Saturday, June 10, 2017

በ5ሚሊዮን ትግሬዎች ላይ የዘር ፍጅት ጥሪ ያስተላለፈው የኢሳት ቴ/ ቪዥን ጣቢያ ዕርቃኑ ሲጋለጥ ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ አዘጋጅ) Ethiopian Semay


በ5ሚሊዮን ትግሬዎች ላይ የዘር ፍጅት ጥሪ ያስተላለፈው የኢሳት ቴ/ ቪዥን ጣቢያ  ዕርቃኑ ሲጋለጥ

ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ አዘጋጅ) Ethiopian Semay

እንደምን ሰነበታችሁ? ሌላ ርዕስ ለመተቸት በዝግጅት ላይ እያለሁ በኢሳት ላይ የተከሰተው የተደበቀ ጉድ ስሰማ ሌለውን አጀንዳ ለሚቀጥለው ሰሞን አስተላለፍኩት።  የዛሬው ቀዳሚው ትችቴ በሩዋንዳው የዘር ማጽዳት ዘመቻ ጥሪ በማስተላለፍ የተከሰሰው የራዲዮ ኮሊን የካቡንጋ ዓይነት ልሳን  በትግራይ ሕዝብ ላይ የዘር ፍጅት እንዲፈጸም በማስተላለፉ በትግሬዎች ጥርስ የተነከሰበት ‘ኢሳት’ የተባለው የግንቦት 7 ቴ/ቪዥን በትግራይ ሕዝብ ላይ በፈረንጆች ዘመን አቆጣጠር በ September 2016 አሰራጨ የተባለው የዘር ማጽዳት መግለጫ ጉዳይ ባጭሩ እንመለከታለን።

ኢሳት በጸረ ትግሬዎች የዘር ፍጅት/ ጀነሳይድ ጥሪ በታዋቂ ትግሬዎች ጥርስ ውስጥ መግባቱ የሰሞኑ መነጋገሪያ መድረክ ሆኗል። ኢሳት በፈረንጆች ዘመን አቆጣጠር September 2016 በመሳይ መኮንን አንባቢነት በኩል ተሰራጨ የተባለው የዘር ማጽዳት ጥሪ ሰሞኑ ስያትል ውስጥ፤በገለልተኞች እና በግንቦት 7 ሚደያዎች አድማቂነት እና በግንቦት 7 ልባቸው የተማረከ ግለሰቦች የተዘጋጀው ሕዝባዊ ስብሰባ፤ ከእንግዶቹ የክብር ዕንግዳና ተናጋሪ የነበረው አንዱ ዶ/ር አረጋዊ በርሔ፤ በአዳራሹ ውስጥ የለነበረው ለኢሳቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ አበበ ገላው ኢሳት ያስተላለፈውን በትግሬዎች ላይ ያነጣጠረ የዘር ማጽዳት በሚከተለው ጥያቄ አቅርቦለት ነበር።

“የኔ ጥያቄ ለወንድሜ ለኢሳት ዳይሬክተር ለወንድሜ አበበ ነው። ሁላችንም እንደምናውቀው የትግራይ ሕዝብ፤ ህወሓት/ኢህአዴግ/የጭቆና “ቤተ-ተሞኩሮ” አድርጎታል።በኢትዮጵያ ያንሰራራው የጭቆና ገፈት ትግራይ ውስጥ በሕዝቡ ላይ ነው የጀመረው።ማሌሊት በሚባል ጽንፈኛ ድርጅት፤ በዛው በኩል ነው የተጀመረው።ከዚያ ሙከራው ሲያልቅ ወደ ሌላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው የዘረጋው።

ይኼ ቀረብ ብሎ ላየው ሰው ግልፅ ነው። ግልጽነቱ አጠያያቂ ስላልሆነ ወደ ዝርዝር ሁኔታ አልገባም፤ ግልፅ ስለሆነ ማለቴ ነው። ኢሳት ጭቁኖችን የማስተባበር ሓላፊነት የተሸከመ ድርጅት ነው እንደ እማዳምጠው። ግን እኔም እራሴ በኢሳት ተገልጋይ ነበርኩ፤ እገለገላለሁ። እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ወደ መድረኩ እየሄድኩ የተለያዩ ቃለ ምልልሶች  አድርጌአለሁ። አብረን ስንታገል ነበርን።
 
በቅርብ ጊዜ ግን ጸረ ሕዝብ የሆነ፤ፀረ ትግራይ ሕዝብ የሆነ፤ ስርጭት በጆሮዬ አዳመጥኩ። ስርጭቱ ምን ይላል፡ “የገማ ዓሳ ከነውሃው ካልተደፋ አይበጅም የሚል ነው”። ይህ አባባል፤ ህወሓት እና የትግራይ ሕዝብ አብሮ መደፋት አለበት ማለት ነው። ይህ “R T L M” የሚባለው ሩዋንዳ ላይ እነ ‘ካቡጋ’ ካስተላለፉት የዘር ፍጅት ሰርጭት በምን ይለያል? አደገኛ አይደለም ወይ? ሕዝብ ከሕዝብ ጋር ማጋጨት አይደለም ወይ? (አቶ አበበ) እንደ ዳይረክተርነትህ መጠን ይህ ነገር ታዝበህ እርማት ተደርጎበታል ወይ? ለትብብራችን ያለው “ነጋቲቭ/አፍራሽ/ አስተዋጽኦ አይታችሁታል ወይ? ለማለት ነው። አመሰግናለሁ።”

 
ሲል ዶክተር አረጋዊ በርሔ ለኢሳቱ ዋና ስራአስኪያጅ ለአቶ አበበ ገላው የጠየቀው ጥያቄ አቶ አበበ ገላው “ምን ብሎ” እንደመለሰለት በዩቱብ የተለቀቀ ስላላገኘሁ፤ ከዚያው የተገኙ አስተማማኝ ሰዎችን ጠይቄ እንደነገሩኝ ከሆነ፤ የሚከተለው ቃል በቃል ሳይሆን ከዚህ በታች የቀረበው ተመሳሳይ ዓይነት መልስ ሰጥቷል ተብሏል። መልሱም እንዲህ ይላል፡

በወቅቱ መግለጨው እንደተነበበ፤ ወዲያውኑ አፍራሽ መሆኑን ስንረዳ ከሚዲያው አውርደነዋል። የተላለፈው መልዕክት ስሕተት ነው፤ ለዚህም ይቅርታ እንጠይቃለን” የሚል ነው ባጠቃላይ በማጠጋጋት የተነገረኝ።


እንዲህ ከሆነ የአበበ መልስ የአረጋዊን ጥያቄ በሚዲያ እንደተለቀቀው ለምን የኢሳት መልስ በቀላሉ ልናገኘው አልቻልንም? ኢሳት በወቅቱ የለቀቀው የዘር ፍጅት የሚያበረታታ መግለጫ ስሕተት ሆኖ ተረድቶት የተላለፈው የቴ/ቪዥን ኤፒሶድ/ ፕሮግራም ከሕዝብ እይታ ሲሰውረው፤ ለሕዝብ ይቅርታ አስተላልፎ ነበር ወይ? ካስተላለፈስ ለምን በዩቱብ ላይ አላየነውም? ከፊተኛው የባሰ ደግሞ “ይቅርታ ሳይጠየቅ ተደብቆ እንዲቀር ማድረጉ “የተላለፈው ቅስቀሳ የብዙ ጅሎችን ሕሊና በመበከሉ፤ ጉዳት ተፈጽሟል እና ጉዳቱ ለመለካት ያስቸግራል ማለት ነው” ለምን እንደተደበቀ አልገባኝም።

በፊተኛው ጥፋት ሳይወሰን ሲያትል ላይ ለቀረበው ጥያቄ አንኳ በጣቢያቸው የይቅርታ መግለጫ ወዲያውኑ ሊያስተላልፉ አልቻሉም። በጭቃ ላይ እንደገና ጭቃ። ለምን? በጣም ያስቆጣኝ ግን ኢትዮ -ሚዲያ የተባለው አሳፋሪ ሚዲያ፤ አዘጋጁ የትግራይ ሰው ሆነ ወዳጁ ብርሃኑ ነጋን እንዳያስከፋ ይሁን ወይንም እርሱ በሚያውቀው ምክንያት ይህ ጉድ ተገልጾ እያለ ሁኔተውን ቀርፆ ለሕብ ከማስተላለፍ ይልቅ፤ የነ ጌታቸው በጋሻው የነ በያን አሰቦ፤ የነ ዳዊት ውልደጊዮርጊስ መናኛ ፕሮፓጋንዳ በቪዲዮ ቀርጾ እንድናይለት ለግንቦት 7 ፕሮፓጋንዳ አመቺነት በመለጠፍ ቅድሚያ ሰጥቷል። ለምን?


ስለ ጸረ ሕዝብ እና የሻዕቢያ አፈቀላጤው ግንቦት7 በኩል ጎላ ያለ ገንዘብ እየተቆረጠለት የሚተዳደረው ስለ ኢሳት የሕዝብ ጆሮ እና ዓይን ነኝ ባይነት ለሚጀጃሉት ሞኞች ማጃጃል ችሏል፤ ለኔ እና ለመሳሰሉ ነገሮች በመለየት ለሚጓዙ ዜጎች የመሳሰሉትን ግን ከቶውንም ማጃል  አይቻለውም። ለዚህ ነው ‘አብዛኛዎቹ ተቃወሚ ሚዲየዎች እና ፖለቲከኞቻቻው፤ ከወያኔ የማይሻሉ አሳፋሪ እና አደገኞች ናቸው እያልኩኝ በጮኹኩኝ ቁጥር በጅላጅሎች የምሰደበውና የምዘለፈው። ሓቅ ግን ለጊዜው ይደበቅ ይሆናል ግን እራሱ ከታፈነበት መንጥቆ የመውጣት ሃይል ማንም አያግደውም።


ይሆን ሆኖም ኢሳት 5 ሚሊዮን እና በ90 ሚሊዮን ሕዝብ መካከል መደረግ ያለበት ግብግብ ሲገልጽ በኢሳት ጋዜጠኛ ተነበበ የተባለውን ከላይ የተጠቀሰው “የተበላሸን ባሕርና ዓሳን ማስወገዱ አንዱ ነው፡’ የባሕር ውሃ ማስወገድ” ለማድመጥ ይህንን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ፡

         ጭምብሉ ሲወልቅ:


        - ESAT calling Genocide attack on Tigreans
        
           አመሰግናለሁ

ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ አዘጋጅ- Ethiopian Semay) getachre@aol.com

 

No comments: