Tuesday, October 23, 2018

ወያኔዎች የጠለፉዋቸው የመስቀል እና የአሸንዳ በዓላት ጌታቸው ረዳ(Ethiopian Semay)



ወያኔዎች የጠለፉዋቸው የመስቀል እና የአሸንዳ በዓላት
ጌታቸው ረዳ(Ethiopian Semay)
ከላይ ያለው ፎቶ ፕሮፌሰር አስራትን የውሸት ሰነድ አዘጋጅቶ ለሞት የዳረጋቸው “ሰው መሳይ በሸንጎ” ወያኔው ደብረፅዮን ገብረሚካል ወደ መድረኩ ሲገባ “አይዞኻ ናህና” (አይዞህ የኛው ሰው!!) በማለት በፍጮት እና በጭብጫባ ወደ መነጋገሪያው መድረክ ከታጀበ በኋላ አጸፋውን በሰላምታ ሲመልስ!

ዛሬ ትግራይ ውስጥ በ2011 የተከበረው የመስቀል በዓል የደብረጽዮን ገ/ሚካል ሌላኛው ቅሌቱን እንመለከታለን። ዛሬ ባለፈው ክፍል መነጋገርያ ርዕሳችን ማለትም “የግብረሰዶም ሰንደቃላማ ምልክቶች የታዩበት የ2011 የመስቀል ደመራ በዓል አስከፊው ገጽታ እና ኦሮሞዎች እሬቻ እና ገዳ የተባሉ ሃይማኖታዊ እና አስተዳደራዊ ባሕል ኦሮሚያ ለሚለው ፖለቲካ መጠቀሚያ እና የትግሬ ወያኔዎች አሸንዳ የሚባለው ሓይማኖታዊ የጭፈራ በዓል ወደ ፖለቲካ የመጠምዘዝ አባዜአቸው ሲፈተሽ  የሚለው የመጨረሻው ክፍል እንመለከታለን።ይህ ክፍል ሳልቀጥልበት በማቆሜ አንገብጋቢ የሆኑ ወቅታዊ ትችቶች ስለነበሩ በዚያ ሳስነብባችሁ ቆይቻለሁ። ዛሬ የመጨረሻው ክፍል እንመለከታለን።

ባጠቃላይ ስንመለከት በመስቀል በዓል የታየው ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን ያሳየቺው በርከት ያሉ አሳፋሪ ትዕይንቶች እና ከዚያም አልፋ እጆችዋን ወደ ፖለቲካ በማስገባት ከአብይ አሕመድ ጋር በመሆን በሉአላዊነታችን ላይ ያሳየቺው ጣልቃ ገብነት በዝርዝር ገልጫለሁ። ያንን አንብቡ።በዛው ጽሑፍ ኦሮሞዎች በተዋህዶ ኦርቶዶክስን ላይ ፖለቲካቸው እና የግንጠላ እና የጥላቻ ባንዴራቸውን የተዋህዶ ካህናትን እና መዘምራንን በማስለበስ ከአገር፤  ሃይማኖት፤ ከሞራል እና ከታሪክ በማፈንገጥ፤ የተዋህዶ ቤ/ክርስትያን ሃይመኖት ሕግን ተጻርረው፤ እንዴት እንደጠለፍዋት አይተናል። ፖለቲካ ሃይማኖትን ጠልፎ መጠቀም እንደሌለበት አፈኞቹ ከአንገት በላይ ሲያወሩ እንሰማቸዋለን። ያ ግን እራሳቸው ሲፈጽሙት አይተናል።

በክልልቻው የሚኖሩ የኦነግ ባንዴራ የማይቀበሉ መስቀልን ለማክበር በዕለቱ የተገኙ ኦሮሞዎች ወይንም ኦሮሞ ያልሆኑ ‘ምዕመናን’ አገራዊ የሆነች በባዓሉ አብራ የምትከበረው የኢትዮጵያ ሰንደቃላማቸውን በማስወገድ በምትኩ በሃይማኖታቸው ላይ የኦነግ የግንጠላ ፖለቲካ ባንዴራ በደመራው ላይ እና በካህናቱ አልባሳት ላይ እንዲለበስ መደረጉ እና ጠቅላይ ቤተክሕነት ጽ/ቤትም በዚህ ጉዳይ አይቶ እንዳላየ መሆኑን ተችቻለሁ። ከፍተኛ ወንጀል (ኮንስፒራሲ) በመፈጸሙ የፖለቲካ ድርጅቶችም ሆኑ ጳጳሳቱ ይህንን ሴራ ተመልክተው ምንም ዓይነት መግለጫ ወይንም ተቃውሞ ወይንም ትችት በኦሮሞዎቹ ላይ አላሳዩም። ብረዛው ተቀብለውታል። የይሁንታ ምልክት ሰጥተዋል ማለት ነው። ስለ ኦሮሞዎች እና ቤተክርሰትያኒቱ ተወያይተናል። ዛሬ የምንወያየው ስለ ወያኔ እና የአሸንዳ እና የመስቀል ሃይማኖታዊ በዓላትን ትግራይ ውስጥ እንዴት ሆኖ የወያኔ ፖለቲካ መጨፈሪያ እና መስበኪያ መድረክ እንደሆነ እናያለን።

ደብረጽዮን በአዲግራት
ታሪክን ወደ ፖለቲካቸው መጠቀሚያ በማድረግ አጣምመው በመዋሸት የታወቁት ወያኔዎች ዛሬም የትግራይ ፋሺስት ወያኔ ሊቀመንበር ‘ደብረጽዮን ገብረሚካል’ አዲግራት መስቀል በዓል ተገኝቶ ‘ትግሬ ሁለተኛ ዜጋ ነበር’ በማለት በሃይማኖታዊ በዓል ላይ የድርጅት ፖለቲካ በመስበክ ወያኔዎች ለሃይማኖት ያላቸው ንቀት በማሳያት መድረኩን የአንድ የፋሺስት የፖለቲካ ድርጅት መስበኪያ እንዳገለገለ እናያለን።

ካሁን በፊት መቀሌ ከተማ በተካሄደው የኢንጂኔር በቀለ የሓዘን መግለጫ ሕዝባዊ ስብሰባ ላይ ሲደረግ ደብረፅዮን በአደባባይ የተነገረውን አስደምጬአችሁ እንደነበር ታስታውሳላችሁ። ዛሬ ደግሞ ባለፈው መስከረም 2011 አዲግራት ከተማ የተካሄደው መስቀል በዓል ላይ ተገኝቶ ያንኑ ደግሞታል። የፋሺስቶቹ አዲሱ መሪያቸው ያንን ንግግር እየደጋጋመ በሕብ ጀሮ ላይ ሊያስደምጥ ለምን እንደፈለገ ለተቺዎች ልተው እና ሃይማኖታዊ በዓልን የፖለቲካ መጠቀሚያ በማድረግ ኦነጎች የተዋህዶ ቤተክርስትያናት እና የመሳሰሉ  የጎሳ እምነቶችን፤ ተቋማት፤ እና በዓላት እንዴት እንደተጠቀሙባቸው ያየነው ያህል ወያኔዎችም አሸንዳ ብቻ ሳይሆን መስቀል በዓልም የፖለቲካ መጠቀሚያ የማድረጉ ባሕሪ ፋሺስቶች የሚያተኩሩባቸው ዒላማቸው መሆናቸውን በዝርዝር እንመለከታለን።

ወያኔው ደብረጽዮን ገ/ሚካል አዲግራት መስቀል በዓል የተገኘው ብቻውን አይደለም። የወያኔው ጳጳስ አቡነ ማትያስም አብረው ነበሩ። ለምን ከአገራችን ርዕሰ ከተማ አዲስ አባባ ይልቅ የትግራይ ውስጥ በዓሉን ሊያከብሩት መረጡ? መልሱን ለጳጳሱ ልተው። ጠባቡ ደብረጽዮን በአዲግራት ከተማ በመስቀል በዓል ተገኝቶ ንግግሩን ከመጀመሩ በፊት ወደ መድረኩ ሲገባ “አይዞኻ ናህና” (አይዞህ የኛው ሰው!!) በማለት በፍጮት እና በጭብጫባ ወደ መነጋገሪያው መድረክ ከታጀበ በኋላ በተዘጋጀለት የመነጋገሪያ ድምጽ ማጉሊያው በመጠጋት ደባሪ በሆነው የትግርኛ ቋንቋ አወጣጥ ስልቱ ንግግሩን እንዲህ ይላል።
Ethiopia True Cross 2018 - መልእኽቲ ዶር ደብረፂዮን ገብረሚካኤል ኣብ በዓል መስቀል ዓድግራት

“ክቡር ብጹእ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ እና የተከበራችሁ የሃይማኖት መሪዎች፤ የተከበራችሁ የአዲግራት ከተማ ናሪዎች፤እና ከኛው ከትግራይ ሕዝብ ጋር የመስቀል በዓል ለማክበር የተገኛችሁ ኤርትራውያን ወገኖቻችን ሁሉ። አስቀድሜ ይህ የማንነታችን መለያ ወደ ሆነው የመስቀል በዓል እንኳን አደረሳችሁ በማለት ደስታየ እገልጽላሁ። የትግራይ ሕዝብ በቋንቋው፤በባህሉ ባጠቃላይ በማንነቱ እንዲዋረድ፤ በገዛ አገሩ እንደ ሁለተኛ ዜጋ ሆኖ እንዲታይ የተደረገበት የታሪክ አጋጣሚነበር። ቋንቋው የወፍ ቋንቋ፤ ሓቀኛ ታሪኩ እየተዛባ እና ጥላሸት እየተቀባ፤የራሱ መንግሥት ትግሬዎችን በማንነታቸው የዘመተባቸው፤እንደ ባዕድ የሚያያቸው፤ የሚጠረጥራቸው እና ግፍ ሰፈጸምበት የነበረ ሕዝብ ነው።እንዲያም ሆኖ የትግራይ ሕዝብ የደረሰበት ግፍ ችሎ የሚምበረከክ ሕዝብ ስላልነበረ በየጊዜው የተፈጸሙበት ግፎችን በመጋፈጥ አንድነቱን አጠናክሮ እና አዋህዶ ባህሉ እና ማንነቱን አስጠብቆ የቆየ ‘ሃብታም ባህል እና ረዢም የስልጣኔ ባለቤት መሆኑን አስመስክሯል’።” ካለ በኋላ ከሕዝቡ ጭብጨባ እና ፍጮት ሲቀልጥ የደመጣል/ይታያል)።

በመቀጠልም እንዲህ ይላል

“የመስቀል በዓል የትግራይ ሕዝብ ለረዢም ጊዜ ጠብቆ ያቆየው ሃይማኖታዊ እና ባሕላዊ በዓል ነው።የተከበራችሁ ክብራን እና ክቡራት ሆይ! ባለፉት ሦስት አመታት በአገራችን ውስጥ ሁከት እና ግርግር ቀስ በቀስ በመምጣት ለረዢም ጊዜ ተረጋግቶ የነበረው አገራችን ሰላሙን ተበጥብጦ፡ ሁሉም የዓለም ሕዝብ ሲመኛት የነበረቺው የተስፋ እና የሰላም አገር ወደ ስጋት እና ተስፋ ቆራጭነት ተለውጣለች። የውጭ እና የውስጥ ጸረ ፌዴራለዊ የሕገ መንግሥታችን ጠላቶች መጠነ ሰፊ ዘመቻ እንደዚሁም ጸረ ‘ሕዝባችን” (ጸረ የትግራይ ሕዝብ) እየዘመቱበት ያለው የማያቋርጥ ዘመቻ በማካሄድ፤ ያሳየው የሰላም እና የዕድገት ጉዞ እንዳይቀጥልበት በማደናቀፍ ሕዝብን የሚጮቁን፤ሕዝብን የሚያበሻቅጥ፤ እና እስካሁን ድረስ ያስመዘገብናቸው ድሎች “ተረት ተረት” ናቸው ብለው በማጣጣል ጸረ ሕዝብ የሆነ  ዓለማቸውን ለማሳካት ነው እየጣሩ ያሉት።

በውጭ አገር እና በቅርብ አካባቢም የነበሩ ተቃዋሚዎች በምሕረት ወደ አገር እንዲገቡ በመደረጉ ያለ-የሌለ አቅማቸውን በማደራጀት በውስጥ እና ከውጭ ሃይሎች ተሳስረው ሕገ መንግሥታችንን በመጣስ “መንግሥት” ለማፍረስ ተደራጅተው እየሰሩ ነው። ሕገ መንግሥታችን እየተጣሰ፤ የዜጎች መብት እየተረገጠ፤ በመረጠው አካባቢ እንዳይኖር የሚቸገርበት ሁኔታ ተፈጥሯል።በዚህ ምክንያት ንብረቱ እና ሕልውናው ዋስትና ያጣበት በየትም ቦታ ተንቀሳቅሶ መስራት የተቸገረበት ሁኔታ ላይ እንገኛለን።

“ሥርዓታችንን ጎትተው ወደ ኋላ ለመጣል የሚጥሩ ክፍሎች በተለይ በትግሬዎች ላይ ያደረሱት በደል፤ፖለቲካዊ ይዘታቸው ስርዓታችን እና አገር ለማፍረስ ነው። ይህ ዘመቻ የውጭ እና የውስጥ ሴረኞች የተቀናጀ ሴራ ነው። ይህ ዘመቻ በትግሬዎች ብቻ ሳይሆን በሞላ ብሔር ብሔረሰቦች ላይ ስርዓት የመቀየር ዒላማ ስለሆነ ከሌሎች የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ጋር ሆነን በመታገል ስርዓታችን እንዲቀጥል እና እንዲጠናከር መጣር አለብን።

“እነኚህ እየታዩ ያሉት ችግሮች የመፍቻ ቁልፎቹ ያሉት በሕዝባችን እጅ ላይ ናቸው። ይህንን ዘመቻቸውን ለማክሸፍ ተነጣጥለን ሳይሆን ተደራጅተን አንድነታችንን አጠናክረን ልንመክታቸው ይገባል። ይኼውም በትግራይ ውስጥ እና ከትግራይ ውጭ ያሉ አቅሞቻችን አሰባስብን አንድነታችን እና ህልውናችንን ዋስትና እንዲያገኝ ብቻ ሳንወሰን፤ የሕዝባችን ኑሮ እንዲሻሻል ለማድረግ በቶሎ የምንረባረብበት የሽግግር ወቅት ነው።

የተከበራችሁ ክቡራን እና ክቡራት!

“የድርጅታችን ህወሓት ጉባኤ ለማድረግ በምንዘጋጅበት ዋዜማ ላይ እየተከበረ ያለው ይህ የመስቀል በዓል ስናከብር ድርጅታችን ጉባኤውን የሚያካሂደው በህዳሴ ጉባኤያችን ራሱን የቻለ ልዩ በሆነ ክስተት ላይ ነው። የለውጥ ጉባኤችን በጥልቅ የምንወያይበት ነው። ከማንኛውም በላይ ውይይቱ የሚያተኩረው ሕዝባችንን ማዕከል ባደረገ ትኩረት የሚወሰንበት ጉባኤዊ ነው። በክልላችን ልማት እና ሰናይ አስተዳደር ለውጥ ለማምጣት ድል የተቀዳጀ ታሪካዊ ውሳኔ እንደሚወሰን አምናለሁ። 

የተከበራችሁ ክቡራን እና ክቡራት! 

ይህ የመስቀል በዓል ትኩረት ‘አንድነታችንን ለማጠናከር’ እየተጋገዝን ከተሞቻችን እና ክልላችን እንድናለማ ‘ልንጠቀምበት’ ይገባል። እኛ ትግሬዎች ተባብረን አንድ በመሆን መደራጀታችንን አጠናክረን ወደ ፊት እንዝመት” (ደብረጽዮን ገብረማርያም በአዲግራት የመስቀል በዓል በተከበረበት በ2011 (2018)  ዓ.ም አቡነ ማትያስ በተገኙበት የመስቀል ደመራ ስብሰባ ተገኝቶ ያደረገው የትግርኛ ንግግሩ፡ -- ትርጉም ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay) 

ከላይ እንዳያችሁት
1-     የትግራይ ሕዝብ በገዛ አገሩ እንደ ሁለተኛ ዜጋ ሆኖ እንዲታይ የተደረገበት የታሪክ አጋጣሚ ነበር። እያለ የውሸት ታሪክ በመፍጠር ትግሬዎች በአመራ ላይ እና ኢትዮጵያዊነትን እንዲፍቁ ቀስ በቀስ የሚደረግ ሴራ ስትመለከቱት ፋሺስቶች በሕዝባዊ በዓላት ላይ እየተገኙ በዓላቱን ወደ ፖለቲካዊ መጠቀሚያ የሚያደርጉበት ባሕሪ ምንድነው? የሚው ትንሽ ልበልበት።

እንደምታውቁት ምንም እንኳ እኔ በጎሳ ሐረጋዊ ትውልዴ ትግሬ ብሆንም፤ ትግሬነቴ ግን እንደ ብዙሐኑ የትግራይ ተወላጆች የወያኔ ትግሬ እንቅስቃሴ “የአማራ በተለይም ‘የሸዋ ምኒሊካውያን’ ጭቆና ከትግሬዎች ጫንቃ ለማላቀቅ እና በምትኩ ‘ዲሞክራሲ እና ፍትሕ’ ለማማምጣት የተመሰረተ ትግሬአዊ አብዮት ነው” ብለው እንደሚያምኑት ብዙሃኑ ትግሬዎች ሳይሆን በጻፍኩዋቸው መጽሐፍቶቼ እና ትችቶቼ ደጋግሜ እንደገለጽኩት የትግሬዎች ዓብዮት ‘ፋሺስታዊ ርዕዮት እንጂ እነሱ እንደሚሉት” እንዳልሆነ ተከራክሬአለሁ።“የአማራ በተለይም ‘የሸዋ ምኒሊካውያን’ ጭቆና ከትግሬዎች ጫንቃ ለማላቀቅ እና በምትኩ ‘ዲሞክራሲ እና ፍትሕ’ ለማምጣት የተመሰረተ ትግሬአዊ አብዮት ነው” ብለው የሚያምኑ ትግሬዎች ብቻ ሳይሆኑ ከትግራይ ሌሎች ነገዶች የተወለዱ አንዳንድ ደነዝ ምሁራንም ይህንን የወያኔዎች መከራከሪያ ያምናሉ።

ለዚህም ነበር ከደቡብ ኢትዮጵያ የሚወለዱ የታሪክ ምሁር የሚባሉት ዶ/ር ላጲሶ “ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ሕዝብ የሥልጣን ምንጭ ሆኗል” በማለት እፎይታ በታባለ የወያኔ መጽሔት ባደረጉት ቃለ መጠይቅ ያረጋገጡት።

ስለሆነም ነው የፖለቲካ እና ታሪክ ምሁራን ሳይቀሩ የወያኔ ትግራይ እንቅስቃሴ ምንነት በቅጡ ሳይረዱት በመቆየታቸው በምሁራኑ እውቀት እና ምርምር ችሎታ ያፈረው የወያኔ እና የኦነጎች ፖለቲካ መስመር “ፋሺዝም ነው” በማለት 27 አመት ሙሉ ምሁራኑን ለማስተማር እና አቋማቸው እንዲያስተካክሉ የጣረው ወዳጄ ዶ/አሰፋ ነጋሽ እንዲ ስል አግራሞቱ ይገልጻል፡-

“…አንድን መንግስታዊ ስርዓት ከምንም በላይ ፋሽስት የሚያሰኘው መስፈርት መንግስት በአንድ ጎሳ ወይም ህዝብ ማንነት ላይ በተመሰረተ አክራሪ የሆነ ብሄረተኛነት ላይ የቆመ መሆኑና መንግስታዊ ፓሊሲዎችም የሚቀረጹት የአንድን ምርጥ ህዝብ የፓለቲካ፤ የኢኮኖሚ፤ ወታደራዊና የባህል የበላይነት ለማረጋገጥ መሆኑና ያንን ቆምኩለት የሚለውን ህዝብ እንደ አዲስ ህዝብ በዳግም ልደት ለመፍጠር መመኮሩ ነው። የኢትዮጵያ ምሁራንም ሆኑ የፖለቲካ ተቃዋሚዎች ይህንን የፋሺሰቶች መሰረታዊ የመነሻ ባሕሪ ሳያውቁ፤ በእውቀት ሳይሆን በደመነፍስ በስሜት የሚመሩ ስለሆነ ህወሓት ከትጥቅ ትግሉ ዘመን ጀምሮ እስካሁን ድረስ የሚከተላቸውፓሊሲዎች ከፋሽስታዊ ተፈጥሮ የሚመነጩ መሆናቸውን ለመገንዘብ አልቻሉም። ስለሆነም በእውቀት የሚመራ የፓለቲካ አሰራር በማይታወቅባት ኢትዮጵያ ውስጥ የህወሃትን ፓሊሲዎችና ድርጊቶች ተቃዋሚዎች አንዴ ከህወሓት ኮሚኒስትነት፤ ሌላ ጊዜ ደግሞ ከህወሓት ስታሊስትነት፤ ጠባብነት ወዘተ ሲፈርጁ ታይተዋል።በማለት ያብራራል።

ስለዚህ የአገራችን ምሁራን እና ፖለቲከኞች ስለ ፋሺዝም ርዕዮት መነሻ እና ግቡ ያላቸውን ዕውቀት የደበዘዘ በመሆኑ ወያኔዎችን የሚገልጸባቸው ትንታኔዎች ለትግሉ ዕንቅፋት ሆነው ቆይተዋል። በኔ እይታ ብዙዎቹ “ወያኔ አፓርታይድ ነው” ብለን ስንከራከር አይቀበሉንም። በጣም እሩቅ ወደ ሆነው ፖለቲካ ተሻገራችሁ በማለት በትንታኔአችን ይገረማሉ። ሃቁ ግን አዎ ወያኔ የመሰረተው ስርዓት “አፓርታይድ” ነው። ይህንን ቪዲዮ አደምጡ/ተመልከቱ እና የሳውዝ አፍሪካ አፓርታይድ በወያኔ እንዴት እንደተደገመ በግልጽ ከዓየይን ምስክር ትረዳላችሁ።


 Former Ethiopian University student's testimony on Federal Police
           https://youtu.be/f3CTMNQSsjs


አብዛኛዎቹ የትግራይ ተወላጆች ለወያኔ ያላቸው ድጋፍ ከምን የመነጨ እንደሆነ እና ስርዓቱ አድላዊ/አፓርታይድ መሆኑን ደ/ር አሰፋ ነጋሽ በማስረጃ አስደግፍፎ የሰጠውን ሰነድ ለግንዛቤ እንዲረዳን ላቅርብ።

በአውሮጳ የአምስተርዳም ኗሪ የሆነው የውስጥ ሓኪም እና የስነ ኣእምሮ (ሳይኪያትሪስት/እስፔሺያሊሰት) ዶ/ር አሰፋ ነጋሽ ስለ ወያኔ አፓርታይድነት በትንሹ እና በቀላሉ እንዲገባን በዚህ ትንታኔ እንዲህ ይላል።


“እስቲ የወያኔ ትግሬዎች የአፓርታይድ ሥርዓት በአዲስ አበባ የከተማ ቦታዎች ሽንሸና ላይ ምን ዓይነት ተፅዕኖ እንዳለው የሚከተለውን የአቶ ዮሃንስ ታደሰ አካን ጥናት ውጤት በማየት ለመረዳት እንሞክር። ካለ በኋላ፦

  “የአዲስ አበባ ከተማ የሪል ስቴት ልማትን የሚመለከት ዝርዝር ጥናት በአስቸኳይ ተዘጋጅቶ ይቅረብ የሚል ቀጭን ትዕዛዝ ከጠቅላይ ሚንስትር ፅህፈት ቤት ሲወርድ ሲዋረድ መጥቶ እኔ ዘንድ ደረሰ። አቶ መኩርያ በቀጥታ እኔ ቡድን አዋቅሬ በአስቸኳይ እንዳቀርብ አዘዘኝ። በጥናቱ ወቅት ከታዘዝኩት ይልቅ ያልታዘዝኩት ቀልቤን ገዛኝ። የሪል እስቴቶቹ ባለቤቶች! በአዲስ አበባ ከ130 በላይ ሪል እስቴቶች ይገኛሉ።  ከ5.000.000.00 ካሬሜትር በላይ ቦታ በሪል እስቴት ልማት ለመኖሪያ ቤት ግንባታ ብቻ የተላለፉ ናቸው። ከዚህ ቦታ ውስጥ አንድ ሶስተኛው በተራው ትግሬ የተያዘ ሲሆን ሌላኛው አንድ ሶስተኛ በአያት ሪል ስቴት የተያዘ ነው። አያት ሪል እስቴት እንደ ዛሬው ጌዜ ሳይከዳው በፊት ጀርባው በምርጥ የጡት አባቶች የተደገፈ ነበርና በግልፅ ይህን ያህል ተብሎ መግለፅ ቢያቅትም በተዘዋዋሪ ምርጦቹን ባለ መሬት እንዳደረገ ይገመታል። ቀሪው አንድ ሶስተኛ በዳያስፖራ ማህበራት እና ሌሎች ባለ ሀብቶች የተያዙ ናቸው። ከነዚህ የዲያስፖራ ማህበራት አብዛኛው የትግራይ ተወላጆች ዳያስፖራዎች ናቸው። በእርግጥ አንዳንድ ነቄ ዳያስፖራዎች ከትግሬዎቹ ማህበር በመጠጋት መሬት የደረሳቸው አሉ። በአጠቃላይ እስታቲክሱን ስናየው በትንሹ ሰባ በመቶ የአዲስ አበባ ሪል እስቴት የተያዘው በትግራይ ተወላጆች እና በአያት አክሲዮን ማህበር ነው[1]”።  


 ”።  (መስመር የተጨመረ)

(ምንጭ- ዮሃንስ ታደሰ አካ፤ “የተስፋው ነፀብራቅ” ሚያዝያ 2013 ዓ. ም. እንደ አውሮፓ አቆጣጠር በጀርመን ሀገር የታተመ መጽሃፍ - ዶ/ር አሰፋ ነጋሽ አክራሪ ብሄረተኛነት በሰዎች ላይ የሚያስከትለው ስነልቦናዊ ለውጥና የሚፈጥረው ተፅዕኖ ክፍል 4-የተጠቀሰ ማስረጃ)

በማለት አፓርታይድ ምን ማለት እንደሆነ በቀላሉ ለማየት ችለናል። የመሬት ቅርምት ወይንም ክፍፍል ፍትሃዊ ካልሆነ አንዱ የአድላዊ/አፓርታይድ ስርዓት መገለጫው ነው።

እንግዲህ ወደ መነሻችችን ስንገባ ዶ/ር አሰፋ ነጋሽ ፋሺዝምን ካጠኑ የውጭ ምሁራን መዛግብት በመመርመር ደጋግሞ በጥልቅ የጥናት ጽሑፉ ውስጥ እንደገለጸው ‘ፋሽዝም በአንድ ምርጥ ሕዝብ ማንነት ላይ ተመስርቶ የቆመና የአንድን ምርጥ ሕዝብ የበላይነት የሚሰብክ የአክራሪ ብሄረተኛነት (ultranationalism) ፍልስፍና’ መሆኑን ነግሮናል። የኢትዮጵያ ፋሺስቶች (ኦነግ/ወያኔ\+ ወዘተ…) የሚየያቀንቅኑት የአንድን ምርጥ ሕዝባቸው ማንነት ለማረጋገጥ በማያቋርጥ አብዮታዊና ስር-ነቀል በሆነ መንገድ መጓዝ ነበረባቸው። ‘ብሄራችን’ የሚሉትን ክፍል በመለወጥ አንድ-ወጥ አስተሳሰብ ያለው ማሕበረሰብ ፈጥረዋል።  ያራመዱት ፖለቲካ “አንድ ወጥ” የሆነ አስተሳሰብ እንዲከተል ማድረግ ነበር እና አድርገውታል።

 ብሔራችን የሚሉትን ክፍል ሃይማኖትህ ፤ ቋንቋህ ፤ ድምበርህ እና ማንነትህ ተጨፍልቋል በማለት የሰበኩትን ክፍል በዳግማይ ልደት ምርጥነቱን ተመልሶ ለማረጋገጥ አዲስ በሆኑ የሞራል እሴቶች የታነጸ አዲስ ሰው መፍጠር ነበረባቸው እና ፈጥረዋል። አዲስ ታሪክ ሰሪ ነህ ብለው ሃይሞኖቱን፤ቋንቋውን፤ባሕሉን የፖለቲካ መጠቀሚያ ድልድይ እንዲሆኑ በማድረግ ከሌላው ጎሳ እንዲለይ ብቻ ሻይሆን አገር ከምትባለዋ ዋናዋ አገር የነበራቸው ትስስር ባሕል እንዲበጠስ ጉልህ ‘ሴራ አድርገዋል”። ይህ የኛ ባህል እንጂ የማንም አይደለም በሚል ምርጥ ልዩ የሆነ የማንነት ማዕረግ ለመላበስ ትግሬዎች (የወያኔ ፖለቲከኞች) አክሱምን ከመሰረቱ ጥንታዊ አገዎች ጋር ፉከክር ገብተዋል።

((በታሪክ አንደምታውቁት ትግሬ/ትግራይ/ትግራዋይ/ትግራዋይነት/… የሚል ስም ወይንም ትግርኛ ቋንቋ በአክሱም ዘመን አልነበረም። የተከሰተው “ቤጃውያን አክሱምን ከወረሩ እና ካፈረሱት ወዲህ ነው። ትግሬዎች ከክራር ጨዋታ ጀምሮ ከበሮ መቺዎች እና እስክስታ አውራጆቸ የትግርኛ አስክስታ “ሲደረብ” (ውረድ ሲባል) ቤጃዎቹ እንደሚያደርጉት ወደ መሬት በመውረድ “ሁለት እግር እንደግመል ወደ ሊት አጥፈው” አንገትን ወደ ሰማይ አንቃርሮ የማንቀሳቀስ ጨዋታ ከቤጃዎች ጋር ይመሳሰላል። ከበሮ መቺዎችም ወደ መሬት ወርደው ሁለቱ እግሮቻቻው ወደ ላ አንደ ‘ግመል’ በማጠፍ ወደ ሰማይ አንቃረው ሲመቱ የቤጃዎችን ባህል ይመሳሰላል) ቤጃዎችም በእስክስታ ዳንኬራው ሲመሰጡ ወደ መሬት ሸብረክ ብለው ወገባቸውን መሬት ላይ ወደ ሊት ለጥጠው በማስተኛት፤ሁለቱንም እግሮቻቻው እንደ ገመል ወደ ላ በማጠፍ አንገታቸው አንቃርረው ዳንኪራውን በትከሻቸው ይረግጣሉ።

 ይህ በእንዲህ እንዳለ ‘አገዎች’ ትግርኛ ወይንም ትግሬ ከሚባለው ክፍል አስቀድመው እዛው አክሱም የነበሩ እና ሰማቸውም በዛው ስም በጥንት ሃውልቶች ጽሑፍ ይጠቀሱ የነበሩ አክሱማውያን ናቸው። የዛሬ ትግሬዎች (ወያኔዎች) ሆን ብለው ከሰቆጣ ዋግ አገዎች ጋር ጸብ ገጥመዋል። ለዚህም አማራዎች ናቸው ብለው ሰይመዋቸዋል። በዚህ ምክንያት ወያኔዎች “አሸንዳ” (የትግርኛ ተነጋሪ አጠራር) “አሸንድየ” (በአገዎች/አማራዎች አጠራር) በሚባለው ጥንታዊ ክርስትያናዊ (ሃይማኖታዊ) በዓል ወደ ፖለቲካ መጠቀሚያቸው አዙረውት ሕዳጣንን ከሕዳጣን ለማጣላት በረቀቀ ፋሽታዊ ስልት ክፍፍሉን ለማጋጋል በየኔ ነው-የማንነት ውዝግብ  እንደገቡ የምታውቁት ታሪክ ነው።

 በነገራችን ላይ ነብሳቸው ይማረው የታሪክ ምሁሩ ደ/ር አለሜ እሸቴ ባንድ በላኩልኝ  የግል ደብዳቤ ጽሑፍ ውስጥ “አማራዎች የጥንቶቹ አገዎች ናቸው ይላሉ። አገዎች ከጊዜ ብዛት ቋንቋቸውን በመለወጥ አማርኛን በመያዝ የወደ አማራ የተለወጡ ናቸው ይላሉ። ለዚህም አገዎች የአክሱም ወታደሮች የነበሩ ሃይለኛ ተዋጊዎች ስለነበሩ ያንን አማርኛ ቋንቋ ወታደራዊ እና ቤተመንግሥታዊ ስለነበረ ‘አገዎች አማርኛን እየተናገሩ’ ‘ብዙዎቹ አገዎች አገውኛውን እየለቀቁ አማራ የሆነውን ሰፊውን ክፍል ፈጠሩ’ ጥቂቶቹ አገዎችም አማርኛ እና አገውኛ ተናጋሪ ሆነው ቀሩ (ልክ ትግሬዎች ወይንም ኦሮሞዎች፤ሶማሌዎች…አዲስ አባባ ሲመጡ አነጋገራቸው/ዘይቤአቸው ‘አዲስ አበቤዎች’ እንደሚሆኑት ማለት ነው)። ለዚህም ነው አገዎች አማርኛን እና አገውን በማዋሃድ ሁለቱንም የነሱ አድርገው ሲዘፍኑት ወይንም ሲናገሩት የሚደመጡት” በማለት በልዩ ማስታወሻ ጽፈው ልከውልኝ እንደነበር አስታውሳለሁ።

ስለሆነም የወያኔው ደብረጽዮን በመስቀል በዓልም ይሁን በተገኘበት የሕዝብ በዓላት በመገኘት የኢትዮጵያ ገናናነት ሳይሆን የትግራይ ገናናነት በማውሳት የትግራይ ሕዝብ ገናናነት በአማራዎች ተረግጦ እና ተንቆ ገናናነቱን የመነጠቁ ታሪክ ለሕዝቡ ሊያወራ የፈለገበት ዋናው አላማ ፋሺስቶች ለተከታዮቻቸው ስለ ብሶት እና በደል እያጋነኑ የማውራት ባሕሪ አለም አቀፋዊ ባሕሪያቸው ስለሆነ ነው። በዚህ ምክንያት ዶክተር አሰፋ እንደገለጸው ብዙዎቹ የፋሺስት አቀንቃኞች፡

) በአፈ-ታሪክና በአብዛኛው በውሸት ላይ የተመሰረተ አዲስ ታሪክ በመፍጠር አንድ ህዝብ እጅግ ደማቅ የሆነ በእጅጉ ገናና የሆነ ታሪክ ባለቤት እንደነበረ ይተርኩለታል።

- ይህ ትላንት በታሪክ የደማቅና ገናና ታሪክ ባለቤት የነበረ ህዝብ በዛሬው ዘመን እየተፈጸመበት ያለውን በደል፤ ወርድትና ብሶት ያስተጋቡለታል።  

- ይህ ትላንት ደማቅና ገናና ታሪክ የነበረው ዛሬ ደግሞ የውርደት፤ የበደል ሰለባ የሆነ ህዝብ ራሱን እነዚህን አዲስ የነጻነትና የአክራሪ ብሄረተኛነት ዜማ የሚያዜሙ መሪዎችን ቢከተል ሊያገኝ የሚችለውን ሲሳይ ይተርኩለታል። ከዚህም በላይ ብሄረተኞች ወገናችን ነው የሚሉትን አንድ ምርጥ ህዝብ አንተ የእኛን መሪነት ተቀብለህ በስራችን ታቅፈህ ከታገልክ ምድራዊ ገነት እናወርስሃለን፤ ከችግርና ከጉስቁልና እናወጣሃለን ብለው የተስፋ መና በማስጨበጥ አንድን ምርጥ ህዝብ ወይም ነገድ በአዲስ ተስፋ ለትግል ያነሳሱታል።እነዚህ ሶስት የብሄረተኝነት ማጠንጠኛ ድርና ማጎች በመከተል።ባህልን ሃይማኖትን እና በዓላትን በመጠቀም የተከታዮቻቸውን አመለካከት ለመቅረጽ ይጠቀሙባቸዋል።

አሁንም ዶ/ር አሰፋ እንደሚገለጸው “ባህልና ከባህል ጋር ተያያዥነት ያላቸውን አፈታሪኮች፤ ባህላዊ ስነስርዓቶች፤ ዘፈኖች፤ ባህላዊ ፉከራዎች/ሽለላዎችን ወዘተ በመጠቀም አንድ የፋሽስት ቡድን ህዝብን በስሜታዊነት በማነሳሳት የባህልን ውጤቶች የፋሽስት የፓለቲካ ዓላማ ማሳኪያና ማስፈጸሚያ መሳሪያዎች ያደርጋል። ባህላዊ ምስሎችና ምልክቶች (cultural images and symbols) ሰዎችን በስሜት አነሳስተው የማሳወር አቅምና ችሎታ አላቸው።” ይላል።

እኔም ካሁን በፊት ይህንን ለማብራራት የጠቀስኩትን ትግሬዎች በሙዚቃ እየታጀቡ የትግራውያን ፉከራ ይዘት ምንነት የገለጽኩት የአንድን በፋሽስት አስተሳሰብ ያበደ ሕዝብ አመለካከት ፍንትው አድርጎ ስለሚያሳይ ነው። ለዚህ ነው ዶከተር አሰፋ ነጋሽ “የትግራይ ሕዝብ ተነስቶ ወያኔን ይጥላል ማለት ቅዠት ነው” በማለት ድምዳሜ የደረሰው። አሁን እውነታው እያየነው ነው። ትግሬዎች እና ወያኔዎች ያላቸው ግንኙነት እና ቃለ ኪዳን የዶከተር አሰፋ ክርክር እውነታ ትክከለኛነት ያረጋግጣል። እነ አብርሃ ደስታ እነ አብርሃም አስራት ያ ሁሉ ሆሆታ በኢትዮጵያውያን እና በመነኛዎቹ የተቃዋሚ ሚዲያዎች ‘አገር ወዳዶች’ እየተባሉ ሲወደሱ፤ ዞረው ዞሮው ማደሪያ እና መነሻቸው ወደ ሆነው ወደ እንደ ሰብአዊ ፍጡር ወደ “ሰውነት ዘብ መቆም” ሳይሆን  ወደ “ትግራዋይነት” ሲቆሙ ያየንብትም የባሕሪና የመስመር ለውጥ መከተል ምክንያት “የወያኔ ፋሺሰት ፖለቲካ “ባህልን ሃይማኖትን እና በዓላትን በመጠቀም የትግራይን ሕዝብ አመለካከት በመስመሩ ሊቀርጽ በመቻሉ ነው

“ኪነጥበብ፤የመስቀል፤የፋሲካ፤የቅዱስ ዮሓንስ፤አገራዊ ክብረበዓላትና ባሕላዊ ምልክቶች የፋሲስቶች እምነት ማስፋፊያ መሳሪያዎች” የሚሆኑበት ምክንያት ፋሽስቶች እነዚህን በአንድ ሕዝብ ውስጥ ጥልቅ መሰረት ያላቸውን ምልክቶች፤ ልማዶችና ክብረ በዓሎች ሕዝብን በስሜታዊነት ለማነሳሳት ለሚያደርጉት ያላቋረጠ ትግል በመሳሪያነት ቀላል እና ሃይለኛ የመጎተቻ ገመዶች ስለሆኑ ነው።

 “የትግራይ ህዝብ በአክራሪ የትግራይ ብሄረተኛነት አማካይነት የራሱን ነገድ ማንነትና ታላቅነት እንዲያመልክ ተደርጎ ለብዙ ሺህ ዘመናት አብሮ ከኖረው የተቀረው የኢትዮጵያ ህዝብ በስነልቦናም ሆነ በእለታዊ ህይወቱና ማህበረሰባዊ ተራክቦው (social interaction) እየተለየ የመምጣቱ ክስተት ፋሺስቶቹ ሕዝባዊ በዓላትን የወያኔዎች መድረክ መለፈፊያ በማድረጉ ነው።ዛሬ የትግራይ ህዝብ ራሱን ኢትዮጵያውያኖች በጋራ ከሚጋሩዋቸው ብሄራዊ እሴቶች በተቃራኒ የቆሙና ጸረ-ኢትዮጵያ የሆኑ፤ በአክራሪ የትግራይ ብሄረተኛነት የተቃኙ ፋሽስታዊ እሴቶች ባለቤት በማድረግ ጨርሶ ከኢትዮጵያ ማህበረሰብ ወጥቷል ማለት ይቻላል። የኪነጥበብ ስራዎች፤ ዘፈኖች፤ ትያትሮች፤ ፊልሞች ወዘተ የህዝብ መዝናኛዎች መሆናቸው ቀርቶ ጦረኝነትን፤ የትግራይን ህዝብ የበላይነት፤ ምርጥነት፤ የንጹህ ዘር፤ የንጹህ ደም ባለቤትነት፤ ልዩና ወደር የሌለው የታሪክ ባለቤትነት፤ የሥልጣኔ ባለቤትነት፤ ጀግንነት፤ አዋቂነት፤ ወዘተ አጉልተው የሚያሳዩ የፕሮፓጋንዳ መሳሪያዎች ሆነዋል።” (አሰፋ ነጋሽ)

በሌላው በኩል ዘፈኖችን፤ ፉከራዎችን፤ ትያትሮችን፤ ፊልሞችን የመሳሰሉ የኪነት ስራዎች ከምርጡ የትግራይ ህዝብ ወይም ጎሳዎች ወይም ህዝቦች ውጭ ያሉትን የሌሎችን ፈዛዛነት ትንሽነት፤ ፈሪነት፤ ድንቁርና፤ ኋላቀርነት፤ የአይምሮ ዘገምተኝነት (ጎጃሞች Retards ናቸው የሚለውን ነጮች የጥቁሮችን የአእምሮ ማነስ ተፈጥሮ እያሉ እንደሚሰነዝሩት ዘረኛነት ሁሉ፤ የአንዲት እብሪተኛ የትግራይ ብሄረተኛ ሴት (ገዛ ተጋሩ የተባለው ፓል ቶክ ባለቤት እና ዋና አዘጋጅ) በጎጃሜዎች እና ጎንደሬዎች ያስተጋባችውን ስድብዩቲዩቭ ውስጥ ገብቶ የተለጠፈውን ድምጽዋን ማዳመጥ ይረዳል) ወዘተ አጉልተው ለማሳየት የሚጠቀሙባቸው መሳሪያዎች ሆነዋል። ዛሬ በርካታ የትግርኛ ዘፈኖችን ይዘት ብታዳምጡ የሚያሰሙት ፉከራ (አንድ ትግሬ ለሃምሳ አማራ ይበቃል የሚለው) ስለ ትግራይ ህዝብ ልዩ ጀግንነት፤ አልበገሬነት፤ ታላቅነት ስለሌላው ደካማነትና ፈሪነት በሕዝባዊ መድረኮች ወይንም ባዓላቶች ውስጥ ያስተጋብዋቸዋል። በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ አንድ ህዝብ እንደዚህ ይሉኝታን ባጣ መንገድ ታላቅነቱን፤ ብቸኛ ጀግንነቱን፤ አልበገሬነቱንና በሌሎች ላይ ያለውን የበላይነት የሰበከበት ወቅት ተፈልጎ ሊገኝ አይችልም።

በአንድ ህዝብ ማንነት ላይ ተመስርቶ በመሆን ወደፊት ብቅ ያለው ፋሺዝም የተባለውና የአክራሪ የትግራይ ብሄረተኛነት መገለጫ የሆነው አዲሱ የፓለቲካ ኃይማኖት ከእሱ እንደሚቀድመው የኢጣሊያን የፋሽስት ስርዓት አዲስ ምድራዊ የፓለቲካ ሃይማኖት እምነትን (አክራሪ ብሄረተኛነትን) እያስፋፋ ላለፉት ሃያ ስድስት ዓመታት በመንግስትነት ሰይሞ በኢትዮጵያ ህብረተሰብ ላይ ራሱን በኃይል በመጫን ለትግራይ ህዝብ የደስታን ዘመን ከትግራይ በታች ላለው አብዛኛው የኢትዮጵያ ህዝብ የጭለማና የመከራ ዘመንን አብስሯል ።ይህ የትግራይን ህዝብ የወል ማንነት (በወያኔ ቋንቋ የትግራይ ብሄር) እንደ ሃይማኖቱ አድርጎ የሚያየው፤ የትግሬነትን የወል ማንነትንና የትግራይ ብሄረተኛነትን መመሪያው ያደረገ ፋሽስታዊ ፍልስፍና የትግራይን ህዝብ የወል ማንነት የተቀደሰ አድርጎ ከማየቱም በላይ የትግራይ ተወላጆች ይህንን በወያኔ መንግስት ቅድስና የተሰጠውንና ከሌሎች የኢትዮጵያ ነገዶች ሁሉ በላይ ወርቅ አድርገው ራሳቸውን እንዲያዩ ያደረጋቸውን አዲሱን ማንነታቸውን ህይወታቸውን ጭምር መስዋእት አድርገው እንዲጠብቁትና እንዲከላከሉት ያስተምራል።

የወርቅ ማንነቱን ለማክበር በየጊዜው የሚያከብራቸው አዲሱ ባዓላቶቹ ስትመለከቱ ይላል ወዳጄ ዶ/ር አሰፋ ነጋሽ ጊዜውን አግኝቶ የትግራይን ቴሌቪዥን በየጊዜው ለሚከታተል ሰው የትግራይ ህዝብ በልማት ስራ ላይ ብቻ አለመጠመዱን ይመለከታል። የትግራይ ህዝብ ልጆቹ ምስጋን ይግባቸውና ታጋዳላይ ጀግኖች ልጆቹ ያጎናጸፉትን አዲሱንና አኩሪ የወርቅ ማንነቱን በየጊዜው በሚያከብራቸው አዲስ በዓላቱ (የየካቲት 11 የግንቦት 20 የአሸንዳ የሰማእታት ቀን፤ የሰራዊት ቀን፤ የሴቶች የወጣቶች ቀን፤ በጦርነት የተጎዱ አካል ጉዳተኞች በዓላት ቀናት ወዘተ በስሜት ሰክሮ ከበሮ እየደለቀ፤ በኦርቶዶክስ ቀሳውስትና ታቦት ታጅቦ ታላቅነቱን፤ ልዩ ጀግንነቱን ጠመንጃ ይዞ በቀረርቶ፤ በፉከራ ጭምር ያስተጋባል። በቴሌቪዥን መስኮቶች የትግራይ ህዝብ ልዩ ጀግንነት በእነ አሉላ አባነጋ፤ ዐጼ ዮሃንስ፤ ኃያሎም ዓርዓያ፤ አሞራው ወዘተ ምስሎች ታጅበው ይቀርባሉ። እነዚህ ዓይነት ያንድን ህዝብ ታላቅነት የሚዘክሩ ትዕይንቶች ወያኔዎች ከደርግ ጦር ጋር በተደረጉ የእርስ በርስ ውጊያዎች በጦር ሜዳ የበላይነት ባገኙባቸው ምስሎች ታጅቦ ይቀርባል። በእነዚህ የጦር ምስሎች ታጅበው የሚቀርቡት የቴሌቪዥን ዝግጅቶች የትግራይን ህዝብ የህዳሴ ጉዞ (renaissance) የዳግም ልደት (rebirth) የሚያሳዩ፤ የትግራይ ህዝብ ከመቶ ዓመታት በላይ በስልጣን ላይ ነበሩ በሚባሉ የአማራ ህዝብ መሪዎች ተቀብሬ ነበር ብሎ ከሚያምንበት መቃብር በጀግና ልጆቹ መስዋእትነንትና ሰማእትነት በትንሳዔ ተነስቶ አዲስ ታሪክ እየጻፈ መሆኑን ያስገነዝቡናል

ለፋሽስቶች ዋነኛና ተመራጭነትና ዋጋ ያለው ችሎታ እውቀት ሳይሆን ጭፍን እምነት ነው። ፋሽስቶችን ለቆሙሉት ዓላማ በቆራጥነት እስተመጨረሻው እንዲዋጉ የሚያደርጋቸው ጭፍን እምነታቸው ነው” አሰፋ ነጋሽ።

በመቀጠል ዶ/ር አሰፋ እንዲህ ይላል።

በደንብ ያላጤናቸውና ያላስተዋልናቸው የትግራይ አክራሪ ብሄረተኞች  ሲያስተጋቡዋቸው የነበሩት የእነ ሙሶልኒ ፋሽስታዊ አስተሳሰቦች ምን ይመስላሉ?

ብስራት አማረ የሚባል የወያኔ ካድሬና የወያኔ ዋና የመግደያና የማሰቃያ እስር ቤት ኃላፊ በመሆን ለብዙ ሺህ ኢትዮጵያውያን፤ በተለይም ለአማራ ተወላጆች ህይወት መጥፋት ተጠያቂ የሆነ ግለሰብፍኖተ ገድልበሚል ርዕስ ስለ ወያኔ ሃርነት ትግል በጻፈው መጽሃፉ ውስጥ የትግራይ ሽማግሎች ለወያኔ ተዋጊዎች የሰጡትን ምክር እንደሚከተለው አስፍሮአል።

ዮሃንስ አራተኛ ከሞቱ ልክ ከአንድ መቶ አምስት አመታት በኋላ መጋቢት 1981 .. ህውሃት መላውን ትግራይ ነጻ አውጥቶ መቀሌን ተቆጣጥሮ ወደ ማእከላዊ ኢትዮጵያ ሲገሰግስ በእድሜ አንጋፋ የሆኑት ትግራውያን እነሱና አያቶቻቸው የከፈሉትን ታሪካዊ ሰቆቃ አስታውሰው በታላቅ ክብር ለታጋዮቻቸው ሲመክሩኢትዮጵያ የናንተ ናት። አሁን የሚያቆማችሁ ኃይል የለም። ልጆቻችን ከእነሱ ይበልጥ ጠቢብና አሳቢ እንደሆናችሁ የንጉስ ምንሊክ ሰዎች አሁን ይማራሉ። እናንተን ለማሸነፍም ሆነ ለማስቆም የሞራል ብቃት የላቸውም። ትግራይ አንዴም ተሸንፎ አያውቅም። ምንሊክ የትግራይን ህዝብ እንደ ጠላት ቅልስልስ አደረጋቸው። እግዚአብሄር ይባርካችሁና በአባቶቻችን እና በራሳችን ስም እናመሰግናችኋለን ብለው ምንሊክ ባንድ ወቅት ታላቅ ለነበረችው ሀገር የተወላት ብልሹና ከፋፋይ አስተሳሰብ እንደ ነበር አስገንዝበዋል (ለዝርዝር መረጃ የብስራት አማረን -
ፍኖተ ገድልየተሰኘ መጽሃፍ ገጽ 41 ላይ ይመልከቱ)

መለስ ዜናዊ በየካቲት 1984 . መቀሌ ላይ ለአስራ ሰባተኛው የወያኔ ምስረታ በዓል ላይ አንድ ሚሊዮን ለሚሆኑ በቦታው ለተሰበሰቡ የትግራይ ተወላጆች ያደረገው ንግግር።

ይህ ሕዝብ አንኳን የሌሎች/የባእዶች አልሆነ። እንኳን ከእናንተ ተፈጠርን። ይህ የእያንዳንዱ ታጋይ አምነት ነው። እንኳን ከናንተው ማህፀን ተፈጠርን። እንኳን የኛ ሆናችሁ። እንኳን የባዕድ የሌላ አልሆናችሁ። እንኳን በማዶ እያየናችሁ የምንቀናባችሁ የሌሎች አልሆናችሁ። እናንተ ወጣቶች! እዚህ ያላችሁበት መድረክ እንደትደርሱ ሲባል ታላላቆቻችሁ ላባቸውና ደማቸው አፍስሰዋል፤ ታላላቆቻችሁ በየጉራንጉሩና፤ በየሸለቆው እና ተራራው ቀርተዋል።ታላላቆቻችሁ አጥንቶቻቸው በየተራራው ተበትኗል። አጥንቶቸው  በየተራራው የተበተነበት ምክንያትም ትግራይ እንድትለማ በሚል ነው። እነኚህን አጥንቶች-እንዳትረግጧቸው፤ አንዳታራኩሷቸው! ሁኔታውን ካመቻቹላችሁ በኋላ እንዳትከዷቸው፤ ሌት ተቀን  መጣር ይኖርባችኋል” (መለስ ዜናዊ)

(ምስጋና ይድረሰውና ወዳጄ የሆነው፤ ወያኔን በግምባር ቀደምትነት በመታገል የሚታወቀው የአክሱም ተወላጅ አቶ ጌታቸው ረዳ ይህንን እዚህ የጠቀስኩትን በመተርጉም የሁል ጊዜ ትብብሩን አድርጎልኛል)


ከዚህ ቀጥሎ የምትመለከቱዋቸው የተላያዩ የትግራይ ዘፋኞች የሚዘፍኗቸው ዘፈኖች

እነዚህ ዘፈኖች ከውስጣቸው እያንዳንዱ ዘለላ ዓረፍተነገር የሚነግሩን ‘በትግራይ ብሔረተኛነት የተቃኘ ፋሺስታዊ ቅንቀናዎች ጎልተው የሚነግሩን የስርዓቱ ምንነትን ነው። በእነኚህ ዘፈኖች ሚሰነዘሩ ስንኖችና መልዕክቶች እንደመብራት ሆነው ብዙዎቻችን ማየት ያቃተንን ‘የትግራይ ብሔረታዊ ፋሺስዝም’ ምንነት ማየት የተሳናቸወ ዓይኖቻችን ላይ እያበሩ ለኛ በጋረደው ዳመና ውስጥ ሰርስረው የሚያሳዩን ፋና ወጊ መብራቶች ናቸው። ትግራይ ወያኔ ወጣት ዘፋኞችና ዘፈኖቻቸውን እነሆ ምን እንደሚል የትርጉሙ ምንነት እንመልከት።

ዑንቂ ባሕሪ (ዘፋኝ ሕሉፍ አለሙ)

ጥግረኛው ለአንባቢ እንዳይራዘም ትቼዋለሁ።

ወደ አማርኛ ሲተረጐም
የትግራይ ሕዝብ የባሕር ኡንቅ
ጀግና የትግራይ ሕዝብ ይገባዋል ክብር
በዛ በመራራው በአስራ ዘጠኝ ሰባሰባቱ (1977)ሕዝብ እንዳይበተን ማገርና ቀምበር
ሆኖ የጠበቀን ታጋይ የትግራይ ሕዝብ ይገባዋል ክብር !
የተፈተናችሁ በቀውጥ ቀን በእሳት
በመራራ ትግል እያባረራችሁ አሳድዱት በሉት
ናችሁና ትግሬዎች
የበረሃ አምበሶች
በመራራ ትግል እያባረራችሁ አሳድዱት በሉት
የባሕሩ የሉል የዑንቅ ልጆች ድል ተጎናጽፈዋል በአሸናፊነት!
ምነው በሞትኩኝ
ምነው ስስት ያዘኝ ለመብላት ቸኮልኩኝ
የትግራይ ሕዝብ ስሙን ሳልጠራ ረስቸው ጎረስኩኝ! (በስመ አብ ወወልድ..የሚለው ተክቶ በስመ አብ ወትግሬ” ማለት ነበረብኝ እንደማለቱ ነው ዘፋኙ እየነገረን ያለው)

ትግራይ ዓደይ (ዝዓበኹልኪ መረበተይ) 
(ዘፋኝ አበበ አርአያ)

ኣይርስዐክን እየ ዓደይ
ዝዓበኹልኪ መረበተይ
ዓይርስዐክን እየ ትግራይ ዓደይ
ፍርይቲ ዓይነይ
ክሳብ መወዳእታ ምሳኺ እየ ትግራይ ዓደይ
ንዓኺ ዘይኸውን የለን ትግራይ ዓደይ
ወርቂ ተሸለምለይ ጸብቕለይ
ርኢኽዮንዶ እቲ ብርሃን ጅግና
ሳላ ዝወለድክዮ ትግራይ ዓድና
ርኢኹሞዶ ሽዶናይ ወዳ
ወደ ትግራይ ጎሚዳ
ርኢኹማዶ ትግራይ ኩሑሎ
ብመብራሕቲ ትሕሎ
ንዓኺ ዘይኸውን የለን ወርቂ ተሸለምለይ

ወደ አማርኛ ሲተረጎም፤
አልረሳሽም አገሬ
ያደግኩብሽ መንደሬ
አልረሳሽም ከቶ ትግራይ አገሬ መንደሬ
ውብ ዓይናማይቱ ትግራይ አገሬ መንደሬ
እስከ መጨረሻ  ካንቺው ጋር ነው ልቤ
ላንቺ የማይሆን የለም ትግራይ አገሬ
ይማርብሽ ተሸላለሚ ተዋቢ ትግራይ አገሬ
አገራችን ትግራይ የቀን ብርሃን አየሽ
ስለወለድሺው ቆፍጣና ልጅሽ
አያችሁት አይደል መራራ ጀግና
የትግራይ ልጅ ጎሚዳ (ደምሳሽ፤ አርበኛ፤ጀግና፤አሸናፊ ….)
ላንቺ የማይሆን የለም ተሸላለሚሊኝ
በወርቅ አጊጢሊኝ
አያችኋት አይደል ታጀባ በመብራት
ውብ ዓይናማዋ ትግራይ ተኩላ  አምሮባት።

ይላል አበበ አርአያ።በጣም የሚገርመው ዘፋኙ (አበበ አርአያ ኗሪነቱ አሜሪካ ነው።) ይህ ከላይ የተጠቀሰው ግጥም እና ዜማ የዘፈነው በረሃ እያለ ነበር የዘፈነው። ዘፈኑትግራይ የዓይኔ ብሌን፤ ትግራይ፤ ትግራይ፤ ትግራይ…) ከሚለው በተጨማሪደርግን፤ ኢሕአፓን፤ኢዲዩን አሸነፍን ወዘተ..ወዘተ እያለ ትግራይን እንደ ልዩ ፍጡር እና አንባሰ በመሳል ሲያሞግስ የገጠመው ነበር: ሆኖም፤ ዛሬ ይህ ፖለቲካዊ ዘፈን 2009 .(2017) ሮማናት አደባባይ መቀሌ ከተማ ውስጥ አመታዊው የአሸንዳ በዓል በተከበረበት ወቅት በሺዎች የሚቆጠሩ የመቀሌ ታዳጊ ንኡሳን ወጣት ሴቶች አደባባይ ተሰብስበው የአሸንዳ በዓል ሲያከብሩ ይህ ፖለቲካ ይዘት ያለው ሙዚቃ እንዲያዳምጡ መደረጉ ባሕላዊ በዓሉን በመጠቀም ፖለቲካዊ ቅስቀሳ እንዲተላለፉ መደረጉ አሳዛኝ ብቻ ሳይሆን ወያኔዎች ሕዝባዊ ባሕሎችን እንደ ናዚዎች እና ፋሺስቶች ወደ የፖለቲካ መድረክ መቀስቀሻ ማድረጋቸው፤ ይቅር የማይባል ፋሺስታዊ እና ሕገ ወጥ እንደሆነ የታሪክ ጸሐፍት እንደሚዘግቡት ተስፋ አለኝ።

ይህ ዘፍኝ ብቻ ሳይሆን ሰለሞን ባይረ (የለየለት ጠባብ ትግራይ ብሔረተኛ ሙዚቀኛ) እንዲሁም ሕሉፍ አለሙ የተባለው እጅግ፤እጅግ በጣም የከረረ ትምክሕት እና የትግራይ ብሔረተኛነት ስሜት ያንገላታው ሙዚቀኛ (ዑንቅ ባሕሪ፤ደቂ ዑንቂ ባሕሪ-- የዑንቅ ባሕር ልጆች) የሚለው ዘፈኑ እና ብዙዎቹ እዚሁ አደባባይ ተገኝተው ነበር የፖለቲካ አጠባቸውን በጥናት ተጠንቶሆን ተብሎለታዳጊ ህጻናት በአሸንዳ ወቅት ሲያስተላልፉ የነበሩት። እጅግ አሳዛኝ ክስተት! ባሕላዊና ሃይማኖታዊ በዓል ለፖለቲካ መቀስቀሻ መድረክ አድርገው ሲጠቀሙበት ማየት አጅግ አስገራሚ ነው።

ሌላው እጅግ አስፈሪ ፋሺስታዊ የትግራይ ብሔረተኛዊነት ትምክሕት በግልጽ የሚያስተምር ግጥምና ዘፈን በቀዳሚ ምሳሌ የምንምለከተው ሙሉጌታ ካሕሳይ (በቅጽል ስሙወዲ ሮሚጥ”) በመባል የሚታወቅ ትግራዊ ብሔረተኛ ምን እያለ እንደሚዘፍን መልዕክቶቹን ስናጤን። የትግራይ ሰው ከሰው ሰውነት አውጥተው ወደ ፈጣሪነትና ልዩ ፍጡርነት (ፈጣሪ…) አስገብተው፤ የሰው ልጅ ብቻ ሳይሆን ግዑዝ (ዕቃ፤ድንጋይ፤ ዛፍ፤ተራራ፤ነፋሰ…) ሁሉ ሳይቀር በትግሬዎች ተደንቀዋልይላል። ያውም ነጋሽ እና አንጋሽ ነን እንጂ ሥልጣን ከማንም ተቀብለን አናውቅም ይላል ፋሺስታዊ ትምክሕት ያለው የገጣሚው መልእክት።

የዘፈኑ ርዐስ
ከመይ ኣለኻ!’
(አንደምን አለህ!?)
ከመይ ኣለኻ?
ዘፋኝሙሉጌታ ካሕሳይ
( ወዲ ሮሚጥ)
ሕዝቢ ትግራይ ክባሃል ውሽጠይ ፍናን፤ፍናን ይወረኒ
ልበይ ታሕጓስ ፍግዕ ይብል አሎየ፤ ልበይ ታሕጓስ ፍንፅሕ ኢሊ
ከመይከ ኣለኻ?
ጥበብ ኮይንካ……..
መዋእልካ
ጻዕዳ ከምፈረስ፤  ኣብ በረኻ ትሕለቕ
ሓንሳብ እውን ሓፂን ፤ሓንሳብ እውን መብረቕ ሕዝቢ ትግራይ ነጋሲን አንጋሲን
አማዕዚንካ መራሕን ገናሕን
እሞድማ ውሑድን ሙሩጽን
እንኳይ ንሰብ ንጉኡዝ ዘህንን
ሕዝቢ ከምሓደሰብ ይጽዋዕ፤
ከም ሓደ ይሕሰብ ከም
ይሕሰብ ማዕርነት ክብሩን
ሕልፊ ዘይደሊ ግን ሕልፊ ገቢሩ
 (ሕልፊ መስዋዕቲ)
ንከይጎብጥ ካን ታአምር
ንዝጎብጦ ግና ሕልፊ እዩ መሪር
ናይ ማዕርነት ብዕሪር፤
ንትንቢተ ኦሪት መላእ እዩ አፉ
ደጊም አይሓልፎን ሕዝበይ ከምሕላፉ
ኣይገድፈናን ሎሚስ ከይተማላኣና
ምን ሒዙ ክኸድ ሰብ ዋና ከለና
ወዲ ትግራይ ክባሃል ከሎ
ፍናን ፍናን ይወረኒ አሎ
ልበይ ብታሕጓስ ፍንጽሕ
ክብል ኢሉ አሎ
ከመይ ከመይ ከምይ ኣለኻ
እንግዳዕኻ ሥልጣነ ፈለማዊ
መቦቆልካ ንግሥተ ሳባዊ
ማይ ፈለግካ ጥበብ ያሬዳዊ
 ፈላስፋዊ ዘርዓ ያዕቆባዊ
ዘረባኻ ይነትዖ ሊቅነት
ማኣድኻ የኩልስ ጅግንነት
ከመይ ኣለኻ?
 2017 በፈረንጅ ዘመን የወጣ አዲስ የትግርኛ ዘፈን።
ዘፋኝሙሉጌታ ካሕሳይ (ቅጽል ስሙወዲ  ሮሚጥ”)
ትርጉም
          እንደምን አለህ ?
 (የትግራይ ሕዝብ ህልውናውን ሲጠይቅ ነው)
 ሙሉጌታ(በቅጽል ስሙወዲ ሮሚጥ”)
የትግራይ ሕዝብ ስም ሲነሳ ውስጤ
ኩራት ኩራት ይለኛል፤
ልቤ በደስታ ይሰነጠቃል
እንደምን አለህ ጤናህ ህልውናህ
ጥበብ ሆነህ፤ጥበብ አስተምረህ
ጥብቅና ቆመህ
መላ ህይወትህ ሰጥተህ
ለግፉኣን ስትል በረሃ ወጥተህ
ለመሆኑ አንተ እንደምናለህ!
ቁመናህ ያምራል እንደ ነጭ ፈረስ
ትሆናለህ አንዴ እንደ ብረት
አንዴ አንደ መብረቅ
የጀርባ አጥንትህ ሥልጣን ጀማሪ
ሥልጣን አስተማሪ፤ ሥልጣን አበሳሪ
መሰረተ ዘርህ ንግሥተ ሳባዊ
ምንጨ ልሳንህ ጥበብ ያሬዳዊ
ፈላስፋዊው ዘርዓ ያዕቆባዊ
ምድርህ ይረጫል/ያመነጫል ሊቅነት
ማአድህም ያጎርሳል ጀግንነት
የትግራይ ሕዝብ ነጋሽ እና አንጋሽ
በየመአዝኑ መሪና አራሚ
ያውም ጥቂት ሆነህ
ብትሆንም ምርጥ ነህ
እንኳን ለሰው ፍጡር ግዑዝን አስገርመህ።
አንድ ሕዝብ አንድ ነህ
ገስግስ አንድ ልብ አንድ ሃሳብ ሆነህ።
ትርፍ የማይፈልግ
ግን ትርፍ ግብሮ/መስዋእት ከፍሎ/
 የራሱ ያልሆነ ከቶ የማይፈልግ
 መልሱ መራራ ነውለሚቃጣው ሁሉ
 አርማ ነው ይጨሳል
 እንደ ብሪር ዕጣን ይጨሳል ይበግናል
ቢፈታተኑትም እንደማለፉ ያልፋል
ብሎ ቸል አይልም ከእንግዲህ ይበቃል!
 ይኼው ማስጠንቀቂያው
ይሞካክረናል ሥልጣን የሚጋራው
ዛሬስ አይተወንም ይዞን እንዳይጠፋ
ባለቤቶቹ እያለን ነጋሽ እና አንጋሽ
ይምጣ ይሞክረን ማንስ ይበገራል!
ማን ሆኖ ነው ማንስ  ይነጥቀዋል!
(ትርጉም ጌታቸው ረዳ ) (112) (የትግራይ ብሔረተኞች በአማራ ላይ ያላቸው ጥላቻ ከምን የመነጨ ነው ከሚለው መጽሐፍ)

እንዲህ እና የመሳሰሉ በጣም በርካታ የሆኑ የትምክህት ሙዚቃዎችና ግጥሞች እያታተሙ የወጡን አስተሳሰብ በጎሰኛነት ትምክሕት ተጠምዶ በጉረኛ መንፈስ እየተጓዘ ሌሎችን በመናቅ አገራዊ ማንነቱን እንዲፍቅ፤የትግራይ ሕዝብ ልዩ ፍጡር የሆነ፤ እሱ ነጋሽ እና ሌሎችን  የሚያነግሥ በሚል የተወጠረ ፋሽታዊ ቅስቀሳ እንደሆነ ተመለክተናል።ሃይማኖታዊ እና ባሕላዊ በዓላትን የፖለቲካ መጠቀሚያ በማድረግ ወያኔም ፋሺስቶች የሚጠቀሙበትን ዘዴ ትክክለኛ ቅጂ በመቅዳት የኪነት ሰዎችን ወደ ፖለቲካው በማሰማራት በተጠቀሱት በዓላት ላይ ከፍተኛ የሕሊና ብረዛ ሥራ ላይ አሰማርቶ ባሕልን ሃይማኖትን ወደ ፖለቲካ ጠልፎታል። ይህ እንዲቆም ለትግራይ የስነ ጥበብ ሰዎች ፋሺስታዊ አገልግሎት መስጠታቸው እና መሳሪያ መሆናቸውን እንዲያቆሙ ጥሪ አቀርባለሁ። ዛሬም ደብረጽዮን ገብረሚካኤል የወያኔው ሊቃነ ጳጳሳት ከሆኑት አቡነ ማትያስ በተገኙበት አዲግራት የ2011 የመስቀል ደመራ ዓበል ተገኝቶ ትግሬዎች እንደ ሁለተኛ ዜጋ ሲታዩ ነበር እያለ ያልሆነውን የውሸት ታሪክ በመፍጠር የወቱን ሕሊና ‘በመበከል’ ሃይማኖታዊውን በዓል የአንድ ትምክሕተኛ እና ፋሺሰታዊ የፖለቲካ ድርጅት መጠቀሚያ ሆኖ በማየቴ በሃይማኖት ላይ እየተደረገ ያለው ሕገ ወጥ ፖለቲካዊ ሰበካ እንዲቆም ጥሪ አቀርባለሁ። 
ሰላም እንሰንብት
ጌታቸው ረዳ (የ Ethiopian Semay ድረገጽ አዘጋጅ) getachre@aol.com







No comments: