Tuesday, October 27, 2020

ተከበናል! ስለዚህ ሓለፈነት አንወስድም? What? ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay) Tuesday, October 27, 2020

 

ተከበናል! ስለዚህ ሓለፈነት አንወስድም? What?

ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)

Tuesday, October 27, 2020

አብን ላይ ብዙ ሰዎች ተሰፋ አድርገው ውሃ ዘግነው ቀሩ። ምናልባትም ለተወሰነ ወቅት አብን መደራጀቱ ውጤት ማግኘት ይችል ይሆናል ብየ አምን ነበር - ይህ እምነቴ መጀመሪያ ሲደራጁ በነበረበት ወቅት ነበር። የአመራሩ አባል የነበረው ክርስትያን ታደለና ሌሎች ምስኪን አማራ ገበሬዎች ከየ አፓርታይድ ክልሎቹ እየታፈሱ ከጀኔራል አሳምነው ግድያ ጋር አያይዘው ወደ እስር ሲወረውርዋቸው፤ ሳይታሰሩ የቆዩ ‘ብዙዎቹ አመራሮች’ በሰላማዊ ሰልፍ ወይንም ሕዝባዊ አመጽ በማስነሳት ያስፈትዋቸው ይሆናል ብየ ብጠይቅ “አይጥ ውስጥ የገባች አይጥ” ሆነው ሳያቸው ከዚያ ወዲህ በነሱ ላይ የነበረኝ ተስፋ ወርውሬ ጣልኩት።

 

ከዚያም አማራን በመግደልና በማስገደል እጆቻቸው ከተጨማለቀው ከታወቁት የኦሮሞ ፖለቲከኞች እና የዘርና የሃይማኖት ጭፍጨፋ በማካሄድ የተካፈለው የሥርዓቱ መሪዎች ጋር ተሰባስበው እርስ በርስ “አንዱን አንዱን አያጋልጥ” ወዘተ በሚል ተዋውለው አብይ አሕመድ ከሰበሰባቸው በሗላ “እነዚህ የአኢዘማ ሁለተኛው ጓዳ ናቸው” አልኳቸው። ከስንት ጊዜ የመግለጫ መንጋጋት በሗላ ይኼው እንደገና ሰሞኑን መጡ እና መሬት አርዕድ አንቀጥቅጥ ተቃውሞአችን እናሰማለን ብለው ሕዝቡን በማሳወቅ “የዋህ አማራ ወጣቶችን” በስሜት ሲየስጋልቡዋቸው ሰንብተው ይኼው እንደገና ተመልሰው “ጽ/ቤታችን እያለን ስለተከበብን መውጣት አልቻልንም እና እኛ በሌለንበት የሚደረግ ተቃውወሞ ሓላፊንት አንወስድም”  የቅንጅት አይነቱ ቅዠት ቃዥተው “የተከታዮቻቸውን ሓሞት አፈሰሱት”፡ ይህ ድርጊት ካሁን በፊት አድርገውት እንደነበር ታስታውሳላችሁ፡ ዛሬም  ይኼው ደገሙት።


 ብትከቡንም  እምቢ አታግዱንም ብለው ግብግብ ፈጥረው ወደ እስር ላለመጋዝ ስለወሰኑ “የኦሮሙማው አፓርታይድ ፖሊሶቹም” ይህን እሺታ ተመለክተው በመጡበት መኪና ተሳፍረው ተመለሱ፡ እነሱም በሚገርም ሁኔታ ወደ ጽ/ቤታቸው ተመልሰው ተወሸቁ። ሰናይ ወሰናይ!!!

የሰላማዊ ተቃውሞ ዋናው መሳሪያ ምንድነው? ተቃውሞን የሚመሩ መሪዎች/አመራሮቹ ሰላማዊ የፖለቲካ ዓይነት ሲከተሉየተወሰኑ ሕጎችን በተለይ  አገዛዙ የሚፈጽማቸው ኢሰብኣዊ ተግባሮችን እና የሰላማዊ ሰልፍ እገዳዎችን ያጸደቀ አዋጅ ወይንም የራዲዮ መግለጫን ለማክበር ፈቃደኛ አለመሆን ማለት ነው (በአጭር አማርኛ!!!):፡ እነዚህ ግን ፖሊሶች ስለከበቡን ተከበናል የተጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ሰርዘናል አሉና ሊቃወሙት የወጡትን እና “ማንም ምድራዊ ሃይል ሰላማዊ ተቃውሞአችንን ከማድረግ የሚያግደን ሃይል የለም” ብለው ፎከሩና መጨረሻ ምድራዊ ሃይል ሳይሆን የ 18 እና የ20 አመት ማሃይም ወጣት ፖሊሶች እጅ ጓንቲ እና ብትር ይዘው ሲመጡባቸው ተከበናል ብለው እርፍ!

ፖሊሶቹ ስትመለከትዋቸው ጓንቲ አጥለቀው ነበር የመጡት። እነሱ የገመቱት አብኖቹ “ምድራዊ ሃይል የሚያግደን የለም ሲሉ ስለተሰማ፤ አማራሮቹ “ታዘዝ አንታዘዝም” ግብግብ ተፈጥሮ ደም እንዳይበከሉ እጃቸውን በጥቁር “የፕላስቲክ ግላቭ’” ሸፍነው ነበር  ውጥረቱን ለመጋፈጥ የመጡት። ሆኖም የተፎከረውና የታየው መልስ ግን እንደጠበቁት ስላላገኙዋቸው ወዲያው ከጥቂት መወያየት በሗላ ፖሊሶቹ ወደ ጣቢያቸው እየተዘባነኑ ተመለሱ። እስክንድር ነጋ የእግር ኳስ ጨዋታ ለማየት ቲኬት ይዞ ወደ በሩ ሲሄድ፤ ፖሊሶች “አትገባም ብለው በሩን ሲዘጉበት “አትዝጉብን አንገባለን “በሕግ አምላክ!!!” እያለ እየጮኸ ለሕዝቡ እይታ ሲያስመሰገብ ነበር”።፡እነኚህ ግን እጃቸውን አጣጥፈው ከጥቂት መነጋገር በሗላ ፖሊሶቹ ወደ መጡበት ተመሉ። ውጥረት የለ ምን የለ!

ፖሊሶቹ ከዚህ ቤት እንዳትወጡ ብለው “ኮምፕላይ” አድርጉ (የምንላችሁን ፈጽሙ) ብለው ጠየቅዋቸው፡ አብኖቹ  ደግሞ በሚገርም መለማመጥ ፖሊሶቹ ያዘዝዋቸውን አደረጉ። እኔ አገር ቤት ነበነበርኩበት ወቅት ከፖሊሶችና ከጦር ሰራዊቶች (ከተማውን ሲጠብቁና ሲያውኩ ከነበሩ ካድሬዎች እና የነበልባል ጦር አለቆች በእምቢተኛነት ቢያንስ ሦስት ጊዜ ከነዚህ ሃይሎች እና ወንጀል ምርምራ ጋር ከዚይም ከጥቂት ዕረፍት በሗላ “እንጠርጥርሃል” እያሉ 4 ጊዜ መጥፎ እስርና ድብደባ ደርሶብኝ እምቢተኛነቴን አሳይቼ ለከፋ እንግልት ለመጋፈጥ ወስኜ በተግባር ማሳየቴን አስታውሳለሁ። በቀዳማዊ ሃይለስላሴ ጊዜም ሥርዓቱን በመቃወም አዳራሽ ውስጥ ንግግር አድርገሃል ተብየ አሁን አውሮጳ በሚኖሮው ፌሰድ ቡክ ውስጥ የምታውቁት “የወዲ ሻምበል” አባት በመቶ አለቃ አማረ ታስሬ ተንገላትቼአለሁ:: አሁንም አብሮኝ ከታሰሩት ውስጥ ዋሺንገቶን ከተማ የሚኖሮው ዶ/ር አበበ ተሰማ ነበር። አበበ ተሰማ የታወቀ የተማሪዎች መሪ ነበር (አዲስ አበባ ዩኒቨረሲቲም ሆነ ትግራይ ውስጥም)።

 

ከሚገርማችሁ ወደ ሱዳን ስሻገር ሸራሮ ውስጥ ከወያኔ መሪዎች ሰብሓት፤ መለስ፤ ክንፈ ሳሞራ፤መረሳ፤ እና አንድ የረሳሁት ሰው ለሦሰት ቀን ተከታታይ የተካረረ ውጠረት የበዛበት ውይይት ከስብሓት ጋር ሳደርግ አብሮኝ የነበረ ጓደኛ ማታ ወደ መኝታችን አሰናብተውን ስንሄድ “እባክህን ረገብ በል እንዳታስገድለን አንተንም አንዳይገድሉህ” ብሎኝ እንደነበር አስታውሳለሁ። የክርክራችን ርዕስ ደግሞ አሁን እየገዛት ያለው ብሔር ማን ነው? የሚል ነበር፤ ሰብሓት አማራ ነው ሲለኝ እኔ ደግሞ ብሔር የሚባል የለም አማራ የሚባል ብሔርም እየገዛ አይደለም የሚል ነበር፡ እንደ ድፍረቴ ምክንያቱን ባላውቀውም እነሱም አከበሩኝ እንጂ ምንም የደረሰብኝ ነገር አልነበረም።)፤ ስለዚህ  አለመታዘዝ ማለት አንድ ዜጋ የተወሰኑ ህጎችን ፣ ጥያቄዎችን ፣ ትዕዛዞችን ወይም የመንግስትን ትእዛዛት ለመታዘዝ  እምቢተኛነትን ማሳየት ማለት ነው። ሌላ ዝባዝበንኬ የለውም። አጭርና ግልጽ ነው። ሰላማዊ ስለተባለ “ውጥረት የለውም ማለት አይደለም። አላማው ውጥረትን ለመፍጠር ነው እንጂ ለመለማመጥ አይደለም።  ከሰላማዊ ሰልፎች ከፀጥታ ኃይሎች ውጥረት መፍጠር ማለት ነው። ያ ግን አገራችን ውስጥ አይታወቅም። አንዳንድ ጊዜ ምነው ኢትዮጵያ  ዓረብ በሆነችና እነዚህን አጋስሶች “አላህ ወ አክበር” እያለ የቱኒዚያ፤ የግብጽ የሌባኖስን አይነት ተቃውሞ በታየ እላለሁ። የአበሻ እንጀራ “እሽታን” የሚያስተምር ማደንዘዣ ሳር ነው። ኤርትራን ተመልከቱ ኢትዮጵያን ተመልከቱ “ሕዝቡ ጭለማ ቀንበር ውስጥ ገብቶ” ዛሬም “እሺታን” አማራጭ አድርጎ “ጫወነቱን” እያስመሰከረ አነገቱን ቀርቅሮ “በብትር በቢላዋ ፣ ሲታሰር ፣ ሲፈታ ፣ ሲገደል ፣ ሲባረር ፣ ሲሰደድ ፣ ሲፈናቀል 29 አመት ገሃነም ውስጥ እንደታሰረ ነው”። እስኪ ደግሞ አብኖች ይህንን ትችት ሰምተው ቢታረሙና  የሚቀጥለው ምን እንደሚሰሩ አብረን እንጠብቅ!

አመሰግናለሁ

ጌታቸው ረዳ   

Saturday, October 24, 2020

የበጎችን በር ሰብረው የገቡት የአብይ አሕመድ ቶክላዎችና የ80 አመትዋ አዛውንት እምባ! ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay) October 24/2020

 

 

የበጎችን በር ሰብረው የገቡት የአብይ አሕመድ ቶክላዎችና የ80 አመትዋ አዛውንት እምባ!

ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)

October 24/2020

ከዚህ በታች ተያይዞ የምታዩት ስዕለ ደምፅ “የ80 ዓመትዋ አዛውንት ከሚኖሩበት ቤት ከነዕቃቸው በአንሶላ ተጠቅልለው ውጭ ተጣሉ” በሚል አዲስ አበባ ውስጥ የሚገኘው የእዮሃ ሚዲያ” ዘጋቢ “ተሻገር ጣሰው”  ኢትዮጵያውያን እንድንመለከተው የዘገበው አሳዛኝ እና የአብይ አሕመድ አፓርታይዳዊ የናዚ ሥርዓት ኦሮሙማው ብልጽግና የማን አለኝህን “የግፍ” እርምጃዎችን የሚያሳይ የዛሬ የመነጋገሪያ አጀንዳ አድርጌ አቅርቤዋለሁ።

በዘገባው ውስጥ የምታደምጥዋቸው እኚህ የ80 አመት ሴት አዛውንት ኦሮሙማው አስተዳደር አዲስ አበባ ውስጥ የተወሰኑ ብሔረሰቦችን ከሚኖሩባቸው ቤቶቻቸው በሃይል በማስወጣት በመንግሥት ሥልጣን  ያለ ሕግ የተኮፈሰው የ አፓርታይዱ የኦሮሙማው መሪ አብይ አሕመድ “ፍንፍኔ” ብሎ በሚጠራት አዲስ አበባ ኦሮሞዎች ብቻ እንዲሰፍሩባት ባቀደው መሰረት በሁለት አመት ተኩል ውስጥ በሺዎች የሚቆጠሩ ኦሮሞ ያልሆኑ ዜጎችን በዘረኛነት ፖሊሲው እየተመራ ወደ በረንዳ በመጣል የዜጎቻችን የሲኦል ኑሮ እንዲኖሩ እያደረገ ነው። በአፓርታይዱ ኦሮሙማው የጥቃት ኢላማ  ቅደም ተከተል ቀዳሚው አማራ ቀጥሎ የደቡብ ሰዎችን የጥቃት ኢላማ ተብለው ግፍ ከሚፈጸምባቸው ቀዳሚ ናቸው።

የናዚ ጀርመን የመጀመሪያ የጀርመን ዘር ጠላት ተብሎ የተቀመጠው አይሀዱ ማሕበረሰብ ሲሆን የተቀሩት እነ ፖል ሮማኒያ እና የፖለቲካ ተቃዋሚዎች እንዲሁም አካለ ስንኩላን ወዘተ መለያ ቁጥሮች እና ቀለሞች ነበራቸው። አሁንም አገራችን ውስጥ በተመሳሳይ  ስልት የለየለት የወንጀለኞች ጥርቅም የሆነው የብልጽግና አፓርታይዱ የአብይ አሕመድ ድርጅት “አማራን፤የፖለቲካ ተቃዋሚዎችን፤ ምሁራንን እና አረጋውያንን” በቀየሰላቸው የማጎርያ ቦታዎች ቀስ በቀስ ያለማቛረጥ ሁለት አመት ሙሉ ወደ ምድር ሲኦል እንዲጣሉ እያደረገ ነው። ለምሳሌ በናዚ ጀርመን ወቅት “ኦሽዊትዝ ማጎሪያ ካምፕ” (Auschwitz concentration camp) ተብሎ የሚታወቀው ስቃይ የሚካሄድበት እስር ቤት ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ የፖለቲከላ ተቃዋሚዎቹን ሰብስቦ ማአከላዊ እና ቅሊንጦ በማጎር በኮቪድ ቫይረስ በሽታ ከተበከሉ እስረኞችና ተራ ወንጀለኞች ጋር ቀላቅሎ ሞራላቸው እንዲነካና በበሽአውም ተበክለው እንዲሞቱ ያስራቸዋል። አደገኛ የሆነው የልብ ሕመም ያላቸው እንደ እነ ልደቱ አያሌው የመሳሰሉ ትንታግ ፖለቲከኞችን እንዳይፈቱ በማንገላታት ልክ እንደ ፕሮፌሰር አስራት በዘዴ እንዲሞቱ እንደተደረገው ልደቱ አያሌውም ያንን የሞት ጽዋ እንዲደርሰው  እየተደረገ ነው። ይህንን በሚመለከት በማዘጋጀው አዲስ መጽሐፍ ልደቱ እና አስራት የአያያዝ ስልት ተመሳሳይነት በሰፊው አቀርባለሁ።

ተቃዋሞዎችን በዚህ መልክ ሲያጉራቸው፤ አረጋውያን ደግሞ ከሚተኙበት አልጋ እየጎተተ  በለበሱት አንሶላ እንደ ዕቃ ጠቅልሎ ደጅ ላይ እንዲጣሉ ተደርገው በረንዳ አዳሪ እንዲሆኑ እያደረገ ነው።

በሚገርም አጋጣሚ ይህን ጽሑፍ ስጽፍ ፤አሁን በካሊፎርኒያ ሰዓት አቆጧጠር 6:25 PM ላይ አንድ አረጋዊ ስለተሰወሩና ስለደህንነታቸው ስላሳሰበን ዜጎች ሁሉ እኚህ አዛውንት ካገኛችሗቸው ባስቸኳይ ለፖሊስ በመደወል አሳውቁ  የሚል “ብሩራዊ የአደጋ ማስጠንቀቂያ” (ሲልቨር አለርት ኢመርጀንሲ”_የሚል የስልክ ደወል ተደውሎልኝ ባየሁ ወቅት ፤በተጸራሪ በዚህ ቪዲዮ የምትመለከትዋቸው የ80 ዕድሜ አዛውንት ሴት  ታመው አልጋቸው ላይ ጋደም እንዳሉ እንዲህ ያሉ ጠበቃ እና እንክብካቤ የሚያስፈልጋቸው አቅመ ደካማ የአዛውንት በር ሰብረው የገቡት የአብይ አሕመድ ቶክላዎችና የ80 አመትዋ አዛውንት እምባ እያወዳደርኩ ስጥል ሳወርድ ‘ኢትዮጵያውያን እንዲህ ያሉ የአፓርታይድ እንሰሳዎች እንዴት እንደምንገላገላቸው ሳስበው ኣእምሮየ ብዙ ጊዜ ይረብሸኛል’።

“የ80 ዓመትዋ አዛውንት ከሚኖሩበት ቤት ከነዕቃቸው በአንሶላ ተጠቅልለው ውጭ ተጣሉ” የሚል ዘገባ ስትመለከቱ ምን ተሰማችሁ? እስኪ ሼር አድርጉትና የግፉ ብዛት ምን ድረስ እንደደረሰ ሰው ሁሉ ይመልከተው። ባንድ ወቅት የደቡብ አፍሪካ ሊቀ ጳጳስ ዲስሞን ቱቱ አፓርታይዱን ስርዐትና ፤ ልክ እንደ አብይ አሕመድ  “የጥገና ለውጥ” አራማጆቹ ለሚደግፉ ደጋፊዎች እንዲህ ብለው ነበር "We don't want our chains made more comfortable, we want it to be removed" ሰንሰለቶቻችን እየላሉ የበለጠ እንዲመቹን ሳይሆን ጭራሽኑ  እንዲወገድ እንፈልጋለን” ብለው ነበር። እኛም በተራችን በሕዝባችን  እግሮች ላይ የተቆለፉት የኦሮሙማ ብልጽግና ፓርታይድ የማሰቃያ የእግር በረቶች እንዲላሉ ሳይሆን ተሰብረው እንዲጣሉ ነው።

ሼር ለምታደርጉት ሁሉ በአዛውንትዋ ስም እና በዘጋቢው ተሻገር ጣሰው አመሰግናለሁ።የ80 ዓመቷ አዛውንት ከሚኖሩበት ቤት ከነእቃቸው በአንሶላ ተጠቅልለው ውጭ ተጣሉ!! | ተሻገር ጣሰው!

https://youtu.be/DxckMgCkThY

አመሰግናለሁ

ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)

October 24/2020

 

    

Tuesday, October 20, 2020

ፓርላማው ወንበር ላይ የሞተው የአይጡ ሽታ! ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ Ethiopian Semay ድረገጽ) October 21, 2020

 

ፓርላማው ወንበር ላይ የሞተው የአይጡ ሽታ!

ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ Ethiopian Semay ድረገጽ)

October 21, 2020


የሕግ ዘርፎችን እና  የፓርላማው አዛዥና ናዛዥ የሆነው “ጨቅላው” አብይ አሕመድ “አምበጣን በመደመር ፍልስፍና” አራኣያነት በመጠቀም ፓርላማ ውስጥ ለተቀመጡት ሎሌዎቹ እና ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ያስተላለፈው ንግግሩ ብዙ ሰው አስቆጥቷል። አገር እመራለሁ እያለ አጉል የሚፈላሰፈው ይህ ግለሰብ “የኢትዮጵያ ገበሬዎች እያስለቀሰና እያደኸየ ያለው አምበጣን የሚያክል “እርኩስ በራሪ” ገበሬዎችን በማስለቀሱ “ደስታውን ለመግለጽ ሲል” አምበጣውን “በመደመር ፍልስፍና” ማወደሱ ብዙዎቻችሁ ያስደነገጠ ቢሆንም  ከሃይማኖትም ከገብረገብነትም ከሞራልም ከብቃትም ከሕግም አኳያ ሲመዘን አገር ለመምራት የማይመጥን እንዳለፉት ጌቶቹ ሁሉ “አገራዊ ፍቅር የሌለው” ሰው የምንለው ለዚህ ነው። 

በዚህ ሳያበቃ “ከየትም ለምኜ ያገኘሁትን የዕርዳታ ገንዘብ ፓርላማው እኔን የመጠየቅ መብት የለውም” ሲል አምላክ ባላጸደቀለት የበሻሻ ንጉሥነቱን በማያሻማ አምባገነናዊ ቃል ነግሮአቸዋል።የዜጎችን ነፃነት በመጻረር ላይ ያለው የፍርድቤቶቸን ትዕዛዝ አላውቅም ስለሚለው ስለ ፖሊሶቹ መረን የለቀቀ አምባ ገነንነት ሲጠየቅም “እንደለመደው አባባሉ” “አልሰማሁም አላየሁዩም” ከማለት ሌላ የሚለው የመማምለጫ ንግገሩ ሌላ ምንም ማለት ስለማይችል ብዙ ሰው ያስቀየመ የተግማማው ጭንቅላቱ የሕዝቡን አፍንጫ ሲረብሽ አምሽቷል።

በጣም የሚገርመው ደግሞ የእንጦጦ ፓርክና የስንዴ አዝርእት ጉብኘቴን እያያችሁ መልካም መልካሙን ለምን አታወሩልኝ ሲል ያደመጡት በየዓለማቱ የተሰገሰጉ ካድሬዎቹ ያንኑ በመድገም “መልካም መልካሙን ለምን አታሸቱም?’ ብለውናል። እኛ የምንለው “የመሪያችሁ ንግግር የጠነባ የሞተ አይጥ ሽታ ነው እያልን ያለነው”።ጥያቄው የሚሆነው ‘የሞተ አይጥ ሲኖር ጥሩውን ማሽተት ይቻላል ወይ? ከባድ ነው! አይደለም እንዴ? ጡሩውን ማሽተት ወይንም ግሙን ማሽተት ምርጫህ ነው የሚሉ ሎሌዎች በብዛት አሉት። ለምርጨውም እኮ ጤናማ አየር ሲኖር እንጂ የሞተ የጠነባን የአይጥ በድን ማዕድ አጠገብ ተጥሎ ሆድ ብላ ቢሉት አፍንጫ በጄ አይልም። የመሪያችሁ ንግግር ከሞተ አይጥ በላይ ይሸታል። መሪያችሁ የሞቱት የአይጦች ሽታ ምልክት ነው። 


ከአንደበቱ የሚወጡት የጠነቡ ንግግሮቹ ሕሊናን ይረብሻሉ። ምላሱ ከመለስ ዜናዊ የባሰ “በኢትዮጵያዊነት ሞራል ያልተቆነጠጠ”፤ ሕዝብን የሚያስቆጣ እና የሚያስቀይም ንግግሮችን ለይቶ የማያውቅ “ከሥልጣኔ የራቀ፤በረሃ አደግ” ግለሰብ ነው። ካሁን በፊት የተማሩ ሳይንቲስት ኢትዮጵያውያን ምሁራንን “ለማንኳሰስ” እና በዘረፋ የበለጸጉትን ሃብታሞቹን ለማስደሰት ሲል “መኪና የሌላቸው በእግራቸው የሚጋዙ” ብሎ ያለውን አንሶት ፤ዛሬ ደግሞ “ሕዝብን እየስለቀሰ ያለውን የአምበጣን መንጋነትና እና ጭካኔነት” ለፖለቲካው መስበኪያ ማድረግ እጅግ የሚገርም ለመሪነት የማይመጥን ሕክምና የሚያስፈክገው በዘመናችን የተዋጣለት “ዕብድ” ግለሰብ ነው። የዓሳ ግማቱ ከጭንቅላቱ!! የተባለው ለካ እውነት ነው።

ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)

Friday, October 16, 2020

አማራን ለጥቃት ከዳረጉ መሠረታዊ ችግሮች ጥቂቶቹ ይነጋል በላቸው (Ethiopian Semay) Friday, October 15,2020

 

አማራን ለጥቃት ከዳረጉ መሠረታዊ ችግሮች ጥቂቶቹ

ይነጋል በላቸው

(Ethiopian Semay)

Friday, October 15,2020

 

ይህችን አጭር ማስታወሻ ካነበቡ በኋላ በምጠቁመው የድረ ገጽ አድራሻ ገብተው ዘመድኩን በቀለ የጻፈውን እጅግ ጠቃሚ መረጃ በአትኩሮት እንዲመለከቱ በትኅትና እጋብዛለሁ፡፡(https://welkait.com/?p=19074)

 

ዓለምን ከጥንት ጀምሮ እየዘወራትና ወደሞቷ እያዳፋት ያለው የሤራ ፖለቲካና የመሠሪዎች ሸርና ተንኮል መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ በግሌ ይህን ዓይነቱን ሤረኝነት እጠላለሁ፡፡ በዚያም ምክንያት ወደ ፖለቲካው መድረክ መቅረብን አልወደውም፡፡ በዚህ መልክ የምንጨረጨረው ግን ያለ ሀገር መኖር የማይቻል በመሆኑና አንድ እንኳን አንባቢ ባገኝ የሚሰማኝን ለማስተላለፍ ነው - ቢያንስ እንደጣሊያኑ ሊቀ ጳጳስ ላለመሆን፤ ኢጣሊያ ሀገራችንን በወረረችበት ወቅት የነበሩት ሊቀ ጳጳስ በአንድ ታዛቢ እንደተተቹት “ዝም ማለት በሚገባቸው ወቅት ተናገሩ፤ መናገር በሚገባቸው ጊዜ ደግሞ ዝም አሉ”፡፡ ግፍና በደል በምድራችን ናኝቶ ሕዝብ እያለቀሰ ዝም ማለት ስህተት ነው፤ ሌላ ማድረግ ባይቻል ስለሚፈጸሙ ግፍና በደሎች መጮህ ይገባል፡፡ ሰሚ ካለ እሰዬው - ከሌለም ላድባሯ፡፡

በመሠረቱ የፖለቲካ ሰው ለመሆን መዋሸት ያስፈልጋል፡፡ ፖለቲካ መስሎ ማደርን፣ መቅጠፍጠፍን፣ ሃቅን ሸምጥጦ መካድን፣ አሽከርነትን፣ ተለማማጭነትን፣ እግር እስኪተክሉ ድረስ አድር ባይነትንና መለሳለስን፣ እንዳስፈላጊነቱ ለሕዝብ የወገኑ መምሰልንና እንዲያ ሲል ደግሞ ሕዝብን መካድን ያካትታል፡፡ ይሁዳንም ጴጥሮስንም መሆን፣ እንደየሁኔታዎች አስገዳጅነት ሰይጣንንም እግዜርንም ሆኖ መተወን፣ መስቀል ከሰላጤ ግራና ቀኝ መታጠቅ… ፖለቲካው አጥብቆ ይፈልገዋል፡፡ ይህን የፖለቲካ ተፈጥሮ በተለይ በአሁኑ ፍጥገታዊ ተለዋዋጭ የሀገራችን ሁኔታ በግልጽ እያየነው ነው - ለዚያውም በከፍተኛ አግራሞት፡፡ በፖለቲካ የ“ኩኑ ከማሆሙ” ሰው መሆን የግዴታ ያህል ነው፡፡ ፈረንጆች  When in Rome, do as Romans do. ይላሉ፡፡ ብዙዎች ግን ይህ ዓይነቱ እስስታዊ ጠባይ አይሆንልም፡፡ ስለሆነም እውነቱን ተናግረን በመሸብን ማደርን፣ መቸገርና መራብ መጠማትም ካለብን ያን በፀጋ ተቀብለን በሰላም መኖርን እንመርጣለን፡፡ እንጂ ሀገር እንዲህ የሤረኞችና የሸፍጠኞች መጫወቻ ስትሆን ዕድሉን ቢያገኙ እናት ምድራቸውን ከአደጋ ሊታደጉ የሚችሉ የየዘርፉ ባለሙያዎች ጠፍተው አይደለም፡፡

“አማራው አሁን ለሚገኝበት አጣብቂኝ የበቃው ለምንድን ነው? ‹የተደገመበት› አፍዝ አደንግዝ ምን ይሆን? ከዚህ አዙሪትስ እንዴት ሊወጣ ይችላል?” ተብሎ ቢጠየቅ በበኩሌ የሚከተሉትን አስተያየቶች እሰነዝራለሁ፡፡ የምታውቁትን ለማስታወስ ያህል እንጂ አዲስ ግኝት አይደሉም፡፡

1.     የአማራ ሥነ ልቦና በኢትዮጵያዊነት የተቃኘ እንጂ በዘርና በዘውገኝነት ዘመን አመጣሽ ወረርሽኞች የተበከለ አይደለም፡፡ በዚህም ምክንያት ላለፉት 30 እና 40 ዓመታት ይህን ሕዝብ ጎጠኛ ለማድረግ በቀጥታም ሆነ በተዛዋሪ መንገድ ዘመቻ ቢካሄድበትም ከሞላ ጎደል ከሽፏል፡፡ ክሽፈቱ ግን ሁለት ተቃራኒ ጎኖች አሉት፡፡ አንደኛው አማራን ጎድቶታል፡፡ ሁለተኛው ጠቅሞታል፡፡ የጎዳው - በአንድነት ተሰባስቦ የዘር ግንዱን በጥቂቶች ሳይቀር ከመጠቃት ሊያድነው አለማድረጉ ነው፡፡ እንደዐይጥ በተገኘበት ከመጨፈጨፍና በመንግሥት በጀት ታግዞ በህክምና ሽፋን ከተካሄደ የዘር ማምከን ዘመቻ አላዳነውም፡፡ የጠቀመው -በመከራ ውስጥ ሆኖም ኢትዮጵያዊነቱን እንዳይክድ ማድረጉ ነው፡፡ ይህም ለመጪዋ ኢትዮጵያ ትልቅ ተስፋ ነው - አማራው ለኢትዮጵያ ዳግም ትንሣኤ እንደ እርሾ ሆኖ ሊያገለግል መቻሉ ፍንጩ እየታዬ ነው፡፡ እንደ ሌሎች ብዙ ዘውጎች በሲሞቅ በማንኪያ ሲቀዘቅዝ በእጅ አማራው አለመኮማተሩና ወደ እንስሳነት አለመውረዱ ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የከፈለው መስዋዕትነት ነው - ይህም ያስመሰግነዋል፡፡

2.     አማርኛ ቋንቋ የመላዋ ኢትዮጵያ የሥራና የመግባቢያ ቋንቋ መሆኑ አማራውን ክፉኛ ጎድቶታል፡፡ እርሱን መስለውና የተኩላ ልብስ ደርበው እርሱን “ሆነው” ላለፉት በርካታ ዓመታትና አሁንም ድረስ አማራው ሳይወክላቸው በጠላቶቹና በአጥፊዎቹ አማካይነት በኩራዝ እየተፈለጉ አማርኛንና የአማራን ባህልና ወግ  የሚያውቁ መሠሪዎች ከየነገዱ ተመርጠው አማራውን እንዲያስተዳድሩ መደረጉ አማራን ክፉኛ ጎድቶታል፡፡ በመልክም፣ በቋንቋም፣ በባህልም፣ በአነጋገር ላሕይም አንተን የሚመስልን ግን አንተን ያልሆነንና አንተን ለመጉዳት በሥውር የተተከለብህን ጠላት መለየት ከባድ በመሆኑ ይህ አካሄድ አማራን እንደኤድስ ቫይረስ ክፉኛ አጥቅቶታል፡፡ አማራ ፈረንሣዊ ነው፤ ወያኔ-ትግሬ እንግሊዝ ነው፡፡ እንግሊዝና ፈረንሳይ ደግሞ ለዬቅል ናቸው፡፡ በስሙ ብአዴንን የመሰሉ የጠላት ድርጅቶች አሽከሮችና ጉዳይ አስፈጻሚዎች ተፈጥረው አማራን ያስጨፈጨፉት በዚህ የሤረኞች ደባ ነው፡፡

 አማራ በልማት መራመዱ ይቅርበትና በድህነት እንኳን እንዳይኖር ከቀየውም ከሌሎች አካባቢዎችም እንዲሳደድ አድርገውታል - ያሳዝናል፡፡ አሁን ከእግዜሩ ከሚጠበቀው የድኅነት ዘመን ውጪ በሰዎች ተስፋ የማንጥልበት ግልጽ ወቅት ላይ እንገኛለን፡፡ “ቂጣም ከሆነ ይጠፋል፤ ሽልም ከሆነ ይገፋል” እንዲሉ አሁን ላይ ያልተገለጠ የተሸፈነ እውነት የለም፡፡ ማወቅ ያለመፈለግ ካልሆነ በቀር፡፡ ይህ ደግሞ ዐውቆ የተኛን እንደመቀስቀስ ነው፡፡ አንድ ሰው ደግሞ በተለያዩ ምክንያቶች ዐውቆ የተኛ የመምሰል መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

3.     ባለፉት 30 እና 40 ዓመታት አማራው በትምህርት እንዲቀጭጭ መደረጉ ሌላው የአማራው ልማትና ዕድገት ፀር ነው፡፡ በትምህርት የወደቀ ማኅበረሰብ በሁሉም ይወድቃል፡፡ ከትምህርቱም ባለፈ በልማትም የተበደለ ነው፡፡ አማራ ሆነህ ራሱ ከትግራይ ውጪ ኢንዱስትሪና ፋብሪካ የማታቋቁምበት በምፀት እያሣቀህ የሚያስለቅስህ ዘመን ነበር፡፡ ደሴ አካባቢ ሊሠራ የነበረው ቴርሼሪ ሆስፒታል እንኳን - ለምሣሌ - ተሰነካክሎ የቀረው ሕወሓት “በአማራው መሬት ይህን መሰል ልማት የሚሠራው እኔ ሞቼ ስቀበር ብቻ ነው” በሚለው ፀረ-አማራነት አቋሙ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ ስለዚህ ማይምነትና በላዩ ላይ ሳይወድ በግዱ አማርኛን እየተናገሩ የተሾሙበት “ሌሎች” ጊንጦች የአማራን ጣዕረ-ሞት አባብሰውታል፡- ግን አይዟችሁ ይነሣል፤ ሲነሳ ደግሞ በልዩ ክብርና ሞገስ ነው - እመ አምላክን ነው የምላችሁ፡፡ የዚህ ትምክህቴ መነሻ ደግሞ ምድራዊ ሳይሆን ሰማያዊ ነው - አንተ ስትፈልግ “ይህ ሰው ዐብዷል” ወይም “በቁም እየቃዠ ነው” ልትል ትችላለህ - እኔ የማየውን ባለማየትህ ባዝንም ስለኔ ባለህ ማንኛውም ዓይነት ግምትና አስተያየት አልከፋም፡፡ “ምድር ክብ እንጂ ጠፍጣፋ አይደለችም” ብሎ የተናገረ እንደኔው “ዕብድ”ም በድንጋይ ተቀጥቅጦ ሞቷልና የኔው ቀላል ነው፡፡

4.     አማራው ለራሱ ወገን አይሆንም፡፡ ምቀኝነት ይበዛዋል፡፡ በአማራው መሬት ለምሣሌ አማራ በሀብትም ሆነ በሥልጣን ከሚያድግ ይልቅ የሌላ ነገድ አባል ቢያድግ  መሰናክሎች ይቀሉለታል፡፡ አወቅሁሽ ናቅሁሽ ይበዛል፡፡ መናናቅ ይበዛል፡፡ አንድ ሰው ሲያልፍለት “እሰይ! ወፌ ቆመች” ከማለትና ከመደገፍ ይልቅ በምቀኝነት በየደብተራውና ቃልቻው ቤት በመሄድ ያንን ሰው በድግምትና በአንደርብ ማሰነካከል ይበልጥ ይዘወተራል፡፡ ይሄ ችገር ቀላል አይደለም፡፡ የምለውን ለማረጋገጥ ጠበሎችንና የባህል መድኃኒት ቤቶችን ደጅ መጎብኘት ይቻላል፡፡ ይህም ከዕውቀት የመቆራረጥ ውጤት ነው፡፡ መስተካከል አለበት - ዛሬውኑ፡፡ መሸፋፈን ይቅር፡፡

 

       ብዙ መናገር ይቻላል፡፡ ወደ መፍትሔው እንምጣ፡፡ አሁን ምን ይደረግ? ከችግሮቹ መፍትሔውን መገመት ቢቻልም   ትንሽ ልበል፡፡ ሥራ ከፈታሁ አይቀር …

1.     አማራ ዘረኛ አለመሆኑ ጥሩ ነው፤ በጊዜያዊ ወረርሽኝ የዘላለም ባሕርይን አለመለወጥ ደግ ነው፡፡ በዚሁ መቀጠሉም ለአማራ ሰፊ ሕዝብ ይጠቅመዋል፡፡ ነገር ግን በተወሰነ ደረጃ ራሱን ሊያውቅ ይገባል፡፡ ኢትዮጵያዊነቱን ይዞ ወገኖቹን ከሚደርስባቸው እንግልትና ስቃይ ሊታደግ ካልቻለ ይህ በኢትዮጵያ መሬት በሕዝብ ብዛት ከአንደኛነት እስከ ሁለተኝነት ቦታ የሚወስድ ሕዝብ እንደቀላል ተበታትኖ መቅረቱ ነው፡፡ “ባለቤቱን ካልናቁ አጥሩን አይነቀንቁ” እንዲሉ ለምሣሌ የኅልመኞቹ ሰሞነኛ ድርጊት መነሻው የአዴፓ ተብዬው መመረዝና ካብ አይገባ ድንጋይነት እንጂ አንድም አማራ ዝምቡን እሽ ሊለው የሚገባ ግፈኛ በተለይ በአሁኑ ወቅት ሊኖር ባልተገባ - “ፍየል ከመድረሷ..” ዓይነት ነው የሆነብኝ፤ እስካሁን ላምነው ያልቻልኩት መራር እውነት፡፡ እነደመቀ መኮንን ከመስመጥ ያዳኑት ዋናተኛ ከድንጋጤው አገግሞ ገና አንድ ዓመት እንኳን ሥልጣን ላይ ሳይቆይ ይህን መሳይ ቀሽም ድራማ እንዲመደረክ መፍቀዱ በአንድ በኩል ጥሩ ሆኖ በሌላ በኩል ግን የበሉበትን ወጪት መስበርን በግልጽ የሚጠቁም ወራዳ ተግባር ነው - ከኢትዮጵያዊ ጨዋት በእጅጉ ያፈነገጠ ነውረኝነት፡፡ “ጥሩ ነው” ያልኩት ቀንድ የሚነክስ ጅብ ሥጋ የማግኘት ዕድሉ ጠባብ መሆኑን ከመረዳት አኳያ እንጂ የ12 ሽህ አባወራ ቤት መፍረሱ አስደስቶኝ ሊሆን እንደማይችል ሊታወቅልኝ ይገባል፡፡ ስለሆነም ከሌሎች በመማር አማራ ራሱን ይፈልግ፡፡ እንደባህሉ “ሞረሽ! ሞረሽ!” ይባባል፡፡ በሞረሽ እየተጠራራ ለአማራ ባላቸው ጠላትነት ብቻ ለሥልት ሲሉ የተፋቀሩ የሚመስሉት ጠላቶቹ ከደገሱለት የዕልቂትና የውድመት ድግስ ራሱን ይታደግ፡፡ ለነገሩ “ስለት ድግሱን ደባ ራሱን” ይባላልና ሁሉም የየሥራውን አያጣም - በጊዜው፡፡ ያው መቼም በፋሲካ የገባችን ገረድ አኳኋን ስለምታውቁ … ምን ይባላል እንግዲህ፡፡

2.     የአማራ ድርጅቶች በአማራ ድርጅትነት መታማታቸው ካልቀረ አማራ ባልሆኑ ሰዎች ድርጅቶቻቸውንና የቆሙለትን ዓላማ ማስመታት የለባቸውም፡፡ አማራው እየተጎዳ ያለው ከጅብ በማያስጥሉ የአህያ ባል አስተኔዎች በመሆኑ ጥንቃቄ ይደረግ፡፡ አዴፓ መጋጃ እንደሆነ መቅረት የለበትም፡፡ ነፍስ ይወቅ፡፡ በወያኔና በሌሎችም የተዞረበትን አፍዝ አደንግዝ መበጣጠስ የሚችለው የተሰገሰጉበትን ጎታቾችና ሰላዮች መንጥሮ ሲያስወጣ ነው፡፡ በዚህ መልክ እንቅፋቶቹን ጠራርጎ ካላስወገደና ለአማራው በትክክል ካልቆመ ሕዝቡ እምነት እንዳጣበት ይቀጥላል፡፡ በአዴፓ ውስጥ የመሸጉ የማንኛውም (ሌላ) ድርጅት የውስጥ አርበኞችን ዛሬ ነገ ሳይል ፈልፍሎ ያውጣ፡፡ ቅቤ አንጓች አስመሳዮችን ይለይ፡፡ ደግሞም በስሞችና በፈጠራ ታሪኮች አይታለል - ወያኔ “ፍትዊ”ን “አገሩ አበረ” ማለት አያቅታትም - “ግደይ”ን “ዋቅቶላ” ብላ ጊምቢ እንደላከችው ሁሉ፡፡ አዴፓ ከሠርጎ ገቦች ጋር እየሠራ የአማራ ይቅርና የድርጅቱ ኅልውና ራሱ አጠያያቂ ነው፡፡ ይህን ያህል ግዙፍ ሕዝብ የሚወክል ድርጅት አሽከርና ገረድ ሆኖ የሚገኘው በድርጅቱ መቦርቦርና በጠላት እንደራሴዎች ነውና ይህ ጉዳይ በይደር የሚቆይ አይደለም፡፡ ሸረኞችና ሆዳሞች በሃቀኛ የአማራ ልጆች መተካት አለባቸው፡፡ ለምሣሌ አለምነው መኮንን ያለበት ድርጅት የአማራ ድርጅት ነው ቢሉኝ መቀበል ይቸግረኛል፡፡ ባጭሩ አማራን አታዋርዱት፡፡ በቁመቱ ልክ የተሰፋችሁ ካባዎች ለመሆን ገና ብዙ ይቀራችኋል፡፡ ሥነ ልቦናችሁን ለመለወጥ በጸሎትም በንባብም መታገል ነው፡፡ እርግጥ ነው - ወያኔ አማራን ስትጫወትበት የምትሾማቸው ሰዎች በአብዛኛው ከዕውቀትና ከትምህርት የተቆራረጡትንና ዘገምተኝነት የሚያጠቃቸውን የአእምሮ ህመምተኞችን ሳይቀር ነው፡፡ ነቃ ያለ ከሆነማ ነገር ሊያመጡ ነዋ! በታሪክ የተመዘገበ ብዙ ጉድ አለ - ብዙዎች አወራርደው የማይጨርሱት፡፡

 

3.     አዴፓ በማዕከላዊው መንግሥት ያለውን ውክልና ያረጋገግጥ፡፡ አሁን እየታዬ ያለው አማራን ከየቦታው የማፈናቀል ሂደት በአስቸኳይ እንዲቆም ማድረግ ካልተቻለ ነገ ለሚፈጠረው ሀገራዊ ትርምስ ዋናው ተጠያቂ ቀን ሰጠን የሚሉት ልበ-ቢሶች ብቻ ሳይሆኑ አማራን እወክላለሁ የሚለው ድርጅት ነው፡፡ ነገ የራሱን ሰዎችና የራሱን ታሪካዊ ፍርድ ይዞ መምጣቱ አይቀርም፡፡ ይህች ሀገር ጠፍታ አትጠፋም፡፡ ልደትን የፈጠረ ሞትንም ፈጥሯልና አንዘናጋ፡፡

 

       ከእምነት ኣባቴ አንድ ማለፊያ አነጋገርን ልዋስ - እውነት እውነት እላችኋለሁ - አማራን አሳምሬ አውቀዋለሁ - ጉራየን ልጨምርበትና ከመወለዴም በፊት አማራን ጠንቅቄ አውቀዋለሁ፡፡ የያዘ ይዞት እንጂ እንኳን ለራሱ ለሰውም የሚተርፍ አቅም አለው፡፡ በላይ ዘለቀን አስብ፡፡ የትናንቱን የሸንኮራውን ጀግና አስማረን አስታውስ፡፡ (የጎጃሙን?)ስንዴውን አስታውስ፡፡ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዴን አስታውስ፡፡ አንድ ጀግናው ብቻ ብዙ ታሪክ የሚሠራ ሕዝብ ነው፡፡ ያስቸገረው ከፍ ሲል የገለጥኩት የሠርጎ ገቦች ደንቃራና የጠላት ተንኮል ነው - ዓለማቀፉ የኢሉሚናቲዎች ድብቅ ሤራ ጭምር፡፡

በመሠረቱ ሁሉም ሕዝብ ጀግና ነው - ፀጉር አትሰንጥቁብኝ፡፡ የሕዝብ ፈሪ የለም፡፡ ይሁንና በመከራና በችግር መሀል ብዙ የተጓዘ፣ በገልቱና ዕንቅላፍም ልጆቹና በነባራዊ ሁኔታዎች ጥመት የተነሣ ብዙ ተስፋ የቆረጠ ሕዝብ ይበልጥ ጀግና ቢሆን ከሚያሳልፈው ተሞክሮ አንጻር አይፈረድበትም፡፡ እስራኤሎች እንዲህ እሳት የሆኑትና በ18 ሚሊዮን አጠቃላይ የሕዝብ ቁጥር ዓለምን በሁሉም ረገድ የተቆጣጠሩት መገፋትና መበደል ኅብረታቸውን ስላጸናው ነው - ምን ሩቅ አስኬደኝ በቅርብ ትግራይ ክፍለ ሀገር እያለችኝ…፡፡ ስለዚህ ነገሩ የሎሚ ተራ ተራ ጉዳይ እንጂ የጀግንነት ብቻም አይደለም - ከመንፈስና ከውዝፍ ዕዳ ክፍያ ጋር የሚያያዙ ብዙ ምሥጢሮችም አሉበት፡፡ እናም ሤረኞችም ሆናችሁ ጊዜያችን ነው ባዮች እያስተዋላችሁ ብትጓዙ ትንቢትን ሙሉ በሙሉ ማስቀረት ባይቻልም የመስዋዕትነትን መጠን መቀነስ ይቻላልና በጊዜያዊ ድል እየፈነደቃችሁ መጠጊያና መሸሻ የሌለውን ሕዝብ ከማስለቀስ ተቆጠቡ፡፡ ለዚህ ያልተባረከ ወንበር የበቃችሁት በአማራውም መስዋዕትነት ነውና ብዙ አትነብርሩ፡፡ ወንድማዊ ምክሬ ነው - ነገ የለሁም፡፡ ዛሬ እያለሁ ስሙኝ፡፡

 ዝም ብዬ እንደነበር ዝም እላለሁ፡፡  ዕድለኞች ከሆን … እንገናኝ ይሆናል፡፡ ጆሮ ያለው ይስማ፤ ዕንቅልፋሙም ዕንቅልፉን ይድቃ፡፡ ሲሞት ይነቃና ይነሳል፡፡ ቻው፡፡

ለማንኛውም አስተያየት yinegal3@gmail.com

   11 “በምትገቡበት ማንኛውም ከተማ ወይም መንደር መልእክቱን መስማት የሚገባውን ሰው ፈልጉ፤ እስክትወጡም ድረስ እዚያው ቆዩ። 12  ወደ ቤትም ስትገቡ ቤተሰቡን ሰላም በሉ።13  ቤቱ የሚገባው ሆኖ ከተገኘ ሰላማችሁ ይድረሰው፤ የማይገባው ከሆነ ግን ሰላማችሁ ወደ እናንተ ይመለስ። 14  የሚቀበላችሁ ወይም ቃላችሁን የሚሰማ ሰው ካጣችሁ ከዚያ ቤት ወይም ከተማ ስትወጡ፣ የእግራችሁን አቧራ አራግፉ።  15  እውነት እላችኋለሁ፣ በፍርድ ቀን ከዚያች ከተማ ይልቅ ለሰዶምና ለገሞራ+ ይቀልላቸዋል።     ማቴዎስ 10፡ 11 - 15

Saturday, October 10, 2020

ድንቁርና የተባለ የአብይ አሕመድ ሸቀጥ ዲሲ ውስጥ ለገበያ ቀርቦ ሲታይ ዋለ ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay) የድንቁርና ሱሰኛነት Saturday, October 10, 2020

 

ድንቁርና የተባለ የአብይ አሕመድ ሸቀጥ ዲሲ ውስጥ ለገበያ ቀርቦ ሲታይ ዋለ

ጌታቸው ረዳ

(Ethiopian Semay)

የድንቁርና ሱሰኛነት

Saturday, October 10, 2020



ድንቁርና ማለት ምን ማለት ነው? የሚል ብትጠየቁ ዘርፈ ብዙ ተርጉም ያለው ቢሆንም ድንቁርና ማለት በራሳችን ላይ የምንጭነው ራስን በራስ የማታለያ ባሕሪ ነው።

ድንቁርናን ለመሸጥ የድንቁርና ጣዕም ያጣጣሙ ደንቆሮ ቸርቻሪዎች መፈለግ የግድ ነው። እነዚህ የድንቁርና ሸመተኞችና ቸርቻሪዎች አሜሪካ ዋሺንግተን ዲሲ ውስጥ ዛሬ ቅዳሜ October 10, 2020 የአብይ አሕመድን የድንቁርናን ጣዕም በጭፈራ ሲገልጹ  በቪዲዮ አይተናቸዋል።

 በሚገርም ሁኔታ ደግሞ የኢትዮጵያ ቀንደኛ ጠላቶች የሆኑትን የሻዕቢያ ባለሠልጣናትን አድናቂ የሆነው አሳዛኙ “የታሪክ ይፍረደን ዘፋኙ!?” “የዛሬው የአቢቹ አድናቂ” “ባለሁለት ምላሱ በአዝማሪው በሻምበል በላይነህ” አጫፋሪነት የታጅበው የድንቁርና ሸቀጣቸውን “በስዕለ ድምጽ” ያሰራጩትን የድጋፍ ሰልፋቸውን አይቼ ተገረምኩኝ።

ትዕይንቱ ያስታወሰኝ ወደ ግንቦት 7 ወደ ሗላ ከጥቂት አመታት በፊት ወደ እነ ብርሃኑ ነጋ እና ንአምን ዘለቀ የሻዕቢያ ባንዴራ እያውለበለቡ ሲያስቁንና ሲያበሽቁን የነበረውን አሳፋሪው የሻዕብያና የግንቦት 7 ጥምረት ሲያደርጉት የነበረው ሰላማዊ ሰልፍ በትዝታ እንዳስታውስ አደረገኝ። እዚህ ሰልፍም የተደገመው ያው ሻዕቢያ በማያገባው አገር ገብቶ ደምጽ ሲያስተጋባ ከውስጥ በጥምረት የተቀናጀ ሰልፍ እንደሆነ የሚያሳየው ባንዴራቸው አብሮ ከኢትዮጵያ ባንዴራ ጎን እኩል ሲውለበለብ ማየት በአገሩ ውስጥ ያልፈቀደውን መብትና ትዕይነተ ሕዝብ ኢትዮጵያ ውስጥ ጣልቃ ገብቶ ሊፈተፍት የፈቀደው ማን ነው የሚል ትልቅ ጥያቄና ስጋት የሚጭር ነው።

 አብይ አሕመድ መሪያችን ነው የሚለው የ2013  ለገበያ ቀርበው ድንቁርና ‘ያውም ሆን ተብሎ’ ‘ድንቁርናን መታገሱ’ (ዊልፉል ኢግኖራንስ) በሕግ መጠየቅ የሚገባቸው እነ አብይ አሕመድ የመሳሰሉ ግዙፋን ወንጀለኞችን ወንጀላቸው እንዲረሳና እንዲቀጥሉበት ማበረታታት ነው። የድንቁርና ቸርቻሪዎች ሚሊዮኖች በርሃብ በታረዙባት አገር እና በሃይማኖታቸውና በነገዳቸው እየደረሰባቸው ያለውን ዓለም ያወቀው ዕልቂት እየተካሄደባት ባለቺው ኢትዮጵያ ያውም በስደት አገር በመሃል አሜሪካ ውስጥ በሙዚቃ እየታጀቡ አደባበይ ለላይ አሳፋሪ ደስታቸውን በሙዚቃ ጭፈራ ሲያስተጋቡ ማየት ሆን ብለው እያዩ ያሉትን ዕልቂት ላለማየት ወስነው በተጠለሉባት አሜሪካ ምድር እንዲህ ያለ የጥጋብ ጭፈራ ውስጥ ገብተው ማየት ሆን ብለው ራሳቸውን እውነትን ከመማር ተቆጥበዋል።

 ይህም  በሕግ ዓይን deliberate disregard of the facts” እያዩ እና እየሰሙ ሰምተው እንዳልሰሙና አይተው እንዳላዩ በሞራልም በሕግና በታሪክ ያስቀጣል (ሕግ ቢኖር)።  

ኢትዮጵያ ውስጥ እየተካሄደ ያለው የችለማ ዘመን የኢትዮጵያውያኖች ጭፍጨፋ ርሃብና ስደት ከመጤፍ ባይቆጥሩትም፡ እዚህ አሜሪካ በቫይረስ በሸታ ደስታዋን በተነጠቀቺውና ስራ በታጣባት ምድር ዋሺንግተን እና አካባቢዋ እየኖሩ እንዲህ ያለ የጥጋብ ጭፈራ ማንጸባረቅ ካሁን በፊት እንዳየናቸው ሁሉ የነዚህም እንዲሁ የፍትሕ ትርጉም ፤ የአገር ትርጉም ከጠላት ባንዴራ ጋር አብሮ መጨፈር እጅግ ዘግናኝ መሆኑን ለደነቆሩ ሰዎች ለማስረዳት ከባድ ነው።

ዋና ተልዕኮአቸው ልክ እንደመሪያቸው አብይ አሕመድና ልክ እንደ ተባባሪያቸው ሻዕቢያ “ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ” እያሉ ፤ ራሳቸውን በጥልቅ የድንቁርና ባሕር ውስጥ እየዋኙ ፤ድሉዥን ውስጥ ገብተው’ የማይዳሰሰውን በመዳሰስ ላይ ናቸው። በሃዘን ድባብ በተወረረች አገር ኢትዮጵያ ላይ ጭፈራ የሚጨፍሩ እንዲህ ያሉ ጨፋሪዎች ሲያዩ ወላጆቻችን ትግሬዎች  “ጨርቁ ዝደርበየ ዕቡድ” (ጨርቁን የጣለ ዕብድ) ይሉታል።

አብይን ለመክሰስ በር የተዘጋባትን “ፍትሕ” ፤ ድምጽዋን ለማፈን የተነሳው ዋሺንገተን የተበሰበው “የብዝሃነት ድንቁርና” የሚነገረን ነገር  ‘አገራችን ውስጥ ለ29 አመት የዘለቀ የወንጀለኞች ሥርዓት ዛሬ ሥልጣኑን ላለመልቀቅና በወንጀል እንዳይጠየቅ የሚያደርጉት ጥረት ፤ በጉራጌው ፤ በጋሞውና በክርስትያኖች ህይወት ጥቃት እንዲፈጽሙ ለማድረግ መሪያችን ነው የሚሉትን አበይ አሕመድ ድሮ በሕቡእ የጥፋት ሃይሎች አባል ሆኖ (በሁለት አለም ሰላይነቱ) ሲያደራጅና ምስጢር ሲያቀብላቸው የነበሩትን ነብሰገዳዮች ጓዶቹ ከውጭ አገሮች ወደ አገር ውስጥ ያለ ምንም ውል እንዲገቡ በመፍቀድ፤  የሰለጠኑ የመንግሥት ወታደሮች ጠባቂ መድቦላቸው ዳግም ወንጀል እንዲፈጽሙ በማድረግ በሺዎቹ የሚቆጠሩ ዜጎች እንደ እንሰሳ ታርደው የዘርና የሃይማኖት ፍጅት እንዲከናወን ያደረገው ተጠያቂው መሪያቸውን ለመከላከል ነው።  

የአባ ጂፋር አድናቂው “የበሻሻው ንጉሥ አብይ አሕመድን” በመደገፍ በሻዕቢያ ባንዴራና ሁለት ዓይነት ይዘት ያላቸው የኢትዮጵያ ባንዴራ በያዙ ኢትዮጵያውያን እና በሻዕቢያ ኤርትራኖች ጭፈራ እየጨፈሩ ከንቱ ዝላይ ቢደረግም ውሎ አድሮ አብይ አሕመድ ከወንጀል ተጠያቂነት ሊደብቁት ከቶ አይቻላቸውም።  “በደንቁርና ሱሰኞች” እውነታዎች ችላ ቢባሉም  መኖራቸው አያቆሙም!

አመሰግናለሁ።

ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)





Friday, October 9, 2020

የአእምሮ ስውር ቦታና ክሕደት (ዲናያል) ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay) October 09, 2020

 

የአእምሮ ስውር ቦታና ክሕደት (ዲናያል)

ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)

October 09, 2020

የአእምሮ ስውር ቦታ ፈረንጆች ሜንታል “ብላይንድ እሥፓት” የሚሉት ጭፍን ሥፍራ ነው። የዘረኝነት ባህሪን የሚያካሂዱ ሰዎች እራሳቸውን እንደ ዘረኛ የማያዩበት ምክንያት በዚህ ክፍል የሚከናወን የክሕደት ውሳኔ ነው። ሰዎች እኛ ዘንድ እንዲህ ያለ ዘረኝነት የለም፤ ዘረኛነት እኛ ጋር ቦታ የለውም ፤ ዘረኛነት እነ እገሌ ናቸው የሚለው ጭፍን ክሕደት የሚከራከሩበት ምክንያቱም ነገርየው በራሳቸው መንደር ሲከሰትና ወደ እራሳቸው ባህሪ ሲመጣ በመሠረቱ “የአእምሮ ስውር ቦታ” አላቸውና ሮጠው የሚወሸቁበት “የአእምሮ ስውር ቦታ በሚባለው የሕሊና ክፍል” ጋር ነው።

ብዙውን ጊዜ መኪና ነጂዎች ለጉዳት የሚዳረጉት ከጎን ግራ በኩል (በግራ በኩል ለሚነዱ አገሮች) ያለውን ለዕይታቸው በጣም ስውር ቦታ በመሆኑ መኪናው አጠገባቸው እያለፈ መሆኑን እንኳ ማየት ስለማያስችላቸው “ለአደጋ ይጋለጣሉ”።አንዳንድ ማሕበረሰዎች በማሕበረሰባቸው ውስጥ ሰላማዊ እንጂ ዘራፊ፤ ነብሰገዳይ፤ ዘረኛ፤ አመጸኛ የለንም የሚል ድምዳሜ ስለሚደርሱ በማሕበረሰቡ ውስጥ ቀስ በቀስ እየተፈለፈለ የሚያድገው ይህ ክፍል በማሕበረሰቡ ምሁራን ክሕደት ምክንያት ወደ አደገኛ ቡድን እና ወንጀለኛ ሆኖ የማደግ ዕደል የመከሰቱ ዕውነታ እውን ይሆናል። አንድ ነገር መከሰቱን ያለማመን በማሕበረሰቡም ሆነ በሌላው አጎራባች ማሕበረሰብ ላይ የከፋ አደጋ ያስከትላል። ኦሮሞ አክራሪዎች እየተበራከቱ ነው ፕሪ-ፕሮፓጋንዳቸውን ባጭር መዋጋት አለብን ብለን ስንል ሰፊው ኦሮሞ ቦታ አይሰጣቸውም “የትም አይደርስም” እየተባለ ይኼው አሁን ላለው ሁኔታ ደርሰናል። እንዲህ ያለውን ክርክር የገጠሙን ብዙዎቹ አማራዎች ናቸው። አክራሪዎችን በድጋፍ ቆመው እኛ ሲሞግቱን ሲዘልፉን የነበሩት ብዙዎቹ አማራዎች ነበሩ። አማራ ወጣት ላይ እየታየ ያለው አክራሪነትም ዉሎ አድሮ ከጫጩትነት ወደ ዘንዶነት ማደጉ አይቀሬ ነው። ይህ የሚሆነው እኔ እየሞገቱኝ ያሉት ሰዎች “ወያኔ እንጂ አማራ በዚህ ስራ በፍጹም አይታለምም አይሳተፍም” የሚሉ የክሕደት ቁልቁለት የሚጓዙት ክፍሎች ናቸው።

 

በቅርቡ ባሕረዳር ከተማ በአክራሪ አማራዎች ትግሬዎች ውጡ የሚለው የተበተነው ወረቀት ሰብስበው የለቀሙት የመንግሥት ወታደሮች ናቸው፡ ይህንን በሚመለከት በለጠፍኩት አስተያት ላይ ብዙ አማራዎች ጣታቸውን የቀሰሩት “አማራ አክራሪ ክፍል የለውም” ፤ ምናልባት ተከስቶ ከሆነ “በወያኔዎች የተደረገ ሴራ ነው” ፤ ብለው ሲከራከሩ አንብቤአለሁ። አንዳንዶቹም እኛ አማራዎች ዘረኝነት አይነካንም ይልና መደምደሚያው ላይ “ቅማላም ትግሬ” እያሉ የትግሬ ጥላቻቸው በኔ ላይ ሲያዘንብ አይቻለሁ። ያ ጽሑፍ ሕዝቡ እንዲመለከተው በሚል አላነሳሁትም፤ አሁንም አለ። ይህ ሰው በዘረኝነት ባሕሪ የሚዋኝ መሆኑን ጥሩ ምሳሌ የሚሆነው የዘረኝነት ባህሪ የሚያጠቃቸው ሰዎች እራሳቸውን ማየት የማይችሉበት “የአእምሮ ስውር ቦታ” ላይ ስለሚገኙ ነው።

 

“የአእምሮ ስውር ቦታ” ባለው አጥር ውስጥ የሚገኙ ሰዎች በደረሰባቸው ተመሳሳይ የጥቃት ባህሪ ምክንያት ያንን ጥቃታቸው፤ውርደታቸውና የበታችነት ስሜትና ቁጭታቸውን ለመወጣት ሲሉ በራሳቸው ላይ የተፈጸመ ዘረኝነት በሌሎች ላይ እራሳቸው ሲደግሙት እናያለን። እስራኤሎች በፍልስጥኤም ህጻናትና አዛውንቶች ላይ፤ ደቡብ አፍሪካ ጥቁሮች ባፍሪካ ጥቁር ስደተኞች ላይ የሚያሳዩት የዘረኝት ነጸብራቅና ግፍ ፤ መነሻው በዘረኝት ተጠቅተው ስለነበር ያንኑ የደረሰባቸው የጥላቻ ግፋና ባሕሪ በሌሎች ላይ ሲወጡት ማየት እኔም አምንበታለሁ የሕሊና ተመራማሪዎችም የሚያምኑት እውነታ ነው።

 

አማራዎች እስካሁን ድረስ በዘረኝት እየተቀጠቀጡ ዘልቀውታል፤ መቋጫም አልተገኘለትም። አማራዎች እራሳቸው ሊያቆሙት አልተቻላቸውም፤ እው ነታው ይህ ነው። አማራ ሪፑብሊክ አገር አንመሰርታለን የሚሉ ወጣቶች አላየንም አልሰማንም የምትሉ አማራ ምሁራን ካለችሁ ያው እናንተም በዚያ ክሕደት ውስጥ መሆናችሁ የሳየኛል። እንዲህ ያለ ሕሊና የሚያንጸባርቁ አማራ ወጣቶች ከሌሎች ኢትዮጵያውያኖች ጋር ለመኖር አንፈልግም ከሚል ከጥላች ሌላ ትርጉሙ ምንድን ሊሆን ይችላል? አንዲህ ያሉ አማራዎች ያበቀለች የአማራ ክልል “ከክልላችን ውጡ” የሚል ቅስቀሳ አያደርጉም ማለት ክሕደት ነው።

የአማራ ወጣት ያደገው መለስ ዜናዊና ኢሳያስ አፈወርቂ የሰጥዋቸውን ኤርትራን ያልጨመረች ቆራጣዋን የኢትዮጵያን የቆዳ ስፋት (ካርታ) አክብረው በየከናቲራቸው፤በፌስቡክ ገጻቸው፤በየቤታቸውና ሕዝባዊና ሰላማዊ ሰልፍ ሲደረግ ያንን ቆራጣ ካርታ ሲያከብሩ ይታያሉ፤ ያደጉበት ትምሕርት ሥርዓት “ወያኔና ፋሺሰታዊ ትምሕርቱን” ተቀብለው “ብሔር፤ብሔረሰብ ሕዝቦች” ሲሉ ይደመጣሉ፡ የኤርትራ ባንዴራ ሲያውለበልቡ አይተናል፡ ፋሺዝም ሲደግፉ አይተናል፤ ፋሺስቱን አብይ አሕመድ መሪያችን እያሉ ከናቲራቸው ላይ አሸብርቀውት ለብሰው በየፌስቡኩ የሚታዩ አማራ ወጣቶች አይተናል። ይህ ሁሉ ስንመለከት የአማራ ወጣት በዘረኛነት አልተበረዘም/አልተበከለም ፤ ዘረኛ ሊሆን አይችልም ብለው የሚከራከሩ ሰዎች ወጣቶቻውን በቅጡ መፈተሽ ያልፈለጉ “በአእምሮ ስውር ቦታ”ውስጥ የመወሸቃቸው ማሳያ ነው። ባህርዳር ጎንደር፤ወሎ፤አዲስ አባባ፤ ባሌ፤ ወለጋ ጂማ ወዘተ… ሰላም ነው ..ወዘተ ምንም ዘረኛነት የለም ወዘተ… የሚሉ ሰዎች አንብቤአለሁ፤ አጠገባቸው ላይ እያንዣበበ ያለው ጥቁሩ ዳመና ያንን ማየት አልተቻላቸውም። የሚገርመው ነገር ከራሳቸው ውጭ በሌላ ሰው ሲፈፀሙ ሲያዩ እነዚያን ባህሪዎች በሌሎች እንጂ እነሱ ተሰታፊ እንዳልሆኑ ያምናሉ።ለዚህ ነው አእምሮ የአደጋ ስውር ቦታ መወሸቂያ ነው የምለውም ለዚህ ነው።

 

ወጣት አማራዎች ውስጥ ዘረኞች ወይንም ጸረ ትግሬነት ባሕሪ የላቸውም ብለው ተከራክረውኛል። በየ ፌስቡኩና ዩቱብ አማራዎች ራሳቸው በትግሬዎች እና በሌሎች የሚያንጸባርቁት ባሕሪ አቅርብ ብትሉኝ አቀርባለሁ። አማራ እንኳን “ ለቅማላም ትግሬ ለጋላም መጠለያ ሆነናል” ብሎ የጻፉልኝ አማራ አለ። አለ፤ ስትል አማራ መሆኑን እንዴት አወቅክ የሚል የሽፋን መከራከሪያ ያቀርባሉ። የዘረኝነት ባህሪን የሚከላከሉ ሰዎች እራሳቸውን የቻሉ ድብቅ ዘረኞች የመሆናቸውን ምልክት ነው። አጠቃላይ ድምደማቸው “አይደረግም” የሚል ድምዳሜ ይደርሳሉ። ምክንያቱም ወደ እራሳቸው ባህሪ ሲመጣ ጥሩ “የአእምሮ ስውር ቦታ” አላቸውና አድራጊው ሌላ እንጂ ከራሳቸው ወገን እንደማይከሰት እርግጣኖች ሆነው ይከራከራሉ። እስኪ አንድ ቪዲዮ እንድታዩት ልስጣችሁ-

ትግሬ ውሽማ እንጂ ባል አይሆንም https://youtu.be/duahOhloZP8

 

"ይጠመቃል በጋን ይጠጣል በዋንጫ እንዴት ነሽ ወልዲያ የትግሬዎች መቅጫ" . “ይጠመቃል በጋን ይጠጣል በዋንጫ እንዴት ነሽ ወልዲያ የትግሬዎች መቅጫ” ከሚለው ወሎየ ገጣሚው* በዚህ ዘረኛ ቅስቀሳ የተደሰተ አማራ ወጣት እንዲህ ይላል፤ “"አቤት ልቤን ነው ቂቤ ያጠጣልኝ*! ሲል የዘረኛነት ደስታውን ገልጿል። ለ29 አመት ኢትዮጵያ ወጣትና አማራ ወጣት ጭምር ከዚህ በሽታ ነፃ ነው ማለት በግብዝ ክሕደት መጓዝ ነው።

 

እንዲህ ያለውን የጥላቻ የፕሮፓጋንዳ እየቀዱ በየቱዩቡ ላይ የሚለጥፉት አማራ ወጣቶች አማራ ወጣት አልተበከለም የምትሉን ንጹሃኖች ይህ መልእክት ስንቱን ወጣት መበከል እንደሚችል ለመገመት አስቸጋሪ አይደለም። እንዲህ ያለ ነጸብራቅ የምን ውጤት ይመስላችሗል? የምሬት፤ የግፍ የመበደል ውጤት ነው ወይስ ይህ ቪዲዮም እናንተ እንደምትሉት ‘የወያኔ ሴራ ነው?” በሞቴ እስኪ ንገሩኝ? በየ ዩቱቡ ላይ ቁልቃል እየቀለጠች ቁልቋሉን እያሳየች “ትግሬ ቁልቋል በሊታ፤አምበጣ በሊታ፤ ቅማላሙ ትግሬ” እያለች የለጠፈቺው በዕድሜዋ በጣም ወጣት ሎጋ የሆነች አማራ ለበርካታ ጊዜ መነጋገርያ የነበረቺው ይህች ወጣት በጀግንነት ሰይመዋት በየፓልቶኩና በየ ዩቱብ ሲጋብዟት የነበረቺው አማራ ወጣት ትዝ አይላችሁም? ጎጃሜ ነኝ የሚል ዮኒ ማኛ የተባለው “ቅማላም ትግሬ አምበጣ በሊታ” እያለ ሲሳደብ ሰምታችሁ አታውቁም? ይህ ሰው አማራ ወጣት አልበከለም ብላችሁ ታስባላችሁ? እንዲህ ያለ ወጣት የ29 አመት የሳብቨርሲቭ አጠባ “ሰለባ ሆኖ” በዛው ርዕዮት ማደጉን ምልክት አይመስላቸሁም? አንዳንዶቹ መረን የለቀቁ ዘረኛ የአማራ ወጣቶች የሚጽፉትን የሚናገሩትን ሰምታችሁ አታውቁም፤ አማራ ወጣት በዘረኛነት ሊበከል አይችልም፤ አይበከልም ፤ አልተበከለም ማለት ምን ማለት ነው?

ከላይ የተመለከታችሁት ቪዲዮ በግልባጩ በትግሬዎች ቢነገር (ተደርጓልም) አማራዎች ድርጊቱ ከራሳቸው ውጭ በሌላ ሰው ሲሰሙት እነዚያን ባህሪዎች እንደ ዘረኛ ያዩዋቸው ይሆን ወይስ ምንም ማለት አይደለም ብለው ይደመድማሉ? መታወስ ያለበት ዋናው ነገር ለ29 አመት የተሰራጨው የፏሲሰቶች ትምህርት ምንም ቢዘገይም ብዙዎቹ ወጣቶች የነገድ ፍቅር ስለሚያጠምዳቸው ዘረኞች መሆቸውን በሚነገራቸው ጊዜ ዘመዶቻቸውም ይሁን እራሳቸው “ዓይነ ስውር ቦታቻውን” (ዳርክ-እስፓት) ማየት አይችሉም ። በዘረኛነት እየተቀጠቀጠ ያደገ ማሕበረሰብ ወጣት ለምን ዘረኛ እንደሚሆን በሚቀጥለው ጽሑፌ በማስረጃ ኢትዮጵያ ውስጥ ያተየው እና ለወደፊቱ የሚታየው በየክልሉ/አፓርታይድ/ ቦታዎች/ ቅሪቶቹ ለረዢም ጊዜ እኛ ጋር እንዴት እንደሚቆዩ አቀ ርባለሁ። ተከታተሉ!

አመሰግናለሁ

ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)

 

 


Thursday, October 8, 2020

የባሕርዳር አማራ አክራሪዎች ትግሬ የሚባል ሁሉ እስከ ጥቅምት 4 ቀን አገራችንን ለቃችሁ ውጡ የሚል ወረቀት በትነዋል፡ መስከረም 28/2013ከጌታቸው ረዳ(Ethiopian Semay ድረገጽ ዋና አዘጋጅ)

 

የባሕርዳር አማራ አክራሪዎች ትግሬ የሚባል ሁሉ እስከ ጥቅምት 4 ቀን አገራችንን ለቃችሁ ውጡ የሚል ወረቀት በትነዋል፡

መስከረም 28/2013ከጌታቸው ረዳ(Ethiopian Semay ድረገጽ ዋና አዘጋጅ)

የኢትዮጵያን ሰማይ ድረገፅ ተከታታዮቼ ሆይ፡ ይህ መልዕክት ስጽፍ በሃያል ንዴት ውስጥ ሆኔ ስለጻፍኩት ምን ብየ እንደምጽፍን ስለማላውቅ መልዕክቱን ብቻ ተረዱልኝ። “ሼር” እንድታደርጉትና  አክራሪዎቹ እንዲያነብቡትም እጠይቃችሗለሁ።

 ይድረስ ባሕርዳር ለምትኖሩ አማራ አክራሪ ወጣቶች ሆይ! ይህንን መልዕክቴ ይድረሳችሁ!

ዜናው የደረሰኝ ባሕርዳር ውስጥ ከሚኖር ታናሽ ወንድሜ  ነው። አሁኢን ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ሥልክ ደውሎ ከአማራ አክራሪ ሃይሎች የተበተነ ወረቀት ትግሬዎች እስከ ጥቅምት 4/2013 ቀን ከአገራችን ውጡ የሚል የጭፍጨፋ ማስጠንቀቂያ ደርሶናል በማለት የግድያ ደወል የያዘ ወረቀት መበተኑን ወንድሜ ከባሕርዳር ከተማ አሁን ሥልክ ደውሎ ነግሮኛል።

ትግሬዎች ከአማራ ምድር ውጡ፤ለሚደርሳችሁ ግድያም ሆነ የንብረት ቃጠሎና ዘረፋ ሃላፊነቱ የናንተ ነው ፤ የትግሬ ንብረትና ቤትም ማንም ሰው እንዳይገዛቸው የሚል ወረቀት በምንኖርበት አካባቢዎች ወረቀት ተብትኗል።  መንግሥትም የትግራይ ተወላጆች በሙሉ ለነገ ስብሰባ እንድትመጡ ብሎ ጠርቶናል፡ ስማችንም አስመዝግበናል፤ ምን እንደሚያደርጉን አናውቅም፤ ብሎ አሁን በስልክ ደውሎ ስጋቱን ነግሮኛል።

ባሕርዳር ውስጥ የቀረነው ጥቂት ትግሬዎች ብቻ ነን። ብዙዎቹ ትግሬዎች ብዙ ዛቻ ሲደርሳቸው ንብረታቸው የእንዳትገዙ እየተባለ ስለተነገረ ንብረታቸው እየጣሉ ባሕርዳርን ለቅቀው ከወጡ ከወጡ አመት ሆኗቸዋል።

ዛሬ ወደ ትግራይ የሚወስድ የጎንደር መስመር መንገዱ ተዘግቷል፤ ወደ አዲስ አባባ የሚወስድ መንገዶችም ቄሮ የሚባሉ ዘግተውታል፡አስተማማኝ መንገድም አይደለም፤ በሁለቱም አቅጣጫ መውጫ የለንም። እንዳንገደል ስጋት አለን፤ ብሎ ስጋቱን  በስልክ ነግሮኛል።

አንባቢዎች ይህንን መልዕክት “ባሕርዳር ውስጥ ለሚገኙ የአማራ አክራሪ ወጣቶች” እንዲያነብቡትና እንዲደርሳቸው “በፌስቡክ “ሼር” እንድታደርጉልኝ እጠይቃለሁ። ለኔ ውለታ ብትውሉ ይህንን መድረግ ብቻ ነው የምጠይቀው!! አክራሪው አማራዎች የማስተላልፈው መልዕክት እነሆ ከዚህ በታች ይድረሳችሁ!

የሴቶችና የህጻናት ህይወት ለመዝመት እየፎከራችሁ ላላችሁ ቦቅቧቃዎቹ የአማራ አክራሪዎች ሆይ!

እኔ ጌታቸው ረዳ እብላለሁ፤ የኢትዮጵያን ሰማይ (Ethiopian Semay) ድረገጽ ዋና አዘጋጅ እና ስለ አማራ ጭቆና 6 መጽሐፍትን ጽፌአለሁ። 29 አመት እራሳችሁን መከላከል እቅቷችሁ፤ ‘ሃሞታችሁ ፈስሶ፤ ወኔአችሁ ‘ተሸማቅቆ’ በየቦታው እንደ ጅግራ የሚያሳድዷችሁን ጠላቶቻችሁን መቋቋም አቅቷችሁ፤ 29 አመት ሙሉ እስካሁን ድረስ እኔው አንድ ትግሬ ኢትዮጵአዊ ስለ እናንተው “ደህንነትና መብት” ስጮህና ስከላከልላችሁ እድሜየን ሙሉ “ስሰደብና ከትግሬ ዘመዶቼ” ስገለል፤ ብዙ ችግር ሲገጥመኝ ዛሬ አማራን የሚጨፈጭፉትን መቋቋም ሲያቅታችሁ ባሕርዳር ውስጥ ዕድሜአቸው ሙሉ የኖሩ ፤ ሰላማዊ እናቶች፤ወጣቶችና ህጻናት ትግሬዎች ስለሆኑ “ከባሕርዳር አማራ መሬት ውጡ፤ እንገድላችሗለን የምትሉትን “ወኔና ሱሪ” ዛሬ ከየት ተገኘ? በሰላማዊ ዜጎች ላይ የምታስፈራሩት ዛቻ እና የዘር ማጥፋት ዘመቻችሁ እስከምን ርቀት ድረስ ሊወስዳችሁ ይችላል?

እናንተ በምታደርጉት የዘር ማጽዳት ዘመቻ ለፋሺሰቶቹ ወያኔዎች ተጨማሪ ተዋጊና ደጋፊ ሃይል እየገነባችሁላቸው መሆኑን እንድታውቁት ብቻ ልነግራችሁ እፈልጋለሁ።

አገሪቷ ወደ ጦርነት ማቅ እንደምትገባም አስቀድሜ ብዙ አመታት አስጠንቅቄ ነበር፤ ይኸየው ዛሬ “የአማራ ናዚዎች” ወኔአቸው በህጻናትና ፤ በሴቶች፤ እና በአዛዉንት ትግሬዎች ላይ የግድያ ደወል ደውላችሗል። ለማንኛወም ትግሬዎችን ከባሕረዳር አስወጥታችሁና ገድላችሁ እናንተ ባሕርዳር ውስጥ በሰላም ተንደላቅቃችሁ የምትኖሩባት ከተማ ሆና የምናይ ከሆነ ጊዜው ሲደርስ እናያለን። ለምስክርነትም ያብቃን!

የሚያሳዝነው ስጋት ግን በመልሶ የማጥቃት ግጭቱ የሚጠቁት ምስኪን ዜጎች እንጂ እናንተማ “ቦቅባቃው የናዚ እና የፋሺቶች ታሪክ የሚያሳየን” “ከፉካራና ቀረርቶ ወኔ አልፎ” ጦርነት ቢጀመር እዛው እሳት ውስጥ እንማትገኙ የታወቀ ነው። የአማራና የኦሮሞ ናዚዎች እስካሁን ድረስ ያየነው ጉልበታቸው በሴቶችና ህጻናት ላይ ሲዝቱና ሲዘምቱ ብቻ ነው፡ እናንተም እንዲሁ። ለሁም ጊዜ መስተዋቱ ሁሉም በጊዜ ያሳየናል!

ውለታ የምትውሉልኝ ሰዎች ካላችሁ ይህንን መልዕክት አክራሪዎቹ እንዲደርሳቸው “ሼር” እንድታደርጉት ታሪክ ይጠይቃችል።

ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay ድረገጽ ዋና አዘጋጅ)    

 

   

Sunday, October 4, 2020

27 አመት በወያኔ ትግሬዎች 2 አመት በ ኦሮሙማ ኦሮሞዎች በቅኝ ግዛት እየማቀቅክ የምትገኝ ኢትዮጵያዊ ሆይ ዘሬስ ቀለበት ውስጥ እነዳስገቡህ ገባህ አይደል? ጌታቸው ረዳ (Ethio Semay) October 4, 2020

 

27 አመት በወያኔ ትግሬዎች 2 አመት ኦሮሙማ ኦሮሞዎች በቅኝ ግዛት እየማቀቅክ የምትገኝ ኢትዮጵያዊ ሆይ ዘሬስ ቀለበት ውስጥ እዳስገቡህ ገባህ አይደል?

ጌታቸው ረዳ (Ethio Semay)

October 4, 2020

ወደ ርዕሴ ከመግባቴ በፊት  Ethio Semay አጋጥሞት የነበረው የቴከኒክ ችግር ወደ ነበረበት ተመልሷል። መጎብኘት ትችላላችሁ።

አሁን ወደ ጥያቄየ ልግባ።

በርዕሱ እንደምትመለከቱት 27 አመት በትግሬዎች አሁን ደግሞ በኦሮሞዎች 2 አመት ሙሉ በውስጥ የቅኝ (በአፓርታይድ) ግዛት አስተዳደር ውስጥ ተይዛ ከጣሊያኖች በከፋ ሁኔታ ሕዝቧ ፍዳውን እያየ እንደሚገኝ እንደ ዱሮው “አሌ ብላችሁ” ልትሞጉቱኝ እንደማትችሉ እርግጠና ነኝ። አሌ የሚሉ ቢኖሩ በየፌስቡኩ እና አገር ውስጥም ያው የአፓርታይዱ እበላ ባይ ወይንም ግብዝ ሕሊና የተሸከሙ ምናምነቴ አሽከሮች እዚህም እዛም አሉ። ጥያቀዬ  የወቅቱ ፓለቲካ አልገባ ብሎአቸው በአዝጋሚ ሂደት እንደምትጓዘው “tortoise/ኤሊ”  የሚንፏቀቁትን ሳይሆን ለ27 አመት ወያኔ ዛሬም ለ2 አመት ሙሉ በወያኔ እግር የተተካው የወንጀለኞችና የሽብርተኞች ስብስብ ቡድን (አብይ አሕመድ ዓሊ እራሱም አሸባሪዎች ገራፊዎች ነን ብሎ እንዳመነው እና ፍርዱን ያልተቀበለው የወንጀለኞች ስብስብ) ኦሮሞ ሪፑብሊክ ለመመስረት አገራችንን በቅኝ ግዛት ይዞ ወደ ማፍረስ አደጋ ሊወስዳት ነው ብየ ስናገር አላምንም ብላችሁ ስትፋክቱ ለከረማችሁ ኢትዮጵያዊያን ነው ጥያቄየን እንድትመልሱ የምጠይቃችሁ። አሁንስ የዚህ የወንጀለኞች ስበስብ ቡድን ምንነት ገባችሁ?

ይህ ቡድን የወያኔ አሽከር ሆኖ ለ27 አመት የሕዝባችንን የባሕል፤የሞራል እሴቶቹ እንዲላሽቅ በማድረግ ወጣቶችን ተሰምቶም ታይቶም በመይታወቅ የግብረገብ ውድቀትና የውጭ ባሕል ወረርሺኝ ተጠቂ ሆኖ፤ ወላጆቹ ያቆዩለትን ሰፊ አገር እና የባሕር ወደብ ከነሰንደቃላማዋ ጋር እየናቀ፤ የኢትዮጵያ ጠላቶች ባንዴራ እያውለበለበ “ወንድማማች ነን እያለ” የተገዢነት ባህል እንዲያዳብር ተደርጎ አሁን ላለው  ምስቅልል እና ውርደት ተዳር ጓል።

 

ሰው አደባባይ ላይ ከነነበሱ በመኪና እየጎተቱ፤ ነብሰጡር በቢላዋ እየቀደዱ ሽል ፍጥረት ገድለው የእናቶችን ኩላሊት በካራ በጥሰው መብላት የማይሰቀጥጠው ትውልድ ተከስቶ በአይናችን እያየን ይኼው ኢትዮጵያ በዚህ ዘመን ትድናለች በማይባልበት እርከን ገፍተርዋታል። አሁንስ የተከበብክበት ቀለበት ምን እንደሚመስል ጎብቶሃል? ለዚህስ ተጠያቂው ማን ነው?

ቀዳሚ ተጠያቂው ለበርካታ አመታት “ይህ ሕዝብ በጠላት ቀለበት ውስጥ ተከብቦ መግደያ መሬት ውስጥ ገብቷል እና ከጠላቶቹ  ጋር አትሞዳሞዱ “ስል ስጮህ” እኔን እየዘለፈ አጋሰሱ ምሁር አልሰማ ብሎ ይኼው የዋሁን ሕዝባችን ለስቃይ በመዳረግ ዛሬም ሐፍረት ሳይሰማው  ከገዢዎች ጋር እየጨፈረ አልመከር ብሎ አሽቸግሯል።

ትናትም ዛሬም አገራችን በቅኝ ግዛት እንድትያዝ ያደረገው ይኸየው “ኢቮሊሽኑ” ያላገባደደው ምሁር ነኝ ባዩና አንደ ቶረተይልስ የሚያዘግመው የወንጀለኞቹ ፎቶግራፎችና ንግገሮችን በየፌስቡኩ እያዳመቀ ያለ ምንም ሐፍረት የሚለጥፈው “በግብዝነት የሚንሿዋሻው” መንጋ ካድሬዎቹም  አብረው እያጫፈሩ እንዳሉትም አትርሱ ።

የአማራው ሰንፍና እ’ማ አይወራ ነው።


አማራው ምሁር ጀሮ ዳባ ባለበት ወቅት፤ አማራው እንዲነሳ እና ራሱን ከሞት እንዲከላከል ብዙ መጽሐፍቶች ጽፌአለሁ።ብዙ ስደብ ፤ብዙ መነጠል ደርሶብኛል፤ አገር እንዳልገባ ተከልክያለሁ። ብዙ መስዋእት ከፍያለሁ።  ያልገባኝ ነገር እሁንም፤አሁንም ሳስበው ያልገባኝ የውርደቱ ተጠቂ እና የውርደቱ አጥቂ እራሱ አማራ ሆኖ ሳየው ፤ዛሬም እዛው እየተላወሰ ሳየው ዛሬም እንቆቁልሹ አልፈታ ብሎኛል።

(አማራ ስል (ገበሬውን አደለም) ምሁሩን ነው። ነፃነት የሚባለው ‘አስቂኝ ነፃነት’ የሐፍረት ማቅ ለብሳ “እርቃንዋ ሆና በምትወዛወዘዋ ኤርትራ ምድር” ድረስ ሄደው በ1984 ዓ.ም አስመራና ከረን ከተሞች ተገኝተው “ለኤርትራ ስቃይ” እኛ አማራዎች ነን እና “ ይቅርታ እንድታደርጉለን ይቅርታ  እንጠይቃለን’ ብለው ጥቂቶች ከጎጃም እና ከአዲስ አበባ የተመረጡ ሆዳም አማራዎች  እና ብአዴን ውስጥ የተሰገሰጉት ኤርትራኖች በሆኑት እነ ታምራት ላይኔ ፤ አዲሱ ለገሠ (ኦሮሞ) ተፈራ ዋልዋ (ኤርትራዊ ጌድኦ) ፤ በረከት ስምኦን (ኤርትራዊ) ፤ ታደሰ ካሳ (ትግሬ/የሰቆጣ አገው)፤ ካሳ ተክለብርሃን (ትግሬ/የሰቆጣ አገው) ፤ሕላዌ ዮሴፍ (ኤርትራዊ) በአማራው ስም ይቅርታ ጠይቀዋል።


በነዚህ ወንጀለኞች ትዕዛዝ በሚሊዮን የሚቆጠር አማራ ለስደት፤ ለሞትና ለስቃይ ተዳርጎ እያለ፤ ከሁለት አመት በፊት ወንጀለኞች ነን ብለው “ምለው ጥለው” አይደግመንም ብለው ሕዝብን አሞኝተው ወደ ሌላ ሥልጣን ዕርካብ ከወጡ በሗላ የከፋ ጭፍጨፋ አድርሰውበት እያለ ያም ቢሆን  ዛሬ የባሰውኑ የአማራ ወጣት ከፉከራ ውጭ ያሳየው ተጨባጭ ትግል የለም።

አማራው የዘር እና የሃይማኖት ጭፍጫፋ ተካሁዶበታል። በርካታ የዩኒቨርሲቲ አማራ ወጣት ሴቶች ታፍነው ጠፍተዋል። እንደ እነ እስክንደር እና ከነልጅዋ ጡት እያጠባች የታሰረቺው ጀግኒት አስቴር እንዲሁም ልደቱ አያሌው፤ይልቃል ጌትነት የመሳሰሉ ጥቂት ጀግኖች ይህንን የወንጀለኞች ጥርቅም በይፋ ተጋፍጠው ለእስር ሲዳረጉ፤ በጎንደር እና በጎጃም የተነሳው “ፋኖ” የተባለው  የደፋሮች ተዋጊ አልገዛም ሲል እርቅ በሚል ሰበብ አኮላሽተውት እና እምቢ ያሉትንም በሆዳም አማራ ትብብር ታድነው በጥቆማ እየተገደሉ ናቸው።

የዘመናችን ኢትዮጵያዊ አስገራሚ ጀግና አሳምነው ጽጌ የመሰለ “የወንዶች ልክ” ለሞት ተዳርጎ እያወቀ የአማራ ወጣት ከፉከራ እና ከሙዚቃ ቀረርቶ ያለፈ አገር አንቀጥቅጥ ሕዝብን የሚያነሳሳ የቁጭት እና የቁጣ የይለይለት ትግል አላደረገም። ለምን? መልስ ስጡ ልስማችሁ!

በብአዴን ተረከዝ እየተጓዘ ያለው አብን የተበለው “ጉድ ፎር ናቲንግ”  የአማራ እናቶች፤ህጻናት እና አረጋውያን የእንሰሳት ህይወት መስሎት የአማራ እናቶች ደም እና ሬሳ ሳይደርቅ፤ ሬሳቸው አፈር ሳይለብስ  ከአማራ ገዳዮች እና ጸረ ኢትትዮጵያ ሃይሎች ጋር እየተሞዳሞደ ቁጭ ብሎ ከእባብ የዕርግ እንቁላል ሲጠብቅ ማየት እጅግ የሚገርም አስደንጋጭ ክስተት ነው። አንዳንዱ ደግሞ “ፖለቲከኞች ስለሆኑ ለነሱ እንተው” የሚሉ አማራ ወጣቶች የሚጽፉትን ሳነብ “ይህ አርግፍ አድርጎ ፖለቲከኞን የማመን፤ፖለቲከኞችን ያለመወጠርና ሁሉም ነገር በነሱ ላይ የመተው  “ሲንድረም” መቼ እንደሚተው ሳስበው ችግሩ የሚፈታ አይመስለኝም።

27 አመት በወያኔ ትግሬዎች 2 አመት በ ኦሮሙማ ኦሮሞዎች በቅኝ ግዛት እየማቀቅክ የምትገኝ ኢትዮጵያዊ  ሆይ! ዘሬስ ቀለበት ውስጥ እንዳስገቡህ ገባህ አይደል? ጉሮሮየ እስኪደርቅ ሌት ተቀን ስነግርህ የነበረው ማስጠምቀቂያ እወን አልሆነም ልትለኝ ነው? የምፅአተ አማራ ደራሲ ክቡር አቶ ተክሌ የሻው እንዳሉት “ሁልጊዜ ጉድ፤ ዘወትር ጉድ፤ ዝምታና ጉዱ እስከመቸ?”

ጌታቸው ረዳ (Ethio Semay)