Saturday, December 21, 2019

የቅጥረኛው አብን ፀረ አማራ መግለጫ !!! ሠዓሊ አምሳሉ ገ /ኪዳን አርጋው (posted at Ethio Semay)


የቅጥረኛው አብን ፀረ አማራ መግለጫ !!!
ሠዓሊ አምሳሉ /ኪዳን አርጋው (posted at Ethio Semay)
አብን አሁንም በመግለጫው እንደ ወያኔ ሁሉ ምርጫው በማንኛውም ሁኔታ ቢሆን ከተያዘለት ጊዜ ሳያልፍ እንዲደረግ አጥብቆ አሳስቧል !!! አንዳንድ በአብን የተታለሉ የዋሃን ወገኖች "አብን ግን ለምንድን ነው ነጻ ፍትሐዊና ተአማኒ ምርጫ ሊደረግ በማይቻልበትና አገዛዙ እንደለመደው አጭበርብሮ 'አሸነፍኩ!' ብሎ ሊወጣ የሚችልበት ሁኔታ ባለበት ሁኔታ እንዴት 'ምርጫመደረግ አለበት !' ብሎሙጭጭሊል ቻለ ?" ብላቹህ ትጠይቁ ይሆናል፡፡

 ይሄ የአብን አቋም ማንን ተጠቃሚ ለማድረግ ታስቦ እንደተያዘ 1+1=2 ለማለት ካልሆነ በስተቀር ማብራሪያ የሚያስፈልገው አይመስለኝም፡፡ 1+1=2 ማለት ደግሞ ሕዝብን ያለቅጥ መናቅ ነው የሚሆነው፡፡ አልገባቹህም እንጅ አብን ሥራ ላይ ነው። እስከአሁን ከተቀጠረበት ወይም ከተመሠረተበት ዓላማ አንዲትም ሳይነጥብ ሥራውንና ተልእኮውን በሚገባ እየተወጣ ነው ያለው፡፡ ያኔ ወያኔ /ኢሕአዴግ ቶሎ ብሎ አብንን ባይመሠርት ኖሮ ምን ይገጥመው ምን ይውጠው እንደነበረ ሳስብ አብንን መሥርተው አማራን የማጃጃል ሥራ የመሥራታቸውን ስልት በእጅጉ እንዳደንቅ ነውየምገደደው !!!

በተለያየ ጊዜ በተደጋጋሚ ሲሉት እንደሰማቹሃቸው አብን ይሄንን አቋም የያዘበትን ምክንያት ሲገልጽ "በሕገመንግሥቱ መሠረት መንግሥት በየ አምስት ዓመቱ ምርጫ የማድረግ ግዴታ አለበት፣ ምርጫ ካልተደረገ መንግሥት የሥልጣን ዘመኑ ስለሚጠናቀቅና ሥልጣኑን ስለሚያጣ ፓርላማው ስለሚበተን ከዚያም በኋላ ወደተለየ የሽግግር መንግሥት ወይም የባለአደራ መንግሥት ወደ መመሥረት ሒደት እንድንገባ ስለምንገደድና ይሄ ደግሞ ለተጨማሪ ችግር ወይም አለመረጋጋት ስለሚዳርገን ከዚህ ይልቅ ከነችግሩም ቢሆን የግድ ምርጫ መደረግ አለበት ብለን እናምናለን!" ነው የሚሉት፡፡

 ይሄ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ይገባቹሃል አይደል ??? ይሄ ማለት ምን ማለት መሰላቹህ ብን ያድርገውና አብን "አገዛዙ ሥልጣን የያዘበት መንገድ ትክክለኛ፣ ተቀባይነት ያለውና ሕጋዊ ነው !" ብሎ ያምናል ማለት ነው፡፡ አብን አገዛዙ በሕገወጥ መንገድ ወይም ምርጫ አጭበርብሮ ሥልጣን እንደያዘ ቢያምን ኖሮ "ምርጫን ማራዘም ኢሕገመንግሥታዊ ነው፣ ሕገመንግሥቱን ይጥሳል !" አይልም ነበር፡፡ ሕገመንግሥቱ መቸ ተከብሮ ያውቅና ነው "ሕገመንግሥቱን ይጥሳል ይሽራል የሚባለው ???

" ለመሆኑ አገዛዙ ሕገመንግሥት የሚለውን ለአንድ ቀን እንኳ አክብሮ ተንቀሳቅሶ ያውቃል እንዴ ??? ልክ እኮ ሕገመንግሥቱ ሲከበርና በትክክል ሲሠራበት የኖረ አስመስለው እኮነው እነኝህ ቅጥረኞች "ሕገመንግሥት ሕገመንግሥት!" እያሉ እየለፈፉ ያሉት፡፡ ለዚህ አገዛዝ ሕገመንግሥት መጣስ ብርቁ ነው እንዴ ??? ምርጫስ ሲራዘም አሁን የመጀመሪያ ጊዜ ነው እንዴ ??? አገዛዙ ስንት ጊዜ ነው 1997 .. ምርጫ ወቅት "ቅንጅት አልረከብም አለ!" በሚል ምክንያት በተፈጠረው የምርጫ መዛባት ምክንያት ከዚያ በኋላ እስከአሁንም ድረስ አገዛዙ የአዲስ አበባንና የድሬዳዋን ከተማ አሥተዳደር እንዲሁም የአካባቢ ምርጫን ስንት ጊዜ ነው ያራዘመው???

 ገዛዙ ሕገመንግሥት ጥሶ ወይም ሽሮ አይደለም ወይ የአዲስ አበባና የድሬዳዋን ከተማ አሥተዳደሮች እንዲሁም የማሟያ ምርጫ ተመራጮች የሥልጣን ዘመናቸው ተጠናቆ እያለ እነ ታከለ ኡማን በሥልጣን ለማቆየት ያራዘመው??? አየ ቅጥረኛው አብን iii እኔ ከዚህ ቀደም እንደምታስታውሱት የወያኔው ኩሊ ዐቢይ አሕመድ አሜሪካ ላይ ዳያስፖራውን "መንግሥት ነጻ ፍትሐዊና ተአማኒ ምርጫ ለማድረግ ቆርጧል እኛ ወጥረን እየተዘጋጀን ነው፡፡ ያለው ጊዜ ሁለት መት ብቻ ነው ኋላ ችግር ላይ እንዳትወድቁ ከአሁኑ ተዘጋጁ !" እያለ ባጃጃለበት ጊዜ እኔ "አገዛዙ እንደሚለው 'ነጻ ፍትሐዊና ተአማኒ ምርጫ አደርጋለሁ !' ማለቱ ከልብ ከሆነና ለዚህም ቁርጠኛ ከሆነ የሕግ አካላት ከፓርቲ ቁጥጥር ነጻ ሳይወጡ፣ የመንግሥት ሠራተኛ ከፓርቲ አገልጋይነትና አባልነት ነጻ ሳይወጡ፣ መንግሥትና ፓርቲ ሳይነጣጠሉ፣ የምርጫ ቦርድ ኃላፊዎችና ወደ አምስት መቶ ሽህ የሚጠጋው የምርጫ አስፈጻሚ ሕዝብ በመረጣቸው አዳዲስ ከፓርቲ ወገንተኝነት ነጻ በሆኑ ኃላፊዎችና አስፈጻሚዎች ሳይተኩ 'ነጻ ፍትሐዊና ተአማኒ ምርጫ እናደርጋለን !' ማለት ፍጹም ዘበት በመሆኑና ያለው ጊዜም እነኝህን ለውጦች ወይም ተግባራት ለመፈጸም በፍጹም በቂ ባለመሆኑ ምርጫው ለሁለት ወይም ሦስት ዓመት ተራዝሞ አገዛዙ ምርጫው ከመደረጉ ሁለትና ሦስት ዓመታት በፊት እነኝህን የለውጥ ተግባራት አጠናቆ ለሕዝብ ያረጋግጥና ከዚያ በኋላ ያለ ጥርጥር ነጻ ፍትሐዊና ተአማኒ ምርጫማድረግ ይቻላል !!!" ብየ እንደነበር ታስታውሳላቹህ !!! ያልኩት አልቀረም ይሄ የወያኔ ኩሊ ዐቢይ አሕመድ ለዳያስፖራው ያንን የተናገረው ለማታለል ለማጃጃል እንጅ ከልብ ስላልነበር እነኝህን ተቋማት ነጻ የማድረግ የለውጥ ሥራ ሳይሠራ ቀርቷል፡፡

ጭራሽ እንዲያውም አጥብቆ የመያዝና የሁሉንም ተቋማት የኃላፊነት ቦታዎች በአዳዲስ ተሿሚዎች በቁጥጥር ስር የማዋል ሕገወጥ ሥራ ነው ሲሠራ የከረመው!!! ይሄም በመሆኑ አገዛዙ እነኝህን ተቋማት የመልቀቅ ወይም ነጻ እንዲሆኑ የመፍቀድ ፍላጎትና ቁርጠኝነት ጨርሶ የሌለው በመሆኑና በዚህ ሁኔታም ነጻ ፍትሐዊና ተአማኒ ምርጫፈጽሞማድረግ ስለማይቻል አሁን ላይ የምርጫ መራዘምና ያለመራዘም ጉዳይ ምንም ፋይዳ የለውም !!! ፋይዳ የሚኖረው ምርጫው ሲራዘም የሽግግር መንግሥት ወይም የባለአደራ አሥተዳደር የሚመሠረት ከሆነ ብቻ ነው !!! እነ አብን ሆየ ጭራሽ እነኝህ ተቋማት በአገዛዙ ቁጥጥር ስር እንዳሉ ወያኔ የሚሰጠውን ምክንያት እንዳለች በመድገም"ምርጫካልተደረገ ሞተን እንገኛለን !" በማለት ለወያኔ ስትራቴጂያዊ ድጋፋቸውን እየሰጡ ይገኛሉ !!! የሽግግር መንግሥት ወይም የባለአደራ መንግሥት የሚቋቋምበት ዕድል ቢኖር ተቋማቱን ከአገዛዙ ቁጥጥር ነጻ ማውጣት የሚቻልበት ዕድል ይገኝ ነበር፡፡ አብን የፈራው ይሄንን ነው፡፡

ርጫው ቢራዘም ፓርላማው ስለሚበተን፣ አገዛዙ አጭበርብሮ በሕገወጥ መንገድ የያዘው የሥልጣን ዘመን ስለሚጠናቀቅና ምርጫ እስከሚካሔድ ድረስ የሽግግር መንግሥት ወይም የባለአደራ መንግሥት መቋቋሙ ግዴታ ስለሚሆን በዚህም ወቅት አገዛዙ የመንግሥት ተቋማትን ከመቆጣጠር ውጭ ስለሚሆንና ነጻ ፍትሐዊና ተአማኒ ምርጫ ለማድረግ ዕድል ስለሚገኝ ይሄ ዕድል ከተገኘም ፀረ አማራው አገዛዝ ወያኔ /ኢሕአዴግ ስለሚያከትምለት ነው አብን ይሄ እንዳይሆን ሽንጡን ገትሮ እየተከላከለ የሚገኘው እንጅ በዚህ አሁን ባለውሁኔታምርጫመደረጉ የአማራን ሕዝብ ተጠቃሚ ስለሚያደርገው አይደለም፡፡ አብን አማራን በምን መንገድ ተጠቃሚ ሊያደርገው እንደሚችልም አንድም ነገር ሲናገሩ ታይተውምተሰምተውም አያውቁም !!! አብኖች ይሄንንም ፀረ አማራ አቋም በግልጽ እያራመዱ እያየ የሚጃጃል ሰው መኖሩ ብቻ ነው እኔን በጣም የሚገርመኝ ነገር፡፡ በተለይም ፊደል ቆጠርኩ የሚለው፡፡ ለነገሩ አሁን እንኳን ይሄ ፌስቡክ ላይ የሚንጫጫው ካድሬ ካድሬው ነው እንጅ ከሕዝቡ አብንን የሚል ያለ አይመስለኝም !!! ከፌስቡክ ወርደን መሬት ላይ ያለውን ተጨባጭሁኔታ ስናይ የምንረዳው ሃቅ ይሄንን ነው !!!

ወገኖቸ እንዲያው አትድከሙ ወያኔ /ኢሕአዴግ እስካለ ጊዜ ድረስ ነው የምላቹህ እንደ አብንና ዐሥራት ሚዲያ ያሉትን እየፈጠረ በመስጠት አማራን ማጃጃሉን ይቀጥላል እንጅ ወያኔ /ኢሕአዴግ እስካለ ጊዜ ድረስ በምንም ተአምር ቢሆን ነው የምላቹህ አማራ ነጻ ሆኖ ለመደራጀትና ለመታገል የመርፌ ቀዳዳ የምታክል ክፍተት እንኳ ይሰጣል ብላቹህ እንዳታምኑ !!! ፈጽሞ አያደርጉትም!!! ይሄንን ብላቹህ ካመናቹህ አማራ በምን ዓይነት ችግርና ፈተና ውስጥ እንዳለና እንዳሳለፈ ፈጽሞ አታውቁም አትረዱም ማለት ነው !!! ይሄም ብቻ ሳይሆን የአማራ ጠላቶች ለአማራ ያላቸውን የጥፋት ዓላማም ፈጽሞ አታውቁም አትረዱም ማለት ነው !!! እየጎዳንም ያለው ይሄ የዋህነት ነው !!! መታገል ካለብን መታገል ያለብን በከንቱ ወርቃማ ጊዜያችንን ማባከኑን ትተን በኅቡዕ አደረጃጀት ነው !!! የሚለው ጥብቅ መልእክቴ ነው !!! ድል ለአማራ ሕዝብ !!! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!! ሠዓሊ አምሳሉ /ኪዳን አርጋው amsalugkidan@gmail.com  (posted at Ethio Semay)

No comments: