በፎቶግራፉ ላይ ከላይ የምታዩት መፈክር መቀሌ ውስጥ ከተደረጉ ሰልፎች የተያዘ መፈክር ነው። መፍክሩ እንደምትመለከቱት “የገነባናት አገር ካላከበረችን የምታከብረን ሃገር ለመመስረት እንገደዳለን!! ድል ለሰፊው ሕዝብ!” ይላል።
ይህ መፈክር ሁለት መልዕክት የያዘ ነው። ‘አንዱ ማስፈራሪያ’ ነው “እኛ ትግሬዎች “ሕግ እየጣስን፤ የባሕር ወደብ አስዘግተን” ኢትዮጵያን ማንበርከካችንን ካልቀጠልን “የትግራይ መንግሥት እንመሰርታለን” የሚል ሲሆን፡ ‘ሁለተኛው መልዕክቱ’ ደግሞ “ኢትዮጵያን የገነባናት እኛ ትግሬዎች ብቻ ስለሆንን” መሪነቱን ካልቀጠልን “ጦርነት ከፍተን አተራምሰናት “አፍርሰናት” እንሄዳለን” ነው መልዕክቱ።
የሚገርመው ደግሞ “የገነባናት
አገር ካላከበረችን የምታከብረን
ሃገር ለመመስረት እንገደዳለን!! የሚል መፈክር ተጽፎበት ባለው መፈክር ላይ በሁለት አግዳሚ መስመሮቹ ላይ የሚታየው ‘ባንዴራ’ የ ህ ወ ሓ ት ባንዴራ እና የህ ወ ሓ ት ‘ጡንቻ’ ሃያልነትን በማስጠንቀቂያ መልክ ይታያል። በጀርመን ናዚዎች ዘመንም ሆነ ናዚዎችን የሚደግፉ የዛሬ ናዚዎች ጀርመኖች እና በሌሎች አገሮች ያሉ የናዚ አምላኪዎች ‘መፈክሮች” ይዘው ሲወጡ የናዚ ስዋስቲካ “ምልክት እና ሰንደቃላማ/” ከመፈክሮቻቸው ጋር አዳብለው ያቀርቡታል። ይህ የሚሆነው የማን ተከታዮች መሆናቸውን ለማሳየት ነው። እዚህም፤ ይህ ሥራ የህወሓት መሆኑን ከምልክቶቹ እና ከመፈክሮቹ ብቻ ሳይሆን ህወሓት ከተመሰረተበት ጀምሮ ያቀነቀነበትን የትግሉ መርሃ ግብር በማኒፌስቶው የቀረጸውን ነው ዛሬ ያቺ ጊዜ መጥታ ለግንጠላ እያስጠነቀቁን ያሉት።
እኔን ያስገረመኝ ግን ለ27 አመት ለትግሬዎች የተሰጣቸው በጠመንጃ ያገኙት ክብር ከቶ ከዚህ ወዲያ “የአዛዥ እና ናዛዥነት” ክብር ምን ዓይነት ክብር እንዲኖራቸው ይጠብቁ እንደነበር ለኔ አስገርሞኛል።
በተለያዩ ትችቶቼ እንደገለጽኩት ፋሺሰቶች ሥልጣን እና ክብር የሚፈልጉት ከጽንፍ እስከ ጽንፍ ያለው ነው። ይህ ደግሞ ለፈጣሪ ብቻ የተሰጠው እንጂ ለሰዎች የሚሰጥ ክብርም ሥልጣንም አይሆንም።
እኔ ትግሬ ነኝ። አስቀድሜ ደጋግሜ እንደነገርኳችሁ ወያኔ የትግሬነት ነገድ ሰጪ እና ከልካይ ሆኖ እራሱን በጠመንጃ በንግሥና እና
ጵጵስና መዓረግ አስቀምጦ “ትግሬ ማለት ማን ነው?” በሚል በማኒፌስቶው ውስጥ በዘረዘረው የትግሬነት መለኪያውም ይሁን ወያኔ ባላስቀመጠው መለኪያ ይህ ጸሓፊ ‘ትግሬ’ ነው (እኔ)። ስለሆነም ይህ ፋሺስት ቡድን ወደ ሃይማኖትነት ለውጠው የሚያመልኩት ሚሊዮኖች የሚሆኑ “ደናቁርት ትግሬዎች” እና የታሪክ ማፈሪያዎች የሆኑት “የትግራይ ምሁራን” ወያኔ በሚያሰምርላቸው መመሪያ አምነው ትግራይን ለመገንጠል ከፈለጉ መንገዱ ጨርቅ ያድርጋለቸው አልልም።
ምክንያቱም እኔ እና ቤተሰቦቼ እንዲሁም የኔን ትግሬነት እና ድምፅ አይወክሉምና። ቢሆንም እንዲሞክሩት ግን ከወደ መጨረሻ ጽሑፌ የሰጠሁት መፈተኛ (ማዕቀብ) ቢደረግ መፈክር ይዞ እንሚደሰቱበት ስሜት አይመጣም።
ከላይ በመፈክሩ ያየነው መልዕክት ‘መነሻው’ ግራ እና ቀኝ ማየት የተሳነው እንደ ፈረስ ወደ
ፊት የሚጋልበው የትግሬዎች “ፋሺስታዊ ትምክሕት!” ነው። ትግሬዎች ለለፉት 27 አመት እጅግ በተለጠጠ ትምክሕት ተወጥረው “እኔ የአክሱም ሥልጣኔ ብቸኛ መስራች እና ዋና ነኝ ከሚለው ክፍል አንስቶ ፤ የኢትዮጵያን ሕዝብ ህይወት እንደ “የቴሌፎን /ቺፕስ/” ዋና አንቀሳቃሽ “ጭንቅላት ነኝ” እስከሚለው ድረስ የተለጠጠ ትምክሕት ሲሰተጋባ ቆይቷል። እንዲህ ያሉ ትምክሕቶች የጦር አውርድ ናፋቂነትን አመላካች ባህሪ ነው።
ይህ ትምክሕት የሚመክተው ስለታጣ “መረን” ለቅቆ አሁን ላለው “አፈርሳችኋለሁ” ትምክሕት ዳርጎናል።
“እኔ የአጋአዚያን ምድር ልጅ ነኝ/” የሚለው ክፍልም ሆነ “ትግራይ የሚለው ስም” “ወዲ ምድሪ ወየንቲ/ የወያኔዎች ምድር ልጅ
ነኝ” የሚለውም ሆነ ‘ትግራዋይ/ትግራይ/የሚለው መጠሪያ በጊዜ ሂደት በነዚህ አዳዲስ የፈጠራ ስያሜዎች ተተክቶ ሲጠሩበት የነበረው መጠሪያ እያሟሸሸ እንዲመጣ እየጣረ ያለው ክፍል አሁን እያስተጋቡት ላለው “የትግራይ አገራዊ ምስረታ” ጋር የተያያዘ ክስተት እና ፍላጎት ነው።
ይህ በራስ ላይ ያለመተማመን እና ከንቱ ትምክሕት ያመጣው ክፉ ባሕሪ መሆኑን ግን መነጋገር አለብን። ትምክሕቱ የመነጨው በሌሎች ላይ “እኔ ሃያሉ አክሱማዊ
ባለቤትነ ነኝ” የሚለው ትምክሕቱ በሌሎቹ ነገዶች ላይ መርጨት ሲጀምር ከብዙ ትዕግሥት በኋላ በምላሹ ከሌሎች ነገዶች “ታገስ ካልሆነ ወደ ታሪክ ማስረጃ እንገባለን……” የሚል ‘መልስ
ሲያገኝ በራሱ ላይ የማንነት ጥያቄ በማስነሳት እራሱን ሰማይ በመስቀል ወደ ኮረንኮቻማ የታሪክ ጉዞ መደናበር እያመራ ነው።
ለመሆኑ “ካላከበራችሁኝ የራሴን አገር እመሰርታለሁ” የሚለው የማን አገር ነው ትግራይን እንደ ብቸኛ ባለቤት እኔ ብቻ ነኝ እያለ ያለው?
በነገራችን አማራ ነኝ የዳአማት መስራች የሚለው አማራዊ የናዚዎች ትምክሕት ልክ እንደ የትገሬ ናዚዎች
እነሱም በሚከተለው ግጥም ተዚሞ በዘፈን ተቀርጾ ለሕዝብ እየተላለፈ ያለው አደገኛው አማራዊ ትምክሕት ጨረፍ አድርጌ ከግጥሙ
ላስነብባችሁ፤ እንዲህ ይላል፡
ዐማራነን፤ ዐምሐራ ነን!
የዳ'ማኣት ባላሻራ፣
የአክሱም ዙፋን አልጋወራሽ፣
ቅመድ-ዓለም መንግሥት ወጣኝ
ቅድመ-ዓለም ጥበብ ጠንሳሽ፤
ዐማራነ ነን ሥልጡን ሕዝቦች
ከአገር በፊት አገር የሆንን፣
የኢትዮጵያ መሥራች ሕዝቦች…”
ይህ እራሳችሁ ፍረዱት። ወደ ርዕሴ ልለፍ
ይህንን የአማራ ትምክሕተኞች መበራከት እና
የትግሬዎች ትምክሕት አገራችን ወደ ችግር ያስገባታል።
ወደ ትግሬዎች ስመልሳችሁ፤ካሁን በፊት ገልጨዋለሁ።ተጋሩ ፥ ትግራይ ፥ ትግርኛ የሚባል በኢትዮጵያ ዘመነ አክሱም በታሪክ ኋላ በ10ኛው ክፍለዘመን የተከሰተ ነገድ ነው። ከዚያም በፊትም ሆነ በኋላ ትግራይ የሚባል ነጹሕ ሐረግ ፤ደም የለም። ትግርኛ የሚባል ቋንቋ የሚናገር ክፍል አለ፤ በደም በአጥንት ግን የጠራ ትግሬ የሚባል ነገድ በላቦራቶሪ ተመርምሮም ቢሆን ጭራሽ እነሱ እንደሚሉት “የጠራ” ትግሬ የሚባል ነገድ ፍጹም ሊያረጋግጡ አይችሉም።
የአክሱም/ኢትዮጵያ ሥልጣኔ “የእኛ የትግሬዎች
ብቻ ነው” የሚለው ከላይ ከሰልፉ ላይ እንደሚቃዡት ላይ
ያለው መፈክር እውነታው “ከቅዠት” አያልፍም።
ሥልጣኔን አስመልክተው ለኢትዮጵያ ሥልጣኔ መስራቾች ነን ብለው የሚያነሱት “አክሱምን” ስለሆነ የአክሱም ሥልጣኔ ቅርሳቅርሶችንና ንግዶችን እንዲሁም ወታደርነቱን/ተዋጊነቱን… የምናነሳ ከሆነ በግምባር የሚጠቀሱት ትግሬዎች ብቻ ሳይሆኑ በጥቅሉ በወቅቱ የበሩ ለኛ ግልጽ ያልሆኑ የሁሉም ነገዶች ውጤት ነው ።
አክሱምም ሆነ ላሊበላን የገነቡት አገዎች ነቸው ቢባልም እርግጠኛነት መናገር አይቻልም። ግምባር ቀደምትነት ስማቸው በነገሥታት አክሱም ተጠቅሰው መሆናቸው አውን
ነው። ትግሬዎች፤ትግሬ የሚባሉት በዚህ ስም የሚታወቁ ነገዶች የተከሰቱት ከ7ኛው ክ/ዘመ አክሱም በቤጃዎች እጅ ስትወድቅ ብቅ ያሉ ነገዶች ወይንም ስም ይዘው የተከሰቱ ነገዶች መሆናቸው አንዳንድ ተመራማሪዎች ይገምታሉ።
ትግሬዎች የሚባሉት ‘ኩናማዎችን አፋሮችን እና ሳሆዎች” አይደሉም። ካለትግሬዎች ትግርኛ ተናጋሪዎች በቀር ከላይ የተጠቀሱት ነገዶች ጥንትም በስማቸው የሚጠሩ በአክሱም ዘመነ መንግሥት ውስጥ የነበሩ የሚታወቁ ነገዶች ናቸው።
‘ትግርኛ የሚናገሩ ትግራይ ነን ብለው ራሳቸውን በበላይነት የሚያመጻድቁትን ግን በታሪክ ከጥንት ጀምሮ እንደተጠቀሱት ነገዶች የሚታወቁ ነገዶች አይደሉም። ታሪኩ እንደሚለው በዚህ ክ/ዘመን ቤጃዎች መሰረታቸው ሲጥሉ ከሱዳን ጀምሮ 6 ሥርወመንግሥቶችን ሲመሰርቱ ትግርኛ ቋንቋ ይዘው ከተከሰቱት አንደኞቹ ትግሬዎች ናቸው።
ትግሬዎች እና ስያሜአቸው ብቅ ያለው ከቤጃዎች ጋር የሚያያዙ መሆናቸው የጥንት ታሪክ ጸሐፊዎች ይከራከራሉ። የአክሱም ዘመነ መንግሥት የትግሬዎች ብቻ ነው ከተባለ፤ ጥንታዊው የመጀመሪያው የሠለጠነው የአክሱም ሥርወመንግሥት አያውቃቸውም። ይህንን ስል በማስረጃ ነው።
ቋንቋው እራሱ ቤጃዎች አክሱም ውስጥ ሰጥመው ሲቀሩ ከኗሪው ጋር እና ከአዲስ ነገዶች ጋር አብረው ከተቀላቀሉ እና ከተከለሱ (ከተዋለዱ) ወዲህ ወራሪዎቹ እዛው ያገኙትን ግዕዝን እና ቤጃዊ እንዲሁም አገዋዊ ቃላቶችን… ቀላቅለው “ትግርኛ” የሚባል ቋንቋ ፈጥረው ትግሬ/ የሚባል “’ነገድ” ፈጥረዋል። ስለሆነም ከትግሬዎች ይልቅ ለአክሱም አገዎችን ታሪክ ይጠቅሳቸዋል። ቀሲስ መንግሥቱ ጎበዜ የተባሉ ምሁር “አክሱም የማን ናት?” በሚለው ጽሑፋቸው እንዲህ ሲሉ ማስረጃውን ያጣቅሳሉ፦
“የአዶሊስ የሃውልት ላይ ጽሑፍ (Adulis Inscription)፣ የ4ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የንጉሥ ኢዛና የድንጋይ ላይ ጽሑፍ (Ezana Inscription)፣ እንዲሁም በ6ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የኮስሞስ ጽሑፍ (Christian Topography of Cosmas Indicopleustes) የአገዎችን እንጅ በዘመናችን የሚታወቁ የሌሎች ሕዝቦችን ስም አናገኝም። ከአገው ሌላ አጋዚ የሚለው ስም በጥንቱ መዛግብት የተገለጸ ሲሆን ይኸውም በአዶሊስ ሐውልት ጽሑፍ (Adulis Inscription)
ላይ የአክሱም ንጉስ ከአጋዚ ነገድ ጋር እንደተዋጋ ተጠቅሷል። በሌላ በኩል ከአክሱም መንግሥት ሥልጣኔ ጋር የቅርብ ዝምድና ሊኖራቸው ይችላል ተብለው የሚታሰቡት ሕዝቦች ስማቸው በጥንቱ የአክሱም ዘመን የታሪክ ሰነዶች አልተካተተም። ለምሳሌ የትግራይ ሕዝብ ለመጀመሪያ ጊዜ በጽሑፍ ተጠቅሶ የሚገኘው በ10ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ከአክሱም መንግሥት ማክተም በኋላ ነው።” (ሰረዝ የተጨመረ)
ስለዚህ
እኛ
የገነባት እኛ
ልናፈርሳት እንገደዳለን የሚለው የፋሺሰት ትግሬዎች
ቅዠት በታሪክ የማይደገፍ ስለሆነ እሱን ለጊዜው እንተው እና ለምንድነው ዛሬ ሃያ ሰባት አመት የፈጸሙትን የወንጀል ድርጊት ሲነቃባቸው “ደጋግመን የማረክናቸው ናቸው እኮ እየፎከሩብን
ያሉት! ያውቁናል እኮ! እንተዋወቃለን
እኮ! እስኪ የትግራይን ድምበር አንድ ‘ስንዝር’
ረግጠው ይምጡ
እና እናሳያቸዋልን! ደጋግመን
የማረክናቸው ስለሆኑ
ሃሞት ስለሌላቸው ያንን አያደርጉትም!” እያለ ደብረጽዮን ለምንድነው አጉል የመፈከር ቅዠት ገብቶ ተከታዮቹን እያሟሟቀ ያለው የሚለውን ልመልስ።
ትግሬዎች ትግሉን ሲመሰርቱ ተደጋግሞ በሐኪም ዶ/ር አሰፋ ነጋሽ እና በኔም በኩል የተናገርነው ለትግሉ መነሻቸው “ትግርኛ ተናጋሪው የትግራይ ነገድ የበላይነት” (ሌሎች ትግራይ ውስጥ ያሉት አገዎች ፥ ኩናማዎች ፥ ሳሆ ፥ ዓፋሮች ፥ “እስላሞች”… እኩል ከትግርኛ ተናጋሪ ትግሬ ክርስትያኖች እኩል ለማድረግ ሳይሆን)… ትግርኛውን አዛዥ እና ናዛዥ አድርጎ የዮሐንስ ንግሥና ሌጋሲ/ስርወመንግሥት/ ‘ለማስመለስ’ ነበር የተነሱት። ያንን እውን ለማድረግ ደግሞ ትምክሕት እና ጥላቻ አንግተው “ፋሺዝም” የተባለ ርዕዮትን አነገቡ።
ፋሺዝም ደግሞ የሚሰብከው “የመሲያኒክ” ፈለግ ነው። የመሲያኒክ ፋሺቶች ዋና ትኩረት ደግሞ “እኛ እንዲህ ነበርን በሚል የጥንት የበላይነት “አሮጋንሲ” (arrogance/ትምክሕት) እየሰበከ “በአዲስ የመሲያኒክ ስካር እጅ ተወርች የተጠመደ ትምክሕተኛ ትግራዋይ ትውልድ” መፍጠር ነው። ፈጥሮም ለመስራች ድርጅት መሪዎቹ ተገዥ ማድረግ ነው። የትግራይ ሕዝብ አሁን እየሆነው ያለው ለፋሺሰት ደርጅቱ ለወያኔ መሪዎች ተገዥ የመሆኑ ክስተት ከመነሻው በፋሺሰት መሪዎቹ የታቀደ ግብ ነው።
17 አመት ጨፍልቀው አገልጋይ ካደረጉት በኋላ፤ ዛሬ የትግራይ ሕዝብ እንደ ጥንቱ ተገድዶ ሳይሆን ወድዶ የወያኔን ደርጅት እንደ መሪ እና አዳኝ ድርጅት አድርጎ በመውሰድ አሳፋሪ ምዕራፍ ውስጥ ገብቶ የፋሺስቶቹ ዋና ተከላካይ ሆኖ አሁን የጦርነቱ ሰለባ ሆኖ እራሱ በተከተላቸው መሪዎቹ ምክንያት ችግር ውስጥ ገብቷል።
ይህ ክስተት የሚያስተውሰኝ፤ በዚህ ድርጅት የተደረጉ ወንጀሎች “ወንጀል አንዳልተፈጸመ” አድርጎ ለወንጀለኞች ተከላካይ እና አዛኝ ሆኖ የመቅረቡ ክስተት ልክ ‘በሲውድን አገር’ በእስቶኰልም ከተማ ውስጥ የታየው “ስቶክሆልም ሲንድሮም”” በመባል በስነሕሊና ተመራማሪዎች የተሰየመው ክስተት “ከትግሬዎች ሲንድሮም” እኩል ይመሳሰላል።
የእስቶክሆልም/ ስዊድን/ የባንክ ዘራፊዎች እና በዘራፊዎቹ የተጠለፉት (እስከ ግብረስጋ መገሰስ የደረሱት ታጋች “የባንኩ ሠራተኞች ሴት ታጋቾች/ሆስተጅ/” ፍቅርና ግንኙነት የሚያስታውሰን ታሪክ “የትግሬዎች ሲንድሮም” ከወያኔ ፋሺስቶች ጋር ያላቸው ግንኙነት ተመሳሳይ እና ሆኖ አግኝቼዋለሁ።
እኔ ከብዙ አመት በፊት ስለ ትግሬዎች ሲንድሮም እና የወያኔዎች ግንኙነት በሰፊው በጻፍኩትም ሆነ አቻምየለህ ታምሩ “ስለ የሃበሻ/ኢትዮጵያውያኖች/ ሲንድሮም” በሚል ስለ ስቶክሆልም ሲንድሮም በተባለ የሕሊና በሽታ የሚከሰት የሰለባዎች በሽታ ለአጋቾቻው
የሚያሳዩት ታዛዥነት
እና ፍቅር’ አቻምየለህ ታምሩ ባቀረበው ተመሳሳይ ትርጉም እኔ ካቀረብኩት ተመሳሳይነት ስላለው ሰለ አማርኛ አቀራረብ አመቺነቱን ስለ የትግሬዎች ሲንድሮም ሳቀርብ የአቻምየለህን አቀራረብ እዚህ ልጥቀስ።
“ስቶክሆልም ሲንድሮም ታጋቾች ከአጋቾቻቸው ጋር ከመላመዳቸው የተነሳ አጋቾቻቸውን አዳኝና ተከላካይ [savior and defender] አድርገው በመውሰድ ስለነሱ ያላቸው ኃዘኔታና ርህራሔ እንዲሁም አወንታዊ ስሜት በጣም ከፍ ወዳለ ፍቅር ያድግና ከአጋቾቻቸው መለየት እጅግ በጣም ከባድ የሚሆንባቸው ደረጃ ላይ የደረሱ ታጋቾችን የሚገልጽ የስነልቦና ክስተት ነው።” አችምየለህ ታምሩ።
በኔ እምነትም ብዙዎቹ ትግሬዎች በዚህ ሲንድሮም/ልክፍት/ የተለከፉ ናቸው። ስለተለከፉም አሁን በትግሬዎች እያየነው ያለው ወንጀለኞችን የመከላከል እና የወያኔዎችን ባንዴራ ማውለብልብም ሆነ ድንፋታቸው ከዚህ ልክፍት ጋር የተገናኘ ክስተት ነው። አቻምየለህ ከኔ የተለየ “የትግሬዎች ሲንድሮም’ ላቅ ብሎም በጠቅላላ ወደ “የኢትዮጵያውያን የተቃዋሚ የፖለተካ መሪዎች “በእስቶክሆልም ሲንድሮም” መያዛቸውን ይተነትነዋል ።
አቻምየለህ እንዲህ ይላል፡-
“የታገተው የኢትዮጵያ ሕዝብም በመንግሥትነት ከተሰየሙት አጋቾቹ የትግራይ ወያኔዎች ጋር እጅግ በጣም ከመላመዱ የተነሳ አጋቾቹን በግፍ ያጎሯቸውን የህሊና ሰዎች በጭካኔ ከሚመትሩበት ከጠባቡ የሰው መታረጃ ቄራ ወደሰፊው የማሰቃያ እስር ቤት ወደ ሆነችው ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲዘዋወሩ ስለፈቀዱላቸው በታጋቾቹ ወገን ያሉ ተቃዋሚ ነን የሚሉ ፖለቲከኞች አጋቾቹን ፋሽስት ወያኔዎች አዳኝና ተከላካይ አድርገው በመውሰድ መቼም ሊለቃቸው በማይችለው የአጋች ፍቅር ተለክፈው የአበሻ ሲንድሮም ውስጥ የወደቁ ይመስለኛል።” ይላል አቻም። በዚህ ትንታኔ የሚከራከር ሰው ያለ አይመስለኝም።
ወደ ትግሬዎች ስንመጣ ለየት የሚያደርገው ግን በኔ እይታ “ኢትዮጵያውያኖቹ” አጋቾቻቸውን እንደ ትግሬዎቹ “የኛ
ናቸው” አይሉዋቸውም። ልዩነታቸው ይህ ነው። ኢትዮጵያውያኖች አጋቾቻውን ተለማመዱዋቸው እንጂ “አላፈቀሩዋቸውም/
አልወደድዋቸውም/”። መለማመድ ለብቻ ነው (ጊዜ አይቶ ጊዜን የሚጠብቅ የሚለማመድ እራሱን በተንኮል ያጎነበሰ ተለማማጅ አለ)። የትግሬዎች ግን እስከ መጨረሻ ድረስ አንደ እስቶክሆልም የባንክ
ሰራተኞች ሴቶቹ ከአጋቾቻው ጋር በፍቅር ተጠምደው ጠበቃ አቁመው፤ እራሳቸውም ቆመው በአደባባይ ወንጀላቸውን እንደተላከሉላቸው ሁሉ “ትግሬዎችም የማይረባ ምክንያት እየደረደሩ” ለ27 አመት (44 የበረሃ ዘመናቸውን ጨምረን) በርካታ አሰቃቂ ወንጀል የፈጸሙ ወንጀለኞችን በትግሬዎች ከለላ ጥላ ስር ይገኛሉ።
እዚህ ላይ ባለፈው እንደገለጽኩት በድርጅቱ ውስጥ ያልታገለ የትግራይ ቤተሰብ አንድም አይኖርም። ስለዚህም “ድርጅቱ የኔ ነው/ የኛ ናቸው” የሚለው ስሜታቸው ምንጩ ዋነኛው ታሳቢ ማድረግ አለባችሁ። “የኛዎቹ አይዙዋችሁ” የሚለው የትግሬዎቹ/
በመሪነት “የእንደርታዎቹ መፈክር” ከዚህ ቤተሰባዊ “የኛነት” የተነሳ መሆኑን ልብ በሉ። ስለዚህ “በመውደድ እና
በመለማመድ” ያለው ልዩነት መገንዘብ ያስፈልጋል። ትግራዊ ቤተሰባዊነትን የመጥለፊያ ገመድነቱን አለመዘንጋት “ለትግራይ የእስቶክሆልም ሲንድሮሙ” ተጨማሪ ፍቅር ሊያዳብር የቻለበት ምክንያት ዋነኛው መስህብ “የቤተሰባዊ ትግራዋይት” የሚለው ነው።
ያ ባይሆን ኖሮ የሚከተለው ግፍ ሲፈጸም ተባባሪዎች ወይንም እኔን እስካልነካኝ በሚል የማዶ ተመልካቾች ባልሆኑ ነበር። ትግሬዎች ለ27 አመት ሥልጣን ላይ ለሕሊና በሚገርም በታሪክ ያልታየ የሥልጣን መንሰራፋት ትግሬዎች በስፋት በንግዱ በሥልጣኑ በሃብቱ በወታደራዊ ዘርፉ በጠቅላላ የህይወት ዘርፍ ሁሉ እንደይዙት ወያነ ትግራይ ትግሬዎች አንዲቆጣጠሩት ፕላኑን በማኒፌስቶው በነደፈበት አኳሃን በሚገባ በገሃድ መርቶታል።
ስለዚህም ትግሬዎች ገዢዎች ነበሩ/ዛሬም ለወደፊትም በአድልዎ እንዲጠቀሙበት የተደረገው የሃገሪቱ ሃብት (ለምሳሌ ኤፈርት የተባለ ትልቅ የካፒታል/የሃብት መዘውር) ወደ መንግሥት ካዝና እንዲገባ ካልተደረገ ለወደፊቱም ከኢትዮጵያ (ካልተነጠሉ) እንደ ደቡብ አፍሪቃ “የአፍሪካና ነጮች” በተቀሩት ዜጎች ላይ የኢኮኖሚው የበላይ የመሆናቸው ጉዳይ ቀጣይ ነው። ካልተወረሰ ‘አፓርታይዱ ቡድን ያዘጋጀላቸው የሃብት የበላይነት” ለረዢም ጊዜ ቀጣይ ነው ማለት ነው።
በሚያስከፋ መልኩ፤ ወያኔ ባቀደው የትግሉ መነሻ ተሳክቶላቸው ትግሬዎች ከሕግ ውጭ በብረት “ገዝተውናል። ቀጥቅጠውናል ፥ መዝብረውናል፤ በሥልጣን ማግጠዋል ፥ አገር አፍርሰው የባሕር ወደቦችን ዘግተው ለጎረቤት አገሮች “እንደንምበረከክ” አድርገዋል።” ከዚህ መሰሪ ስራቸው ስንመለከት እነዚህ ዜጎች ናቸው ለማለት የሚሰቀጥጥ አባባል ይሆናል።
በዚህ ሳይወሰኑ “ትግሬዎች ሲያስተዳድሩ በሺዎቹ የሚቆጠሩ ሴት እና ወንዶች ኢትዮጵያውያን በዓረብ አገር በግርድና “በባርነት” እንዲያገለግሉ ከዓረቦች ጋር እየተስማሙ ለስቃይ ዳርገዋቸዋል። እስር ቤት ውስጥ ለመግለጽ በሚያስቸግር ትምክሕት በተሞላበት “እኛ ትግሬዎች እንዲህ ነን የምናደርጋችሁ!” ፥ “ሽንታም አማራ ምን ታመጣለህ!” እያሉ እየደበደቡ ፥ በእስረኛ ገላ “ሽንት ሸንተዋል” ፥ ሴቶች ደፍረዋል። የቤተክርስትያን ታቦት በአክራሪ እስላም አሮሞ በሆነች “ሴት ከንቲባ” ትዕዛዝ ሽንት ቤት ተጥሎ ፖሊስ መካዝን ላይ አልባሌ እንዲታሸግ ተደርጓል (የወያኔ መሪዎች እነ ስብሓት ነጋ ለክርስትና ያላቸው ጥላቻ ከሚናገሩት ፈቃድ በመነሳት)።
አንባቢዎቼ በሕዝባችን
የተፈጸመው ግፍ
ደጋግምን ስንናገር
አይሰልቻችሁ፡ መነገር
አለበት!! ቁስላችን
ገና አልዳነም!
በምናኔ የሚኖሩ ቅጠል እየበሉ ከእግዚአብሔር ጋር በፀሎት የሚገናኙ የገዳማት አንስት መኖክሲቶች በወያኔ አጋንንቶች መደፈራቸው ነግረውናል። ይህ ዜና ኢሳት ላይ ቀርበው በራሳቸው አንደበት መነኮሳቱ እያለቀሱ አምርረው አብየት ብለዋል። አደለም እንዴ? እናት በልጇ ሬሳ ተቀምጣ የረዳት ያለህ አልቅሳለች።ኢትዮጵያ ለ27 አመት አገራችን በተዘጋጀላት ሞት፤ ስደት፤ ውርደት፤ አመጽ፤ እንግልት፤ እስራት፤ ድብደባ፤ ጦርነት፤ ግድያ፤ ዘረፋ፤ ክሕደት፤ ግብረሰዶማዊ ዝሙት ሞገደኛ’ ማዕበል ውስጥ ገብታ ትንገላታለች። “ፍሬደሪክ ኒቼ” እንዳለው በእነዚህ “በኩፉዎቹ ኩፉ አውሬዎች” ምክንያት ሕዝባችን አይሆኑ ሆኗል!!!
ብሔራዊ ስሜት በራቃቸው እነዚህ ‘የቀወሱ’ ሰዎች የአገራችን ሕይወት ሸምቀው ይዘውታል። ባዘጋጇቸው የጭለማ እስርቤቶች እርግብ ወጣት ሴቶችን መድፈር ሳያንሳቸው ወንዶችንም ደፍረዋል። በዚያ ግፍ ሳይረኩ እንደገና ጣሊያኖች ያላደረጉት “አውላላ ሜዳ ላይ በቆሙ የኢትዮጵያ ሸበላ ወጣቶች “እንደ ጅግራ አደን” ከሰማዩም ከፎቁም ጥይት አዝንበውላቸዋል”። መጨረሻ ላይ ሕዝባችን በእያሪኮ ጩኸት እስከ መቸ? ብሎ በመጠየቅ ዛሬ ላለው ጥገናዊ ለውጥ አምጥቷል።
ይህ ሁሉ ጉድ መፈጸሙን እያወቁ ትግሬዎች ይህን የክፉ ሁሉ
ክፉ አውሬ የሆነን ወያኔ የሚባል ወንጀለኛ ቡድን ደግፈው ወንጀለኞችን አጥልለው “እንዲገዙን አንፈቅድላቸውም ግን የኛ ናቸው እና አሳልፈን አንሰጣቸውም” ብለው የዓረና መሪዎች እንደ እነ አብርሃ ደስታ የመሳሰሉ “ወያኔ ኮትኩቶ አሳድጎ
ያስተማራቸው የትግሬ
ሊሂቃን በመገናኛ
ድረገጾች ሳይሸማቀቁ ወንጀለኞችን
በመደገፍ በግልጽ
እየጻፉ ነው።” ተራ የወያኔ ደጋፊ ጀሌ ሕዝብም የነ አብርሃ ደስታ ቅስቀሳ እየሰማ ወንጀለኞቹን
“የኛ ታጋዮቻችን ናቸው እና አሳልፈን አንሰጥም” ካልሆነ ግን “አገር እንገነጥላለን” እያለ ሰላማዊ ሰልፍ ወጥቷል።
ከዚህ ወዲያ ወዴት? የሚለው ልንጠይቅ ይገባል። ወንጀለኛን ማስጥለላቸው እና መደገፋቸው ሳይበቃ አገር እናፈርሳለን ድንፋታ በማስጠንቀቂያ
መፈክር አስነብበውናል። ከዚህ ወዲያ የአብይ አስተዳደር የሚፈተንበት ወቅት ነው። ስለዚህም የሚታገስበት አቅል ሊኖር አይገባም።
ወያኔዎች ፋሺስቶች ናቸው። ስለዚህም በደምብ ሳይዘጋጁ መላው ኢትዮጵያ ሰልፍ ወጥቶ በየቦታው እንዲያወግዛቸው ጥሪ
አቀርባለሁ። ይህ ከሆነ በኋላ ወንጀለኞችን አሳልፈው ካልሰጡ፤ መስርተነዋል ብለው እራሳቸው በመሰረቱት የፍርድ ቤቶት ትዕዛዝ ካላከበሩ ‘ከመአከላዊው
አስተዳደር እንደተገነጠሉ
ተቆጥሮ’ “በትግራይ
ላይ የባጀት
እና የምጣኔ
ሃበት ማዕቀብ እንዲሁም በደብረጽዮን እና በተቀሩት በወንጀል የተጠረጠሩት የወያኔ
ሹሞች የዝውውር ማዕቀብ
አንዲጣል ጥሪ
አቀርባለሁ።
በሰሩት ወንጀል መፀፀት ሲገባቸው እንደገና “እንተዋወቃለን እኮ!!” ሲሉ ድንፋታ በቃችሁ ተብሎ የመነገሩ ጊዜው አሁን ነው። ይህ ጥሪ ለሁለተኛ ጊዜ ነው እየጠራሁ ያለሁት። ስለዚህም ተግባራዊ ይሁን! የክፉዎቹ ክፉ አውሬ “ፋሺዝም” ለመጨረሻ ሞቴ
ሞቼ ልረፈው
ብሎ “እያሳከከው
ስለሆነ” ሞቱ
ለመሞት ተዘጋጅቷልና
“የተመኘውን አትንፈጉት”!
አመሰግናለሁ
ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ)
No comments:
Post a Comment