Sunday, July 23, 2017

የትግሬ ምሁራን የሚከተሉት ፋሺዝም፤ ሙሉወርቅ ኪዳነማርያምና ወልቃይት ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ አዘጋጅ)


የትግሬ ምሁራን የሚከተሉት ፋሺዝም፤ ሙሉወርቅ ኪዳነማርያምና ወልቃይት

ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ አዘጋጅ)


ከታች የሚታው ፎቶግራፍ ዶ/ር ሙሉወርቅ ኪዳነማርያም ነው። ሙሉወርቅ በዕድሜ  

ቢበልጠኝም እስከ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ‘አብርሃ ወ አጽብሃ’ አክሱም’ ነው የተማረው። ከዚያ ወደ ትውልድ ቦታው ወደ ‘ዓድዋ’ ሄደ። እኔ እስከማውቀው ድረስ በትምህርቱ ሰነፍ እንደነበር እና ቆይቶ ግን ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ገብቶ የታሪክ ምሁር ሆኖ ዶክተር ተብሎ  ዛሬ ትግራይ ውስጥ ከሚገኙት ዩኒቨርሲቲዎች አንዱ (ሳባ ዩኒቨርሲቲ ?) ‘ዲን’ (ርዕሰ-አስተዳዳሪ ) ነው። ሙሉወርቅ  በወያኔ የትግራዋይነት ፋሺዝም ስነልቦና ከተቀረጹ እውቅ የታሪክ ተመራማሪዎች እና በትግራይ ውስጥ የወያኔ ዘመን ምሁራን አንዱ ነው። የወያኔ አሽከር ከመሆኑ በፊት የኢሕአፓ አባል ነበር። ወደ ወያኔ ፖለቲካ ከገባ ወዲህ ግን በጣም ነውራማ/ነውራም/ የሚባሉ የጎሰኛነት ክርቢት ከሚጭሩት ምሁራን ግምባር ቀደም ቦታ ይዟል። የድሮ ባሕሪውን ሳስታውስ፤ እንዲህ ካለው የታሪክ ነውር ውስጥ ‘የትግሬነት ፋሺስዝም’ ርዕየት ከሚያራምዱት ቡድኖች  እራሱን እንዴት ሊቀላቅል እንደቻለ ሊገባኝ አልቻለም።

የሙሉወረቅ ንግግሮች ሁሉም ነጥቦች በማስታወሻ መያዝ ያለባቸው ስለሆኑ ፤ትርጉም እና መልስ ስሰጥ ጽሑፉ ትንሽ ረዘመብን ብላችሁ ለምታጉረመርሙ አንባቢዎች ማሳሰቢያ አለኝ። የተያያዝነው የብዕር ጦርነት የሕሊና ጦርነት ነው። በከፋ መልኩ እየመጣብን ነው። የወያኔ ፋሺዝም ቅስቀሳ ብዙ ሰዎችን እየበከለ ነው። ጠላቶቻችን በረዢሙ ሲቀሰቅሱ ምን እንደተናገሩ ሳይደክመን እየተነተንን የምናዘጋጅላችሁን የደወል ጥሪ ለማድመጥ ለ15/20/ደቂቃዎች ጊዜአችሁን ሰውታችሁ ማንበብ ካልቻላችሁ፤ የታሪክ ተወቃሾቹ እኛ ሳንሆን የናንተው ዕዳ ይሆናል።  

ዶ/ር ሙሉወርቅ የትግራይን ነገሥታትና መሳፍንት እጅግ በማድነቅ በሕዝቡ ላይ ሲፈጽሙት የነበረውን አረመኔ እርምጃዎች ሁሉ በመደበቅ ‘ብጹአን የትግራይ ሕዝብ አለኝታዎች” አድርጎ በመሳል፤ ትግሬ የሆኑ ገዢዎች፤መሳፍንቶችና ነገሥታቶቹ (ሸዋ ውስጥ እንጂ ትግራይ ውስጥ መስፍን  የሚባል አልነበረንም ሲል መስፍንነት ከጋሻ መሬት ብቻ የተያያዘ የመሰለው ሳውዲ  ረቢያ የሚኖር ትግሬ ‘ሚሊዮዮነር’  ሲናገር አድምጫለሁ) በባንዳነት ስማቸው ያላስጠሩ፤ በአገር ያልተደራደሩ፤ ብቸኞች ጀግኖችና አገር ወዳዶች አድርጎ በመቅረጽ ትግሬዎች ስለሆኑ ከታሪክ ተወቃሺነት ‘ነጻ’ እንዲወጡ ከሚታገሉ “የትግሬ ነገሥታት ነፃ አውጪዎች” አንዱ ነው”።
 
ከዚህ በታች በተራ ቁጥሮች የዘረዘርኳቸው በትግርኛ የተናገራቸው የሙሉወርቅ ንግግሮቸ ተርጉሜ ለናንተ ሳቀርብ ለመተረጎም የሚያስቸግሩ በጎሰኛ ቃላት የተለወሱ እጅግ ዘግናኝ የሆኑ አድማጮቹን እያስሳቀ የተናገራቸው የጥላቻ ቀልዶችን ወደ ጎን ትቻቸዋለሁ። ሲናገር በተፈጥሮው ከልጅነቱ ጀምሮ ‘የሚታገለው ምላስ’ ቢኖሮውም፤ ሙሉወርቅ እጅግ ማራኪ ቃላቶችንና ባህላዊ ምሳሌዎችን በመጠቀም፤ ምሁራዊ ችሎታው ጋር ቀላቅሎ ሲናገር የአድማጩ ልቦና በቀላሉ የሚሰልብ አንደበት አለው።ንግግሩ በትግርኛ ሆኖ፤ ‘አይጋ ፎረም’ ከተባለ የወያኔ ፕሮፓጋንዳ ስርጭት ድረገጽ ውስጥ ከጥቂት ቀናት በፊት ተለጥፎ ያደመጥኩት ነው ወደ አማርኛ መልሼ ለናንተ የማቀርበው።

ይህ በዓይነቱ ልዩ የሆነ፤ድፈረት የተሞላበትና ታሪክን የማይፈራ የዶ/ር ሙሉወርቅ ኪዳነማርያም ንግግር የተቀዳው፤ ስለ ‘ወልቃይት ጸገዴ’ ትግሬነት የሚገልጽ ‘ወልቃይት’ የሚል በሁለት የወያኔ ጋዜጠኞች (መዝገበ ጎይተኦም እና ተኸስተ ጎይተኦም) የተጻፈ 250 ገጽ የያዘ አዲስ የትግርኛ መጽሐፍ ለመመረቅ መቀሌ ከተማ ውስጥ ‘ሚላኖ ሆቴል’ (አገራዊ የከተማ ስም ባልታጣ) በሚባል የመመረቂያ ንግግር እንዲያደርግ በታገበዘበት ወቅት ነው።

 የሙሉ ወርቅን ንግግር የቀዳው ጋዜጠኛ “ታምራት የማነ” ይባላል።ጋዜጠኛው በአውድዮው መግቢያ እውቁ ባለ “ለዛ ልሳን” ሲል አስተዋውቆታል። የማነ ታአምራት ግምባር ቀደም የወያኔ “ቱሪናፋ’ ነው። የዚህ ልጅ ክስተት ሁሌም ሚገርመኝ፤ የእንደርታ ተወላጅ ትግርኛ ቋንቋ  ተናጋሪ ሆኖ  የ “አሽዓ” እና የኤርትራ ትግርኛ ቃላትን እየለቀመ  እነሱን ለመምሰል ሲጥር ከምላሱ “የላንቃ ወፍጮ’ ሲፈጩ የሚያመልጡት ‘ላንቃ ፋቂ’ ቃላቶች እያሳበቁበት ሳደምጥ ፤ ሰዎች እስከዚያ ርቀት ለምን እንደሚጓዙ ይገርመኛል። እንደርታዎች እንዲህ ያለ ራስን ዝቅ አድርጎ የማየት የንግግር ዘዴ በጣም በርካታ (በሚሊዮኖች) እንደርታዎች የታዘብኩት እና በወያኔ ጋዜጦች እና ቲቪ/ራዲዮ እና ሙዚቀኞች (ሴት/ወንድ) የማደምጣቸው የእንደርታነት መለያቸው የሆነ ‘የንግግር ልሳን’ ለማስወገድ የሚጥሩ በብዛት አሉ። ይህ ደግሞ በእነ ‘ገብሩ አስራት’ በነ መስፍን አማረ፤ ሳዓረ መኮነን፤ ሕቡር ወዘተ  የመሳሰሉ የእንደርታና አካባቢ ተወላጆች ያስተላለፉላቸው አስገራሚ ክስተት ነው። ኤርትራኖች እና አሻዓዎች በእንደርታ፤ተምቤን እና የራያ ልሳን ተናጋሪዎች ላይ ለዘመናት ያንጸባረቁት “የትምክሕት/የንቀት አነጋጋር ዘይቤ” ለዚህ ክስተት አስተዋጽኦ አድርገዋል። (ሜዳ ውስጥ በ “አሻዓዎች” ለ12፣ 13፣ 17፣ 16፣ 15 ዓመታት በታጋይነት ሲኖሩ ከተደረገላቸወ የአነጋገርና የአጻጻፍ አጠባ ‘ጫና’ ተጨምሮበት ማለት ነው)። በዚህ እራሱ የቻለ ርዕስ ይዤ እመለስበታለሁ።

ይሀ ጽሑፍ የማቀርበው በትችት መልክ ሳይሆን የወልቃይት ምሁራን እና ሌሎች ስለ ወልቃይት ታሪክ የሚያውቁ ኢትዮጵያዊያን የትግሬ ሊሂቃን እና የሙዚቃ ባለሞያዎች እና የወያኔ ደራሲያን ማሕብር ስለ ወልቃይት እና ስለ አማራዎች ምን እያሉ እንደሆነ ለማሳወቅ እና መልስ እንዲሰጡበት በታሪክ ማሕደር ለማስገንዘብ ነው።

ይህ የዶ/ር ሙሉወርቅ ንግግር ትምክሕት ሳደምጠው ምናልባት ድምጹን አነጋገሩን በትግርኛ ብታደምጡት ኖሮ እዚህ ከተረጎምኩት በላይ ነው የሚያስደነግጣችሁ። በድምጽ ሲደመጥ እና በትርጉም ሲነገር የሚሰጠው ጫና ይለያያል። ስለሆነም፤ የታሪክ ጸሐፍት ጉዳዩ በቀላሉ ባታዩት መልካም ነው። ቀጥተኛ ማሳረጊያው ግን ያው የትግሬ ፋሺዝም’ እየተጠናከረ እንደሄደ የምናይበት መነጽር ነው።

ፋሺሰትነት ለኢትዮጵያ አዲስ አይደለም። በታሪካችን በመልክ ይለያዩ እንጂ በብዙ ተግባር አንድ የሆኑ ‘ፋሺስታዊ’ ክስተቶች በሕዝባችን ላይ ተከናውኗል። ፋሺስትነት ሕዝባዊ/ጅምላዊ/ ጭፍጨፋ ነው። አሁን ያለው የወያኔ ትግሬዎች ፋሺዝም ለየት የሚያደርገው፤ጥንት ከታየው ‘ሃይሞኖታዊ ፋሺዝም’ (ግራኝ አህመድ..ጉዲት..) ለየት ይላል። የእነግራኝ፤ የነ ጉዲትና የነሙሶሎኒ… በግለሰብ የተመራ ነበር። የትግሬ ፋሺዝም ከሌሎቹ ለየት ይላል። በግለሰብ እና በቡድን እየተፈራረቀ የሚጓዝ ነው። ሁሉም ፋሽቶች ‘አገር ወዳዶች ናቸው”። የትግሬ ፋሺዝም ግን “ጎሳ ወዳድ ነው”። ሌሎች ፋሺስቶች፤ አገራቸው በባዕድ እንዲረገጥ አይወዱም። ታሪክ ወይንም አገራዊ ክብር፤ ሰንደቃላማ፤ መሬት፤ድምበር ፤ወደብ፤የሕዝብ ባሕል፤ሃይማኖት ለጠላት አሳልፈው አይሰጡም (አገራቸው ከከብራቸው ጋር ስለሚያ ያ ይዙት እጅግ ውድ እሴት ነው ስለሚሉ)። እነ ሙሶሎኒ አስከፊ ቢሆኑም ሲበዛ በጣም አክራሪ አገር ወዳዶች (Agresivee  nationalist) ናቸውና አገራቸውን እጅግ አንደ ብሌን ያያሉ። የትግሬው ፋሺስት ቡድን ግን የተቃራኒው ነው (ልዩ የሚያደርገውና የሚያስገርመው ደግሞ ይህ ባሕሪውና እርምጃው ነው)።
 
ለትግሬ ፋሺስቶች ‘ኢትዮጵያ’ ማለት በነገድ ተከፋፍላ በግንጣላ ታርጌት/ ኢላማ/ የገባች እንደ ‘ባዕድ’ አገር ነች። በትግሬ ፋሺስቶች ዓይን፤ የአገሪቱ ታሪክ፤ አገር፤ ሃይማኖት፤ ቋንቋ፤ እግዚአብሔር፤ ሉኣላዊነት እና ሰንደቃላማ፤ በጥላቻ የተፈረጀ፤ በውጭ አገር ታዛቢዎች ፊት በፓርላማ የሚዘለፍ’ ፤ የሚብጠለጠል፤ ብዙዎቻችን ያስገረመ፤ እንደ የባዕድ ዕቃ የሚንቋሸሽ ነገር ነው። የትግሬዎች ፋሺዝም የሚመራው “ታሪክ በማይፈሩ” እኔ Intellectual Lampoons የምላቸው ‘በዱርየነት ባሕሪ የሚመሩ፤ ማአከላዊነትን የሚያጠብቁ ምሁራን’ እና ከድርጅቱ ውጭ ላሉ ‘ሆድ አደር’ ምሁራንን ለመምራት ‘የሚደፍሩ’ ነፍጥ ባነገቡ ‘ባልተማሩ ዱርየዎች’ የተመራ ዘመናዊ ‘መስፍንቶችን’ ያፈራ፤ በነብሰገዳዮች የሚታዘዝ፤ ቀኝ አክራሪና “በፓራኖይድ ፐርሶናሊቲ ዲስኦርደር” የተጠቁ ሰዎች የሚንከባከቡት፤የድሮ ግሎሪ (ልዕልነት) የሚዘክር ‘መስያኒክ’ ድርጅት ነው።

 
ወያኔ የተጠቀመው የጎሳ ፋሺዝም፤ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ደጋፊ ትግሬዎች አፍርቷል።  ተካተዮቹ በትግሬነታቸው እንደተጠቁ በማሳመን፤ ጠንካራ ድርጅት መስርቶ አማራን በጠላትነት መድቦ፤ ለትግራይ ድህነት አማራ ተጠያቂ በማድረግ፤ አማራን ጨፍጭፎ፤ አማራዎች የሚኖሩባቸው ብዙ ቦታዎች ወደ ትግሬ መሬት በመከለል፤ የፋሺዝም ዋናው የመሬት መስፋፋት መለኪያው በተግባር አሳይቶናል። ድርጅቱ የጥንትን ሥልጣኔ ባሕል ታሪክ ማንነት፤ጀግንነት (መስያኒክ) ተከታዮቹን እያስታወሰ፡ ያ ሁሉ ኩራት በአማራዎች እንደተደመሰሰ በማስተማር፤ ያንን ተነጠቅን የሚለው ኩራት፤መሬትና ታሪክ፤ መመለስ ቀዳሚ ትግላችን ነው ብሎ በማስተማሩ ዘመቻ ውስጥ የትግሬ ምሁራን እነ ዶ/ር ሙሉቀን ኪዳነማርያም የትግራይን ሕዝብ በማሳሳት፤በተለይ ወጣቱን ትውልድ አክራሪ የነገድ ፍቅር አንዲከተል በማስተማር ታሪክ የማይፍቀው ወንጀል እየሰሩ ነው።

   ወደ ሙሉወርቅ ኪ/ማርያም ንግግር እናምራ። እንዲህ ይላል፦

1)    “ወልቃይት የሚል ቃል ከማንኛቸውም የትግራይ አካባቢ ስሞች በዘመነ አክሱም የነበረ እና በኤዛና ድንጋይ ቅሬቶች ሁሉ የተጻፈ ስም ነው/ ኤዛና ተዋግቼአቸው ነበር የሚል ጽሑፍም አለ።” ይላል።(ዶ/ር ሙሉወርቅ ኪዳነማርያም)

 (ነገሩ  አክሱም የትግሬ ነው ስለሆነም ወልቃይትም በአክሱም ጊዜ ከነበረ የትግሬ ነው፤ ለማለት ነው)። በአክሱም ዘመን ወልቃይት የሚል ስም የነበረ ነው፡ ልክ ነው። ግን ‘ትግሬ’ የሚል ቃል ለምን ኤዛና አልጻፈም ነው እኔ የምጠይቀው። ኤዛና ወልቃይትን ሲጠቅስ እኔ “የትግራይ ንጉሥ ኢዛና” የሚል ጽሑፍ ለምን መጻፍ አልቻለም? ምክንየቱ ግልጽ ነው። ትግሬ በ7ኘው ክ/ዘመን በቤጃዎች የተከሰተ የማሕበረሰብ ስም እና ቋንቋ ነው። ትግሬ የሚባል ግዛት/አካባቢ/ሕዝብ በዘመነ አክሱም አልነበረም። አይታወቅም! ስለዚህ የወልቃይት ለም መሬቶች “የትግሬዎች ብቻ” ነው ብሎ ሕዝብን ያላማከረ ‘ነፍጥ ያነገበ’ ድርጅት የወሰነው በጉልበት ለም መሬት ወደ ትግሬ መከለል ፋሺስታዊ ነው።

ወልቃይት ከዘመነ አክሱምና ከዚያም በፊት ጀምሮ የነበር ነው። ሕዝቡም “ወልቃይቴ” ብሎ እራሱን ከዘመነ አክሱም ከምሮ ሲጠራበት የነበረ ነው። ኢዛናም ወልቃይቶች ብሎ ይጠራቸዋል። ወልቃይቶች ትግሬዎች ከነበሩ እንዴት የትግሬን ንጉሥና የትግራይን አምብርት አክሱም ድረስ መጥተው ሊወጉት ቻሉ?

 የተገላቢጦሽ ያውም ወልቃይቶች አክሱምን ለመውረር ወደ አክሱም መጥተው የሆነውን በማስረጃ ከራሱ ከንጉሡ ጽሑፍ ላስነብባችሁ። በወቅቱ አክሱምን ሲገዛ የነበረው “ሃፃኒ” (ገዢ/አጼ/…) ዳኒኤል የተባለው በራሱ ጽሑፍ ድንጋይ ላይ በ9ኛው ክ/ዘመን  ጽፎ ትቶልን የሄደ ማስረጃ አለ። የተጻፈበትም ቦታ እኔ በወጣትነት ልጅነቴ ጊዜ አዘውትሬ ስጫወትበት የነበረ ቦታ ነው። ልብ በሉ፡ አክሱም የፖለቲካ ርዕሰ ከተማ መሆኗ ያቆመቺው በ7ኛው ክ/ዘመን ነው። ቤጃዎች አካባቢውን ደርመሰው ነገሥታቱን ካባረሩ በላ ፤ቦታቸውን ተክተው ‘ትግርኛ እና ትግሬ’ ለመመስረት የጀመሩበት ዘመን ይመስላል ( ይህንን በሚመለከት ሌላ ቀን እምለስበታለሁ) እንዲህ ይላል፦

ወልቃይቶች አክሱምን ለመውረር ወደ አክሱም መጥተው የሆነውን እንመልከት።  

“In the name of the Father and of the Son and of the Holy Spirit, I have written this, hartsani Daniel… when the people of Wolqayt devastated the land… and came to Aksum, I expelled them and killed them and captured 102 foals and 802 catle” (Ancient Ethiopia Aksum: Its antecedents and Successors by David W. Phillipson- p-128 quoted Munro-Hay Axum an African Civilization of Antiquity 1991 (231)

2)   ባለፈው ሰሞን አንድ የትግራይ ሰው ስለ “ትግራይ “ ሲገልጽ አስገራሚ እና የሚደነቅ አባባል ብሎ ነበር። “ትግራይ የመላ አካባቢያችን “ሲም ካርድ” (Sim Card) ነች። ስልክ ቁጥር፤ምን፤ምን ታሪክ የያዘች ነች። ትግራይ የታሪክ ቀፎ ነች። የአካባቢያችን ቀፎ ነች። ትልቁ የቴሌፎን ሞባይል ‘ያለ ደቃቃዋ/ትንሿ “ሲም ካርድ” ህይወት የላትም። ትግራይ ማለት ደግሞ እንዲሁ የሁሉም አካባቢያችን ክልሎች/አገሮች/ቦታዎች ሁሉ “ሲም ካርድ” ነች። ያለ ትግራይ ሁሉም አካባቢዎች ታሪክ የላቸውም። መነሻው እኛ ነን። ሁሉም የሚጀምረው ከትግራይ ነው፤ “ሃይማኖት፤ፖለቲካ፤ስልጣኔ….መነሻዎች እኛ ነን። (ዶ/ር ሙሉወርቅ ኪዳነማርያም)

ስተነትን ጽሑፌን እንዳለስረዝምባችሁ፡ እራሰችሁ ተንቱኑት እና ፤ባጭሩ ያለትግሬ የተቀረው ፍጡር በራሱ አፈጣጠር ተንቀሳቅሶ የማያውቅ እና አሁንም የማይችል ታሪክ የሌለው በእኛ በትግሬዎች ሕሊና የሚመራ ግኡዝ የሆነ (አንደ ትልቁ የቴሌፎን ቀፎ) ፍጡር ነው፡ ነው የሚለን። ባጭሩ ፋሺስታዊ “ትምክህት” ማለት ይኼ ነው።

3)   ወልቃይቶች ታሪካቸው ከዚህ ሲጀምር (ኤዛና/አክሱም/ ማለቱ ነው) ዛሬ ወልቃይት የኛ ነው! የኛ ነው! እያሉ የሚፎክሩ (አማራዎች)‘በዛው ወቅት አልተፈጠሩም ነበር። አይታወቁም ነበር። እንደዚያ የሚባሉ (አማራ) የሚባሉ ሰዎች አልነበሩም። በዛው ወቅት (በአክሱም ዘመን) አማራ የሚል መጽሐፍት ውስጥ ተመዝግቦ አይቼ አላውቅም። (ዶ/ር ሙሉወርቅ ኪዳነማርያም)

ዶ/ር ሙሉወርቅ ኪዳነማርያም በታሪክ ትምህርት  ‘በዶክተርነት”ማዕረግ  ይመረቅ እንጂ፤ ድሮ ተማሪ እያለን የነበረው ደደብ ሕሊና አልለቅ ስላለው መሰለኝ፤ አማራዎች ‘የራሳቸው፤ጽሑፍም፤ ታሪከም፤ጀግንነትም የላቸውም፤ ከኛ እየሰረቁ ነው የኛ ነው የሚሉት….’ በማለት ከኢሕአፓ ከወጣ በሗላ ‘ህወሓት ያስተማረውን ትዕቢትን ድንቁርና ትምህርት”   አርሱ እና  የእርሱ ቡድንና ወዳጆች የሆኑት ደ/ር ሃይሉ ሐፍቱ እና መምህር ገብረኪዳን ደስታ ቢዘላብዱም ሃቁ ግን ከትግሬዎች አስቀድመው አክሱም ውስጥ የነበሩ አማራዎች እና አገዎች መሆናቸውን የአክሱም ታሪክ ዘግቦታል። ለምሳሌ አማራዎች ትተውልን የሄዱ አከሱም ውስጥ የሚገኝ የጥንት ጽሑፋቸውን በማስረጃ እና በዓይን ምስክሮች ምን ብለው እንደነገሩን እንመልከት።
 
ማኑኤል በረዳ ይባላል። የፖርቱጋል ተወላጅ ነው። አክሱም ከጎበኙ አንዱ የውጭ ሰው ነው። ወቅቱም 1626 (አካባቢ) አክሱም ሲጎበኝ በጽሑፍ አስፍሮ የተወልንን እንመልከት፡- 

Emmanuel Barradas, who accompanied de Almeida's mission, also left some notes (de Villard 1938: 68-71) on Aksum's monuments, some of which were `very large and of notable majesty', including `high and beautiful columns or pyramids', evidently the stelae, which bore comparison with the biggest and best at Rome. He also mentions an inscription with letters on one side in `Amharic' of an ancient style, and on the other letters which appeared to be Greek or Latin. The thrones are described, and also the `Tomb of Kaleb and Gabra Masqal'.”’

ሃቁ ይህ ነው።


4)   አማራዎቹ ወንድሞች ነን ካሉን “ጥሩ” “ትዕግሥት” (አደብ (ጸባይ)  የሚል ቃል ነው በትግርኛ የተጠቀመው) ይግዙ፡ ወንድማሞች እንሁን። የሚያዋርድ ወንድም የለንም; ወንድምህ ከሆነ ‘ታከብረዋለህ፤ያከብርሃል፤ ትወደዋለህ ፤ይወድሃል።(ዶ/ር ሙሉወርቅ ኪዳነማርያም)

 
አማራ ቀንደኛ የትግራይ ጠላት ነው ብሎ አዋጅ ያወጀ፤ ‘አክሱም’ ለወላይታው ለጎንደሬው ምኑ ነው ከሚል ድርጅት ጋር ተጣብቆ የጥላቻ ፕሮፓጋንዳ የሚነዛ ምሁር፤ አማራውን ’አደብ እንዲገዛ’ የሚያስጠነቅቅ የወንድምነት ትርጉም ለመተንትን አንዴት እንደሚደፍር ይገርመኛል። 

5)   አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ እያለሁ (በደርግ ጊዜ ነበር ሙሉወቅ ዩኒቨርሲቲ ሲማር የነበረው) አሞኝ ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ  ክሊኒክ ሄጄ፤ ጥዋት ነው ፤ተራ ይዤ እንዳለሁ፤ “ዛሬ ስንት ቀን ነው?” አለችኝ። “በኢትዮጵያ ነው ወይስ በፈረንጅ?” ስላት “በአማርኛ አለችኝ” “እኔ ደግሞ ‘በትግርኛ ነው የማውቀው” አለኳት። (አድማጩ ቷ…… ብሎ ይስቃል!) አዎ፤ እንዲህ ካላልናቸው “አደብ’ (ጸባይ /ልክ አይገቡም) ሊያደርጉ አይችሉም።(ዶ/ር ሙሉወርቅ ኪዳነማርያም)

ይህ የሙሉወርቅ ኪዳነማርያም የጥላቻ ድንቁርና፤ በቀና ለሚጠይቅ ዜጋ እንዲህ ያለ የትግሬና አማራ በሚለው የጎሳ ጥላቻ ፖለቲካ እራስን የሚዘፍቅ ምሁር የሄደበትን ርቀት ለመተንተን እጅግ ስለሚዘገንነኝ ለናንተ ልተወው። ጠያቂዋ ኢትዮጵያዊት ነች፡ ሙሉወርቅ እንደ “የቤት ዓይጥ” ‘የጎሳ ሽንኩርት’ ለማሽተት ማፎንፎኑን ፈልጐ ካልሆነ ሰዓቱን ዝም ብሎ ቢነግራት ምን ይጎድለዋል?

6)   ሙለወርቅ ኪዳነመርያም “ትግራይ” እንጂ ‘ትግሬ’ አንባልም፤ ሲሉ ከነበሩት ደናቁርት ምሁራን አንዱ ነበር። ትግሬ የሚል መጠሪያ አማራዎች የፈለሰፈልን ስም ነው እያሉ በድንቁርና ባሕር ሲዋኙ የነበሩ እና በዚህም ሰፊ ፖለቲካ ንትርክ ሲያደርጉ ለቆዩት እንዲህ ይላል “ የግዕዝ እውቀት ባይኖረኝም ‘የግዕዝ መጽሐፍቶች “ትግሬ” ሲሉ ነው የሚጠሩን” በማለት  ሳይወድ በግዱ መጠሪያቸው ለማያውቁ ‘ትግራይ እንጂ ትግሬ’” አንባልም ሲሉ ለነበሩ እሱ እና መሰሎቹ  ከስንት ጊዜ ቆይታ ዛሬ አምኗል።(ዶ/ር ሙሉወርቅ ኪዳነማርያም)።

መልካም የበጎ ባሕሪ እርምጃ ጅማሮ!


7)   (አማራዎች) ወልቃይትን በሚመለከት አንድም የሚሟገቱበት መጽሐፍ  እስካሁን ድረስ ያሳተሙት  ነገር የለም። ዘፈን ግን አዎ! እንኳን ለነሱ ሰዎች፤ የነሱ ያልሆነውን ሁሉ ፤ዘፈን እየዘፈኑ  “አስክስታ አስጨፍረውታል”። እንኳን የኑሰ የሆነ “የኛም ሰው” አስጨፍረውታል። (ዶ/ር ሙሉወርቅ ኪዳነማርያም)

የትግሬ ፋሺስዝም ፖለቲካ አስፋፊው  ሙሉወርቅ ኪ/ማርያም በንግግሩ ታዳሚውን በሳቅ ቷ!!!!!!! እስኪል  አስቆታል።አውነት ከአንድ የታሪክ ምሁር ያውም በዶክተርነት ደረጃ ማዕረግ የተመረቀ ሰው፤ እንዲህ ዓይነት ብልግና ከአንደበቱ ሲነገር፤ የትግሬ ምሁራን በቆረቆዘ  ፋሺስታዊ ትምክሕት የተተበተቡ እንደሆነ ያሳየናል።

 አማራዎች በሙዚቃ ቃናቸው ትግሬዎችን ማስተማር፤ማስጨፈር የተካኑት ብቻ ሳይሆን በመጻፍም መጻፍ የጀመሩት ከትግሬዎች ቀድመው ነው።ትግርኛ የሚባል  አክሱምን የወረሩ ‘የቤጃ ጦሮኞች እና ሰፋሪዎች’ በዛሬው ትግራይ ውስጥ ተበትነው ሲኖሩ ከግዕዝ፤ከቤጃና ከአማርኛ ደባልቀው የፈጠሩት ‘ትግርኛ’ አክሱም ውስጥ ተጽፎ የተተወ ማስረጃ የለም። ምከንያቱም ትግርኛ እራሱ የጽሑፍ ከመሆኑ በፊት መነጋገሪያ ብቻ ነበር። ትግርኛ መደመጥ የተጀመረው ወይንም ትግራይ/ትግሬ የሚለው ቃል ከወደ 7ኛ ክ/ዘመን መጨረሻ አካባቢ እንደሆነ ይነገራል። በደምብ የታወቀው ግን በጣም ቆይቶ ነው። አማራዎች ግን ጽሑፋቸው ትተውት የሄዱት አክሱም ውስጥ ነው። የዛሬ ትግሬዎች አማራዎች ታሪካችን፤ጽሑፋችን ነጠቁን የሚሉት፤አማራዎች ከዘፍን ውጭ የሚያወቅት ነገር የለም የሚለው “ድንቁርና” በሙሉወርቅ ቃላት ልጠቀም እና “ትግሬዎች አደብ ብንገዛ መልካም ነው”። ምክንያቱም አማራዎች አክሱም ውስጥ ነበሩ፤ ፁሑፋቸውም ይመስክራል፡ “ማኒኤል በራዳ” እንዲህ ይላል፡

“…..inscription with letters on one side in `Amharic' of an ancient style, and on the other letters which appeared to be Greek or Latin. The thrones are described, and also the `Tomb of Kaleb and Gabra Masqal'.”

ይህስ ትግሬዎች ናቸው የጻፉት? ጽሑፉስ ‘ትግርኛ’ ነው ወይስ ‘አማርኛ’? ዘመኑስ? ቦታውስ? አክሱም ነው? ትግሬ ነው? ኤርትራ ወይስ የት ነው? ጹሑፉ አማርኛ ስላለው የትግሬ ፋሺስቶች ጎዳናዎች፤ ታሪካዊ ገጠሮች፤ከተሞች፤ተራሮች፤ወንዞች፤ በወያኔ ታጋይ ስሞች እየተኩ ጥናት ለማካሄድ ወደ ስፍራው በሚመጡ የታሪክ ተማራማሪዎች ፍለጋ እንዲሰወሩ/እንዳይታወቁ/ እያደረገ አንዳለው ወንጀል፤ ይህ ማስረጃም ‘አማርኛ’ጽሑፍ ስለሆነ ሰባብረው ጥለውት ይሆናል ወይንም እንደማይነበብ ወቅረውት ይሆናል። አማራን የሚጠላ ቡደን አያደርግም አይባልም። ወደብን ለዓረብ የሰጠ ቡደን ይህ አያደርግም አንልም።

8)   የፕሮፓጋንዳ ስራ የምትሰሩ ወገኖቻችን፤ የኪነት ባለሞያዎች ሁላችሁም፤ እዚህ መቀሌ ውስጥ ታጥራችሁ አይደለም ማስተማር ያለባችሁ “መቀሌ’ የራሷ ሕዝብ አቅፋ፤ ተደራጅታ ትኖራለች፤ ቅስቀሳ አያስፈልጋትም። ቅስቀሳ የሚያስፈልገው ወልቃይት ውስጥ ያለው፤ የኛ ሰው ነው እያልን ላለነው ሕዝብ ነው ሄዳችሁ ማንነቱን ሄዳችሁ መቀስቀስ ያለባችሁ። ተውጦ የነበረው ባሕሉ እንዲታደስ፤ እንዲያስታውሰው እንዲችል መርዳት አለብን። ይህ መጽሐፍ እዛ ወልቃይት ፀገዴ ውስጥ ያሉ ወገኖች ይህ መጽሐፍ ሲደርሳቸው፤ ለልጆቻቸው እና ልጅ ልጆቻቸው፤ “ይኼውልህ እኛ ማን መሆናችን” ብሎ እንዲላቸው መጽሐፍቱ እዛው ላለው ሕዝብ ዝንዲዳረስ ማድረግ ቀዳሚ ሥራ ነው። ይኼውልህ አባቴ ፤ቅድመ አያቴ…. እዚህ መጽሐፍ ተጽፎ ስማቸው ይገኛል፤ ምስክርም ይኼው፤ ይህ ሰነድ/መጽሐፍ/ ብሎ እንዲል ሕዝቡን መቀስቀስ አለብን። ስለዚህ ይህ መጽሐፍ ትልቅ አስተዋጽኦ እና ድጋፍ ነው። ይህ መጽሐፍ ደራሲያንን፤ የኪነት ባለሞያዎች እና የመሳሰሉ የሚያነሳሳ ሥራ ነው። ትግራይ ማን ማንን ወለደ ዘራችን ማወቅ አለብን። የነ አጼ ዮሐንስ ትውልድ..ማወቅ…..ማን ማንን ወለደ ..ስናወቅ ትግሬነታችን ይጠነክራል፤ ማንንታችን እናውቃለን። ከነገሥታቶች ጀምረን እስከ ትላለቅ ሰዎች እና የመሳሰሉ ስማቸው ከየት እንደመጡ ስናውቅ፤ ድሮ ‘ለቡሰቦቻችሁ ቤተሰባዊ ትስስር የሌለ መስሎአችሁ” እንደ ሌላ ሰትመለከትዋቸው የነበሩ ታላላቅ ትግሬዎች “የናንተ አጥንት ፤ደም” መሆናቸውን በላ ልታውቁዋቸው ትችላላችሁ። ባዕድ አይደለንም፤ ከአንድ ሐረግ የወጣን/የተመዘዝን/ ነን። ከታች እስከ ላይ ያለው ትውልድ ሐረግ ስላልተረዳችሁ ነው። ሃይል እንዲኖረን ይገባል። እውቀት፤ሕብረት ማለት ነው። የዋህነት በጎ ቢሆንም ፤ ተንኮል ጥበብ መኖር አለበት። እኔ ግዕዝ አላወቅም፤ ግን “ኩኑ የዋህነ ከመ  ዕርግብ፤ ወጠቢባነ ከመ አርዌ ምድር” የሚለው ተረድቼዋለሁ፡ የኛ ስለሆነ። ይላል (ዶ/ር ሙሉወርቅ ኪዳነማርያም)

ሙሉወርቅ እያሰተማረን ያለው አስቀድሜ የነገርኳችሁ የሐረግ መምዘዝ፤ (የመሲያኒክ ግሎሪ)፤በታላላቅ ሰዎቻቸው ታሪክ፤ባሕል፤ማንንት መመካትና የነሱ ዘር መሆናችን፤ አንድነታችን “በደም በአጥንት የተሳሰረ” ፤ ከሌሎች ጋር ያልተደባለቀ፤ አንድ ወጥ ግንድ መሆኑን እና በተንኮል እየተጓዙ “ኦምኒፖተነስ” የማያልቅ የማይገሰስ የትግሬ ሃያልነትን ተቀብሮ ከነበረው ‘እንደገና በማስመለስ’ ሃያሎች እንድንባል፡ የሚቀሰቅስ የፋሺስቶች ዋነኛው መመሪያ ትምህርት ነው።

 
9)   እነሱ (አማራዎች) ቴሲስ ዘፍነው ከሆነ እኛ ደግሞ “አንታይ ቴሲስ” መዝፈን፤ “አፀፋ መልስ” መመለስ ነው ያለብን። መልስ ካልመለስክለት፤ “ሞኝ ተናገረው ሁሉ ልክ ነኝ ስለሚል” እኔ ቆንጆ ነኝ ካለ ‘ለካ ቆንጆ ነኝ” ስለሚል ወደ ዕብደት ይለወጣል። ወልቃይት የኛ ነው እያሉን ያሉት ሰዎች  (አማራዎች) በዛ ወቅት አልነበሩም፤ አማራ የሚባል ሰው መጽሐሀፍ ውስጥ አንብቤ አላወቅም።(ዶ/ር ሙሉወርቅ ኪዳነማርያም)

ሙሉወርቅ ትግሬዎችን እያሰተማራቸው ያለው፤ አሁን በትግራይ ውስጥ በስፋት እያደመጥነው ያለውን ‘’በነገዳዊ ፋሺዝም” የተቀመሙ፤ በትምክሕትና መጥን የሌለው ጉራ የተሞሉ “ተራራ ያንቀጠቀጠ ነገድ፤ ቆረጥነው፤መተርነው፤አምበረከክነው…እኛ ጀግኖች ታምር ሰሪዎች፤ ንጉሦችን፤ መሳፍንቶችን አንጋሾች፤ ሌሎች ተከታዮች…..” የሚሉ የመሳሰሉ ግጥሞች እና የትምክሕት ዘፈኖች ‘በትግራይ ወጣቶች’ በስፋት ያለምንም ‘ቁጥጥር’ እየተዘፈኑ በሌሎች ታዛቢ ሕሊናዎች እየተቀረጸ ያለው ትዕዝብትና ቁጭት እንዲቀጥል የሚመክር ‘ናዚያዊ’ ቅስቀሳ ነው።  

 
10)  አማራ ከ 13/14 ክፍለ ዘመን የተፈጠሩ ናቸው። ወልቃይት ከዚያ በፊት አለ።ወልቃይቶች  ከ‘አክሱም’ በፊት የነበሩ ናቸው። ወልቃይቶች በዘመነ ጉዲትም ነበሩ። እነሱ የታሪክ ማስረጃ/ክርክር አያደርጉም። ክርክራቸው። የሰሊጥ አገር ‘ትግሬዎች’ወሰዱት’ ምንትስ ምንትስ ነው ክርክራቸው፡ ይኼው ነው ሙግታቸው።(ዶ/ር ሙሉወርቅ ኪዳነማርያም)

 
ዶ/ር ሙሉወርቅ ንግግሩን ስመዝነው፤ የወልቃይት ምሁራን እና ሌሎች ኢትዮጵያዊያን እያሳተሙዋቸው ያሉት ጽሑፎች እና የታሪክ መጽሀፍቶች ፤የተከታተለ  አይመስልም። የጥንት ስማቸው እንደያዙ የሚጓዙት የወልቃይት አማራዎች ትግሬዎች ‘ሰሊጥ የምንዘራበት ለም መሬታችን ዘረፉን” ብለው ቢሉ ሕጋዊ ጥያቄ ነው። ሰሊጥ የሚያመርት ወልቃያት ሑመራ ተወሰደብን ብሎ አይደለም እንዴ ‘ወያኔ’ ወደ ትግሬ ያጠቃለለው? ለነገሩ- ሰሊጥ ብቻ አይደለም ክሱ፤ የዘር ማጽዳት ክስም ነው!!!!  ወልቃይቶች  ትግሬዎችን እየከሰሱ ያሉት። አደብ አደብ፤ ወያኔዎች የትግራይን ሕዝብ ወዴት እየመሩት ነው? አምና የታየው “አማራዎች ያሳዩት የቁጣ ቁጭትና መዘዙ” ትግሬዎች መማር አልቻልንም? ደወሉ አይሰማንም ወይ? ትግሬዎች ወያኔዎችን በተሎ አስወግዱዋቸው። ወደ አደገኛ  ጭለማ ውስጥ እየከተቱን ነው። ልብ እንግዛ!!!!!!!!


11)     የመሬት ጥያቄ እየጠየቁ ‘ወንድማማቾች ነን’ ቢሉን አንሰማቸውም። ወንድምህ ከጠላህ ወዳጅነት፤ወንድምነት የሚባል የለም ።በማለት የዓድዋው ሰው ‘ ሙሉወርቅ’  በምሳሌ እየመሰለ አድማጩን አስቋል።\(ዶ/ር ሙሉወርቅ ኪዳነማርያም)

“የአማራ ብሔር/ሕዝብ” ቀንደኛ ጠላታችን ነው ፤ ስለሆነም ሰላምና ዕረፍት ማግኘት የለበትም፤ብሎ ከ 40 አመት በፊት በማኒፌስቶ ሕዝብን የቀሰቀሰ የናዚ ቡድን ‘ወንድማማቾች ነን” ብለው ለሚሉን አማራዎች  የሚያዳምጥ ጀሮ ከየት ሊያመጣ ይችላል? ያልተፈጠረበት ጀሮ ከየት ይፈጥረዋል!

12)   ትግራይ የኢትዮጵያ ‘ ሲም ካርድ’ ነች። እኛ ትግሬዎች ኢትዮጵያዊያን ሳይሆነ፤ ኢትዮጵያን ያደረግን የመሰረትን ነን። የእኛ ኢትዮጵያዊነት ‘ ምስክር’ አያስፈልገንም፤ ምስክር የምንሆንለት ካልሆነ በቀር። ብያምኑም ባያምኑም፤ ሃቁ ያ ነው። (ዶ/ር ሙሉወርቅ ኪዳነማርያም)

ይህንን ፋሺስታዊ ትምክሕት ደጋግሞ ተናግሮታል። ትንሽ ነካክቼዋለሁ፤ የተቀረው ለናንተው ልተው።

13)  ትግራይ ውስጥ ያልተደረገ ታሪክ የለም። ሁሉም የኛ ነው። ጥልፍ መጥለፍ፤ የሴቶች ጸጉር አሰራር ዘፈን/ሙዚቃ፤ የፊደል ጽሁፍ ጥበብ ሁሉም የትግሬዎች ነው። እነዚህ ሁሉ ግን (አማራዎች)የኛ ነው እያሉ እየወሰዱት ነው። “አሰርቲቭ” መሆን አለብን። አስቀድሜ እንደገጽኩት አሞኝ ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ክሊኒክ ሄጄ፤ ጥዋት ነው ፤ተራ ይዤ እንዳለሁ፤ “ዛሬ ስንት ቀን ነው?” አለችኝ። “በኢትዮጵያ ነው ወይስ በፈረንጅ?” ስላት “በአማርኛ አለችኝ” “እኔ ደግሞ ‘በትግርኛ ነው የማውቀው” አለኳት። “አሰርቲቭ” ማለት ይኼ ነው። እኛ ነን መጀመሪያ የቀን መቁጠሪያውም ያወጣነው  (“አመራ” አይደለም) ማለት አለብን። እንዲያ ካላደረግናቸው “አደብ” ጸባይ አያደርጉም። ደብተር ስንገዛም “የአማርኛ ደብተር” ብለን ከገዛን፤ “ለትግርኛ’ የማይሆን ደብተር ለምን እንገዛለን? አማራ አልሰሩትም። ደብተርን የሰሩ ፤ ለእንግሊዝኛ፤ለማንኛ….ለማንኛውም የሚያገለግል ነው። ሳይሰሩ የኛ ነው፤ አማርኛ ደብተር እያልን መጥራት ስሕተት። ሳይሰሩ “በጨው ደንደስ በርበሬ ተወደስ”  ነው። (ዶ/ር ሙሉወርቅ ኪዳነማርያም)

ይህም ለናንተው ልተው።
 
14)  እኛ ትግሬዎች ልባችን አንድ ነው፤ ስሜታችንም አንድ ነው።(ዶ/ር ሙሉወርቅ ኪዳነማርያም)
 

ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም ‘የትግሬዎች አስተሳሰብ እንደ ካንድ ፋብሪካ እንደወጣ ሳሙና ሁሉም አንድ አይነት አስተሳሰብ አለው” ብለው ፕሮፌሰር ወ/ማርያም ሰደቡን እያለ እራሱም ሆነ እነ ገብረኪዳን ደስታ እሪ እያሉ ፕሮፓጋንዳ ሰርተው መስፍን ወ/ማርያም ‘ጸረ ትግሬ ነው’ እያሉ ሲወራጩ እንዳልነበረ፤ ዛሬ ያንን ተረስቶ “ትግሬዎች ልባችን እና ስሜታችን አንድ ነው” ሲል ከመምህር ሙሉወርቅ ኪዳነማርያም መስማታችን ፤ፕሮፉሰሩ አልተሳሳቱም ነበር። ትግሬዎች ሲሉት ልክ የሚሆነው፤ ሌሎች ሲሉት ግን ልክ የማይሆነው እና በያዙኝ ልቀቁኝ የምንወራጭበት መብት እንዴት ሊከሰት ቻለ? ብየ ጽሑፌን የትግሬ ፋሺዝም ዓይኑ በሚያስፈራ ደራጃ አድጎ አገሪቷን ወደ መሃምቅ እየገፋት እንደሆነ፤ ማስረጃዎች አቅርቤላችኋል። የመቀበል፤ያለመቀበል የናንተው ነው። ጨርሻለሁ።

አመሰግናለሁ ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ -  ሰማይ አዘጋጅ)

 

 

No comments: