ተደብቆ የነበረው የኢሳያስ አፈወርቂ
“ትግራይ ትግርኚ” ዓላማ ይፋ ሆነ!
ጌታቸው ረዳ (Ethiopian
Semay)
በዚህ ርዕስ ውስጥ ሁለት ጉዳዮችን እንመለከታለን። ሰሞኑን
የትግራይ ‘ወጣት‘ ምሁራን ስለ ትግራይ ትግርኚ ምስረታ እንደ አማራጭ ፍላጎታቸው ያንጸባረቁበት 20 ወጣት ምሁራን ባካሄዱት ስብሰባ
ላይ የተንጸባረቀው ፍላጎት እንመለከታለን። ሁለተኛው ክፍል ውይይታችን
ደግሞ፤ ኢሳያስ በትግራይ ትግርኚ የነበረው አቋም እንመለከታለን። ባጭሩ የተለያዩ ሁለት ማስረጃዎች ግን አንድ ግብ ያላቸው ሰነዶችን
አቀርባለሁ።
Photo-Abraha Desta participating on Ethnic Federalism and secession convention (secession as option |
(Abraha Desta participating on Ethnic
Federalism and secession convention (secession as option)
ሁለተኛው ምስል (ፎቶ) ስለ ትግራይ መጪው ዕድል እንደ
አማራጭ ያቀረባቸው አማራጮች ገለጻ የሚያደርገው አቶ ጉዑሽ በርሄ ጣቱ ላይ ቀስሮ እያመለከተበት ያለው ኣንቀጽ 39ን ሲያብራራ ነው
(A39 በሚል ስም በመስጠት ቻርቱ ላይ ሲያብራራ ነው)
የብሄር ተኮር ፌደራሊዝም ለበርካታ አመታት በኢሳያስ አፈወርቂ
የሚመራው ሻዕቢያ የተባለው በፋሺስት ርዕዮት የተመሰረተው እጅግ ዘረኛ እና ነብሰገዳይ ድርጅት ብዙ ሰዎች ሻዕቢያ ስለ የትግራይ
ትግርኚ ምስረታ ዓላማ ይቃወም ነበር እያሉ ሲከላከሉለት እንደበር እናስታውሳለን። ድርጅቱም እራሱ የትግራይ ትግርኚ ዓላማ ይቃወመው
እንደነበር ሲያሰራጫቸው ከነበረው የማታለያ ተመጻዳቂ በራሪ ሰነዶች እና በራዲዮኑ ሲያስተላልፈው እንደነበር ማስረጃየ ብሎ የሚጠቀምበት መከራከሪያ እንደነበርም ይታወቃል። ያ ሁሉ “ቡትለካ” (መናፍሕ)
ማታለያ እንደነበር ዛሬ ከድርጀቱ ከፍተኛ አባል ምስጢሩ የተቃራኒ እንደነበር ገሃድ ሆኗል። እዚህ ላይ ወያነ ትግራይ ከትግራይ ትግርኚ
ዓላማው ትቶት ነበር ማለት እንዳልሆነ ይሰመርበት።
ወደ ማስረጃው ከመግበታችን በፊት፤ ታስታውሱ እንደሆን ኢሳያስ
መቸም ቢሆን ትግራይ ትግርኚ የሚለው ዕቅድ እንደማይቃወመው እኔም ሆንኩኝ በይበልጥም ታላቁ ኤርትራዊው የሕግ ምሁር እና በጀርምን
አገር ብረይመን ዩኒቨርሲቲ የሕግ ፕሮፌሰር ዶ/ር ተስፋጽዮን መድኅኔ በተለያዩ ሰነዶቹ ገልጾት እንደነበር ይታወሳል። ፕሮፌሰር ተስፋጽዮን መድኅኔ ኢሳያስ በረሃም እያለ በፈረንሳዊው ዲፕሎማት፤ተመራማሪ እና ጋዜጠኛ ‘ፕሮፌሰር
ረኔ ሊፎርት’ ኢሳያስ አፈወርቂ የጥንቱ የአክሱማዊ ስርወ መንግሥት እንደገና ለማደስ ዓላማ እንደነበረው ኢሳያስ ከተናገረው ንግግር
የተመዘገበው ሰነድ ወዳጄ ፕሮፌሰር መድኅኔ መጽሐፍ ውስጥ (Eritrea Dynamics of a Nation Question – by
Tesfatsion Mehanie) ገልጾት እንደነበር ላስታውሳችሁ እፈልጋለሁ።
ከላይ የተጠቀሰው የፕሮፌሰር መድሃኒየ መጽሐፍ በ1986
በፈረንጅ ዘመን አቆጣጠር በጻፈው እጅግ ጠቃሚ መጽሐፍ በገጽ 115 እንዲህ ሲል ዘግቦት ነበር።
“…The TPLF now focused on the principle
of self-determination in the name of this principle, it claimed to seek the
equality and freedom of the Tigrean people and other nationalities within a
united Ethiopia. It stressed however that this could be realize only under a
“democratic” government in Ethiopia and not under the “fascist” PMAC. It
emphasized that “if the existing national oppression continues or is
aggravated”- so long as the PMAC or another revolutionary democratic regime is
in power in Ethiopia-self determination “means the birth of an independent
Tigray” (51)
Clearly the TPLF aimed to overthrow
the revolutionary government in Addis Ababa. The idea of severing Tigrai from
Ethiopia was a threat designed to serve this goal.
The EPLF and the TPLF renewed their
intimacy. They became twin organizations and again charted a common plan of
work.
Some TPLF leaders gave clear
indications of their wish to unite Eritrea and Tigrai, portraying it as an
alliance against the “Showan regime,” the PMAC in Addis Ababa. French writer
Rene Lefort has recorded a revealing incident which he witnessed while touring
the EPLF held territory in Eritrea. He recalled listening to “a long very long
soliloquy” by an EPLF leader on the reason for the struggle of the Eritreans
(52) He added that EPLF leader concluded the talk by saying, “We are the
inheritors of the kingdom of Axum. We will have nothing to do with this Showan
regime.” (53)
The perceptive Lefort commented
that, in those words of the EPLF leader, “there was…more than a mere verbal
sally.” (54)- (Eritrea Dynamics of a Nation Question – by Tesfatsion Mehanie
May 1986-p.115)
*51- (Rene Lefort, Ethiopia: An Heretical Revolution? (London: Zed Press,
1983), P.268 *52-Ibid -- *53-Ibid
እንግዲህ ከላይ እንደተመለከትነው ኢሳያስ የትግራይ ትግርኚ
ዓላማ የጀመረበት ወቅት በግልጽ ባይታወቅም፤ የአክሱም ስርወ መንግሥት ተረካቢዎች መሆናቸውን እና ለዚህ ተረካቢነት ዝግጁነትም በትግራይ
ትግርኚ ዓለማ መተግበር እንዳለበት ኢሳያስም ሆነ ባልደረቦቹ ለተስበሳቢ ጉባኤተኛ እና ለውጭ አገር ተጋባዥ እንግዶች በግልጽ
እንደተናገረ ፕሮፌሰር ተስፋጽዮን መድኅኔ (1986) እና ረኔ ሊፎረት (1983) ነግረውናል።
የሁሉም ድርጅቶች ድብቅ ‘ዓላማ’ የተሰናከለበት ወቅት ሁለቱም
ማለትም ወያኔ እና ሻዕቢያ ወደ ጦርነት ከገቡ በኋላ እንደሆነ የምናየው ማስረጃ ከዚህ ቀጥሎ አዲስ ዜና እንመለከታለን። ሁለቱም
ድርጅቶች ከመጣላታቸው በፊት ግን ድብቅ ዓላማቸው ላለማሳወቅ ሲሉ ከዚያ በፊት ሁለቱም ‘ወፈፍ’ ሲያደርጋቸው (ኢሳያስ ወያኔን ‘በየ
10 አመቱ አንዴ ወፈፍ ያደርጋታል’ ይል እንደነበረው ሁሉ) ያንን ፍላጎታቸው በድብቅ ይዘውት፤ለማስመሰል ብቻ በሻዕቢያ በኩልም
ሆነ በወያኔ በኩል የትግራይ ሩፑብሊክ ምስረታ “አንደግፍም” የሚል በራሪ ሰነድ ሲበትኑ እንደነበር ይታወሳል። ሆኖም ሻዕቢያ የተቃወመው
(በኔ ግምገማ) የትግራይን ከኤርትራ በመወሃድ “ትግራይ ትግርኚን መመስረት” ሳይሆን የተቃወመው ፤ ትግራይ በራስዋ አገር ለመሆን
“የትግራይ ሪፑብሊክ” አገራዊ ምስረታ ነው ሲቃወም
የነበረው (ካሁን በፊት ባንድ ትችቴ ገልጬዋለሁ)።
ለዚህ አባባሌ በቂ
ድጋፍ እንደ ማስረጃ የሚሆነኝም ሰሞኑን ‘ኤስ ቢ ኤስ - ራዲዮ’ (SBS radio) በመባል የሚታወቀው የአውስትራሊያ የትግርኛ
ራድዮ ክ/ጊዜ ካሁን በፊት በሱዳን የሻዕቢያ አምባሳደር የነበረው አምባሳደር
ኣብደላ ኣደም ኢሳያስ ስለ ትግራይ ትግርኚ ምስረታ ግብ ፍላጎት እንደነበረው ሰሞኑን በሰጠው የትግርኛ ቃለ መጠይቅ
ሰምተነው የማናውቀው ተደብቆ የነበረ ትኩስ ዜና አስደምጦናል። ኢሳያስም ሆነ ወያኔዎች፤ የትግራይ ትግርኚ ዓላማ ምስረታ ፍላጎት
እንደነበራቸው የሚያሳይ ማስረጃ ባለፉት 20 ምናምን አመታት ተቃዋሚዎቻቸው በየአገራቸው ቢያስታጥቁዋቸውም፤ አንዱ አንዱን እንዳይጎዳ
ሲያሳዩት የነበረው ለዘብ ያለ “ያለመጎዳዳት” ባሕሪቸው ጥርጣሬ ውስጥ የሚከትት አመላካች እንደበር ፕሮፌሰር ዶክተር ተስሃጽዮን (በተለያዩ ሰነዶች በሰፊው በትግርኛ
እና በአማርኛ ደጋግሞ በኢንትርኔት ሚዲያዎች በማሰራጨት ገልጾታል። አንዳንዶቹ ሰነዶቹም በአዲሱ መጽሐፌ ታሪክ እንዲመዘግበው ለማስረጃ
አትሜኣቸዋለሁ። ያንን መመልከት ጠቃሚ ነው) እንዲሁም ሌላው ምሁር ፕሮፌሰር ረኔ ሊፎርትም ጭምር ሲገልጹት የነበረው የኢሳያስ ድብቅ ዓላማ ይኼው ዛሬ ከስንት አመት
በኋላ እውነታው ጋሃድ ሆኗል።
ከዚህ ቀጥሎ የአምባሳደር
ዓብደላ ኣደም የትግርኛውን ቃለ መጠይቅ ወደ አማርኛ ትርጉም ይቀርባል። ከዚየም ትግርኛ ለምታደምጡ አንባቢዎች የትግርኛው አውድዮው/የድምፅ
ቅጂው/ አቀርባለሁ።
እንዲህ ይላል፦
“ከኤርትራ ነፃነት
በኋላ ማለትም አምባሳደርነቴን ትቼ ጥገኝነት ጠይቄ ተቃዋሚ ከሆንኩኝ በኋላ 2003 ወደ አዲስ አበባ ሄጄ ነበር። በወቅቱ ነብሱ ይማረው መለስ ዜናዊ
በህይወት በነበረበት ጊዜ ለሁለት ሰዓት ያክል አነጋግሬው ነበር። መለስ ያለኝ፤ ‘እንደ እነ ናይዝጊ ክፍሉ የመሳሰሉ ከፍተኛ ባልሥልጣኖች
ወደ ትግራይ እየተላኩ ስለ ትግራይ ትግርኚ አገራዊ ምስረታ እንድንቀበል ይጠይቁን ነበር' በማለት መለስ ዜናዊ በግል ለኔ አጫውቶኛል።
መለስ ዜናዊ እንዲህ ብሎ ሲነግረኝ የነበሩ የወያኔ ባለስልጣኖች ለምሳሌ ስዩም መስፍንም ሌሎችም አብሮውን ነበር።” በማለት ዓብደላ
ኣደም
ይህ ለጆሮኣችን
አዲስ የሆነ ትኩስ ዜና አድርሶናል።
የ ‘ኤስ ቢ ኤስ
- ራዲዮ’ (SBS radio) ጋዜጠኛ እንደዘገበው ‘ዓብደላ ኣደም በ977 (ፈረንጅ ዘመን) ጀምሮ የሻዕቢያ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ
አባል የነበረ ነው። ከነፃነታቸው በኋላም የሰንሒት አውራጃ ከዚያም የደቡባዊ ቀይ ባሕር አስተተዳዳሪ፤ ከዚያም የጂቡቲ እና የሱዳን አምዳሳደር
ነበር። ሱዳን ውስጥ ሁለት አመት አምባሳደር ሆኖ ከቆየ በኋላ ዓብደላ ኣደም ከ15ቱ የኢሳያስ ተቃዋሚዎች (ሪፎርሚስቶች) መካካል
አባሪ ስለነበር፤ ባስቾኳይ ወደ ኤርትራ እንዲመለስ ትዕዛዝ ከተላለፈለት በኋላ ሁኔታው ስላላማረው፤ ወዲያውኔ መጣሁ ብሎ ወደ እንግሊዝ
አገር በመሄድ እንግሊዝ አገር ጥገኝነት በመጠየቅ በስደት ይኖራል። በማለት ስለ አምባሳደሩ የሥራ ልምድ ገልጾታል። ሙሉውን የትግርኛ
ቃለ መጠይቅ ለማድመጥ ይህንን የድምጽ ሰንድ ያድምጡ።
ሌላው ዜና ሰሞኑን ከትግራይ የተለቀቀው ቪዲዮ እነ
አብርሃ ደስታ እና 20 የሚሆኑ ወጣት ምሁራን ስለ ተሳተፉበት
ሰሚናር በሚመለከት።
የስበሰባው መሪ
“ጉዑሽ በርሀ” ይባላል። ሰውየው ብዙም አይታወቅም። የትምህርት መስኩም ምን እንደሆነ አይገልጽም። በቪዲየው መግቢያ እራሱን ሲገልጽ
ከውጭ አገር እንደመጣ ይገልጻል። ሰውየው ከውጭ አገር ወደ ትግራይ ሲመጣ ‘ግጭት/ኮንፍሊክት/” ሲከሰት እንደሆነ ይገልጻል። ካሁን
በፊት አንዴ መጥቶ እንደነበር፡ ለዚሁም በቋንቋ የተነሳ ችግር ተከስቶ በነበረበት ወቅት ይህንን ገለጻ ለማድረግ እንደመጣ በገለጻው
ውስጥ ይናገራል።
ተስበሳቢዎቹ ከ20
አይበልጡም። ሁሉም ወጣቶች ናቸው። አንዳንዶቹም ከአብርሃ ደስታ በዕድሜ ያነሱ ይመስላሉ። የስብሰባው ተካፋዮች ከተለያዩ የአውራጃ
ቋንቋ ተናጋሪዎች መሆናቸው ከልሳናቸው ማወቅ ይቻላል። 99% ምናልባትም 100% ማለት በሚባል የትግራይ ትግርኚ (ስለ ግንጠላ)
ፍላጎትም ሆነ፡ ከእንግዲህ ወዲህ ትግራይን እና የትግራይን ሕዝብ ዕጣ ፈንታ ‘ማዕከል’ (ትኩረታቸው) ባደረገ ፍላጎት ብቻ ማትኮር
እንዳለባቸው በአጽንኦት ይስማማሉ።
የስብሰባው ገለጻ
አድራጊ ጉዑሽ በርሀ ትግርኛ ሲናገር ከእንግሊዝኛ
ቃላት ጋር እየደባለቀ ስለሚናገር በቅንፍ እያደረግኩ ለማብራራት ሞክሬአለሁ። በተቻለ መጠን ለአንባቢዎቼ በይበልጥ የሰውየው ንግግር
ግልጽ ለማድረግም በቅንፍ ያስቀመጥኳቸው የራሴ አገላለጾች አሉ።
እንዲህ ይላል፤-
“ሲስተሙ (ስርዓቱ)
በኤትኒክ (በጎሳ) ፌደራሊዝም የማይሰራ (የማይቀበል) ከሆነ የራሳችን ኦፕሺን (አማራጭ) መውሰድ ይቻላል። እኛ እንደ ትግሬዎች
ሦስት ኦፕሺን (አማራጮች) አሉን። ያ “ኦፈር” የምናደርገው ፌደራሊዝም (ያ የሰጠናቸው ፌደራሊዝም) ተቀባይነት ካላገኘ አማራጮቹ
የሚከተሉት ናቸው፡ እንደ ኢትዮጵያ አካል ሆኖ መኖር፡ ከኤርትራ ጋር “ጆይን” (ውህደት) የማድረግ ፖሲቢሊቲ (የሚቻልበት ዐድል)
አለ።ሌለው ኮንፌደረሺን ነው። በመጨረሻ እገልጸዋለሁ። ምክንያቱም እኛ
እና ኤርትራኖች የጋራ የሆነ የማንነት አንድነት ስላለን በቀላሉ መዋሀድ እንችላለን።
ለምሳሌ ወደ ሌላ
አቅጣጫ ወሰድከን አትበሉኝ እንጂ ይላል አቶ ጉዑሽ በርሀ፦ ‘የተስፋጽየን አጋዚያን ጽንሰ ሓሳብ አለ’ (ተናጋሪው ተስፋጽየን
ብሎ በስም የጠቀሰው ሰውየ በየቱዩቡ ተጥዶ ቀንም ሌሊትም ስለ አማራ ጥላቻ የሚሰብክ፤ቀለም ያልቃኘው፤ በሌብነት ተከስሶ የተፈረደበት
አንድ አጭበርባሪ ኤርትራዊውን ነው “አጋዚ መሪ ብሎ እየጠራው ያለው” ተስፋጽየን የብዕር ስም እንጂ ሓቀኛ ስሙ “ዕዮብ” ይባላል።)
… ይቀጥልና- አሁን ባለው ክስተት(እኛ ትግሬዎች ያለንበት ሁኔታ)
‘በሥልጡንነታችን ጽንሰ-ሃሳብ መመዘኛ ስንመዝነው (ከሌሎቹ ቀደም ብለን ሥልጡኖች እንደመሆናችን መጠን) እኛ በሌሎች እየተጎተትን
እንጂ እኛ ሌሎችን እየጎተትናቸው አይደለንም ያለነው’ (በተገላቢጦሽ ላይ ነን)። ምክንያቱም እኛ የትግራይ ምሁራኖቻችን ወደ መሃል
(ኢትዮጵያ) አሰራጭተን ኢንቬስት ያደረግነው፤የረባነው ነገር እስካሁን ድረስ ምንም የለም። ወደኋሊት ነው እየተመለስን ያለነው (ሌሊችን
እንጂ ሕዝባችንን አልጠቀምንም)።
ግልጽ ለማድረግ፤በኤርትራ
እና በትግራይ ውስጥ ጠንካራ መሪዎች ከተገኙ እርስ በርስ እየተረዳዱ በየአለንበት ሆነን የጋርዮሽ ተጠቃሚዎች ልንሆን የምንችልበት
መንገድ መቀየስ ይቻላል። ሦስተኛው አማራጭ ኮንፌደረሺን ነው። አጋአዚያን መንግሥት (ትግራይ ትግርኚ) መስርተህ የራስህ መንግሥት
መስርተህ ከሌሎቹ ጋር በፀጥታ፤ ቴክኖሎጂ ወይንም በፋይናንስ የመሳሰሉ የተወሰኑ ጥቃቅን ነገሮች ተስማምተህ መኖር ነው። እኛ ትግሬዎች
የተደራጀ ሕዝብ ስላለን ሌሎችን ቀድመን መመንጠቅ እንችላለን።በተለይ ኤርትራ እና ትግራይ ለማዋሃድ እንዲመች እንደ ቅድመ ኩነት
(ዝግጅት) መደረግ ያለባቸው ነገሮች ‘የሁለቱም ሕዝቦች ምሁራን በመገናኘት በሁለቱም ሕዝቦች ያሉት ችግሮች ነጥረው በማውጣት ተወያይተው
ዕንቅፋቶቹ እንዲወገዱ ከተደረገ በቀላሉ መዋሃድ እና የተፈለገው ንድፍ ማጠናቀቅ ይቻላል።
ወያኔ አማረዎችን
እና አሮሞቹን እንዲሁም ሌሎቹ እንዲተባበሩ ሲረዳ ፤ለራሱ ሕዝብ (ለትግራይ) እንዲተባበር አላደረገም። እርስ በርስ ልንደማመጥ አልቻልንም።
ወያኔ ማለት--- 'እንቆቅልሽ ምን አውቅልሽ?' ተብሎ ቢጠየቅ “እራሱን ሳያስተባብር ሌሎችን አንድ እንዲሆኑ የረዳ ንገረኝ?” ተብሎ ቢጠየቅ
መልሱ “የእራሱን ሕዝብ ሳያስተባብር ሌላውን ያስተባበረ “ወያኔ” ነው የሚል መልስ እናገኛለን። (በዚህ የእንቆቅልሽ መሳሌ ተሰብሳቢው
ሁሉ በአዎንታ መስማማታቸውን በቪዲዮው ድምፅ ውስጥ ይደመጣል)። ስለሆነም ለዘመናት እየተደፈርን እና እየተሰቃየን ያለንበት ምክንያት “ስላልተባበርን
ነው”።
አቶ ጉዑሽ ንግግሩ
ይቀጥል እና “.. ስንነጣጠልም “ስሙዝ ላንዲንግ” (smooth
landing) (ያለ ምንም ደም መፋሰስ እና ግጭት) መጠናቀቅ አለበት። አንቀጽ 39 በጣም ጠቃሚ ነው። ያንን ለመጠቀም ግን የመነጠል
መብት እንዲተገበር 51% የሚለው ድምፅ ሕገ መነግሥቱ ተሻሽሎ ቢያንስ 3/4% መሆን አለበት። ድምጽ ሰጪው ዕድሜ ወደ 18 ዝቅ
ማድረግ እና ብዙ የመገንጠል ድምጽ ሰጪ ማግኘት ይቻላል። ምክንያቱም 49% ሕዝብ አልገነጠልም ካለ እና በ51% ልገንጠል ብሎ ግንጠላው
ተግባራዊ ቢሆንም፤ ብንገነጠልም እነዚያ 49% አልገነጠልም ያሉት የጊዜ ጉዳይ እንጂ የኋላ-ኋላ በውስጣችን ከፍተኛ ችግር እና ግጭት
ሊያስነሱ ይችላሉ። በተቻለ መጠን ሁሉንም በግንጠላው እንዲስማማ ከፍተኛ ጥረት ሲደረግ መረጋጋት ይቻላል። ለስሙዝ ላንዲንግ”
(smooth landing) ሂደትም ይረዳል። ከሌሎቹ ጋር በተቻለ ቅራኔ ውስጥ ሳይገባ ግንጠላው እንዲከናወን ያላሰለሰ ጥበብ ያስፈልጋል።
እኛ ስንገነጠል፤
በውስጣችን ያሉ ብሔሮች እነደ እነ ኩናማ፤ ሳሆ….የመሳሰሉ መብታቸው ማክበር አለብን። ሌላው ነጥብ ዛሬም ሆነ ለወደፊቱ የዘር ሄጂመኒ
(ሌለው ጎሳ በሌላው ጎሳ መዋጥ እንዳያጋጥመን) የምንመሰርታቸው ኢንዱስትሪዎች የሕዝብ ቁጥር ‘ብዛት’ ባለው የጎረቤት አካባቢ ኗሪዎች
ጠረፍ አጠገብ መመስረት የለባቸውም። ምክንያቱም እኛ ጥቂት ሆነን ኢንደስትሪዎቻችን (አንድም ይሁን ሁለትም ይሁን) በኛ መሃል
(በጥቂቶቹ) እና ብዛት ባለው ጎረቤት ሕዝብ ጫፍ (ድምበር) ላይ ከተመሰረቱ ስራ ፍላጋ ‘በቀላሉ ወደ ቦታው በሞግረፍ’ ኢንዱስትሪው
ወዳለበት ማዕከል በብዛት በመምጣት ቀስ በቀስ እየኖሩ እየተዋለዱ ብዙሃኑ ጥቂት የሆኑትን ነባሮቹን (ኢንዲጂነሱን) ሊውጡት ስለሚችሉ
ከጊዜ ብዛት -ማለትም አንድ ወይንም ሁለት ወይንም ሦሰት ትውለድ ካለፈ በኋላ ይህ የኛ መሬት ነው ብለው “ዞር በል” ብለው ችግር
ሊፈጥሩ ይችላሉ።ዞር ብል ሲሉህ ብዙሃን ስለሆኑ ‘ምን ማድረግ ትችላለህ?’። ስለዚህ ኢንዱስትሪዎች ሲመሰረቱ በተቻለ መጠን የት
ቦታ መመስረት እንዳለባቸው ጥንቃቄ እና ጥናት ማድረግ አስፈላጊ ነው።’ በመለት ገላጸ ሲያደርግ
አቶ ጉዑሽ በርሀ
ገለጻ ካደረገ በኋላ፤ የወያኔዎች ተከታይ የሆነው ‘ጌታቸው አረጋ’ዊ' የተባለው የ ‘ውራይና’ ጋዜጣ አዘጋጅ ወጣት ጋዜጠኛ (ታስታውሱ
እንደሆነ ‘አባይ ፀሐየን ያናደደው ወጣት’ እያሉ ያልገባቸው አንዳንድ ‘ደደቦች’ በዩቱብ የለጠፉለት አክራሪ ብሔረተኛ የወያኔ አሽከር ነው ጌታቸው
አረጋዊ ማለት)፡ ከጉዑሽ ጋር በመስማማት እንዲህ ይላል፡-
“አንተ የምትለው
ልክ ነው። በተግባር የሆነውን አንድ ምሳሌ ልስጥህ። “አብደራፊ” የሚባል የትግራይ መሬት አለ። ይህች መሬት በአማራዎች ክልል
የተጠጋች ድምበር (በአስፋልት የተለየች?) ነች። መጀመሪያ ወደ እዛቺው መሬት የሰፈሩ ትግሬዎች ናቸው። ከዚያም እነ ገዱ አንዳርጋቸው
ዓላማቸውን ለማሳካት ሲሉ በብዛት ቀስ በቀስ አማራዎች ወደ እዛቺው ቦታ በማጉረፍ አሁን ቁጥራቸው አማራው እና ትግሬው እኩል እንዲሆን
አደረጉ። ፍጥጫ ሲነሳ አሁን እነሱ ቁጥራቸውም እኩል ከእኛዎቹ ጋር ስለሆነ ችግር አለ ማለት ነው። ስለዚህ ኢንዱስትሪ ሲተከል ከጎረቤት
አገር /አካባቢ/ ያሉት ሕዝቦች ብዛት አንጻር እየተገመገመ (አካባቢውን እያጠኑ) ካልሆነ በሌሎች የመዋጥ ዕድል ሰፊ ነው።” በማለት
ድጋፉን ሰጥቷል።
ባጭሩ እንዲህ ያለ
ንግግር ምን እንደሚያመለክት የሚገባችሁ ይመስለኛል። ፋሺዝም የሚያደርገው የመጀመሪያው ጥንቃቄ ሌላ ዘር፤ሌለ ደም፤ሌላ ጎሳ፤ባዕድ
ወደ "እንደ የጥዋት ውሃ የጠራው ዘር” ወደ ‘ወርቁ’ ጎሳ እንዳይዳቀልና ማንነቱ እንዳይዋጥ ማድረግ የመጀመሪያው የዘር ጥራት
(racial Hygiene) ጥንቃቄ ማሳያ ነው (eugenic)። ያም ሆነ ይህ በዚህ ስብሰባ የተነገረው እጅግ አስፈሪ
እና አሳፋሪ አስተያየቶች ስላሉ እሱን ሌላ ጊዜ ሲያስፈልግ በሌሎች ትችቶች ምን አንደተነገረ እጠቅሳቸዋለሁ። የስብሰባው ቪዲዮ በትግርኛ
ለመመልከት/ለማድመጥ ይህንን ተመልከቱ
አመሰግናለሁ!
ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)
ብሄር ተኮር ፌደራሊዝም ሓቀኛን ሓደገኛን ብጉዑሽ በርሀ 1ይ ክፋል
2 ክፋል ብሄር ተኮር ፌደራሊዝም ሓቀኛን ሓደገኛን
No comments:
Post a Comment