Monday, December 30, 2019

መጠመዘዣ ላይ ቆመዉ መጠምዘዝ ያቃታቸዉ የዑዘይር አህዬች ጌታቸዉ ረዳ ethiopian semay ሰኞ ታሕሳስ 2011 – Dec, 30/2019


መጠመዘዣ ላይ ቆመዉ መጠምዘዝ ያቃታቸዉ የዑዘይር አህዬች
ጌታቸዉ ረዳ ethiopian semay
ሰኞ ታሕሳስ 2011 – Dec, 30/2019
ሀማ ቱማበዝብርቅርቅ ፖለቲካ”-መጣጥፉ የሚለዉ ወይንም   “Democratic Cannibalism” መጽሃፉ ላይ “Of Boring Politicos and Change of Times” ያነበብኩትን ትዝ ሲለኝ አንዳንድ የፖለቲካ ተቃዋሚ ቡድን መሪዎች እና ደጋፊዎቻቸዉ ለኢትዮጵያ ላላቸዉ ራዕይና የመታገያ ስልታቸዉ ዕዉነትምዝብርቅያለ ነዉ።  ከግንቦት 1983 . አስከ  2012 ዓ. ቅጥረኛዉ  መንግስት "ታዋቂ ምሁራን፤  ብዙዎቹ ጋዜጠኞችበሺዎቹ የሚቆጠሩ የጦር ሜዳ ጀግኖች የማረካቸዉ ወታደሮችና መኮንኖች… (ብዙ ዜጎቻችን) በወያኔ የሰቆቃ (ቶርች) ቻምበር ሲያሰቃዩበት/ሲገደሉበት በነበረበት ከባድ የጨለማ ዓመታት  ትዝታው ቁስሉ ከታሳሪዎችና ከተጠቂዎች ሳይደርቅ" ዛሬ አብይ አሕመድ የተባለ ሌላ ሴረኛ ሥልጣን ይዞ ተረኛ በመሆን የኦሮሞ መንግሥት መሥርቶ ሕዝብ ሲያሰቃይ እያዩ በምሕረት የገቡና እዛው አገር የነበሩ ምሁራን ተብየዎች የፖለቲካ ግብዝናቸዉን ይብልጥ አጠናክረው አብይ አሕመድ አዳኝና ዲሞክራት ነው እያሉ ሲሰብኩ ሳደምጣቸው የሃገሪቱ ሁኔታ ሳስበዉ ጭንቀቴ ከልቤ ጋር ሲተናነቅ ደረቴን ሰንጥቆ ለመዉጣት የሚያደርገዉ ትግል እስከ ናላየ ድረስ እንደምላጭ ስለት ሲተለትለኝ ይሰማኛል።

አሁን ያለዉ አሳዛኝ የፖለቲካ ዝብርቅርቅነትና ፋሺስታዊ ሥርዐት እየደገፉ ላሉት ጉዶች  የዑዘይር አህዬችንአንድ ለማለት ነዉ። የዑዘይር አህያ ታሪክ ላናነበባችሁ-ዑዘይር ምንድነዉ እንዳትሉ- ረዢሙን ታሪክ አላቀርበዉም። አደም የተባሉ ጸሃፊ በሐጅራ ዕትም ያቀረቡትን ዜጋ መጽሄት 1995 . ዕትሙ አቅርቦት ነበር። ዑዘይር የሰዉ ስም ነዉ።ፍልስጢማዊ ነዉ። ዑዘይር የትልልቆቹ የጫካ አህዬች/የባዝራዎቹ ሳይሆን የትንንሾቹ ለማዳ አህዮች ባለቤት ነዉ።

በዑዘይር ታሪኩ የሚጠቀሰዉ አህያ እንደ ሰዎች መናገር ይችላል። በየመንገዱ በየአፈሩ ላይ የቀሩት ኮቴዎችን ማንበብ እና አለቆቹ የማያያዩትን የማየት ችሎታ አለኝ ይላል።በዑዘይር ከመገዛቱ በፊት፤በዱላ ሲነርቱት ከነበሩት አይምሬ ጨካጮች ጌቶቹ ሲነጻጸር ዑዘይር የዋህ እና ደግ ነበር፤ ይላል አህያዉ። ዑዘይር ለማገልገል ሞቶ ቢነሳም ምንም ጌዜ ቢሆን ወገቤ ለእርሱ ዝግጁ ነዉ ይላል።

ከእለታት አንድ ቀን ዑዘይር እህያዉን እንደ በቅሎ መጭ ብሎት ወደ እሩቅ ጉዞ ሲጓዙ ወደ መድረሻቸዉ ሲቃረቡ አንዱን ከተማ አልፈዉ ለማረፍ ዕቅድ ስለነበራቸዉ በአንድ የከተማ ሰፊ መካነ መቃብሮች አካባቢ ሲደርሱ ጌታዉ ዑዘይር -አህያዉ በተቻለዉ ፍጥነት እተጣደፈ በድንገት ፍጥነት መጨመሩን ሲረዳዑዘይር”-በአህያዉ ላይሳቀ”-አህያዉ እንደፈራ ያዉቃል። ከቦታዉ እስከሚርቁ ድረስ አህያዉን በእጁ መታ መታ እያደረገ ያረጋጋዉ ጀመር። የከተማዉ ሰፊ መካነ መቃብሩን ካለፉት በሗላ ባንድ የአትክልት ሥፍራ እንዳረፉ ይተርካል።

ጌታዉ ዑዘይር ጋደም ብሎ በሀሳብ እና በማስተዋል እንደተዋጠ አህያዉ ተመለከተዉ። ዑዘይር በዓይኑ ትኩር ብሎ ስለፈራረሱት እና የተሰባበሩት አጥንቶች ፀጥ ወዳሉ ሙታኖች የሚመለከት መሆኑን ከፊቱ ይነበባል። የአላህን ችሎታ ለራሱ እንደሚያረጋግጥ ሰዉ የህችን ከተማ ከሞተች በሗላ እንዴት ሕያዉ ያደርጋታል?” ሲል ሰማሁ (አልበቂራ፡259) ይላል የዑዘይር አህያ። ዑዘይር ይህንን ቃል ተናግሮ ከማብቃቱ በፊት ከባዱና ድንገተኛ እንቅል ይዞት ጭልጥ አለ። የዑዘይር አህያም ስለጌታዉ መተከዝ ተጨንቀቆ ሲያስብ እሱም እንቅልፍ ወርሮት ከጌታዉ ጋር አብሮት አንቀላፋ።ይላል። የዑዘይር አህያ እንቅልፉን ጨርሶ ሲነሳ ዑዘይር እንዳንቀላፋ በዛዉ ሳይነሳ ተሸንፎ ቀረ። ይህች ከተማ አላህ እንዴት ሕያዉ ያደርጋታል? እያለ ነበር በዛዉ ያንቀላፋዉ። አላህም ገደለዉ። መቶ ዓመት አቆየዉና ከእዚያ አስነሳዉ። ምን ያህል ቆየህ? አለዉ።አንድ ቀን ወይንም የቀንን ከፊል ቆየሁአለ።አይደለም መቶ ዓመት ቆየህአለዉ።ወደ ምግብ እና ወደ መጠጥም ሂድ እና ያልተለወጠ መሆኑን ተመልከት አለዉ።

ወደ ጉዞዉ ሲሄድ ከድኖት የቆየዉ የወይን ጠጅ መጠጡንም እንዳለ ሳይለወጥ ቆየዉ። ዑዘይርም ወደ አህያዉ ተመለከተ። የዑይዙር አህያም ጌታዉን ዑዘይር ሲመለከት በደስታ ተዉጦ ከሞት መነሳቱን ደስ ብሎት ወዳሰበዉ መንደር ለመጓዝ ከመቶ ዓመት በፊት ተቋርጦባቸዉ ወደ ነበረዉ ጉዞ እንዲመራዉ ጠጋ ብሎ ወገቡን አለጥልጦ ፈቃደኛነቱን እና ዝግጁነቱን ለጌታዉን ለዑዘይር እንደገለጸለት ይተርካል።

 ወያነ ወደ መቀሌ ከሸሸሸ በሗላ ዛሬም ቢሆን  በፋሺሰቱና አጭበርባሪው “የሻዕቢያው የምስጢረኛ ወዳጅ” አብይ አሕመድ ጊዜዉ መብረሩን እንጂ ለመጣ ሁሉ የሚያደገድጉ ነፈዝ ኢትየጵያውያን አገራችን ከድጡ ወደ ማጡ እየተጓዘች እያወቁ  ገዳዬችን፤ ረጋጮችን፤ ዘረኞችን፤ አገር አፍራሾችን በተረኛነት በድጋሚ ይርገጡን እያሉ…’እንደ ዑዘይር አህያ’ ወገባቸዉን አለጥልጠው ጌቶቻቸዉን ለማገልገል ቁም ሲባሉ እየቆሙ መጠመዘዣዉ ላይ ቆመዉ መጠምዘዝ ያቃታቸዉ አህዬችን ስንመለከት ‘ፀጥ ብሎ’ በመታዘብ ላይ ያለዉ የሙታኖች አጥንት ዛሬም ከመቸዉም ጊዜ በበለጠ ጉደኛዉ ጊዜ ሳያስገርማቸዉ እንዳልቀረ እርግጠኛ ነኝ።

 ከታች በቅንፍ የምታነብቡት የዑዘይር አዮች ጥቅስ ላስነብባችሁና ልሰናበታችሁ።

ፕሮፈሰር መስፍን

ፕሮፈሰር መስፍን እንዲህ ይላሉ፦ 


እግዚአብሔር የኢትዮጵያን ሕዝብ ጸሎት ሰማ፤ ዓቢይ አህመድንና ለማ መገርሳን ኮርኩሮ ቀሰቀሰ፤ ቀስቅሶ አሰማራ፤ አሰማርቶ ከውስጥም ከውጭም አቀጣጠለ፤ ትንሣኤ አቆጠቆጠ፤ አረንጓዴ ብቅ አለ፤ የተስፋ ጮራ ፈነጠቀ፤ እሾሁ ጠወለገ፤ ኢትዮጵያ ዓቢይን ይዛ ቦግ አለች፡፡ለማናቸውም ከዓቢይ ጋር በክብር ቆመን ስናጅበው ደስታ ይሰማናል፤ የሚተክዙ የኢትዮጵያ ጠበኞች ናቸው፡፡ዶ/ ዓቢይ ያበርታህ!” ኢትዮጵያና ዓቢይ (ፕሮፈሰር መስፍን ወልደማሪያም)።


‘አስቴር በዳኔ

ሌላዋ የየዑዘይር አህያ ደግሞ “ፕረዚዳንት ለመሆን ወደ ምርጫ እገባለሁ” የምትለን ‘አስቴር በዳኔም  “አብይ አሕመድ “በአንድ አመት ውስጥ የሰራው ስራ የአሰር አመት ስራ ነው”  “ቆሻሻ ስለሚጠርግ ይሰደባል፤ ችግኝ ስለተከለ ይሰደባል፤ሰው ስለማያስር ይሰደባል፤ ሰው ስለማይገድል ይሰደባል፤ ሰው ስለማይሰደብ ይሰደባል፤ አንዳንድ ጊዜ ሕዝቡ ምን እንደሚፈልግ ግራ ይገባኛል!” ብላለች። “ወርቅ ቢያነጥፉለት ፋንድያ ነው የሚል ሕዝብ ነው”  እንዳሉት ሊቀመንበር መንግስቱ ሃይለማርያም;;  ኢትዮጵያ የፈራረሰች የምትመስለው “ፌስ ቡክ” ላይ ነው” ትላለች አዲስ ዘመን ከተባለው የወያኔ ቱለቱላ ጋዜጣ ቃለ መጠይቅ ቀርባ የሰጠቺው ‘ትኩሲትዋ ፖለቲከኛ’። በላያቸው ላይ ተኝተው በቡልደዘር እየፈረሰባቸው ላሉት እና ለሚፈናቀሉት፤ለሚታረዱት፤ለታመጹት ልጃገረዶች እና ባለትዳር እመቤቶች “አገራቸው እየፈራራሰች እየሄደች መሆንዋን በፌስ ቡክ ላይ ያዩት የሕልማቸው ቅዠት ነው” እያለች ነው ይህች ከያኒት።  ‘አስቴር በዳኔም በተለዋዋጭ ምላስዋ።’


ደበበ እሸቱ
ደበበ እሸቱ ሰማዕቱን ጀኔራል አሳምነው ጽጌን እንዲህ ይሰድባቸዋል።

ደበበ እሸቱ ሰማዕቱን ጀኔራል አሳምነው ጽጌን ከኮነነባቸው ዘግናኝ አገላለጾች መካከል «ሕሊና ቢስ»፤ «በአውሬያዊ ባሕሪ የተለከፈ» ፤ «ከእስር ሰንሰለት ነጻ ባወጣው ላይ የመሳሪያ ምላጭ የሳበ የሞት መልዕክተኛ» የሚሉ ልብ ሰባሪ ቃላት ይገኙበታል። ደበበ እሸቱ እንዲህ ያለ ለመስማት የሚቀፍ ውግዘትና ኩነኔ በጀኔራል አሳምነው ላይ ያወረደው የሰማዕቱ ጀኔራል ዐይን እንኳ ሳይፈርጥ ነው።
 ‘የቢሲ አማርኛ ጋዜጠኛ  ደበብን “ወደ መንግሥት እየተጠጋ ነው ብለው የሚተቹህ ሰዎች ገጥመውኛል” በማለት ጥያቄ ላቀረበለት ጥየቄ ሲመልስ
“ደግ አደረኩ! ነፃነቴን የሰጠኝ ዐቢይ ነው። ዶ/ር ዐቢይ ነው ቤተ መንግሥት ያስገባኝ። ዶ/ር ዐቢይ ነው ፕሮግራም ምራልኝ ያለኝ። ከመሸማቀቅና ማን አየኝ ከሚል መሳቀቅና መገላመጥ ያወጣኝ ዶ/ር ዐቢይ ነው። ስለዚህ ያደላሁት ወደ መንግሥት ሳይሆን ወደ ዶ/ር ዐቢይ ነው። ለእሱ ደግሞ መልሴ ደግ አደረኩ ነው።” የሚል ነበር።

ታማኝ በየነ

...ሀገሪቱ ወደ ሕግ አልባነት ስርዓት ተቀይራለች፤ ሕገ መንግስቱ እየተጣሰ ነው” እያሉ በነጋ በጠባ ሽንጣቸውን ገትረው የቅጥፈት ስዕል ለመሳል የሚያደርጉትን ከንቱ መንፈራገጥ እና ባዶ ጩኸት በአርምሞ እና በቁጭት እየተመለከትነው እንገኛለን፡፡ ይህም በሕይወት እና በሞት መካከል የሚደረግ ከንቱ መንጠራወዝ ካልሆነ በስተቀር ከወደቁ በኋላ መንፈራገጥ ለመላላጥ ነው ከሚለው የአበው ብሂል የሚያልፍ አይሆንም፡፡…ሁሉም ኢትዮጵያውያን ዓይኖቻቸውን ካገኘነው ስጦታ ላይ እንዲያተኩሩ እንጠይቃለን፡፡እንደመር፣ አንቀነስ፣….” ( ታማኝ በየነ ከአለማዮህ ገብረማርያም -አልማርያም በጋራ)

አንዱአለም አራጌ

የ አዜማው አንዱአለም አራጌ እንዲህ ይላል፡
“አብይ አሕመድ እንደኛ ሰው ነው “በሆነ አጋጣሚ ወደ ሥልጣን የወጣ እንደ ማንኛውም ፍጡር ሰው የሆነ እንጂ የተለየ ክንፍ የለውምና እባክችሁ ታገሱት” ሲል እንደ ፖለቲከኛ ሳይሆን ሕዝብን በቄስነት ባሕሪው ተማጽኗል። ያውም በሚሊየኖች ለተፈናቀሉና በሺዎች ለተገደሉ፤  ቤቶቻቸው በቡልዶዘር ለፈረሰባቸው እርጉዞች፤ እናቶች፤ ‘ትምህርታቸው የተጓጎለባቸው ህጻናትን” እና እምባ ለሚያቀርሩ አዛውንቶችን!! ነው ታገሱት እያለ “ሽምግልና ገብቶ” የሚማጸናቸው። መጠመዘዣ ላይ ቆመዉ መጠምዘዝ ያቃታቸዉ እነዚህን በምሳሌ ወስዳችሁ በሺዎቹ የሚቆጠሩ የዑዘይር አህዮችን እንዴት እንገላገላቸው?

አመሰግናለሁ
ድል ለኢትዮጵያ
ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ)




No comments: