በታማኝ በየነ እና አምባሳደሩ መካከል የነበረው አለመግባባት
በኢትዮጵያን ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ
እይታ
ባለፈው ወር አብይ አሕመድ ወደ አሜሪካ በመምጣት ኢትዮጵያውያንን
ለማነጋጋር በተካሄደው ዝግጅት በሚመለከት ጉዳይ በኢትዮጵያ የወያኔ/ኢሕአዴግ የዋሺንገተን ዲሲ አምባሲ አምባሳደር በከያኒ ታማኝ
በየነ ላይ ‘ሴራ’ በመጎንጎን መድረክ እንደነፈጉት ተደርጎ እራሱ ታማኝ በየነ በኢሳት ቴ/ቪዥን ቀርቦ የሰጠው የራሱን ምላሽ ሰምተነዋል።
ብዙ ሰዎች አኔም ጨምሮ ታማኝ በተናገረው ቅሬታ ወደ ማመን ሄጄ ነበር (እስከ ዛሬዋ ድረስ የመልስ መልስ ስላላደመጥን)። ዛሬ የአምባሳደሩን
መልስ የቪ ኦ ኤዋ የአማርኛ ክፍል ጋዜጠኛ ጽዮን ግርማ ጋር የተደረገው ቃለ መጠይቅ ካደመጥኩኝ በኋላ ግን የአምባሳደሩ
ስም በውሸት እንዲጠቁር መደረጉ በጣም ስሕተት ነበር። ስለዚህ ይህንን ቃለ መጠይቅ ካደመጣችሁ በኋላ በአምባሳደሩ ላይ የነበራችሁ
የተሳሳተ እይታ ያላችሁ ሰዎች ካላችሁ ዕይታችሁን አስተካክሉ። ከታች የምሰጣችሁ መረጃ ከቀረበላችሁ በኋላ የሰው ስም በከንቱ
በማጥፋት ላይ ችክ የምትሉ ሱሰኞች ካላችሁም አደብ ግዙ። ይህን ስላልኩኝ ደግሞ እንደ አመላችሁ ጌታቸው ረዳ አምባሲው ጋር መሞዳሞድ
ጀመረ እንዳትሉ ያው በዚያ አንደማልታማ የምታውቁ ይመስለኛል። ምድረ አሽቃባጭ ስትደመር አሁንም ገና ነኝ አልተደምረኩም፡ ስለዚህ አምባሳደሩን ልቀቁት። ታማኝ
በየነ የመድረክ አዘጋጅ እንዲሆን ያልተደረገበት ምክንያት ከአገር ቤት የተመደበ ሰው ስለነበረ (ዳንኤል ክብረት ለማለት ይመስለኛል)
እንጂ ታማኝን በማግለል አይደለም ብሏል አምባሳደሩ በቅንነት። ሁኔታው ከአምባሳደሩ የሰው መዳቢነት ሥልጣን በላይ ነው ማለት ነው።
እኔም በዚህ አምባሳደሩን አምኜዋለሁ። ለማንኛውም ይህንን ቃለ መጠይቅ አድምጡ እና ሰውን ማመንዠኩን አቁሙ (አሁንም በየ ዩቱቡ
ላይ እንደ ምጣድ ተጥደው በዚህ ጉዳይ የሚቃዡ ስላስተዋልኩ ነው ይህንን መረጃ የሰጠሁዋችሁ። የምቃወመው ሰውም ቢሆን ሰው በከንቱ
ስሙ ሲጎድፍ ያበሳጨኛል፡ አልወድም! ዶ/ር ፍስሃ እሸቱ በሚያሰራጨው የፖለቲካ እቃወመው ነበር ፤ የዲሲ ግብረሃይል የተባለ የጋንግ
ቡድን “ያለፈቃዱ በቁጥጥር ስር አውለነዋል/Involuntary Imprisonment/” ብለው በሕዝብ ፊት ሲያስሩትና ሲሰድቡት የተሰማኝ
ንዴት በወቅቱ በጽሑፍ ገልጫለሁ። አሁንም በዚህ መልክ የምንቃወማቸው ሰዎች ላይ በሓሰት ስማቸው ሲጠቁር እውነታውን ፈልጎ ማወቅ
ያስፈልጋል።
Ethiopia: ጽዮን ግርማ አምባሳደር ካሳን አፋጠጠቻቸው
ጌታቸው ረዳ (Editor - Ethiopian Semay)
በአባቱ ላይ ወንጀል የፈጸመው አረጋዊ በርሔ የሚመራው የህወሓት ሠራዊትን ያሞገሰው የትግሬ ምሁር በጎሳ ጥናት ተመራማሪዎች እይታ
ጌታቸው ረዳ
Ethiopian Semay
የርዕሳችን መነሻ የሆነው ከላይ በምስል/ፎቶግራፍ ቆሞ በሕዘባዊ
ስብሰባ እየተናገረ ስለየሚታየው ተናጋሪ ነው ። ከላይ የሚታየው ምስል/ፎቶግራፍ “አብርሃ ማንጁስ” ይባላል። ጣል ጣል ከሚያደርጋቸው
ከልሳኑ የሚወጡ ቃላቶች እንደምረዳው የእንደርታ ወይንም የተምቤን… ተወላጅ ይመስለኛል። “ይመስለኛል” ልል የቻልኩበት መነሻም እንደርታዎች
ከነበራቸው ባሕሪ እያፈነገጡ የቋንቋ ልሳናቸው እየተው የ “አሸዓ” ልሳን ወስደው በእንደርታዊ ልሳን እና ከሌላው የትግሬዎቹ ልሳን
እየቀላቀሉ ከምላሳቸው ጋር ትግል ሲገጠሙ ሳደምጣቸው ማን ከየት አውራጃ መሆኑ እያዳገተኝ በመምጠቱ ነው “ይመስለኛል” የሚለው ቃል
የተጠቀምኩበት ምክንያት። እንደርታወችን ማንሳቴ ላልቀረ ወደ ርዕሴ ከመሄዴ በፊት አንድ ነገር ልብል።
እንደርታዎች ባሕሪያቸው እየተለወጠ በወያኔ ስነ ልቦና እና
አስተሳሰብ እየተመሩ የመሄዳቸው ሁኔታ ግን እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ደርሷል። እንዳውም ወያኔ ዋና ምሽጉ መቀሌ ካደረገበት ጊዜ ጀምሮ
እንደርታዎቹ ከሌሎቹ እጅግ አክራሪ የወያኔ ጀሌዎች ናቸው ከሚባሉት ቅድሚያውን ቦታ እየያዙ መምጣታቸው አሳሳቢ እየሆነ መጥቷል
(በዚህ ጸሐፊ እይታ)። ስለሆነም አብርሃ ማንጁስ ከልሳኑ በመነሳት እንደርታዊ ነው ብየ ልደምድም እና አብርሃ ማንጁስ የዴንማርክ
ናሪ መሆኑን ራሱ ይናገራል።
አብርሃ ማንጁስ የበረሃ ታጋይ ይኑር አይኑር አላወቅኩም። ማንጁስ
የሚለው “ጩጬ” የምንለው አማርኛ፡ ዓረቦች “ማንጁስ” የሚሉት ቃል በረኸኞች (ሻዕቢያ) የሚጠቀሙበት ቃል ስለሆነ በረሃ ካልነበረ
ይህ የበረሃ ቅጥያ አሰጣጥ ስም እንዴት እንዳገኘው ባላውቅም ሰውየው ለብዙ አመታት የወያኔ ጀሌ እንደነበር ግን አያጠራጥርም።
አብርሃ ማንጁስ መቀሌ ከተማ በሓምሌ 2010 (ኦገስት መጀመሪያ
በፈረንጆች 2017) በተካሄደው የወያኔ ተቃዋሚም ደጋፊም የሆኑ በመላ
ዓለም የሚገኙ ትግሬዎች የተገኙበት ስብሰባ ከዴንማርክ ወደ ትግራይ ሄዶ እነ አረጋዊ በርሔ እና ቱባ የወያኔ መሪዎች
በተገኙበት ስብሰባ ላይ የተናገረው በዚህ ትችት እንደ ርዕስ ለመነሻ የተጠቀምኩበት የአብርሃ ማንጁስ ንግግር ልጥቀስ እና ወደ ትንታኔ
እንገባለን፦
“አብርሃ ማንጁስ እባላለሁ። የመጣሁት ከዴንማርክ ነው። ህወሓት
ማለት አንዳንድ ሰዎች ትርጉም ላይ ይሳሳታሉ። ህወሓት ማለት የትግራይ ሕዝብ ድምር ማለት ነው።የትግራይ ሕዝብ ሠራዊት ማለት ነው።
አረጋዊ በርሔ በህወሓት ውስጥ ጀግንነት “ኢንስቲቱሽናላይዝ” እንዲሆን
ያደረገ ጀግና ታጋይ ነው። አረጋዊ በርሔ በግሌ የሰራው ስራ አለወይ? ከትግራይ መሳፍንት ተብለው በፊውዳልነት ተወንጅለው የታሰሩት
የቆሰሉት እና የተገደሉት ውስጥ አንዱ የኔ ወላጅ አባት ነው። ይህ ወንጀል የፈጸመው ደግሞ አረገዊ በርሔ ሲመራው የነበረው ወታደራዊ
ክንፍ የተፈጸመ ነው። ሆኖም እንደ አንድ “ፌየር-ትግሬ/ አንደ አንድ fair Tigrayan” አረጋዊ ማለት ለኔ በትግራይ ተጋይ
፤በትግራይ ሕዝብ ሠራዊት ውስጥ ጀግንነት ማለት ምን ማለት እንደሆነ “ማተርያላይዝ” ያደረገ ጀግና ሰው ነው።ህወሓት የትግራይ ሕዝብ
ንብረት እና ኢንስትቱሽን ነው…..” በማለት አባቱን የገደለለትን ድርጅት እና ወንጀል ፈጽሟል ብሎ በወነጀለው ሠራዊት መሪ ላይ
የጀግንነት ሙገሳ ለግሶለታል። ምንጭ Ethiopia - Tigray Governance forum Part 4/1
https://youtu.be/Ihonciy2DJc
ለሙገሳው ምክንያት ሲሰጥ ደግሞ (እጅግ ያስገረመኝ አባባሉ”
የሚከተለው ነው፡’-
“እንደ አንድ “ፌር-ትግሬ/ እንደ አንድ fair
Tigrayan” እንደ አንድ ሚዛናዊ ሰው ሆኜ ነው” የሚለው ነው አባቱን የገደለለት ሠራዊት የመራውን አረጋዊን ጀግና ነው ለማለት
የበቃው። እንዴት አንድ ሰው ‘እኔ ሚዛናዊ ሰው ነኝ” ብሎ አባቱን የገደለለትን ሠራዊትን የመራ ወይንም ድርጅትን ሊያሞግስ በቃ?
የተገደሉት ወላጅ አባቱ ሲገደሉ ወያኔ የሰጠው ምክንያት እራሱ አብርሃ አንደሚለው ደግሞ “ከትግራይ መሳፍንት ተብለው በፊውዳልነት
ተወንጅለው የታሰሩት የቆሰሉት እና የተገደሉት ውስጥ አንዱ የኔ ወላጅ አባት ነው።” በሚል ነው። መስፍን ስለሆኑ/ከበርቴ/ሃብታም
ስለሆኑ ብቻ ነው ህወሓት የገደላቸው። አይደለም እንዴ? ታዲያ ሓብታም/መስፍን በመሆናቸው ብቻ ሲገደሉ “እኔ እንደ አንድ ሚዛናዊ
“ፈየር” የሆንኩኝ ትግሬ ሲል አባቱ ያለፍትሕ ሲገደሉ በአባቱ የተፈጸመውን ወንጀል ፍትሓዊ ነው ብሎ ወያኔን ሊያሞግስ የሚያስችለው የሚዛን መለኪያው ከየት አገኘው? የሚለው ጥያቄ አስከትሎብኛል። አንድ ፍትሓዊ ወይንም ሚዛናዊ ሰው
ነው ሊባል የሚያስችለው አባቱ የተገደሉበትን ምክንያት አመዛዝኖ ሕጋዊነቱን ካረጋገጠ በኋላ እንጂ እንዴት አባቴ መስፍን ስለነበረ በመስፍንነቱ ብቻ
ሲገደል ሚዛነዊ ስለሆንኩኝ ለገዳዮቹ አደላለሁ ብሎ አባቱን የገደሉለትን ገዳዩቹን እንዴት ሊያሞግስ ይነሳል? የአብርሃ
ጭፍን ጉዞ መነሸው ምንድ ነው? እንከታተል።
እንግዲህ አብርሃ ማንጁስ እየነገረን ያለው ህወሓት በወላጅ
አባቱ ላይ ወንጀል መፈጸሙዋን ነግሮናል። ይህ በወላጅ አባቱ ላይ የፈጸመው ሠራዊት የሚመራው ዶ/ር አረጋዊ በርሔ (በሪሁን) እንዴት
በዚያ ቃል ሊያሞግሰው ቻለ? የሚለው ጥያቄ በጎሳ እና በስነ ልቦና እንዲሁም በስነ ኣዕምሮ መስክ የተገናኘ ጥናት ያደረጉ የመስኩ
ባለሞያዎች የሚሰጡን ትንታኔ መመርመር ሰፊ ትንታኔ ሊጠይቅ ነው።
በቅርቡ ወዳጄ ደ/ር አሰፋ ነጋሽ በጻፈው ”አክራሪ ብሄረተኛነት በሰዎች ላይ የሚያስከትለው ስነልቦናዊ ለውጥና የሚፈጥረው ተፅዕኖ” በሚለው ትንታኔው ውስጥ የትግራይ ተወላጅ በሆኑት በታወቁት የታሪክ ምሁሩ ፕሮፌሰር ደ/ር ገብሩ ታረቀ እንደማሳያ አድርጎ ያቀረበው አንድ ጥናት ላይ እንዲህ ይላል።
“ከላይ የጠቀስኩት የፕሮፌሰር ገብሩ ታረቀ ጽሁፍ አንድ ሰው
በአክራሪ ብሄረተኛነት ስሜት አይምሮው የተበከለ አዋቂ ሰው የሰባት ዓመት ህጻን ልጅ እንኳን ሊያይ የሚችለውን እውነታ እንደሚክድ
ያሳየናል" በማለት ፕሮፌሰሩ ወያኔ የሚሰራቸው አገር አፍራሽ አስነዋሪ እና አራዊታዊ ስነ ምግባሮችን ማየት አቅቶአቸው ወያኔን
በትግሬነታቸው የጎሳ መነጽር አትኩረው ስለተመለከቱት የወያኔ አራዊታዊ ተክለሰውነትን ሰብኣዊ እና አገራዊ ድርጅት አድርገው በመሳል
ህጻን እንኳ ሊያየው የሚችለውን ወንጀል ማየት ለምን እንዳቃታቸው
ሰፊ የሆነ ጥናት በማድረግ በሳቸው መጽሐፍ እና ምርምር ላይ ያደረገው ጥናት ስንመለከት አብርሃ መናጁስ አባቱን የገደሉበትን የወያኔ
ሠራዊት የመራውን አረጋዊ በርሄ መክሰስ ሳይሆን እንዴት ልያሞግስ እንደተገፋፋ የሚያሳየን ምክንያታዊ መነሻው አንድ ሰው ቅጥ ባጣ
የድርጅት ወይንም የጎሳ ወይንም የሃይማኖት ፍቅር ከተጠመደ በራሱ ሕሊና ማሰብ ያቆምና ሕሊናው ለሚወደው ድርጅት/ጎሳ/ሃይማኖት በማስረከብ
ድርጅቱ ስለ እርሱ እንዲያስብለት አሳልፎ ስለሚሰጥ ነው። እንዲህ ያለ የመንጋ አባል በራሱም ሆነ በቤተሰቡ ላይ የሚፈጸም ወንጀል
እና “ኢ-ፍትሓዊ” ሁሉ አሜን ብሎ ያለምንም ጥያቄ ይቀበላል ማለት ነው። ለዚህ ነው አክራሪ ብሄረተኛነት በሰዎች ላይ የሚያስከትለው
ስነልቦናዊ ለውጥና የሚፈጥረው ተፅዕኖ
በጣም ከባድ እንደሆነ ዶ/ር አሰፋም ሆነ ሌሎች በዚህ ጥናት መስክ የተመራመሩ ምሁራን እየነገሩን ያለው።
አብርሃ እኔ ሚዛናዊ ሰው ነኝ እና ሚዛናዊ አስተያየቴን ልስጥ
ብሎ አባቱን የገደለለትን ድርጅት ሲያሞግስ “ለምን” ብሎ የሚጠይቅ በጣም በርካታ ሰው እንዳለ አውቃለሁ። በተለይ በጎሳ መስክ ብዙ
ያላነበብን ሰዎች ግራ የሚያጋባ ክስተት ነው። አብርሃ ማንጁስ ታዲያ እንዴት ወደ እንዲህ ያለው ድምዳሜ እና አሞጋሽነት ሊደርስ
ቻለ የሚለው ጥያቄ ለመመለስ በዶ/ር አሰፋ ጥናት ጽሑፌን ልደምድም፡
“አንድ ሰው አክራሪ ብሄርተኛ ሲሆን እንደ ግለሰብ ከሌላ ሰው
የሚለየውን የግል ማንነቱን አጥቶ በራሳቸው አስተሳሰብ መመራት የማይችሉና በደመነፍስ (instinctively) አድርጉ የተባሉትን
ሁሉ ካለአንዳች ጥያቄና ማወላወል የሚፈጽሙ የሰዎች መንጋን (human crowd) ይቀላቀላል። የሰው መንጋ ቡድንን የተቀላቀሉ የአንድ
ነገድ ተወላጆች ከጊዜ ወደ ጊዜ አስተሳሰባቸው ከእውነታ እየራቀና (their reality testing is impaired) የሚያስቡትን
ነገር ሁሉ በእርግጠኛነት ማድረግ የሚችሉ (delusional state of mind) እየመሰላቸው ይመጣሉ።
የአክራሪ ብሄረተኛነት በሚፈጥረው ህሊና አሳዋሪ ስሜት ምክንያት
ያበደ የአንድ ነገድ ተወላጅ የራሱን የግል ማንነት ድንበር አፍርሶ ከሌሎች እንደ እሱ የግል ማንነታቸውን ድንበር ካፈረሱ የነገድ/የጎሳ
አጋሮቹ ጋር አንድነት በመፍጠር ሀሴትን ያደርጋል፤ የአክራሪ ብሄረተኛነት ስሜት በሚፈጥረው የፈንጠዚያ ዓለም (ecstatic
world created by ultra-nationalism) ውስጥም ይገባል። በዚህ ሁኔታው ውስጥ አንድ ሰው የአንድ ማህበረሰብ አባል
ሆኖ በህይወቱ ውስጥ ለሚወጥናቸውም ሆነ ለሚያደርጋቸው ነገሮች ኃላፊነት መውሰድ ያቆማል። በአክራሪ ብሄረተኛነት ስሜት ያበደ ሰው
ህይወቱን እንደ አምላክ ለሚያመልከው የራሱ ነገድ ድርጅት አሳልፎ ይሰጣል።” (ደ/ር አሰፋ ”አክራሪ ብሄረተኛነት በሰዎች ላይ የሚያስከትለው ስነልቦናዊ ለውጥና የሚፈጥረው ተፅዕኖ ” Ethiopoian Semay ድረገጽ የታተመ
ጽሑፍ )።
ስለሆነም ነው አንድ ሰው አባቱን የገደለለትን ወንጀል የፈጸመውን ድርጅት በማሞገስ በሕዝብ ፊት አባቱን መገደላቸውን እያወቀም
ቢሆን፤ ወላጆቹን ያቆሰሉለትን፤ ያሰሩለትን ወይንም ያሰቃዩለትን የህወሓት ሠራዊት እና ሠራዊቱን የመራውን በጀግንነት ሊያሞግስ የተገፋፋ
ሰው የመነሻ ምክንያት በስነ ልቦና እና በኣዕምሮ መስክ ባለሞያዎች
የሚሰጡን መልስ ከላይ የተመለከትነው ምክንያት ነው ማለት ነው። ወላጆቻቸው፤አህቶቻቸውን ወይንም ዘመድ ወንድሞቻቻውን እራሳቸው የገደሉ፥ ወይንም የይገደሉ ፈቃድ የሰጡ የድርጅቱ አባሎች በርካቶች ናቸው።
ያም ሆኖ ድርጅቱን እስከመጨረሻ ድረስ ያመልኩታል። ምክንያቱም ከላይ እንደተገለጸው ከሰው መንጋ የተቀላቀሉ የአንድ ነገድ ወይንም
የሃይማኖት ተከታዮች ከጊዜ ወደ ጊዜ አስተሳሰባቸው እየተሸረሸረ ፥ ሙሉ ማነንነታቸው በድርጅቱ ፈቃድና መመሪያ አንዲንቀሳቀስ እና እንዲመራ በመፍቀድ ድርጅቱ
የሚወስደው ማንኛውም ወንጀል እና እርምጃ ሚዛናዊ እና ሕጋዊ አድርገው ስለሚቀበሉት ፥ በቤተሰቦቻቸው ለሚደርሰው ጥቃትና ስቃይ የትብብር እሺታ ያሳያሉ
ማለት ነው። መቀሌ ላይ የተደመጠው እንዲህ ያለ ክስተት ሁላችንም የሚያሳስበን አስገራሚ ክስተት ነው። ፈጣሪ ከዚህ በሽታ ይሰውረን!!!
የድርጅት ፥ የጎሳ እና የሃይማኖት ፍቅር
መጠን ሲያልፍ አደገኛ ነው የምንለውም በዚህ ምክንያት ነው።
አመሰግናለሁ!
ጌታቸው ረዳ (Ethiopoian Semay)
No comments:
Post a Comment