Tuesday, October 20, 2020

ፓርላማው ወንበር ላይ የሞተው የአይጡ ሽታ! ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ Ethiopian Semay ድረገጽ) October 21, 2020

 

ፓርላማው ወንበር ላይ የሞተው የአይጡ ሽታ!

ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ Ethiopian Semay ድረገጽ)

October 21, 2020


የሕግ ዘርፎችን እና  የፓርላማው አዛዥና ናዛዥ የሆነው “ጨቅላው” አብይ አሕመድ “አምበጣን በመደመር ፍልስፍና” አራኣያነት በመጠቀም ፓርላማ ውስጥ ለተቀመጡት ሎሌዎቹ እና ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ያስተላለፈው ንግግሩ ብዙ ሰው አስቆጥቷል። አገር እመራለሁ እያለ አጉል የሚፈላሰፈው ይህ ግለሰብ “የኢትዮጵያ ገበሬዎች እያስለቀሰና እያደኸየ ያለው አምበጣን የሚያክል “እርኩስ በራሪ” ገበሬዎችን በማስለቀሱ “ደስታውን ለመግለጽ ሲል” አምበጣውን “በመደመር ፍልስፍና” ማወደሱ ብዙዎቻችሁ ያስደነገጠ ቢሆንም  ከሃይማኖትም ከገብረገብነትም ከሞራልም ከብቃትም ከሕግም አኳያ ሲመዘን አገር ለመምራት የማይመጥን እንዳለፉት ጌቶቹ ሁሉ “አገራዊ ፍቅር የሌለው” ሰው የምንለው ለዚህ ነው። 

በዚህ ሳያበቃ “ከየትም ለምኜ ያገኘሁትን የዕርዳታ ገንዘብ ፓርላማው እኔን የመጠየቅ መብት የለውም” ሲል አምላክ ባላጸደቀለት የበሻሻ ንጉሥነቱን በማያሻማ አምባገነናዊ ቃል ነግሮአቸዋል።የዜጎችን ነፃነት በመጻረር ላይ ያለው የፍርድቤቶቸን ትዕዛዝ አላውቅም ስለሚለው ስለ ፖሊሶቹ መረን የለቀቀ አምባ ገነንነት ሲጠየቅም “እንደለመደው አባባሉ” “አልሰማሁም አላየሁዩም” ከማለት ሌላ የሚለው የመማምለጫ ንግገሩ ሌላ ምንም ማለት ስለማይችል ብዙ ሰው ያስቀየመ የተግማማው ጭንቅላቱ የሕዝቡን አፍንጫ ሲረብሽ አምሽቷል።

በጣም የሚገርመው ደግሞ የእንጦጦ ፓርክና የስንዴ አዝርእት ጉብኘቴን እያያችሁ መልካም መልካሙን ለምን አታወሩልኝ ሲል ያደመጡት በየዓለማቱ የተሰገሰጉ ካድሬዎቹ ያንኑ በመድገም “መልካም መልካሙን ለምን አታሸቱም?’ ብለውናል። እኛ የምንለው “የመሪያችሁ ንግግር የጠነባ የሞተ አይጥ ሽታ ነው እያልን ያለነው”።ጥያቄው የሚሆነው ‘የሞተ አይጥ ሲኖር ጥሩውን ማሽተት ይቻላል ወይ? ከባድ ነው! አይደለም እንዴ? ጡሩውን ማሽተት ወይንም ግሙን ማሽተት ምርጫህ ነው የሚሉ ሎሌዎች በብዛት አሉት። ለምርጨውም እኮ ጤናማ አየር ሲኖር እንጂ የሞተ የጠነባን የአይጥ በድን ማዕድ አጠገብ ተጥሎ ሆድ ብላ ቢሉት አፍንጫ በጄ አይልም። የመሪያችሁ ንግግር ከሞተ አይጥ በላይ ይሸታል። መሪያችሁ የሞቱት የአይጦች ሽታ ምልክት ነው። 


ከአንደበቱ የሚወጡት የጠነቡ ንግግሮቹ ሕሊናን ይረብሻሉ። ምላሱ ከመለስ ዜናዊ የባሰ “በኢትዮጵያዊነት ሞራል ያልተቆነጠጠ”፤ ሕዝብን የሚያስቆጣ እና የሚያስቀይም ንግግሮችን ለይቶ የማያውቅ “ከሥልጣኔ የራቀ፤በረሃ አደግ” ግለሰብ ነው። ካሁን በፊት የተማሩ ሳይንቲስት ኢትዮጵያውያን ምሁራንን “ለማንኳሰስ” እና በዘረፋ የበለጸጉትን ሃብታሞቹን ለማስደሰት ሲል “መኪና የሌላቸው በእግራቸው የሚጋዙ” ብሎ ያለውን አንሶት ፤ዛሬ ደግሞ “ሕዝብን እየስለቀሰ ያለውን የአምበጣን መንጋነትና እና ጭካኔነት” ለፖለቲካው መስበኪያ ማድረግ እጅግ የሚገርም ለመሪነት የማይመጥን ሕክምና የሚያስፈክገው በዘመናችን የተዋጣለት “ዕብድ” ግለሰብ ነው። የዓሳ ግማቱ ከጭንቅላቱ!! የተባለው ለካ እውነት ነው።

ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)

No comments: