስኗወቸው “አፈንጋጩ” *እኔ የምተረጉመው (አፓርታይዱ) “ኢትዮጵያ” የሚለው ሃይል ነው  የፈጠረው  የሚለው ክርክራቸው ካንድ የታወቀ ከፍተኛ ምሁር የሚጠበቅ ንግግር እይደለም። አፈነገጠ ማለት “ሄደ ወጣ፤ከመስመር ውጭ ከማዕከል ተሰናበተ፤ተገነጠለ……ወዘተ ያለው ትርጉም ነው። ተገንጣዩ ለአፈንጋጭነቱ እሳቸው የሚሉት ምክንያት ቢሰጥም ሃቅነት የለውም።

“ከኢትዮጵያ ማፈንገጥ የተጀመረው ማፈንገጥ ፈልጎ ሳይሆንና ፈረንጆች ቆርቁረውት ሳይሆን” የሚለው ክርክራቸው ስንፈትሽ፤  የመከነ ትውልድ ይልቅኑ ለምን ተፈጠረ የሚለው ብከላ ቢያጤኑት እየመከርኩ፤ ለምሳሌ የወላጆቹና የድሮ ቅድመ ኣያቶቹ DNA ከውስጡ ተለየው ‘የ27” አመት አዲሱ ትውልድ በትንሹ እንፈትሽ ብንል በፈረንጅ ባሕል ቁርቆራና በውስጥ አርበኞች የባሕል ወረራ አጥማቂ ቡድኖች መሆኑን ባንድ ገጣሚ የተገጠመውን ግጥም እንስማማና በዚሁ ግጥም አንባቢዎቼን ልሰናበት፦

ወይ አዲስ አበባ ወይ አራዳ ሆይ!

ሲታሰር ለሽ ብለሽ ሲፈታ ሆይ ሆይ!

የሚለው ስለ ሕዝብ የታሰሩትን ለማስፈታት ከመታገል ይልቅ ተሰቃይተው ከእስር ሲፈቱ በሆይ ሆይ እና  ዕልልታ የሚጨፍርና የሚቀበል፤ እንደ አህያ ሜዳ አደራሽ ወለል ላይ እየተንከባለ አጭበርባሪ የሃይማኖት ሰባኪዎች የሚጫወቱበት የሃይማኖት ተሰባኪ የተፈጠረባት ኢትዮጵያዊ አዲስ ትውልድ የተረጨበት አዚም ስንፈትሽ “ኢትዮጵያ” የሚለው ሃይል ሳይሆን “አዚም” ሰሪዎቹ ለ35 አመት በወጣቱ ሕሊና ያጠነጠኑት ድብቅ የውስጥና የውጭ አገር የአስፈንጋጮችና የአፈንጋጮች አዚም መሆኑን ይህችን ትንሽዋን ምሳሌ ማየት በቂ ነው።

እርስዎ “ቁርቆራ” (ውትወታ) የሚሉት እኔ “የውስጥ ቅኝ ግዛት” ብየ የምተረጉመው “ቁርቆራ” ለ35 አመት ኢትዮጵያን እያሰቃያት ያለው ሃይል “ኢትዮጵያ” የሚለው ቡድን ሳይሆን ጸረ ኢትዮጵያ የሆኑ በውጭ ሃይላት የተሰበኩና የተቀጠሩ አፈንጋጭ ሃይሎች ናቸው።

ሰላም እንሰንብት!

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay

 

Tuesday, June 27, 2023

ይህንን ጥንታዊ ሕዝብ ለምን ከምድረገጽ ሊያጠፉት ፈለጉ? ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 6/27/23


ይህንን ጥንታዊ ሕዝብ ለምን ከምድረገጽ ሊያጠፉት ፈለጉ?

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay

6/27/23

ከአውሮጳ ስመለስ አንድ የትግራይ ተወላጅ ምሁር የሆነ ወዳጄ በአንድ ጽሑፌ ላይ “ወያኔዎችና ኦነጎች እንዲሁም አክራሪ እስላም ኢትዮጵያዊያኖች አሁን እየተከተሉት ያለው የክልል/የቋንቋ/የሃይማኖት/ አስተዳዳር ፋሺሰት ጣሊያን በኢትዮጵያ ስያስተዳዳርበት የነበረው  የተቀዳ አስተዳዳር ነው” የሚለው ባንድ ድረገጽ የጻፍኩትን የቆየ ጽሑፌ ሲመለከተው ግራ ገብቶት “ይህንን አላውቅም ነበር፤ የመጀመሪያ ጆሮየ ነውና ማስረጃውን ላክልኝ” ብሎኝ እኔም በጠየቀኝ መሰረት አማዞን የመጽሐፍት መሸጫ መደብር ጣሊያናዊው “ፕሮፌሰር አልቤርቶ ሰባኪ” (1985) የጻፈውን መጽሐፍ ገዝተህ አንብብ ብየው፤ ያንብበው አያንብበው ባላውቅም ብዙዎቻችሁ ወጣቶች ይህንን መጽሐፍ ስትመለከቱት ወያኔ በሕገመንግሥቱ ያሰፈረው የህንኑ የጣሊያኖች አስተዳዳራዊ ስልት ነበር።

ያ መጽሐፍ የሚነግረን ኢትዮጵያን ለመቆጣጠር ጣሊያን አማራውን ማሕበረሰብ ካላጠፋ ኢትዮጵያን ለረዢም ጊዜ መያዝ እንደማይቻል ይናገራል። ይህ ብቻ ሳይሆን ጀርመኖችም ኢትዮጵያን አፍርሶ የምስራቅ አፍሪካ “ኢምፓየር” ለመዘርጋት መጀመሪያ አገር ዳሳሽ የነበረው “ቄሱ/ፓስተር/”  Rev. Dr.J.Lewis Krapf በወቅቱ በታሪክ ጸሐፍት  “ጋላ” በመባል ሲታወቅ የነበረውን ማሕበረሰብ በፕሮተስታንት ሃይማኖት አስጠምቀህ በመያዝ ጅርመናዊ አምላኪ ማድረግና ሰማቸውን በመሰየም “በላቲን ፊደል” እንዲጽፍ ማድረግና በምፅዋ በኩል አድርጌ በ1836 ወደ ኢትዮጵያ ገብቼ የመጀመሪያው ስልት የተጠቀምኩት መጽሐፍ ቅዱስን ጋልኛን በላቲን እንዲጽፉና እንዲያኑ ማድረግ ነበረብኝ ይህንንም አድርጌአለሁ በማለት “የሃይማኖት ሰባኪ” መስሎ ስብከቱን ሲጀመር፤ የተናገረውን ከመጽሐፉ ልጥቀስ፡- እንዲህ ይላል፡

“ቋንቋቸውን ተማርኩ፤ ይህንንመ ምስራቅ አፍሪካን ለመግዛት ያመቸናል። የሮማው ሚሺኔሪው ቻይናን ስጡንና ኢስያያን የኛ እናደርጋታለን እንዳለው ሁሉ እኛም ጋላን ስጡንና ምሥራቅ አፍሪካን የኛ ትሆናለች” ሲል Rev. Dr.J.Lewis Krapf በራሱ መጽሐፍ Travels, Researchs and Missionary During Eighteen Years Residence in Eastern Africa” (1960) PP.32”

ጥርስዋን መሾል የማታቆመው የዓረብ አገሮች ማሕበራ አባል የሆነቺው አክራሪዋ ሶማሌም ሆነች ከጥንት ጀምሮ ያልተኙብን አረቦችና በዙርያችን የከበቡንን አክራሪ እስላም አገሮች ሁሉም ያተኮሩት ኢትዮጵያን በመገንባት ቀዳሚ ሚና የተጫወተው አማራው ነው (ይህ ታሪክ ከአክሱም ጀምሮ በተለይ በ12ኛው ክ/ዘመን የተነሳው አማራው ንጉሠ ነገሥት ይኩኖ አምላክ እና ልጆቹና የልጅ ልጅ ልጆቹ….የገነቡዋትን ኢትዮጵያና ገድል ለማወቅ “ሰሎሞናውያን” የሚለው በዶ/ር ደረሰ አየናቸው የተጻፈ አዲስ አስገራሚ መጽሐፍ እንድታነቡ እመክራለሁ። ያንን “ሌጋሲ” በመያዝ ነው አማራንና ኦርቶዶክስን ስታጣፋ አብራ ኢትዮጵያም ትርመሰመሳለች ከሚለው የጣሊያን፤ የጀርመን ፤ የእስላምና የአረብ አገሮች ዕቀድና ትንኮሳ መነሻውና ምንጩ።

በሚገርም ሁኔታ ፤ ጣሊያኖች፤ ጀርመኖች፤እንግሊዞችና እስላማዊና ዓረባዊ አገሮች  ከስንት የዘመናት አዝጋሚ ፍትግያና ጦርነት በመጨረሻ እነዚህ በቪዲዮ የምትመለከትዋቸው “ባለሃገር” ጥንታዊ የእግዚአብሔር ልጆችን ለማሰቃየትና ለማጥፋት በከሃዲዎቹ “የትግራይ፤ ኦሮሞ እና በአክራሪ እስላማዊ ሃይላት” ቡችላዎቻቸው በኩል  ከምድሩና ከሰማዩ ከዳመና እና ከአምላካቸው ጋር ሲነጋጋሩ የሚውሉትን እነዚህ ጥንታዊ ባለሃገሮችን ለማጥፋት ወያኔዎች፤ አብይ አሕመድና ኦነጎች እነኚህን የዋህ ገራገር ጥንታዊ ሕዝብ ለምን እንዲህ ያለ ጭካኔ እየፈጸሙ ከምድረገጽ ሊያጠፉዋቸው ፈለጉ? ምን ዓይነትስ አንጀት ቢኖራቸው ነው? የሚለው ለመመለስ ከባድ ነው።

ይህ ሁሉ ልጽፍ ያስቻለኝ፤ ድንገት “You Tube” ላይ ገብቼ አንድ ነገር ስመለከት በምን ምክንያት እንደሆነ በማላውቀው ጫን ስለው አንጀት የሚበሉ የዋህ የጎጃም ባለሃገሮች እስክስታ ስመለከት ቀልቤን ሳቡኝና በነዚህ “እርግቦች” ላይ የተሳለው የጨካኞች ቢላዋ ሳስበው እንባየ አቀረረ።

 እስኪ የነዚህ ጥንታዊ ባለሃገሮች እስክስታ ካለቀ በላ በመጨረሻው የጨዋታው ማሳረጊያ የሰጡትን የአንድ አረጋዊ አባት እሮሮ አድምጡ “ድሃ ተበደለ ፍርድ ተጓደለ የሚል አስተዳዳሪ ይስጠን” ይላሉ። አሜን!

ጨረስኩ!

 ጌታቸው ረዳ

ካሲናው ጎጃም | አስቻለው ፈጠነ (አርዲ) | Aschalew Fetene (Ardi) | New Ethiopian Music 2023 (Official Video)

https://youtu.be/dSh0jJXCd_E

 

Sunday, June 25, 2023

ለወዳጄ ለገብረመድህን አርአያ ማስታወሻ ባለህበት ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay) 6/25/2023


ለወዳጄ ለገብረመድህን አርአያ ማስታወሻ

 

ባለህበት

 

ጌታቸው ረዳ

 

(Ethiopian Semay)

 

6/25/2023

ጤናህ እንደተጎዳ ከወዳጄ ሰምቻለሁ። አምላክ ምህረቱን ይስጥህ እያልኩ ኢትዮጵያዊያን አርበኛንና የትግል ባለውለታዎችን የማስታወስ ችሎታም ሆነ የማክበር ባሕሪ የላቸውም። ውለታህ የተረሳ ሆኖ ስለታዘብኩ፤ ሰው የረሳህም መስሎ ስለተሰማኝ ፤ ትዝ ቢላቸው ብየ የተወክልንን  የወያኔ ወንጀል የታሪክ ላስታውሳቸውና ባንተው ንግግር ጥቅስ ልጀምር፡

በሕይወት ከቆየሁ፤ ኢትዮጵያ ከወያኔ ፋሽስት አገዛዝ ነፃ ስትወጣ ለሚመለከተው በመምራት የጅምላ መቃብሩን ቦታዎች አሳያለሁ።” ገብረመድህን አርአያ (የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይን ታሪክ እንወቀው የወያኔ ፋሽስት ስርዓት በኢትዮጵያ’ ከሚለው የላክህልኝን ሰነድ።

እስኪ አንባቢዎቼን እንዲያስታውሱህ ስለ ወያኔ የግድያ ሱስ እና ወንጀል ምን ብለህ ነበር? ልጥቀስ፤

<< አንድ ወንድ ወይም ሴት ከመገደላቸው በፊት በምርመራ ሰቆቃ ይደርስባቸዋል። የምርመራው ሂደት፤እስረኛው ሁሉ በቶርቸር ማሰቃየትም ሆነ መግደል ከታች ተዘርዝረው ያሉትን መሰቃያ ዘዴዎች መሆን እዳለበት በዝርዝር በመወያየት ያፀደቁት 1 ስብሃት ነጋ 2 ግደይ ዘራፅዮን 3 አረጋዊ በርሄ 4 አባይ ፀሃየ ሲሆኑ ህዝብም ያለቀው በዚሁ አሰቃቂ ቶርቸር ነው ።

1.     ጎማ በለበሰ ብረት ጭንቅላትን፤ ብልትን እና ሆድን መቀጥቀጥ፤

2.    ሴትን ደግሞ ብልቷ ላይ የፈላ ውሃ በማፍሰስና ጡትን መግረፍ፤

3.    በጋለ ብረት ማቃጠልና እንጨትና ገለባ እሳት አቀጣጥሎ የተመርማሪውን ገላ መለብለብና እስትንፋሽ ማሳጣት 

4.    የፈላ ውሃ ጭንቅላት ላይ ማፍሰስ፤

5.  24 ሰዓት ሙሉ እርቃን አድርጎ በግንድ ላይ በማሰር   ለፀሃይና ለብርድ ማጋለጥ፤

6.  ቀኑን ሙሉ በገመድ ዘቅዝቆ መስቀል፤

7.  የወንድ ብልት ላይ 10 ኪሎ አሸዋ ማንጠልጠል፤

8. በምግብና በውሃ ውጥ መርዝ መጨመር፤  በብዙ ጨውና ላምባ (ናፍጣ) የተነከረ እንጀራ መስጠት፤ ምግብና ውሃ ለሳምንት መከልከል የመሳሰሉት ናቸው።

ይህ ጭካኔ አገር ውስጥ መንግሥት ከሆኑም በኋላ ቀጥለውበታል።

ይህንን አሰቃቂ ድርጊት ብዙውን ጊዜ የሚፈጽሙት፤ እነዚ ገዳዮችም በስብሃት እና  በግደይ ሰልጥነዋል ። ዋና ዋናዎቹ ገራፊዎችና ርሽና ሲያካሂዱ የነበሩ የሚከተሉት ናቸው

1. አለምስገድ ኢንቺ

2. ብስራት አማረ

3. ድለዊ

4. ሙሉጌታ አለምሰገድ  

5. ክንፈ ገብረመድህን

6. ሃሰን ሽፋ

7. አበበ ዘሚካኤል

8. ወዲሻምበል፤

9. ሙሉጌታ( ወዛም)ፀጋይ

10. ህቡር ገ/ኪዳን

11. አበበ ተ/ሃይማኖት (ጆቤ)

12. ሃይሉ በርሄ (ሃይሉ ሳንቲም)

13. ዘርአይ ይህደጎ

14. ታደሰ መሰረት ናቸው። (የነዚህ አወቃቀር ፈለግ ተከትሎ ብዙ ገዳይ መርማሪዎች በየገጠሩ ተሰማርተው ነበር)

እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ግለሰቦች በምርመራ በጣም የታወቁ  ጨካኞች ነበሩ። አበበ ተ/ሃይማኖት ማለት በወያኔ ዘመን የአየር ሃይል ሃዛዥ የነበረ፤ አቶ ገዛኢ ረዳ የተባሉት እና ሌሎች አዛውንቶችንና ወጣቶችን በእሳት እያቃጠለ ሲመርምር የነበረ አረመኔ ነብሰገዳይ መርማሪ ነው።

ከዚህ ሳንወጣ ግን ‘ሓለዋ ወያነ’ በአካባቢው የፈጸማቸውን የጅምላ የመቃብር ቦታዎችን እንመልከት፤

1. ጻኢ ሓለዋ ውያነ

2. ወርዒ

3. በለሳ ማይ-ሃማቶ  

4. ዓዲ ጨጓር

5. ዓዲ በቅሎ

6. ሆያ እገላ

7. ጻዕዳ ምሸላ - ዓዴት

8. ቡምበት

9. ሱር

10. ቃሌማ ገሃንብ

11. ባኽላ  

12. ጂራ ዓዴት በዋናነት የሚጠቀሱ ናቸው።

ምስክርነትን በተመለከተ፤ ኗሪው ሕዝብ፤ መሬቱና እኔ፤ የዚህ ጽሑፍ ደራሲ ገብረመድህን አርአያ፤ ሁሉንም ቦታዎች ስለማውቅ፤ በሕይወት ከቆየሁ፤ ኢትዮጵያ ከወያኔ ፋሽስት አገዛዝ ነፃ ስተወጣ ለሚመለከተው በመምራት የጅምላ መቃብሩን ቦታዎች አሳያለሁ።>>

ይላል ወዳጄ ገብረመድህን። ሆኖም ኢትዮጵያ ከወያኔ ፋሽስት አገዛዝ ነፃ በትወጣም ሌላ የወያኔ አገልጋይ የነበረ ኦሮሙማ አብይ አሕመድ ተተክቶ ሁለቱም በሕግ ላለመጠየቅና በጦርነት ሰበብ ዕድምያቸው ገፍቶ ሳይጠየቁ ሞተው ያልሞቱትም በቀጠርዋቸው በፈረንጅ አገሮች በፖሊካ ስደተኛ ስም ተመዝግበው “በሰላም” እንዲኖሩ ጦርነት በመክፍት ዕድመያቸው እየገፋ ማምለጫ አድርገውታል እና አንተም ባለህበት አውትራሊያ ጤናህ እንዲመለስ ጸሎቴ ነው።

የምን ግዜም የጥንቱ የጥዋቱ አብሮ አደግ ወዳጅህ ጌታቸው ረዳ ከአገረ አሜሪካ!!

Ethiopian Semay

Friday, June 23, 2023

ሦስት ወራት ሦስት መቶ ዓመታት ሆነውብኝ ተቸገርኩ!! ዳግማዊ ጉዱ ካሣ Ethiopian Semay 6/23/2023

 

ሦስት ወራት ሦስት መቶ ዓመታት ሆነውብኝ ተቸገርኩ!!

ዳግማዊ ጉዱ ካሣ

Ethiopian Semay

6/23/2023

ለበርካታ ዓመታት ዐይን ያልነበረው ሰው “ነገ ዐይንህ ድኖ ማየት ትጀምራለህ” ቢሉት “የዛሬን እንዴት አድሬ?” አለ ይባላል፡፡ እውነቱን ነው፡፡ የለመድከው ነገር ብዙም አያስጨንቅም፡፡ አዲስና የምትመኘው ነገር ሲቃረብ ለማየት ትጓጓለህ -  ተፈጥሯዊም ነው፡፡

እኛ ኢትዮጵያውያን ግን በተለይ አንድን መጥፎ ነገር ከለመድን በኋላ ያን የለመድነውን ነገር ለመተው እንቸገራለን፡፡ መጥፎ ነገር ዕጣ ፋንታችን የሆነ ይመስል ለዘመናት ከተጣባን ክፉ የአስተዳደር ደዌ ነፃ ለመውጣት ስንታትር አንታይም፡፡ ወይም በሌላ አገላለጽ ሌሎችና ጥቂቶች ታግለውና መስዋዕትነት ከፍለው እኛ ምንም ወጪ ሳናወጣ ነጻ መሆንን ነው የምንሻ፡፡ ያደለው ሕይወቱን ቤት ንብረቱን፣ ትዳሩን …. ገብሮ ሀገርንና ሕዝብን ነጻ ያወጣል - እኛ ብዙዎቻችን ግን ገንዘባችንንም ወደን ነፍሳችንንም ወደን ነጻነትን በነጻ ለማግኘት እንመኛለን፡፡ ብቻ ኢትዮጵውያን በብዙ ነገር እንለያለን፡፡ እንደሚባልልን ስለመሆናችን እርግጠኛ ለመሆን ጥናት ያስፈልገዋል፡፡ አንድዬ ጥሎ አይጥለንም እንጂ ይህ መጥፎ ዐመላችን ከምድር ጨርሶ ሊያጠፋን ምንም ያህል የቀረው አይመስልም፡፡

እንደምን ሰነበታችሁ ውድ አንባቢያንና አድማጮች፡፡ ለተወሰኑ ጊዜያት አልተገናኘንም፡፡ ብዙዎች የሀገራችንን በፍጥነት እየተለዋወጠ የሚሄድ ታሪካዊ ክስተት በአርምሞ እየተከታተሉ እንደመገኘታቸው እኔም የዚያው አካል ሆኜ ነው ዝምታን የመረጥኩት፡፡ እንጂ እናውራ ብንል በቀን 24 ሰዓት አይበቃም፡፡

ከመስከረም 2016 በፊት የሆነ የንጋት ምልክት እንደሚታይ ካለፉት ጥቂት ዓመታት ጀምሮ ብዙዎች ሲናገሩ ይሰማል፡፡ እኔም የዚያ ደገኛ ትንቢት ተጋሪ ነኝ፡፡ እናም ችግራችን ሊወገድ የቀሩን ጊዜያት ከሦስት ወራት አይበልጡም፡፡ ግን መጥፎ ሦስት ወራት ናቸው፡፡ የረጂምነታቸው መንስኤም እሱው ነው - መጥፎነታቸው፡፡ በአንጻራዊነት የትወራ እሳቤ - “ሪሌቲቪቲ ቲዮሪ” - ረገድ ካየነው የአንድ ቀን ደስታ በደቂቃዎች ሲገመት የአንድ ደቂቃ ስቃይ ለቀናትና ለወራት እንደሚሰማ ስቃይ ነው ይባላል፡፡ ሌላም እንይ፡፡ የሴት ጓደኛውን የሚጠብቅ ጎረምሳ ከተቃጠሩባት ሰዓት አሥር ደቂቃ ብትዘገይበት ለርሱ አሥር ሰዓት ነው፡፡ ከተገናኙ በኋላ የሚያሳልፉት አምስትና ስድስት ሰዓት ደግሞ የአምስት ደቂቃ ያህል ነው፡፡

ለዚህ ነው እኔም በርዕሴ እንደጠቀስኩት የኢትዮጵያ ሀገራችን የነጻነት ዘመን ሦስት መቶ ዓመታት ያህል የቀረው ሊመስለኝ የቻለው፤ እንጂ ደጃፋችን ላይ ቆሟል፡፡ ሁሉም ነገር አልቋል፡፡ ፊሽካውም ተነፍቷል፡፡ ጥሪው የደረሳቸው ጀግኖች ጀምረውታል፡፡ እግዚአብሔርም ከነሱ ጋር ነው፡፡

አማራውና የአማራው ወገኖች የሚያሸንፉት ወደው አይደለም፡፡ ተገደው ነው፡፡ ካላሸነፉ ኢትዮጵያን እርሷትና እነሱም ከምድረ ገጽ ስለሚጠፉ ነው፡፡ ኦሮሙማ ቀላል ኃይል አይደለም፡፡ ሰይጣንነት ላይ ዕብደትን ጨምሩበት፡፡ ዕብደት ላይ የዘር ጥላቻን አክሉበት፡፡ የዘር ጥላቻ ላይ ሆዳምነትንና ስግብግብነትን ደምሩበት፡፡ በሁሉም ላይ ደግሞ ድንቁርናንና ሰገጤነትን ጨምሩ፡፡ እነዚህ ኦሮሙማ የሚባሉ ጉዶች ዓለማችን አይታውና ሰምታው በማታውቀው የዕብደትና የሥነ አእምሮ ደዌ ተለክፈው ይይዙትንና ይለቁትን አጥተዋልና በቅርብ ጊዜ ውስጥ ወደመጡበት ሲዖላቸው ይሸኛሉ፡፡

ትግሬዎች አትንካቸው እንጂ እንድትኖር ይፈቅዱልህ ነበር፡፡ ከነሱ አትብለጥ እንጂ ፍርፋሪ ሥልጣንም ሆነ የተወሰነ ሀብት ቢኖርህ ጉዳያቸው አልነበረም፡፡ ብልጦች ነበሩ፡፡ በብልጠታቸውም ላይ የተወሰነ ብልኅነት ነበራቸው አሁን ዞሬ ሳስበው ነው ታዲያ፡፡ እነዚህኞቹ ግን ከምኑም ከምኑም ያልታደሉ ድኩማን ናቸው፡፡ ኃጢኣታችንና ክፋታችን ያመጣብን በሰው ቅርጽ የመጡ አጋንንት ናቸው፡፡

ተመልከት፤ አንድ አካል ካላበደ በስተቀር አንድን ማኅበረሰብ አጥፍቼ የራሴን የቅዠት ሀገር እመሠርታለሁ ብሎ አይነሳም፡፡ አንድ ሰው ሀገር ምድሩ በችጋርና በችግር እየተቆላ፣ በሰው ሠራሽ ጦርነት እየታመሰ፣ በኑሮ ውድነት እየተንገበገበ፣ በዘር ፖለቲካ እየታመሰ … ይህን ሁሉ ችግር የፈጠረው ግለሰብም እንበለው ቡድን ከመሬት ተነስቶ ሚሊዮኖችን እያፈናቀለና ቤት አልባ እያደረገ በሌለ በጀት በትሪሊዮን ብር የሚገመት ቤተ መንግሥት እሠራለሁ ብሎ አይነሳም፡፡ ይህን ድርጊት በዕብደት ብቻ መግለጽ ራሱ በቂ አይደለም - ሌላ አዲስ ቃል መፈጠር አለበት፡፡ ከአእምሮ በላይ ነው፡፡

ለዚህ ቤተ መንግሥት መሥሪያ ተብሎ ከድሃ ዜጎች በግብርና በቀረጥ የሚዘረፈው አንሶ አሁን ደግሞ በንብረት ታክስ ለማያዝበት የመኖሪያ ቤት፣ ንብረቱ ላልሆነ የመንግሥት ሀብት ቀረጥ ክፈል ተብሎ ሕዝቡ ያለ የሌለ አንጡራ ሀብቱን እየተገፈገፈ ነው፡፡ ለዚያውም በራሱ ፈቃድ ሌሊት ሳይቀር ወረፋ እየያዘ የሚከፍለውን ሰው ስታይ ኢትዮጵያውያንን ምን ነካቸው፣ ምንስ አስነኳቸው ብለህ ትጨነቃለህ፡፡ ለአንዲት ደሳሳ ጎጆ ከሃያ ሽህ ያላነሰ ብር በዓመት ይጠይቃሉ፡፡ ሕዝቡም እየከፈለ ነው፡፡ ዕንቆቅልሽ ሕዝብ ማለት የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው፡፡ የሚበላው ቢያጣ ለመንግሥት የሚከፍለው አያጣም፡፡

አዲስ አበባ እያበደች ነው፡፡ ቲማቲም መቶ ብርን እየታከከ ነው፡፡ ነጭ ሽንኩርት እንደቡናው ከ300 ብር አልፏል - አይቀመስም፡፡ ቀይ ሽንኩርትም ብር 80 እና ከዚያ በላይ ነው፡፡ ነገሩ ሆን ተብሎ አዲስ አበቤን የማሳበድ ሥራ እየተሠራ ነው፡፡ እንደሰማሁት አንድ አትክልት ይዞ የሚገባ የጭነት መኪና መንገዱን እንዲያልፍ ለኦነግ ሸኔ በመቶ ሽዎች የሚቆጠር ብር ይከፍላል አሉ፡፡ ያን የከፈለውን  ለማወራረድ ታዲያ ዕቃው ላይ ይከምሩበታል - ለዚያውም ለማለፍ ከተፈቀደለት፤ አለበለዚያም ከፍሎም ዕቃው ላይሰጠው ይችላል - በተለይ አማራ ከሆነ፡፡

እናም በ5 ብር የገዙትን አትክልት አዲስ አበባ ሲገባ ዋጋው ሰማይን ያልፋል፡፡ በነገራችን ላይ ሰው ብቻ ሳይሆን ዕቃም እየታገተ ከፍተኛ ገንዘብ እየተጠየቀበት ነው፡፡ የሰሞኑን የሹፌሮች እገታ ግን አንድዬ ይግባበት - የሚጠየቅባቸውም በሰው አንድ ሚሊዮን ብር ነው፡፡ እግዜር ይግባበት የምለው ከልምድ በመነሳት የተጠየቀው ገንዘብ ቢከፈልም እንኳን የመትረፍ ዕድላቸው አነስተኛ በመሆኑ ነው፡፡ የስኳር ፋብሪካዎችም በአቢይና ሽመልስ ይሁንታ በሸኔ ተይዘዋል፡፡

ቀድመን ተናግረናል፡፡ የተናገርነው እየሆነ ሲታይ መደመም ብቻ ነው፡፡ አማራም ሆነ ሌላው ዜጋ ከእንግዲህ በአዲስ አበባ መኖር አይችልም፡፡ እንኳን አዲስ አበባ በወያኔ ተሰፍሮና ተለክቶ በተሰጠው ክልል ተብዬ አካባቢም መኖር እንዳይችል ጨፌ ኦሮምያ ወስኖ ኦነግ ሸኔ እየተላከበት ነው፡፡ ብአዴን የተባለው መጋጃም የኦነግ ተባባሪ ነው፡፡ ለርሱ መላ ካልተፈለገለት የአማራ መጨፍጨፍ በቀላሉ አይቆምም፤ ነጻነትም ከሦስት ወር ባለፈ ሊዘገይ ይችላል፡፡

በዚህ አጋጣሚ አማራ ሆኖና አማራን በማንኛውም ረገድ ወክሎ እያለ ለኦሮሙማ አድሮ ይህን የዋህና ቅን ሕዝብ የሚያስጨፈጭፍ አማራም ሆነ ሌላ ዜጋ ጥቁር ውሻ ይውለድ ማለት እፈልጋለሁ፡፡ ሁሉም በሠራው ልክ እንደሚከፈለው ብረዳም አማራን እወክላለሁ ብሎ አማራን ለጭዳነት እንደሚዳርግ ሆዳምና ኅሊናቢስ ሰው በንዴት የሚያጨሰኝ የለም፡፡ እርግጥ ነው - ክርስቶስን የሸጠው የራሱ ወገንና እንዲያውም የራሱ ደቀ መዝሙር ይሁዳ ነው፡፡ ይሄ ሆድ የሚሉት ትንግርተኛ ነገር ሰውን የማያደርገው የለምና እነደመቀ መኮንንንና አገኘሁ ተሻገርን፣ ሰማ ጥሩነህንና ተመስገን ጥሩነህን ባሪያ ቢያደርጋቸው ከዕውቀታቸው ማነስም አኳያ ብዙም አይፈረድባቸውም፡፡ ግን መሽቶባቸዋል፡፡ በወደዱት ቆርበዋልና በቆረቡት ሰይጣናዊ ሥጋ ወደሙ ሊኮነኑበት የፍርድ ሚዛኑ አጠገባቸው ደርሷል፡፡

ለማንኛውም አማራው እንዳያርስም፣ እንዳይነግድም፣ ተዘዋውሮ ባመቸው ሥፍራ በገዛ ሀገሩ እንዳይኖርም ከተደረገ ቆዬ፡፡ አማራ ሸገር ከሚባለው የምናብ ከተማ ሲባረር ለቤቱ ማፍረሻ ብር ከፍሎ፣ እምቢ ካለም ከነሚስትና ልጆቹ ተገድሎ፣ ሀብት ንብረቱንና ቆርቆሮውን ሳይቀር በአፍራሾቹ ተዘርፎ፣ ባካባቢው ልከራይ ቢል ተከልክሎና ላከራይ የሚል ኦሮሞ ቢኖር እንኳን በብርና በእሥራት ተቀጥቶ፣ … ብዙ ነው ታሪኩ ወገኖቼ - ሲዖላዊ ሕይወት እየገፋ ነው አሁን የሚገኘው፡፡ የዚህን ሁሉ ግፍና በደል የዞረ ድምር ማን እንደሚከፍል የሚተርፍ ያየዋል፡፡ ወንድሞቼ ኦነግ አሁን በርትቷል፤ እሽቅንድር አድርጎታል፡፡ ሽመልስ አብዲሣም የሚያደርገውን ብቻ ሳይሆን የሚናገረውንም አሳጥቶታል፡፡ ሲሻው ሶፍት ያድለናል፤ ሲሻው “ገና ምን አይታችሁ! በመቶ ሽዎች የሚገመቱ ቤቶችን እናፈርሳለን!” እያለ ያስፈራራናል፡፡ ከተራበ ለጠገበ መታዘኑ ለዚህ ነው፡፡ እኛ ርሀባችንን ስንችል እነሱ ጥጋባቸውን መቻል አቃታቸው - እንደዘመናዊው አገላለጽ - ጥሩ አማርኛ!! ወይ ኦሮሙማ፡፡ ጥላቻ እንዲህ ያሳብዳል? ብለው ብለው እኮ “ህጋዊ ድሃ” የሚል ዘዬ ፈጥረው በ“ቋንቋ ዕድገት”ም እያስደመሙን ነው፡፡

ልብ በል፡፡ አማራ በአዲስ አበባ መኖር ከተከለከለ አምስት ዓመታትን አስቆጠረ፡፡ አሁን እየኖሩ ያሉ አማሮችም በገንዘብ ኃይል እንጂ ደልቷቸው አይደለም፡፡ ይህም ዕድል በቅርቡ ይጠፋል፡፡ አማራ ከሆንክ አዲስ አበባ ውስጥ መነገድም ሆነ በመንግሥት መሥሪያ ቤት ሠርተህ መኖር አትችልም፡፡ ጉሊትና የሸቀጥ መደብሮች ሁሉ እየፈራረሱ ነው፡፡ የሳጠራና የሸራ ቤቶች ሁሉ እየፈረሱ ውድማ ሆነዋል - ፒያሣን እይ ለምሣሌ፡፡ እነዚያ ለአራዳ ክፍለ ከተማ ውብ ጌጥ የነበሩ መነጽር ቤቶች ዛሬ ፈራርሰው በረሃ መስለዋል፡፡ ለምን ሲባል አንድ የኦነግ ባለሥልጣን ቋንቋም እንደካልሲ አጥሮት “በሸራ ቤቶች ውስጥ የጦር መሣሪያ ለማግኘት ሞክረናል” ሲል እንዳሳቀን ሁሉ በየአርከበ ሱቆቹ ውስጥ ታንክና መትረየስ እየተገኘ የአማራ ጸንፈኛ ህገ መንግሥቱን በኃይል ለመናድ ሙከራ ሲያደርግ የተደረሰበት ሁኔታ ተፈጥሮ ነው የሚገኝ፡፡  ጉድ ነው ኦነግና ኦሮሙማ የሚያሳዩን ድራማ፡፡ በማከያው ግን አዲስ አበባ ውስጥ በተለይ ቀምሶ የሚያድር ሰው በጣት የሚቆጠር ሊሆን ጥቂት ጊዜ ብቻ ይቀራል፡፡ ሁሉም ወደ ድህነት እየተገፋ ነው፡፡

አዲስ አበባ አሁን ያለች ትመስላለች፡፡ ግን የለችም፡፡ ኦሮሙማ እንዳሻው የሚፈነጭባት ካምሱሯ የተቀጣጠለ ባግዳድና ደማስቆ ናት - ያኔ ዱሮ በሰላማዊነቷ ዓለም የሚያውቃት አዲስ አበባ፡፡ ማን እንደሚተርፍ ልናይ ነው - ፈጣሪ በፀጋው የሚሸፍናቸው ነገን ያያሉ፡፡ አማራው ግን በርታ፡፡ በቅድሚያ ታዲያ ቤትህን አጽዳ፡፡ ጓዳ ጎድጓዳህን ከመዥገሮችና ከነቀዞች ሳታጸዳ ትግል ብትጀምር በቀላሉ ስኬታማ አትሆንም፤ ብዙ ዋጋ ትከፍላለህ፡፡ ድሉ ያንተው ነው - በዚህ ጥርጥር አይግባህ፡፡ ግን መጠንቀቅ ያለብህ ከራስህ ጉዶችና ከድል አጥቢያ አርበኞች ነው፡፡ ሁሉንም መናገር አይገባኝም፡፡ ትግሉ ከአስመሳዮች፣ ከሌሊት ወፎችና ከእስስቶች፣ ከጅቦች፣ ከተኩላና ቀበሮዎች ከዓሣማዎች ነጻ ከሆነ በአጭር ጊዜ ውስጥ ኢትዮጵያን ከመፈራረስ አማራንም ከተደገሰለት ዓለም አቀፍ የጥፋት ዐዋጅ መታደግ ይቻላል፡፡

እዚህ ላይ ሳልጠቅሰው ማለፍ የሌለብኝ ነጥብ አለ፡፡ እሱም የሃይማኖት ጉዳይ ነው፡፡ ለኢትዮጵያ ጥፋት ከዋና ግብኣትነት ባልተናነሰ ኦርቶዶክስ ውስጥ የተሰገሰጉ የአጋንንት ወኪሎች ትልቅ ሚና አላቸው፡፡ ይሄ በሁለት ቢላዎ የሚበላ የሃይማኖት አባት ነኝ የሚል ሁሉ ሊጸዳ ጥቂት ጊዜ ቢቀረውም እየሠራው ያለው ደባ ግን መታወቅ አለበት፡፡ ሃይማኖታችን በማን እንደተያዘ እናውቃለን - በአለባበስና በአነጋገር አንታለልምና የውስጡን ለቄስ አባቶችን ገመና የማናውቅ ከመሰላቸው ተሳስተዋል፡፡ ደመወዝ ብዙ ይናገራል፤ የኑሮ ዘይቤ ብዙ ይናገራል፤ የሰውነት አቋም ብዙ ይናገራል፡፡ አካባቢና ጎረቤት ብዙ ያውቃል፡፡  ከቫቲካን እስከ እስክንድርያና እስከ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሣጥናኤል እንደተቆጣጠረ ከግምት ባለፈ እናውቃለን፡፡ ብዙ ምሣሌ መጥቀስ ቢቻልም ደብረ ኤልያስ ገዳም አንድ መነኩሴ እስኪቀር ሲደበደብና ንዋየ ቅድሳት ሲዘረፉ፣ ሲቃጠሉና ሲወድሙ አንድም የሲኖዶስ አባልና ሲኖዶሱም ራሱ ትንፍሽ አላሉም፡፡

ይህ የሚጠቁመን ሃይማኖቱም በዓለማውያን ቁጥጥር ሥር እንደሚገኝ እንጂ አንድ ጴጥሮስና አንድ ተክለ ሃይማኖት ቢኖሩን ኖሮ ይሄኔ የተወሰነ ለውጥ ማየት እንችል እንደነበር መገመት አይቸግርም፡፡ ስለዚህ ቤተ መንግሥቱ ብቻ ሳይሆን ቤተ እምነቱም መጽዳቱ የሚጠበቅ ነው - ሁሉንም የተቆጣጠረው አንድ ኃይል ነውና፡፡ በተለይ ስለሃይማኖቱ የተናገርኩት በጣም ትንሽ መሆኑን እንድትረዱልኝ እፈልጋለሁ፡፡

 

 

Thursday, June 22, 2023

ለትውስታችሁ አማራውን ለማግለል አብይ የሄደበት ግልጽ ስበሰባ ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay) 6/22/2023


ለትውስታችሁ አማራውን ለማግለል አብይ የሄደበት ግልጽ ስበሰባ 

ጌታቸው ረዳ

(Ethiopian Semay)

6/22/2023

ሰነዱ የተገኘው ከታሪክ ተመራማሪና የምጣኔ ሃብት ምሁር አቻምየለህ ታምሩ ነው።

ይህ ሰነድ እንድታስታውሱት በሚል ነው፤ በማሕደራችሁ ለታሪክ ማስታወሻ አስቀምጡት።

አፓርታይዱ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ትክለኛ ገጽታ!

(አቻምየለህ ታምሩ)

የአገሪቱ ከፍተኛው ባለሥልጣን ጠቅላይ ሚንስትሩ የተገኘበት ይህ መድረክ የኢትዮጵያ እጣ ፈንታ ከሚወሰንባቸው መድረኮች አንዱ ነው። በዚህ የኢትዮጵያ እጣ ፈንታ ከሚወሰንባቸው መድረኮች አንዱ በሆነው «የለውጥ» ጉባኤ የኢትዮጵያን ሕዝብ ሰባ ከመቶ በላይ የሚሆነውን ከሚሸፍኑት ሁለት ነገዶች አንዱ የሆነው አማራ ግን አልተወከለም ወይንም ባለጊዜዎቹ እንዲወከል አልፈለጉም ። ይህ በአጋጣሚ የተደረገ አይደለም! ይህ አማራን ማግለል የኢትዮጵያ ፖለቲካ ትክክለኛ ገጽታ ነው። ላለፉት ሀያ ሰባት ዓመታት የኖርነው ልክ በፎቶው ላይ እንደሚታየው በኢትዮጵያ እጣ ፈንታ እንዳንሳተፍ ተቀሟዊ በሆነ መልኩ ተገለንና መንግሥታዊ እግድ ተጥሎብን ነው። የኢትዮጵያ ፖለቲካ የአፓርታይድ ፖለቲካ ስለመሆኑ ከዚህ በላይ ማሳያ ሊቀርብ አይችልም!

«ለውጡን እናግዝ» የሚሉን ሰዎች እናግዝ እያሉን ያለው ይህንን አማራ መቶ በመቶ ከጨዋታ ውጭ የተደረገበትን ሴራ ነው። ተጀመረ የሚሉን የለውጥ ሂደት እንዳይደናቀፍ አግዙ እየተባልን ያለነው አማራን እንዲህ እያገለሉና እንዲገለል እያደረጉ ከአማራ የጸዳ አካባቢ ለመመስረት እንደተንቀሳቀሱ ሁሉ የኢትዮጵያን ፖለቲካ ከአማራ ለማጽዳት እያደረጉት ያለውን የአፓርታይድ ተግባር ነው።

ከአማራው መካከል የወጡ የሌሎች ጉዳይ ፈጻሚዎችም በውጭም በውስጥም ሆነው ለአማራ አንዳች ነገር ጠብ ያለለት ይመስል «ለውጡን እናግዝ» በማለት ከአማራ አንጻር የቆሙ የአፓርታይድ አራማጆችን እያገለገሉ ያሉት አማራው ተጠናክሮ እንዳይደራጅ ማደንዘዝንና በላዩ ላይ የተጫነውም የአፓራይድ አገዛዝ አማራው መቶ በመቶ እ እንዲህ እያገለለ የሚያካሂደውን ፋሽዝም እንደለውጥ ቆጥረውት ነው።

እስቲ የተጀመረው የለውጥ ሂደት እንዳይደናቀድ አግዙ ስትሉ የምትውሉ ለአማራው የትኛውን ነው ለውጡ? ከታች የምታዩዋቸው ስድስቱ ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ ከዛሬ ሀያ ሰባት ዓመታት በፊት በሐምሌ 1983 ዓ.ም. በወያኔ፣ በሻዕብያና ኦነግ አጋፋሪነት አማራን አግልለው በኢትዮጵያ ምድር ሰላምንም ዲሞክራሲንም ለመቅበር በአፍሪካ አዳራሽ በተካሄደው «የሰላምና ዲሞክራሲ» ኮንፍረንስ በአንድም በሌላው መንገድ ተሳታፊዎች ነበሩ አልያም ወኪሎቻቸው ተሳትፈዋል። ከሀያ ሰባት ዓመታት በፊት ዋና ተዋናይ የነበረው ሻዕብያ በዚህ መድረክ ባይገኝም በኢትዮጵያ ጉዳይ ወሳኝ ሁኖ «ጠረጴዋው» ላይ ግን ዛሬም አለ። ዶክተር ብርሃኑም ቢሆን ከሀያ ሰባት ዓመታት በፊት የሽግግር መንግሥት ተብዮው ኮንፍረንስ ተሳታፊና ታዛቢ የነበረው የጉራጌ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ግንባር አባል ነበር።

ዛሬ የጎደለው መለስ ዜናዊ በአካል አለመኖሩና ከ27 ዓመታት በፊት በአምስት ድርጅቶች የተወከለው ኦሮሞ ዛሬ በሶስት ድርጅቶች መወከሉ ብቻ ነው። ሰዎቹ ኢትዮጵያን ቢወክሎ ጥያቄ ባልተነሳባቸው ነበር። ሆኖም ሰዎቹ የወከሉት ኢትዮጵያን ሳይሆን ነገዳቸውን ብቻ ነውና የተቀረው ነገድ በነሱ ውስጥ ራሱን ባያይ አይፈረድበትም።

ዛሬም፣ ከሀያ ሰባት ዓመታት በፊትም ሁለት ተመሳሳይ ነገሮች ይታያሉ። አንዱ መለስ በአካል ባይኖርም የራዕዩን ተሸካሚዎች መድረኩ ከጫፍ እስከጫፍ መሙላታቸው ነው። ሁለተኛው ደግሞ ዛሬም ከሀያ ሰባት ዓመታት በፊትም አማራው በመድረኩ አለመኖሩ ነው። ከሀያ ሰባት ዓመታት በፊት በአማራ ጥላቻ የናወዙት እነዚህ ስድስቱ ግለሰቦች ወይንም ወኪሎቻቸው አማራ እንዳይገኝ አድርገው ከፕሮግራማቸው በማውጣጣት ሕገ መንግሥት ያሉትን የቅሚያና የግድያ ደንብ አዘጋጅተው ነበር። እነሆ ዛሬ ከ27 ዓመታት በኋላ ስድስቱም የ27 ዓመታት የሥራ ውጤታቸውን ለመመረቅ በመድረክ ተገናኝተው ሽር ብትን እያሉ ናቸው።

እነዚህ ስድስቱ ዛሬ ከሀያ ሰባት ዓመታት በኋላ ለውጥ፣ ለውጥ እያሉ ቢሰብኩም የተለየ ውጤት እናመጣለብ ብለው እያታከቱን ያለው ግን አንዳች የመዋቅርና የሕግ ለውጥ ሳያካሂዱ በተመሳሳ መንገድ [በአብዮታዊ ዲሞክራሲ፣ በጎሳ ፌድራሊዝም፣ ሕጋዊነት በሌለው ሕገ መንግሥት፣ ወዘተ] በመሄድ የመንፈስ አባታቸውን የመለስ ዜናዊን ራዕይ እያስቀጠሉ ነው። ዛሬም ችግሩን በፈጠረው አስተሳሰብ እየተመሩ፣ አገዛዙ የተዋቀረበት ርዕዮተ ዓለም ሳይቀይቱና የመዋቅርና የአደረጃጀት ለውጥ ሳያደርጉ የተለየ ውጤት ሊያመጡና አገራዊ ተቋማትን ሊፈጥሩ ያስባሉ!

ደግነቱ ዛሬ ትናንት አይደለም! «ለውጡን እናግዝ» ብለው የተኮለኮሉት የኛዎቹ አደንዛኞችም ሆኑ ባለጉዳዮቻቸው እነ ዐቢይ ባይፈልጉትም የአፓርያድ አገዛዝ የወለደው አማራው ግን በሚገርም ፍጥነት ራሱን ለመታደግ በአንድ ላይ ተነስቷል፡፡ ካሁን በኋላ እንደ ሰማንያ ሶስቱ የፋሲካ ዶሮ ለመሆን ለዳግም እርድ የሚዘጋጅ አማራ የለም! የአገሩና የመንግሥት ባለቤት እስኪሆን ድረስ የጀመረውን የኅልውና ተጋድሎ ያለርሕራሔ ይቀጥላል::

Posted Ethiopian Semay – Source File –Achamyeleh Tamiru

 

Wednesday, June 14, 2023

ብዙ አካለ ስንኩል ወጣት የያዘቺው ትግራይና በባዶ ካዝና እየተራመደ ያለው አፓርታይዱ ኦሮሙማው መንግሥት ጌታቸው ረዳ (EEthiopian Semay 6/14/2023

 

ብዙ አካለ ስንኩል ወጣት የያዘቺው ትግራይና በባዶ ካዝና እየተራመደ ያለው አፓርታይዱ ኦሮሙማው መንግሥት

ጌታቸው ረዳ

(EEthiopian Semay

6/14/2023

ኢትዮጵያ እንደሃገር ሳይሆን የከሸፈች ሃገር (ፈይልድ ስቴት) ሆናለች። ከሆነችም ቆይታለች (በዚህ ርዕስ ብዙ፤ብዙ ብለናል) በዚያ ምክንያትም ነበር የአማራው ወጣትና ምሁር ክፍል ሕዝባቸውና እራሳቸውን ከተነጣጠረባቸው የዘር ማጥፋት ዘመቻ ለመከላከልና ብሎም ለማስቆም ራሳቸውን ቶሎ ነፃ ማውጣት አለባቸው ስንል የነበርነው።

በከፊልወድዶ ሳይሆንመሆን እንዳለበት የጠበቅነው ሕዝባዊ ማዕበል እንኳ ባይሆንም ተገድዶ የአልሞት ባይ ተጋዳይ በትንሹም ቢሆን የሽምቅ ውግያውብሎ ጀምሮታል፡ እንዲበረታበትም እንመክራለን።

አገርን ማስተዳዳር ችሎታ የሌለው በባዶ ካዝና እየተንከላወሰ የዕርዳታ ስንዴ እየሸጠ በመተዳዳር ላይ ያለው ማፈሪያው አብይ አሕመድ ኢትዮጵያን በማፍረስ ሂደት የአምበሳው ድርሻ በመውሰድ ከወያኔ ትግሬዎች ጋር ወዳጀነት ግምባር ገጥመው አማራን ለማጥፋት በተናጠልና በጋራ ዛሬም ተቀናጅተው ቀጥለውበታል።

በዘርና አገር በማፍረስ ተጠያቂ የሆነው መለስ ዜናዊን የተካ ሚሳይል ወደ ተተኮሰባት ምድር ባሕርዳር እንዲጎበኝና ፡እንዲሁም የኦሮሙማ አህዮችን የሚሸከመውቂሉ ማሞንየተካው ይልቃል የተባለውጌኞመቀሌን እንዲገበኝ በአለቃቸው አብይ አሕመድ ትዕዛዝ በታዘዙት መሰረት ሁለቱም ስለ ወልቃይትና ራያ ወደ ትግራይ የማዋሃድ ስምምነት አውን ለማድረግ በሁለት አቅጣጫ ጦርነት የመከፍት ጥናት ለመነጋጋር እንደሆነ ግልጽ ነው።

ስለ አብይ አሕመድ ሁላችሁም ስለምታውቁት ብዙ አልሄድበትም። ይልቅኑ ውስጥ ለውስጥ ምን እየተካሄደ እንዳለ ትግርኛ ለማታደምጡ ወገኖች እንድታውቁ ባጭሩ ላብራራ፡

ትግሬዎች ለመገንጠል ሦስት ሂደቶችን እያሳኩ ነው።

1- ሊሂቃን ስለመገንጠል ተከታታይ ስብሰባ እያደረጉ ይገኛሉ

2- የወያኔ ጳጳሳትና ቀሳውስት ተዋህዶ ቤተክርሰትያንን በማፍረስ ከማኣከላዊው ሲኖዶስ በመነጠል  የትግራይ ሪፑብሊክ ሃገረ ስብከትበይፋዊ አዋጅ ተነጥለው መስረተዋል።አዲስ አባባ ውስጥ የተቀመጡት በጳጳስነት ወንበር የተሾሙት አባ ማትያስ በዚህ ሴራ ላይ በግላቸውም ሆነ በሲኖዶሱ በኩል ያሉት ነገር እንደሌለ ነው እስካሁንዋ ደቂቃ ድረስ የማውቀው።

3- ጌታቸው ረዳ፤ በሚመራው መንግሥትፈራ ተባእያለ ለትጥቅ ትግል በመጠባበቅ ላይ ያለውውስጥ ለውስጥበመደራጀት ላይ ላለው ለአንጃው የሽምቅ ፓርቲ የውስጥ እገዛ ለመስጠት ያለው ገጽታ ሦስቱን እንመለከታለን።

“Undoubtedly, war is the greatest source of the evils which oppress civilized nations. Not so much actually war, but rather the never-ceasing and indeed ever increasing preparation for a future war.” Page 66 (Kant on History) published by the Library of Liberal arts) ይላል ፈላስፋውካንትይህንን በራሴ ልተርጉመው፡ እንዲህ ይላል።

"ጦርነት የሰለጠኑ ሀገራትን የሚያወድም የክፋት ምንጭ መሆኑ አያጠያይቅም። ክፋቱጦርነትሳይሆን የማያቋርጥ እና ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ላለው የጦርነት ዝግጅት ይበልጥኑ አሳሳቢነቱ የላቀ ያደርገዋል።" ገጽ 66 (ካንት  በታሪክ ላይ”) በሊበራል አርትስ ቤተ መጻሕፍት የታተመ ትንሽየ መጽሐፍ)

ጦርነት የክፋቶቹ ሁሉ የክፋት ምንጭ ነው ሲል አውዳሚነቱን እየገለጸ ነው። የወያኔ ትግሬዎች በከፈቱት ጦርነትና አብይ አህመድ በሴራ በተባባራቸው የጦርነት አውድ ላይ ባለፈው ሁለት አማታት ውስጥ በሚሊዮኖች ወጣት ትግሬዎችና ኢትዮጵያዊያን አካለስንኩል እና ሙት ወይንም መፈናቀልና የሕሊና በሽተኛ እንዲሆን አድርገዋል። ለዚያ ሁሉ ወንጀል ዛሬም ተጠያቂ የለም። ስለሆነም ዛሬም ሁለቱ በሴራ ተስማምተው ያልጨረሱትን አማራን የማጥፋት አጀንዳቸው ዛሬም ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ናዚዎች በአውሮጳ አይሁዶች ላይ እንዳወጁትየፋይናል ሶሊሽንየዘር ማጥፋት ዘመቻቸው ጀምረውታል።

 ብዙ አካለ ስንኩል ወጣት የያዘቺው ትግራይ ክፍለሃገር ወዴት እየተጓዘች ነው? የሚለውን ላወያያችሁ። ከላይ የጠቀስኳቸው ሦሰት ነጥቦች እንመልከት።

የጌታቸው ረዳና የይልቃል ወደ ባሕርዳርና መቀሌ የመጎብኘት ትዕይንትን በሚመለከት፡

ሚሳይል የተኮሰባት ባሕርዳርን እያስተዳደሩ ያሉት የኦሮሙማ እልፍ አስከልካይብአዴኖችወልቃይትና ራያን ወደ ትግራይ ለማስረከብ በሁለቱ አቅጣጫ የሚካሄድ የጦርነት ሰልት ለመንደፍ እንደሆነ የውስጥ አዋቂ ምንጭ አያስፈልግም (ግልጽ ነው)

ምክንያቱም እነ ጌታቸው ረዳ በጉጉት እየጠበቁት ያሉት ወልቃይት የውጭ አገር መውጫ በር ካገኙ ሳይውሉ ሳያድሩ በፕሪቶርያው ስምምነቱ መሰረት (ማሃይምዋ አበበች አዳኔ እንዳለቺው መገንጠልን የሚከለክላቸው ስለማይኖር)  ሕዝብ ሰብስበው የመገንጠል ሪፈረንደም የማካሄድ መብት እንዳለቸው ተፈራርመው ስላሉ ያንን ለማካሄድ ከአብይ አሕመድየገዳይነት የምሰክር ወረቀትተሸላሚ የሆኑትን ቡዱኖች ይዞ ባሕርዳር ላይ ይገኛል።

የትግራይ ሊሂቃኖችም ሰሞኑን በተከታታይትግራይ የት ላይ ቆማለች? እያሉ ከሕልማቸው በድንገት የተሰወረችባቸውን ትግራይበዳሰሳላይ ናቸው።

ሰሞኑን መቀሌ ውስጥ ሁለት ትዕይነቶች ታዝቤአለሁ።

1ኛው ስብሰባ ከህጻንነተቻው ዕድሜ ጀምሮ ኢትዮጵያንና አማራን በመጥላት በየትምህርት ቤቶቻቸው የጥላቻ ትምህርት እየተጋቱ 27 አመት ያደጉ ጎረምሶችና እንዲሁም የድሮ የወያኔ ታጋዮች ትግራይ ከኤርትራ ወይስ ኢትዮጵያ ጋር መዋሃድ የሚልቅዠትውስጥ ገብተው መቀሌ ባንድ አዳራሽ ውስጥ በመሰብሰብ አገር በማፍረስሴራላይ ሲተነትኑ ቱብላይ አድመጠናል።

ይህ ቡድን ማሕበረሰቡን በፕሮፓጋንዳ እያጠበ ለማይቀረው የግንጣላ ጦርነት ለዳግም የሕሊና ዝግጅት በማካሄድ ላይ ነው።

2ኛው ሴራ የትግራይ የወያኔ ጳጳሳትና ቀሳውስት ውሳኔ ነው።

ሰሞኑን ከሕግ ውጭ ከዋናው ሲኖዶስ በመነጠል ኢትዮጵያ የምትባል አገር የትግራይ ቅኝ ገዢ ነችና አናውቃትም ብለው አዋጅ በማስነገር ከወሰኑዋቸው ውሳኔዎች ውስጥኢትዮጵያየሚል ቃል ከእምነት ማሕደሮችና ቤተክርትያን ተቋማት እንዲሰረዝ በማድረግ በመጽሐፍ ቅዱስም ሆኑ ሃይማኖታዊ መጻሕፍት እንደገና እየተጣሉ ወይንም እየተሰረዙ በምትኩትግራይበሚል ቃል ተተክተው ለአዲስ ሕትመት እንደሚዘጋጁ ሳያመነታ ገልጸዋል፡ (ይህ የታሪክ፤የቅርስ፤ የጽሑፎች፤የሃውልት፤የመንገዶች ስም ስረዛና ድለዛ በወያኔዎች የተጀመረ ቢሆንም ሃይማኖት መሪዎች ነን የሚሉ ካድሬ ቀሳውስት እየሰሩት ያለው ግን ከፍተኛ ወንጀል መሆኑን በዓለም ውስጥ በታሪክ አዋቂነቱና መምህርነቱ የታወቀው ሟቹ Eric Hobsbawm “The Age of Extremes 1914-1991”  በተባለው መጽሐፉ ወንጀል መሆኑን ይገልጻል። የኛ የሃይማኖትና የፖለቲካ ወንበዴዎች ግን ነባር ቅሪቶችንና ስሞችን በመለወጥ ወንጀል በመስራት ማሃይምነታዊ ድፍረታቸውን ሲገልጹ እናያቸዋለን።

 አማርኛ የሚባል ቋንቋና ኢትዮጵያ የሚል ቃል ጭራሽ እንዳይደመጥ በሙሉ ተስማምተዋል። የትግራይ ሪፑብሊክ ተዋህዶ ቤተክርስትያን በሚል እየተዘጋጀ ያለው ኢሕጋዊ አገራዊ ግንጠላየወያኔ ፖለቲካዊ የሃይማኖት ክንፍ በመሆን 1968 . ጀምሮ  በወያኔዎች የሚታዘዝበእነ ደብረጽዮን እና በእነ ጌታቸው  ረዳበውስጥ አበራታችነት እየተከናወነ ያለሁለተኛው ረድፍአገር የማፍረስ ሴራ ነው።

እነዚህ የትግራይ ጳጳሳትና ቀሳውስት ኢትዮጵያን ስያስወግዱ ኢትዮጵያ የምታቀርበው የባንክ፤የስልክ፤ የገንዘብ፤ የሸቀጥ፤የመብራትና መድሃኖቶችና ሆስፒታሎች፤ የመገናኛ አውታሮች፤ ነዳጆች እንዳይታገዱ የመጠቀም መብት እንዲኖራቸው፤ በእነ ጌታቸው ረዳና በአብይ አሕመድ ፈቃጅነት ዛሬም ኢትዮጵያን እየጠሉ ምርትዋን እንዲጠቀሙ እየተደረገ ነው (አገር ወዳድ ተጋሩ የኔን ዘመቻ ሰምታችሁ እገዳ እንዲደረግባቸው ተቃውሞአችሁን እንዳተስተጋቡ ጥሪ አቀርባለሁ፤መንግስት ቢኖር ነው ግን!!”)

አሁን ያለው መሪ አገር ወዳድ ቢሆን ኖሮ ወይንም እኔ መሪ ብሆን ኖሮ  አገልግሎት እንዳያገኙ በሕግ እንዲታገዱ አደርግ ነበር። (እናንተ ምን እንደምትሉ ባላውቅም እውነታው ግን እየሆነ ያለው አሁንም የኢትዮጵያ ምርትና አገልግሎት ልክ እንደ ሕዝቡ  እኩል አግልገሎት እያገኙ ነው።)

3ኛው በዚህ ጽሑፌን ልደምድም።

ጌታቸው ረዳና አንጃው ጦረኛ የድብቅ ሴራቸው፡

ጌታቸው ረዳ፤ በሚመራው መንግሥትፈራ ተባእያለ በመጠባበቅ ላይ ያለውውስጥ ለውስጥበመደራጀት ላይ ላለው ለአንጃው የሽምቅ ፓርቲ የውስጥ እገዛ ለመስጠት ያለው ገጽታ ገልጬ ልደምድም።

ሰዎች ይህንን ሴራ አያውቁም የሚል ግምት አለኝ። ታስታውሱ ከሆነ ካሁን በፊት November 16, 2022 

የትግሬዎች ፎኒክሲዝምበጻፍኩት ሐተታ ላይ እንዲህ ጽፌ ነበር።

ትግርኛውን ልጀምር << ሞይትና ዘይንሞት ሓመድ ልሒስና ዝተሳእና

ዓለም ዘገረምና

መስተንክር አፋጣጥራና >>

ሞተን እንደገና በዳግም ልደት አመድ ልሰን የተነሳን!

ዓለምን ያስገረመ መስተንክር ስነ አፈጣጠራችን!

ትናንትም ዛሬም አስገራሚ ልዩ ፍጡሮች ነን!!

እያሉ በንግግራቸውም ሆነ በሙዚቃዎቻቸው የሚያስተጋቡት የፎኒክስዋ ታሪክ 99% ትግሬዎች የፎኒክስዋ ዳግም ልደትና የትግሬዎች ዳግምአመድ ልሰን የተነሳንቅቡልነት የመፈክራቸው ተመሳሳይነት በዚህ 3 አመት በጆሯችሁና በዓይናችሁ ያያችሁትና ያደመጣችሁት አጋጣሚ ነው።ብየ ነበር።

 በመቀጠልም የፕሪቶሪያ ስምምነት ተብየው ከተፈራረሙ ማግስት ብዙ ሰውሲደሰትእኔ ተቃውሜ ነበር። በዚህም ጽሑፍ November 2, 2022

<< ከዚህ በኋላስ ወዴት? ከዚህ በኋላ ወያኔ ውስጥ ለውስጥ ተዋጊ አንጃ ይፈጥራል>> በማለት በጻፍኩት ጽሑፍ ላይም:-

ሁለቱም ፋሺስቶች መጨረሻ ሕዝብ አስፈጅተውና ፈጅተው አርስበርሳቸው ተቃቅፈው ያለ ምንም ተጠያቂነት ጦርነቱ ይቋጫል ብየ ደጋግሜ ከነሓሴ ጀምሮ ጽፌአለሁ፡ ስንት ሰው እንዳነበበው ባለውቅም እውነታው ይኼው ዛሬ ተፈራረሙ። ሆኖም ችግሩ እስካልተፈታ ድረስ የሁለቱ የፋሺስት ሰላም እንጂ የማሕበረሰባችን ሰላም ሊፈታ አይችልም።በማለት ስጽፍ፡ አስደግፌም እንዲህ ብየ ነበር፡

እንድታውቁልኝ የምፈልገው ወያኔ የሰላም ስምምነት ያድርግ እንጂ ትግራይ ውስጥየትግራይ ሪፑብሊክዓላማ ለማስቀጠል በውጭም በውስጥም ፍላጎት ያላቸው ትግሬዎች ስላሉ ወያኔዎች ቦታውን (ትግራይ ውስጥ) አስተዳደሩን ከተቆጣጠሩት በሗላ አንጃ ለሚፈጠረው ድጋፍ ሰጪ ሆነው ይቀርባሉ ብየ ነበር። ይህንን ዛሬ እውን እየሆነ አዝማሚያው እያየሁ ነው። ያንን ላብራራ።

ከዚያ በፊት ግን ስለ ጌታቸው ረዳ የጻፍኩት April 19, 2022

መቀሌ ዩኒቨርሲቲ የተነገረ የወያኔ ትልቁ ንድፍ

ነፋስ ላይ በአእዋፍ የተሠራች ዩቶፒያ ከተማጌታቻው ረዳ Ethiopian Semay) በሚል የጻፍኩት ላይ የጌታቸው ረዳ ንግግር ልጥቀስ፡

ጌታቸው ረዳ ለግንጣላ ከሚያሴሩት አንዱ ነው፡ በጣም ደብቅ ሴረኛነትና ጮካነት ከወያኔ የቀሰመው ትምህርት ተሎ ቀስሞ ተግባራዊ ካደርጉት አንድ ጌታቸው ነው። መቀሌ ዩኒቨርሲቲ መምህራን ጋብዘውት የተናገረውን በድጋሚ ላስታውሳችሁ እሻለሁ።

እንዲህ ይላል

ብዙ ወዳጆች አሉን፤ ብዙ ነገሮች ውስጥ ለውስጥ ለማምጣት እየሞከርን ነው። እነሱ ይህንን የሚያደርጉልንመለስን ስለሚወዱ እኔን ሰለሚወዱ ወይንም ትግራይን ሕዝብ ስለሚወዱ እንዳይመስላችሁ የትግራይ አገርነት ፍላጎት በመደገፍ የነሱን ፍላጎት ይጠቅመናል ከሚሉት ጋር በማገናዘብ ሊደግፉን እየተንቀሳቀሱ ነው። ለምሳሌ ተከብበናል ስንል በድንገት … (?) ብሎ (ድሮን ?) ለማለትአግኝተናልለማለት ይመስላል::

ሶርያ አግኝታለች” “የመኖች አግኝተዋልበማለት በደፈና ስለ የውጭ ዕርዳታ ምን እንደተሰጣቸው ፍንጭ ሳይሰጥ ስለ የመኖች ሲያወራድሮንእንደተሰጣቸው የሚመስል  ፍንጭንግግር ሲናገር ይደመጣል። (ተረክበናል ከሚላቸው መሳሪያዎች አሁን በርክክብ አልታየም- ምክንያቱም አግኝተናል የሚላቸው ዘመናዊ መሳሪያዎች ደብቀዋቸዋል)

በመቀጥል እንዲህ ይላል፤

ትግራይ እንደ አገር ዓለም እንዲያውቋት የሚገደድበት ስራ መስራት አለብን። ያንን ማድረግ ከቻልንኢን ኤቭሪ እስቴፕ ኦፍ ወይ” (በያንዳንዱ ዘርፍ)ተፈላጊዎች እንሆናለን ማለት ነው። መጀመሪያብሔረ ሃገረ ትግራይለመመስረት አስፈላጊኢንስትቱሽንመስራት አለብን።ሠራዊታችንየዚህ አካባቢጎብለልእንዲሆን ካደረግነው ራሳቸው ይፈልጉናል። Red Sea/ የቀይ ባሕር/ ሃያሎች መሆናችን አሁን እያመኑ ነው። የዚህ አካባቢእስታብሊቲ” (የሰላም ምሰሶዎች) መሆናችን ማየት ጀምረዋል።

ሲል ጌታቸው ረዳ የግንጣለው ሴራ የውጭ ሃይላት እየገፉበትና ወያኔዎችም በዚህ ሴራ እየገፉት እንዳሉ ሳይደብቅ የተናገረውን አስነብቤአችሁ እንደነበር ይታወሳል።

ስለ ሃይማኖቶኞቹ መገንጠል ገልጫለሁ፤ ስለ ሊሂቃኖቹ ገልጫለሁ፤ አሁን ድግሞ ጌታቸው ረዳ እና መሰሎቹ አስተዳዳሩን የተቆጣጠሩበት ዋናው ምክንያት፤ዛሬ በየአዳራሹ ስለ ግንጣላ የሚሰብኩ በርካታ የትግራይ ምሁራን ቅስቀሳው እያካሄዱ ወጣቱን በሕሊና ዝግጅት ለዳግም ጦርነት እያዘጋጁት ሲሆን፤ ከውስጥ እነ ጀነራል ምግበይ እና የመሳሰሉ በወንጀል የተጨማለቁ ወንጀለኞች በየገጠሩ እና አውራጃው እየሄዱ የቆየው ድብቅ የጥርናፈ (የማደራጀት) ስራ በመካሄድ በሰላም ሰበካ ስም እየሄዱ ገጠሬውና ከተሜው እንዲሁም ታጣቂው ውስጥ ለውስጥ ሲሰብኩት ጌታቸው ረዳ ደግሞበሰላም ጡሩምባውአገራዊ ኢትዮጵያዊነት እየሰበከባንኩን ስልኩንና ሸቀጣ ሸቀጦችን ወደ ነበሩበት ደረጃ እንዲያድጉ ካደረገ በኋላ፤፤ እነ ደብረጽዮን እነ መንጆሪኖ እና የመሳሰሉ መሰሪ ወያኔዎችንኣንጃእንዲያዘጋጁ በማድረግ ከጌታቸው ረዳ ወይንም ከመጪው ወያኔዊ አስተዳዳር ጋርበዲሞክራሲ ስምጸብ የፈጠሩ መስለው በረሃ በመውጣት አገራዊ ግንጠላ ለማካሄድ እየተዘአጋጁ ነው።በውስጥ የሽኩቻ ባሕሪ የለም ማለት ግን አይደለም፤ አብሮም ወያኔን ከሚቃወሙ እኔን መሳይ ጥቂቶችም ግፍትና ፍትግያ እንዳለበትም አትዘንጉ። በዛው ላይ አካለ ሰንኩላን ሆነው ባለሰቡት ህይወት የወደቁት እሮሮ ሲጨመር ውጥረቱ የት የሌለ ያደርገውና ምናልባትም ትግራይ በብርት የሚጨራረሱ ሥርኣተ አልባየአናርኪጋንጎች ምድርም ልትሆን ትችል ይሆናል። በተለይ ኤርትራ ኢሳያስ ሞት በኋላ እነዚህ ቡዱኖች የሚኖራቸው ሚና አካባቢው ለውጥርት ይዳርጋል። ይህ የሚሆነው ሁነኛ አገራዊ መንግሥት እንዳሁን ካጣች ሁኔታው ይባባሳል።

ከኢትዮጵያ ሳይገነጠሉ አገሪቷ ለትግራይ ሕዝብ  የምታቀርበውን ሸቀጥና ገንዘብ ትግራይ ውስጥ በውስጥ አባሎችና እራሳቸውም በመዝረፍ 17 አመት ሽምቅ ተዋጊያቸውን እየቀለቡ ለድል ደርሰው እንደነበር ይታወሳል።ግንጠላ ለማካሄድም ዕደል ነበራቸው፡ ምቹ ነበር።

ያኔ ምቹ ሆኖ በድል ሲገቡ ዛሬ ሁሉ ጥንካሬና ብረት ይዘው ለምን ተሸነፉ ብንል፤ ዛሬ ከመአከላዊ መንግሥት ጠቅላላ የባንክ ፤የንግድ የስልክ የገንዘብ ጠቅላላየኑሮ ቧንቧዎችሁሉ ዝግ ስለተደረገ እንኳን ተዋጊው ሕዝቡ ችግር ውስጥ በመግባቱ ተዋጊዎቻቸው የሚቀልቡበት መንገድ ስላልነበራቸው በቀላሉ ተከብበው ተሸነፈዋል።

በለመሳካቱ ምክንያቱን  ወደ በመፈተሽ በመግባት ለመሸነፋቸው ዋናው ምክንያትየምጣኔ አቅም ዝግ ስለነበርና ሕዝቡ ሊቀልባቸው ባለመቻሉየስምምነቱን ዕድል በመጠቀም አስተዳደሩን ከተረከቡ በኋላ ትግራይ አስፈላጊውንፋሲሊቲና ጥቅማጥቅምካገኘች በኋላ ትግራይ የኢትዮጵያ አካል ሆና እንደነበረቺው በክልል ደረጃ እንድትቆይ እያደረጉ የምታገኘው ጥቅም በሕዝቡ በኩል እያገኙ ልክ እንደ 17 አመቱ ትግል በመጀመርአንጃቸውንወደ በረሃ በመላክ የተጣሉ አስመስለው የሽምቅ ውግያ ከፍተው አገራዊ ግንጠላውን በቀላሉ ላማሳካት እንዲመቻቻው እየሰሩ ነው።

ያንን ከማድረጋቸው በፊት መጀመሪያ የወልቃይትና የራያን ነገር እልባት ማወቅ ይኖርባቸዋል። ወልቃይትን ካገኙ የሽምቅ ተዋጊ መስርተው ወደ ሱዳን መውጫ በር ከፍተው ካሁን በፊት ያሳየሁዋችሁ የፖርትሱዳን እና የወያኔ ዕቅድ በመቀጠል ምናባዊዋንዓባይ ትግራይ” (ታላቅዋን ትግራይ) ይመሰርታሉ። ሆኖም

በዳመና ውስጥ በአእዋፍ የተሠራች ምናባዊ ከተማመጪው ህይወትዋ ምን ይመስል ይሆን? የሚለው ትልቁ ጥያቄ መልስ ሊገኝለት የማይቻል ጥያቄ ነው።

ጽሑፉን ብትቀባበሉት ምሁራንና ሌሎቹ እንዲያዩት ይረዳል።

ጌታቻው ረዳ

Ethiopian Semay