Friday, December 31, 2021

የአማራ ሰቆቃና የአማራ ምሁራን ቸልተኛነት ጌታቸው ረዳ ETHIO SEMAY 12/31/2021

 

የአማራ ሰቆቃና የአማራ ምሁራን ቸልተኛነት

ጌታቸው ረዳ

ETHIO SEMAY 12/31/2021

መጀመሪያ ይህንን ካርቱን ላዘጋጀው ሰው አመሰግአለሁ።

ዶ/ር ሲሳይ መንግሥቴ የተባሉ የአማራ ተወላጅ ስለ ወያኔ የሚያቀርቡት ሙግታቸው ሁሉ የረቀቀ የበሰለ ነው። ይመቹኝ ነበር። ሆኖም ምሁር ዋለልኝ መኮንን ፍልስፍና “ዛሬም” በማመጎሳቸው አጭር የፎቶ ተቃውሞ የለጠፈ አንድ ፌስቡክ ስመለከት፤ የአማራ ሰቆቃ ጉልህ ሆኖ ዓይናቸው ላይ ተገትሮ እያዩት ባሉበት ወቅትም “ብዙዎቹ የአማራ ምሁራን” ለምን እንዲገባቸው እንዳልቻለ እንቆቅልሽ ነው።ዋለልኝ መኮንን “በንጉሡ ዘመን ስራ ፈላጊ ሕዝብ የአማራ ስም ካልያዘ ሥራ አንደማይሰጠው” ዋሽቷል።

ነፍጠኛ እያለ የሚጠራው አማራን  “በምግብ፤ በሻማ አስለባሽነት፤ አማርኛ ሙዚቃ አስፋፊነት”  እያለ አማራን በማይገባ ወንጀሏል። ሌላም ሌላም።

ያ ጦስ ያቀጣጠለው እስካሁን ድረስ አማራው “ተጠቂ” ሆኗል። የ27 አመት ጥቃት በዝምታ አልፈውት ስንጮህባቸው ዛሬ ይነሱ ይሆን ብለን ስንመለከት፤ ይባስ ብሎ ጸረ አማራ የሆነውን “አብይ አሕመድን” መሪየ እየሉ አንዳንዶቹ በአማካሪነት አንዳንዶቹ በጀሌነት ሲያሞግሱት እያየሁ ለመገረሜ ገለጻ ቃላት አጥሮኛል።

ካሁን በፊት አማራዎች በጉምዝ ሰዎች ተገድለው ሥጋቸው ተቀቅሎ እየተበላ ነው ብለን ዜናውን ስናስተጋባ “አማራ” ነን የሚሉ አንዳንድ የኢሕአፓ አባላት “እኔን እና አቶ ተክሌ የሻውን” የጉምዝ ሕዝባችን እና ኢትዮጵያ እንዲም የአፍሪካ ሕዝብ ስም በፈረንጅ እና በዓለም ፊት ስማችንን ለማጥፋት ያደረጋችሁት ሴራ ነው፤ በማለት ቃላት እስኪያጡ ድረስ የራቸው ስደብ ሳይቀረ ሙልጭ አድርገውናል።

ታስታወሱ እንደሆነ “የአመቱ ባለጌ ሰው” በሚል የተቸሁት አለምነው መኮንን የተባለ

አማራው ተጠቃ ስንል “አማራ ተናጋሪ” እንጂ ኣማራ የሚባልየብእዴኑ ምክትል ሓላፊ የነበረ ባሕርዳር ከተማ ውስጥ አማራውን “አማራ በባዶ እግሩ እየሄደ በስንፋጭ ትምክሕት የታጀለ መርዝ ንግግሩን እስካሁን ድረስ ማቆም ያልቻለ፤ትምክህት እየተመገበ ያደገ፤……” እያለ አማረውን መሳደፉ ታስታውሳላችሁ።

ሌላም ላስታውሳችሁ “አማራ የሚባል ማሕበረሰብ የለም” የሚሉ እራሳቸው “አማራ” የሆኑት ፐሮፌሰር መስፍን ወልደማርያምም “አማራ የሚባል የለም” እያሉ ሲከራከሩን ያንን ሳያምኑበት ከዚህ ዓለም ተለይተዋል። በትንተና አንጻር ስንመለከት እውነታ ሊኖራቸው ይችል ይሆናል። ማለትም ኢትዮጵያዊያን በደም የመሰበጣጠራችን ውሁድነት አንጻር ማለቴ ነው።  አሁን እየታየ ባለበት አማራዎች ተለይተው በሚጠቁበት ወቅት ግን ክርክራቸው መሰረተ ቢስ ነበር።

ከላይ የጠቀስኳቸው ዶ/ር ሲሳይ መንግሥቴ የተባሉት ምን  ዋለልኝ እያሞገሱ ስለ አማራ ምን እንዳሉ በዝርዝር ባላገኝም ይህ  “አማራ የለም የሚለው ያላስተዋለ ክርክር እና ግራ ዘመም ፖለቲከኞ ዋለልኝ የአማራ እና ኢትዬጵያዊ ቤዛ ነው” የሚል ችግር ያለበት ፖለቲካዊ ክርክር፤ ያውም አክራሪ ነገዶች የሚጠቀሙበት ችግር ላንዴና ለመጨረሻ መቆም እንዳለበት ይታየኛል።

አማራ ምሁራን ዛሬም ከዚያ እንዝህላልነት ያልወጡ ስላሉ ዛሬም ጉዳዩ ማንሳት ያስፈልጋል።

የካሁን በፊት አማራ ምሁራን ችግር አንዱ እንደምሳሌ የፐሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ታሪክ ላስታውሳችሁና  ሎቻችሁ አማራ ምሁራን ከዚህ እንድትማሩ ስንከራከርበት የነበረው የፕሮፌሰሩ አቋም መማርያ እንዲሆን እነሆ፤

 ፕሮፌሰር መሥፍን ወልደማርያም፦

«ሥልጣን፣ ባህልና አገዛዝ፤ ፖለቲካዊ ምርጫ» በሚል ርዕስ 2003 ባሳተሙት መጽሐፈዎ ገጽ 120 ላይ እንዲህ ብለዋል። 

ኅዳር 1951 ዓም ከአጼ ኃይለሥላሴ ጀምሮ እስከ ታላላቆቹ ባለሥልጣኖች ባሰራጨሁት የጥናት ጽሑፍ ስለኦጋዴን የሚከተለውን ብየ ነበር። «በጠቅላላው የአማሮቹና የሱማሌዎቹ ግንኙነት ላስተዋለው፣ አማራዎቹ የሚያሳዩት የበላይነት መንፈስና በሱማሌዎቹ ላይ ያላቸው ንቀት፤ ሱማሌዎቹ በበኩላቸው ያላቸው ኩራት በአማራዎቹ ንቀት እየተነካባቸው የሚሰማቸው ስሜት በአንዴ ይታወቃል። ``ቆሻሻ ሱማሌ``በያለበት የሚሰማ ነው። በዕድሜም ሆነ በክብር ከፍ ያሉትን ሱማሌዎች እርሰዎ እያለ የሚያነጋግራቸው በቁጥር ነው።---እንደዚህ ዓይነቱ የሌለውንየአማራ የበላይነትና የሱማሌ የበታችነት በግልጽም በድብቅም የሚያሳይ መንፈስ የሱማሌዎቹን ልብ በጣም እንደሚያሞክረው የሚያጠራጥር አይደለም። ሱማሌዎቹ ልክ እንደአማራዎቹ መሆናቸውን ሁሉ የተገነዘቡት አይመስሉም፤ ሱማሌዎቹም ሁሉ የሚውቁት አይደለም።……”

( መስፍን /ማርያም «ሥልጣን፣ ባህልና አገዛዝ፤ ፖለቲካዊ ምርጫ» በሚል ርዕስ 2003 ባሳተሙት መጽሐፈዎ ገጽ 120)

መጽሐፉ ካላችሁ ማንበብ ትችላላችሁ።

በወቅቱ እኔም ሆንኩኝ “የምጽአተ ዐማራ መጽሐፍ ደራሲ ክቡር አቶ ተክሌ የሻው” በወቅቱ ይህንን ተቃውመን ለየግላችን ፕሮፌሰሩን ተችተናቸዋል። በወቅቱ እኔ ያልኩት

“ እንግዲህ ክቡር ፕሮፌሰር መስፍን ይህ ግፍ ሲፈጸም በመጽሐፍዎ የዘገቡት በመረጃ ያልተረጋገጠ አማራውን የመወንጀል ዘመቻዎ በአገራችን የነበረው የተለመደ ዕርስ በርስ የመሰዳደብ ልምድ አማራውን ብቻ እንደሚናገረውና እንደሚሳድበብ አአድርገው  ነጥለው “ለአማራ መስጠትዎ” ያሳዩን/ ወይንም እርስዎ ያደረጉት የተደገፈ ጥናት የለም። ባልሰሩት ጥናት በዘፈቀደ ተነስተው አማራው በሶማሊ ተወላጆች ላይ ዘለፋ ያደርግ ነበር ማለትዎ ካንድ ምሁር የሚጠበቅ ጽሑፍ አልነበረም።

ያስ እንደ እምነትዎ እንቀበለው፡ ሆኖም በ1951 ዓ.ም አማራ የሚባል ማሕበረሰብ እንደነበር ለመጥፎ ነገር ሲጠቀሙበት በቅርቡ ግን “አማራ የሚባል ማሕበረሰብ” የለም ሲሉ “ነበር” ያሉት አማራ ፡ዛሬ ወይም ከ1951 ዓ.ም በላ ወዴት ተሰወረ? ምን በላው?

ይህንን ተንተርሰው ሰበቡ የአካባቢው የአካባቢው አክራሪ እስላሞች በአማራው ሕብረተሰብ ላይ ያነጣጠረ የተቀነባባረ ጥቃት ልክ አንደ እነ “የወያኔው ም/ጠ/ሚኒስትር “ታምራት ላይኔ” ንግግር ለዛሬው ግፍ የእርስዎ ምስክርነት ተጨማሪ ብትር አላቀበልኩም ሊሉ ይችላሉ?” ብየ ጽፌ ነበር። 

የሆነውንም ለማሳየት አንድ ምሳሌ አቅርቤ ነበር። በሕይወት የሌለው ዋለልኝ ስለ አማራው እንዲህ አጣምሞ ተማሪውን ሲቀሰቅስ፤ በሕይወት የሚገኙት ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ሶማሌ “ክልል” ውስጥ አማራዎች እንጂ ትግሬዎች ጠላታችን አይደሉም እያሉ የክልሉ አስተዳዳሪዎች በግልጽ ለመናገር የበቁት ፕሮፌሰሩ አስተዋጽኦ የለበትም ማለት ይቻላል?  ብየ ነበር።

በዚህ የተነሳ፡ይህንን አንብቡ

በአገራችን  አቆጣጠርበ2006 (በፈረንጅ 2014) በጅግጅጋ (ጅጅጋ) የሚኖሩ አማራዎች ወደ ኢሳት ቲ/ቪ እና ራዲዮ ጣቢያ የተላከው ደብዳቤ እና የስልክ ጥሪ መልዕክት ላስታውሳችሁ፡ እንዲህ ይላል፤

 “ ቤታችን እየተነጠቅን ለጎዳና ተዳዳሪነት ተጋልጠናል። እስካሁን ድረስ በከተማዋ ውስጥ የነበሩት የአማራዎች ዋና ዋና የንግድ ተቋማትን እየተነጠቁ ለሶማሌ ተወላጆች እያስረከቡ ስለተደረገ አብዛኛዎቻችን ከተማውን እየለቀቅን ወደ መሃል አገር ሄደናል። ተወልደን ያደግንበትን አገራችን አንለቅም ያሉትንም ፌደራላዊ ጫናዎች እየተደረጉ ከተማዋን ለቅቀው እንዲወጡ በደብዳቤና በቃል ትዕዛዝ ተነግሯቸዋል።

የአንድ ቤሔር የበላይነት በሰፈነበት መልኩ “አማራ ወይንም ሐበሻ” የሚል መጠሪያ ተደርጎልን፤ እነሆ ከህጻናት እስከ ትልቅ በመንገድ በቢሮም እየተሰደብን መኖራችነን ሳያንስ፤ አሁን ደግሞ ያለምንም ልዋጭ ቤቶቻችን ተቀምተን ሜዳ ላይ ተጥለን እንገኛለን። የኛ ልጆች አንደልብ መንገድ ላይ መሄድ አይችሉም፤ ሱሩ የለበሰች ሴት ‘አማራ ነች’ እየተባለ በፖሊስ በዱላ ትደበደባለች። ማንፖሊስ ማን ሃላፊ እንደሆነ በማናውቀው ሁኔታ የ “ሸሪዓ ፍርድ ቤት” ተቋቁሞ ቤቶቻችን እንድንለቅ እየተደረገ ነው። ተወልድን ባደግንበት አገር አንደ ሁለተኛ ዜጋ እንደ ቆሻሻ እየታየን ነው” ብለዋል።

አንድ ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ የከተማዋ ኗሪ በከተማዋ የመኖር ስሜታቸው እየተሟጠጠ መሄዱ ደግሞ በስልክ እንዲህ ሲሉ ተናግረዋል።

“በዚህ አካባቢ የመኖር ስሜታችን ተሟጥዋል። ያፈራነውን ያለንን ነገር ለቀቅቀን ለመውጣት እየተዘጋጀን ነው። ሰላሳ እና አርባ አመት እና ከዚያም አመታት በላይ የኖርክብትን ቦታ ለቅቀህ ስትሄድ ዝም ብለህ ወፍ አይደለህ፤ በርረህ አትሄድም። አንዳንድ ያፈራሃቸው

ነገሮች ሊኖሩ ይችላሉ፤ ልጆች ይኖራሉ..አንዳንድ ንብረቶች ይኖሩሃል… እነሱን ጥለህ አትሄድም፤ አጋጣሚና ዕድል ይገኝ እንደሆነ ብለን፤ አንዳንዶቻችን ያንን እንደምንም ብለን እያስተካከልን ብለን ነው እስካሁን እየተንገዳገድን ያለነው። የወደፊት በዚህ ከታማ የመኖሩ ተስፋ እንኳን እንጃ!..እንጃ!” 

ሲሉ አማራዎች እንደ ሶማሌ እስላም “ሸሪዓ ፍርድ ቤት” ቀርበው ንብረታቸው እያስረከቡ ወደ አገራችሁ ሂዱ እየተባሉ እንዲባረሩ ሲወሰንባቸው; ልጃገረዶች ልጆቻቸውም “ሱሪ” ታጥቃ ስትሄድ

አንደ ሳውዲ አረቢያ “ሰፋጢን” ተብለው በሚጠሩ የሃይማኖት ፖሊሶች “አማራ/ሐበሻ” እየተባሉ በዱላ ይደበደቡ እንደነበር አማራዎች በጅጅጋ የደረሰባቸውን ግፍ አስረድተዋል።

እንግዲህ ይህ ሁሉ ሰቆቃ ሲፈጸም ዛሬም ብዙዎቹ አማራ ምሁራን እና “የኪነት/አክቲቪስት/” የሆኑ አማራዎች ከዚያ ጥቃት ሳይማሩ ዛሬም ያንን ጥቃት በሰፊው እየተካሄደ ባለበት ወቅት “ ይህንን ጥቃት ማቆም ያልፈለገው “በአብይ አሕመድ የሚመራው የኦሮሙማ መንግሥት” ደጋፊዎች ሆነው ማየት እጅግ ፤ እጅግ ከፍተኛ በሽታ ነው።

በዚህ አጋጣሚ በርትተው አልበገርም ብለው ለሕዝባቸው የቆሙ “አማራ” ምሁራን ምስጋና ይገባቸዋል። እንደዚህ ስል ግን ቅጥ ባራ ስሜት ገንፍለው ፋሺሰትንት ለመከተል ያማራቸው ዘፋኞች፤ገጣሚዎች  እና ‘የፌስ ቡክ አርበኞች’ ወደ አክራሪ አማራነት እየተበራከቱ ስለመጡ አማራን ልክ እንደ ትግሬ ማሕበረሰብ ከማድረጋቸው በፊት ትኩረት ይደረግ እላለሁ።

እኔ ያለኝን ኢትዮጵያዊ ድርሻየ አድርጌአለሁ፤ ጽሑፉን ማሰራጨት ግን የናንተ ተራ ነው።

ጌታቸው ረዳ

ETHIO SEMAY

እስኪ በዩ ቱብ ስዕለ ድምፁን በዓይናችሁ እና በጆሮአችሁ እነሆ

አድምጡ።

TPLF puppet Somali president secret video exposed TPLFs hate against Amhara May 8 2013

https://youtu.be/Kj2sNJ5B2j0

 

Tuesday, December 28, 2021

“ትዕዛዝ አልደረሰንም” - አማራን ማስጨፍጨፊያ ኦነግ/ኦህዲዳዊ ሥልት ዳግማዊ ጉዱ ካሣ 12/28/2021

 

“ትዕዛዝ አልደረሰንም” - አማራን ማስጨፍጨፊያ ኦነግ/ኦህዲዳዊ ሥልት

ዳግማዊ ጉዱ ካሣ

 (ma74085@gmail.com)

12/28/2021


አማራን ከምድረ ገጽ ለማጥፋት አማራን ራሱን ሳይቀር ከሥሩ አሰልፎ የመጨረሻውን ዘመቻ ለመጀመር ፊሽካውን በመጠባበቅ ላይ የሚገኘው የአራት ኪሎው ዘንዶ ልክ እንደጥንቱ ደራጎን የኢትዮጵያውያንን ሥጋና ደም የዕለት ከዕለት ግብር አድርጎ አለልክ እየተቀለበ በከፍተኛ ደስታ ተውጦ ጮቤ እየረገጠ ይታያል - በአጨብጫቢዎች ብዛትም ሰክሮ የሚሆነውን አጥቷል፡፡ ይህ የሰው ደምና ሥጋ ጠጥቶና በልቶ የማይረካና የማይጠግብ ደራጎን አማራን በአክራሪ ኦሮሞና በወያኔ ትግሬ ሁለት ነበልባላዊ እሳቶች መሀል ጥዶ በነዚህ ነዲዶች እየተቃጠለ መፈጠሩን ከሚራገመው ንጹሕ አማራ በሚወጣ የሲቃ ድምጽ መዝናናቱን ቀጥሏል፡፡ በሰው ስቃይ የመደሰቱን ገሃነማዊ ተፈጥሮውን ደግሞ በአስመሳይ የፌዝኝነትና የሸንጋይነት ተፈጥሮው በመሸፈን በርካታ አማሮችን እያነሆለለ አሽቃባጮቹ አድርጎ አማራውን በአማራ ላይ ማዝመት ችሏል፡፡ ይህ እውነት ቢወዱትም ቢጠሉትም ያለና በገሃድ የሚታይ አሳዛኝ እውነት ነው፡፡

አንድ ጤናማ ኢትዮጵያዊ አሁን በሀገራችን ውስጥ እየሆነ ያለውን አስቀያሚ ታሪካዊ ክስተት ሁሉ እየተመለከተ የዘንዶው ደጋፊና ተባባሪ ሆኖ የሚሊዮኖችን ዕልቂትና የንብረት ውድመት እንዲሁም ከገዛ ቀዬ መፈናቀል “የኢትዮጵያ ትንሣኤ ምልክት ነው” ሊል አይችልም፡፡ እንደዚያ የሚል ቢኖር ከለየለት ዕብድ ወይም በድግምት ከታሰረና ጠበል ከሚያሻው ምስኪን ሰው ተለይቶ ሊታይ አይገባውም፡፡ አማራውና ትግሬው በኦሮሙማ የፖለቲካ ሤራ ሲጨራረሱ እያዬ፣ በወለጋና በሌሎች ኦሮምኛ በሚነገርባቸው አካባቢዎች የሚኖረው አማራ በኦነግ ሸኔ በየቀኑ አንገቱ ሲቀላና ንብረቱ ሲወድም ሲዘረፍ እያዬ፣ በፌዴሬል ተብዬው የሥልጣን ቦታዎች የሚሾመው ሁሉ በአብዛኛው አክራሪፕሮቴስታንት ኦሮሞ መሆኑን እየታዘበ፣ ማንን እያለገለ እንዳለ የማያውቅ የኦሮሙማ ፓስተር ስብከቱና “የትንቢቱ ቃል” ሁሉ ለዘንዶውና ለነገዱ አጋድሎ በግልጽ ሴተኒዝምን እያስፋፋ እያዬ፣ አዲስ አበባ ቀስ በቀስ በኦሮምያ ክልል እየተጠቀለለች መምጣቷን እያዬ፣ የጥቂት መቶ ብሮች ጉቦ ሽቅብ ተወንጭፎ ለትንሽ ጉዳይ ሳይቀር በመቶ ሽዎችና በሚሊዮኖች መሆኑን እያዬ፣ ብአዴን ተብዬው አጎዛ ድርጅት ለኦህዲድ/ኦነግ ሰግዶ የኦሮሙማ ምንጣፍ ጎታች መሆኑን እያዬ … ኢትዮጵያዊ ነኝ የሚል አንድ ዜጋ በዘንዶው አምልኮት ታውሮ “ከእገሌ አመራር ጋር ፉልዱረት(ወደፊት)!” ብሎ ክችች ካለምንም በማያጠራጥር ሁኔታ ጤንነቱ የተቃወሰ ነው፤ ከዚህ አንጻር “My Dragon…” ማለቴ … “My PM is on duty!” ለሚሉ ልበ ሥውራን ምሁር ተብዬዎች ማዘን ተገቢ ነው፡፡ ስም መጥራት ሳያስፈልግ ከኢዜማ እስከ አብን፣ ከግንቦት ሰባት እስፈ የካቲት 11፣ ከአርቲስት እስከ አክቲቪስት፣ ከዲፕሎማ እስከ ፕሮፌሰርነት …. ከሞላ ጎደል በሚዲያ እየወጣ ለዘንዶው የሚያሽቃብጠው ሁሉ በነገይቷ ኢትዮጵያ እንዲኖር ከፈለገና ጠባቧን ድልድይ ተሻግሮ ከተራፊዎች ጋር የሚመደብ ከሆነ አስቀድሞ የአእምሮ ቀዶ ህክምና ያስፈልገዋል፡፡

 አፎምያን ከደራጎን ላንቃ ያወጣት ቅዱስ ጊዮርጊስ መሆኑን ኦርቶዶክሳውያን አባቶች ይናገራሉ፡፡ ኢትዮጵያን ደግሞ አማራ የተባለ የዘመናት የበቀልና የጥላቻ ውጤት ገፈት ቀማሽ ነገድ ከዚህ ዘንዶ ጉሮሮ አውጥቶ ለትንሣዔዋ ያበቃታል፡፡ ይህም ቀን በብርሃን ፍጥነት እየመጣ ነው፡፡ ይህ ከራሱ ጀምሮ ተቆጥሮ የማይዘለቅ ጠላት ያለው ሕዝብ ዕድሜ ለጠላቶቹ አሁን ወደአንድነት እየመጣ ነው፡፡ ትንቢት ይዘገያል እንጂ እንዲቀር የሚያደርገው አንድም ምድራዊ ኃይል እንደሌለ ማመን ደግሞ ከአላስፈላጊ ጀብደኝነትና የጥፋት መንገድ ይታደጋልና ጥሩ ነው፡፡እውነቱ ይህ ከሆነ ዘንዳ አማራን እንደግፈው፡፡

“ትዕዛዝ አልወረደልንም” የሚባል የመከላከያ ነጠላ ዜማ መስማት ከጀመርን ስድስት ወር ገደማ ሆነን፡፡ ወያኔን በቀደመው የትግራይና ወሎ-ጎንደር ክፍለ ሀገራት ወሰን ማስቆም እየተቻለ በዚህ ትዕዛዝ መሠረት መከላከያው ብቻ ሣይሆን የአማራም ጦር እንዳይዋጋ ሽባ እየተደረገ በማይታመን መብረቃዊ ፍጥነት ወያኔ አዲስ አበባን እንድትጠጋ ተደረገ፡፡ ይህም ብቻ አይደለም፡፡ በ17 ቀናት ጦርነት ባዶ እጇን ቀርታ የነበረችው ወያኔ ዘንዶውና ሼሪኮቹ በውስጥ መስመር ባደረጉት በዓላማ ትስስር ላይ በተመሠረተ (more of telepathic) ስምምነት ቁጥር ሥፍር ከሌለው አበረታች ንጥረ ነገር (ሀሽሽ) ጀምሮ እስከ ከባድ መሣሪያና ስንቅ እንዲሁም የሳተላይት ምስል መረጃ ድረስ በገፍ እንዲደርሳት ተደርጎ ይቺው ጉደኛ አማራና አፋር ላይ ዘምታ ያደረገችውን አደረገች፡፡ ያኔ በአማራው “ፈሪነት” ኦሮሙማዎች ሣቁ፡፡ ያኔ በአማራ ውድመት ምዕራቡም አውሮፓም ጥርሱን ተነቅሶ ሣቀ፡፡ ያኔ በኦርቶዶክስና በአማራ መቀመቅ መውረድ አሜሪካ ከት ብላ ሣቀች፡፡ ያኔ ግብጽ፣ ሱዳንና ዐረቦችም ጥርሳቸውን ጉራማይሌ ተወቅረው ሣቁ፡፡ ሁሉም የአማራና የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ጠላት በዕቅዳቸው ስኬት አንዱ ከሌላው እየተያዬ ተሣሣቀ፤ ተሣለቀ፡፡ ከአድማስ ወዲያ ማዶ ሀገር ያለ የማይመስለው ንጹሕ የአማራ ገበሬም የቁም ስቅሉን አዬ፡፡ ዓለም ውስጥ ታይቶና ተሰምቶ የማያውቅ በደልና ስቃይ በወያኔና ተባባሪዎቿ አማካይነት ደረሰበት፡፡ ያን ሁሉ ግፍና በደልም ፈጣሪ መዝግቦ ያዘው፡፡ ብድራቱን ለመክፈልም ቀጠሮ ያዘላቸው፡፡ ቀጠሮውም እየደረሰ ነው፡፡ አንቸኩላ!! እኔ አልቸኩልም፡፡ ….

ወያኔ አሁን አይቀጡ ቅጣት ተቀጥታ ወደኋላዋ አፈግፍጋለች - ራሷ እንደምትለው ለሥልትም ይሁን እርሷና ዘንዶው ለሚያውቁት ሌላ ጉዳይ - ግዴለም - ብቻ አፈግፍጋለች፡፡ ዘንዶው ግን ወያኔ ወሎንና ጎንደርን ጨርሳ ሳትለቅ ጦርነቱን አቁሙ ብሎ አዘዘ፡፡ ወልቃይትና አላማጣ-ኮረም እስከአሸንጌ ሐይቅ በተጋሩ ምስክርነት ራሱ የትግሬ አካል ሆነው እንደማያውቁ የተመሰከረለት ሃቅ ነው - መለስ የወሰደውን መሬት ልጁ ዘንዶው ለትግራይ ሊያጸድቅ በከንቱ መፍጨርጨሩ ነው አሁን፡፡ ነባሩን ታሪካዊ እውነት ትግሬዎችም የሚያውቁት መሆኑ እንዳለ ሆኖ ወያኔ አንዳችም ምድራዊና ክልላዊ ህግ ሳይገዛት እስከደብረ ብርሃን የሚገኝን ሕዝብ አራቁታና ንብረት ዘርፋ ወይ አውድማ ከተባረረች በኋላ እገባችበት ገብቶ ወንጀለኛን መያዝና ለፍርድ ማቅረብ፣ የተዘረፈ ንብረትንም መመለስ ሲገባ የተሟሟቀን ጦር እዚያ ማስቆም በየትኛውም መለኪያ ፍች-አልባ ነበር ወይንም ነው - ያ ዓይነቱ ትዕዛዝ ለወያኔ ለራሷ ዕንቆቅልሽ ሳይሆን አይቀርም፡፡ የቃቃ ጨዋታ ነው እሚመስለው ያን መሰሉ ወታደራዊ አመራር፡፡ይህ የዘንዶው ትዕዛዝ ታዲያ ደባ መሆኑን እንኳንስ አማራው ጀምጀሙና ሙርሲው ያውቁታል፡፡ ዘንዶው በርሱ ቤት ሤራውን ማንም የማይደርስበት ልዩ ዐዋቂ ነው፤ ተንኮሉ የማይታወቅበት ብልጥ ነው፤ ለአማራ የሚዘረጋው ወጥመድ ሁሉ የማይነቃበት እጅግ “ጥበበኛ” እንደባብ ተስለክላኪ ፍጡር ነው፡፡ የሚገርም ተፈጥሮ ያለው ታዳጊ ዘንዶ ስለመሆኑ በበኩሌ መመስከር እችላለሁ፡፡ ወያኔ ቤት ማደግ ወያኔን የሚያስንቅ እስከዚህን ብልጣብልጥ እንደሚያደርግ አላውቅም ነበር፡፡

ያቺ ወያኔን ያለ ብዙ ጦርነትአዲስ አበባ ጥግ እንድትደርስ ያደረገችው ትዕዛዝ ሰሞኑን በወልቃይት በኩል ልትደገም እንደሆነ እየሰማን ነው፡፡ የአብንን ሰዎችና የግንቦት ሰባትን መሠሪ የአማራ ጠላቶች በዙሪያው የኮለኮለው የአማራን ደም ጠጥቶ የማይጠግበው ዘንዶ አማራን በወልቃይት በኩል በሚተም የወያኔ ጀሌ ጎንደርንና ባህር ዳርን አልፎ ደብረ ማርቆስን ረጋግጦ ጎሃ ጽዮን ድረስ ልክ እንደወሎውና እንደሰሜን ሸዋው የቀረችዋን የአማራ ጥሪት ሊያወድም ሕዝቡንም ሊጨፈጭፍና ሊያዋርድ ተዘጋጅቷል፡፡ ይህን የሚያደርገውም የአማራን ጦር እንደለመደው ከአካባቢው በማስወጣትና ቅን ታዛዡን መከላከያን በመተካት በዚያች በተለመደች “ትዕዛዝ አልደረሰንም” የተበላ ዕቁብ ዓይነት ማጨናበሪያው አማራን የዶጋ ዐመድ ለማድረግ በማቀድ ነው፡፡ ይህን መሰል ቁጭ በሉ ከሞት የተረፈው አማራ ይቀበለዋል ወይንስ አይቀበለውም የሚለውን ቆይተን የምናየው ነው፡፡

የዘንዶው ዕቅድ ግን ይሄው ነው፡፡ዕቅዱ ግቡን እንደሚመታለትምበጣም እርግጠኛ ነው፤ ምክንያቱም “ሲጠሯቸው አቤት፤ ሲልኳቸው ወዴት” የሚሉ ቅን የብአዴን አጋሰሶች አሉት፡፡  እነዚህ ብአዴናውያን የሚባሉ የሰው ግማሾች አማራን እንዳዋረዱት ማንም አላዋረደውም፡፡ ለአማራ ተቆርቋሪ ናቸው የሚባሉትን ደግሞ ዘንዶው ለዓላማው ስኬት ሲል አስቀድሞ ውጧቸዋል፡፡ አማራ አሁን ባዶውን ነው ፤ ባዶ እንደሆነ ግን አይቀርም፡፡ ዘንዶውን የሚሰለቅጥ መብረቅ ከላይ ወርዷል፡፡

ወደዝምዝማቱ እየመጣሁ ነው ትንሽ ታገሱኝ፡፡ አማራን ለማጥፋት ከአማራ ጠላት ጋር የተሰለፋችሁ ሁሉ ወደኅሊናችሁ ተመለሱ፡፡ ስማችሁን መጥራት አልፈልግም - ጠርቻችሁም አልዘልቀውም፡፡ ግን ግን ስማችሁን ቄስ ከመጥራቱ በፊት ለዚህ ሞልቶ ለማይሞላ ከርሳችሁ ስትሉ፣ ረክቶ ለማይረካ የሀብትና የሥልጣን ፍቅር ስትሉ ከገባችሁበት አዘቅት በቶሎ ውጡ፡፡ የነገድ ተዋፅኦዋችሁ ምንም ይሁን ምን - ሲፈልግ አማራነታችሁ 10 በመቶም ይሁን 86 በመቶ - አማራነት ይበልጡን በአስተሳሰብና በአመለካከት ላይ የተመሠረተ እንጂ እንደውሻ ደምና አጥንትን በማነፍነፍ ላይ የተመረኮዘ አይደለምና እየሸጣችሁት ወደምትገኙት ኢትዮጵያዊነት ፈጥናችሁ ተመለሱ፡፡ ይሉኝታና ሀፍረት አይያዛችሁ፡፡ አማራም ሆነ ኢትዮጵያ ይቅር ባይ ናቸውና ይቅርታን አታጡም፡፡ አንዳንዶቻችሁ ልጆች እንደመሆናችሁ ልጅነት ደግሞ ለዝናና ለሥልጣን ጉጉ ሊያደርግ ስለሚችል ስህተታችሁ ይገባናልና ወደጤናማው መንገድ ለመመለስ ጊዜ አትፍጁ፡፡ ከኢትዮጵያ ጠላት ጋር ተዋርዳችሁ የሞት ሞት ከምትሞቱ ከኢትዮጵያ እናታችሁ ጋር ሆናችሁ ለክብራችሁ ስለክብር ተዋድቃችሁ በክብር ሙቱ፡፡ ያኔ ዘላለማዊ የሀፍረት ማቅ ሳይሆን የምንጊዜም የክብር አክሊል ትቀዳጃላችሁ፡፡ ያኔ “እገሌ ባባቱ እንዲህ ያለ ዘር ነበር፤ እገሌ ደግሞ በአያቱ እንዲህ ያለ ነገድና ጎሣ ነበር” እያለ ምናልባትም እናንተ ባላሰባችሁት መንገድ ዘር ማንዘራችሁን እየጎተተ የሚዘባበትባችሁ አቃቂረኛ አይኖርም፡፡ እናታችሁን በቁራሽ እንጀራ አትለውጧት፤ እንደዔሣው አትሁኑ፡፡ የዓላማ ጽናታችሁን በፍርፋሪ ሥልጣን አትቀይሩት፡፡ ሁሉም ያልፋል - ሀብትና ሥልጣንም፡፡ ትናንትን አስታውሱ፤ ዛሬን ተመልከቱ፤ ስለነገም አስቡ፡፡ ሰው ሆኖ መገኘት ዕዳ ቢሆንም ሰው ለመሆን ሞክሩ፡፡ በሰው ቁስል ደግሞ እንጨት አትስደዱ፡፡ መስከረም አበራን እዩ፤ እስክንድር ነጋንም እዩ፡፡ በነሱ አትቀኑም?

እንግዲህ ኢትዮጵያ ልትነሣ፣ ጠላቶቿም አፈር ከድሜ ሊግጡ የቀረው ጊዜ በጣም - እጅግ በጣም አጭር መሆኑን ልናገርና በሚታየኝ ሁለንተናዊ እውነት ልሰናበት፡፡ ወያኔ ያለች የምትመስለው የውሸት ነው - አልሞት ባይ ተጋዳይ ከሆነች ጥቂት ቀናት ምናልባትም ሣምንታት አለፉ፡፡ እርሷን ጃዝ ብለው አማራን እያስጨረሱ የሚገኙ ወፍራም የሆኑ ያህል የሚሰማቸው ግን ከንፋስ የቀለሉ የአማራ ጠላቶችም ቀናቸውን የሚጠብቁና የትም የማይደርሱ ዳግማዊ ወያኔዎች ናቸው፡፡ የሚወጣና የማይወጣ እንጀራ ከምጣዱ ያስታውቃል፡፡ እነዚህን ከፈጠረቻቸው ከወያኔ ውድቀት እንኳን ቅንጣት መማር ያልቻሉ የታሪክ አተላዎችን ዳግማዊ ወያኔ ስል ከነሙሉ ወያኔያዊ ጥቅም፣ ክብርና ሞገሱ ጭምር ማለቴ ነው፡፡ ለአጭር ጊዜም ቢሆን ወያኔ ያየችውን ክብርና ሞገስ ከነሙሉ ግርማ ሞገሱና ጥቅሙ አይተዋል፡፡ አራት ዓመት መፈራትና አፄ በጉልበቱ ሆኖ መንገሥ ቀላል አይደለም፡፡ ይሁንና የነሱም መጨረሻ ከወያኔ ቢብስ እንጂ የሚሻል አይሆንም፡፡ ደስ የሚለውና ማንም በድርድር የማያስቀረው አንድ እውነት አለ፡፡ እሱም ሀገራችን ኢትዮጵያ ሁሉንም እንደሥራው የሚከፍልና ጊዜውን ጠብቆ በምሕረት እጆቹ የሚዳብሳት አምላክ ያላት መሆኑ ነው - ለዚህ እውነት ታሪክን አንብብ፤ ዐዋቂ ሰውም ጠይቅ፡፡“ከአያያዝ ይቀደዳል ከአነጋገር ይፈረዳል” ይባላልና ቀጣዩን መራር ሀገራዊ እውነት ተመልከቱልኝና የኢትዮጵያን ትንሣኤ መቃረብ ተረዱልኝ፡፡

ጴንጤ እየተመረጠ የሚሾምባት፣ ኦርቶዶክስ እየተመረጠ የሚታረድባት፣ ኦሮሞ እየተመረጠ የሚሾምባት፣ አማራ እየተመረጠ አንገቱ በሠይፍ የሚቀላባት፣ ወጣት ባለጊዜ እየተመረጠ የሚሾምባት፣ ያልተማረ ደነዝ እየተመረጠ ሥልጣን የሚይይዝባት፣ የሀብት ክፍፍሉን የቀን ጅቦች የሚያደላድሉባት፣ እውነተኛ ባንዲራ እየተቀማና እየተቃጠለ በቤተ ሙከራ ተሠርቶ እንደቡና ቁርስ በከዚህ መልስ የሚታደል መናኛ ጨርቅ የሚውለበለብባት፣ ሀገሩን ወዳድና ዐዋቂ ዜጋ እየተመረጠ የሚታሰርና የሚገደልባት፣ ሙሰኛ እየተመረጠ የሚሾምባት፣ ወጥቶ መግባት ብርቅ የሆነባት፣ ከዘንዶው ጋር ወልዶ አሳዳጊ ጌታን በካድሬነት ያገለገለ በኩራዝ እየተፈለገ የሚሾም የሚሸለምባት፣ ከተረኛው ነገድ ውጪ ሌላው ከሀብትም ከሥልጣንም የሚባረርባትና ከዚያም ባለፈ እንደሰው የማይቆጠርባት፣ በአንዲት መናገሻ ከተማ የሁለት መንግሥታት አዛዥነት የነገሠባት፣ ሥርዓት አልበኝነት የሰፈነባት፣ ጠያቂና ተጠያቂነት የጠፋባት፣ ርሀብና በሽታ የሚፏልሉባት፣ ድህነትና የኑሮ ውድነት አለቅጥ የሚዘባነኑባት፣ ሞት የረከሰባት፣ ሰው ሆኖ መፈጠር የሚያስረግምባት፣ የጦርነትና የዕልቂት ዐዋጅ የሚጎሰምባት፣ የውሸት ዲግሪና የፈጠራ ትርክት የሚናኝባት፣ በሀሰት ታሪክ በቆሙ ሀውልቶች ሕዝብ እንዲባላ የሚደረግባት፣ ዕውቀት ዕርሙ የሆኑ ማይምና ደመነፍሳዊ ወጣቶች በሕዝብ ደም የሚጨመላለቁባት፣አለቃና ምንዝር የተናናቁባት ….ሀገር እንዳለች አትቆጠርምና እውነተኛዋ ኢትዮጵያ ልትነሣ የግድና የጊዜ ጉዳይም ነው፡፡ እርግጥ ነው ከዚህ ሁሉ ሃቅ አኳያ ስንታዘብ ጨለማው ደንግዟል፡፡ የጨለማው መጠንከርም የንጋትን መቃረብ ይጠቁማል፡፡ እንግዲያውስ …. የቆመ የሚመስለው ይጠንቀቅ!! ከአስመሳዮችና ከእበላ ባይ ሆዳሞች ራሳችንን እንጠብቅ፡፡ ከይሁዳዎች ራቅ እንበል፡፡ ለወራት ዕድሜ ብለን የታሪክ ትዝብት ውስጥ አንግባ፡፡ የተሳሳቱ ወገኖቻችንን ፈለግ አንከተል፡፡ ብቻችንን የሆንን ቢመስለንም ወይም ብንሆንም እንኳን ከእውነቱ አናፈንግጥ፡፡ ዛሬ አያጥበርብረን፡፡ በሆድ ማሰብን እናቁም፡፡ በቃ፡፡

ዳግማዊ ጉዱ ካሣ

 (ma74085@gmail.com)

 

Saturday, December 25, 2021

ስር የሰደደ የበታችነት ስሜት የወለደው የትግሬ ፋሽስታዊ ልዕልና የቪዲዮ ማስረጃ ጌታቸው ረዳ ETHIO SEMAY 12/26/2021

                                     ስር የሰደደ የበታችነት ስሜት የወለደው

የትግሬ ፋሽስታዊ ልዕልና የቪዲዮ ማስረጃ

ጌታቸው ረዳ

ETHIO SEMAY

12/26/2021

ዛሬ በዚህ በለጠፍኩት በስዕለ ድምፁ የምታደምጡት የወያኔ ወረበላ “ታጣቂ” “በኢትዮጵያዊያን የጦር ሙርከኞች ሕሊና” ላይ የፈጸመው ነውረኛ ስነመግባር እንመለከታለን። ቪዲዮውን ስትመለከቱት ሙርከኞቹ ከውስጥ የተሰማቸው ቅሬታና ንዴት፤ መፈክሩን የማስተጋባቱን ውስጣዊ ልግመተኛነት ማየት ትችላለችሁ።

 ወያኔ ድሮም ሆነ በቅርቡ በወረራቸው የአማራ “ክልሎች” የተከተለው የፋሺሰቶች ፖለቲካ ደጋግሞ ያሳየን አስነዋሪነቱ በ ከዓለም አቀፍ ሕግ ውጭ በሆነ አያያዝ የሰው ልጆች ልዕልና እና ክብር በሚነካ የሙርከኞችን ሕሊና በሚጎዳ መልኩ “ጠመንጃ” ደግኖ በማስፈራራርት “የእራሳቸውን እና ወላጆቻቸውን” ሰብአዊ ክብር የሚነካ “መፈክር” እንዲያስተጋቡ ወረበላው የሚያስተጋባውን መፈክር ተገድደው እየደጋገሙ እንዲያስተጋቡ በኢትዮጵያዊያን ነውር የሚባለውን ነውር ለጀሮአችን የሚቀፍ እንግዳ ነገር አይተናል።

 ይህ ድርጊት በስነ ሕሊና ምሁራን ትርጉም አለው።ድርጊቱን ስትመለከቱት ወያኔ በሚገርም ባሕሪ የበታችነት ስለሚያጠቃው “የበታችነቱን ስሜት ለመደበቅ” ሲል “ልዕልናውን እንዲአስተጋቡለት” ሙርከኞቹን እንዲጨነቁ አድርጓል።

እኔ እንደገባኝ በትምክሕት የተወጠረው የበላይነት እና የበታችነት ስሜት ሁለቱ በውስብስብነት ተጋምደው አንዱ አንዱን ለመሸፈን የሚደረገው የሕሊና አለመረጋጋት የሚታዩ የስነልቦና ክስተት ነው። ሁለቱም እርስ በርሳቸው ተመሳሳይ ናቸው። በዚህ ሙያ የሚያስተምሩ ሊቃውንት እንደሚሉት “ልዕልናን ለማሳየት መሞከር የበታችነትን ስሜት ለማካካስ የሚያገለግል “የመከላከያ ዘዴ” ነው ይላሉ።

 

የበላይነትን ለማጎናጸፍ የሚዞሩ የወያኔ የበታች ስሜት “በሽተኞች” እራሳቸው በአሸናፊነት ረድፍ በማስቀመጥ የበታችነት ስሜታቸው እየተባባሰ በሄደ ቁጥር ለበታችነታቸው ስሜት “ምክንያታችን” ነው ብለው ለሚወነጅሉት ማሕበረሰብ አጋጣሚውን አግኝተው “በቁጥጥራቸው ሥር ሲገባ” ከዛው ማሕበረሰብ በመጣ “ሙርከኛ” ላይ እራሳቸው የሚሰቃዩበትን “የበታችነታቸውን ስሜት” ይጭኑበታል። ይህንን ሲያደርጉ በበታችነት የሚሰቃዩበት የሕሊና ጭንቀታቸው እንደ መውጫ መስኮት ይጠቀሙበታልታል። በዚህ ቪዲዮ ላይ ወያኔዎች በማረኩዋቸው ወታደሮች ላይ የፈጸሙት አስነዋሪ ስነምግባር እያየነው ያለው ዓይነተኛው መነሻ ከላይ ከጠቀስኩት እውነታነት የተነሳ ነው።

ድርጊቱ እጅግ መረን የለቀቀ ነው። “እራሳቸውንና በጦርነቱ ውስጥ የሌሉትን የሙርከኞቹ ወላጆች” በዓለም አቀፍም ሆነ ሃይማኖታዊ ሕግ “injurious to dignity” የሚባለው “ክብረ ነክ” የሆነ የትግሬዎች ፋሺሰታዊ የስነ ልቦና ሲመረመር “የሞራል መበስበስ” ብቻ ሳይሆን ወንጀልም ነው። ኢትዮጵያዊያን ለታሪክ ማስረጃ ሊዘግቡት የሚገባ ቪዲዮ ነው።

ቪዲዮው ዛሬ አንድ ወዳጄ ልኮልኝ ነው ያየሁት። ቪድዮው በተመለከትኩበት ዓይን እራሴን መልሼ የምጠይቅበት አጋጣሚ ነበር። ወደ ሱዳን ስሄድ ከወያኔዎች በተለይ ከነ አባይ ጋር “ትግራይን ከጫፍ እስከ ጫፍ” እየተዘዋወርኩ ወደ 4 ወር ሰንብቼአለሁ። አያያዛቸው ከሌሎች ትግሬዎች እጅግ የሚገርም ወንድማዊ መስተናግዶና አያያዝ ነበር። ለደግነታቸው ከመሪዎቹ አብሮ አደግነት መስሎ ብገምተውም ‘እኔን ወደ ድርጅታቸው ላማስቀረት የጣሩበት ምክንያት’ ዋነኛው ነበር ብየ እገምታለሁ። ሆኖም አልተሳካላቸውም።

በወቅቱ ከላይ እስከታች ያሉትን መሪዎች የፖለቲካ ንትርክ ገጥሜ አብረውኝ የነበሩ ጓዶኞቼ “እባክህ እራስን አስገድለህ እኛንም እንዳታስረሽነን” ባታምንበትም የሚሉትን ፖለተካ እመንላቸው እስኪሉ ድረስ ስከራከራቸው ነበር።  አሁን አሁን እራሴን ስፈትሽ “እውነታዊ ተፈጥሮ” ወይንም “ጠበብ አልባ ግትረነት” ስለነበረኝ ይሆን እንዲያ ከነዚህ አረመኔዎች ጋር ፖለቲካው በግትርነት ሳልፈራቸው ስከራከራቸው የነበረው? ብየ አሁንም እራሴን እጠይቃለሁ።

ክርክራችን ከብሔር ፖለቲካ እስከ አማራና ትግሬ እስከ ምኒልክ እና ዮሐንስ እስከ የሌቦች ቅጣት ፤እስከ ዘርኣያዕቆብ ወዘተ…ወዘተ… ነበር።

 

አጋጣሚ ይህ ቪዲዮ ስመለከት በትንሽነቴ ወዳደግኩበት “ሰመማ” ወደ እሚባል ገጠር የሚወስድ “ማይ አድራሻ|” ከሚባል ሽሬ እንዳስላሴ እና ሰለኽለኻ መካክል አቋርጠን ከወያኔ ተጋዮች ጋር ስንጓዝ፤ “ስሙን የማላስታውሰው” ነገር ግን መልከመልካም እና ለግላጋ ረዢም የሆነ የታጋዮቹ ዋና መሪ ጋር እያወራን እንጓዝ ነበር። በእዛች ቦታ ስንደርስ የሆነ የራዲዮ መልእክት ጥሪ ደረሰውና መነጋገር ጀመረ። በንግግሩ ውስጥ ከዚህ ቪዲዮ ጋር ተመሳሳይ የሆነ ንግግር ከተጣራው የራዲዮ ሞገድ ላይ “ወላጆቻቸውን ማርከን ልጆቻቸውንም እየማረክን ነው!” …“ተቀበልከኝ” ለማለት ይመስለኛል የሆነ “ኮድ” ነገረው: እርሱም “አዎ! አዎ!” እንደማለት ይመስለኛል በፈገግታ እርሱም “በኮድ” መልስ ሰጠውና “ግንኙነቱን” በዛው ተቋጨ።

ስናወራው የነበረው ጥሞታል መሰለኝ ልጁ ወደ እኔ መለስ ብሎ “አካባቢያችን” ውግያ ነገር ስላለ ፤ ቃኚ እስኪያጣራልን ድረስ ትንሽ እዚህ እንቆያለን ብሎኝ ከኔ ራቅ ብሎ ሄዶ ጥቂት እንደቆየን “ጉዞአችን እንድንቀጥል ሆነ” ፤

ዛሬ ያየሁት ቪዲዮና ያደመጥኩት መፈክር ተመሳሳይነቱ ሳነጻጽረው ይህ የስነሉባና ትምክሕታዊ የበታችነት ስሜት ቀደም ብሎ በረሃ ላይ እያሉ የነበረ መሆኑን ራሴን የማስታውስበት አጋጣሚ ሆኖ ሳገኘው፤ እጅግ ገርሞኛል።

እናንተስ ምን ትላላችሁ? ተቀባበሉት “ሼር” አድርጉት፤ ሕዝቡ ይመስግበው።የስነሉባና ትምክሕታዊ የበታችነት ስሜት ቀደም ብሎ በረሃ ላይ እያሉ የነበረ መሆኑን ራሴን የማስታውስበት አጋጣሚ ሆኖ ሳገኘው፤ እጅግ ገርሞኛል።

እናንተስ ምን ትላላችሁ? ተቀባበሉትሼርአድርጉት፤ ሕዝቡ ይመስግበው።



  እናንተስ ምን ትላላችሁ? ተቀባበሉት “ሼር” አድርጉት፤ ሕዝቡ ይመስግበው።

Tigrean fascist magnanimity humiliating captives out of war rules

https://youtu.be/MeauhEGT_cs

 

ጌታቸው ረዳ

ETHIO SEMAY

Friday, December 24, 2021

ዋናው ጠላት ትግሬው እራሱ ወይስ አፈወርቅ ገብረ ኢየሱስ? ጌታቸው ረዳ POSTED AT ETHIO SEMAY 12/24/2021

 

 

ዋናው ጠላት ትግሬው እራሱ ወይስ አፈወርቅ ገብረ ኢየሱስ?

 

ጌታቸው ረዳ

POSTED AT ETHIO SEMAY

12/24/2021

 

የትግራይ ሰው የሆነው በሙያው “አርቺቴክተር” የሆነው ወጣት ኤርሚያስ አማረ በሚያዘጋጀው ፌስቡክ የትግራይ ሕዝብ “የወያኔ አስተዳደር” በቃኝ ማለት እንዳለበት\ በጻፈው ትችት ላይ “ኣፅብሃ ኣፅብሃ ሃጎስ”  የተባለ አንድ የወያኔ “ቆዛሚ” “የጥላቻ መመህር የነበረው ፋሺስቱ “መምህር ገብረኪዳን ደስታ” የጻፈውን መጽሐፍ በመጥቀስ አንዱን ኢትዮጵያዊ አያቶችህ እኛን ትግሬዎች ከማጥፋት አይቦዝኑም ነበር በማለት  ፤ ለቄሳራዊው ጣሊያን ያደሩት የድንቅ መጽሐፍ ደራሲ የሆኑት “ጦቢያ” እና “የዳግማዊ አጤ ምኒለክ” መጽሐፍ ደራሲ ዶ/ር አፈወርቅ ገብረ ኢየሱስ

 ”ስለ ትግሬ አንስተው በጻፉት “ምኒልክ መቸ ይነግሡልን እና ይኼ አምበጣ ትግሬ በጠፋልን እያለ የማይመኝ በኢትዮጵያ አልነበረም።” ብለው የጻፉትን በኤርሚያስ አማረ ፌስቡክ ላይ ‘አፅብሃ አፅብሃ ሃጎስ’ የተባለ ወያኔ ለቁመዘማው እንዲመቸው ጠቅሶት ስላየሁት “ዋናው ጠላት ትግሬው እራሱ ወይስ አፈወርቅ ገብረ ኢየሱስ? በሚል ርዕስ የወያኔ ጀሌዎች ማወቅ ያለባቸውን እውነታ በራሳቸው በትግሬ ሰዎች እንደ ወዳጄ ገብረመድህን አርአያ

(በነገራችን ላይ ገብረመድህን እኔ ጋር መገናኘት ካቆመ ቆይቷል፤ በዚህ አጋጣሚ ይህንን ጽሑፍ እንዲያየውና እንዲደውል አውስትራሊያ ያለችሁ ወዳጆቹ ጋዜጠኞች አቀብሉት)

እንዲሁም ሌለው የትግራይ ሰው የሆነው “ትግሬዎች በትግሬዎች ላይ እንዴት እንደሚጨክኑ” የትግሬዎች እርስ በርስ መጠፋፋት ወንጀል ተጨማሪ ማስረጃ በሃውዜን ጭፍጨፋ የተደረገው የወያኔዎች ወንጀል አብርሃ ደስታ ያቀረበው ማሕደር ለማስታወሻችሁ ከሚለው ወርሃዊ አምዴ እነሆ መዘከሩ አስፈላጊ ስለሆነ አንባቢዎቼ እነሆ ለታሪክ መዝግቡልኝ። መልካም ንባብ፦

Sunday, June 22nd, 2014  

ሰኔ 15 የሰማታት ቀን ነው!

ABRAHA DESTA

POSTED AT ETHIO SEMAY ጌታቸው ረዳ

 

ሰኔ 15 የሰማእታት ቀን ነው። ሰኔ 15, 1980 ዓም በሐውዜን 2500 በላይ ንፁሃን ዜጎች በአንድ ፀሓይ የተጨፈጨፉበት ቀን ነው። ጭፍጨፋው የህወሓት እጅ እንደነበረበት ይነገራል። ይህ ማለት ቦምቡ የጣሉት ጀቶች የህወሓት ነበሩ ማለት አይደለም። ህወሓት በግዜው በሓውዜን ከተማ ጉባኤ እንደሚያደርግ ሆን ብሎ (የህዝብ ድጋፍ ለማግኘት) ለደርግ የሐሰት መረጃ አስተላልፏል። ብዙዎቹ የደርግ ጀነራሎችና መርማሪዎች የህወሓትስርዒትነበሩ። የአብዛኞቹ የደርግ ባለልስጣናት ፀሓፊዎች የህወሓት ስርዒት (ሰላዮች) ነበሩ። (አግአዚ ኦፕሬሽን ፊልም ይመልከቱ) ለህወሓት የሚሰሩ ወታደራዊ መኮነኖችና ፓይለቶች ነበሩ።

የሐውዜን ደብዳብ የታቀደ ድራማ ስለመሆኑ ጥርጥር የለውም። ነገር ግን ደርግም ሐላፊነት ይወስዳል። ደርግ መንግስት እስከነበረ ድረስ ህዝብን ማዳን ነበረበት፤ መረጃው ማስተካከል ነበረበት። ሲጨፈጨፍ የነበረው ሰለማዊ ሰው እንጂ ታጣቂዎች እንዳልሆኑ ይታወቅ ነበር። ስለዚህ ሁለቱም ሐላፊነት ይወስዳሉ።

ህወሓት መጥፎ ተግባሩ እንዳይታወቅ በመስጋት ድራማውን የሚያውቁ ታጋዮች እንዲረሸኑ ተደርጓል። ከድር የተባለ ታጋይምን ስንል ነበር? አሁን ምን እያደረግን ነው?” ብሎ በመጠየቁ ተገድሏል። ዳዊት የተባለምበሐውዜን የተደረገው ነገር ስህተት ነበርብሎ በመከራከሩ ምክንያት ተረሽኗል። ከዛ ጦፍ ተልኳል ተብሏል።

 

አሁንም ይሄ ጉዳይ አለ። በሐውዜን ጉዳይ ጥናት ያደረገ የሐውዜን ተወላጅ የሆነ ጋዜጠኛ አፈወርቂ አርአያ የሐውዜን ጉድ በማጋለጡ ምክንያት ታስሮ ነበር፤ አሁን ደብዙ ጠፍቷል። ሚስጥር ያጋልጣል በሚል ስጋት እንዲጠፋ ተደርጓል (የት እንዳለ የምታውቁ ንገሩኝ) ሌላ ገብረአነንያ ገብረስላሴ የተባለ የሐውዜን ተወላጅሓመድ ሓውዜን፡ መን ንመን?” በሚል ርእስ ብዙ ሚስጢሮች በማጋለጡ ምክንያት በሰበብ አስባቡ በመቐለ ከተማ ዓዲሓቂ ፖሊስ ጣብያ ያለ ምንም ፍርድ ለሦስት ወራት ታስረዋል፤ አሁንም እዛው በእስር ይገኛል።

 

ህወሓት ከደሙ ንፁህ ከሆነ ስለጉዳዩ የሚናገሩ ሰዎችን ማሳሰርና እንዲጠፋ ማድረግ ለምን ፈለገ? የሐውዜን ጉዳይ አልፏል። ማስታወስ አንፈልግም፤ ይሰማናልና። ለፖለቲካ ፍጆታ መዋልም የለበትም። ግን የእስርና እንግልት ምንጭ ደግሞ መሆን የለበትም። ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ ሰዎች መታሰር የለባቸውም።

የሆነ ሁኖ አልፏል። የኛ ያሁኑ ጉዳይ የሐውዜኑ ዓይነት ጨፍጫፍ በሰዎች ላይ እንዳይደገም መከላከል ነው። ዳግም ደም መፍሰስ የለበትም። ስለዚህ ህወሓትም ይፈፅመው ደርግ መደርጉ ስህተት ነው። ስሀተት በስህተትነቱ እናወግዘዋለን። ያሁኑ ጉዳይ ማነው የፈፀመው አይደለም። ያሁኑ ጉዳይ መፈፀም የለበትም፣ አልነበረበትም ነው።

ክብር ለሰማእታት! It is so!!!

በማለት አብርሃ ደስታ ስለ ሓወዜን ጭፍጨፋ በሚገርም ዘገባ ነግሮናል።

አብርሃ የተጠቀመው “ጦፍ” የሚለው የተጋዮች ቃል “መልዕክት” (መልዕክት ለማድረስ/ ተልዕኮ/ ሚሽን) ማለት ነው።

አመሰግናለሁ

ጌታቸው ረዳ   ETHIO SEMAY