Wednesday, March 29, 2023

አማራ ሆይ! ይልቁናስ ለማይቀረው ፍልሚያ ተዘጋጅ!! ዳግማዊ ጉዱ ካሣ Ethiopian Semay 3/29/23

 

አማራ ሆይ! ይልቁናስ ለማይቀረው ፍልሚያ ተዘጋጅ!!

ዳግማዊ ጉዱ ካሣ

Ethiopian Semay

3/29/23

     “በበቀል ጥማት የሚነድ፣ የለም እንደአቢይ አህመድ” በሚል ርዕስ ግጥም ቢጤ መጻፍ አማረኝና ወደለመድኩት የዝርው ጽሑፍ ዞርኩ፡፡ “ሥነ ግጥም መክሊትህ አይደለም!” ብባልስ በኪናዊ አገላለጽ፡፡

        ኢትዮጵያን ምን ዓይነት በቀለኛና ተራ የተራ ተራ ውዳቂ ግለሰብ እየገዛት እንደሆነ ተመልከቱ፡፡ ያቺን የመሰለች ድንቅ ሀገር በዚህ ከሲዖል ባመለጠ ሰውዬ እጅ መግባቷና ለዚህን ዓይነት ውርደት መጋለጧ እጅግ የሚያሳዝን፣ ኅሊናንም የሚሰቀጥጥ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ትንሣኤዋ እስኪበሠር ድረስ እንደእሥራኤሉ የቀድሞ ፕሬዝደንት እንደኤሪየል ሻሮል በሰመመን ውስጥ ብቆይ ደስታው አይቻለኝም፡፡ ሻሮል ለአምስት ዓመታት ገደማ ሳይናገር ሳይጋገር በሰመመን ውስጥ በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ነበር ከዚህች ምድር የተሰናበተው፡፡

        አቢይ አምባገነንነቱ እንዳለ ሆኖ በበቀለኝነቱ ከምድር ፍጡራን በእጅጉ የተለዬ ነው፡፡ ከኢንጂነር ስመኘው ጀምሮ እንኳን የገደላቸውን ብንቆጥር ሥፍር ቁጥር የላቸውም፡፡ ያሰራቸውንና ከሥራና ከቤት ንብረታቸው ያፈናቀላቸውንም ቤታቸው ይቁጠራቸው፡፡ እርሱ ሳያውቅና ይሁንታውን ሳይሰጥበት የሚከናወን ግፍና በደል ደግሞ የለም፡፡ ይህ ሰው መንግሥትን ያህል ሥልጣን ይዞ እንደተራ የመንደር ዱርዬ በቂም በቀል በመመረዝ ሕዝብን እየፈጀ ነው፡፡ የመንግሥት መሪነትን ሚናና ግለሰብኣዊ የግል ፍላጎትን ድምበር አያውቅም ወይም ሊያውቅ አይፈልግም፡፡ በመሠረቱ መንግሥት እንደመንግሥት ከግለሰቦች ጋር እልህ ተጋብቶ የሕጻናት ፉክክር ውስጥ አይገባም፡፡ መንግሥት ተቋማዊ እንጂ በአንድ አምባገነን ሰው ፍላጎት የሚዘወር ጠጅ ቤት አይደለም፡፡ እግዜር እንዴት ቢጣላን ይህን ሰው አምጥቶ አራት ኪሎ እንደጎለተብን ሳስበው ይገርመኛል፡፡ የሰውነት ጠባይ በጭራሽ የለውም፡፡

ተመልከት! ኢትዮጵያን በዘርና በጎሣ ካልበታተንኩ ብሎ ዕድሜ ልኩን በዘር ፖለቲካ መሃንዲስነት የሚታወቀውን ስብሃት ነጋን ማንም በማይቀናቀነው አምባገነናዊ ሥልጣኑ ከእስር ፈትቶ እያቀማጠለ ሲያኖር ቆዬና ሰሞኑን ደግሞ ለህክምና ወደ ውጪ እንዲወጣ ፈቀደለት - እርግጥ ነው ይሄ በራሱ መልካም ነገር ነው፡፡ በሌላ በኩል ግን አቢይ ሥልጣኑን በወያኔ እንዳይቀማ በቅርቡ ሕይወቱን እስከመስጠት የደረሰውንና በጥይት ቆስሎ የተመለሰውን ጄኔራል ተፈራ ማሞን ህክምና እንዳያገኝ ከልክሎታል - ይሄኛው ወደርየለሽ ግፍ ነው፡፡ ይህ ስም የለሽ ዕንቆቅልሽ ጤነኛ ነኝ የሚልን ዜጋ ሁሉ ያሳምማል፡፡ የአቢይ የበቀል ስሜት እየጋመ የሚሄድና ራሱንም ለለየለት ዕብደት የሚዳርገው መሆኑን ልብ ይሏል፡፡

        ለነገሩ አቢይ ተፈራ ማሞን አይደለም ህክምና የከለከለው፡፡ አቢይ በዚህ ሰይጣናዊ ድርጊቱ ለአማራ ያለውን ጥላቻና ቂም በቀል ነው የገለጸው፤ በተፈራ በኩል አማራን ነው ሊገድል የቋመጠው - አማራን ተስፋ ለማሰቆረጥ፡፡ ነገር ግን የአማራን ማሕጸን አላወቀውም፡፡ በጄኔኔራል ተፈራ ውስጥ ያለውን በ50 እና 60 ሚሊዮን የሚገመት አማራ ቢያንስ ቢያንስ በምናቡ ለመግደል አቢይ የማይፈነቅለው ድንጋይ የለም፡፡ ይህን ሁሉም አማራ ሊረዳ ይገባዋል፡፡ እንጂ ተፈራ በግሉ አቢይን የበደለው ነገር የለም፡፡ አቢይና ሽመልስ አማራን የሚያደርጉት ጠፍቷቸዋል፡፡ ከአራቱም ክፍላተ ሀገሮች አማራ ወደ አዲስ አበባ እንዳይገባ የተደረገው ለምን እንደሆነ ማወቅ አለብን፡፡ በጎጃምና በወሎ መስመር አማራ ወደ አዲስ አበባ ትውር እንዳይል ሲከለከል ስንትና ስንት የሪፈራል ታካሚ ሕይወቱ አልፏል፤ የጄኔራሉ ጉዳይ አነጋጋሪ የሆነው ታዲያ አንደኛ ጄኔራሉ የአቢይ ባለውለታ ሆኖ ሳለና እንዲያውም መንግሥት ራሱ አለ በተባለ ምርጥ ሆስፒታል ማሳከም ሲገባው በራሱ ወጪ ሊታከም ከሀገር ልውጣ ቢል የመከልከሉ ምሥጢር አልገባን በማለቱ ሲሆን ሁለተኛ መንግሥትን ያህል ትልቅ አካል ያለምንም ምክንያትና የህግ አግባብ አንድን ለሀገሩ ሲል የቆሰለን ከፍተኛ መኮንን ህክምና ከልክሎ የሞት ፍርድ የበየነበት በመሆኑ ነው፡፡ ይህ አቢይ ይህችን ሀገር ምን እስኪያደርጋት እንደምንጠብቅ ሳስበው አንዳንዴ ይጨንቀኛል፡፡ ግና ደግሞ ቋቱ እስኪሞላና በፈረንጅኛው ፈሊጥ ለመግለጽ ያህል የግመሉን ወገብ የምትሰብረው የመጨረሻዋ ገለባ በአቢይ የሥልጣን ኮርቻ ላይ እስክታርፍ በትግስት መጠበቅ ሊኖርብን ነው (The last straw that breaks the camel’s back. ይለዋል ፈረንጁ)፡፡

        አቢይ ከአምባገነንም በላይ መሆኑንና ራሱን ከፈጣሪም አስበልጦ በኛ ላይ እንደሚዘባነን ለመረዳት ጥቂት ምሣሌዎችን እንመልከት፡፡ ይህ ሰው በሚገዛት ሀገር ውስጥ መኖር በራሱ እንዴት እንደሚያሣፍረኝ አትጠይቁኝ፡፡

-   ቀደም ሲል አሻንጉሊት የፓርላማ አባላቱ ወግ ደርሷቸው “ማን ባጸደቀው 49 ቢሊዮን ብር ነው አዲስ ቤተ መንግሥት እየሠራህ የምትገኘው?” ብለው ይጠይቁታል፡፡ እሱ ደግሞ በንዴት ይፎገላና “በመጀመሪያ የተሳሳተ መረጃ ነው የያዛችሁት፡፡ የጠቀሳችሁት በጀት 49 ቢሊዮን ሳይሆን 56 ቢሊዮን ነው፡፡ ስለሌላው እናንተን አያገባችሁም፡፡ለምኜ በማገኘው ገንዘብ የፈለግሁትን ብገነባ የናንተ ጉዳይ አይደለም፡፡” ብሎ በሀፍረት ኩምሽሽ አድርጓቸዋል፡፡ (የቅንፍ ወሬ ጥሩ ነው፡፡ የ1997ቱን የወያኔ ምርጫ ተከትሎ በርካታ ቀልዶች ነበሩ፡፡ አንዱን እነሆ! ፌዴራሎች “ተጭበርብረናል” በሚል መሪ ቃል ሠልፍ ወጡ፡፡ ጋዜጠኞችና የመንግሥት አካላትም ወደሠልፉ ይጠጉና “ምንድን ነው የተጭበረበራችሁት?” በማለት ችግራቸውን ይጠይቋቸዋል፡፡ በአጋዚያን ጦር የተሞላው የፌዴራሎቹ ቃል አቀባይም “ተጭበርብረናል፤ተጭበርብረናል! በመንግሥት ሚዲያ ‹ከፌዴራልና ከመከላከያ በተተኮሰ ጥይት 35 ሰዎች ሞተዋል‹ የተባለው ትክክል አይደለም፡፡ የገደልነው 165 እንጂ 35 አይደለም፡፡ ተጭበርብረናልና ይስተካከልልን፡፡” ይህ አቢያዊ ቀልድ ፈገግ ከካላሰኛችሁ አዝናለሁ፡፡) 

-  የጉራጌ ሕዝብ ሰሞኑን የክልል መንግሥትነት ሲጠይቅ አቢይ ምን አለ? “ክልል እንድትሆኑ ብፈልግ አምስት ደቂቃ አይፈጅብኝም፡፡ ግን ስለማይጠቅማችሁ አልፈቅድም፡፡”

አዲዮስ ፓርላማ! አዲዮስ የሚኒስትሮች ካቢኔ! በአንድ ሰው በጎ ፈቃድ ውሎ የሚያድር የምሥኪን 120 ሚሊዮን ሕዝብ ሕይወት በምናባችሁ ይታያችሁ፡፡ በቅርቡ በቀን ስንቴ መተንፈስ፣ ስንቴ ዐይኖቻችንን ማርገብገብ እንደሚኖርብን በዐዋጅ ሳይደነግግ ይቀራል? የአቢይ መንግሥት እኮ ምን ዓይነት ቀለም የተነከረ ልብስ መልበስ እንዳለብን የሚወስን፣ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ቀለማትን ከመጥላቱ የተነሣ በልብሳችንም ሆነ በሰውነታችን እነዚህን ቀለማት ብናሳይ አይቀጡ ቅጣት የሚቀጣን ምስኪን ዞምቤዎች ሆነናል፡ ዞምቤ ማለት በሰው አምሳል የተፈጠረ እንደኛው ተናጋሪ እንስሳ ማለት ነው፡፡

-   የትግራይ ሽግግር መንግሥት ጉባኤ ሰሞኑን ደብረ ጽዮንን የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝደንት አድርጎ መረጠ ተባለ፡፡ የአራት ኪሎው አፄ ቦካሣ ያን ምርጫ አልቀበለው ይልና ሌላ ምረጡ ይላቸዋል፡፡ ጌታቸው ረዳን መረጡ ተባለና ውጤቱ ወደ አፄው ይላካል፡፡ እንደናርሲሰስ በራስ ፍቅር የወደቀው አጅሬ አያ እንደልቡ ግን ምርጫ ምናምን ሳይጠቀስ ጠ/ሚኒስትሩ ራሱ ለጌታቸው ረዳ ሹመት እንደሰጠው በሚዲያ አስለፈፈ፡፡ አዲዮስ ትግራይ! አዲዮስ ሕወሓት! አዲዮስ ምርጫ! (እዚህ ላይ ታዲያ “እዩኝ እዩኝ” ማለት “ደብቁኝ ደብቁኝ”ን እንደሚያስከትል ከወያኔ ይማሯል! ከምላሴ ፀጉር ይነቀል - ኦነጎች ግን ይህችን የወያኔን ዕድል እንኳን አያገኟትም፡፡) ሁሏም ተጠቅላላ በአንድ ዕብድ ሰው እጅ ገባችና ዕንቆቅልሹ ከቀን ወደ ቀን ይበልጥ እየተወሳሰበ ሄደ፡፡ መጨረሻችን ያማረ ቢሆንም የጨለማው አስፈሪነት ግን አሳሳቢ ነው፤ የመስዋዕትነቱ ከግምት ያለፈ መጠን ያስጨንቃል፡፡

-   በቀጥታ ከአቢይ ጋር ባይገናኝም - ለምንስ አይገናኝም ኧረ ይገናኛል - በተለይ ካለፉት አምስት ዓመታት ወዲህ በኢትዮጵያ ምድር እየተስፋፋና እየተንሰራፋ የመጣው በሃይማኖት ስም የማጭበርበር ሰይጣናዊ አካሄድ በአሁኑ ወቅት ጫፍ ደርሷል፡፡ ይህ ድርጊት በሁሉም የሃይማኖት ተቋማት የሚታይ ነው፡፡ የዘመኑ ፍጻሜ ይመስላል፡፡ ነቢይት ብርቱካን ለአቢይ የተነበየችለትን የሃሳዊ መሲሕ የቁጩ ትንቢት ጨምሮ እነኢዩ ጩፋና እሥራኤል ዳንሣ በፕሮቴስታንት ስም በየቸርቹ የሚያሳዩት የተጠና ድራማና የሚረጩት መርዝ ቀላል አይደለም፡፡ እነትዝታውና በጋሻውም እንዳሻቸው የሚግጡትን ምዕመን መርጠው ጎራቸውን በመለየታቸው የሃይማኖቱ ጦርነት ጦፏል፡፡ የአቢይ ታናሽ ወንድምና ታላቅ እህት የሚመስሉኝ የፍቅርሲዝሙ ነቢይ ደምሳሽና የጸረ-ኦርቶዶክሷ ወ/ሮ ስንዱ (ራሷን እህተ ማርያም ብላ የምትጠራው ወፈፌ) ደግሞ መሣቅ ሲያምረኝ የምዝናናባቸው ናቸው፡፡ የየራሳቸውን ቤተ ክርስቲያን መሥርተው ጠበል የሚያጠምቁና አዳሜ ሔዋኔን ኪሱን የሚያጥቡ ባለትዳር መነኮሣትና “ብፁኣን” አባቶች ቁጥር ደግሞ ከምንገምተው በላይ ነው፡፡ ዘንድሮ ብቻ ጉድ ነው፡፡….  


        አቢይ በበቀል ጥማቱ ማንም አይወዳደረውም ብያችኋለሁ፡፡ ይህ ሰው አንድን መንግሥት የሚመራ ሳይሆን ራሱ ጠፍጥፎ የሠራቸውን አሻንጉሊቶች እንዳፈተተው የሚጫወትባቸው ነው የሚመስለው፡፡ ሀገሪቱንም ሕዝቧንም እንደራሱ የእጅ ሥራዎች ቆጥሮን ድመት ዐይጥን ከያዘቻት በኋላ ከመብላቷ በፊት እንደምትጫወትባት እየተጫወተብን ይገኛል፡፡ ይህንን ደግሞ ሌላው ዓለም በተለይም ምዕራቡ በሚገባ ያውቃል፡፡ አቢይ የሚወስዳቸውን ሀገር በታኝና ሕዝብ አስለቃሽ እርምጃዎች ሁሉ የላኩት የውጭ ኃይሎች ጠንቅቀው ያውቃሉ፡፡ ዓላማቸው ኢትዮጵያን ማጥፋት በመሆኑ ግን አይቆጡትም ብቻ ሳይሆን ሁለንተናዊ ድጋፍ ያደርጉለታል፡፡ የነዚህ ኃይሎች ዋና ዓላማ በአቢይና በጀሌዎቹ አማካይነት የፈረደባቸውን አማራንና ኦርቶዶክስን ማጥፋት ነው፡፡ ስለሆነም ጄኔራል ተፈራ ለህክምና ከሀገር እንዳይወጣ መከልከሉን የተረዱት አሜሪካኖች ስብሃት ነጋ ዘንጦ በባሌ ሳይሆን በቦሌ ሲወጣ ትንፍሸ አይሉም፡፡ “ኢትዮጵያንና አማራን ለማጥፋት ሲዖል ድረስ እንሄዳለን” ያለው ጌታቸው ረዳ የትግራይ ፕሬዝደንት ሲሆንና አዲስ አበባ ላይ ሲምነሸነሽ የአንድ የሀገር ባለውለታ ጄኔራል ጤንነት ለአሜሪካ ቀርቶ ለሀገሪቱ መሪ ተብዬ ደንታው ሊሆን አልቻለም፡፡ አሜሪካ በኬንያውያኑ ግዛቶች በነሞምባሣና ማርሳቤት መኖር አለመኖር ራሱ የኔን ያህል እንኳን የምታውቀው ነገር ሳይኖር በወልቃይትና በራያ ያን ያህል ስትጨነቅ ማየት አጃኢብ ያሰኛል፡፡ ወያኔ የሌላ አካባቢ ግዛት በጉልበት ወስዳ ወደራሷ ስታካትት ትንፍሽ ያላለች አማሪካ ዛሬ ደርሳ በሰው ሀገር የውስጥ ጉዳይ እንዲህ የእርጎ ዝምብ ስትሆን ማየት የሰውን ልጅ የፍላጎት ባርነትን ያሳያል፡፡ ይህ ሁሉ ዕንቆቅልሽ በቅርብ ማለፉና ታሪክ መሆኑ ባይቀርም ለጊዜው ግን ያሳብዳል፡፡

        ካህንን በአደባባይ በጥፊ መምታቱና ቤተ ክህነትን ማዋረዱ አቢይ አህመድ ለምዕራባውያን ያሳየው የኦርቶዶክስ ጠልነቱ ዋና ምልክት ነበር፡፡ ሰሞኑን ደግሞ ጥፊው ስላልበቃው እዚሁ አዲስ አበባ እምብርት ላይ ኃይሌ ጋርመንት በሚባለው አካባቢ በጠራራ ፀሐይ አንድን ካህን እንደ ሰማዕቱ እስጢፋኖስ በመንጋ ሆነው በመጀመሪያ በዱላ አናታቸውን በመቀጥቀጥና ቀጥሎም ሬሣቸውን በድንጋይ በመውገር የሥልጣን ማቆያ ቀብዱን  በዐይን ጥቅሻና በአውራ ጣት የሞራል ድጋፍ ከምዕራባውያኑ ተቀብሏል፡፡ ይሄ አሰለጥ አቢይና መንጋው በዚህን በ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ይህንና ከዚህም የከፉ ወንጀሎችን ሲፈጽሙ የሚታዘበው የምዕራቡ ዓለም ዝምታውን አፅንቷል፡፡ ይሄኔ የኬንያው ፕሬዝደንት የቤት ውሻ በአጥንት ታንቃ ብትሞት ኖሮ ቢቢሲንና ሲኤንኤንን የመሰሉ ምዕራባውያን የሚዲያ አውታሮች ቀዳሚ ዜናቸው ባደረጉት ነበር፡፡ እነኚህ ለይምሰል ያህል በብር ኖቶቻቸው ላይ “በእግዚአብሔር እናምናለን” (In God we trust.) የሚሉ ጉዶች አፍሪካዊ ወኪሎቻቸው የሚያካሂዱትን የሕዝብ ጭፍጨፋ እንዳላዩ የሚያልፉ መሆናቸውን እንደማናውቅላቸው ሁሉ ስለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ግን ላንቃቸው እስኪበጠስ 24 ሰዓት ይጮሃሉ፡፡ በእግዚአብሐር የሚያምን ሰው በሰው ልጅ እኩልነት ያምናል፤ በእግዚአብሔር የሚያምን ሰው በዘርና በቀለም፣ በፆታና በሃይማኖት ልዩነት ሕዝቦች እርስ በርስ እንዲተላለቁ አያደርግም፡፡ በአጭሩ ዓለማችን የአስመሳዮችና የገንዘብ አምላኪዎች መድረክ ሆናለች፡፡ ይህ ደግሞ ቃሉ ነው፡፡ ቃሉ ይፈጸም ዘንድ ደግሞ የግድ ነው፡፡ “ሰማይና ምድር ያልፋሉ፤ ቃሌ ግን አያልፍም” ብሏላ! ደግሞስ ገና ምን አይተን! እሳት ከሰማይ የሚያዘንቡ ሓሣውያን በስሙ ይመጣሉ፡፡

        የአማራውንና የእውነተኛ ኢትዮጵያዊውን አሸናፊነት ምንም ዓይነት ምድራዊ ኃይል አያስቀረውም፡፡ አማራውያን አሸናፊ የሚያደርጋቸው ግፍና በደል የሚወልደው የጀግንነት መንፈስ ብቻ ሳይሆን ኦሮሙማዎች የሚከተሉት ለከት የሌለው ጥጋብና ዕብሪት ከጽርሓ አርያም የመንበረ ፀባዖት ችሎት የሚታዘዘው መብረቃዊ ቅጣት ነው፡፡ ቄስ አባይ መለሰ ሥጋ ወደሙ አቀብለውና ተቀብለው ወደቤታቸው ሲሄዱ በድንጋይ ተወግረው ሰማዕት የሆኑት ለዐረመኔ ጨፍጫፊ ኦሮሙማዎች ሳይሆን ሻሸመኔና ጉራፈርዳ፣ መተከልና ወለጋ በኦነግ ተጨፍጭፈው እንደእንስሳ በግሬደር ለተቀበሩት ምስኪኖች የደም ካሣ ለመሆን ነው፡፡ ለሚረዳ ሰው ካህኑ በጥፊ የተመቱት፣ ለመቁጠር የሚያታክት አማራና ሌላው ንጹሕ ኢትዮጵያዊ በኦነግ/ኦህዲድ ሸኔ የታጨደው ለኢትዮጵያ ትንሣኤ እንደግብኣት ሊሆን እንጂ ለከሰረ የዘር ፖለቲካ መደላድል ሆኖ ወያኔና ኦነግ በኢትዮጵያ መቃብር እንዲጨፍሩ አይደለም፡፡ ስለዚህ ኢትዮጵያ የመነሳቷ ነገር አያሳስብህ፡፡

        ለጦርነቱ ግን እንዘጋጅ፡፡ ኦሮሙማና ሕወሓት ሥልታዊ ትብብር በማድረግ አማራን ለመውጋት ዝግጅታቸውን አጠናቀዋል፡፡ ኦሮሙማ በደቡብ፣ ወያኔ በሰሜን በኩል አማራን ወጥረው ለመያዝ ተስማምተዋል፡፡ ኦነጋውያን በአቢይ በኩል ሁሉም ዓይነት የበጀትና የዘመናዊ ትጥቅ ድጋፍ ለወያኔ እየሰጡ ነው - ትብብራቸው እንዳልኩህ ለሥልት እንጂ ወያኔና ኦነግ እሳትና ጭድ ናቸው - የሚያገናኛቸው ነገርም የለም፡፡ ወያኔዎች አጉል እልህና የአልሞትኩም ብዬ አልዋሽም ዓይነት ወኔ ተጠናውቷቸው እንጂ ከኦነግ ይልቅ አማራው በብዙ ጅማቶች እንደሚተሳሰራቸው አጥተውት አይደለም፡፡ ግና እንደሚባለውም እልህ ጩቤ ያስውጣልና ወደባዳ አላምጠው ወደዘመድ መዋጥ አቃታቸው፤ ትዕቢት ደግሞ ውድቀትን ትቀድማለች፡፡ ከመነሻቸው ኦርቶዶክስንና አማራን ማጥፋት ዒላማ አድርገው መነሳታቸው ምን ጊዜም የሀፍረታቸው ምነጭ ነው፡፡ በዚያም ምክንያት በካፈርኩ አይመልሰኝ ትግራይን ይዘው ሊጠፉ ጀግነዋል፡፡ አጀማመርህ አጨራረስህን ይጠቁማል፤ ለማንኛውም ይቀጥሉበት፡፡ ማን እንደሚያተርፍ እናያለን፡፡ ኢትዮጵያ ግን ትነሣለች!!

        የኦሮሞ ሸኔ በገፍ እየሠለጠነና በገፍ እየታጠቀ፣ የወያኔ ሠራዊት ከሞት አንሰራርቶ በገፍ እየሠለጠነና እየታጠቀ ሳለ አማራው ግን በብአዴን ታፍኖ ሥልጠናውና ትጥቁ ቀርቶበት የለት ከለት ሕይወቱን ለመምራት እንኳን እንዳይችል በገዛ ቀየው እየተሳደደ ነው፡፡ አማራው በሌሎች ክልሎችና አካባቢዎች ይቅርና በራሱ ክልልም እንዳይኖር ጠላቶቹ እየተናበቡ ከፍተኛ የኅልውና ሥጋት ደቅነውበታል፡፡ አማራው ንብረት ማፍራት እንዳይችል፣ እንዳይበለጽግ፣ አካባቢው እንዳይለማ፣ መንገድ እንዳይኖረው፣ ፋብሪካና ኢንዱስትሪ፣ መብራትና ውኃ፣ መልካ አስተዳደርና ዘመናዊ ትምህርት ቤት እንዳይኖረው፣ ቢታመም እንዳይታከም፣ ከሥፍራ ሥፍራ እንዳይንቀሳቀስ በትልቅ እስር ቤት ተጠርንፎ የመከራ ኑሮ እንዲኖር ተደርጓል፡፡ ይህ ሁሉ ግፍና በደል የሚፈጸምበት ደግሞ ገና ትናንት ነፍስ ባወቀው በገልቱው ኦሮሙማ ነው፡፡ አፋርና ሶማሌም፣ ሲዳማና ጉራጌም፣ ወላይታና ከምባታም፣ ጋሞና ጠምባሮም፣ ጀምጀምና ደራሳም፣ አኙዋክና በርታም …. ሁሉም ተራውን እየጠበቀ እንጂ የአማራው ዕጣ ፋንታ እንደሚደርሰው ገሃድ የወጣ እውነት ነው፡፡ ይህ ሁሉ ኦሮሙማዊ የጥፋት ጉዞ ግን የፍጻሜው መጀመሪያ ነው፡፡ ጥሩ አባባል አለ፡- በአቀበት ቁልቁል ሰውን የሚያባርር ሰው ለራሱም መጠንቀቅ አለበት፡፡ ምክንያቱም ተባራሪው መሮት ዘወር ቢል አባራሪው አቀበት ይሆንበታልና፡፡

ለብርጋዴየር ጄኔራል ተፈራ ማሞ እንጸልይለት፡፡ እንደአቢይ የማይሆነው እግዚአብሔር እንዳይጨክንበትና የነገይቱን ወርቃማ ኢትዮጵያ ሳያይ እንዳያልፍ ሁላችንም በጸሎታችን እናስበው - ሌላማ ምን ሲቀርበት፤ “ተኖረና ተሞተ” አሉ፤ የአሁኑ የኢትዮጵያ ኑሮ ምኑም አያስቆጭም፡፡ የሆነ ሆኖ ወደ ደጉ ዘመን እንሸጋገር ዘንድ በዚያም ላይ ሁሉም እንደየሥራው ምንዳውን ያገኝ ዘንድ ለሱም ለኛም እንጸልይ፡፡ ጸሎት ከአቶሚክ ቦምብም በላይ ነውና፡፡

ሁሌም እንደምለው የሃይማኖት አባቶች በየበዓታችሁ ዝጉና ለበጎቻችሁ ጸልዩ፡፡ እረኞች ካለበጎቻቸው ምንም ማለት አይደሉምና መጽሐፉም “ተዓቀብ ዘንተ በዐቢይ ትጋህ” ይላልና አንዳንዶቻችሁን ከምናማበት አልባሌ ተግባራት ተቆጥባችሁ በጸሎትና ምህላ ሀገራችሁን ከአረማውያን የጥፋት ውርጂብኝ ታደጉ፡፡ ሌላውን ለሥውሩ የመለኮት ተዓምር እንተወው፡፡ ቀኑ ደርሷል፡፡ ሆኖም ቢሆን ወዮ ለኦነጋውያን!! ወዮ ለዚህ ሥጋ ለባሽ የአጋንንት ውላጅ!! ወዮ ለምድሪቱ፤ በሚታየኝ ነገር ሣር ነከስኩ፡፡

Ethiopian Semay       

Friday, March 24, 2023

ለበለጠ ችግር ማነሳሳት የትግራይ ህጻናት በሱዳን! ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 3/24/2023


ለበለጠ ችግር ማነሳሳት የትግራይ ህጻናት በሱዳን!

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay 3/24/2023

በዚህ ስዕለ ድምፅ (ቪዲዮ) የምትመለከትዋቸው የትግራይ ህጻናት በስደት አገር ሱዳን “ኡምራኩባ” በሚባል የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ የሚገኙ ናቸው። ህጻናቶቹ ከ10 እስከ 13 ዕድሜ ያላቸው ሲሆኑ፤ ወያኔዎች ዛሬም በስደት የሚገኙ የትግራይ ተወላጆች ህጻናት ሕሊና ላይ የሕሊና አጠባ ጨዋታቸውን አላቆሙም።

እነዚህ ህፃናት “አማራ ጠላታችን ነው” ከወልቃይት አስወጥቶ ቤተሰቦቻችን ጭፍጭፎብናል’’ እያሉ ከሚናገሩት ፍሬ ቃል  ከሚያስሰሙት ቃለ መጠይቅ ሌላ ፤ የትግራይ ሪፑብሊክ አገር ምስረታቸው ሕልም ዛሬን ስላልተውት ህጻኖቶቹ ‘የአካልእንቅስቃሴ እና የሰርከስ ካራቴ’ ትምህርት ስልጣና ሲያካሂዱ የሚያስደምጡት መፈክር፤ (ሃገረ ትግራይ ትስዕር) (ትግራዋይ  ይዕወት) “ሃገረ ትግራይ ታሸንፋለች” “ትግራዋይ አሸናፊ ነው”፤ በሚል ለበለጠ ችግር የሚያነሳሳ ትምህርትና ቅስቀሳ ሲሰጣቸው የሚያሳይ ማስረጃ ነው።

የወያኔ ወንጀለኞች ህጻናትን ለበለጠ ችግር አእምሮአቸው እንዲያዘጋጁ ሲያጥቧቸው ማየት ትናንት ወያኔዎች በሚሊዮን ሕዝብ ያስገደሉትና አካለ ስንኩል የሆነውን የትግራይ ወጣትና ምሁራን ከመጤፍ ሳይቆጥሩት ዛሬም እነዚህን ህጻናት “ትግራይ ታሸንፋለች” በሚለው የፋሺሰቶች አገር ምስረታ መፈክር  ፤ በህጻናት ነብስ የደም ጥማታቸው ለማርካት መጫወቻ ሊያደርጓቸው እንደሆነ ስንመለከት ከማዘን እና እነዚህ ወንጀለኞች ወደ አለም አቀፍ ፍርድ ቤት ከማቅረብ ሌላ እንደማይታረሙ ህያው ሰንድ ማሳያው ይህ ነው።

ብዙዎቹ ህጻናት ከሰጡት ቃለ መጠይቅ የሚሉት “በሰርከስና አካላዊ አንቅስቃሴ የላቀ ትምህርት ወስጄ “ለአገሬ ለሃገረ ትግራይ ስምዋ እንዲጠራ ማድረግ ነው ምኞቴ” ይላሉ፤ አንዱ ደግሞ “ህይወቴ ሙሉ ለሃገሬ ለሃገረ ትግራይ እሰጣለሁ” ይላል። ህልውናችን እና ደህንነታችን በጉልበታችን ይጠበቃል! ትግራይ ታሸንፋለች!” ይላሉ።

በሚገርም ሁኔታ ህጻናቱ ስደት አገር ውስጥ መኖር እንዳንገሸገሻቸውና “ሰርከስ” ትርኢት እያሳዩ እንደ ድሮው ህይወታቸው እንዲቀጥሉ ወደ አጋራችን መሄድ እንፈልጋለን ቢሉም፡ “ትግራይ ትዕወት” (ትግራይ ታሸንፋለች) የሚለው የትግራይ ሪፑብሊክ ምስረታ “ኦፊሲዮላዊ መፈክር” ካስደመጡን እና ትግራይ አገር እስክትሆን እና አገራችን የሚሏት ትግራይ እንደ አገር እስክትታወቅ ድረስ ፡ኡምራኩባ/ሱዳን’’ ከመቆየት ሌላ አማራጭ የላቸውም። “ነጭ መጭዋን” ነው የሚለው ብርቱው ኢትዮጵያዊው መድኩን በቀለ! ግልጽ ግልጹን እንነጋገር!!በነዚህ ህጸናት ላይ እየተረጨ ያለው ትምህርት ሰጪ አካላት በዓለም አቀፍ በሕግ ካልተጠየቁ  ለአገራችን በጣም አስቸጋሪ ክስትት እየፈጠሩ ናቸው። አብይ አሕመድ ጭምር ፍርድ ካልቀረበ አገር መምራት ስለማይችል ከድጡ ወደ ማጡ እየከተታት ነውና ችግሩ ብዙ ነው።

 በነዚህ ህጻናት ሕሊና “ትግራይ” እንጂ ኢትዮጵያ እንደ አገራቸው ስለማያውቋት፤ “አገራችን’ የሚሏት ትግራይ እስክታሸንፍና አገር እስክትሆንላቸው ድረስ ከመቆየት ሌላ አማራጭ የለም ሰንል በምክንያት ነው።ኢትዮጵያን እየጠሉ ትግራይን እንደ አገር እያዩ ከማኛው ጤፍ ላኩልኝ ፤ባጀቱም ሰንዴውም፤ማሩም ወተቱም ወደ ትግራይ ላኩ (እየበላን እየጠጣን ሃገረ ትግራይ እንመሰርታለን)፤ ጤፍ አምራችዋና ባጀት ላኪዋ “ኢትዮጵያ ጠላታች”ን ነችና አንታገላታለን፤ ዓይኑዋን አያሳየን የሚለው የዘንድሮ የትግሬዎች መፈክር ላንዴና ለመጨረሻ እንዲቆም ካልተደረገ ፤ አምና እና ታች አምና የተጠነሰሰው “ትግራይ ትዕወት ምስረታ ሃገረ ትግራይ” በህጻናት ሕሊና ላይ ስር የሰደደ ጭራቃዊ ችግር እንደገና መፈጠሩ አይቀሬ ነው።

ለወላጆችና ቤተሰቦቻቸው እንደወላጅነታቸው የምመክረው ምክር እነሆ!

የትም የማያደርሰው የጦርነት ቀስቃሽ መፈክር ለዳግም  የጦርነት ሰለባ ከመሆን  ልጆቻችሁ ለመመክር ባስቸኳይ እድትጀምሩ አሳስባለሁ። እንዚህ ህጻናት አገራችን ናፈቀን ይላሉ፡ ስለ "የትኛዋ አገራቸው" እያወሩ እንደሆነ ነግረውናል። ወደ ኢትዮጵያ መመለስ ከፈለጉ አገራችን ኢትዮጵያ የሚል የሕሊና መሰረት ማስያዝ አለባችሁ፡ ካልሆነ አገራችን ትግራይ ነች የሚሉ ከነሆነ “ሀገረ ትግራይ” አገር እስክትሆን ድረስ በአካል እየገለበቱ እንዳሉት አድገው ብረት ታጥቀው እስኪመጡ ድረስ ባሉበት ሰርከት ማሳየት ነው።  ከሥጋው ጿሚ ነኝ ከመረቁ ስጪኝ” ከሆነ ትንሽ ያራምድ እንደሆነ እንጂ ዘለቄታ ኣይኖሮውም።

 ወላጆችና ወዳጆች እነዚህ ልጆች ከልብ የምትወድዋቸው ከሆነ “አካለ ስንኩሎች” ከመሆን እንዲድኑ፤ በፋሺስት ርዕዮተ ዓለም አእምሮአቸው እንዲታጠቡ ከማድረግ ይልቅ ኢትዮጵያዊነታቸው እንዲወዱ በማድረግ “የድሮ አስደሳች ኑሮ ናፈቀን” እያሉ እየነገሩን ያሉት ህጽናት “የእምየ ኢትዮጵያ የድሮ ፍቅር” እንዲገባቸው ከማድረግ  ሌላ የተሻለ መንገድ የለም። ህጻናትን ለበለጠ ችግር ማነሳሳት ውጤቱ ትግራይ ውስጥ በቅርቡ ያየነው መከራ እንደገና እንዲከሰት ማድረግ ስለሆነ ከጦርነቱ በፊትም ሆነ ከጦርነቱ ወዲህ ደግመን ደጋግመን የምናስተላልፈው ምክራችን ዛሬም እነሆ አድምጡን እንላለን።

 

Monday, March 20, 2023

የዚህን ሰውዬ እንጨት እንጨት የሚል ቀልድ ላለመስማት የት ልሂድ? ዳግማዊ ጉዱ ካሣ Ethiopian Semay 3/20/2023

 

የዚህን ሰውዬ እንጨት እንጨት የሚል ቀልድ ላለመስማት የት ልሂድ?

ዳግማዊ ጉዱ ካሣ

Ethiopian Semay

3/20/2023 

የአእምሮ ህመም ዓይነቱና መጠኑ ብዙ መሆኑን የዘርፉ ምሁራን ይናገራሉ፡፡ ወደምሁራን ሰፈር ሳንዘልቅ እኛ የሙያው ባይተዋሮችም በተሞክሮና በተጨማሪ ንባቦች በዚሁ በአእምሮ ህመምና በሌሎችም አካላዊና ሥነ ልቦናዊ(አእምሯዊ) ደዌያት ዙሪያ የማይናቅ ዕውቀት እንደሚኖረን ግልጽ ነው፡፡ ስልሣና ሰባ ዓመታትን በምድር ላይ ኖሬ ስለበሽታዎች ምንነትና ጉዳት አላውቅም ማለት በመሠረቱ ትናንት ኅልውናውን ያገኘውን ዘመናዊ ትምህርት ብቸኛ የዕውቀትና ግንዛቤ ምንጭ ማድረግ ነው፡፡ ይህ ደግሞ ስህተት ነው፡፡ እንደሚባለው ከሆነ አንድ ሰው 25 መቶኛውን ዕውቀቱን ከትምህርት ዓለም ሲያገኝ 75 መቶኛ የሚሆነውን ደግሞ ከሕይወት ተሞክሮው ያገኛል፡፡

ስለአጠቃላይ አካላዊና መንፈሣዊ የህመሞች ዓይነትና መፍትሔያቸው አሁንና እዚህ አናወራም፡፡ ስለጀመርነውና በአሁኑ ወቅት ሀገራችንን ከሞላ ጎደል በሁሉም አቅጣጫ እያመሳት ስለሚገኘው የአእምሮ ልክፍት ግን በመጠኑ እንዳስሳለን፡፡ እርግጥ ነው መድኃኒቱ ይበልጡን ከታች ሳይሆን ከላይ ነው፡፡

የአንድ ሰው አእምሮ መቃወሱን ወይንም ጤናማነቱ መጓደሉን በምን እናውቃለን?

ይህ ጥያቄ በራሱና መልሱ እንደየመላሹ አስተሳሰብና ፍልስፍና አንጻር ከባድ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ ምክንያቱም የአስተሳሰብ አድማሳችን በተለያዩ ገጠመኞችና የሕይወት ተሞክሮዎች ሳቢያ የአንዳችን ከሌላኛችን በተለያዬ መጠን እምነታችንና አስተሳሰባችን ስለሚለያይ ለዚህ ጥያቄ የምንሰጠውም መልስ ለዬቅል መሆኑ አይካድም፡፡ በዚያ ላይ የሀገሮች ሥልጣኔና ዕድገት፣ የዜጎች ባህላዊና ሃይማኖታዊ እሳቤዎች ከቦታ ቦታና ከሀገር ሀገር መለያየት ወዘተ. በእምነታችንና ግላዊ ፍልስፍናችን ላይ የሚያሳርፈው ጥላ ቀላል አለመሆኑን መረዳት ተገቢ ነው፡፡

የሆነው ይሁንና ከፍ ሲል የተጠቀሰውን አስቸጋሪ ጥያቄ ለመመለስ የብዙኃንን ገዢነት መቀበል ሊኖርብን ነው፡፡ ይህም ማለት አብዛኛው የሚቀበለውን የአእምሮ ጤንነትና በሽተኝነት ሳንወድ በግዳችን ከተቀበልን - ለአብነት ያህል - መቶ ሰዎች ዕብድ ሆነውበት አንድ ሰው ጤነኛ የሆነበትን ጉዳይ ገለባብጠን ዕብዱ አንዱ ሰው እንደሆነ መቶዎቹ ግና ጤናማ እንደሆኑ ልናምን እንገደዳለን እንደማለት ነው፡፡ ሌላ ምርጫ እምብዝም የለንም፡፡ ከብዙዎች አሠራር፣ ከብዙዎች እምነት፣ ከብዙዎች አስተሳሰብ፣ ከብዙዎች የባህል፣ የወግ፣ የታሪክ፣ የሞራልና የዕሤቶቻችን ቅቡል ትውፊታዊ ሥርዓት የሚያፈነግጥ ሰው ስናይ ለአእምሮ ቀውስ እንደተጋለጠ ልንረዳና ወደሥነ አእምሮ ሐኪም ወይም ወደሚቀርበን ጠበል ወስደን ልናሳክም እንገደዳለን፤ ሊያውም ሰውዬው ፈቃደኛ ከሆነ፡፡ ሰውዬው ፈቃደኛ ካልሆነና የሚያሳክመው ዘመድ አዝማድም ከጠፋ የሚያስከትለው ጉዳት ከራሱ አልፎ ለማኅበረሰቡም ይተርፋል፡፡

ሀገራችን በአሁኑ ወቅት በአእምሮ ህሙማን ተጥለቅልቃለች፡፡ የዚህ ህመም ጠንቅ በግለሰብ ደረጃ ቢሆን ዕዳው ቀላል ነው፡፡ ችግሩ የሚጎላው ታማሚው ሰው በሥሩ የሚያስተዳድረው ቤተሰብ ወይም ድርጅታዊ አካል ካለ ነው፡፡ ከዚህ አኳያ በተለይ የሀገራችንን ፖለቲካዊ ድባብ ስንመለከት በከፍተኛ አእምሯዊ ደዌ የሚሰቃዩ ዜጎች ስለተቆጣጠሩት ሀገራችን ጣር ላይ ለመገኘቷ ዋና ሰበብ ሆኗል፡፡ የአእምሮ ጤንነት ደግሞ በተፈጥሮው ፀረ-ዕውቀትና ፀረ-ማስተዋል ነው፡፡ የአእምሮ ህመም ሆድን ሲያሰፋ የማስተዋልንና ትምህርትን በአግባቡ ጨርሶ የመመረቅን ሂደት ያጨናግፋል፡፡ ለዚህም ነው በ1996 ዓ.ም 12ኛ ክፍልን የጨረሰ ሰው በ1994 ዓ.ም ቢኤውን እንደያዘ የምንሰማው፡፡ በአእምሮ ህመም የተለከፈ ሰው የማይጥሰው የምድርና የሰማይ ህግ የለም፡፡ ህገ-ወጥነት የበሽታው መገለጫ ነውና፡፡

ጠቅለል ባለ አነጋገር አእምሯዊ ህመሞችን በሁለት ጎራ ከፍለን ልናያቸው እንችላለን፡፡ እነሱም በራሴው አገላለጽ በውስጣዊ ግፊት መያዝ (obsession/ኦብሴሽን) እና በውጫዊ ግፊት መያዝ (possession/ፖሴሽን) ሊባሉ ይችላሉ፡፡ ኦብሴሽን ማለት ከራስ የውስጥ እጅግ የተጋነነ ፍላጎት መርካት አለመርካት ጋር የተገናኘ በሽታ ሲሆን ፖሴሽን ማለት ደግሞ ከውጫዊ የእርኩስ መንፈስ ቁርኝት ጋር በተዛመደ መልኩ ይበልጡን የክፋት ድርጊቶችን የመፈጸም ዝንባሌ ነው፡፡ ማንም ቢሆን በአንድ ወይ በሌላ መንገድ ከነዚህ በአንዱ ወይ በሌላው ወይም በሁለቱም የመጠቃት ዕድሉ ዝግ አይደለም፡፡ ህመምን በጊዜው ተረድቶ ህክምና ለማግኘት መሞከር ግን ለሁሉም ጠቃሚ ነው፡፡ አለበለዚያ ከነዚህ ህመሞች በአንዱ የተጠቃ ሰው ለምሣሌ እንደሂትለር ወይንም እንደሞሶሊኒ ወይም እንደ አፄ ቦካሣና ኢዲ አሚን ዳዳ አለዚያም ልክ እንደኛው ጉድ እንደ አቢይ አህመድ በሽዎች ለሚቆጠሩ ጂኒዎች ዋሻ ይሆንና አገርን መቀመቅ እስከመክተት ሊደርስ ይችላል፡፡ የአእምሮ ህመም በመሪዎች ላይ ሲከሰት በዘዴ ዘወር ካላደረጓቸው ጣጣው ብዙ ነው፡፡ በአእምሯዊ በሽታዎች ሳቢያ በርካታ ሀገሮች ጠፍተዋል፡፡ ኢትዮጵያም ከነዚህ አገሮች ተርታ ተሰልፋ ግብኣተ መሬቷ እየተጠበቀ የምትገኝ አሳዛኝ ሀገር ሆናለች፡፡ እግዚአብሔር በቶሎ እንዲደርስላትና ቃል የተገባላትን ትንሣኤ ፈጥኖ እንዲልክላት በርትተን እንጸልይ፡፡

ከአእምሯዊ በሽታዎች የተወሰኑት እነዚህ ናቸው፡፡ አንድን የሚነገር ነገር በጭፍን ከማመንና በዚያም ላይ ተመሥርቶ ቂም በቀልና ጥላቻን ከመቋጠር የሚመነጭ አእምሯዊ በሽታ፣ በልጅነት በሚደርስ ጥቃት ሳቢያ ውስጥ ለውስጥ እያሸተና እየጎመራ የሚያድግ አእምሯዊ በሽታ፣ ከትውልድ ወደ ትውልድ በዘር የሚተላለፍ የዕብሪት፣ የኩራት፣ የማንአለብኝነት፣ የ“ከኔ በላይ ላሣር” ትዕቢትና ትምክህት፣ “እኔ ከማንም በታች የሆንኩ የማልረባ ፍጡር ነኝ” ዓይነት የበታችነት ስሜት የሚወልደው አእምሯዊ ልክፍት፣ የራስ ወዳድነትና የአልጠግብ ባይ ስግብግብነት በሽታ፣ የመዋሸትና የማስመሰል በሽታ፣ ከእውነተኛው ተጨባጭ ሁኔታ እጅግ ባፈነገጠ መልኩ በምናባዊ ዓለም የመኖርና ሌሎችንም በዚያው የምናብ ዓለም የማስመጥ በሽታ፣ ምንም የሚያስፈራ ነገር በሌለበት ሁኔታ በፍርሀት ቆፈን መቀፍደድና አልባሌ ነገሮችን የማድረግ ደዌ፣ በአንድ ጊዜ የብዙ ሰዎችን የተለያዩ ባሕርያት ተላብሶ ክፉም ደግም፣ ብልጥም ሞኝም የመሆን ሥነ ልቦናዊ አባዜ፣ ወዘተ. በዋነኝነት ሊጠቀሱ የሚችሉ የአእምሮ ህመሞች ናቸው፡፡ ይህ ዘመን ደግሞ የተለዬ ሆኗል፡፡ ዕብዱን ከጤናማው ለመለየት የተቸገርንበት እጅግ ፈታኝና ክፉ ዘመን!!

ስለአቢይ አህመድ የአእምሮ ህመሞች ጎተራ መሆን ብዙ ጊዜ ተነግሯል፡፡ ዋና ተልእኮው ኢትዮጵያን ማፍረስ መሆኑ ሳይዘነጋ ይህ ሰው በዋናነት በ“MPD (Multiple Personality Disorder), delusion, megalomania, ‹Amharophobia›, ‹Ethiophobia›, paranoia, bipolar disorder, pathological lying…” እና በመሳሰሉት ሥነ ልቦናዊና አእምሯዊ በሽታዎች የተጠቃና እነዚህን በሽታዎቹን ለዓለም ሕዝብና መንግሥታት በተግባር ለማሳየት 120 ሚሊዮን ምሥኪንና ከርታታ ዜጎችን ከፈጣሪ የተቸረው “ዕድለኛ” የዐውሬው 666 ልዑክ ነው፡፡ ከሃይማኖት አኳያ አንድ መገንዘብ ያለብን ነገር ደግሞ ከሁለቱ ኃይላት መካከል (ከፖሲቲቭ ኢነርጂና ከኔጌቲቭ ኢነርጂ ማለቴ ነው) አፍራሹን ሚና የሚወክለውና እውን የሚያደርገው ሣጥናኤል የሚባለው ከሃዲ ሲሆን አወንታዊውን ኃይል ተግባራዊ የሚያደርገው ደግሞ ክርስቲያኖች እግዚአብሔር ብለን የምንጠራው የሰማይና የምድር ፈጣሪ ነው፡፡ ትልቁ ጦርነትም የቀረበ ይመስለኛል፡፡

እንግዲህ ኢትዮጵያ በምን እጆች ውስጥ እንዳለች እያየን ነው፡፡ አሁን ሥልጣን ላይ ከሚገኙት የየትኛውም ነገድና ጎሣ አባላት መካከል ለዋናው የአራት ኪሎው ብዔል ዘቡል እስከታዘዙ ድረስ ሚናቸው የሰይጣን ወይንም የአፍራሹ ወገን ነው፡፡ አወንታዊ ኃይል ሰውን በነገዱ እየለዬህ በጥላቻ ፖለቲካም ተመርዘህ ግደለው፣ አሰቃየው፣ አፈናቅለው፣ ቤቱን አፍርሰው/አቃጥለው፣ ቀማው፣ ዝረፈው፣ አሳደው … አይልም፡፡ ይህ ከማንኛውም ዓይነት የብዙኃንን ተቀባይነት ካገኘ ሃይማኖት ያፈነገጠ ዕኩይ ድርጊት መንግሥታዊ ቅርጽ ይዞ እውን ሲሆን ስታይ መንበረ መንግሥቱን የያዘው ሊቀ ሣጥናኤል መሆኑን በግልጽ ትረዳለህ፡፡ የወል መንግሥትነትን ሥልጣን ይዘህ ስታበቃ በ40 እና በ50 ሚሊዮን የሚገመትን ነገድ ከምድረ ገጽ ለማጥፋት ሌት ተቀን መሥራት ዓለማችን እስካሁን ያላየችው መርገምታዊ በሽታ ነው፡፡ በሰይጣን መንፈስ ተይዘው ራሱን ሊገድሉት ለከበቡት ጻፎችና ፈሪሣውያን የራራው ክርስቶስ አሁን ቢመጣ እነዚሀ ደናቁርት ኦሮሙማዎች በሚሠሩት ሥራ ተበሳጭቶ የአባቱን የእግዚአብሔርን ሰውን የመፍጠር የስድስተኛውን ቀን ሥነ መለኮታዊ ክንዋኔ አጥብቆ በተቃወመ ነበር፡፡ አንድዬ ይቅር ይበለኝና ስድስተኛዋን ቀን ብዙም አልወዳት፡፡

በነገራችን ላይ ወያኔና ኦሮሙማ ለአማራ ጨፍጫፊ ጀሌዎቻቸው በጫካም ሆነ በቤተ መንግሥት ውስጥ የሚሰጡት ሥልጠና አንድ ዓይነት ነው፡፡ ይህንን እውነታ ደግሞ ጨፍጫፊዎቹ እጅ ሲሰጡ ወይንም ሲያዙ ከሚናገሩትና ከተግባራቸውም መረዳት ይቻላል፡፡ አንድ ፊደል የቆጠረ “ሰው” በምን ሥሌትና የጥላቻ ፕሮፓጋንዳ ሰክሮ ይሆን ሠልጣኞችን ከፊቱ አሰልፎ እንዲህ የሚላቸው፡- “አማራን ስታገኙ ምንም አትራሩለት! ነፍሰ ጡሯን አማራ ሆዷን ዘርግፋችሁ ጽንሱን ስትፈልጉ ብሉት ወይም ቦጫጭቃችሁ ጣሉት፡፡ ሴት ወንድ ሳትሉ ድፈሯቸው፡፡ አንገት አንገታቸውን ቁረጧቸው፤ ቤት ንብረታቸውን ዝረፉ ወይም አውድሙ፡፡ ከያሉበት አፈናቅሉ፡፡ አማራ እንደሰው የማይቆጠር አህያ ነውና በሉት፡፡ ሰው እንደገደላችሁ አትቁጠሩ፡፡ ለዚህም መንግሥታችንና ክልላችን ከጎናችን አሉ፡፡…” ከዚህ በላይ መረገም ይኖር ይሆን ወገን?

አቢይ በትናንትናው ምሽት ይሁን ቀን አሻንጉሊቶቹን ሰብስቦ መጽሐፉን ያስመርቅ ነበር፡፡ ይህ በራሱ ዓለም የሚኖር የአእምሮ በሽተኛ በአንድ መጽሐፍ ሽያጭ የጎንደርን የፋሲለደስ ቤተ መንግሥትና የሶፎሞርን ዋሻ ሊያሳድስ እንዲሁም በአዲስ አበባ በርካታ ስቴዲየሞችን ሊያስገነባ የነዚህን አካባቢዎች መሪዎችን ወደ መድረክ ጠርቶ እንደሕጻን ይጫወትባቸው ነበር፡፡ ለነገሩ ይልቃል የተባለው የአማራው ክልል መሪ ተብዬ ነው እንጂ መቀለጃ የሆነው ሌሎቹ የኮንቪንስና የኮንፊውዝ ኬኛ ፖለቲካ ድራማ ተዋንያን ስለሆኑ እየሣቁ ማለቴ እየገለፈጡ በትወናው ቢታዩ ለነሱ ምንም ማለት አይደለም - ከዚያ ከጉማሬ አሣሣቅ የተረዳሁትም ይህንኑ ፌዝ ነው፡፡ አቢይ መቼም ቀልዱ አያልቅበትም፤ ለብዙዎቻችን ግን እንጨት እንጨት ካለን ቆየን፡፡ ችግሩ የት እንድረስ? ይህን መሰል የጠነዛ ቀልድ ላለመስማትስ እምን ውስጥ እንግባ? ያገራችን ፖለቲካዊ ዕብድ ደግሞ አጃቢውና አጨብጫቢው  ብዙ ነው፡፡ (“አጨብጫቢ ነኝ” የሚለውን ዘፈን እባካችሁን ተጋበዙልኝ፡፡)

ለማንኛውም ኦሮሙማ በርትቷል፡፡ ኢትዮጵያን ሰልቅጦ ሊውጥ ወይም የዋጠውንም ሳይቀር አንቅሮ ሊተፋ የቀረው ጊዜ ግፋ ቢል ከአሁን በኋላ አራት ወይ አምስት ወራት ብቻ ናቸው፡፡ በነዚህ ወራት ውስጥ የመጨረሻው ፊሽካ ይነፋና ሁሉም ነገር ይለያል፡፡ አዲስ አበባ ከሞላ ጎደል ሁሉም ቦታና ሁሉም ሥልጣንና ኃላፊነት የተያዘው በኦሮሙማዎች ነው፡፡ ይህም የልብ ልብ ሰጥቷቸው አማራን ከአማራ ክልል ወደአዲስ አበባ ላለማስገባት ብቻ ሣይሆን የአማራን ክልል ራሱን በሞግዚት እያስተዳደሩት ይገኛሉ፡፡ ጅል ሰው አያሸንፍህ ወዳጄ፤ ሞኝ አይንገሥብህ ወንድማለም፡፡ ኦሮሚያ ውስጥ ማንኛውም ታጣቂ በፌዴራሉና በክልሉ መንግሥት ቀጥተኛ የበጀት ድጋፍ ሲሰለጥንና ፀረ-አማራ ዘመቻውን አማራ ክልል ድረስ ዘልቆ ሊያፋፍም ዝግጅት ላይ እያለ ተላላኪው የአማራ ክልል መንግሥት ግን አማራ ያለቺውን አንድዬዋን የፋኖ አደረጃጀትም ሊያጠፋ ጥረት ላይ ነው፡፡ ብዙ የሚገርሙ ነገሮችን እያየን ነው፡፡ እኔማ መጨረሻውን ባላውቀው ኖሮ ሦስት ሜትር ገመድ አንጠልጥዬ ወደሚቀርበኝ ዛፍ በሮጥኩ ነበር፡፡ ነገር ግን ዕድሜ ለዕድሜየ ብዙ ነገር ተምሬያለሁና ይብላኝ ለደናቁርቱ ኦሮሙማዎች እንጂ ሀገሬማ ልትነሣና ታላቅቷን ለናቋት ሁሉ ከፍ ብላ ልታስመሰክር ተቃርባለች፤ የፈለግኸውን ብትለኝ ግዴለኝም፡፡ ለዚህ ሁሉ ውጥንቅጥ ችግር የዳረጓት የውጪዎቹም የሥራቸውን ሊያገኙ ጣር ላይ ናቸው፡፡ ስለሀገሬ መጨረሻ የማውቀውን ያህል ጧት የበላሁትን ቁርስ አላውቅም፡፡ ይልቁንስ አማራና አማራውያን ለሁሉም ተዘጋጁ!! ፍልሚያው ቀላል አይደለም፡፡

በአእምሮ ህመም እንደጀመርኩ በዚያው ልውጣ፡፡ በዩቲዩብ፣ በቲክቶክና በመሳሰለው ማኅበራዊ ሚዲያ ከሚጃጃሉ የአእምሮ ህሙማን ተጠንቀቁ፤ ብዙ ናቸው፡፡ ገና ለገና ሣንቲም አገኘን ብለው የሆነ ያልሆነውን በወጣቶች ቋንቋ ልግለጽላችሁና የሚበጠረቁ ብዙዎች አሉና እነዚህን ገስጹ፡፡ አማራ መስለው ስለአማራም የታገሉ መስለው ነገር አማረልን ብለው ሃያ አራት ሰዓት የሀሰትና የጠብ ጫሪ ቱሪናፋ የሚለቁ አሉ፡፡ ከነዚህም አንዱ ሰሞኑን ወዳገር ቤት መጥቶ የዘባረቀውን ሁሉ ሰምተናል፡፡ አሣፋሪ ነው፡፡ ማይምነት ድፍረትን ይሰጣል፡፡ ያበጠ ኪስ አእምሮን ይቀማል፤ ማስተዋልንም ይነሳል፡፡ እጅ መንሻዎች አቅልን ያስታሉ፡፡ ሀገር ደግሞ በገንዘብም ሆነ በመኖሪያ ቤት ስጦታ አትሸጥም፡፡ እንደውነቱ ከአንድ እንጀራ ለማያልፍ ሆድ ይህን ያህል መውረድና መዋረድ ባልተገባ ነበር፡፡ ወዳገር ካልገቡት ውስጥም ተደማጭነትንና በዚያውም የሽቀላ ሣንቲምን ለማግኘት ሲሉ ኃላፊነት ሳይሰማቸው አማራንና ቀደምት የሀገራችንን ነገሥታት ባልተሞረደ አንደበታቸው የሚወርፉ አሉ፡፡ እዩኝ እዩኝ እንዳሉ ደብቁኝ ደብቁኝ የሚሉበት ዘመን ከመምጣቱ በፊት ከአሁኑ ንስሃ ገብተው ትክክለኛ መረጃ ይስጡ፡፡ የአሁን አድማጭና አሸርጋጅ ነገ አይኖርም፡፡ የዛሬ የዩቲዩብ ክፍያ ነገ አገር ስትስተካከል ድርቅ ይመታዋል፡፡ ያኔ አንገትን ከመድፋትና ከማፈር የዛሬ መራብ ብዙ ዋጋ አለውና አሽቃባጮችንና በአፋቸው የሚጸዳዱ የኢንተርኔት ተጧሪዎችን አሁን ምከሯቸው፡፡ ከኦሮሙማ ጋር ተሰልፈው ኢትዮጵያን እየሸጡ ያሉ ሀብታም ነጋዴዎች፣ ጳጳሣት መነኮሣት፣ አርቲስት አክቲቪስቶች፣ ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞች፣ ሁሉም አደሽዳሽ ሆዳም ይጠንቀቅ፡፡ ሀገርንና ፈጣሪን፣ ፍቅርንና መዋደድን ከገንዘብ እናስቀድም፡፡ ከኔ ከድሃው መማር ይቻላል፡፡ እንዲህ እንደጨለመ አይቀርምና ከታሪክ ትቢያነት ለማምለጥ ሁላችንም አካሄዳችንን እንመርምር፡፡ ዛሬ የሚያሽቃብጥልንና ያልበላንን የሚያክልን ሁሉ ነገ ጊዜ ዘመም ሲል እኛኑ ለማማትና ለማበሻቀጥ ወደባለጊዜው ለመገልበጥም የሚቀድመው የለምና ሁላችንም ወደየኅሊናችን እንመለስ፡፡ ሚዛናዊና አስተዋይ ኅሊና እንዲኖረን መጻሕፍትን እናንብብ፤ የሃይማኖት ሰዎችም እንሁን፡፡

በመሠረቱ ሁሉም ነገር አላፊ ጠፊ ነው፡፡ ሞት ቢምርህ ዕርጅና አይምርህም፡፡ በሽታ ቢምርህ ድንገተኛ አደጋ አይምርህም፡፡ ከአሁኑ ዕድሜህ ላይ - ለምሣሌ - 50 ዓመታትን ደምርበት፡፡ ያኔም በሕይወት እንዳለህ ቁጠርና እንዴት እንደምታስጠላና ሞት እንኳን ባቅሙ ምንኛ እንደሚጠየፍህ ገምት፡፡ እኔ በዚያን ጊዜ 110 አካባቢ እሆናለሁ፡፡ በሕይወት እንኳን ብገኝ ውሻ በጨው የማይበላኝ የሰዎች መሣቂያ ነኝ፡፡ እንኳን ያኔ አሁንም እንደዚያው ነኝ ለነገሩ - የዛሬ 30 ዓመት ገደማ በ20ዎቹ መጨረሻ አካባቢ እያለሁ ግን … ምን አስቀባጠረኝ፡፡ ታዲያ ለዚች ዕድሜ ኖሯል በዘርና በጎሣ፣ ባለውና በሌለው፣ በተማረና ባልተማረ፣ በአርሲና በባሌ፣ በወለጋና በጥሙጋ፣ በጎንደርና በሸገር፣ በትግሬና በአማራ፣ በኦሮሞና በአማራ-ጉራጌ …ተቧድነን የምንተረማመሰውና የምንጨራረሰው? በደምብ አስበው፡፡ ለምኑ ብሎ ነው ጫልጪሣ አመንቴ ሞላ ፍላቴን ወዶና ፈቅዶ ባልተወደበት የዘር ሐረግ ምክንያት የሚጠላውና የሚገድለው? የአእምሮ ህሙማንን ስብከትና የዘር ጥላቻ ተከትለን ሺህ ዓመት ቀርቶ መቶ እንኳን በቅጡ ለማንደፍንባት የምድር ዕድሜ በከንቱ የምንጨራረሰው ለምንድን ነው? ትንሽነትን እንዋጋ እንጂ፤ ኢትዮጵያውያን እኮ በታሪክ ታላቅ ሕዝብ ነበርን፡፡ አሁን እንደዚህ የወረድነውና የቀለልነው ለምን እንደሆነ ተገንዝበን ወደጥንታችን እንመለስ፡፡

ደግሞስ እግዜር በፈጠራት መሬት እኛ ጠፍጥፈን የሠራናት ይመስል “ይሄኛው የኔ፣ ያኛው ያንተ” ለመባባል ማን ሥልጣን ሰጠን? “ኦሮምኛ ቋንቋ ከአማርኛ ቋንቋ ይበልጣል” እያልን ልጆችን ማስተማሩን ከየት አገኘነው? ስለዓለም ከንቱነት ማስተማር ሲገባው “አዲስ አበባ የኦሮሚያ ናት፤ እደግመዋለሁ፤ አዲስ አበባ የኦሮሚያ ናት” እያለ በሰማይ ቤት የሚገኙ አዳምና ሔዋንን ሳይቀር በሣቅ ጦሽ የማድረጉንስ ምሥጢር ለኦሮሞ ካህን ማን ገለጠለት? በአንዲት የጋራ ከተማ ውስጥ ሁለት ብሔራዊ መዝሙር ማዘመርንና ሁለት ባንዲራ መስቀልን ከየት ተማርነው? ባሏን የጎዳች መስሏት ሰውነቷን በጋሬጣ እንደወጋችው ሴት ሆነን የጤፍን ዋጋ እንደዕንቁ ሰቅለን ሕዝብን በኑሮ ውድነትና በገንዘብ ግሽበት ማሰቃየትን ከየት አመጣነው? በሀፍረት የምንሸማቀቅበት ነገር መብዛቱ!! ግዴላችሁም፤ ኦሮሙማዎች አንጎላችሁን ለመጠቀም ጥቂት አረፍ ብላችሁ አስቡ፡፡ ነገ ሌላ ቀን ነውና ከገባችሁበት የህልም ዓለም በአፋጣኝ ውጡ - ጊዜ ካላችሁ ነው ሊያውም፡፡

Tuesday, March 14, 2023

የሀገሪቱን አንድነት ዋጋ እያስከፈለ ያለው ትግሬዎችና ኦሮሞዎች የሚከተሉት አደገኛው የአፓርታይድ ፖለቲካ ፓተርያሪኩ ሊያጤኑት የሚገባ ጉዳይ (ካለፈው ክፍል 1 የቀጠለ) ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 3/14/2023

 

የሀገሪቱን አንድነት ዋጋ ያስከፈለ ያለው ትግሬዎችና ኦሮሞዎች የሚከተሉት አደገኛው የአፓርታይድ ፖለቲካ  ፓተርያሪኩ ሊያጤኑት የሚገባ ጉዳይ (ካለፈው ክፍል 1 የቀጠለ)

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay

3/14/2023

ክቡር ብፁእ ወቅዱስነትዎ  ሆይ!

ኢትዮጵያውያን 27 አመት ሕዝብን በቋንቋ በዘር፤በሃይማኖት ከፋፍሎ የገዛውን ወያኔን ለመመከት  ጥቅምት 24/2012 በሰሜን ዕዝ ጦር የፈጸመው  ድንገተኛ ጭፍጨፋ በመቃወም ኢትዮጵያውያን ባንድነት የቆሙት ለምንድነው? ብለው እራስዎ ቢጠይቁ መልሱ ለማግኘት ትንሽ ጥልቅ ምርመራ ቢያደርጉ ለምን እንደሆነ ይረዱታል።

የኢትዮጵያ ህዝብ በሚሊዮኖች በየቦታው ለጦሩ ድጋፍ ድምጹን ሲያስተጋባ የወያኔ የኦነግ ዘረኛ ፖለቲካ ጡጦ እየጠባ ላደገው ወንጀለኛው አብይ አሕመድ በመደገፍ ሳይሆን የሀገሪቱ ጦር በሰሜናዊ ክልል ጥቃት ስለደረሰበት ጥቃት ፈጻሚውን  የትግራይ ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ ጦርን በመቃወም ነው።

ወያኔ ሥልጣኑ ከተቀማ በኋላ በቀጥታ የገባው “ኢትዮጵያ እና ትግራይ” ወደ እሚለው የሁለት አገር ፖለቲካ  ስንጠቃ በመግባቱ ሕዝቡ ይህንን አገር የማፍረስ ሴራ ማክሸፍ ስለነበረበት መላው አገሪቱ ሆ ብሎ ባይሆንም ብዙ አርበኛ ከውጭም ከውስጥ አገርም ወደ ጦር ግምባር ዘምቶ በአሜሪካኖችና አውሮጳ የስለላ ሳተላይቶች የተደገፈው የወያኔ አንድ ሚሊዮን ተኩል ጦረኛ እንቅስቀሴው እንዲገታ በማድረግ በመጨረሻም በተደረገው የአንድነት ርብርቦሽ ከጦርነቱ በፊትና በኋላም በጥቅምት 24 ሰራዊቱ በተኛበት አዘናግቶ ጨፍጭፎ የታጠቃቸው ከባድ መሳሪያዎቹን እንዲፈታ እና እንዲያስረክብ ተደረጓል።

10 ሺሕ ሕዝብ ሆን ተብሎ ምግብ ዕርዳታ በመዝጋት በርሃብ ምክንያት አልቋል እየተባለ የተነዛው የወያኔ ፕሮፓጋንዳ ውሸት መሆኑን ባለፈው ክፍል አንድ ጽሑፌ የአለም አቀፍ የምግብ ተራድአ ድርጅት የኢትዮጵያ ዋና ዳይሬከተር አስተባባሪ ኬኒያዊው “እስቲቭ ኦሙማ” (At the Center of the World – Ethiopia) በሚል በጻፈው አስገራሚ መጽሐፍ ዓይን ያወጣ የወያኔዎችና የተባበሩት የአለም አቀፍ የውሸት ቋቶች ያራገቡት ዜና መሆኑን ነግሮናል።

እርስዎን ካሳዘነዎት አንዱ የትግራይ ሴቶች መደፈር መሆኑ ተናግረዋል። ይህ እውነት ነው። ሴቶች በወታደሮች እንደተደፈሩ እውነት መሆኑን እራሱ አብይ አሕመድም ነግሮናል። የታሰሩ እንዳሉም ተናገሯል። ምን ያህል በፍትህነት እንደተከናወነ ግን አላውቅም። ወያኔዎች ግን 150000 ሴቶች እንደተደፈሩ ሲነግሩን፤ እንዲህ ያለ ብዛት ግን፤ ገለልተኛ አጣሪ እስካልነገረን ድረስ እውነትነቱን ለመቀበል ያስቸግራል።

ሌላው በንግግርዎ እርስዎ የጠቀሱት የማሕበረዴጎይ (ናዕዴር ወረዳ አክሱም) የሰላማዊ ሰዎች ዩጅምላ ርሸና አንዳሳሰበዎት እውነት ነው። ትግሬዎች በመሆናቸው ብቻ እየተለቀሙ በጦሩ እየተረሸኑ ወደ ገደል እየተጣሉ በቪዲዮ የተደገፈ ወንጀል አይተናል። ያ ደግሞ ካሁን በፊት በለጠፍኩት ቪዲዮ ላይ ድርጊቱን የፈጸሙ ወታደሮች በወያኔ እስር ቁጥጥር በነበሩበት በመቀሌ ከተማ እንደተናገሩት << መንግሥት ሰላማዊ ሰው እንዳይገድሉ በደብዳቤ የተላለፈ ጥብቅ ወታደራዊ ትዕዛዝ ከታች እስከ ታች ያሉት ዕዞችና ወታደሮች በደብዳቤና በገላጻ እንደተገለጸላቸው በድርጊቱ በየተሳተፉት ወታደሮች ተናግረዋል።

ነገር ግን ድርጊቱን የፈጸሙት የበታች አዛዦች በራሳቸው አነሳሽነት እንጂ ሆን ተብሎ በመንግሥት የታዘዘ ድርጊት እንዳልሆነ ድርጊቱን ካዘዙትና ከፈጸሙት አንዱ አምሳለቃ ማዕርግ ያለው ወታደር “እራሴ ሁለት ሰዎችን ረሽኛለሁ ወደ ገደል እንዲጣሉም ሆኗል” የሚለው አምሳለቃ ወታደር ወያኔዎች ባደረጉለት ቃለ መጠይቅ ይፋ አድርጎታል። ስለዚህ ወታደሮቹ የጀኖሳይድ ወንጀል ትዕዛዝ እንዳልፈጸሙ ሲናገሩ በሕግ ዓይን “የጦር ወንጀል” ፈጽመዋል ማለት ግን ያስኬዳል።

ትግራይ ውስጥ ጀነሳይድ (የዘር ማጥፋት) ወንጀል ተፈጽሟል የሚለው ደግሞ በገለልተኛ ምርምራ እስኪጣራ ድረስ እንቆይ። አብይ አሕመድ እና ወያኔዎች ግን ምርመራው የሚፈልጉት አይመስሉም (ለምን እንደሆነ ግልጽ ነው)

ብጹእነትዎ ሆይ!

ትግሬዎች ከኢትዮጵያ ለመነጠልና ኢትዮጵያን ለማፍረስ የነጻነት መዝሙር ሲዘምሩ እና አለም አቀፉ የቄሳሮች ቡድን ወያኔ በመደገፍ አገር ለማፍረስ ሲሯሯጡ በአንጻሩ ደግሞ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ አገራዊነቱን ላለማስደፈር በቁጭት “ቄሳሮችን” በውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ከመግባት እንዲቆጠቡ የተቃውሞ ጥሪ በማስተጋባት አንድታቸውን አሳይተዋል።

 ያ ዓለም አቀፍ ጥሪ ግን የአብይ አሕመድ ካድሬዎች ለአብይ አሕመድ ድጋፍ እንዲሆን ጠልፈውት ፕሮፓጋንዳ ሲሰሩበት መኖራቸው ሃቅ ነው። በዚህም ማሕበረሰቡ ለሁለት ተከፍሎ እንደ ነበር ይታወሳል።

ወያኔዎች ባገኙት የሳተላይትና የራዲዮ ግንኙነት መሳሪያዎችና  የስላላ እገዛ እስከ ደብረብርሃን ድምበር ቢደርሱም ህዝቡ አብይ አሕመድን በመቃወም ከፓርክና ከሰላጣ ችግኝ ተከላ ጨዋታ ተሎ እንዲወጣና ጦሩን እና ሕዝቡን እንዲያስተባብር ጥሪና ቁጣ ስለተላለፈለት “ተሎ ደንግጦ” ሕዝቡን በማስተባባር በህወሓት ላይ በቆራጥነት ሕዝባዊ መከታውን ጸንቶ በመላ አገሪቱ በአንድነት በመቆም የኢትዮጵያን ሰራዊት በመቀላቀል ሚሊዮኖችም ለዚሁ አላማ የስንቅና የፕሮፓጋንዳ ድጋፍ በመስጠት ወያኔን ኣይቀጡ ቅጣት አግኝቶ አሁን ላላው ሁኔታ ደርል። ሰሞኑ ጌታቸው ረዳ ከሚጠላት ኢትዮጵያ ደሞዝ ተልኮለት ፤ የመጀመሪያ ደሞዙ ለሲጋራና ለመጠጥ እንዳዋት” በዝማሬ ለሕዝቡ ሲዘፍንለት አይተናል። ለሚሊዮን ሕዝብ ዕልቂት ምክንያት ለሆኑ ወንጀለኞች ደሞዝና አንክብካቤ የምትሰጥ አ ብቸኛዋ ኢትዮጵያ አለቀስኩላት፤አዘንኩላት (ኢትዮጵያ አገሬ  ሞኝ ነሽ ተላላ የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ)።

አሳዛኙ የዚህ ጦርነት ገጽታ ግን “ኢትዮጵያዊው ጦር እና ሕዝቡ” በሁለት ጠላቶች ማለትም በኦሮሙማው አብይ እና በወያኔ ትግሬዎች ጦር መሃል ተከብቦ በሴራ ተጠቅቶ ወያኔ እስከ መጨረሻው ተከብብቦ እያለ ፍጻሜው ከመፈጸም ይልቅ ‘ግማሽ መንገድ” ትቶት ዛሬም በወያኔ ቁጥጥሩ ሥር ያሉት ማሕበረሰቦች ስቃይ ውስጥ ይገኛሉ።

አባ ማትያስ ሆይ!

ብፁእነትዎ ህወሓት ለ27 አመታት ሀገሪቱን በጭካኔ መግዛቱን ያውቃሉ።እርስዎን የሾመውም እራሱ በወያኔ ፈቃድነት እንጂ ባይፈቅድ አይሾሙም ነበር። በትግሬዎች ዘመን ሁለት ትግሬ ጳጳሶች ተሽሟል፡ አንዱ እርስዎ ነዎት።

በዚህ ወቅት ትግሬዎች መንግሥታቸው አድርገው ሲቀበሉት ብዙዎቹ ግን ለጥቂት ውቅት ካልሆነ በስተቀር ተቀባይነት አልነበረውም። የትግሬ ወያኔ መሪዎች በነገሡበት በ27 አመት ወቅት ኢትዮጵያን ዘርፈው አገሪቱ አይታው በማታውቀው ዘርፈ ብዙ እና ውስብስብ ማህበራዊና ፖለቲካዊ፣ ችግሮች ውስጥ አስገብተዋት ሄደዋል። በተለያዩ ብሄረሰቦች መካከል አለመተማመንን የመዝራት ፖለቲካን ያራምዱ እንደነበር እርስዎ ያወቃሉ። በሁለቱ ትልልቅ ብሄረሰቦች በኦሮሞ እና በአማራ መካከል አለመግባባት ለመፍጠር በአደባባይ በመስራት ሁለቱም እርስበርስ የሚቃረኑ መሆናቸውን በመግለጽ የሀገሪቱን አንድነት ዋጋ ያስከፈለ አደገኛ እርምጃ በማራመድ ጣሊያን ሲከተለው የነበረው ፖለቲካ በመተግበር የሕዝብ እልቂት አስከትሏል። አሁን የእርስዎ መንበር እየተናጠ ያለው የሰበቡ ምንጭ ወያኔዎች የተከሉት የዘር አስተዳዳር ነው።

በ27 አመት ውስጥ የሕወሃት አባላት የፖለቲካ ምህዳሩን ከመቆጣጠር በተጨማሪ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትን እና ሌሎች ቁልፍ የጸጥታ መዋቅሮችን ተቆጣጥሮት እንደነበር ያውቃሉ። ዛሬም በምትኩ የተተኩ ኦሮሞዎች ያንኑ የትግሬዎች ፈለግ ተከትለው ጦሩን በቁጥጥር ስራቸው አድረገውታል።ሃይማኖቱም እንዲሁ ከሞላ ጎደል ተቆጣጥረው በከፊል ወደ እርስዎ መጠተው መንበርዎንም እያወኩት ይገኛሉ።

 እንደሚታወቀው በኢትዮጵያ ብሔራዊ መከላከያ ሰራዊት ውስጥ ካሉት 49 ከፍተኛ የጦር ጄኔራሎች 34 (70 በመቶው) በህወሓት የተሾሙ የትግራይ ተወላጆች መሆናቸውን ይታወቃል።

የሕወሃት ብሄር ተወላጆች በሌሎች ወሳኝ የመከላከያ ክፍሎች ማለትም በመሀል እና ዝቅተኛ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ተመሳሳይ አብላጫውን ይዘው ነበር። በዚህ የሙሉ በሙሉ ቁጥጥር በመነሳት የሰሜን ዕዝ ጦር በተኛበት ድንገተኛ ጥቃት በመፈጸም ሙሉ በሙሉ ጦሩ አዘናግተው ከነመሳሪያው እና ከፍተኛ አገር አቋራጭ ተምዘግዛጊ ሚሳይሎችን ሁሉ በቁጥጥር አውለው የአገሪቱ ደህንነት አደጋ ላይ በመጣል ሱዳኖች ድምበር አልፈው ቦታ ይዘዋል። ወያኔ ከሱዳኖች የጋራ ሴራ መፈጸማቸው ይታወቃል። አሁንም ሙሉ ድጋፍ እያደረጉላቸው ነው።

ክቡር ፓትርያሪክ ሆይ!

በግዛት ክልል ህወሓት ኢትዮጵያን በመዝረፍ፣ አዋጊ ጀኔራሎችና ኮለኔሎቹንና እንዲሁም አለም አቀፍ የሰላም ጓድ ወታደሮች (በብዛት ትግሬዎች ስለነበሩ) ተመድበው የነበሩ ወታደሮች ሳይቀሩ በገፍ ተጠራርተው አገሪቱን ከድተው ያንን ሁሉ የሰው ሃይል ተጠቅሞ የትግራይን ወሰን ማስፋት፣ ታላቋን ትግራይን የመመስረት አላማ እንደሆነ እርስዎ አይስቱትም። ስለሆነም ጦርነቱ አገርን የማዳንና አገር በማፍረስ መካክል የታየ ጦርነት ነበር አርስዎ አይስቱትም ብየ እገምታለሁ።

 ብፁእነትዎ እንደሚያውቀው ህወሓት ከቀደመው አላማው ጋር የተጣጣመ የሚመስሉ በርካታ እርምጃዎችን ወስዷል። ህወሀት ከወሎ እና ከጎንደር አጎራባች ክልሎች መሬቶችን በተሳካ ሁኔታ ያጠቃለለበት ምክንያት አገር ለመመስረት እና ወደ ሱዳን በር ለመክፍት እንደነበር እርዎም አይስቱትም።

ትግሬዎች ኢትዮጵያን እስከገዛ ድረስ (እርስዎም ከገዢው አንዱ የዘርፍ መዋቅር ነበሩና (በሃይማኖቱ በኩል) ጸንቶ ይቆያል’ ሥልጣን ከተነጠቀ ግን ወደ ግንጣላ እንደሚያቀና አስቦበት ስለነበር፤በኢኮኖሚው ዘርፍ ህወሓት ስልጣን እንደያዘ ብዙም ሳይቆይ ትግራይን መልሶ ለመገንባት ኢንዶውመንት ፈንድ ፎር ሪሃቢሊቴሽን (EFFORT) በማቋቋም አገሪቱን በዝብዞ በትግራይ በርከታ ተቋማትን መስርቶ በመንግሥታዊ ሌብነት የተመሰረቱ የሃብት ምንጮች ወደ ትግራይ በማስጋዝ (The pillage of Ethiopia by Eritreans and their Tigrean surrogates Assefa Negash, (PhD) 1996 ) መጽሐፍ ይመልከቱ (ዛሬም አማዞን የመጻሕፍት መደብር ገበያ ውስጥ ይገኛል) በዘረፋ በተገኘ ከፍተኛ መጠን ያለው የኢትዮጵያ ካፒታል የተደገፈ ትግራይን እንደ አገር ለማስቆም ብዙ ሴራ ተፈጽሟል።

ትግሬዎች እንደልባቸው ተንደላቅቀው ያለ ስጋት ሲኖሩ ንግዱን ተቆጣጥረው ብዙ ቪላዎች ሲገነቡ ሌለው እሰርቤት እየገባ ግፍ ተፈጽሞበታል። ይህንን ግፍ እርስዎ ያውግዙ አያውግዙት ያየሁት ነገር የለም።

ትግሬዎች ጦርነቱን ከወያኔ ወንጀለኞች ጋር የወገኑበት ምክንያት ግልጽ ነው። ከፍተኛ መጠን ያለው የመንግስት ሃብትና የአለም አቀፍ እርዳታ ለብዙ ሚሊዮኖች ህወሓት ግለሰቦችና አመራሮች የዕድገት ምንጭ ነበር።

የወያኔ መሪዎቹ ብዙዎቹ (በወታደሩም በሲቪሉም) የነበሩ ባለሹመኞች በአሜሪካ የስላላ ድርጅት አባልነት ተመልምለው የነሱ ተላላኪዎች ሆነው “ዲሞክራሲያኖች” ናቸው በሚል ሽፋን “የምዕራባዊያን እና አሜሪካኖች”  ተላላኪ ስለነበሩ የፈለጉት የብድር ገንዘብ ፈቅደውላቸው  ከኢትዮጵያ መንግሥት ባንኮች ለኢትዮጵያ የተበደረውን ከፍተኛ መጠን ያለው ዓለም አቀፍ ዕርዳታና ብድር ዘርፈውታል።  ከሕወሃት ጋር ግንኙነት የነበራቸው ፕሮጀክቶችና ግለሰቦች ላይ መጠቀሚያ እንዲውል ተደርጓል።በዚህ ምክንያት ከማዕድን እስከ ኮንስትራክሽን ያሉ ዋና ዋና የንግድ ድርጅቶች ከትግሬዎች አልፎ የተረፈው ለህወሓት አጋር የጎሳ የንግድ ድርጅቶች ፍጆታ ውሏል። ይህንን ከእርስዎ የሚሰወር  ምስጢር አይደለም።ሁሉም በዓይኑ ያየው አስገራሚ ምዝበራና የትግሬዎች ቅጥ ያጣ ትምክሕታዊና ስግብግብ የበላይነት ነበር። (ዛሬም ኦሮሙማው አብይ አሕመድ ያንኑ ስግብግብነት ለኦሮሞዎች ፍጆታ እያስቀጠለው ነው)

ባለፈው 27 አመት የኢትዮጵያ የፖለቲካ ምህዳር ሙሉ በሙሉ የተዘጋ እና የፖለቲካ ተቃዋሚዎችን በጅምላ በማሰር፣ እስረኞች ላይ ግብረሰዶም ሲፈጸም  ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ረገጣ ሲፈጸም አሁን ለትግሬዎች  እንደሚያነቡ እርስዎ  በዘመነ ወያኔ አንድም ቀን ውግዘት ሲያስሰሙ እኔ አልሰማሁም። ካለም ለመስማት ዝግጁ ነኝ።

በሕወሃት እጅ ውስጥ የነበረችውን ጥንታዊና ታሪካዊ ኢትዮጵያ ከመበታተን ለመታደግ ውስጥና ከውጪ ያሉ ኢትዮጵያውያን ባንድነት በመነሳት ተቃውሞ ያስሰማበት ምክንያት እርስዎ በ27 አመት ውስጥ ደምጽ ሳያስሙ ዝምታን መርጠው በነበረበት ወቅት (ካለም ለስሕተቴ ይቀርታ እጠይቃለሁ) ወያኔ በሰሜን ዕዝ ላይ ጭፍጨፋ ሲያካሂድ ተመልሶ ወደ ሥልጣን እንዳይመጣ ሕዝቡ ስጋት ስላደረበት፤ ዜጋ ሁሉ በትግሬ ተዋጊዎች ላይ የተባበረ ክንዱን አስተባብሮ ግስገሳውን ለጊዜውም ቢሆን አሁን ባለበት እንዲቆም ሆኗል።

ብፁእ ፓትርያሪክ ሆይ!

ኢትዮጵያ ዛሬም ከትግሬዎች የድጡ አገዛዝ ወደ ኦሮሞ የማጡ  አገዛዝ (ከትግሬዎች የበላይነት የውስጥ የቅኝ አገዛዝ ወደ  ኦሮሞዎች የበላይነት ውስጥ አገዛዝ) እየተጎተተች እንደሆነ ከእርስዎ የበለጠ የዓይን እማኝ የለም። ትግራይ ውስጥ የተፈጸመ የጦር ወንለጀል ሙሉ በሙሉ ተጠያቂዎች ወያኔ መሪዎች እና አብይ አሕመድና ሹሞኞቹ መሆናቸውን እንዲገነዘቡልኝ እፈልጋለሁ።  

ዐቢይ አገሪቷን ወደ አንድነት ለማምጣት ሳይሆን እየጣረ ያለው ጦርነቱ መነሻም የሁለቱ ሕገወጦች የሥልጣን ጥም ሹኩቻ ያስነሳው ጦርነት እንደሆነ እንዲያውቁት እጠይቀዎታለሁ።

ትግራይ ውስጥ ያሉት ውጭ አገርም ያሉት ምሁራን እና አዲሱ የትግራይ ትውልድ ኢትዮጵያን በመጥላት የተመረዘ ሕሊና ይዘው አገር ለማፍረስ እየተንቀሳቀሱ መሆናቸው እርስዎ ግንዛቤ እንዲያደርጉ ስጠይቅ፤ አሁን ያለው የትግራይ ምሁርና አዲሱ ትውልድ አገር ከማፍረስ ካልተቆጠበና ከዚህ ጦርነት ጉዳት ያስከተለው መዘዝ ትምህርት ካልቀሰመ እና የትግራይ ሕዝብ የሚያደርገው የጦርነት አንቅስቃሴም ሆነ አገር የማናጋት እንቅስቃሴ ራሱን መልሶ ወደ ከፋ ጭለማ እና ጉዳት የሚመራው እንደሆነ አባታዊ ምክርዎን በጽኑ እንዲመክሩ አደራ እያልኩ፤ ትግራይ ውስጥ ያሉ ቀሳውስቶችም ከጠመንጃ ፍቅር፤ቅድስት ኢትዮጵያን ከመዝለፍ ወጥተው ከኮሚኒስታዊ አስተሳሰብና ከአገር ግንጣላ ወጥተው ወደ መንፈሳዊ ትምህርት ጉዞ እንዲያተኩሩ የእርስዎ ምክር ወሳኝ ስለሆነ በዚህ ላይ ትኩረትዎ እንዲበረታ አደራ እያልኩ፤ በመጨረሻም ትግራይ ውስጥ የደረሰው ጉዳት እንዳሳሰበዎት ሁሉ እርስዎም እንደ የሁሉም ዜጋ አባትነትዎ ወደ ዓፋርና አማራ ሕዝብ ሄደው በትግራይ ተዋጊዎች የደረሰውን ጉዳት እንዲያዩና የሕዝቡን ዕንባ የልጃገረዶች መጠቃት ፤ የሴት መነከሳትና አረጋዊያን እናቶች በትግሬ ተዋጊዎች የደረሰባቸው መጠቃት እና የንግድና የሕክምና ተቋማት፤ በአብያተ ክርስትያናትና መስጊዶች የተፈጸመ ጥቃትና የፈራረሱ መኖርያዎች የንብርት ዘረፋዎች ጥልቀት ለመረዳት እንዲችሉ የሕዝቡን እሮሮ እንዲያደምጡ እዛው ድረስ በአካል እንዲጎበኙና ሚዛናዊ ግንዛቤ እንዲያገኙ አጥብቄ እንደ ልጅዎ ድምጼን በማስሰማት እጠይቀዎታለሁ።

አመሰግናለሁ

ጌታቸው ረዳ

 

 

Sunday, March 12, 2023

ኢትዮጵያን ሬሣ እንዳሳደዳት ብዙ አትቆይም!! ዳግማዊ ጉዱ ካሣ Ethiopian Semay 3/12/23

 

ኢትዮጵያን ሬሣ እንዳሳደዳት ብዙ አትቆይም!!

ዳግማዊ ጉዱ ካሣ

Ethiopian Semay

3/12/23

በመላው ዓለም ሰላም ባይኖርም ነገርን በሰላምታ መጀመር መልካም ነውና እንደምን ሰነበታችሁ ውድ አንባቢያን እንዲሁም አድማጮች፡፡ በያላችሁበት ሰላማችሁ ይብዛ፡፡

ይህን “ጸሐፊ” ጨምሮ ብዙ ብዕረኞች ለዘመናት ሲጮሁበት የነበረው ሀገራዊ ጉዳይ ከእሳቱ ወደ ረመጡ፣ ከድጡ ወደ ማጡ እየተንከባለለ መጥቶ ወደድንም ጠላንም አሁን ላይ ወደ እልባቱ እየደረሰ ነው፡፡ ብዙ ብንለፈልፍም የሚሰማን አጥተን ይሄውና “ነባይነ ነባይነ ከመዘኢነባይነ ኮነ” ‹ጮኽን ጮኽን እንዳልጮኽንም ተቆጠርን› የሚለውን ነባር ብሂል በማቀንቀን ላይ እንገኛለን፡፡ “ምከረው ምከረው እምቢ ካለ መከራ ይምከረው” የሚለውንም በድራቦሹ አልዘነጋነውም፤ መጥፎነቱ መከራው ለሁሉም መሆኑ ከፋ እንጂ፡፡ የመጣው የመከራ ዶፍ የሚብሰው ለመከራ ጠማቂዎቹ መሆኑ ግን ይታሰብበት፡፡ በነገራችን ላይ የመጻፍ ፍላጎቴን ከተኛበት ለመቀስቀስ ስንት እንደተቸገርኩ እኔ ነኝ የማውቀው፡፡ በአዝመራ ወቅት ንግግር ማብዛት ገበሬን ሥራ ማስፈታት ነው፡

ሀገራችን ያለችበት ሁኔታ የተዘበራረቀ እንደመሆኑ እኔም በዚህች ማስታወሻ የማስተላልፈው መልእክት ሥነ ጽሑፋዊ ውበትና መልክ የሌለው እንዲሁ አለሁ ለማለት ብቻ ብሶት ወለድ ዝባዝንኬ መሆኑን አስቀድሜ መግለጽ እወዳለሁ፡፡

በርዕሴ ስለጠቀስኩት ቁም ነገር አዘል ግለሰባዊ ገጠመኝ ትንሽ ላብራራ፡፡ ብዙዎች በተለያዬ አጋጣሚ ለንግግራቸው ማጣፈጫነት ቢጠቀሙበትም ነገሩ እውነት ነው፡፡ አንድ ባለጠመንጃ ከኋላው ዱላ ብቻ የያዘ ባላንጣው ያሯሩጠዋል፡፡ ሞይዘር ታጣቂው ሰውዬ ዱላ የያዘው ጠላቱ አሯሩጦ ቢደርስበት በያዘው ውኃ የማያሰኝ ዱላ አናቱን ቀንሽሎ እንደሚጥለው ያውቃል፡፡ ዘወር ብሎ በጥይት አናቱን ብሎ እንዳይገነድሰው ደግሞ አሳዘነው፡፡ የመሣሪያቸው አለመመጣጠንም የባለጠበንጃውን ኅሊና ሸንቆጥ ሳያደርገው አልቀረም፡፡ ጂቡቲ አሜሪካንን ልትወጋ ጦር ስታሰልፍ ይታያችሁ፡፡ ችግሩ ደግሞ ትግስትህ በዝቶ ፍርሀት እስኪመስል ድረስ አንድን ጠብ ስትሸሸው ጠበኛህ ልግነንብህ የማለቱ ፍቺ-አልባ ዕንቆቅልሽ ነው፡፡ እናልህ ያ የሚሸሽ ባለጠበንጃ ሲብስበት “ወገኖቼ፣ እባካችሁን ከዚህ ሬሣ ገላግሉኝ፤ ሬሣ እያባረረኝ ነው፡፡” በማለት የሰዎችን ዕርዳታ ተማጠነ ይባላል፡፡ ሲጀመር ጠላት አያጋጥምህ፤ ካጋጠመህ ደግሞ አስተዋይ ጠላት ያጋጥምህ፡፡ ያን ባለዱላ ጅላጅል ሰው የመሰለ ኦሮሙማ የሚባል ጠላት ሀገራችንን ገጥሟት እየሆነች ያለችውን ሁላችንም እናውቃለን፡፡ አያድርስ በሉ፡፡

ብአዴን ሰሞኑን ታላቅ የሚባል ዝግ ስብሰባ አድርጎ ነበር - መቼም ወግ አይቀርም፡፡ አሳዳሪዎቹ ጨፌዎች ሲሰበሰቡ አይቶ እኮ ነው፡፡ ውጤቱን ብዙዎቻችን በጉጉት ብንጠብቅም ባርነትን ባሕርይው ካደረገ አካል ዱሮውንም የሚገኝ አጥጋቢ ነገር የለምና ቄሱም መጽሐፉም እንደተሸበቡ ስብሳቦሹ ማብቃቱ ተነገረ፡፡ አንዱ “ዝምቤን እሽ ትልና ዋ! አሳይሃለሁ!” በማለት አንዱን ወጠምሻ ጓደኛውን ይዝትበታል አሉ፡፡ ወጠምሻው የዋዛ አልነበረምና የሸሚዙን እጀታ እየጠቀለለ “ምናባህ ልታደርግ ፈለግህ?” ብሎ ቢያፈጥበት “እታዘብሃለኋ! ሌላማ በምን አቅሜ!” አለው አሉ፡፡ አዎ፣ ማውራት ቀላል ነው፡፡ ያወሩትን መተግበር ግን ልብ ይጠይቃል፡፡ እንጂ ከ100 ሚሊዮን የሚበልጥ ሕዝብ ከጎኑ ሊሰለፍለት የሚችል አንድ ድርጅት ተፈጥሯዊ የዘረመል ችግር ከሌለበት በስተቀር ለነፃነት በተነሳሳ የሚሊዮኖች የነፃነት ትግል ስሜት ላይ ቀዝቃዛ ውኃ ባልከለሰበት ነበር፡፡ ይሁን ይህም ለበጎ ነው፡፡ ምናልባት በዚያ በኩል የሚመጣ ነገር አዋጪ ባይሆን ነው፡፡ ከኢሕአዲግ ጉያ የወጣውን አሻጋሪ እስኪያቅረን አየነው አይደል?

ብአዴንን ባሰብኩ ቁጥር ወደአእምሮየ ከሚመጡ ሥነ ቃላዊ ይትብሃሎችና የመጻሕፍት ንባብ ትውስታዎቼ መካከል የፍቅር እስከ መቃብሩ ፈረጃ የሚባል ገጸ-ባሕርይ ቀዳሚው ነው፡፡ ፈረጃ፣ አመቴ፣ ሰጠኝ መርቆና የመሳሰሉት ስሞች በዱሮው ዘመን የወንድና የሴት ባርያዎች ስሞች ነበሩ፡፡ ፈረጃ የፊታውራሪ መሸሻ ባርያ ይመስለኛል - ካልተዘነጋኝ፡፡ የብዕር ስም አባቴ የጉዱ ካሣ ወዳጅ ነው፡፡ ጉዱ ካሣ ደግሞ በዚያን ዘመን ተራማጅ አስተሳሰብ ያላቸውን ወገኖች የሚወክልና በዚያም ሳቢያ እንደዕብድ የሚቆጠር ነበር፡፡ ጉዱ ካሣ ባርነትን ስለሚቃወም የፈረጃን ስም ወደ ዕዝራ ይለውጥና በዚያ ስም እንዲጠራ ፈረጃን ወደርሱ ጠርቶ ያስረዳዋል፡፡ ፈረጃም የጉዱ ካሣን ገለፃ ካዳመጠ በኋላ በራሱ የሚጣፍጥ አንደበት እንዲህ ይለዋል፤ “አይይ! ገቶች፣ ኢኔን ሶው ሚያቁኝ በፈረጃ ኖ ንጂ ቤዝራ አዴሌም፡፡ ገቶች፣ ኢሂ ሲም ኢቅርብኝ፤ ሰዎቹ ኢሲቁቢኛል ኢኔን፡፡” ባጭሩ ብአዴን ማለት ፈረጃ ነው፡፡ ፈረጃና ብአዴን የባርነት አስተሳሰባቸውን ከሚለውጡ የክርስቶስን አባባል ልዋስና ግመል በመርፌ ቀዳዳ ብትሾልክ ይቀላል፡፡ ባርነትን በአንድ አእምሮ ውስጥ ለማጽናት ዐርባ ዓመታት ከበቂ በላይ ናቸው፤ ስለዚህም አይፈረድባቸውም፡፡ ከአሁን በኋላም ሥነ ልቦናቸው ሊስተካከል አይችልም፡፡

 ዛሬ ድንገት ተነስተህ ብአዴንን አማራን ነጻ አውጣው ማለት ከእባብ ዕንቁላል ዕርግብ እንዲፈለፈል የመጠበቅ ያህል ጅልነት ነው፡፡ ስለዚህ ሰሞኑን የነበረን ተስፋ ከንቱ እንደሆነ መረዳት ተገቢ ነው፡፡ ይህ ማለት ግን ነጻነታችን ይቀራል ማለት እንዳልሆነ መገንዘብ ይገባል፡፡ በፍጹም!!

አንድ እውነት እንረዳ፡፡ አማራ ሁለት ነው፡፡ ኦሮሞ ሁለት ነው፡፡ ትግሬም ሁለት ነው፡፡ እያንዳንዱ ነገድና እያንዳንዱ የሰው ልጅ በተናጠልም ሆነ በቡድን እንደአጠቃላይ እውነት ሲታይ ሁለት ነው፡፡ ይህም ሁለትነት አንድም ክፉ አንድም ደግ በሚል ይገለጣል፡፡ ክፋትና ደግነት በዘር ሐረግና በቀለም ወይም በፆታና በሃይማኖት የሚወሰን አይደለም፡፡ አማራ ሆኖ ከወያኔና ከኦነግ/ኦህዲድ ጋር በመተባበር አማሮችን የሚፈጅ አለ፡፡ ከነዚህ ዜጎች መካከል ብዙዎቹ “የባንዳ ልጆች በመሆናቸው ቂም በቀል ቋጥረው ነው ለዚህ ሥነ ልቦናዊ ደዌ የተጋለጡት” መባሉን ሳንረሳ፡ በዚህ ረገድ ከበፊትም ሆነ ከአሁን ትውልዶች እነክፍሌ ወዳጆን፣ እነ ገነት ዘውዴን (ዮዲት ጉዲትን)፣ እነ ሙሉጌታ አሥራተ ካሣን፣ እነ ደመቀ መኮንንን፣ እነ አገኘሁ ተሻገርን፣ እነ ተመስገን ጥሩነህንና በርካታ ይሁዳዎችን መጥራት እንችላለን፡፡

ከነዚህ ክፉ ሆዳሞች በተቃራኒ ደግሞ አማራ ሳይሆኑ ለአማራ ከባርነትና ከዘር ፍጂት ነፃ መውጣት ቤት ንብረታቸውን ይቅርና ሕይወታቸውን ሳይቀር ሳይሰስቱ የሰጡ የሌሎች ነገዶች አባላት አሉ፡፡ ምሣሌ መጥቀስ ቢያስፈልግ የቅርብ ወዳጄ ትግሬው የethiosemay.blog.com ባለቤት ጌታቸው ረዳ ከየትኛውም አማራ በበለጠ ወያኔን ሲታገል የነበረና አሁንም ኦሮሙማን እየታገለ ያለ ብዙም ያልተዘመረለት ድንቅ ዜጋ ለምለው ነገር ኅያው ምስክር ነው፡፡ ወላይታው ታዲዮስ ታንቱ አሁን ድረስ በእስር የሚማቅቀው አገኘሁ ተሻገርንና ሒሩት ካሣን፣ ዳግማዊት ሞገስንና ንጉሡ ጥላሁንን ከእስርና ጊዜውን ጠብቆ ከማይቀርላቸው የበላዔሰብ ዕርድ ነፃ ለማውጣት ነው፡፡ እነታምራት ነገራ፣ እነታዬ ቦጋለ፣ እነፋንታሁን ዋቄ… ኦሮሞ ሆነው ሳለ ብአዴን የሞት ፍርድ የፈረደበትን አማራ ከብአዴን ከራሱ ጭምር ነጻ ለማውጣት የሚታገሉ ከዘር፣ ከቋንቋና ከሃይማኖት የመካኖች አምልኮት ነፃ የወጡ ብርቅዬ ዜጎች ናቸው፡፡

ሕይወት ዕንቆቅልሽ ናት፡፡ አማራ፣ ትግሬ፣ ኦሮሞ … መባባሉ ካለዘር ክፍፍሎሽና ካለቋንቋ ልዩነት እንጀራ ቀምሰው የሚያድሩ ከማይመስላቸው ድውያን ፖለቲከኞች ሌላ የሚጠቅመው አንድም የኅብረተሰብ ክፍል የለም፤ ለነገሩ አገኘሁ ተሻገር በዚህ ዕውቀቱ ለዘበኝነትም የማይበቃ ገልቱ ደንቆሮ፣ አቶነቱን በተጭበረበረ ‹ኮሎኔል ዶክተር› የተካው የኢንጂኔር ዶክተር ሣሙኤል ታናሽ ወንድም አቢይ አህመድ ከአትክልተኝነትና ግፋ ቢል በትወናው ዓለም ኢያጎንና ሻይሎክን ከመሳሰሉ የትራጂ-ኮሜዲ ትያትሮች የገጸ ባሕርይ ሚና በዘለለ ለአንድም ኃላፊነት የማይታጭ ሰው ይቺን መከረኛ እንጀራ ሊያበስል የሚችለው በረከሰ እንጂ በተቀደሰ መንገድ ሊሆን እንደማይችል ከመነሻው ግልጽ ነው፡፡ ስለሆነም በዘርና በቋንቋ መፈራረጁ ለበለጠ ውድመት ከመዳረግ ውጪ አንዳችም ጥቅም እንደሌለው አሁን ከመሸም ቢሆን መረዳት በተለይ በኢትዮጵያ ሰማይ ሥር ጥቁር የኦሮሞ ታሪክ ለማስቀመጥ የሚራወጡ ጥቂት ኦሮሞዎች ቢረዱ መልካም ነው፡፡ በነገራችን ላይ የደጋጎችንና የክፉዎችን ምጣኔ (ሬሽዮ) በተመለከተ መነጋገር ይቻላል፡፡ በኔ ዕይታ ለምሣሌ አብዛኛው ትግራዋይ በወያኔ አንደርባዊ ምላስ ተረትቷልና የቀደመችዋን ባንዲራውን ንቋል፡፡ ጊዜ ይፍታው፡፡ በአሁኑ ወቅት ደግሞ ይሄ ኦሮሙማ የሚሉት ወንዝ የማያሻግር ሰይጣናዊ ዕቅድ ብዙዎችን በተለይም ከትምህርትና ከዕውቀት የራቁ ወጣቶችን በህልም ዓለም ስካር ዘፍቆ አሳራቸውን እያበላቸው እንደሆነ መረዳት አይከብድም - ይህንንም ጊዜ ይፍታው፡፡ ስለሆነም የቁጥር መበላለጥ ካልሆነ በስተቀር በሁሉም ነገድና ጎሣ ክፋትና ደግነት አለ፡፡ ምርጫው የኛ ነው፤ ለምርጫ ደግሞ የጊዜ ገደብ የለውምና ለአላፊ ጠፊ ሀብትና ሥልጣን ብለን ታሪክ እያጠፋን ያለን ሰዎች ልብ እንግዛ፡፡

 

ኦሮሙማ አሁን ምን እያደረገ እንደሆነ የአደባባይ ምሥጢር ነውና መናገሩ ትርፉ ድካም ነው፡፡ ቢሆንም በተለይ የአማራ መፈናቀልና በያለበት እንደዐይጥ መጨፍጨፍ ዱሮ ሩቅ የነበረው አሁን አዲስ አበባ መግባቱን ማስታወስም አግባብ ነው፡፡ ዱሮ ጉራፈርዳ ነበር፤ ዱሮ አሰቦትና ገለምሶ አካባቢ ነበር፡፡ ዱሮ ባሌና ሻሸመኔ፣ አርባጉጉና በደኖ ነበር፡፡ በቀደምለት ወለጋና ሻምቡ፣ ደምቢዶሎና ጊምቢ ነበር፡፡ አሁንና ዛሬ ግን የፈራነው ነገር ድሆ ድሆ መጣና እዚችው አዲስ አበባ ውስጥ ገባ፡፡ ሸገር የተባለ ሳተርን የሚባለውን ፕላኔት የመሰለ ከተማ በ154 ሸህ ሄክታር የመሬት ስፋት፣ 54 ሽህ ሄክታር በምትገመተዋ የቀድሞ አዲስ አበባ የአሁን መጋላ ፊንፊኔ ቫቲካን ዘኦሮምያ ከተማ ዙሪያ ተመስርቶ በዚህ ከተማ ውስጥ የሚገኝ ኢ-ኦሮሞ ሁሉ በአጭር ጊዜ ውስጥ ሊጠረግ ሥራው ተጀምሯል፡፡ በዚህም ሳቢያ ለዘመናት ያፈሩትን ሀብት ንብረት እንኳን ይዘው ለመውጣት ሳይፈቀድላቸው ቤታቸው በዶዘር እየፈረሰ ነው፡፡ እምቢ የሚሉትንም በጥይት እየቆሉ ለጅብ ሲሳይም እየዳረጉ ሕዝብ እንደኢየሱ ክርስቶስ በማያባራ ኤሎሄ ላይ ይገኛል፡፡ አማራ ወደ አዲስ አበባ የሚገባው ሽመልስ አብዲሣ ሲፈቅድ ብቻ ነው፡፡

የኑሮ ውድነቱም ከዘር ፍጂቱ ባልተናነሰ ሕዝቡን በርሀብ እየቆላው ነው፡፡ የሁለት ሽህ ደሞዝተኛ የአሥር ሽህ ብር ጤፍ እየገዛ ቤተሰቡን እንዲቀልብ ፀሐዩ የኦሮ-ፌዴራል መንግሥታችን ዕድሉን አመቻችቶለታል፤ ዘንድሮ መቼም ጉድ ነው፡፡ አዲስ አበባ ነዋሪዎቿ እየተፈናቀሉ ሰው አልባ የመናፈሻ ብቻ ደሴት እየሆነች ነው፡፡ ባጃጆችም በዘር ተፈርጀው አማራ ሆኑና ሥራ እንዲያቆሙ ተደርገው ትራንስፖርቱም ወደ 16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ተመልሶ በፈረስና በአህያ በሚጎተቱ ጋሪዎች እንዲከናወን ኦሮሙማ አውጇል፡፡ በሃይማኖቱ ረገድም ዱርዬ ልጆችን ከየጫትና ሺሻ ቤቱ ሰብስበው ጳጳሣት በማድረግ አስቂኝ ትያትር እየሠሩ ነው - ኦርቶዶክስን ለማጥፋት፡፡+ አዲስ አበባ ውስጥ ኦሮሞ ካልሆንክ ሥራ አትይዝም፤አትነግድም፤ ጉዳይህ አይሳካም፤ ትናቃለህ፤ ትንጓጠጣለህ፤ ትሰደባለህ፤ ምን አለፋህ ከሰው በታች ነህ - ለነሱ፡፡ የኦሮሙማን ስንክሳር አውርቶ መጨረስ አይቻልም፡፡ ኦሮሞ ነኝ የሚል ከሌሎች ወዳጆቹ ጋር ተባብሮ እነዚህን የብዔል ዘቡል ልጆች በቶሎ አደብ ካላስገዛ እኔ ስለወደፊቱ ታሪካችን በጣም እፈራለሁ፡፡ ጥቂት ኦሮሞ ብዙውን ኦሮሞ ይዞት እንዳይጠፋ ትልቅ ሥጋት አለኝ፡፡ የነዚህ ሰዎች ዕቅድ መና የሚቀር ስለመሆኑ ግና ሃሳቡ አይግባችሁ፡፡

 

አቢይ አህመድ የሊቀ ሣጥናኤል ልጅ ነው፡፡ እዚህ መናገር በማልፈልገው ብዙ ነገሮች የምጠረጥረው ይህ ብላቴና ወዶና ፈቅዶ በገባበት የሰይጣን ዓለም ውስጥ እንደልቡ እየዋኘ ያሻውን እያደረገ ነው፡፡ ሲጀመር ይህ ሰው ዕብድም ነው፡፡ ነገረ ሥራው ሁሉ ከለዬለት ዕብድም በከፋ ቅዠቱን ሁሉ እውን ለማድረግ ዕንቅልፍ አጥቶ የሚቃትት ወፈፌ ነው፡፡ ሴቴኒዝም ቀላል ወጥመድ እንዳይመስላችሁ፡፡ በሰይጣናት አብያተ-አጋንንት ሥጋ ወደሙ የሚፈተተው በሰው ሥጋና ደም መሆኑን መቼም ታውቃላችሁ፡፡ እናም አቢይን መሰል የአጋንንቱ ዓለም ወኪሎች እንዲገደሉ ዒላማ ተደርገው የሚሰጧቸውን ምስኪን ዜጎች በየቀኑ ካልገደሉና የሰው ደም ካላፈሰሱ ምድራዊ ጌቶቻቸው ይቆጧቸዋል፤ የጥልቁ ባሕር ንጉሣቸው አያ ሉሲፈርም ይገስጻቸዋል፤ ይቀጣቸዋልም፡፡ ስለዚህም ለጌታቸው ቢቻል በየቀኑ ጭዳ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ጦርነቱ በሰውና በሰው ብቻ ይመስላል፡፡ ነገሩን ሲመረምሩት ግን ቀላል አይደለም፡፡ ሰይጣን ሌላውን ዓለም ተቆጣጥሮ ራሽያንና ኢትዮጵያን የመሳሰሉ ጥቂት ሀገሮች ብቻ ስለሚቀሩት የሞት የሽረት ትግል እያካሄደ ነው - ዘመኑም ደርሷልና፡፡ ለዚህ ጦርነቱ ከመለመላቸው ውስጥ የኡክሬኑ ዘለንስኪና የኛው ጉድ አቢይ በዋነኝነት ይጠቀሳሉ፡፡ ግብራቸው ተልእኳቸውን በግልጽ ይመሰክራል፡፡ የዘለንስኪ ሰዎች በጥቁሮች ላይ የሚሠሩትን ግፍ ልብ በሉ፡፡ ይህ ሰው ይህን ሁሉ ዕልቂት ወዳገሩ ያመጣው በምን ውል እንደሆነ ተረዱ፡፡

ነገር አበዛሁ፤ ይቅርታ፡፡ የኔም የሀገራችንም ማጠቃለያ ደርሷል፡፡ ውስጤ በል ያለኝን ነው የምናገረው፡፡ ሰይጣን ይሸነፋል፡፡ የሚሸነፈው ግን በሥራ እንጂ በምኞት አይደለም፡፡ ወደመፍትሔው ስንመጣ የሃይማኖት አባቶች በቅድሚያ ራሳችሁን ፈትሹ፡፡ ነገራችን ሁሉ “ቤታቸውን ከፍተው ሰው ሌባ ይላሉ” እንዳይሆን እግዚአብሔርን ከሚያስከፋ ነገር ተቆጠቡ - በዚህ ዙሪያ ሆን ብዬ ብዙ ነገር አልናገርም፡፡ ግና የምትሰብኩትን ሁኑ፤ የምትሉትን ኑሩበት፡፡ ጸሎት ምህላችሁን እንደሥራ ግዴታ ሣይሆን የእውነት ይሁን፡፡ ያኔ ከፈጣሪ ጋር የሚኖረን ግንኙነት በምንም መንገድ “ጃም” አይደረግም - ኩልል ይላል፡፡ እኛ ምዕመናንም ሳል ይዞ ስርቆትንና ቂም ይዞ ጸሎትን እንጠየፍ፡፡ ፈጣሪ ንጹሕ ልብን ይሻል፡፡ ከልብ መዋደድን፣ ከልብ መተዛዘንን፣ ከልብ ይቅር መባባልን እንልመድ፡፡ ሰው ሰው እንሽተት፡፡ ከሜካኒካዊ የሮቦት ሕይወት በአፋጣኝ ወጥተን የፈጣሪን መንገድ እንከተል፡፡ በክፋትና በኃጢኣት መንገድ እስከተጓዝን ድረስ እኛም ሆን ኦሮሙማዎች ለፈጣሪ አንድ ነን፡፡ በቅርቡ እንደሚደረግ ለሚጠበቀው የመለያ ምት “ጨዋታ” ብቁ ሆነን ለመገኘትና የዋንጫው ባለቤት ለመሆን ከፈለግን ከጠላቶቻችን ደካማ ጎን በመነሳት የሣምሶንን ሥጋዊና የክርስቶስን መንፈሳዊ የማጥቃት ጥበብ ከወዲሁ እንላበስ፡፡ ያኔ ዳዊትን እንሆንና ራሳቸውን በትዕቢት እንደጎልያድ ሰማይ ድረስ የቆለሉ የሣጥናኤል ወኪሎችን በቀላሉ ድል እንነሳቸዋለን፡፡

የሆነው ሁሉ ቢሆን የማታ የማታ ከዚህ ሁሉ ትርምስ በኋላ ድሉ የማን እንደሆነ እኔ ብቻ ሳልሆን እነሽመልስም ያውቁታል፡፡ ለዚህም ነው ክፉኛ የሚቅነዘነዙት፡፡ ሰይጣን ኀሊናን ሲያሳውር ጭላንጭል እንኳን አይተውም፤ ለዚህ ነው እነአቢይ በአሁኑ ሰዓት የእግዜርን ዐይን እየቧጠጡ የሚገኙት፡፡ ግን ግን በመጨረሻው የሕወሓትን ዕድል እንኳን እንደማያገኙ በጣም ግልጽ ነውና እባካችሁ የምትቀርቧቸው ንገሯቸው፡፡ ለከት የሌለው ዕብሪት የሚያስከትለውን መዘዝ ታሪክን እያጣቀሳችሁ አስረዷቸው፡፡ //

Friday, March 3, 2023

ለአባ ማትያስ ጥያቄ፦ አገርዎ የት ነው? ከበባውና ጭፍጨፋውስ ማን ጀመረው? የከበባውና የእገዳው ተጫዋቾችስ እነማን ናቸው? ትግራይ የቀመሰቺው መከራስ ለምን ሌሎችም መቅመሳቸውን አስደሰትዎት? ጌታቸው ረዳ Ethiopian Sema 3/3/23


ለአባ ማትያስ ጥያቄ፦ አገርዎ የት ነው? ከበባውና ጭፍጨፋውስ ማን ጀመረው? የከበባውና የእገዳው ተጫዋቾችስ እነማን ናቸው? ትግራይ የቀመሰቺው መከራስ ለምን ሌሎችም መቅመሳቸው አስደሰትዎት?

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Sema

3/3/23

አቡነ ማትያስ ጨካኝ አነጋርና ወገንተኛ ንግግራቸውን ከተናገሩት ንግግር መካካል በዚቺው ሐረግ ልጀር:_

 <<፡ትግራይ ብቻዋን አይደለችም ትግራይ ያየቺው መከራ ሁሉም ቀምሶታል፡ “ለምን”? ብትሉ “መቸም እግዚኣብሔር “ዳኝነቱን አይተውምና ሌሎቹም እንዲሁ መከራና ግፍ እንዲቀምሱዋት አድርጓዋል።” እግዚአብሔር ከትግራይ ጋር ነው የቆመው ብሎ የነገሩን የእዚአብሔር ወኪላችን የሆኑት አባ ማትያስ ከትግራይ ጋር የቆመው እግዚአብሔርም ሌሎቹም መቅመስ እንዳለባቸው እግዚአብሔር በትግራይ ውክልናው ሌላውም ሕዝብ አብሮ እንዲሰቃይ ማድረጉን መደሰታቸው "ሚዛናዊ" መሆኑንም በሚገርም ወገንተኛነትና ጭካኔ ተናግረዋል።       

አሁን ወደ ዝርዝር ንግግራቸው ልግባ:-

የኢትዮጵያ ፓትርያሪክ አባ ማትያስ ለአቡነ ዮሐንስ ቀብር ትግራይ መቀሌ ከተማ ተገኝተው ያደረጉት የትግርኛ ንግግራቸው ከመጥቀሴ በፊት ለአባ ማትያስ ቅርብ የሆናችሁ ሰዎች ስለ ትግራይ famine (የርሃብ ሁኔታ) እና ሰብአዊ መብት ጉዳይ ጥሰት በሚመለከት በተባበሩት መንግሥታት የኢትዮጵያ “የዓለም አቀፍ ምግብ ተራድኦ መርሃ ግበር’’ በዋና ዳይረክተርነት ተመድቦ በቅርብ የትግራይን ሁኔታ በአካል እዛው ሆኖ የተመለከተና ያስተባባረ ኬኒያዊው እስቲቨን ኦማሞ (S.W.Omamo) At the Center of the World in Ethiopia የተባለው አስገራሚ የአይን እማኝ የጻፈውን መጽሐፍ ገዝታችሁ ብጹእነታቸው እንዲያነቡት ብትሰጥዋቸውና እሳቸው እየነገሩን ካላቸው  አጭር አረዳድ ሰከን ብለው እንዲመረምሩት ይረዳቸው ዘንድ እየተማጸንኳቸው በንግግራቸው የተጠቀሙባቸው የወያኔዎች የሚጠቀሙዋቸውን ቃላቶች “ቃል በቃል” ሳይለውጡ ሳይቀንሱ “ከበባን ዕጽዋን” የሚሉትን << የከበባውና የቁለፋው>> ተዋናይ ወንጀለኞቹ የሆኑት የወያኔዎችን ፕሮፓጋንዳ አድምጠው ከመሳሳት እንዲድኑ እውነታው በዛው መጽሐፍ ተዘግቦ ስለሚያገኙት በንጽሕ ልቦና ጸልየው መጽሐፉን እንዲያነቡት አደራየን እያስተላለፍኩ አሁን  ወደ ንግግራቸው እገባለሁ።

ለአብነ መትያስ እንኳን ደህና መጡ ንግግር ያደረጉት ከዋናው ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ከተገነጠሉት አንዱ የሆኑት የዌያኔ ተከታይ አቡን ናቸው። እሳቸው እንዲህ በሚል ንግግራቸውን ከፈቱ፡

<<ብጹእ ወቅዱስ ፓትርያሪክ ዘኢትዮጵያ ተለያይተን በማንገናኝበት በዛች ሰዓት አባታችን ከሕዝባቸው ከትግራይ ሕዝብ ጋር ሆነው በሩቅ ዕንባቸውን እያነቡና እያለቀሱ፤እየፀለዩ ለሰላም ሲፀልዩ ነበር። በፈጣሪ ፈቃድ በመሃላችን ተገኝተው እነሆ እንኳን ደህና መጡልን።>> በሚል ንግግር ከተቀበሉዋቸው በኋላ

 ብጹእ ፓትርያሪክ አቡነ ማትያስም የእንኳን ቆያችሁ ንግግራቸውን “እንባ” ባጨናበሰው ዓይናቸው እንዲህ እያሉ ንግግራቸውን ጀመሩ፡

<< ትግራይ ውስጥ የደረሰው መከራ በዓለም ምድር ውስጥ ታይቶ ተሰምቶ የማይታወቅ ግፍ ደርሷል። ለአስተርዕዮ ማርያም ለመምጣት ዕቅድ ይዤ ነበር፤ሆኖም ‘ባለሁበት አገር‘ ትልቅ ችግር ስለተከሰተ ችግሩን ለማስተናገድ ሁኔታው ስላልፈቀደ መምጣት አልቻልኩም።ተከብባችሁና ተቆልፎባችሁ የኖራችሁትበን ህይወት በዓለም ውስጥ ያልተሰማ ያልተደረገ በታሪክም ያልተፈጸመ ድርጊት ትግራይ ውስጥ መድረሱ ለመግለጽ እንዴት ብለን እንግለጠው? ስም የለውም፡ ለመግለጥ ለመግለጥ የሚቸግር ተሰምቶም ተደርጎም የማያውቅ በትግራይ ውስጥ ደርሷል፤ ያ ችግር እንዲያልፍ ያደረገው አምላክ ምስጋና ይድረሰው እንላለን። የትግራይ ሕዝብ ጥንካሬ ግን ታአምራዊ ነው፡ከሁለት አመት በላይ ‘ተከብባችሁና ተዘግቶባችሁ’ ኖራችሁ ከዚያ ከተቆለፈባችሁና ከተከበባችሁበት ያወጣችሁ አምላክ ደግሜ ምስጋና ይድረሰው። የትግራይ ሕዝብ ፅናት እንደ ብረት የጠነከረ ነው። ለፅናታችሁ ለጥንካሬአችሁ እግዚአብሔር አምላክ ‘ከናንተው ከትግራይ ሕዝብ’ ጋር ነው ያለው። በሁለመናው ስንመለከተው የእግዚአብሔር እጅ ያለበት ነው። አምላክ ከናንተው ከትግራይ ሕዝብ ጋር ነው ያለው። ያለፈው ሁኔታ አመጣጡ ሃያልና ክፉ ነበር። ግን እነሱ እንዳሰቡት እግዚአብሔር ክፉ አላደረገውም፡ ሆኖም አሁን ያለው ሰላም እንዲጠናከር እየጸለይን የቤተክህነትና የዘመናዊ ትምህርት ተማሪዎች ወደ ትምህርታቸው እንዲመለሱ እንዲሁም እናንተም የትግራይ ሕዝብ ትግራይን ለማቅናትና ለማልማት ሃይልና ብርታቱን እንዲሰጣችሁ ያለፈው መከራም ተመልሶ እንዳይመጣ እግዚአብሔር እናንተንም እኛንም ይጠብቀን። >>

ሲሉ የእንኳን ደህና ቆያችሁ በማለት ለትግራይ ሕዝብ ያደረጉት አጭር ንግግር ይህ ነበር።

አሁን አንድ ባንድ ነጥቦችን ለፓትሪያሪኩ ልጠይቅ።

<< ትግራይ ውስጥ የደረሰው መከራ በዓለም ምድር ውስጥ ታይቶ ተሰምቶ የማይታወቅ ግፍ ደርሷል።>> ሲሉ ደርሶ ሊሆን ይችላል። ሆኖም እርስዎ እንደ የተዋህዶ ክርስትና ሃይማኖት ዋና መሪነትዎ በትግራይ ውስጥ የደረሰው መከራ በዓለም ምድር ውስጥ ታይቶ ተሰምቶ የማይታወቅ ግፍ የትግራይ ሕዝብ እንደ ሕዝብ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ልጆቻቸውን ስንቅ አስንቀውና አስታጥቀው መርቀው ወደ “አማራ እና ወደ ዓፋር ሕዝብ” “ክልል” ገብተው ያደረሱት ግፍና አመጽ ዝርፍያ መነኮሳትና አዛውንት እናቶች መድፈር እንዲሁ በዓፋርና በአማራ ሕዝብስ በትግሬዎች “ተከብቦና ተዘግቶበት” እንደነበርስ ያውቃሉ? ካላወቁስ ለምን እንዲያውቁ ጥረት አላደረጉም?  ከላይ የጠቀስኩት መጽሐፍ ሲመለከቱ እውነትም ከትግራይ ይልቅ የጠቀስኳቸው “የክልሎቹ” ሕዝብ በበለጠ በርሃብና በአመጸኛ የትግራይ ተዋጊ አረመኔ እርምጃዎች እንደተሰቃዩ ይናገራል።

ሰላማዊ የምግብና የመገናኛ አውታሮች ያለ ምንም እንዳይንቀሳቀሱ፤የከተማዎች መብራትን ስልክ በመበጣጠስ፤ ተደጋጋሚ ጦርነት በመክፈትና አውራ ጎደናዎቹን ድልድዮችን በማፍረስና በመቆጣጠር ያወኩትን ያህል ወያኔዎች ትግራይ ውስጥ በየመጋዝኑ ተከምሮ የነበረው ምግብ እና እንደዚሁም የተላከ እና አዲስ ምግብ ተጨምሮ በስርዓት ለትግራይ ሕዝብ እንዳይዳረስ ለዚህ ጉዳይ መዋል የሚቸለው ነዳጅና ከተባባሩት መንግሥታት ምግብ ይዘው ወደ ትግራይ የተጓዙ የጭነት መኪኖች እየተመላለሱ ምግብ እንዳያመጡና በየአውራጃው እንዳያዳርሱ መኪኖቹ ባግባቡ ከመጡበት ወደ አዲስ አበባ እንዲመለሱ ሲጠየቁ ወያኔዎች አሻፈረኝ ያሉበትን በዳሪክተሩና በትግራይ የምግብ አቅርቦት ዋና ሓለፊው በቲዊተር የተመላለሱብትን መልዕክት እነሆ፡

In the previous few months, I had tweeted and re-tweeted pieces like this:

<< Concerning. None of the 149 trucks in the convoy that reached #Mekelle#Ethiopia last week returned only 38 out of 466 trucks that entered #Tigray since 12 July returned> We need trucks to deliver lifesaving assistance to people in #Tigray.>> (P-35)<<

ባለፉት ጥቂት ወራት፣ ከትዊት ወደ ትዊት እንደገና ተደጋጋሚ ትዊት እያደረግኩላቸው ነበር።

<< የሁኔታው አሳሳቢበት!! - ባለፈው ሳምንት ምግብ ጭነው በኮንቨይ/በጥበቃ/ #ከአገሪቱ ወደ #መቀሌ ከገቡት 149 የጭነት መኪኖች ውስጥ አንዳቸውም አልተመለሱም። ከሓምሌ ወር ጀምሮ #ትግራይ ውስጥ ከገቡት 466 መኪኖች ውስጥ 38ቱ ብቻ ሲመለሱ ሌሎቹ ሳይመለሱ እዛው ትግራይ ውስጥ ቀርተዋል። (ገጽ 35)

<< Continued encouraging progress with support of Federal, #Afar and #Tigray authorities. We need hundreds more trucks to come out of Tigray so that large volumes of food can be moved quickly to 5.2 million food insecure people in the region………..>> (ከፌዴራል፣ ከአፋር እና ከትግራይ ባለስልጣናት ጋር በመሆን አበረታች እድገት ቀጥሏል። ከፍተኛ መጠን ያለው ምግብ በፍጥነት ወደ 5.2 ሚሊዮን የምግብ ዋስትና ችግር ወደ ክልሉ እንዲሸጋገር በመቶዎች የሚቆጠሩ ተጨማሪ መኪናዎች ከትግራይ እንዲወጡ እንፈልጋለን።(ገጽ 35)_

  እያለ ወያኔዎችን ለተዋጊዎቻቸው አመላላሽ አድርገው የያዝዋቸው የጭነት መኪኖች ተሎ እንዲመልሱዋቸው ከተማጸናቸውና ወደ የበላይ አካልም ስለ ሁኔታው ካመለከተ በ

እንዲህ ይላል፡

<< For me the issue was very simple: - On trucks, if WEP- contracted trucks did not come out of Tigray, there was no way for us to deliver food into the region at the required scale predictability. Millions of Tigrayans will go hungry…. The bureau Head had himself indicated to my team in Mekelle that the available fuel in the region stood at mill of litters, but that the TPLF’s position was that this fuel would not be provided to WFP and other humanitarian actors, because there were other “more important strategic priorities’’ for the fuel than humanitarian assistance “our fighters are fighting for Freedom”.

 (<< ለኔ ጉዳዩ በጣም ቀላል ነበር፡- WEP ኮንትራት ያሉ ምግብ የምናመላለስብቻው የጭነት መኪናዎች ከትግራይ ካልወጡ፣ በሚፈለገው መጠን ወደ ክልሉ ምግብ የምናደርስበት መንገድ አይኖርም። በዚህ በምክንያት በሚሊዮን የሚቆጠሩ የትግራይ ተወላጆች ይራባሉ። የትግራይ የቢሮ ኃላፊው እራሱ መቀሌ ለሚገኘው ቡድኔ/ለወኪሎቼ/ እንደደገለጸው <<በክልሉ ያለው ነዳጅ በሚሊየን ሊትሮች መጠን ላይ እንደሚገኝ ነገር ግን የህወሓት አቋም ‘’ይህ ነዳጅ ደብሊው.ኤፍ.ፒ. እና ሌሎች ግብረ ሰናይ ድርጅቶች እንደማይሰጥ ነበር የነገራቸው። ምክንያታቸውም ሲገልጹላቸውም ከሰብአዊ ርዳታ ይልቅ ለነዳጁ አስፈላጊ ስትራቴጂካዊ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ሌሎች ጉዳዮች ስላሉን እና ተዋጊዎቻችንም ለነፃነት እየተዋጉ ስላሉ ነው የሚል ነበር።>> 

ይላል።

Later, I shared news of the TPLF’s position on fuel with WFP leadership, expecting that this would lead to a denouncement of some kind…….ይልና ኒውዮርክ ወይንም ጀኔቫ ላላው መ/ቤቱ ቢያመለክትም ምክንያቱ ባላወቀው ምክንያት አጥጋቢ መልስ ሳያገኝ ሲቀር ለትግራይ እርዳታ ሓላፊው ተመልሶ የጭነት መኮኖቹ ተሎ እንዲመለሱ እራሱ ቢጠይቀው አንተ “የአብይ ሮቦት” (አንተ የአብይ አሻንጉሊት ነህ) በሚል ስርዓት በጎደለው መልስ ሲመልስልኝ በጥንቃቄና ጭዋነት በተሞላ እንዲህ አልኩት ይላል።

<< I respectfully but forcefully restating my basic points. We need trucks for our operation. Trucks were not coming out of Tigray. We need fuel for our operations. He himself admitted that the TPLF had fuel. He should let us have it so that we could move food to vulnerable food insecure people. “We have other priorities”, he responded. “Ask Abiy Government for fuel”. This was war. Brutal. (<< አሁንም በአክብሮትና በጥንቃቄ ግን አጽንኦት መሰረታዊ ነጥቦቼን ደግሜ ነገርኩት። የጭነት መኪኖቹ ለሥራችን እንፈልጋቸዋለን። መኪናዎች አሁንም ከትግራይ እንዲወጡ አልፈቀዳችሁም። አብሮም ለሥራችን መቀናት ነዳጅ እንፈልጋለን ስለው፤ እሱ ራሱ በቂ ነዳጅ አለን ብሎ ሲያረጋግጥልኝ፡ ይህ ለአደጋ ተጋላጭ የሆኑ የምግብ ዋስትና ለሌላቸው ሰዎች ምግብ እንድንወስድ ሊፈቅድልን ይገባል ስለው። "ሌሎች ቅድሚያ የምንሰጣቸው ነገሮች አሉን" ሲል መለሰልኝ። በመቀጠልም "ነዳጅ ከፈለግክ የአብይ መንግስትን ነዳጅ ጠይቅ" ብሎኝ እርፍ አለው።>> ይላል ገራሚው ዘገባው ደራሲው በመገረም “ጦርነት ነበር! እጅግ አረመኔ! ይልና “ለመሆኑ ሕዝብ በረሃብ እንዳይሞት ከሰብአዊ ዕርዳታ በላይ ቅድሚያ ሌላ ጉዳይ አለን ሲሉን ከዚህ ወዲያ ቅድሚያ እና አንገብጋቢ ምን ኖርዋቸው ኖሮ ኢሆን?” ሲል የተገረመበትን በሰፊው ይተነትነዋል። አንግዲህ በኢትዮጵያ የአለም አቀፍ የምግብ ተራድኦ መርሃ ግብር ዋና ዲሬክተር ኬኒያዊው “ኦማሞ” የታዘበውን አለም አቀፍ የውሸት ዜና ዘጋቢዎች ባሕሪ እና የወያኔ መሪዎች ሓላፊነት የጎደለው ወንጀለኛ ባሕሪ በመደመም በዛች በመጽሐፉ “This is a book about what I saw, what I felt, what did as Representative and Country Director of United Nation World Food Programme (WFP) in Ethiopia from 2018 t0 2021. How I did, what I did, why and so what effect. What went well, what did not, and why. What I learned. What surprised me, what exited me. What disappointed me. And why. እያለ የዘገበው የመግቢያ ገጽ መጽፉን ትግራይ ውስጥ፤ አማራ እና ዓፋር እና የወያኔ መሪዎችና ተዋጊዎች የታዘበውን በሚገርም ሁኔታ ዘግቦታል።

 

እንግዲህ አባ ማትያስ “የተከበበ፤ የተዘጋበት ሕዝባችን” እያሉ አባ የሚናገሩለት ሕዝብ የችግሩና የከበባውና የመዘጋቱ ምንጭ ቅድሚያ ከሕዝቡ ይልቅ ለራሳቸው ተዋጊዎች ቅድሚያ በመስጠት ሕዝቡ ችግር ውስጥ እንዲገባ ሃላፊነቱ መውሰድ ያለባቸው እራሳቸው የትግራይ ብሔረተኛ መሪዎቻቸው እንደሆኑ ዓለም ምግብ ተራድኦ የኢትዮጵያ ወኪል ዲሬከተር የተመለከተውና የገጠመው አስቸጋሪ ሁኔታ በመጽሐፍ መልክ ሰፊ ዘገባ ማቅረቡን አባ ማትያስ እንዲመለከቱት እጋብዛለሁ።

በመቀጠል ወደ ሌሎቹ የአባ ማትያስ ንግግር ልቀጥል

እንዲህ ያሉትን እንመለክት

<<………

ያንን የአባ ማትያስ ንግግር አንድ ባንድ በሚቀጥለው ክፍል ሁለት ከመተንተኔ በፊት አባ ማትያስ ትግራይ ውስጥ በታሪክና በዓለም ምድር ተፈጽሞ የማያወቅ ድርጊት ሲሉ የሚከተለው ድርጊት ጭምር ይሆን?

<< በበርካታ ካምፖች የትግራይ እናቶች ሠራዊቱ ሲታፈን (ጥቅምት 24 ማለት ነው) ፈንድሻ እየበተኑ ቄጤማ እየነሰነሱ፤ከበሮ እየመቱ የሠራዊቱን አስከሬን እምቧለሌ እየዞሩ ጨፍረውበታል፡ ገድላችሁ ደማቸውን አሳዩን እያሉ የእናት አንጀት የሌላቸው እናቶች ደግሞ ወጠቱን አነሳስተው ሠራዊቱን አስጨፈጭፈዋል፡…….. ገርሁ ሥርናይ ከተማ ፈደግሞ እጅ በሰጡ ሴት ጓዲቶች ላይ የተሰራው ግፍ ሕሊና ያቆሰለ እጅ ከሰጡት ሴት ወታደሮችን ልበሳቸውን አስወለቁ። በብልታቸው እንጨት እየከተቱ አሰቃዩዋቸው። ስቃዩን መቋቋም ሲያቅታቸው ለመንፈራገጥ ሲሞክሩ ፀጉራቸውን ይዘው መንገድ ለመንገድ ላይ ጎተቷቸው። ይህ አልበቃቸው ሲል ራቁታቸውን እንደሆኑ የከተማው ሕዝብ እያያቸው እንዲሮጡ አደረጉ። ይህን የሚያደርጉት ከበሮ ይዘው እየጨፈሩና ራቁታቸውን የሆኑ ሴቶችን ፎቶ እያነሱ ቪዲዮ እየቀረጹ ነው።>> የተከዳው የሰሜን ዕዝ ደራሲ ከታፈኑት ወታደሮች ውስጥ የነበረው ጋሻዬ ጤናው (ቻቻው)

የአባ ማትያስ ንግግር አንድ ባንድ ለመተንተን

በክፍል 2 ይቀጥላል።……….

 አመሰግናለሁ

ጌታቸው ረዳ

መልኽቲ ብፁእ ወቅዱስ ኣቡነ ማትያስ ኣብ ስርዓት ቐብሪ ብፁእ ኣቡነ ዮሐንስ ዳግማዊ ተረኺቦም ዘሕለፍዎ መልእኽቲ / ካብ መቐለ

https://youtu.be/Bf-s1JnS77c