Saturday, December 26, 2020

ይጀመራል ከቤት፣ ይከተላል ጎረቤት! አገሬ አዲስ (Ethiopian Semay) ታህሳስ 17ቀን 2013 ዓም(26-12-2020)

 

 

ይጀመራል ከቤትይከተላል ጎረቤት!

አገሬ አዲስ

(Ethiopian Semay)

ታህሳስ 17ቀን 2013 ዓም(26-12-2020)

 

የአንድ ቤተሰብ ሰላምና ክብር በሌሎቹ ዘንድ  ሊጠበቅ የሚችለው የቤተሰቡ አባላት ፍቅራቸው የጠነከረ፣ ለክብራቸውና ለሰላማዊ ኑሮዋቸው ቀናዊ ሲሆኑ ነው።ሰላም፣ፍቅርና መተሳሰብ በሌለበት ቤተሰብ ውስጥ ሽኩቻ፣የእርስ በርስ ጠብና ግጭት መከሰቱ አይቀሬ ነው።ጠብና ግጭቱ በከረረ ቁጥር ቤት ይፈርሳል፣ቤተሰብም ይበተናል። በውጭ ይጠባበቅ የነበረው ደበኛ ወይም ዘራፊ ሰርጎ ለመግባትና ያሻውን ለማድረግ ምቹ ሁኔታ ይፈጥርለታል።  አድብቶ ለማጥቃት የሚጠባበቅ ጠላት በቤተሰቡ ውስጥ ይህ ሁኔታ እንዲከሰት ያላሰለሰ ጥረት ያደርጋል።ከቻለ ሁሉንም አጥፍቶ የቤተሰቡን ቤትና ንብረት ለመውረስ አለያም ለእርሱ የሚመቸውን በመርዳት  ጥቅሙን ለማስከበር የሚነሳበት ወቅት የቤተሰቡ ሁኔታ ከሚፈጥረው ግርግርና ጭቅጭቅ ጋር የተያያዘ ይሆናል።

 በተመሳሳይም በአገራችን ላለፉት ሰላሳ ዓመታት የኢትዮጵያን ሰላምና አንድነት ለማናጋት ብሎም ለመበታተን በውጭ ሃይሎች ድጋፍ የሚንቀሳቀሱት በጎሳ የተደራጁት የፖለቲካ ድርጅቶች በዘረጉት ስርዓትና በሕገመንግሥት ስም በነደፉት የጥፋት ሰነድ እውቅና የተቻረው የጥፋት ዘመቻ ሳቢያ የተከሰተው ሁኔታ ይህንኑ ይመስላል።በውስጥ የነዚህ የጥፋት ሃይሎች መብቀል ለአሁኑ የውጭ ሃይሎች ሰርጎ ገብነትና ወረራ በር የከፈተ ነው።ሁለቱም የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጾች ናቸው።

የመጨረሻው ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ሃይለሥላሴ በየካቲቱ ሕዝባዊ እንቅስቃሴ ወቅት ከሁሉም የመከላከያ  ጦር ክፍሎች የተውጣጡትን ወታደሮች  በቤተመንግሥታቸው ቅጥር ግቢ ውስጥ ሰብስበው ባደረጉት ንግግር ወታደሩ አገሩንና መንግሥቱን ከአደጋ እንዲከላከል ማሳሰቢያና ትዕዛዝ ሰጥተው ነበር።በዛም እለት “ውሻ በቀደደው ጅብ ይገባበታል” የሚለውን የተለመደ አባባል ተጠቅመው የውጭ ጠላቶች መጠቀሚያ መንገድ እንዳያገኙ ነቅቶ መጠበቅ እንደሚገባ አሳስበው  ነበር። ያሉት አልቀረም ከጥቂት ዓመታት በዃላ አገራችን የውጭ ሃይሎች በተለይም አረቦች  በቀጥታና በተዘዋዋሪ ጣልቃ ገብተው እስከአሁንም ድረስ የሚያተራምሷት አገር  ሆነች። አዎ! ለውጭ ጅቦች መግቢያና መሳሪያ የሆነው አገር በቀሉ ውሻ ነው።

አሁን በሱዳኖች ለተጀመረው ድፍረት፣የድንበር መጣስና ወረራ ግብጾች ከዃላ ተሰልፈው የሚመሩት ለመሆኑ አጠያያቂ ባይሆንም ለነሱ የጥቃት እርምጃ የበለጠ ሞራልና ጉልበት ብሎም አጋር የሆናቸው በዬጎሳው ስም ተደራጅተው የሚንቀሳቀሱት አገር በቀል እራስ ጠል የሆኑት ቡድኖች ናቸው።ለጎሳ ትውልዳቸው ሕዝብና ቦታ መሻሻል ፣መብትና ነጻነት በሚል ሽፋን  ለዘረፋ የሚያበቃቸውን  ሥልጣን ለመጨበጥ ላላቸው ስግብግብ ዓላማ ተገንና መከታ የሚያደርጉት ጸረ ኢትዮጵያ የሆኑትን የውጭ ሃይሎች ነው።ኢትዮጵያ ታፍራና ተከብራ ለዜጎቿ የተመቸች ዴሞክራሲያዊት አገር ሆና ከማዬት ይልቅ ፈራርሳ የውጭ ሃይሎች እንደዬ አቅማቸው የሚቀራመቷት የቄራ ከብት ሆና ማዬትን ይመርጣሉ።እነሱም የአንድ ልዑላዊት አገር ዜጋና ባለቤት ከመሆን ይልቅ በቅኝ ገዥዎች ሰንሰለት ታስረው ባርያና አገልጋይ መሆንን ይሻሉ።ቀደም ሲል የኤርትራ ተገንጣይ ሃይሎች ፣ጀበሃና ሻእብያ፣በነሱም ጥላ ስር የተፈጠሩት ህወሃትና ኦነግ የኢትዮጵያን መጥፋት እንጂ እንዳገር መኖር አይፈልጉም።ከመፈራረስዋ በፊት ግን በሃብቷ እንፈጥረዋለን ላሉት አገር  የአቅም ግንባታ አንዳንድ የልማት መስኮችን በተለይም የመከላከያ አቅም ሲገነቡ ኖረዋል።ላለፉት ሰላሳ ዓመታት በኢትዮጵያ ላይ የሰፈነው የጎሰኞች  የፖለቲካ ስርዓት ይህንኑ የሚያስፈጽም ተልእኮ የተሸከመ ነው።በመካከላቸው በተነሳ የጥቅምና የሥልጣን ሽኩቻ አንዳንዶቹ ቢከስሙም የቀሩት አሁንም በቦታው ላይ አሉ።ለእኩይ ዓላማቸው ሕዝብን ከሕዝብ ማናከስ አንዱ ስልታቸው ነው።ወያኔዎች አማራውንና ኦሮሞውን እሳትና ጭድ ብለው እንዳይተማመን ሲያደርጉት ቆይተዋል።የአሁኖቹም ባለተረኞች የኦነግ ውልዶች አማራውንና ትግሬውን ደም አቃብተውታል።

እነዚህን በታሪክ፣በባሕል፣በሃይማኖትና በማህበራዊ ትስስር ለአያሌ ዘመናት አብረው የኖሩ፣በደም ና እትብት የተሳሰሩ፣ለኢትዮጵያ አገራዊ ምሥረታ ግንባር ቀደም የሆኑ ማህበረሰቦች “አቢሲኒያ” በሚል ስያሜ እዬጠሩ ባገሪቱ ውስጥ ለተከሰተው ችግር ሁሉ ፣ለአዬር ለውጡና መዘዙ ጭምር ሳይቀር ተጠያቂ አድርገው በጠላትነት ፈርጀዋቸዋል።በስልጣን ላይ ያለው ባለተረኛው ኦነግ/ኦህዴድ -ብልጽግና መንግሥት በህወሃት የሚመራውን ቡድን በጦር ሲያንበረክክ የአማራውን ጎሳ ተጠቅሞ ነው።ካለው ቅርበትና የውጊያ ችሎታ ጦርነቱ በአጭር ጊዜ እንዲጠናቀቅ ታላቁን ሚና ተጫውቷል።ለሰራው ጀብዱ ግን በመንግሥት በኩል ምስጋና ቀርቶ እውቅና አልተሰጠውም።  የኦሮሞ መራሹ ቡድን እግሩ ትግራይ መሬት እንደረገጠ በወያኔ መዳፍ ስር የነበረው ያገሪቱ ሃብት፣የጦርና የልማት መሳሪያዎች ቀን በቀን ተጭነው ወደ ኦሮሞ ክልል ተዘርፈው መወሰዳቸውን የሚያወሱ ዜናዎች አጋልጠዋል።ይህም አድራጎት  የቀጣዩን ሂደት አመላካች ነው።ከዚያም ቀጥሎ ጦርነቱ ሙሉ ለሙሉ ሳይጠናቀቅ ፊታቸውን ያዞሩት ህይወቱን ዳርጎ፣የፈንጂ ማብረጃ ሆኖ ባዳናቸው፣ በግላጭ ብቻውን በቀረው፣ለኢትዮጵያ ህልውና በጽናት በቆመው የአማራ ጎሳ ላይ ነው።ይህ ትልቅ ሕዝብ በሚኖርበት ቦታ ሁሉ ኦነጎችና በሥልጣን ላይ ያሉት ተከታዮቹ ግልገል ቡችላ የሆኑትን ጥቃቅን ጎሰኛ ቡድኖች በማስታጠቅና በመምራት ተደጋጋሚ ጥቃት እንዲሰነዘርበት አድርገዋል። ይህንን ሲያደርጉ ግን ለከባቢው ደሃ ኑዋሪ አስበው አይደለም፤የመተከልን ለምና የብዙ ማዕደን ጓዳ የሆነ ሰፊ መሬት ወሮ ለመያዝ፣በተለይም ለወደፊቱ የሃይል ማመንጫነት በሁሉም ኢትዮጵያዊ እርብርቦሽ በመገንባት ላይ ያለውን ትልቁን  የህዳሴ ግድብ በክልላቸው ውስጥ ለማስገባት ነው። ለዚያም እንደ አዲስ አበባ ከተማ የሕዝቡን ስብጥር ለመለወጥ ካላቸው እቅድ የነዋሪውን ስነልቦና በመስለብ በግድ የኦሮሞ ቋንቋ ተናጋሪ እንዲሆን በኦሮሞ አስተሳሰብ በማጥመቅና ቁጥሩ በኦሮሞ ተወላጆች እንዲዋጥ የኦሮሞ ተወላጆችን ከሌላ ቦታ በማምጣት በማስፈር ነው። ቢቻላቸው በዚሁ መልክ መላ አትዮጵያን  ኦሮሚያ ለማድረግ ባይቻላቸው ኢትዮጵያን አመንምኖ ኦሮሚያ የተባለ አዲስና ትልቅ አገር ለመፍጠር ነው።

 

አሁን በአማራ ጎሳ ላይ የሚደረገው ጭፍጨፋ ነገ በሌሎቹ ጎሳዎች ላይ ላለመደረጉ ዋስትና የለም።ዛሬ በሰሜኑና በምዕራቡ ክፍል የሚካሄደው የመሬት ቅርምት ነገ በሌሎቹ ቦታዎች ላይ ላለመደረጉ ማረጋገጫ የለም።ሁሉም በዬተራ የሚጋተው መራራ እጣ ፈንታ ነው።ያንን ተገንዝቦ በማንዣበብ ላይ ያለውን የመዋጥ አደጋ በህብረት ሊያሶግዱት ይገባል።በኢትዮጵያዊነት ተሰልፎ በጋራ ከመቆም የተሻለ አማራጭ የለም።     

አገራችን መሪ አልባ በሆነችበት በአሁኑ ጊዜ ፣በውስጥ ሽብርና ቀውስ በምትናጥበት ጊዜ፣በጎሳ ማንነቱና በሃይማኖቱ ሕዝብ እዬተለዬ በሚጨፈጨፍበት ጊዜ፣በአጠቃላይ የእርስ በርስ ውጊያ (ሲቪል ዋር) ከዳር እስከዳር ለመከሰት ጠርዝ ላይ በሚገኝበት ጊዜ፣ የውጭ ሃይሎች በጋራ መቆማቸው የሚያስገርም አይሆንም።የሚያስገርመው ነገር ቢኖር በሥልጣን ላይ ያለው ጠ/ሚኒስቴር አብይ አህመድ ይህንን የውስጡን ችግር የሚያቀጣጥለው የጎሳ ፖለቲካና በተለይም እሱን ያሳደገው የኦነግ መሪዎች የሚዘውሩት መንግሥት መሆኑን ክዶ ሁሉንም ችግር በውጭ ጠላቶች የተጠነሰሰ ሴራ ነው ማለቱ ነው።ፍዬል ወዲህ ቁዝምዝም ወዲያ!

በቅርቡ በመተከል የተከናወነውን የንጹሃን ዜጎች ጭፍጨፋ ምክንያት በማድረግ አካባቢውን በጎበኘበት ስብሰባ ላይ “ የውጭ ሃይሎች በጎሳ፣በብሔርና በሃይማኖት ከፋፍለው ሊያጋድሉን ሙከራ አድርገዋል፤እያደረጉም ነው፤ግን አይሳካላቸውም ” ሲል ተደምጧል። ጅንጀሮ የራሱን መላጣ ሳያይ በሌላው ጅንጀሮ መላጣ ይሳለቃል እንደሚሉት ነገር ነው።ለመሆኑ አገራችንን ለመበታተን ፣ሕዝቡን ለእርስ በርስ ግጭት፣ግድያና መፈናቀል የዳረጋት እራሱ የሚመራው የዘር ፖለቲካ የሚያራምደው መንግሥት ተብዬው ስብስብ መሆኑን ዘንግቶት ይሆን?የጥላቻ ጡጦ አጥብቶ ያሳደገው ኦነግና ህወሃት የተባሉ አገር አጥፊ ቡድኖች መሆናቸውንና የዘረጉት የጥፋት መረብ መሆኑን እረስቶት ይሆን? እርሱ የሚመራው  መንግሥት የሚመራበት ሕገመንግሥት ተብዬው አገር የሚበታትንና ለዚህ አደጋ ያጋለጠንን ሰነድ መኖሩን ሳያውቅ ቀርቶ ይሆን?አይደለም። ዓይናችሁን ጨፍኑ ላታላችሁ ከሚለው ብልጣብልጥነት  ወይም ሕዝብን ከመናቅ  ልማዱ የመነጨ ትርክት ነው።ሕዝብን  ከአንድ ጊዜ በላይ ማታለል እንደማይቻል ቢያውቀው ጥሩ ነው።ያልተናገረ ሕዝብ አያውቅም ማለት አይደለም።

አጎንብሶ ቢሄድ ሞኝ ነው ወይ በጉ፣

ነገርን ካልተውት ናቅ እያደረጉ።

የሚለውን የትዝብት ስንኝ ማስታወሱ  መልካም ይሆናል።

በውስጥም ሆነ በውጭ  ላለመደፈር፣ብሔራዊ  ዳር-ድንበርን ለማስከበር በኢትዮጵያዊነት አስተሳሰብና ዓላማ ላይ ያረፈ አደረጃጀትና አሰላለፍ ያስፈልጋል።ለዚያ ደግሞ አሁን በአገራችን ተደራጅተው የሚንቀሳቀሱትን የጎሳና የሃይማኖት የፖለቲካ ድርጅቶችና ስብስቦችን በሕግ ማገድ ተገቢ ነው። ያም ብቻ በቂ አይሆንም፤ለነሱ ሕጋዊ እውቅና የሚሰጠውንም ሕገመንግሥት ተብዬ  የጥፋት ሰነድ ቀዶ መጣል አስፈላጊ ነው።ይህንን ወሳኝና ታሪካዊ እርምጃ የአብይ መንግሥት በራሱ ላይ ዘምቶ ይወስደዋል ብሎ መጠበቅ ሞኝነት ነው።ስለሆነም አገራችን የተደቀነባትን የውስጥና የውጭ አደጋ ለመቋቋም የሚችል ጠንካራ ወታደራዊ፣ፖለቲካዊና ሕዝባዊ ተቋም ያለው አካል መፍጠር የግድ ይላል።ከአገር ወዳድ ሃይሎች የተውጣጣ የቀውስ ጊዜ መንግሥት ወይም አስተዳደር (War time Administration or Government)ማቋቋም ለነገ የማይሉት ብቸኛ ምርጫ ነው።

አብይ አህመድ  ደፍሮ በጡት አባቶቹ በኦነግ/ኦህዴድ፣በሕወሃትና በዘረጉት መረብ ላይ መቀስ ያነሳል ተብሎ አይጠበቅም፤እሱ እራሱ የወንጀሉ ተካፋይ፣ለሥልጣንም ያበቃው የጎሳ ፖለቲካ ስለሆነ ለደረሰው ጥፋት ሁሉ አንዱ ተጠያቂ ነው።ለዚያም ነው ወንጀለኞቹን ህወሃትን፣ኦነግንና ሌሎቹንም በጭፍጨፋ (ጀኖሳይድ)ወንጀል ለመፈረጅ ያልደፈረው።መስተዋት ቤት የሚኖር ሰው በድንጋይ አይጫወትም ይባል የለ!የአብይ መንግሥትም እንደዚያው ነው።የሚወረወረው ድንጋይ እራሱንም ስለማይምረው ደፍሮ እጁን አያነሳም፤ቢያነሳም በደቃቃዎቹ ላይ  እንጂ በግዙፎቹ ላይ አይሆንም።ለግላጋ ወጣት ተማሪዎችን አግቶ ቤተሰብ የሚያስለቅሰውን የኦነግ ታጣቂ ወንጀለኛ ቡድን በሃይል አስገድዶ ወጣት ተማሪዎችን ከማስለቀቅ ይልቅ ወንጀሉን በመሸፋፈንና ያጋለጡትን በማስፈራራት ፍትሕ እንዳያገኝ አድርጓል።

ሌላው የአብይ ጉልበቱ በእውነተኛ የፖለቲካ ድርጅት መሪዎችና ተቃዋሚዎቹ ላይ ነው። በነሱ ላይ ፍትሕን እረግጦ ያሻውን ያደርጋል። በባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ መሪዎችና አባላት ላይ የተጣለው ክስ፣ እስራትና መቋጫ የሌለው ቀጠሮ፣በአቶ ልደቱ አያሌውና በኢንጅነር ይልቃል ጌትነት ላይ የደረሰው ሕገ ወጥ እርምጃ ፣በትንታግ ጋዜጠኞች፣በተመስገን ደሳለኝ፣በአልማዝ ሙሃመድ፣በመስከረም አበራ፣በአስቴር በዳኔና በሌሎቹም  ላይ የሚደረገው ወከባና ዛቻ የዚሁ የዘረኞቹ ማን አለብኝነት የወለደው የግፍ ውጤት ነው።የምርጫ ቦርዱን ብትር አድርጎ በመጠቀምም ሰሞኑን በምርጫ ውድድር ያሰጉኛል የሚላቸውን ድርጅቶች ከማይረቡት ጋር በማቀላቀል ሰርዟቸዋል።እነ እስክንድርንም በምርጫው እንዳይሳተፉ ለማድረግ የመጀመሪያውን የምስክር ቃል መቀበያ ፍርድ ቤቱን ቀጠሮ አሽቀንጥሮ ወደ አራት ወር ወርውሮታል።የሌሎቹን ምስክሮች ቃል ለመስማት ከዓመት በላይ እንደሚፈጅ ይህ አማላካች ነው። መታወቅ ያለበት ነገር ቢኖር የአንድን ድርጅት መሪዎች በማሰር የሕዝብን ድጋፍ ማቆም እንደማይቻል ነው።የደቡብ አፍሪካው መሪ ማንዴላ የአገሩን ሕዝብ ብቻ ሳይሆን የዓለምን ሕዝብ ድጋፍ ያገኘው በሮቢን ደሴት እስርቤት ውስጥ በሚማቅቅበት ጊዜ ነው።የባልደራስንም ሆነ የሌሎቹን  ድርጅቶች የሕዝብ ድጋፍ መሪዎቹን በማሰርና በማሶገድ ለጊዜው ቢመስልም ዘለቄታ አይኖረውም።

ከሁሉም በፊት ግን ለሃቀኛ ምርጫ ሃቀኛና አስተማማኝ ሁኔታ በአገሪቱ ሲሰፍን፣ድርጅቶች በነጻነት ከዳር እስከዳር ተንቀሳቅሰው ሕዝቡን ለመቀስቀስ የሚችሉበት ሁኔታ ሲፈጠር ነው።በአሁኑ ሁኔታ ምርጫ ለማድረግ የሚደረገው እሩጫ ግን ባለተረኞቹን ሕጋዊ እውቅና እንዲኖራቸው የሚያደርግ ከዝግ ችሎት ያልተናነሰ ሂደት ይሆናል።      

አብይ አህመድ ከፊት ለፊት ሆኖ  ሕዝብ እያጃጃለ፣ኦነግና የኦነግ ውልድ የሆነው ኦህዴድ የወደፊቷን ኦሮሚያ የተባለች አገር ለመመሥረት ደፋ ቀና እያለ ነው።አዲስ አበባን ከኢትዮጵያውያን እጅ ፈልቅቆ  በመውሰድ ፊንፊኔ በሚል ስም ሰይሞ ዋና ከተማው ለማድረግ የቤት ሥራውን ከጀመረ ውሎ አድሯል።የነዋሪውን ሕዝብ ስብጥርነት (ዴሞግራፊ) ለመቀዬር  በግላጭ የተነገረው በተግባርም እዬተገለጸ ነው።የኦሮሞ ከፍተኛ ፍርድ ቤት፣የኦሮሞ ባህል ማእከል፣የኦሮሞ ርዕሰመንግሥት ቢሮ።የኦሮሞ ወጣቶች ማእከል…ወዘተ የሚሉት ተቋማት ባጀት ተመድቦላቸው በመገንባት ላይ ናቸው።ባንኮችማ በኦሮሞ መዳፍ ስር ከወደቁ ቆይቷል።የማዕድን ዘርፎችም እንዲሁ።ወንጀል የፈጸሙት የኦህዴድ ባለሥልጣኖች ከቦታ ቦታ እዬተቀያዬሩ ከመሾምና ከመሸለም በተረፈ ለፈጸሙት ወንጀል ተጠያቂ አልሆኑም።ሁሉም ነገር የጎሳ ታፔላ ተለጥፎበት ህጋዊ እውቅና ተሰጥቶታል።የኦሮሞ ታፔላ ግን ከሁሉም ይበልጣል።በባለተረኝነት ስሜት፣ሁሉም የእኔ በሚል መረን አልባ ስግብግብነት ወይም ቅዤት ከጫፍ እስከጫፍ በእብደት ፈረስ እዬጋለበ ነው።በአጠቃላይ ጎሰኝነትን በቃህ የሚለው፣ የሚያስቆመው ኢትዮጵያዊ  ልጓም፣ አገር ወዳድ ሃይል ሊነሳ ግድ ይላል።

ኢትዮጵያ በውስጥ ችግር በምትገባበት ወቅት የውጭ ጠላቶች መነሳታቸው የአሁኑ የመጀመሪያ አይደለም።በታሪክ ተደጋግሞ ታይቷል። በዘመነ መሳፍንት ጊዜ የሥልጣን ሽኩቻ ሲነሳ  የምዕራብ አውሮፓ አገሮች በተለይም ጣልያንና እንግሊዝ ግጭቱን በማባባስ፣ለአንዱ እርዳታ በማቀበል የቅኝ ግዛት ፍላጎታቸውን ለማረጋገጥ ሞክረው በኢትዮጵያኑ ብልህነትና ቆራጥነት በአንድ ላይ በመቆም በወሰዱት እርምጃ  ሳይሳካላቸው ቀርቷል። ከዚያም ማእከላዊ መንግሥት እንዳይጠናከር ተደጋጋሚ ሙከራዎች አድርገው አልተሳኩላቸውም። ከዛሬ ሃምሳ ዓመት ወዲህም በተለይም በደርግ ጊዜ የነበረውን ውስጣዊ የፖለቲካ አለመረጋጋት ተከትሎ ተገንጣይ ሃይሎችን ከመርዳት ባለፈ፣የሶማሊያ መንግሥት ሲሻና ሲመኝ የነበረውን የኢትዮጵያን ግዛት ቆርሶ ለመውሰድ አጋጣሚውን ለመጠቀም በተነሳበት ጊዜ ሱዳን፣ግብጽ፣የአረብ አገራትና የምዕራብ አገሮች በአሜሪካ መሪነት የተቀናጀ ጦርነት አውጀውባት ነበር።በዚህም ጊዜ በኢትዮጵያውያኑ ቆራጥ እርምጃና አሁን የግራ ፖለቲካ ተብሎ በስህተት በሚፈረጀው በሶሻሊስት ስርዓት ይመሩ በነበሩት አገሮች በተለይም የሶቪዬት ህብረት፣ምስራቅ ጀርመን፣ኩባና የመን ድጋፍና የጦር ሜዳ ውሎ ጠላት ድባቅ ሆኖ ጉዳይ አስፈጻሚ የነበረው የሶማሊያ ጦር ተሸንፎ የዃላዃላም የራሱንም አገር እስከማጣት ደረሰ።

የውጭ ጠላት ሴራ በዚህ ብቻ አልቆመም ለወያኔ መራሹ ስርዓት መስፈንና ለኤርትራም መገንጠል ምክንያት ሆኗል።የአሁኑም ከዚያ አይለይም።መፍትሔውም ከዚያ የተለዬ አይሆንም።አሁን የምዕራቡ አገሮች በአሜሪካ መሪነት የሰብአዊ መብት ማስከበር በሚል ሰበብ ለሕዝቡ ያሰቡ መስለው በሚጠቀሙበት በተባበሩት የዓለም ድርጅትና በስሩ ባሉት ተቋማት በኩል ለጣልያን ወረራ ያደረጉትን ድጋፍ በሚመስል መልክና ደረጃ ለግብጽ ጥብቅና በመቆም ጸረ ኢትዮጵያ የሆነ ዘመቻቸውን ክፍተዋል።  አገር ወዳዱ ሃይል ተሰባስቦ የውስጥና የውጭ ሃይሎችን ድባቅ ለመምታት የሚያስችል ቁመና ላይ መገኘት አለበት።ያ ካልሆነ ግን  የግብጽና ሱዳን ብቻ ሳይሆን የደቃቃዎቹ ጎረቤት አገሮችም፣ የደቡብ ሱዳን፣ኬንያ፣ጅቡቲና ሶማሊያ መቀለጃ መሆናችን ሳይታለም የተፈታ ነው።ባዶ ቤት በቁንጫ ይወረራል ይባል ዬለ!

የውጩን ጠላት ከመቋቋሙ ጎን ለጎን  የውስጡን ባንዳ  መምታቱ ተነጥሎ መታዬት አይኖርበትም። አዎ! ባዶ ቤት በቁንጫ ይወረራል!ቁንጫውን ለማሶገድ ቤቱ በየቀኑ መጠረግ አለበት።ብጉር ከታገሱት ኪንታሮት ይሆናል!ክንታሮት ከመሆኑ በፊት ግን ማፍረጡ ከጉዳት ያድናል።

የሕዝብን እንባና ስቃይ፣ያአገርን ውድቀት ሃይል እንጂ ልመና አያቆመውም።  

ለአገር አድን ተጋድሎ የአገር ወዳዶች ፖለቲካዊና ወታደራዊ ግንባር ይመስረት!

አገሬ አዲስ           

Wednesday, December 23, 2020

አብይ አሕመድ ዓሊ የውጭ ሃይሎች ቅጥረኛ እንጂ መሪ አይደለም! ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay Wedensday, December 23, 2020

 

 

አብይ አሕመድ ዓሊ የውጭ ሃይሎች ቅጥረኛ እንጂ መሪ አይደለም!

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay

Wedensday, December 23, 2020

ከመገረሜ ብዛት ከመጻፍ ልቆጠብ እልና አላስችል ይለኛል።  የሩዋንዳን የዘር ፍጅት ያስናቀው ለ30 አመት በመላዋ ኢትዮጵያ በተለይ ደግሞ በኦሮሞዎቹ ክልል እና በጉሙዞች መተከል ውስጥ እየተካሄደ ያለው በአማራ ላይ እየተፈጸመ ያለው የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ እየባሰ የመሄዱ ጉዳይ ስመለከት አንጀቴ “እሬት” እስኪተፋ ድረስ ያቅረኛል። ይህ ሁሉ ጭፍጨፋ ሲካሄድ መንግሥት ማስቆም ያቃተው እንዳይመስላችሁ። አብይ እየመራው ያለው የ3 አመት አገር በቀል የቅኝ ግዛት አስተዳደር ነው ብየ እስኪደክመኝ ድረስ ጽፌኣለሁ። አብይ ስለ አማራ በተመለከተ ሲናገራቸው የነበሩት ንግግሮቹ ወደ ሗላ መርምሩዋቸው። ሃቁን ከምላሱ ታገኙታላችሁ።

 

 ክስተቱ 27 አመት በትግሬዎች 3 አመት በኦሮመዎች እጅ የወደቀች አገር ምስጢሩ “የተረኛ ቅብብሎሽ ምስጢር” መሆኑን ማየት ምትችሉት ዘር ጥቃት እና ግድያዎች እየተባባሱ እንጂ መቆማቸው እንዳልሆነ በቂ ማሳያ ነው። ለዚህ ከስተት ደግሞ “ተቃዋሚ ተደማሪ” እየተባሉ የሚጠሩት ወደ ነዳሃቸው የሚነዱ በጎች ለውጭ አገር ለተረኛው ንጉሥ ለአብይ አሕመድ ከፈተኛ ድጋፍ እና ድምጽ በመስጠት አማራ እንዲያልቅ ተጨማሪ እሾሆች መሆናቸውን አትዘንጉ። ተርኞቹ ዛሬም አጨብጫቢ አላጡም። በትንሽ ነገር ይረካሉ በትንሽ ነገር ያፍራሉ።

 

ኢትዮጵያ ውስጥ በወያኔ ፋሺሰት አገር ገንጣይ መሪዎች እና በኦሮሙማው ፋሺሰቱ መሪ ኮ/ል አብይ አሕመድ “ቸልተኝነት ምክንያት” የተከሰተው ጦርነት ያስከተለው የሰው እና የንብረት ጥፋት አስቀድሞ መቆጣጠር ወይንም መቀነስ ይቻል እንደነበር ብዙ ምክር ቢሰጠውም ያንን ካለመቀበል አሁን ላለው ዕልቂትና የውጭ አገር ከበባ ዳርጎናል። በሚገርም ሁኔታ ዛሬም እንደ ባድሜው “ካድሬዎቹ” ያለምንም ሓፍረት በባድሜ ጦርነት ከሚገባው በላይ ለመለስ ዜናዊና መሰሎቹ የተቸረው “ኢትዮጵያ ጀግኖች ” እያሉ በውሸት ሰንደቃላማችንን ስያውለበልቡ በነበረበት ወቅት ሲቸራቸው የነበረው “ኢትኦጵያዊነት” የመሆን ጋጋታና ሙገሳ ልክ እንደዛው ሁሉ ዛሬ ያንኑ ስዕል ለአብይ አሕመድ ተችሮታል።

 

 እነ እስክንድርን እና እነ ልደቱን እንዲሁም ብዙዎች ብርቱ እህቶቻችንን እስር አስገብቶ በሽብር በመወንጀል ማሰቃየቱን እንድንረሳው ለማድረግ ያንን ወንጀለኛ እና ቅጥረኛ ውሳኔውን ወደ ጓዳ ገሸሽ ተደርጎ “አብይየየየ ኢትዖጵያዊየየ! መሪየየየ” እያሉ የሕሊና ቀውስ ያሰቃያቸው የፌስቡክና ዩቱብ “ዕብዶች” ሲያቆላምጡት ሰምተናል። ይህ የሚያሳፍር “የማሽቃበጥና የማንቛለጥ”ታሪክ እንደገና ያፈርንበትን እንደገና ተደጋግሞ የመደገሙ ክስተት ምን ማድረግ እንደሚሻል ግራ ገብቶኛል።   

 

ፒየር በርጌሮን የተባሉ ቄስ ይሁኑ ዳኛ ብቻ እንዲህ ያሉትን “ቅጠረኛ እና እረኛ” ልይነቱ  ምንድነው? በሚል የጻፉት አንብቤ ልቤን የነካው አባባላቸው ላጋራችሁ። እረኛ የሚሉት “እየሱስን ነው”፡ ቅጥረኛ ደግሞ በገንዘብ ወይንም በሥልጣን የተደለለ የውጭ ተላላኪ፤መሰሪ፤የጥፋት ሃይል፤አታለይ ማለት ነው።፡እንዲህ ይላሉ፡እረኛው ለመንጋው  በፍቅር እና በፍላጎት ሲያገለግል በሌላ በኩልአገልግሎቱን ለተለያዩ ጥቅማጥቅሞችና ስምምነቶች የሚሸጥቅጥረኛእንጂ የሕዝብ እረኛ ሊሆን አይችልም ፡፡” ይላሉ፤ እውነት ነው።

 

 አንድ ቅጥረኛ አገልግሎቱን ከሸጠላቸው ሰዎች ጋር የተለየ ስሜትና ዝምድና አለው እረኛው ደግሞ ለመንጋው ሙሉውን ልብ በመስጠት እለት ከለት ደቂቃ በደቂቃ በጎቹ በአራዊት እንዳይበሉ በጋለ በፍቅር ይከታተላል፤ይከላከልላቸዋል። ዘርዘር አድርጌ እንዲህ ላስቀምጠው። በአንድ አገር አደጋ ወይም ችግር በሚመጣበት ጊዜ የቅጥረኛው ተሳትፎ ውስንነቶች አሉት፡ አንዴ ወዲያ አንዴ ወዲህ የማለት ሸንጋይነትና፤ ወላዋይነት ባሕሪ በመያዝ ውሳኔዎችን በማቅማማት ጎርፉ “በርትቶ እንግዳ ደራሽ” እስኪሆን ድረስ ይጠብቃል። ምክንያቱም ህይወቱን እና ምቾቱን ከቀጠሩት ሰዎችና ከሚፈልጋት አልጋ (ዙፋን) ጋር የተያያዘ ነው ፡፡

 

በተቃራኒው እረኛው ሙሉ በሙሉ መንጋውን ከአደጋ ለመዋጋት ቁርጠኛ ነውና በጎቹን ለመጠበቅ የበጎቹ እንቅስቃሴዎችና የአራዊት ኮሽታዎችን ለመመዘን ሁሌም ዝግጁ ነው ፡፡ እንደ አብይ አሕመድ ያለው ኩሌ/ቅጥረኛው (ባጭሩ) በሰዎች ላይ (የአማራ ማሕበረሰብን ህይወትና ሰቆቃ) ምንም ልዩ ፍላጎትና ትኩረት ሳያድርበትዙፋኑና የከተማ ውበቶችን ብቻ “በእዩልኝ እዩልኝ” ያተኮረ ነው።

 እረኛው መንጋውን ስለሚመራ በየደቂቃው  ምግብን መመሪያን እና ጥበቃን” ይሰጣል ፡፡ እጅግ የሚያሳዝነኝ ግን ወታደሩ ለናት አገሩ ሲል በተጠራበት ወቅትና ደቂቃ በፅናት እና በክብር መስዋዕት ለመሆን ዋጋ ለመክፈል የማይፈሩ  ታማኝ ወንዶች እና ሴቶች ወታደሮቻችን ሁሌም አንጀቴን ይበሉታል።  ኢትዮጵያ አሁን ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ምንሊክ ቤተመንግሥት ውስጥ አብይ አሕመድን የሚተካ አውነተኛ ዕረኛ ትፈልጋለች ፡፡ ከሕግ ይልቅ ክብር ያለው ነገርራስን ከማገልገል ይልቅ የራስን ጥቅም መሥዋዕት ማድረግ ምን ማለት ነው  እንደሆነ የሚያሳየን እረኛ እንሻለን፡፡ አመሰግናለሁ ፡ ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ) Ethiopian Semay

 

Sunday, December 20, 2020

ነሽመልስ አብዲሣም ልክ እንደነስብሃት ነጋ … ይነጋል በላቸው EthiopIna Semay Decmber 20, 2020

 

እነሽመልስ አብዲሣም ልክ እንደነስብሃት ነጋ

ይነጋል በላቸው

EthiopIna Semay

Decmber 20, 2020 

        አማራነትና ኢትዮጵያዊነት ዐይኑን ባፈጠጠ መልኩ ላለፉት አምስት አሠርት ዓመታት ከፍተኛውን ሙቀት በሚያመነጭ ሥሑል ነበልባላዊ እቶን ውስጥ መገኘታቸው ይታወቃል፡፡ አሁንም በዚያው ጊሎቲን ወኦሽትዊዛዊ ‹ቻምበር› ውስጥ ለመሆናቸው የአቢይ አህመድ የቀኝ እጅ የሆነው ሽመልስ አብዲሣ የሚያሽከረክረው ኦሮሙማ በመተከልና በወለጋ ጫካዎች የሚያፈሰው የአማራ ደም ምሥክር ነው፡፡ ሽመልስ ሆይ በምታፈሰው ደም ደስ ይበልህ!

 

        ሙት ወቃሽ አያድርገኝና የወያኔው ቃል አቀባይ የነበረው ያ ገልቱ ጌታቸው ረዳ አቢይ አህመድ ሁሉንም ነገር እንደሸጠ ሲናገር የነበረው በተወሰነ ደረጃ እውነት መሆኑን መረዳት አይከብድም፡፡ እናም አቢይ፣ አማራንና ኢትዮጵያን ለሰይጣን አምላኪዎቹ ምዕራባውያን እንደሸጣቸው ቢታመን ከሚታየው ነባራዊ ሁኔታ አኳያ ብዙም ስህተት አይሆንም፤ እንዲህም ስል ሞት የተፈረደባቸውን የማኅበረሰብ ክፍል አባላት ጨምሮ በዚህ ብላቴና ፍቅር ያበዱና የከነፉ ብዙ ልበ ሥውራን ዜጎች እንደሚቃወሙኝ ምናልባትም ከዚያም ባለፈ ፋቱዋ እንደሚያዝዙብኝ አላጣውም - ፍቅር ዕውር መሆኑ የሚነገረው ለዚህ ይመስለኛል፡፡ እንጂ በአቢይ አግላይና ፍትኅ የተዛባበት አመራር ኢትዮጵያና አማራ ይበልጥ ጠፉ፣ ይበልጥ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕረፍት አጡ እንጂ ጮቤ የሚያስረግጥ ምንም የተለዬ ነገር የለም፡፡ መሸጥ ሲባል ደግሞ በግድ በገንዘብ አንጻር ብቻ መታየት የለበትም፡፡ ሽያጭ ሁሉ ከማቴሪያላዊ አስተሳሰብ ትንሽ ወጣ ባለ ሁኔታ ከነፍስም ከጨለማው ንጉሥ የቃል ኪዳን ውልና ከሌላ ሌላም ነገር ጋር ሊገናኝ ይችላል፡፡ ለምሣሌ አቢይ አህመድ አንድም ቁሣዊ ነገር ሳይቸግረው ነፍሱን ለአጋንንቱ ዓለም አንደዜ ፈርሞ በማስረከቡ ግና ቢሊዮን ዶላር ቢሰጡት አማራን ከመታረድ ሊያድን አይችልም፤ ጓደኞቹም እንደዚሁ - የ“ሙታንሳዎቹ” የነኢዩ ጩፋና እስራኤል ዳንሣ አለቃ ሆኖ ከማስመሰል ባለፈ የእግዚአብሔርን መንገድ ይከተላል ብሎ ማመን የዋህነት ነው፡፡ እርኩስ መንፈስ የተጠናወተው ሰው መልካም ነገር ለማድረግ የሚነሳሳው ያ የሚያደርገው መልካም ነገር ለዓላማው ስኬት አንዳች አስተዋፅዖ ካለው ብቻ ነው፡፡ ትርፍና ኪሣራቸውን አስልተው ነው ሰይጣናውያን ደግ ሰው በዋለበት ሥፍራ የሚውሉት፡፡ ነገሩ የገንዘብ ወይም የመብላት የመጠጣት ጉዳይ ብቻ አይደለም፤ የዓላማ ቁርኝትም እንጂ፡፡

 

        በነፍስ ከቆየሁ ከትንሣኤ ወዲህ ወደዚህ ዓይነቱ የሰለቸኝ መድረክ ባልመጣ ደስ ይለኛል፡፡

 

        እናላችሁ ዓላማ መጥፎም ይሁን ደግ ቀፍዳጅ ነው - የሰይጣንን ቀብድ በልቶ፣ ከሰይጣን ጋር ውል አስሮ በሰላም ተኝቶ ማደር ዕርም ነው፡፡ ወደህና ፈቅደህ የገባህበት ዓላማ በነፍስህም ሊመጣ ይችላልና መውጫው ጭንቅ ነው፡፡ ምናልባት በመጨረሻው አካባቢ ከነቃህና የሠራኸው ግፍና በደል አላስቆም አላስቀምጥ ካለህ ጨርቅህን ጥለህ ልታብድ ወይም ራስህን ልታጠፋ ትችላለህ፡፡ እጅግ በጣም ጥቂቶች ግን በንስሃ ጠበል ታጥበው የበደሉትን የሚክሱበት አጋጣሚ አለ - ልክ እንደፊተኛው ሳዖል (የኋለኛው ጳውሎስ)፡፡ ለበጎም ሆነ ለክፉ ሥራ መመረጥን ይጠይቃል፡፡

 

        የአማራ ጠላቶች አሁን በሙሉ አጋንንታዊ አቅላቸው እየተንቀዠቀዡ ናቸው፡፡ ዘመኑ የመጨረሻቸው መሆኑን ሳይረዱ አልቀሩም፡፡ በአዲሱ አገላለጽ ከውጪም ከውስጥም ሆነው በከፍተኛ መናበብ አማራንና ኢትዮጵያን በነባሩ አነጋገር ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ድባቅ ለመምታት እየተራወጡ ይገኛሉ፡፡ የፌዴራል ተብዬውን የመንግሥት መዋቅሮች ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል ሁኔታ ከላይ እስከታች ተቆጣጥረው ያለ ቆንጣጭ ያለ ገልማጭ ያሻቸውን እያደረጉ ነው - ማግኘት ብርቁ የሆነ ሰው አያግኝ ወገኖቼ - ሰው አያስቀምጥማ! ሌላው ቀርቶ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ወደ ኦሮሚያ ንግድ ባንክ ለመለወጥ በሚያሣዩት ቅጥየለሽ ሩጫ የወጪና ገቢ ቫውቸሮች ላይ የማንንም ቡራኬና ፈቃድ ሳይጠብቁ አማርኛንና እንግሊዝኛን አስከትሎ ኦሮምኛ በላቲን ፊደላት ከፊት እንዲጻፍ አድርገዋል፡፡ ኦሮምኛን ቀርቶ ቻይንኛንና ኩናምኛን ቢጽፉ ለኔ ግድ የለኝም፡፡ የቋንቋ ጠብ የጅሎችና የደደቦች ጠብ መሆኑን ስለምረዳ የኦሮምኛው መጨመር በራሱ ምንም ማለት አይደለም፡፡ ቋንቋ ባለቤት የለውም፡፡ የሁሉም ነው፡፡

 

ችግሩ ሌላ ነው፡፡ ችግሩ ሽመልስና ቡድኑ አማርኛንና አማራን በእግረ መንገድም ኢትዮጵያን በአካልም በመንፈስም በሥነ ልቦናም አጥፍተው ኦሮሙማ የሚሉትን አዲስ ዘይቤ በመትከል ሰማንያውንም ብሔር ብሔረሰብ በአንድ አዳር ኦሮሞ እንዲሆን ካልፈለገም አንገቱ በሜንጫ ተቀልቶ እንዲሞት የሚያደርጉት ሁለገብ ዘመቻ ነው፡፡ በንግግራቸውም በድርጊታቸውም የምናየው ይህንኑ ነው፡፡ ይህ ደግሞ ለቀሪው የኢትዮጵያ ሕዝብ የኅልውና አደጋን ይደቅናል፡፡ በተወደደ የዘመናችን ምድራዊ ዕድሜ ሰማንያው ነገድና ጎሣ በአንድና በሁለት ወር ውስጥ ኦሮምኛን ለምዶ አማርኛን ደግሞ ረጋግጦ ሲጥል ይታያችሁ - ወይ ሞኝነት፡፡

 

     አማርኛን ከአማራ ያለመለየት ድንቁርና መዘዙ ብዙ ነው፡፡ ቀደምት ገዢዎች ከየትም ጎሣ ቢመጡ የሚጠቀሙት የአስተዳደር ቋንቋ አማርኛን ነበር - የቅርቡን ወያኔን ጨምሮ፡፡ ያን ያደርጉት የነበረው የራሳቸውን ልሣን መጠቀም አቅቷቸው ወይም አማራ የተባለው ሕዝብ የርሱን ቋንቋ የጋራ እንዲያደርጉለት ለምኗቸው ሣይሆን ለአገዛዛቸው ከሌሎቹ ይበልጥ ምቹ ሆኖ ስላገኙት ነው፡፡ በዚያም ምክንያት አማርኛ እስከቅርብ ዓመታት ድረስ እጅግ ብዙው የኢትዮጵያ ሕዝብ ይናገረዋል፤ ከኢትዮጵያም ባለፈ አሜሪካንንና ጀርመንን በዋናነት ጨምሮ በሌሎች ሀገራት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት እናያለን፡፡ ይህ ክስተት አክራሪ ኦሮሞዎችን ከማስቀናትና ከማስመቅኘት ይልቅ የራሳቸው ሀብት የሆነውን ይህን ቋንቋ በመግዣ መሣሪያት ቢገለገሉበት የአማርኛ ተናጋሪውን ብቻ ሣይሆን በዚህ ቋንቋ እንደሰምና ፈትል ተዋህዶ ከሚኖረው ቀሪው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር ዕርቅና ስምምነት በፈጠሩ ነበር፡፡ ለዚህ አልታደሉም፡፡

አሁን ሁሉም የአቢይ ልጆች ከፍተኛ ሥራ ላይ ናቸው፡፡ የማነ ንጉሤ የተባለው የአቢይ የጡት ልጅ ሳይቀር ጦርነት በባለ አራትና አምስት ኮከብ ሆቴል እየተንፈላሰሱ በሀገር ሀብት ፒዛ እንደመግመጥና ከቆነጃጅት ጋር እንደመማገጥ መስሎት “ልዩ ኃይላቸውን ከራያና ከወልቃይት ካላስወጡ አማሮችን ለመደምሰስ እኔም እንደሕወሓት በረሃ እገባለሁ!” በማለት ይሄን መከረኛ ጥርሳችንን ሳንወድ በግድ እያስገለፈጠ ነው፡፡ አማራ የፍየል ሥጋ የሆነባቸው አካላትና ግለሰቦች ሁሉ በአሁኑ ወቅት ከምን ጊዜውም በላይ ወብርተዋል፤ ለያዥ  ለገራዥ አስቸግረው ያዙኝ ልቀቁኝ እያሉ ነው፡፡ ታዬ ደንደኣ፣ አዲሱ አረጋ፣ ሕዝቅኤል ጋቢሣ፣ ፀጋየ አራንሣ፣ አሉላ ሶሎሞን፣ … ሁሉም እንደቀትር እባብ እየተቅነዘነዘ ነው፤ የታየው ነገር መኖር አለበት፡፡ አዎ፣ መጽሐፉም እኮ “አፍ ይፀውዖ ለሞት” ይላል፡፡

 

        ለነሱ ባይታይ እኔ እማየውን ልንገራቸው፡፡ ከዚያ በፊት ግን አቢይ አህመድ ጀምበሩ ሳታዘቀዝቅ በተቻለው አቅም ሁሉ አማራን ይጨፍጭፍ፤ ያስጨፍጭፍ፡፡ ጠፍጥፈው የፈጠሩት የቀድሞ ጌቶቹ ለይስሙላ ያቆሙትን ወልጋዳ ህገ መንግሥት ተብዬ ሳይቀር እንዳሻው እየደፈጠጠ ኦሮሙማን በአፋጣኝ ይገንባ፡፡ ወትሮም ልጅ ያቦካው ለእራት አይበቃም - እሱና እሱን መሰሉ ሽመልስ አብዲሣ ገና ንፍጣቸው ሳይደርቅ አባታቸው ሉሲፈር ፈቅዶ በሰጣቸው ሥልጣን ደጋግ አባቶቻቸው ያቆዩዋትን ሀገር ተል ተሎ ብለው ያፍርሱ፡፡ የደቡብ ሱዳን ዜጋ መሆኑ በሚነገርለት በቤንሻንጉሉ የቁጩ ፕሬዝደንት በአሻድሊ አማካይነት በመተከል የሚገኘውን አማራ ይጨርሱ - ከዚያ ሰሞኑን በ“ምን ታመጣላችሁ” የልጆች ዓይነት ብሽሽቅ እንዳሳዩን ኬክ እየቆረሱ ሲፈልጉ በለስላሳ ሳይፈልጉ በሻምፓኝ ይራጩ፤ ኦነግ ሸኔም ያለውዴታው በግድ በሠፈራ ፕሮግራም በደርግ መንግሥት ተወስደው በወለጋና በሌሎች አካባቢዎች የሚኖሩ አማሮችን ቶሎ ቶሎ ይግደል፡፡ ኦነጎችም ይባሉ ኦህዲዶች ጊዜ የላቸውም፡፡ አበቅቴያቸው አልቋል፡፡ ሃሳዩ መሲሕ በእውነተኛው የሕዝብ ልጅ የሚተካበት ወርቃማ ዘመን እየገሰገሰ ነው፡፡

        በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የመሰ(ሸ)ጋችሁ ጳጳሣትና ኤጲስ ቆጶሣት እንዲሁም ምድረ ትብታባም ደባትርና ካህናትም ውስልትናችሁንና ዘሟችነታችሁን በርቱና ቀጥሉ፡፡ የእናንተ ብልግናና የሰይጣን አገልጋይነት ነው ሀገራችንን ለዚህ ያበቃት፡፡ (ቅናት አይደለም - እኔ 33 ዓመታትን ሥራ ላይ ቆይቼ ብስክሊት የለኝም - ዕድሜው 30 ዓመት ያልሞላ የ… ቤ/ክርስቲያን ካህን ግን ቪትዝ አለው - አንድ ወይ ሁለት ብቻ ደግሞ እንዳይመስሉህ፤ ብዙ ጉድ መዘርገፍ እችላለሁ፤ ሕዝቡም ያውቃል) ጥምጥምን ማሳመርና ቃለ እግዚአብሔርን ቀን ከሌት መቀለጽ ብቻውን የትም እንደማያደርስ በተለይ ባለፉት 40 ዓመታት አየነው - ለዕውቀትማ ሊቀ ሣጥናኤልንስ ማን ያማዋል፡፡ በኖኅና በሎጥ ዘመናት የፈጣሪ መቅሰፍት የተላከው ልክ እንዳሁኑ መልካም እረኞች በዓለማዊነት ጠፍተው በጎች በቀበሮና በተኩላ በመበላታቸው እግዚአብሔር ተቆጥቶ ነው፡፡ የአሁኑም ከዚያ የተለዬ አይደለምና ራስህ ፍቅር ሳይኖርህ ዐውደ ምሕረት ላይ ቆመህ “ተአምሁ በበይናቲክሙ…፤ ፍቅርሰ ሰሃቦ ለወልድ ወልድሰ ሰሃቦ ለአብ…” እያልክ ከእዳሪ ለማያልፍ እህል ውኃ ብለህ አንተ እማትተገብረውን ቃለ እግዚአብሔር ካንተው ለማይሻለው ጠፍ ምዕመን የምትሰብክ ወምበዴ ሁላ ቀንህ ቀርቧል፤ ያንተን የተሳሳተ የሕይወት ጎዳና ተመልክቶ ባንተ የተሳሳተ አርአያነት ምክንያት በሰፊው ጎዳና የሚነጉደው “ሕዝበ ክርስቲያን” ወደ አምልኮ ቦታዎች ሄዶ “አንቺ ቅድስት ማርያም፣ የእገሌንና የእገሊትን መጨረሻ እስከዛሬ ወር ካሳየሽኝ አንድ ባኮ ሻማ ስለት አስገባልሻለሁ” እያለ በቀነ ገደብ የተወሰነ “ጸሎት” አድርሶ ሊመጣ የቻለው በእውነተኛ አባቶች መጥፋት ነው፡፡ ይህ አሁን የበሰበሰና የተግማማ የፖለቲካና የሃይማኖት ተቋም ሁሉ በመለኮታዊ ሠይፍ ድራሹ የሚጠፋበት ዘመን እየመጣ ነው፡፡ ዘረኝነት ታሪክ የሚሆንበት ተባራሪና ተሳዳጅ ሀገርን ተረክቦ በፍትኅ የሚያስዳድርበት ጊዜ ከፊት ለፊታችን ተገሽሮ ይታየኛል፡፡ ከተባለው የቀረ የለም፤ ከሚባለውም የሚቀር አይኖርም፡፡ ስብሃት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል፡፡ አሜን፡፡  ma74085@gmail.com

        

Thursday, December 10, 2020

ደስታችን ገደብ ይኑረው፤ ጦርነቱ አሁንም አልተገባደደም! ይነጋል በላቸው Ethiopian Semay

 

ደስታችን ገደብ ይኑረው፤ ጦርነቱ አሁንም አልተገባደደም!

ይነጋል በላቸው

Ethiopian Semay

      ሕወሓትን ማጥፋት እንደዚህ ቀላል የሆነበትን ምክንያት መመርመር አስፈላጊ ነው፡፡ ወያኔ ግማሽ ምዕተ ዓመት ለሚጠጋ ረጂም ዘመን የገነባው የጦር ኃይልና የመሣሪያ ጋጋታ እንዲሁም ምሽግና የመሬት ውስጥ ለውስጥ ዋሻ አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ እንኩቶ የሆነበትን ምክንያት መርምሮ ማወቅ ከተደጋጋሚ ውድቀትና ሽንፈት ይታደጋል፡፡ አሸናፊው እውነትና ወኔ እንዲሁም ጊዜ እንጂ የመሣሪያና የወታደር ብዛት እንዳልሆነ ማወቅ ጠቀሜታው እጅግ የጎላ ነው፡፡ እኔ በበኩሌ እንደ አንድ አንጋፋ ዜጋ የሚሰማኝን ከአሁን በፊትም ሆነ አሁን እናገራለሁ፡፡ እኔና መሰሎቼ ባለፉት 30 ዓመታት ውስጥ አስቀድመን ተናግረን በኋላ ላይ በተግባር የተከሰተውን “የትንቢት” ቃል ሁሉ አንድ በአንድ ከነተጻፈበት ዓመት ለትውስታ ያህል ጊዜው ሲደርስ መዘከራችን አይቀርም - ለዚያ ይበለን፡፡

 

ሰሞነኛ ወሬዎች ብዙ ናቸው - የቱ ተነስቶ የቱ እንደሚጣል ማወቅ እስኪቸግረን ድረስ በሀገራችን ብዙ ነገር በየቀኑ በሚባል ሁኔታ እየተከሰተ አግራሞታችንን ሲያንረው ይታያል፡ ሁሉን መናገር ያስቸግራል፤ ከተለያዩ ምክንያቶች አንጻርም ሁሉንም ነገር ዘርግፎ መናገርም እንደዚሁ አስቸጋሪ ነው፡፡ ግን ሊነገሩ ከሚችሉ ውስጥ አንኳር አንኳሮችን መጥቀስ መጥፎ አይደለም፡፡

ወያኔ በፖለቲካም በጦርነትም ተሸንፏል፡፡ የተሸነፈ ኃይል መንፈራገጡ አይቀርምና በተለያዩ ግልጽና ድብቅ ሥፍራዎች የወያኔው ርዝራዘዦች ለተወሰነ ጊዜ መስዋዕትነትን ማስከፈላቸው አይቀርም፡፡ ወደ ሱዳን የሄደ ኃይላቸውም ከውጪ ጠላቶቻችን ሁሉን አቀፍ የገንዘብና የጦር መሣሪያ ድጋፍና ዕርዳታ በመታገዝ ችግር መፍጠራቸው የሚጠበቅ ነው፡፡ የኢትዮጵያን የማይቀር ትንሣኤ ግን ሊያደናቅፍ የሚችል ምድራዊ ኃይል የለም፡፡ ይህ ተብሎለት ተብሎለት ያለቀ ወርቃማ ዘመን ሊብት መሆኑ ደግሞ በጣም ግልጽ ነው - አንድዬ የተመሰገነ ይሁን ከዋሻው ጫፍ ደርሰናል፡፡ የብርሃን ጭላንጭሉም መታየት ጀምሯል፡፡

 

እነ ታዬ ደንደኣ ቢጠነቀቁ ይሻላቸዋል፡፡ በሽሮና በጎመን ጥጋብ የሚደነፉ ሁሉ አደብ ቢገዙ የራሳቸውን ታሪክ ከማበላሸት ይቆጠባሉ፤ ደግሞም ለማያውቃቸው ይታጠኑ፡፡ በኢትዮጵያ ታሪክ አንዱ ነገድ ተለይቶ አንድን ጦርነት ያሸነፈበት አጋጣሚ አልተመዘገበም፤ ሁሉም በኅብረት ሆኖ ነው የውጪውንም ሆነ የሀገር ውስጡን የከሃዲዎች ጦርነት ድባቅ ሲመታ የኖረው፡፡ ጀግንነትና ፍርሀት ደግሞ ግለሰብኣዊ እንጂ ቡድናዊና ነገዳዊ ወይም ጎሣዊ የኮታ ቅርጫ የለውምና ከዚህ ዓይነት የተሳሳተ ግንዛቤ በአፋጣኝ እንውጣ፡፡ እርግጥ ነው - ብዙ የተበደለና የተገፋ ወገን ብሶት የሚወልደው ብርታትና ኃይል ስለሚኖረው የተለዬ በሚመስል ጀግንነትና ወኔ ጠላቱን የማንበርከክ ልማድ በየትም ሀገር የነበረና ያለ በመሆኑ ይህን እውነት ልብ ማለት ክፋት የለውም፡፡ ለማንኛውም ጎሣና ነገዱ ምንም ይሁን ምን ኢትዮጵዊነትን የያዘ ኃይል አሸናፊ ስለመሆኑ ታሪካችን ኅያው ምሥክር ነውና ወፍ ዘራሾች አንደበታቸውንም ብዕራቸውንም አደብ ቢያስገዙ የመጀመሪያዎቹ ተጠቃሚዎች ራሳቸው ናቸው - ለምሣሌ በሁሉም ተሣትፎ የተሸነፈውን ወያኔ “በኛ የአመራርና የውጊያ ብቃት ነው የተሸነፈው” በሚል ዕብሪት አገር ይያዝልኝ ማለት ትልቅ ነውርና የጮርቃነት ውጤት ነው - የታሪክና የድል ሽሚያ ውስጥ ገብቶ መነታረክ ዓላማን መዘንጋትና ለቀጣይ ወያኔነት ራስን እንደማዘጋጀት የሚቆጠር ግብዝነት ነው፡፡ አክራሪዎች የዱባ ጥጋብ ካለስንቅ ማዘመቱን ተረድተው ረጋ ይበሉ፡፡ ሀብትና ገንዘቡንም፣ ሥልጣኑንም፣ መሬቱንም ... ሁሉንም ጠቅልለው መያዛቸውን ይግፉበት (መቼስ ማልጎደኔ!) - እንደወያኔ ግን ግድያና እሥሩን ይተውት፤ በፍጹም አይጠቅማቸውም፡፡ አላበሳቸው ያሰሯቸውን የኅሊና እስረኞችም በአስቸኳይ ይፍቱ - ዕድሜያቸውን ክፉኛ የሚያሳጥር ጽላሎት በዲያቢሎሣዊው አክሊላቸው ላይ ወድቆ ይታየኛልና ንጹሓንን ማሰርና መግደል እንደማይጠቅማቸው የምትቀርቧቸው ምከሯቸው፡፡ ወያኔን መኮረጅ የተማሪውን ደብተር ስታበላሽ የነበረችውንና ተማሪው በደንደሱ በኩል አንገቱን ገዝግዞ ያስቀመጠውን ቢላዎ አንስታ በስለቱ በኩል ማንቁርቷን በጥሳ እራሷን እንደገደለችው ሞኝ ጦጣ መሆን ነው፡፡ ዛሬ ቤተ መንግሥቱ በኦነግ/ኦህዲድ ቁጥጥር ሥር ሆኖ አክራሪ ኦሮሞ በኦነጋዊ የኬኛ ፖለቲካው ቢፈነጭበትም ይህ ሁኔታ እንዳለ ይቀጥላል ማለት እንዳልሆነ ግልጽ ሊሆን ይገባል - ተጠየቁ እኮ ቀላል ነው፡- የደርግን መጨረሻ ማስታወስ ነው፤ የወያኔን መጨረሻ ማየት ነው፤ በሌሎች የዓለም ሀገራት ያሉና የነበሩ አምባገነኖችን የመጨረሻ ዕጣ ፋንታ ማስታወስ ነው - የኅዋ ሣይንስ ምርምርን የሚጠይቅ አይደለም ነገሩ፡፡ ከዚህ ከዚህ አለመማር ድፍን ቅልነት ነው፡፡

 

የሆድ ዘመን እየጨለመበት፣ የኅሊና ዘመን እየፈካና እየጎመራ የሚሄድበት ወቅት ላይ ነን፡፡ ሆድ ውስጥ ወርዶ የተሸጎጠው ኅሊና ወደመደበኛ ሥፍራው ወደ ጭንቅላት መውጣቱ የጊዜ ጉዳይ እንጂ መቼም ቢሆን አይቀርም፡፡ ከሁኔታዎች መገንዘብ እንደምንችለው ይህ የማይቀር ሂደት የጀመረም ይመስላል፡፡ አሽከር ሲያመር ገድሎ ይጠፋል፤ ውሻ ሆድ ብሶት ጌታውን ሲከዳ ቢችል ጌታውን ነክሶ ከግቢ ይጠፋል፡፡ በቅሎ ሲመራት ጌታዋን ጥላ በእግሯ ትረመርመውና ትገድለዋለች፤ ሆድ ለኅሊና ቦታውን የሚለቅበት ጊዜ አለ፤ አዲስ ነገር እየተናገርኩ አይደለም፡፡ እናም መቀናጆውን ብአዴንን የከዳው ኦህዲድ ጌታውንና ጓደኛውን እንደከዳ ሁሉ ሌላ ታሪክ ሊፈጠር እንደሚችልም መዘንጋት አይገባም፡፡ ጊዜ መስታወት ነው፤ ገና ብዙ ነገር እናያለን፡፡

 

ስለዚህ በተረኝነት ስካር የምትናውዙ አክራሪ ኦሮሞዎች ይህን አቅለቢስ መንታላ(busiest) ልጅ እየተጠቀማችሁ ሕዝብን ከሕዝብ ለማናከስ አትፍጨርጨሩ፤ ልጁ እርግጥ ነው ላይ ላዩን ሲታይ ደህና ይመስላል፤ በዚህም ሳቢያ “የተመረጡትን” ሳይቀር አነሁልሏል - ውስጡ ግን ልዝብ ሰይጣን መሆኑ በጓደኞቹ ማንነት መታወቁ አልቀረም (የሽመልስ አብዲሣ የዓላማና የፍላጎት ባልደረባ ሆኖ ኢትዮጵያን ይወዳል ቢባል በትንሹ ድንቁርና ነው፤ ብዙዎችን በፍቅሩ የሚያጃጅልበት አንዳች ምትሃታዊ ነገር ሳይኖረው አይቀርም (ይባልማል))፡፡

 

ለማንኛውም የአሁን ተረኞች ሆይ! ኢትዮጵያ የትግሬ፣ የኦሮሞና የአማራ ብቻ እንዳልሆነች ወዳችሁ ሣይሆን ተገዳችሁ በቅርብ የምትረዱበት ጊዜ ይመጣል፡፡ ከአንድ ሚሊዮን ያላነሰ ሥልጡን ጦርና ለብዙዎች ዓመታት የሚያዋጋ ስንቅና ትጥቅ እንዳለው የሚገመተው ሕወሓት በቀናት ፍልሚያ የማሽላ እንጀራ ሆኖ መፍረክረኩ ልቦና ላለው ሰው ትልቅ ትምህርት በሆነው ነበር፡፡ ግን ትዕቢትና ዕብሪት ሁለመናን ያሣውራሉና ብዙዎች ማሰቢያቸውን  ላልባሌ ፍላጎታቸው አዋሉት፡፡ በዚያም ምክንያት ይሄውና አቢይን የተማመነው አክራሪ የኦሮሞ ኃይል በቤንሻንጉልና በሌሎች በርካታ አካባቢዎች አማራን ማረዱን ቀጥሏል፡፡ በተለይ ሽመልስ አብዲሣ የተባለው ፀረ-አማራ ግለሰብ አማራን ያሳረደውን የቤንሻንጉል ጉሙዝ ፕሬዝደንት ጠርቶ ኬክ ሲያስቆርስ ማየት የዘመኑ ታላቅ የትራጂ-ኮሜዲ ተውኔት ነው፡፡ ይህ እየሆነ ያለው ደግሞ በአቢይ አስተዳደር ሥር ነው፡፡ የአቢይንና እርሱ የሚወክለውን የኦነግ/ኦህዲድን መሠረታዊ ፍላጎትና ዓላማ ቁልጭ አድርጎ የሚያሣይ ድርጊት ነው ይህ በዚህ ኅብረትንና አንድነትን በሚሻ አደገኛ ወቅት በድፍረት የተከናወነ የኬክ ቆረሣ ድራማ፡፡  ያሳዝናል፡፡ አማራ ብዙ የቤት ሥራ እንዳለበት አመላካች የሆኑ ወቅታዊ ሁኔታዎችን መርሣት ብዙ ዋጋ እንደሚያስከፍል መረዳት ተገቢ ነው፡፡ ጥጋብ መጥፎ መሆኑን አሁን ይበልጥ ተረዳሁ፡፡ ጥጋብ ጊዜን አይመርጥም፤ ጥጋብ ዐይንንና ጆሮን ይጋርዳል፡፡ ጥጋብ ልብን ይደፍናል፡፡ “ከተራበ ለጠገበ አዝናለሁ” መባሉም ለዚህ መሆን አለበት፡፡

ጦርነቱ እንደተጀመረ እንጂ እንዳላለቀ በርዕሴ ጠቁሜያለሁ፡፡ አዎ፣ ከወያኔ ጋር የተጀመረው ጦርነት ገና ተጀመረ እንጂ አላለቀም፡፡ የወያኔ አባላት የሆኑ ሁሉ “ምነው ወያኔ አርገህ ፈጠርከኝ!” በሚል ፈጣሪያቸውን በጠማማ አንጎላቸው ፊት የሚከሱበት ዘመን በቅርብ ይመጣል፡፡ ወያኔዎች የሠሩት ግፍና በደል እንዲህ በቀላሉ ታጥቦ የሚጸዳ አይደለምና ብዙ የደም ጎርፍ ይጠብቀናል፡፡ በቀላል ደስታ ተውጠው በትናንሽ ድሎች ጥይታቸውንና ደስታቸውን የሚያባክኑ አማሮችን ሃይ እንድትሏቸው በዚህ አጋጣሚ አደራ ማለት እፈልጋለሁ፡፡ ደስታን አላግባብ መደሰት ዋጋ እያስከፈለ እንደሆነም እየሰማን ነው፡፡ ዒላማውን የሳተ ጥይት ሰውን እየገደለ፣ በመቶዎች ብር የሚገዛ ጥይትም አለመላው እየከሰረ እንደሆነ ይነገራልና በዚህ ጉዳይ ዙሪያ ጥንቃቄ ይደረግ፡፡ ዘመድኩን በቀለን የምታገኙ ሰዎች ይህን መልእክቴን እባካችሁን ለርሱ አድርሱልኝ፡፡

 

በፌዴራል ተብዬው መንግሥት ውስጥ ያላችሁ አፋዳሾችና አክቲቪስት ነን ባዮች ሁላ ወደየኅሊናችሁ ተመለሱ፡፡ ደግሞም አታስቁን፡፡ ቢቻል በምናምን እየመረቀናችሁ የሚሰጣችሁን ሁሉ በሚዲያችሁ አታውጡ፡፡ ሆዳምነታችሁንና ቅጥረኝነታችሁን ከማጋለጡም በተጨማሪ አመኔታን ያሳጣችኋል፡፡ “ሳያጣሩ ወሬ፣ ሳይገድሉ ጎፈሬ” ይባላልና እባካችሁ ለማጣራት ሞክሩ፡፡ ሰሞኑን ከታዘብኩት አስቂኝ መረጃ አንደኛው ለምሣሌ ወያኔዎች ለነኢትዮ360 እና ርዕዮት ሚዲያ በየወሩ ብዙ ዶላር እንደሚከፍሉ የወጣው መሠረተ ቢስ መረጃ ነው፡፡ የሀሰት ፍብረካ ልክ ሊኖረው ይገባል፤ አለዚያ ከፍ ሲል እንደጠቀስኩት አመኔታን ለሚያሳጣ ቋሚ ትዝብት ይዳርጋል፡፡

 

እውነት ነው - በነዚህ ሚዲያዎች የሚሠሩ ሰዎች ሰው ናቸውና ሊሳሳቱ ይችላሉ፤ ማንም ፍጹም የለምና፡፡ ሽህ ጊዜ ቢሳሳቱ ግን ለነዚህ ሚዲያዎችና ግለሰቦች ወያኔ ቀለብ ይሠፍርላቸዋል ብሎ መዘገብ ሕዝብን መናቅ ነው - አንድ ሰው ካላበደ በቀር በቦምብ ለሚያደባየው ሰው ቀለብ አይቆርጥም፡፡ እንደዚህ ያሉ ማጅራት መቺዎች ያሉበት መንግሥት ደግሞ እንኳንስ ሀገርንና ሕዝብን ሊያሻግሩ ይቅርና እነሱም ከወያኔ የማይሻሉ ተራ አሉቧልተኞችና ሲመቻቸውም ነፍሰ ገዳዮች ናቸው - እያደረጉ ያሉትም ይህንኑ ነው፡፡ ንጹሓንን የሚያስርና የሚገድል “አሻጋሪ” የሰበሰባቸው አክቲቪስቶች ብዙ ተዓምር እያሳዩን ነው፡፡ ነገሩ ያለቃ ገ/ሃናን ተረት ያስታውሳል፡- በቤታቸው ያንገሸገሻቸውን የጎመን ይሁን የሽሮ ወጥ ጠልተው ወደጓደኛቸው ቤት ቢሄዱ እዚያም ተመሳሳይ ወጥ ጠበቃቸውና “በየት ዞረህ ቀደምኝ” አሉ ይባላል፡፡ የአቢይ አካሄድ የገጸ ባሕርያት ወይ የባለታሪኮች ለውጥ እንጂ የድርጊት ለውጥ የለውም፡፡

 

ለማንኛውም በአሁኑ ወቅት ከነስህተታቸውም ቢሆን ለኢትዮጵያ ከቆሙ የግል ሚዲያዎች መካከል አንዱ ኢትዮ360 መሆኑን በዚህ አጋጣሚ ባልመሰክር እኔም ወያኔ ማነው ኦነግ/ኦህዲድ መሆኔ ነውና ይሄውና መሰከርኩ - መረጃ ቲቪንም ጨምሩልኝ፡፡ ግን ግን በጥሩ ሥራ መኩራት እንዳለ ሁሉ በስህተትም መጸጸትንና ይቅርታን መጠየቅን ማወቅ፣ በከንቱ መታበይንም ማራቅ መልካም መሆኑን በዚህ አጋጣሚ ማስታወስ እፈልጋለሁ፡፡ ትኅትናን እንላበስ፤ መታበይን እንናቅ፡፡ ከከንቱ ውዳሤ ራሳችንን እናርቅ፡፡ የሰይጣን መግቢያ ቀዳዳዎችን ሁሉ በተቻለን መጠን እንድፈን፡፡

 በመጨረሻም ፈጣሪ ሳይደግስ አይጣላምና መምህር ዘመድኩን በቀለንና ስማቸውንና ግብራቸውን  እዚህ ዘርዝሬ የማልጨርሰው ወገኖቼን በዚህን ክፉ ዘመን እውነቱን ይዘው እንዲሟገቱና ለተገፉ ብዙኃን አለኝታ ሆነው ሌት ተቀን እንዲደክሙልን እግዚአብሔር ስለሰጠን ስሙ ለዘላለም የተመሰገነ ይሁን፡፡ ይህ ብላቴና በትናንትናው የኅዳር 30 ቀን 2013 ዓ.ም የመረጃ ቲቪ ዝግጅቱ ላይ ያቀረበውን ሃተታ ማዳመጥ እጅግ ጠቃሚ ነውና እባካችሁን ጎብኙት፡፡ ዘመዴን መሰሎችን ያብዛልን፡፡ ጠላቶቻችን ምንም ዓይነት ይሉኝታና ሀፍረት የሌላቸው የፍየል ዐይን በጨው ቀቅለው የበሉ እንደመሆናቸው እነሱን ለመታገል አንዳችም ዳተኝነትና ይሉኝታ እንደማያስፈልግ ከዘመዴ መማር ይቻላልና እግዚአብሔር አብዝቶ ይባርከው፤ ልጅም ይውጣለት፡፡ ዜጋ ማለት እንዲህ ነው፡፡ መጥምቁ ዮሐንስ በበረሃ አንበጣ እየበላ የመንግሥተ ሰማይን መቅረብ ይሰብክ ነበር ...

መልካም ዘመን ለሀገራችን!

Tuesday, December 8, 2020

የአሉላ ሰለሞን የጥላቻ አዋጅ እና ምላስ ብቻ የሆነው ተግባረቢሱ የኢትዮጵያ ማሕበረሰብ! ከትግርኛ ወደ አማርኛ ትርጉም ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay) ትርጉም Sunday, December 06, 2020

 

የአሉላ ሰለሞን የጥላቻ አዋጅ እና ምላስ ብቻ የሆነው ተግባረቢሱ የኢትዮጵያ ማሕበረሰብ! 

ከትግርኛ ወደ አማርኛ ትርጉም ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)

ትርጉም Sunday, December 06, 2020

ወደድንም ጠላንም “ኤርትራኖችና ትግሬዎች” ለሚያምኑበት በጽናት የመቆማቸው ባሕሪ ማድነቅ እንጂ ማናናቅ አይቻልም። በአንጻሩ  ይህ ትርጉም ተርጉሜ ሳቀርብ፤ ደደቡ ውጭ አገር የኢትዮጵያ ማሕበረሰብ (በተለይ የንግድ ባለቤቶችም ሆኑ አማራዎች)  በአሉላ ሰለሞን የተነገረው መርዛማ ንግግር ምንም እርምጃም ሆነ ስሜት እንደማይሰማቸው አውቃለሁ። ለታሪክ እንዲቀረጽ ግን ተርጉሜ አቅርቤዋለሁ።

 

“በትግራይ ሚዲያ ሃውስ”  የተላለፈው ማሕበረሰብንና አገርን የማፍረስ እንዲሁም ጋብቻ በዘርና በፖቲካ ከ የመከፋፈል ቅስቀሳ ሲያስተላልፍ ልክ ሩዋንዳው ውስጥ ፖለቲካን ተንተርሶ “ሁቱ እና ቱትሲ” ለፍጅትና ለትዳር ፍቺ ይቀስቅስ የነበረው “radio Mille Collines”  “አሉላ ሰለሞንና የትግራይ ሚዲያ ሃውስ” ባልተናነሰ ቅስቀሳ ሲያውጅ፤ ከላይ የጠቀስኳቸው ማሕበረስቦችና ንግድ ቤቶች በላያቸው ላይ የተላለፈው የጥላቻ ቅስቀሳ ምንም እንደማይሰማቸውና አውቃለሁ።  የማንበብና የተተረጎመውንም ለሕዝብ እንዲዳረስ እንኳ የማድረግ ፍላጎት እንደሌላቸው ከፌስቡክ ገጾች ማየት ትችለላችሁ።  ድክመታችሁ እስከዚህ ጥግ ይደርሳል።

ወያኔዎች የኛን የኢትዮጵያዊያን በተለይም የአማራውና በተለይ የነጋዴው ማሕበረስብ “ልፍስፍስነት” እና ደደብነት ለ30 አመት ስለሚያውቁት፤ የፈለጉት ቢናገሩ ምንም እንደማይሆኑ አውቀዋልና ፤ አሉላ የፈለገው የጥላቻና አገር የማፍረስ ቅስቀሳ በኩራት በድፍረት እና በሃይለቃል አስተላልፏል ። እኛ ወደ ቁልቁል ስንወርድ እነሱ ወደሽቅብ ሲሄዱበት የነበረበት የ30 አመቱ ጉዞ ምስጢሩ ፤ለሚያምኑበት ተሎ “ሪኣክት” በማድረግ አቋም ይወስዳሉ። ትግራዋይነት ብለው በኩራት የሚናገሩበት አቋምም ይህ ነው። እኛ ኢትዮጵያዊያን ግን በተለይ አማራዎችና የንግድ ባለሃብቶች “ከምላስ” በስተቀር ቢሰደቡም ፤ቢዋረዱም ደንታ እንደማይሰጣቸው ለ30 አመት አይቻለሁ፡ ዛሬም ያው ናቸው።  አመማችሁ አይደል? እንዲሰማችሁ ነው እየጻፍኩ ያለሁት!! ከአሉላ ሰለሞን ምላስ ይልቅ የኔ ከተሰማችሁ ምንም ማድረግ አይቻልም። አሁን ወደ አሉላ ሰለሞን አማርኛውን  አስተካክየ የተረጎመኩትን ንግግሩ ይኼው። ትከክለኛ ቅጂው ኢትዮጵያን ሰማይ አሁን ተለጥፏል። ለፌስቡክ አንባቢም እነሆ።

ከትግርኛ ወደ አማርኛ ትርጉም ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)

ትርጉም Sunday, December 06, 2020

ብዙ ሰዎች ከተረጎምኩት የማይረቡ ነጥቦችን እየቀነጫጨቡ በየፌስቡክ ሲለጥፉ በማየቴ አንባቢዎች ሙሉውን ትርጉምና ይዘት ለማየት እዚህ ኢትዮጵያን ሰማይ ላይ ተለጥፏል ይኼው።

 

የአሉላ ሰለሞን የጥላቻ አዋጅ የተላለፈበት ቴ/ቪዥን  Tigrai Media House

 

ቀን 12-05 20 

 

ቃለመጠይቅ አቅራቢ አቶ ሃይለ - የTigrai Media House መድረክ አዘጋጅ)

 

 የመድረኩ ተሳታፊ - አሉላ ሰለሞን፡ (የሚዲያ ሃውስ ዋና ሥራ አስክያጅ)

 የውይይቱ አርዕሰት ትግራይ - ዛጊድ ዝተረኸቡ ዓወታት ምዕቃብ 12/05/2020(ትግራይ  ውስጥ እስካሁን ድረስ የተገኙ ድሎች ስለ መጠበቅ 12/05/2020)                                       

ፌስቡኩ ላይ ተያያዥ ሆኖ የተለጠፈው ሌላ ርዕስም  በትግራይ ህዝብ ላይ የቀጠለው የዘር ማጥፋት ዘመቻ 12-05 20” የሚል ይነበባል።  https://youtu.be/uFyMwSg_MM0

የቃለመጠይቁ ምንጭ ከታች የተለጠፈው የፌስቡክ ድረገጽ፡

https://www.facebook.com/tmhtv/videos/400078718098046

ትግራይ - ዛጊድ ዝተረኸቡ ዓወታት ምዕቃብ 12/05/2020(ትግራይ ውስጥ እስካሁን ድረስ ስለ ተገኙ ድሎች መጠበቅ 12/05/2020

ከቃለ መጠይቁ የተወሰዱ ፍሬ ነገሮች፡ ከትግርኛ ወደ አማርኛ እንደሚከተለው ተርጉሜዋለሁ።

ማሳሰቢያ

አቶ አሉላ ሰለሞን እነዚህን በሚመለከት በጽሑፍ ካሁን በፊት ማቅረቡን እራሱ ይናገራል። ጽሑፉ የት እንደለጠፈው አላየሁትም። ሆኖም በራሱ ፌስቡክ ወይንም በሚዲያ ተለጥፎ ከነበር ለወደፊቱ እፈልገዋለሁ። እስከዛው ግን ተጨማሪ ብሎ ያቀረበው የቃለ መጠይቁ ይዘት እነሆ እንዲህ ይላል።

1-ሃይማኖትን በሚመለከት፡

ትግሬዎች ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ፤ ከኢትዮጵያ ካቶሎክ፤ ከኢትዮጵያ ፕሮተስታንት ቤተጸሎቶች እንዳይጽልዩ !! እራሳቸው ከነዚህ ተቋማት እንዲያገልሉ በጽሑፍ ካሁን በፊት አቅርቤአለሁ፤ ዛሬም ይህንኑ ጥሪ አቀርባለሁ። በተለይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርሰትያን መደረማመስ አለባት (ትግርኛው “ዱዋዕዋዕ ክትብል አለዋ”)። ትግራዋይ ሁሉ አቅምህና ንብረትህ ትግሬዎች በሚመሰርትዋቸው ተቋማት እና በትግራይ ብቻ እንድታውለው ይሁን። therefore (ዘርፎር) የኢትዮጵያ ቤተክርስትያን ከምትባል እራስህን አርቅ። የትግራዋይ ቤተክርስትያን እንጂ ኢትዮጵያ የምትባል ጠላታችን ስለሆነች መጠሪያችን “የትግራይ ተዋህዶ፤ የትግራይ ካቶሊክ፤ የትግራይ የፕሮተስታንት ቤተክርስትያን ፤የትግራይ ኢቫንጀሊካል ቤተክርስትያን ተብለው እንዲሰየሙ ማድረግ አለበን” (period! ፒሪየድ!)። እስላም ከሆንክም “የትግራይ ምስልምና” ብላችሁ  መስርቱ።

 የትግራይ ሕዝብ ሆይ! እነዚህ ፈጽመው አይፈልጉህም። በተጠቀሱት እምነቶች በትግሬነታቸው ችግር አይታይባቸውም። ችግሩ ያለው በዋናነት ኦርቶዶክስ ላይ ነው። ዋሻ ነው። ያ ዋሻ መፍረስ አለበት!!

ካሁን በፊት ቀደም ብለው ይህንን እንደሚመጣ ቀደም ብለው  ያወቁ አስተዋይ ትግሬዎች የትግሬዎች ቤተክርስትያን መስረት ስለነበር አሁን ከዚች ከዳተኛ ከሆነቺው የኢትዮጵያ ተዋህዶ ቤተክርስትያን እራሰክን አግልል። ቄሶች ድያቆናት ጳጳሳት የሆናችሁ ትግሬዎች ሁሉ ከዚያ ውጡ! ወጥታችሁ የትግራዋይ ቤተክርስትያን መስርታችሁ ትግሬዎችን  ብቻ አገልግሉ።

2- “ቢዝነስ” በሚመለከት የሚከተለው ጥሪ አቀርባለሁ፤

የእንጀራ ቤቶች፤ ምግብ ቤቶች የሥጋ ቤቶች በጠቅላላ የኢትዮጵያዊያን ንግድ ተቋማት በሚባሉት ሁሉም ቦታ  ግብይት እንዳታደርጉ!! በገንዘብ እቅማቸውን ማጠናከር ብቻ ሳይሆን መርዝ አስገብተው እንዳይፈጅዋችሁ። ይፈጅዋችሗልም። እነዚህ ጨካኞች ናቸው!! ብምትመገቡዋቸው ምግቦች ውስጥ መርዝ አስገብተው እንዳይፈጅዋችሁ ተጠንቀቁ። በመርዝ ተመርዛችሁ ከመሞት ለመዳን ከፈለጋችሁ መፍትሄው ትግሬዎች፤ ኤርትራኖች እና በአካባቢያችሁ ባሉት የኦሮሞ ንግድ ቤቶች/ቢዝነስ/ ካሉ ከነሱ ጋር ተገበያዩ። በተለይ ደግሞ ያቺ ልሙጥ ባንዴራ የሰቀሉ ወይንም በንግድ ቤቶቻቸው ውስጥ ካያችሁ እንዳትገበያዩ ሌላ ቀርቶ ቅመምም ጭምር እንዳትገዙ።

በኢትዮጵያ የሚጠራ ወይንም ኢትዮጵያ የሚባል ስም ያለባቸው ማሕበራት እንዳትገቡ። መረዳጃ ማሕበር ይሁን ምንም ይሁን “ኢትዮጵያ” የሚል ካለበት ከነዚህ ማሕበረሰቦች ጋር እንዳትቀላቀሉ። በሙሉ አግልሏቸው። ገንዘባችሀ በትግሬዎች ብቻ “Spend” አድርጉ። አንዳንዱ “አሉላ ሰለሞን” “ራዲካል” ሆነ ምናምን ሊሉዋችሁ ይችላሉ። ኖ! እስኪያማቸው ድረስ መነገር አለበት። ማወቅ አለባቸው። ኢትዮጵያዊያን ትግሬዎችን አይወዱህም እና ባጭሩ ከነሱ እራስክን ነጥል።

3- የእግዚአብሔር ሰላምታን በሚመለከት።

አማራዎች “ወንድሞቼ ሰላም እንባባል እንጂ ወንድማማቾች እኮ ነን  ምናምን ብለው “ሰላም” ቢሏችሁ ሰላም እንዳትሏቸው። ከአማር ጋር ጭራሽ እንዳታነጋግሩዋቸው! አማራ የሚባል “ሱፐር ማርኬት፤ ሞል ፤ ሌላም ሌላ ቦታ ስታገኝዋቸው ሰላም አትበሏቸው። ወዳጅነት ኖሯችሁ፤  አብራችሁ ስተበሉ ስትጠጡ የነበራችሁ ሁሉ “አቁሙ!” ጦርነቱ ሳይደግፍ “ሳይለንት”  (ዝም ካለም) ፤ አማራም ቢሆን ተባባሪ ነውና  አቁም! የትግራይ ሕዝብ ሲበደል አሳዝኖኛል ስትል ስላልሰማሁህ ጠላት ነህ ብላችሁ መልሱለት። ወዳጅነታችሁን አብሮ መብላት መጠጣትን አቁሙ። ስለትግራይ መበደል ምንም ያልተነፈሰ ሰው “ከዚህ ሰው ጋር በጋራ አብራችሁ “እንጀራ በሳህን” የምትበሉ የምትጠጡ ከሆነ ያ የምትመገቡት ምግብ ጸር ሆኖ ይገላችሗል። የምትጠጡትም የወንድሞቻችሁ ደም ማለት ነው። ስለዚህ በተለምዶ ተዋልደናል ትዳር መስርተናል ምናምን የሚባል ዝበዝንኬ ዛሬ አይሰራም።

ትዳር መስርታችሁ ከሆነ ወይንም ወልዳችሁ ከሆነ ወላጀቻቸው ናቸው በቦምብ ሕዝብን እየጨረሱ ያሉት። ስለዚህ አንድ ሰው ከትግሬ ጋር ተጋብቶ ትዳር መስርቶ ወልዶ ከብዶ ከሆነ ወይንም ከትግሬ ጋር ፍቅር ይዞት ከሆነ  የመጀመሪያ “requirement ሪኳየርመንት” መሆን ያለባት “በትግራዋይ ላይ የታወጀው ጦርነት ማውገዝ መቻል አለበት” ይህ ሰው ከትግሬ ሴት ጋር ለመጋባት ኳሊፋይ ለመሆን ሪኳየርመንቱ ይህ መሆን አለበት። አንድ ሰው ከትግሬ ሴት ጋር ወይንም ከትግሬ ወንድ ጋር ለመዳር ከፈለገ ወይንም ከፈለገች “በችግራችን ወቅት ከትግራይ ሕዝብ ጋር እቆማለሁ የሚል ወይንም የምትል መሆን አለባት። መመዘኛው ይህ መሆን አለበት። ካልሆነ ግን “ኢትዮጵያ” ምናምን የምትል ከሆነ “ዞር በይ! ብላችሁ አባርሯት”!!

4- ኢትዮጵያ ምናምን እያለች እራስዋን በኢትዮጵያ የምትሸሽግ ከሆነ

-ወዲያ በሏት! ከቤታችሁ አባርሯት ወይንም አባርሩት፤

-ግንኙነታችሁ በጣጥሱት!!

-ጓደኝነት ከሆነም (ወዳጅነታችሁን) በጣጥሱት

-ትዳር ከሆነ አፍርሱት፤ ማሕበራዊ ግንኙት ከሆነ በሙሉ በጣጥሳችሁ ወደ ቆሻሻ መጣያ  ጣሉት!

 -ባጭሩ እንዲሰማቸው ማሳየት አለባችሁ!

Life ለኛ መራራ ሆና ለሌላኛው መጣፈጥ የለባትም። ባጭሩ ህይወት ማለት “ትግራዋይ” ሳይጥማት ሌላው ተመችቶች እያጣጣመ እንደማይኖር ማሳየት አለባችሁ። ይህ ከየት ይጀምራል ብትሉኝ። መጀመሪያ ከቤተሰብ መጀመር አለበት። ቤተሰቦቼ እየተጨፈጨፉ እየተሰደዱ እኔ ከነዚህ ለመሰደዳቸው ምክንያት ከሆኑት ጋር ቁጭ ብየ ከበላሁ ከጠጣሁ ማፈር አለብኝ። ስለዚህ ለጠየቅከኝ ጥያቄ “ድል በድል ሆነናል” የምለው ምክንያት “ትግራዋይ ሁሉ በጠቅላላ ይንን ተግባራዊ እያደረገ መሆኑን ስለማውቅነው፤ በዚህ በኩል ነው ስኬታማ ነን የምለው”። በማለት

5- በመጨረሻም  ማንኛውም ትግራዋይ በኢትዮጵያ አየር መንገድ  እንዳይጓዝና  ቦይኮት ማድረግ እና በንግዱ በኩል የነበረው ገቢ ዓለም እንዲጠየፈው በማድረግ እንክትክት እስኪል ድረስ ዘመቻ ማድረግ አለብን።

በማት የቃለመጠይቁ አዋጅ በዚህ ይደመድማል።

ትርጉም ጌታቸው ረዳ ((Ethiopian Semay) Sunday, December 06, 2020

 


Sunday, December 6, 2020

አብይ አሕመድ እና የወያኔ መሪዎች የአፓርታይድ ስርዓት ለማስቀጥል በውጭ አገሮች የተቀጠሩ ሰላዮች ናቸው! ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay) December 6/ 2020

 

አብይ አሕመድ እና የወያኔ መሪዎች የአፓርታይድ ስርዓት ለማስቀጥል በውጭ አገሮች የተቀጠሩ ሰላዮች ናቸው!

ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)

December 6/ 2020

በመጀሚያ ይህንን ልበልና ወደ ርዕሴ ልግባ። እብሪተኛው ፋሺታዊው ወያኔ በጫረው እሳት እራሱን አቃጥሎ እንደ ዝንጀሮ በፈርሃት ቆፈን ዋሻ ለዋሻ ተደብቆ እየተመታ ተበታትኖ ሲሸሽ ማየቴ ደስታየ ወደር የለውም። እራሱ በለኮሰው እሳት ለመቃጠሉ ተጠያቂው እራሱ እንጂ ማንም እንዳልሆነ ብቀብልም፤ እዚህ ድረስ ጠግቦ ብዙ ኪሳራ እስኪያመጣ ድረስ የታገሰው ልፍስፍሱ አብይ አሕመድም እንደ መንግሥት መሪ ሆኖ ባለመገኘቱ ለኪሳራው ተጠያቂ ነው። ይህ ካልኩ ዘንድ ወደ ርዕሴ ልግባ።

አሜሪካኖችና ሶቭየቶች እንዲሁም ቻይናዎች ዓለምን ለመግዛት ባላቸው ጉልበትና ፍልስፍና በቀጥታም በተዘዋዋሪም ሲፋለሙ፤ ይህ ተፋላሚ ሃይል በውስጥ ከቀጠርዋቸው ሰላዮቻቸው በኩል በ1960ዎቹ ወደ አገራችን በመግባት እንደተቀረው ኢትዮጵያን በምስራቅ እና በምዕራብ ፍልስፍና ተወጥራ እንደ ወተት ስትናጥ የኛ ሊህቅ ተማሪዎች መሪ ተዋናዮች ነበሩ። ከተዋናዮቹ መካከል የዛሬዎቹ የዳግማይ ወያኔ መሪዎች አንደኞቹ ነበሩ። በሚቀፍፍ ሁኔታ ኢሕአፓም፤ መኢሶን፤ ወያኔም፤ ሻዕቢያም ከውጭም ከውስጥም ሆነው በተሰበኩበትና ባነበቡት የባእድ ፍልስፍናዎች ፍቅር ተጠምደው የአገራችን ‘ባሕልና ወግ’ በማፍረስ በአፍሪካ ውስጥ በጣም አጥፊ ተግባራት በመፈጸም አገራችን አሁን ላለችው ክስተት ዳረግዋት።

በዓለም ላይ ሁሉ ፣ በምስራቅም በሰሜንም በደቡብም፣ያደገም፤ያላደገም አገር ሁሉ አሜሪካኖች በሚመሩት ዓለም አቀፍ የባንክ እና የስለላ ኮርፖሬሽን በተዘረጋው አዲስ አብዮት (ኒው ወርልድ ኦርደር) ምክንያት ‘ሶቭየት ሕብረት’ ብትንትንዋ እንድትወጣ በማድረግ የአሜሪካ የኮርፖሬት ካፒታሊዝም የበላይነቱን ተቀዳጀ፡፡ በዚህ መልክ አጋጣሚውን በመጠቀም የኮርፖሬት ካፒታሊዝም የበላይነቱን ሲይዝ በአፍሪካ ውስጥ በጣም አጥፊ ተጽዕኖዎችን ማድረግ ጀመረ። ዓለም አቀፍ ካፒታሊዝም “የአፍሪካን ዳግም ቅኝ ግዛት” በመባል በሚታወቀው በቀጥታም ሆነ በእጅ አዙር የጀመረው በሌሎች አፍሪካ አገሮች ቢሆንም አገር በሚያፈርስ መልኩ ዘመናዊ ባሮችን በመግዛትና በማዟዟር እንዲሁም ሕዝባችን በጎሳ እንዲሸነሽን በመርዳት ኢትዮጵያ ውስጥ የተለየ መሰሪ ተከትሏል።

 

እ.ኤ.አ. ከ 1990 ዎቹ መጀመሪያ ጀምሮ አፍሪካዊው ማንነት እየተደመሰሰ በተለይም በኢትዮጵያ በምዕራባዊያን የባህል ወረራ መስፋፋትን ቀዳሚ ስፍራ መያዝዋን ሁላችሁም የምታውቁት ነው። ወያኔዎች በእነ ፖል ሔንዝ እና በእነ ሐርማን ኮኸን ተደግፈው ኢትዮጵያን ተቆጣጠሩ። ኤርትራም እንዲሁ በ ሲ አይ ኤው ምልምል በኢሳያስ መሪነት “ባሕረ ነጋሽ” ተገነጠለች። በመላ አፍሪካ እርስ በርስ የመዋጋት ባሕል ተከሰተ። ዛየር ፣ ሴራሊዮን ፣ ላይቤሪያ ፣ አንጎላ ፣ ሩዋንዳ ፣ቡሩንዲ፤ አይቮሪ ኮስት፤ የሶማሊያ የጦር ቀጠና ሆኑ። በእነዚህ ሁሉ የአፍሪካ ሀገሮች የተቋቋመው መንግስት ሲወድም ሕዝቦች አልቀዋል፡ ተቁዋማት ወድሟል። ለውድመቱ ምክንያት ደግሞ ከውስጥ "ኤሊት" ተብሎ በሚጠራው በ kleptocratic ማፊያ በሚመሩ "የጎሳ" ግንባሮች ፍልሚያ ውስጥ እጁን በማስገባት በሁለቱም ተፋላሚ ግምባሮች “የኮርፖሬት ካፒታሊስት የስለላው መረብ” ሁሉንም ዓይነት ሠራዊቶች በገንዘብም በሃሳብም በመደገፉ ነው።

ዓለም አቀፍ ሕጎችን በመጣስ በተፋለሚ ወገኖች በቀጥታ ጣልቃ በመግባት ተጠያቂነት የሌለባቸው ተፋላሚ ወንጀለኞች ያሻቸው እንዲያደርጉ የተቻለውን አደረገ። በዚህ ፍልሚያ አደራጅ ሆኖ የታየው የስለላው መረብ እስራኤልና አሜሪካ እንዲሁም ጂሃዳዊው እስላም ከመካከለኛው ምስራቅ ቱጃሮች በመቀናጀት ኢትዮጵያ ውስጥ ሉአላዊ ድንበሮችዋን በሚጻረር መልኩ “ጎሳዊ” ግንባሮችን በመፍጠርና በመደገፍ ኢትዮጵያ እንደትፈርስ ከተፈረጁት አገሮች አንድዋ ሆና አሁን ላለንበት እልቂትና የዘር ፍጅት ተዳርጋለች።

የአይሁዶቹ የሞሳድ ድርጅት የውስጥ ሰላዮችን በማደራጀት የአይሁድ ሃይማኖት ተከታዮች የሆኑትን በተለምዶ “ፈላሻ” የሚባሉትን ኢትዮጵያዊያንን አገራቸው እንዲክዱ በማድረግ በምስጢር የዘረጉትን መዋቅር ስብከት ፈላሻዎቹም ኢትዮጵያ አገራችን አይደለችም በሚል ፖለቲካዊና ሃይማኖታዊ ሰበካ ተቀብለው፤  በሺዎች የሚቆጠሩ ትግርኛ፤ አማርኛና አገው ተናጋሪ ኢትዮጵያዊያን ወደ እስራል በማስገባት ዛሬም ነተኛሁ ሰላዮቹን በመላክ ባለፈው ሰሞን ተጨማሪ ፈላሻዎች በገፍ ጭነው በመውሰድ የሰው ሃይል እየበዘበዘች ነች። ቻይንም ሕንድም ሆነች አሜሪካ እንዲሁም አረቦች ግብርናውና ማአድኑን አንድ ባንድ ተንሰራፍተው ተቀራምተውታል።

እንዲህ ያለው ዘረፋ በአገራችን ብቻ ሳይሆን በመላ አፍሪካ እና እስከ ኢራቅ፤ሶርያ እና ሊቢያ ድረስ ጣልቃ ገብተው ሀብቶቻቸው ሁሉ ተቆጣጥረው አገሮቹ እንዲፈርሱ ሆነዋል። ኢትዮጵያ አሁን ላለችበት የጦርነት ፍልሚያ በሁለቱ ወገኖች የሥልጣን ሽሚያ እና በውጭ የታቀደ ዕርዳታና ሴራ ውጤቱ የሰው እልቂትን እያስከተለ ነው። ኢትዮጵያ “ፌይልድ ስቴት” (የተንኮታኮተች አገር) ተብላ ከተመዘገበች ቆይታለች። ብያንስ በኔ እና በመሳሉ ጓደቼ በኩል ይህንን እናምናለን።

ወያኔና ኦነግ ተንከባክበው ባሳደጉት ተማሪያቸው “በአብይ አሕመድ” መካከል እየተካሄደ ያለው ጦርነትና ውግያ አፍሪከ ውስጥ በዓይነቱ ለየት የሚያደርገው ነገር፤  አገር በሚያፈርሱና የጎሳ የበላይነት በሚፎካከሩ ሁለት የጎሳ መሪዎች የሚካሂዱት  መሆኑን ጎልቶ የሚታይ ጉዳይ ነው። አብይ አሕመድ አገር አትፈርስም የሚለው እርሱ በጎሳ ስርዓት ኢትዮጵያን እስከተቆጣጠራት ድረስ ሲሆንወያኔ ደግሞ ያጣሁት ሥልጣን መልሼ ካልያዝኩ ትግራይ ትግርኚን እመሰርታለሁ በሚል ቅዠት ምሲኪን ሕዝብ እንዲታረድ ባመድረግ ሁለቱም በመንግሥታዊ ስርዓት አያያዝ ጉድለትና ወንጀል ተጠያቂዎች ናቸው።

ሁሉም ዓይነት ዱርዬዎች እየተከሰቱባት ያለቺው ኢትዮጵያ ሁለቱም ግምባሮች በሚከተሉት መንግሥታዊ ስርዓት መሆኑን መታወቅ ይኖርበታል። በውጭ አገር የተደገፈው “የጎሳ ስርዓት” ተወግዶ አዲስ መሪ ካልመጣ የሁሉም አይነት ዱርየዎች መናሃሪያ የሆነቺው ኢትዮጵያ ወደ ከፋ ጭለማ መገፍተርዋ መጠራጥር የለባችሁም።

አላመን ካልሆ በቀር እውነታው በሁሉም አቅጣጫዎች አገራችን በሁሉም ዓይነት የግልና የጎሳ ታጣቂዎች ወደ ገደል እየተጎተተች ያለቺው አገራችን  አዲስ መፍትሄ ያሻታል። በእነዚህ ታጣቂ ዱርየዎች ላይ እንደ አብይ አሕመድ እና ወያኔ የመሰሉ በውጪ የተመለመሉት የባዕድ አገልጋዮች የሚከተሉት ፓለቲካ ስንመለከት፤ ያውም እንደ እነ እስክንድር እና ልደቱ እንዲሁም አስቴርና ብዙ ጀግና እመቤቶች በሽብርተኛነት ወንጅሎ የሚያስር መሪ ኢትዮጵያዊ ነው በሎ መቀበል እጅግ ያስቸግራል።

ይህ ግለሰብ የሚመራው ስርዓት እጅግ የሚያማምሩ ገበርዲኖች ለብሰው ሰው የሚመስሉ በወንጀል ሥራ የተሳተፉ ኢትዮጵያ እና አማራ የሚሉ ቃላቶች ሲደመጡ የሚባንኑ ፤ በቤቶችና በገንዘብ ዘረፋ የሚሳተፉ መንግሥታዊ ዱርየዎች የተከማቸበት መንግሥት የምትመራ  ኢትዮጵያ አገር ሆና ትድናለች ብለን ካልን ከፈጣሪ በስተቀር “እስካሁን ድረስ ፍትሕ ያልፈተሻቸው ዱርየዎቹ”  መፍትሄ ናቸው ተብሎ እንደመንግሥት መቁጠር ተራ ጅልነት ነው።

 

ወዳጄ እና መምህሬ የነበሩት ፕሮፌሰር ዓለሜ እሸቴ ባንድ ወቅት በጻፉልኝ ደብዳቤ እንዲህ ብለው ጽፈውልኝ ነበር፤ “…the Mafia robbery going on in each "tribal state" (or Kelel) with Weyane kleptocrats being the greatest of all the robbers.” ከወያነ ክሊፕቶክራቱ ትልቁ ዘራፊ በተጨማሪ በእያንዳንዱ “የጎሳ ግዛት” ውስጥ ማፊያዊ ዘረፋ  እንደቀጠለ ነው።” (ፕሮፌሰር ዓለሜ እሸቴ) ብለው ነበር።

ሌላ ቀርቶ እስከ አሁንዋ ድረስ እየገረመኝ ያለው ሁኔታ “የጎሳ ነጻ አውጪዎች” ሴራ እንዳይበቃ በላዩ ላይ “ጎሳዊ” የፖለቲካ ፓርቲዎች ህጋዊ ሆነው ሲደመሩበት አገሪቷ 30 አመት ሙሉ ምን ያህል የቆረቆዘ “ሚዘራብል” (ደደብ አሳዘኝ) ምሁር ጫንቃዋ ላይ እንዴት አስችሏት እንዳዘለቻቸው ሳስበው ይገርመኛል።

ምሁሩ ብቻ ሳይሆን የአብይ አሽቃባጮችም ሌሎቹ ጉዶች ይገርሙኛል። አብይ አሕመድ የሚመራው ስርዓት “ወድዶ ሳይሆን ተገድዶ” ወያኔን አሳድዶ በመቅጣቱ ደስታቸውን ከመግለጽ ይልቅ፤ ይህንን የጦርነት ድል አስታክከው “ከወያኔ ያልተሻለው የጎሳ ሕገ መንግሥት ጠበቃው ጸረ አማራው አፓርታይዱ አብይ አሕመድ “መሪዬ ነህ” እያሉ እንደ ሜዳ ፍየል ሜዳው አልበቃ ያላቸው “የፖለቲካ ማሃይሞችንም” ላግራሞቴ ተጨማሪዎች ናቸው።

በዘም ወረደ በዚህ አብይ አሕመድ ከኦነግና ከሻዕቢያ፤ የወያኔ መሪዎች ደግሞ በነበሩበት የበረሃ ትግላቸው የውጭ አገር ቅጥረኛነታቸው ያየነው ሲሆን፤ ወያኔ ወደ መንግሥነት ከገባም በሗላ አብይ አሕመድና መሰል የወያኔ የስለላ ሰራተኞች በነበራቸው የመንግሥት ሥልጣን እና ቦታዎችአውቅና ተጠቅመው በሞሳድና በአሜሪካ እንዲሁም በእንግሊዝ የስለላ ድርጅት የተቀጠሩ የተለከፉ ሰላዮች መሆናቸው መጠራጠር የለባችሁም። የግሎባል ካፒታሊዝም ልዕለ ሃያሉ አገር እነዚህን እንዴት እንደሚጠልፋቸው ለማወቅ ለፈለገ ሰው ”By way of deception” የሚል የሞሳድ ሰራተኛ የነበረው ካናዳዊ አይሁድ መመልከት ነው። ለማንኛው “ኢትዮጵያ ታበጽህ ኢደዊሃ ሃበ እግዚአብሔር!”

ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)