Sunday, October 7, 2018

የግብረሰዶም ሰንደቃላማ ምልክቶች የታዩበት የ2011 የመስቀል ደመራ በዓል አስከፊው ገጽታ እና ኦሮሞዎች እሬቻ እና ገዳ የተባሉ ሃይማኖታዊ እና አስተዳደራዊ ባሕል ኦሮሚያ ለሚለው ፖለቲካ መጠቀሚያ እና የትግሬ ወያኔዎች አሸንዳ የሚባለው ሓይማኖታዊ የጭፈራ በዓል ወደ ፖለቲካ የመጠምዘዝ አባዜአቸው ሲፈተሽ ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay ኢትየጵያን ሰማይ)


የግብረሰዶም ሰንደቃላማ ምልክቶች የታዩበት የ2011 የመስቀል ደመራ በዓል አስከፊው ገጽታ እና ኦሮሞዎች እሬቻ እና ገዳ የተባሉ ሃይማኖታዊ እና አስተዳደራዊ ባሕል ኦሮሚያ ለሚለው ፖለቲካ መጠቀሚያ እና የትግሬ ወያኔዎች አሸንዳ የሚባለው ሓይማኖታዊ የጭፈራ በዓል ወደ ፖለቲካ የመጠምዘዝ አባዜአቸው ሲፈተሽ
ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay ኢትየጵያን ሰማይ)

ይህ ክፍል የኦሮሞዎች እና የትግሬ ናዚዎች ያስፋፉት የወንጀለኛ ስነልቦና ባሕል ለማስወገድ ሦስት ትውልድ ሊጠይቅ ነው” በሚል ርዕስ ባለፈው ሰሞን የተቸሁበት ክፍል ተያያዥነት ያለው ቀጣይ ክፍል 2 ትችት ነው።

እንደምን ሰነበታችሁ? ሁሌም ሃቅ ሲነገር የሚጎመዝዛቸው ሰዎች አሉ። ታሪክን በተጨባጭ አስረግጠን ስናቀርብ ያንን ታሪክ መቃወም ሲያቅታቸው በቀጥታ የሚጠቀሙበት አማራጭ ተቺውን በጸረ ኦሮሞ ወይንም በጸረ ትግሬ የማላከከክ አባዜ የተለመደ ነው። ቢሆንም ሃቅ ‘ሃቅ’ ነውና በራሱ ቢቀብሩት በእግሩ የመውጣት ችሎታው በብዙ አጋጣሚዎች ስለታየ ብዙም ሳንጨነቅ ሃቅ ሃቁን መነጋጋር አንቀጥልበታለን። ይህ ተቺም ለበርካታ አመታት ከሃቅ ቆሟል ዛሬም ነገም ይቀጥላል።

በተለያየ መልእክት በርታ ብላችሁ ትችቴን ያስደሰታችሁ ወገኖች አመሰግናለሁ ለናንተም ለቤተሰብም መልካም መስቀል እንዳሳላፋችሁ ተስፋ አለኝ።

ስለ ሰሞኑ ‘የፋሺስቶች የሃዋሳ’ ትዕይንት አንድ ልበል እና ወደ ርዕሳችን እንገባለን።

የቀድሞ መምህራን ማሕበር ሊቀመንበር አርበኛው ዶ/ር ታየ ወልደሰማያት በኢትዮፓትርዮት ድረገጽ በሰጠው የሰሞኑን ቃለ መጠይቅ እንዳለው “እስር ቤት መግባት የነበረባቸው ብዙ ወንጀል የፈጸሙ ወንጀለኞችን ከሥልጣን ስንብት በሚል የምስጋና ምስክር ወረቀት ተሰጥቶአቸው ገለል እንዲሉ ከመደረግ ትዕይንት ጀምሮ” ሞቅ ደመቅ ባለው የአዋሳው (ሃዋሳ) ሽር ጉድ ተገኝታችሁ የወያኔው ቀዩ ባንዴራ እጃችሁ ላይ ጨብጣችሁ የታደማችሁ እነ ብርሃኑ ነጋ የመሳሰላችሁ ተደማሪዎች እንኳን ደስ አላችሁ! ምርኩዝ ሰጥቶ የጥገና መንገዱን እያሳያችሁ የሚገኘው ኢሕዴግ ብሎ ራሱን የሚጠራ “የፋሺስቶች ጥምረት” በትዕይነት (ድራማ) በሙዚቃ በግጥም እና በጭብጨባ ተሞሽሮ በሰሞነኛው ጫጉላ (ቬኬሽን) ሰንብቶ ብቅ ብሏል። ጉደኛ ምሁር እና ጋዜጠኛ ተብዬውም በፋሺስቶች የወንበር ውድድር ማን ተወዳድሮ እንዴት እና ስንት ቁጥር እንዳገኘ ትልቅ መነገጋርያ አድርጎ ማሃይሙ የፓልቶክ ማሕበረሰብ እያዝናና ሰንብቷል። ለማንኛውም ወደ ርዕሳችን እንግባ።


ዛሬ የምንወያይባቸው ጉዳዮች በርካታ ርዕሶች ናቸው። ሰሞኑን የ2011 ዓ.ም የኦርቶዶክስ የመስቀል ደመራ በዓል ሲከበር የታዩ የግብረሰዶማዊ ቀለሞች በበርካታ ዜጎች በማሕበራዊ ድረገጾች የተለቀቁት አንዳንድ ቅሬታዎች እና ኦሮሚያ በተባሉት ቦታዎችም ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን የምታውለበልበው ሰንደቃላማ እና መዘምራን የሚለብሱት ልብስ የኦሮሞ ባንዴራ እና መዘምራኑም በኦሮሞ ባንዴራ ለብሰው ደመራውን በማክበራቸው የታየው በጣም ነውረኛ ፖለቲካ ኦርቶዶክስ ላይ ለ27 አመት የተፈጸመው ግፍ ዛሬም እንደመር በሚባልበት አናርኪያዊ/ሥርዓተ አልቦአዊ “የመደመር ስልት” ተጠቅመው ኦርቶዶክስን የማጥቃት ሴራው በጉልህ የማደጉን ሁኔታ አሳሳቢነቱ አንባቢዎቼ ግንዛቤ እንዲኖራችሁ ያለማመንታት በሙሉ መነጽር እንድትመረምሩት እነሆ አቀርባለሁ። ከዚያም ኦሮሞ እና ትግሬዎች በተመሳሳይ እየተከተሉት ያለው ባህላዊ ብረዛ እንመለከታለን።  

መጀመሪያ አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በመስቀል በዓል የታየው የግብረሰዶማዊ ሕብረ ቀለማት ጉዳይ እንመልከት። በቅድሚያ ግን ይህንን ፎቶግራፍ ባመስረጃ ተመልከቱ።
ስትማቅቅ የነበረቺው  “ኤርትራ ያለቀላት የተበላሸች መንደር” በውስጥ በተሰገሰጉ ማንነታቸው የማይታወቁ የሻዕቢያ ወኪሎች መልሰው ህያው ዘርተውላት ይኼው በመዲናችን በሰረገላ ብቻ ሳይሆን የምትንፈላሰፈው፤ በሃይማኖታችን ውስጥም ዘውድ ጭና እንድናንጨበጭብላት እና እንድታሾፍብን ተደርጓል። ኤርትራውያን ዛሬም በአጅ አዙር ወኪሎቿ ትብብር ዛሬም እየገዛችን ነው። ይህንን ውርደት ስታዩ የሚቆጫችሁ ወገኖች የደም ግፊት እንዳይፈጥርላችሁ እንዳይጥላችሁ ገና ከዚህ የከፋ ውርደት ስለምንጠብቅ ትዕግስት እናድርግ።

“በዚያኛው ተገርመን ብዙ ሳንቆይ
የዚህኛው መባስ አያስቅም ወይ ?
ይኸ ሁሉ ነገር ስንት ዘመን ኖሮ
በጣም ያስገርማል ጉድ አየን ዘንድሮ”

ተብሎ  ሦስቱን አልማዞች በሚለው ጥላሁን ገሠሠ የዘፈነው ግጥም የተገጠመው ለካ ለዋዛ አልነበረም።

እንደምታውቁት የኢትዮጵያ ቤተክርስትያናት ሃይማኖታዊ በዓላት ሲከበርም ሆነ ቤተክርስትያናት እና ገዳማት እንዲሁም እስላማዊ መስጊዶች (እስላማዊ በዓላታቸው) ሳይቀር የሚያሸበርቁበት ቀለም ሦስት ሕብር ብቻ የያዘ አረንጓዴ ቢጫ እና ቀይ ቀለም ብቻ ነው።ቢያንስ ክርሰትያን አማኞች እንደ እየ አተረጓጎማቸው ቢሆንም ሰንደቃላማዋ ሦስት ሕብር “አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ” በሚል ትርጉም የሚሰጡት አሉ። በእዛው የመተርጎም እና አለመቀበል የናንተ የግል መብት ሲሆን ክቡርነቱን ለመግለጽ ግን እስከዚያ ድረስ መሄዱ ሦስቱ ቀለማት የተከበሩ መሆናቸውን ያሳያል።

በታሪካዊ በዓላትም፤ በሠርግም፤ በሙታን ሬሳዎችም፤ የመቃብር ስፍራዎችና ሃውልቶች እንዲሁም  ማንኛወም ሃይማኖታዊም ሆነ መንግሥታዊ በዓላት ላይ በዚህ ቀለም ብቻ ይሸፈናሉ/ያጌጣሉ። ይህም የኢትዮጵያ ሰንደቃላማ ነው።

‘መምህር ለማ በሱፈቃድ’ የተባሉ የቤተ ክሕነት ሰው በድረገጻቸው እንዲህ ሲሉ ስለ ሰንደቃላማ እና የማተብ ምንነት እንዲህ ይገልጹታል፡

“አንዲት ሀገር ነፃና ሉዓላዊ መኾኗ የሚታወቀው ወይም ራሷን የቻለች መንግሥት ያላት ከባዕድ ቀንበር ቅኝ ግዛት ነፃ የወጣች መኾኗ በቀዳሚነት የሚለየው በባንዴራዋ ምልክትነት እንደኾነ እንደዚኹም አንድ ክርስቲያን በክርስቶስ አምኖ በጥምቀት ከዲያብሎስ ቁራኝነት ነፃ መውጣቱ፣ ነፃነት ያለው አማኝ መኾኑ የሚታወቀው በማተቡ ምልክት ነው።” ይላሉ። እውነት ነው።

ቤተክርስትያናቶቻችን ዛሬም ግን ከዲያብሎስ (666) ሰንሰለት ዛሬም አልተላቀቁም። ለዚህ ውርደት የዳረገን “ግብረሰዶማዊው ወያኔ” ለ27 አመት የሰራበት ስራ ስለሆነ ሕዝባችን ከመበከሉ በላይ ቤተክረስትያኒቱ እና አማራውን እናንበረክካቸዋለን ብሎ በይፋ እንደተናገረው ይኼው ሴራው ዛሬም በ2011 ዓ.ም የመስቀል ደመራ በዓል በሚያስደነግጥ ትዕይንት እንድናይ በቅተናል።መምበርከክ እና አከርካሪ መስበር ማለት የሚከተለው ትዕይንት በግብር ሲፈጸም ማለት ነው።
ከላይ ያሉት ወጣት ግብረሰዶማውያን ኢትዮጵያውያን ወንዶች እና ወጣት ሴቶች ሲሆኑ
ከታች ሥር ያሉት ደግሞ ኤርትራውያን ወጣት ሴት ለዝቢያን (ሴት ግበረሰዶማውያን) ናቸው።
እነዚህ ሁለቱ የኤርትራ ሻዕቢያ  ወጣት ማሕበር አባሎች ናቸው። የለበሱትም የማሕበሩ መለያ ነው:
People’s Front for Democracy and Justice “ሕዝባዊ ግምባር ለፍትሕ እና ለዲሞክራሲ” የሚለው የሻቢያ ወደ ሥልጣን ከወጣ ወዲህ ለራሱ የሰጠው አዲስ መጠሪያ ስሙ ነው (ልክ ወያኔ ከህወሓት ወደ ኢሕአዴግ እንደሰየመው ማለት ነው)። ያንን ለማጎልበት ወጣቶቹ በ People’s Front for Democracy and Justice “Y” የሚለው ፊደል ከፊት በመጨመር “YPFDJ” የሚለው ከናቴራ ለብሰው የምታዩዋቸወም ለዚህ ነው።  

 የኤርትራኖቹን ወደ ጎን እንተው እና በአገራችን ኢትዮጵያ ማሕበረሰብ ሕሊና ውስጥ              እንዲህ ያለ ‘ትውልድ ገዳይ” የሆነ ሴራ በፖለቲከኞች ሲፈጸም፤ በቤተክርስትያናት ውስጥ ያሉ አስተዳዳሪዎችም ሁሉም ባይሆኑም በዚህ ሴራ ተባባሪዎች ሆነው የብረዛ (ሳብቨርዢን) ሴራ ተካፋዮች በመሆን እጃቸውን አስገብተውበታል የሚል ጥርጣሬ አለኝ። እርግጥ በተዋህዶ ቤተክርስትያን ያሉ አንዳንድ ጠንካራ ካህናት እና ዲያቆናት የባሕል ብረዛውን ለመከላከል ከፍተኛ ጥረት ማድረጋቸው በመጽሐፌ ውስጥ የጠቀስኳቸው ሰዎች እንዳሉ ሆኖ። አሁን ግን በመንግሥት ደረጃ ቤተክርስትያኒቷ በወያኔው አሽከር በሥርዓተ አልበኛው በአብይ አሕመድ አይዟችሁ ባይ አበረታችነት ቤተክርትያኒቷ ፖለቲካ ውስጥ ገብታ መዘባረቅ ጀምራለች። የ27 አመቱ የበከላት “የፖለቲካው ቅጥኝ” ዛሬም ኩፉኛ እያሳከካት እያየን ነው።

 በዚህ መልክ “አንዲት ሀገር ነፃና ሉዓላዊ መኾኗ የሚታወቀው ወይም ራሷን የቻለች መንግሥት ያላት ከባዕድ ቀንበር ቅኝ ግዛት ነፃ የወጣች መኾኗ በቀዳሚነት የሚለየው በባንዴራዋ ምልክትነት እንደኾነ’ እየታወቀ “ቤተክርስትያኒቷ በኢሳያስ አፈወርቂ ፖለቲካ ተበክላ እጆችዋን ፖለቲካ ውስጥ በመንከር የኢትዮጵያ መስቀል በዓል ከኤርትራ ባንዴራ ጋር በማያያዝ የኢትዮጵያ ቅዱስ ሰንደቃላማ የተዘረጉባቸው ድንኳኖች ላይ በኤርትራ ሜዳ ላይ ኢትዮጵያውያን ሲጨፈጨፉ ስትውለበለብ የነበረቺው ከፋሺስት ጣሊያኖች ባንዴራ የማንለያት የሻዕቢያ ድርጅት የወንጀለኞች ባንዴራ አብሮ በማያያዙ ሴራ ሳይቆጠብ እንደገና ይግረማችሁ ብሎ የመስቀል በዓል “ግብረሰዶማዊ ሕብር” እንዲኖሮው ሆን ተብሎ በማበላሸት የኢትዮጵያን ሉኣላዊነት በመጋፋት ተጨማሪ ወንጀል በመስራት ላይ ነች።

ባንዲት ቤተክርስትያን በስልጣን ሽሚያ ጉጉት ልቀቅ አልለቅም በወያኔዎች ሴራ የተጎነጎነ ሴራ ምክንያት ለዓለማዊ ሥልጣን ሲባል ተሰምቶ የማያውቀውን አሳፋሪ ሁለት ፓትርያሪኮች እንዲኖርዋት የመደረጉን ወንጀል ሳይበቃት፡ አሁን ደግሞ ባንድ ነፃ አገር ራሱ ሌላ ነፃ አገር ነኝ ብሎ ባወጀ የሌላ አገር የጠላት ባንዴራ በሃይማኖት ውስጥ ፖለቲካን በማስገባት ፖለቲካዊ ሴራ መስራትዋ እጅግ የሚገርም ነው። ይህ ደግሞ ሆን ተብሎ በውጭ ቅጥረኞች ሳይሆን በውስጥ  ቅጥረኞች የተሰራ የክለሳ (የ ሳብቨርሲቭ) ደባ ነው። ማን ነው ይህንን ያቀናበረው? የሚለው ጉዳያችን አይደለም። ተጠያቂው እራሳቸው የቤተክሰርስትያኒቱ የበላይ አስተዳዳሪዎች ናቸው። በሚቀጥለው 2012 የመስቀል ደመራ በዓል ቤተክርስትያኒቷ እጆችዋን ከፖለቲካ በማስወጣት እርማት እንደምታደርግ ተስፋ አደርጋለሁ።

በተቃራኒው ኤርትራኖች በተነሱበት “ጣሊያናዊ ሠራሽ ኤርትራዊ ሉአላዊነታቸው” እና በሃይማኖታቸው የማይደራደሩ ስለሆኑ በመደመር የማይበገሩ መሆናቸው አስመራ ከተማ ውስጥ ስለተከናወነው የመስቀል ደመራ አንዲትም የኢትዮጵያ ሰንደቃላማ ለምልክት እንዳትታይ በማድረግ የኤርትራ ቤተክሕነት መሪዎች እና ሕዝቡ ያሳዩት መስመራዊ ጽናታቸውን ለድርድር እንደማያቀርቡ በደመራው ላይ ያሳዩት አቁዋማቸውን ይህንን ማስረጃ ተመልከቱልኝ እና በሁለቱ በኩል የተከናወነው ልዩነት ፍርዱን ለናንተ ልተው።

meskel celebration in Asmara - ኣበዓዕላ መስቀል ኣብ ኣስመራ 2018

ከላይ ያለው የአስመራ የመስቀል በዓል ትዕይንት ስትመለከቱ በኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን መካከል ያለው የመምበርከክ እና ያለመበገር የመደመር እና ያለመደመር ልዩነት ስትመለከቱ የእኛው ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ የተባለው በከላሾች የተበከለ ቤተክርስትያን ፖለቲካ እና ሃይማኖት በማደባለቅ በመስቀል በዓል ላይ ሕዝቡም ጭምር ተምበርካኪነቱን ፤ክሕደትን እና አለቅላቂነቱን አሳይቷል። አልጌና ናቕፋ እና ምፅዋ ባሕር ላይ ያቺኑ ባንዴራ ላለማየት በገዛ ሽጉጣቸው እየመዘዙ የኢትዮጵያን ሰንደቃላማ ለብሰው ራሳቸውን መስዋዕት ያደረጉ የኢትዮጵያ ወታደሮች እና ሲቪል አርበኛ ዜጎች ዛሬ ከስንት አመት በላ ‘በተወለዱባት ኢትዮጵያ የአገራቸው መዲና አዲስ አበባ ከተማ” ውስጥ የሃይማኖታቸው እና የማተባቸው ምሰሶ በሆነው በመስቀል በዓል ውስጥ የገዳያቸው የሻዕቢያ ድርጅት ባንዴራ በክብር እየተከበረች በበቅሎ ሰረገላ ዘውድ ጭና ስታላግጥብን ተነስተው ብያዩ ሙታን አርበኞቻችን “ምን ይሰማቸው ይሆን?” ብላ ቤተክርሰትያኒቷ አስቀድማ ያለመጠየቅዋ በታሪክ መዝገብ ውስጥ በብሔራዊ ክሕደት መዝገብ ሊመዘገብ የሚገባ ክሕደት ፈጽማለች።

እንዲያ ከሆነ የሰዲን ፤የናይጄሪያ የኬንያ የሶማሊያ የአሜሪካ….ፖለቲካዊ እና አገራዊ ሰንደቃላማዎችስ በመስቀል አደባባይ ለምን እንዲቀላቀሉ አልተደረገም? አንድ ነን ለማለት ከሆነ ኤርትራኖች አንድ ያለ መሆናችንነ ባሳዩት የመስቀል በዓላቸው ነግረውናል፡ ስለዚህ ቤተክርስትያኒቱ የወያኔ እና የአብይ ፖለቲካ ማንጻበረቋን እንድታቆም እንጠይቃለን። ለዚያውም እንደ አንድ ክርስትያናዊና ኢትዮጵያዊ ለቤተክረስትያኒትዋ በክፉ ቀንዋ ጥብቅና የቆምኩኝ ፖለቲከኛ ተሟጋች እና ጸሐፊ ይቅርታ እንድትጠይቀኝ እጠይቃለሁ። ከጊዜ ወደጊዜ እየጨነቀኝ የመጣ የሚያስጨንቀኝ ጥያቄ ኢትዮጵያን እንደ ኢትዮጵያ ተከራክሮ ማንነትዋን የማያስደፍር መሪ ከየት እንደሚመጣ በጣም እየጨነቀኝ ነው። አብይ የተባለው የክለሳ ደማሪ አገራችን እና ሰንደቃላማችን ተምበርካኪ እንድትሆን ከወያኔ ጋር እኩል እየሰራ ነው። ወያኔ ያስተማረው የባንዴራ ክለሳውንም እውን እንደሚያደርግ ደጋግሞ ቢነግረንም ዛሬም ተምበርካኪው ተቃዋሚ ቡድን እና ምሁሩ ዛሬም በሚያሳፍር ሁኔታ በኮቴው ስር እየተጎተተ የተለያ  ባንዴራዎች እያውለበለበ ‘ኮት ኮት’ ማለቱ እና ቢውለበለብም “የዲሞክራሲ ዕድገት” ነው በማለት አገር በማፍረስ ትብብር እና በሳብቨርሲቭ/በብከላው ዘመቻ እጁን ማስገባቱ በማየታችን ዛሬም በድርጊቱ ደጋግሞ እየተገረምን ነው ።

አማራ ፋኖ የተባለው ለአመራ ቆምያለሁ የሚል ወጣት ክፍልም ሰንደቃላማን አስመልክቶ ቄሮ ለተባለው ‘ኦሮሞ ወጣት’ በላከለት ያልበሰለ አሳፋሪ መልእክቱ እንዲህ ይላል፦

“ባንዴራን በተመለከተ የማለያየታችን ብቻ ሳይሆን የማፋቀሪያችን ማድረግ ይቻል ነበር፡ ይኼውም አንተ የኔን ባንዴራ ይዘህ በራስህ ክልል ላይ ስትወጣ እኔም ያንተን ባንዴራ ይዤ ክልሌ ላይ በመውጣት ነው።ልክ እንተ ‘ጣና ኬኛ’ ብለህ አረም እንድትነቅል እንደመጣኸው ማለት ነው።” ሲል በተለቀቀው ‘ዩቱብ’ መልዕክቱ እጅግ አሳፋሪ እና የኢትዮጵያዊነቱን አርማ የካደ መልዕክት አስተላልፏል። ኦሮሞ በገዛ አገሩ ጣና ለኔም ይደርሰኛል አገሬ ነው ብሎ ዜግነታዊ ግዳጁን በማሳየቱ በዚያው ልክ የዚያው ብድር ማወዳደርያ የሚሆን አማራን ስትጨፈጭፍ የነበረቺወ የግንጠላ እና የጥላቻ አርማ የሆነቺውን “የኦሮሞ ነፃ አውጪ” (የኦነግ) ባንዴራ በአማራ ምድር ላይ እንዲውለበለብ የሚሰብክ የአማራ ወጣት ንቃቱ የዘቀጠ መሆኑን እና አገሪቱ ለደረሰችበት የብከላ እርከን ተዋናይነቱን እና ፈቃደኛነቱን ያሳየበት በተቃራኒ የተጎተተ፤ “የሚጓዝበትን መርሆ የማያውቅ” ትውልድ መፈጠሩ የተበከለው የትውልድ ሕሊና ምን ያህል መሆኑን ይህ ግልጽ ማስረጃ ነው። ብከላውን ለማጽዳት ‘ሦስት ትውልድ’ ይፈጃል ብየ የምከራከረውም ለዚህ ነው። ባሕርዳር ላይ ጃዋርን ጋብዘው “27 አመት ሲሰቃዩ አስታዋሽ አጥተው ለነበረው ለአመራ ማሕበረሰብ በመቆምህ እጅግ እናመሰግናለን” ብለው እንዳሉት አይነት ወጣቶች ለ27 አመት ከተበከለው ብከላ ለመጽዳት በርካታ ትውልድ ይፈጃል። 

ኦሮሞዎ ተገንጣዮች እና የመስቀል በዓል ብከላቸው

“የኦሮሞ ነፃ አውጪዎች እና የትግሬ ነጻ አውጪ” የተወለዱባቸው ጎሳዎች ነባር ባህሎችን ድርጅቶቹ ከሚከተሉት የፋሺስት እምነታቸው በማዋሃድ ባህልን የፖለቲካ መነገጃ ያደረጉበትን አባዜአቸው እንመልከት።   

ኦሮሞዎች እና ትግሬዎች ለ27 አመት የተከተሉት ፖለቲካ “የፋሺስቶች”  ዕዮተ ዓለም  እንደሆነ ብዙ ጊዜ ገልጸነዋል። ኦሮሞዎች ዛሬ በወያኔ ተበድለናል ቢሉም ይህ ጸሓፊ ለብረካታ አመታት ኦሮሞዎች  በወያኔዎች ስርዓት ተጠቃሚዎች እንደነበሩ ተከራክሯል። ኦሮሞዎቹ ወያኔዎች ጋር አባሪ ተባባበሪ ሆነው 3/4 ኛ የመላዋ አገሪቱ ዜጎች የመሬት ይዞታ የኦሮሞዎች ነው በማለት በአፓርታይዳዊ በባለቤትነት ዋና ባለቤቶች ሆነው ዜጎችን በማፈን እና በማባረር ሰፊ ግዛት ይዘዋል። አገርን ለማፍረስ ፋሺስታዊ መንገድ በመከተል ለኦሮሞ ጥብቅና ቆመናል የሚሉ የተለያዩ የኦሮሞ ድርጅቶ ኦሮሚያ ተብሎ አዲስ ስም በተሰጠው 3/4ኛው “አፓርታይድ ክልል” የሚኖሩ የኢትዮጵያውያን ዜጎችን ዘር በማጥፋት እና ከክልላቸው በማስወጣት አፓርታይዱን ስርዓት አሞግሰው ተቀብለው በቅርሚቱ ተካፍለዋል። በዚህ ወንጀል የተካፈሉ ድርጅቶች ማለትም “ኦነግ፤ኦሕዴድ፤እስላማዊ ኦረሚያ ነጻ አውጪ (ጃራ የሚመራው) … ናቸው። እነዚህም በዋናነት በወያኔ አይዞህ ባይነት እና መሪነት ኦሮሞ ባልሆኑ ገበሬዎች አስተማሪዎች ነጋዴዎች “በተለይም” በአማራ ላይ የስነ ኣእምሮ የንብረት እና የአካል ጉዳት አድርሰዋል።

ኦሮሚያ የተባለው “የአፓርታይድ ክልል” ብዙ ግፍ የተፈጸመበት ክልል ነው ብቻ ሳይሆን እዛው ያሉ ኦሮሞዎች እና ሌሎች ኢትዮጵያውያን ከዋና ኢትዮጵያዊነት ባህል እና ምልክት አስወጥተው ድሮ “ጋሎች” ሲጠቀሙበት የነበረው “ገዳ” የሚባል ጭካኔ የበዛበት ባሕል ኦሮሞዎች ታይቶ የማይታወቅ ‘ሰብአዊነት የተላበሰ ዲሞክራሲያዊ’ አስመስለው በማቅረብ (አብይ አሕመድም በቅርቡ ሊሰብከን የሞከረውን አስታውሱ) ኦሮሚያ ለተባለ አዲስ የአገር ቀረጻ ፖለቲካ በማዋል የዓረቦች ቀለም የያዘ የገዳ ባንዴራ በመፍጠር “ኦሮሚያ” በሚባል ፖለቲካ እጁን በማስገባት አንዳንዴም በማስፈራራት (አብይ ካልተመረጠ ኦሮሞ በሙሉ ቢላዋ ይዞ ይጠባባቅ እንደነበር የሚለው የአባ ገዳ በየነ አስደንጋጭ ንግግርን አስታውሱ) አዲስ የሕሊና ለውጥ በወጣቱ ላይ እንዲቀረጽ አስተዋጽኦ እያደረገ ነው።

አባ ገዳ በየነ ማለት በሚከተለው ፎቶ ከጃዋር መሓመድ ጋር ያሉት አዛውንት ናቸው፤
ኦሮሞዎች በወያኔ ስርዓት ተጠቃን የሚሉት በጣም በቅርብ ነው። ኦሮሞዎች ተጠቅተዋል ቢባልም፡ ቢጠቁም እንኳ ኦሮሞዎች ሰፊ መሬት እና የራሳቸው ሰንደቅ፤ መዝሙር፤ ባህል፤ የላቲን ባዕዳዊ ፊደል ተበድረው አማርኛን በማስወገድ ቄሮ የሚሉዋቸው “ወጣት’ ኦሮሞ ትውልድ ከተቀረው ዜጋ እንዳይግባቡ አደንቁረው፤ ወጣቶቹ ለዚህ አደገኛ መለያየት ተዳርገው ኢትዮጵያን ባዕድ አድርገው የራሳቸው ባንዴራ ቀርጸው ሌሎች ዜጎች አስመስለው ራሳቸው በማቅረብ ከላይ የተጠቀሱ የፖለቲካ ድርጅቶች ሰለባዎች ሆነዋል።

በዚህ 2011 በተከበረው የመስቀል ደመራ አከባበር በዓል ከኢትዮጵያዊ ተዋህዶ ቤተክርስትያን አገራዊ ሰንደቃላማ እምነት ውጭ ኦሮሞዎቹም የናዋ ቤተክረስትያን የብከላ ድርጊት እየተማሩ የራሳቸው ኦሮሚያ የሚባል አዲስ አገር እና አዲስ ባንዴራ ከነ ልብሳቸው ለብሰው በዓሉን ሲበክሉ ውለዋል። ገዳ የሚባለውም ቤተክርስትያኒቱን ተቆጣጥሮ የራሱን ባንዴራ እና ምልክት ተክሎባታል። ይህንን ባንዴራ እና የደመራ በዓል ተመልከቱልኝ፡-ኢትዮጵያ ሰንደቅአላማ ከቤተክርስትያኒቱ ጨርሶ እንዲወገድ አድርገውታል። ጌታቸው ረዳ ስሕተት ከሆንኩኝ ስህተቴ የት እንደሆነ አስረዱኝ።


ይህንን ስንመለከት አገራችን ሃይማኖትዋን፤ ማሕበራዊ ግንዛቤዋን፤ባሕልዋን ቋንቋዋን አንድነትዋ ለ27 አመት የተሰነዘረው የብከላው (ሳብቨርዥን) ዘመቻ እዚህ ድረስ መድረሱ ለምትረዱ ዜጎች ኢትዮጵያ የቁም ሙት መሆኗን መረዳት አለባችሁ። አልሞተችም ብላችሁ አትጃጃሉ። ኢትዮጵያ ሞታለች! ጠላቶች አሸንፈዋል። ቤተክርስትያኒቷም አከርካሪዋን ሰብረናታል ብለው የፋሽቶች ድርጅት የወያኔ መሪዎች የሆኑት ስብሓት እና መለስ እንደተናገሩት ዛሬ እውነትም እነሱ ያቀዱት አከርካሪዋን የመሰበር አውነታ አይተናል። ልባችን በሃዘን ተሰብሯል።

ቤተክርሰትያኒቷ ከሕግ ውጭ በሥልጣን ጉጉት ምክንያት በሚያሳፍር ክስተት በሁለት ፓትርያሪኮች እየተመራች ነው። ስለሆነም ድክመቷ አይተው አከርካሪዋ መሰበሩን የታዘቡ ጸረ አንድነት ሃይሎች የፈለጉትን ባንዴራ በማውለብልብ እና ደመራውም ገዳማቱንም ቤተክርስትያናቱም ቅዱስ ጽላቱም ጭምር በሚገርም ሁኔታ እያራከሱዋት ይገኛሉ። መደመር ማለት ትርጉሙ እስኪጠፋን ድረስ የእስላሞችን ተገንጣዩም የግብረሰዶማዊ ህብረ ቀለማቱንም የፈለገው ባንዴራ እና ቀለም በማውለብለብ እና ቅዱሳን አልባሳትም በፈለጉት የፖለቲካ እና ግብረሰዶማዊ ሕብረ ቀለማትና ምልክቶች ቢለብሱ ቅር የሚለው ሰው እንደሌለ እስኪመስል ድረስ ሕሊናችንን በይፋ መፈታተን ጀምረዋል።


 ቤተክረስትያኒቱን ለማራከስ በታቀደው ሴራ መሰረት፤ የፋሺስቶች አባል “የሆነው የጥገና መሪ” አብይ አሕመድ “ማንም ሰው/ድርጅት/የፈለገው ባንዴራ ማውለብለብ ዲሞክራሲያዊ መብቱ ነው” ባለው መሰረት ቤተክርሰትያኒቱም የጥገናው ስርዓት መሪዋን ንግግር እውን ለማድረግ በቤተክርትያኒቱ ዙርያ የሚውለበለቡ ባንዴራዎች አልባሳት እና የሚንጸባረቁ ውስጠ ትዕይንት ምስጢጢራዊ (ኮዶች) ነጸብራቆች እና የሚደረጉ ድርጊቶች መቆጣጠር አቁማለች። በአብይ እና አድናቂዎቹ መሰረት ማንም ሰው የፈለገው ባንዴራ ምልክት ይዞ “666 ኢሉሙናቲዎች እና ግበረሰዶማውያኖችም ባንዴራቸውን ይዘው አደባባይ ወጥተው ማውለብለብ ይችላሉ ብለዋል እና ብከላው ይቀጥላል።” ፈጣሪ በቤተክርሰትያኒቷ መሪዎች የአባ ጳውሎስ መቅሰፍት እና የመለስ ዜናዊ መቅሰፍት ፍርድ በቅርቡ ቢያወርድባቸው ምን እንደምትሉ አላውቅም።

የገዳ እና እሬቻ ጠባሉት የኦሮሞዎቹ ወታደራዊ እና ሃይማኖታዊ ስርዓቶች

 የገዳ ስርዓት ምንጩ የኦሮሞዎች ነው የሚሉ አሉ፡ የነሱ አልነበርም የሚሉም አሉ። አካራካሪ የሆነው የማን ነው የሚለው ሳይሆን ይህ ወታደራዊ ባህል ከጋሎች የተወረሰ ወታደራዊ አስተዳደራዊ ባሕል መሆኑን ግን በወቅቱ የነበሩ የመጀመሪያው ገዳ አስተዳደር በጽሑፍ ቀርጸው ለዓለም እና ለዛሬዎቹ ኦሮሞዎች በግዕዝ ዘግበው የተውላቸው የተዋህዶ ቤተክርሰትያን የገዳም  ርዕሰ ደብር የነበሩ ኢትዮጵያዊው ጋሞገፋው ተወላጅ/ኗሪ?/  “አባ ባሕሪ”  እንደሆኑ በተውልን የግዕዝ መጽሐፍ ለማወቅ ተችሏል። በብዙ አገር የውጭ ቋንቋዎች ቢሰተረጎምም ብቸኛው እና በጥሩ ትርጉም ከግዕዝ ወደ አማርኛ ተርጉሞው ያሳተሙልን “የአባ ባህሪ ድርሰቶች” የሚለው በክቡር ፕሮፌሰር ጌታቸው ሃይሌ የታጻፈውን መጽሐፍ ያረጋግጣል።

የገዳን አስተዳዳር እና አወቃቀር ለማወቅ የተተረጎመው አስገራሚ መጽሐፍ ያንብቡ። ኦሮሞዎቹ ይህ ስርዓት ዲሞክራሲያዊ ነው በማለት ቢያሞካሹትም ሠዓሊ አምሳሉ ገብረኪዳን እንዲህ ሲል ስለ ገዳ ምንነት ይገልጻል።

“በገዳ ሥርዓት በመሪነት የሚሾመው አባ ገዳ በመባል የሚጠራው ሰው ቢያንስ ቢያንስ የሌላ ጎሳ የሆነ አንድ ሰው የወንድ ብልት የሰለበ መሆን እንዳለበት ይደነግጋልና ነው፡፡ ለአባገዳነት በሚደረገው የምርጫ ሒደት በርካታ ሰው የሰለበ ሰው የተሻለ የተመራጭነት ዕድል ያገኛል፡፡ሌላው ቢቀር ግን አንድ ሰው ያልሰለበ ሰው ለአባገዳነት በፍጹም ብቁ አይደለም፡፡ አባገዳዎች የወንድ ብልት ቅርጽ ያለው ምስል በጌጥ መልክ እንደ ቀንድ ግንባራቸው ላይ ቀስረው የሚያስሩት ይሄንን ለማመላከት ነው፡፡ አውሬ ወይም ለማደን አስቸጋሪ የሆነን እንስሳ የገደለ አዳኝ የገደለውን አውሬ ወይም እንስሳ ጥርስ፣ ጎፈር፣ ቀንድ፣ ለምድ ወይም አንዳች ነገር “የዚህ አውሬ ገዳይ ነኝ!” ለማለት ምልክቱን አንገቱ ላይ ወይም ጆሮው ላይ እንደሚያንጠለጥለው ወይም ጭንቅላቱ ላይ እንደሚያደርገው ሁሉ ማለት ነው፡፡ በዚሁ ልማድ እነዚህም ሰው የሰለቡ መሆናቸውን ለማመላከት/ለመግለጥ የወንድ ብልት ቅርጽ ያለውን ምሥል ግንባራቸው ላይ ያደርጋሉ። የዚህ በጌጥ መልክ የተደረገ የወንድ ብልት ቅርጽ ምሥል ምንነት፣ ዓላማና መልእክት ይሄው ነው ሌላ ነገር የለውም፡፡ 

ዛሬ ላይ ያሉ የገዳ ሥርዓት አራማጆችና ትንሣኤ የሰጠው ወያኔ ሥራዓቱ የደነገገውን የመስለብን ግዴታነት ቢሸፋፍኑትም በግልጽ በተቆረጠ የወንድ ብልት ቅርጽ ግንባር ላይ የሚቀሰረውን የወንድ ብልት ምስል የባሕላዊ ትውፊት ግን መደበቅ አልቻሉም::

እሬቻም እንዲሁ ችግር ያለበት ባሕላዊ ሥርዓት ነው”” በማለት በዘመኑ የዓየን ምስክሮች ያረጋገጡት ጽፈውት የተወትን መዛግብት የተረጋገጡበትን ነው አምሳሉ በእርግጠኛነት እየነገረን ያለው። ይህንን ጉድ ለማጥናት ከፈለጋችሁ ከላይ የተጠቀሰው ምጽሀፍ አማዞን የመጻሕፍት መሸጫ መደብር ላይ ፈልጋችሁ ማንብብ ትችላላችሁ
በገዳ ስርዓት ደምብ መሰረት አንድ ወጣት ለመዳር ከፈለገ ከመዳሩ በፊት አንድ የወንድ ብልት መስለብ አለበት። መስለቡንም በይፋ አዳባባይ ይዞ ማሳየት አለበት።ካልሆነ ጸጉሩን ሳይላጭ ዕደሜ ልኩ በቅጫም እና ቅማል እየተበላ ይኖራል። ይህ ዲሞክራሲያዊ ነው እየተባለ ለዓለም የመጀመሪያ ዲሞክራሲየ የተበረከተ የሚባልlት የወረራ እና ጥንታዊ ጨካኝ ወታደራዊ ስርኣት ነው። ለወረራ ወይንም ለሰለባ ሲዘጋጅም “ሰለባው ወይንም ግድያው እንዲቀናው” በአባ ገዳ መሪዎች ተመርቆ ይሰናበታል።

ወደ አምሳሉ ልመልሳችሁ። ሠዓሊ አምሳሉ ስለ እረቻ እንዲህ ይላል።
“እሬቻም እንዲሁ ችግር ያለበት ባሕላዊ ሥርዓት ነው፡፡ይል እና  አሁን አሁን የሌለውና የማይፈጸምበት ለማስመሰል ጥረት ይደረግ እንጅ እሬቻ ዋነኛ የባዕድ አምልኮ መፈጸሚያ መድረክ ነው፡፡ ወያኔ እሬቻን ከጠፋበት ፈልጎ ወደ መድረክ ያመጣበትና ሰብስቦ እያስጨፈረ ሰፊ የብዙኃን መገናኛ ሽፋን በመስጠት እንደገና ለማስተዋወቅ ብዙ የደከመበት ምክንያትና ዓላማም የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ተከታይ የሆነውን ኦሮሞን ሕዝብ ክፍልምን የመሰለ የራሳቹህ ሀገር በቀል ባሕላዊ እምነት አላቹህ! ከመካከለኛው ምሥራቅ የመጣ መጤ ሃይማኖት አያስፈልጋቹህም!” እያለ በመስበክ ከክርስትና ለማስወጣት ለመለየትና ከአማራ ጋር ያለውን ትስስርና አንድነት ለመበጠስ ለማራራቅ ነው ሌላ አይደለም! ይላል አምሳሉ ገብረኪዳን። አስገራሚ የሚያደርገው ግን ተዋህዶ ቤተክርስትያን ቀሳውስት ካባቸውን ለብሰው በዚህ በዓል ከእረቻ አምላኪዎች ሳር በመያዝ አብረው ሲያከብሩ (ሲያመልኩ እንበል) ታይተዋል።
የሚገርመው ደግሞ እረቻ አክባሪዎችም ሆኑ የገዳ ተከታዮች የሚለብሱት ልብስ ያሸበረቀው
ልብሳቸወን ሆነ የሚያውለበልቡት ሰንደቃላማ የኢትዮጵያ ሰንደቃላማ ሳይሆን የገዳ ባንዴራ ሆኖ የግብፆች ሰንደቃላማ ቀለም ያለው ቀይ ነጭ እና ጥቁር ቀለም ያለው እራሳቸው የፈለሰፉት የመለያ ባንዴራ አርማቸው ነው። ለዚህም ብዙ ኦሮሞ ፖለቲከኞች ይህ እስላማዊው የጀኔራል ጃራ ሰራዊት ሲያውለበልበው የነበረው በዚህ ቀለም የታጀበ ዓረባዊው የባንዴራ ቀለም ነው የሚለብሱት የሚባለው።ስለሆነም ነው ግብፆቹ የራሳቸው ሰንደቃላማ ኦሮሞ ውስጥ  መውለብለቡ ደስታቸውን በመግለጽና ኦሮሞዎች ለሚታገሉት የግንጠላ ትግላቸው አስፈላጊው እርዳ እንደሚያደርጉ ቃል በገቡበት “አባይ ግድብን” አስመልክቶ በተደረገው ባንዲት ግብጻዊት ሴት ጋዜጠኛ ቃለ መጠይቅ ቄሮዎች ይህንን ባንዴራ እያውለበለቡ መኪኖችን ሲያቃጥሉ በነበረበት ወቅት ግብጾቹ በቪዲዮ እያሳዩ  በለቀቁት የደስታቸው ቃለመጠይቅ አድምጠል። ታስታውሱ እንደሆነ ከብዙ አመት በፊት (አመተምህረቱን አላስተውሰውም) በጣት የሚቆጠሩ ኦሮሞዎች በዚህ እረቻ በዓል ተገኝተው የኢትዮጵያ ሰንደቃላማ በባህል ልብሳቸው ላይ ደርበው በመልበስ “የራሳችን ሰንደቃላማ ይህ ነው” ብለው አጊጠው ላንድ ጋዜጠኛ ቃላቸውን ሲሰጡ አስታውሳለሁ። ያኔ ብሔረተኞቹ እጅግ የጋለ የሰንደቃላማ ብከላ ሲያካሂዱ በነበረበት ወቅት ነው። ዛሬ ሙሉ በሙሉ የግብጾቹ ቀለም የያዘ እና የኦነግ ባንዴራ አሸናፊ ሆኖ በሽማግሌዎቹም በኩል እየተውለበለበ ነው። 

በመጨረሻም ስለ እረቻ ከመደምደሜ በፊት “እሬቻ በወያኔ ፖለቲካዊ ዓላማ ከሞተበት የተነሣ ባዕድ አምልኮ! በሚል አምሳሉ እንዲህ በቅርቡ የጻፈው ትችት “እሬቻ የሚባልን የባዕድ አምልኮ ጠፍቶ ከነበረበት ፈልጎ ያመጣው ወያኔ ነው፡፡ ደርግ ጎጅና ኋላ ቀር ልማድ ብሎ አጥፍቶት ነበረ፡፡ወያኔ ኦሮሞ ከሌሎች ብሔረሰቦች በተለይም ከአማራ ጋር ያለውን ጥብቅ የሃይማኖትና የባሕል ትስስርን ወይም ግንኙነትን ቆርጦ አለያይቶ በራሱ አጥር ብቻ ታጥሮ እንዲኖር ለማድረግ በማሰብ ነው። እሬቻን ከተቀበረበት ቆፍሮ አውጥቶ የብዙኃን መገናኛውንና እስከ ታች እስከ ገበሬው ድረስ ያለውን የአሥተዳደር መዋቅሩን በመጠቀም ከፍተኛ ቅስቀሳ ውትወታና ስብከት በማድረግ በሚገርምና አስቂኝ በሆነ ሁኔታ ፊደል የቆጠረ፣ የነቃ በሚባለው የኦሮሞ ተወላጅ ሳይቀር በድምቀት እንዲከበር ያደረገው። ወያኔ የኦሮሞና የአማራ ጥምረት ግንኙነት የህልውናው ሥጋቱ አድርጎ ያምናልና”። ሲል ደምድሞታል።

እሬቻም ሆነ ገዳ የፖለቲካ መጠቀሚያ በመሆን የኢትዮጵያዊነት ምልክት ሚባሉት ሁሉ እያፈገፈገ በፈለሰፍዋቸው የራሳቸው ባንዴራ የሚንቀሳቀሱ ከፖለቲከኞች እና ቄሮ ከሚባለው ክፍል ጋር ሆኖ ጥልቅ ፖለቲካው ውስጥ ገብቶ ማየት ምንጩ በክለሳ እና ብረዛ የተከናወነ ሴራ መሆኑን ለመረዳት አያዳግትም።፡ለዚህም ነበር ገዳ የሚባለው ኦሮሞአዊ ማሕበረሰባዊ አደረጃጀት የሚሰራ ድረጅት እኛ ባለንብት ክፍለ ዓለም  “ተስፋየ ገብረአብ” (አኖሌ ልበወለድ ደራሲ) የተባለ የሻዕቢያ ሰላይ እና ዛሬም ጸረ ኢትዮጵያ ቅስቀሳ እያደረገ “ኦሮሚያ መገንጠል አለባት” እያለ የኦሮሞ ወጠቶችን በመቀስቀስ ላይ ያለ ግለሰብ በገዳ ስርዓት በማሞገስ “ኦሮሚያ የሚባል አገር ዜግነት እና ስም በመስጠት” ገዳ እየተባለ ብዙ እየተነገረለት ያለው ባህላዊ አሰራር የሚከተል ማሕበር “ኦሮሞ ይገንጠል የሚሉ አፍራሽ ሃይላትን” የሚያበረታታ ማህበር መሆኑን አስመስክሯል።

ጥንት ያንበረከክናቸው፤ ዛሬ በወያኔ በር ተከፍቶላቸው ቅኝ ገዢዎች የልብ ልብ ተሰምቷቸዋል። ያሰቡት ተሳክቶላቸዋል። የትግሬው በጋሚዶ “ወሮበላ ስርዓት” ጫካ ውስጥ እያለ “ጸረ ኢምፔሪያሊስት ነኝ እያለ ንዳልተሞላቀቀ ሁሉ፡ ወያኔ ለገንዘብና ለሥልጣን ሲል የኢምፔሪያሊሰት አሽከር ሆኖ የሕዝባችን ማንነትና ክብር እንዳሻቸው እንዲረግጡን ለባዕዳን አሳልፎ ወጣቶቻችንን ሰጥቷቸዋል። ኢቫንጀሊካል፤ ጴንጤ እና በሸሪዓ መንግሥት ፖለቲካ የተበከሉ ወጣት ኢትዮጵያውያን በባህል ብከላው አስተዋፅኦ እያደረጉ ነው።

በፈረንጅ ዘመን አቆጣጠር በ8/6/17 በአሜሪካ ራዲዮ የአማርኛ ድምጽ የተላለፈው ዘግናኝ ዜና የ8 እና የ 6ዓመት ወንዶች ልጆች በግብረሰዶማዊያን እየተደፈሩ መሆናቸውና ለዚህም ወላጆቻቸው የሕሊና ሕክምና እንዲደረግላቸው ለፋሺስቶቹ መንግሥት አቤት ቢሉም፤ ወያኔዎቹ ኢትዮጵያን ለማጥፋት ስለመጡ፤ እሮሮአቸውን ለማድመጥ አልፈለገም ሲሉ ወላጆች በአሜሪካ ድምፅ አማርኛ ስርጭት ዘጋቢዎች ቀርበው ለሕዝብ አቤት እንዳሉ ታስታውሳላችሁ። ዘገባውም በመጽሐፌ ለታሪክ እንዲዘገብ በሚል ጽፌ አብሮ ዜናው ታትሞአል።

አንድ ወንጀል በሌላ ወንጀል እያነባበረ በሕዝባችን ላይ ስቃዩ እየጨመረብን ያለው የትግሬው ወያኔ፤ ለወደፊቱ የምትመካባቸው ወጣቶቻችን በሃይማኖት፤በአደንዛዥ እፅ ተበክሎ ማንነቱን እንድያጣ በባሕር ማዶ ፈረንጆች እና የናይጄሪያ የሕሊና ሰላቢዎች መጫወቻ ሆኖ እንዲዋረድ የትግሬዎች መንግሥት ፈቅዷል። ኢትዮጵያ መሬቷም፤ ሕዝቧም፣ሃይማኖትዋም ተደፍሯል። በሌቦች አልጠግብ ባይ ወረበሎች እና የአገር ክብር በማያውቁ ብሔራዊ ስሜት በራቃቸው ለመንጋ ኢምፔሪያሊስቶች ያደሩ ‘ወያኔዎች’ ሕዝባችን እንዴት አየተዋረደ እንዳለ፡ ደጋግሜ ዘግቤአለሁ። ዕድገት እና ዲሞክራሲ በሚል ሽፋን ወያኔዎች ፤ኦነጎች፤… በመንፈስ እና በግብረገብ የበሰበሰ ማሕበረሰብ በመገንባታቸው በመጪው ሦስት ወይንም በአራት ትውልድ ታጥቦ የማይጠራ የሕሊና እና ሉአላዊ ብከላ ፈጽመዋል። እነዚህ ወንጀለኞች ለሰሩት ወንጀል ተጠያቂ እንዳይሆኑ በዲሞክራሲ እና መቻቻል ሽፋን ረቂቅ የማጃጃል ሴራ እየተሰራ ነው። አገሬ ሆይ! ምድር ለምድር ከሚሳቡ እባቦች እና ጊንጦች ነድፈው ሊጠግቡሽ አልቻሉም፡ ከዚህስ ወዴት ይሆን ጉዞሽ? ከማለት ሌላ ምን ልበላት?

ክፍል 3 የወያኔ ትግሬዎች ጸረ ሃይማኖት እና ጸረ ባህል ስለሆኑ በፋሺስታዊ አወቃቀር እና እምነት የተነሳ ሃይማኖታዊውና ባህላዊ “አሸንዳን” የፖለቲካ መጠቀሚያቸው እንዴት እንዳደረጉት እንመለከት እና እንደመድማለን። በዛው ሴራ ውስጥ የትግራይ ሙዚቀኞች ተዋናያን ፤ገጣሚዎች እና ደራሲዎች ለፋሺስታዊ መርሆ እንዴት እያገለገሉ እንዳለ በማስረጃ አቀርባለሁ።
ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay) getachre@aol.com







No comments: