Friday, May 5, 2017

በሞረሽ ላይ ዘመቻው ተጧጡፏል፤ ለምን?ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ)



በሞረሽ ላይ ዘመቻው ተጧጡፏል፤ ለምን?
ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ)
ለበርካታ አመታት የዘለቀ በግል የታዘብኩት የተቃዋሚውም (ውጭም አገር
ውስጥም ያለው) ሆነ የተቃዋሚው ሚዲያ ባሕሪ አማራው ላይ ሲመጣ ሁለት ባሕሪያትን አይቻለሁ። ስለ ኢትዮጵያ ይጮሃሉ፤ስለ ኦሮሞ ስለ ጋምቤላ ስለ ሶመሊ..ጮክ ብለው ሲጮሁ አድምጫለሁ። አማራው ላይ ሲሆን፤ ጯሂ ልሳናቸው ይሰላል ወይንም ከጮሁም ‘ዳበስ ዳበስ’ አድርገው ይተውታል። ግለሰቦች እና ጋዜጠኞች ሲታሰሩ ወይንም "ዓለም በእስልምና ስትመራ ሰላም ወርዶ ነበር፤ ኩፍሪሎች ሲሰፍኑ ዓለም ሰላም አጣች " የሚሉ የግራኝ ‘አህመድ አሞጋሾች’ የሆኑት ‘ለአንዳንድ የድምጻችን ይሰማ’ መሪዎች፤ከሚሊዮኖኖች አማራዎች በላይ ሲጮሁላቸው እና በየተባበሩት መንግሥታት እና ሰብኣዊ ድርጅቶች እየሄዱ ሲሟገቱላቸው ታዝቤአለሁ።
 
አስገራሚ የሚያደርገው ደግሞ በዚህ ባሕሪ የሚተውኑ ግምባር ቀደም ተዋናዮች ‘ጎልተው የሚታዩት’ አማራዎች ናቸው። ለምን እንዳ እንደሆነ ሁሌም የሚገርመኝ ጥያቄ ነው። ሰሞኑ ባንዳንድ መረጃዎች ያነበብኩዋቸው እና የደመጥኳቸው አንዳንዱም ወደ ግል ኢመይሌ የተላኩልኝ በሞረሽ ላይ፤በወጣት ሄኖክ የሺጥላ እና በጋዜጠኛ ደምስ በለጠ ላይ ያተኮረ ዘለፋ ስመለከት የተጠቀሱ ደርጅቶች የሚፈለፍሉዋቸው ከወያኔ የባሱ ጋጠወጦች/ጋንጎች/ እንዴት ማረም እንደሚቻል ደጋግሜ ሳስበው እነኚህስ እንኳን አገር ውስጥ አልሆኑ፡ ያሰኘኛል።እኔ የሞረሽ አባል አይደለሁም፤ ነገር ግን ሞረሾች እያደረጉት ያሉትን አማራን ከጠላት የመከላከል ሙከራ፤ ሐኪም አስራት አማራው መደራጀት እንዳለበት የቀየሱትን ግብ መከተላቸው እጅግ ደስ ብሎኛል። ሳስበው፤ሳስበው፤ ለአግራሞቴ መልስና መቋጪያ ያገኘሁት የሚከተለው ነው። የጋዜጠኞች፤የወይዘሪት ብርቱካን፤የአቡበከር፤ የወዘተ….የወዘተርፈ… እስረኞች ስም እና ስቃይ ብቻ ነጋ ጠባ እያነሳችሁ፤ ኢትዮጵያ! ኢትዮጵያ! ስትሉ ለ24 ዓመት የዘለቃችሁ የአማራን ሕዝብ
ሰቆቃ እንዳይታይ ጭለማ ውስጥ ደብቃችሁት የተጓዛችሁ ወገኖች፤ አንጀቴን እንዳሳረራችሁኝ ሁሉ፤ "ሞረሾች" ስጠብቀው የነበረውን መብራት ‘ጨለማው ላይ’ "ቦግ" አድርገው ማብራታቻው እጅግ ደስ ብሎኛል። ጸረ ሞረሽ/ጸረ አማራዎች ደግሞ የመብራቱ ደማቃነት እና ሃያልነት ካስበረገጋቸው "የበረገገው ዓይነ ሕሊናቸው" እንዲጠገን "ሓኪሞችን" ማማከር ነው።
 
አብዘዛኛዎቹ ጸረ ሞረሽ የሆኑት ደግሞ ኢሕአፓ እና ግንቦት 7 ናቸው። እነኚህ ሱልጡን ዲሞክራት ተቃዋሚዎች በታሪክ ያስመዘገቡት ልቅሶ ሲፈተሽ "ለማንም እስረኛ ያልተደረገ (እጅግ አስገራሚ) ከኢትዮጵያ ወደ ለንደን ስልክ ደውሎ ልጆቹ እና ሚሰቱን ለማነጋገር ለተፈቀደለት "አንዲ ጽጌ" ውይ!!!! ውይ!!!! ዋይ!!!ዋይ!!! ተብሎ ሲለቀስለት" በሚሊዮኖች ለጠፉ አማራዎች ግን አታልቅሱለት ይሉናል ሱልጡን ዲሞክራት ተቃዋሚዎቻችን።" (መልስ ለምኒሊክ ሳልሳዊ ከሚል ጽሑፍ ከጌታቸው ረዳ March 13, 2015 የተገኘ ጥቅስ)።
 
እኔ እንደታዘብኩት ሞረሽን በአደናጋሪ ስልት ለማኮላሸት በግልጽ የመጡ በርካታ ክፍሎች አሉ (ኤለመንትስ)።አንደኛው፤ የአማራውን ጥቃት ሕዝባችን እና ዓለም በግልጽ እንዳይነጋገርበት ወያኔ እና ኦነግ የሚያሴሩት ጥረት ነው። ሌላው ከኦነግ ጋር እስክታ የሚወርደው ከተክሌ የሻው ይልቅ "ኢሳያስ አፈወርቅን እመኑ" የሚለው የግንቦት 7 ጸረ አማራ ጀሌዎች ናቸው። የተቀሩት ከነዚህ ለየት ብለውም ሆኑ ተዳብለው ድብብቆሽ እየተጫወቱ ተጨማሪ የፕሮፓጋንዳ ጥቃት የሚያደርሱ ተማጻዳቂ ከአማራ አብራክ የወጡ በተቃዋሚ ጎራ የተሰለፉ አማራዎች ናቸው። አነሱ ናቸው የባሰውን የወላጆቻቸው እና የዘመዶቻቸውን የአማራውን ሕዝብ ሶቆቃ እንዳይደመጥ አጉል ፖለቲካ እያሰራጩ እንቅፋት ሆነው ያሉት። በግልጽ እንነጋገር!!!
 
እንደገና አማራ ነን ብለው አደገኛ የሆነ ቅስቀሳ የሚያካሂዱ "ቤተ አማራ" የሚል ስም ለድርጅታቸው ሰጥተው ለአማራው ሕዝብ በውኑም በሕልሙም ያልነበረበት "የመገንጠል ዓላማ" እናራምዳለን ብለው በግልጽ የሰበኩ ወደ መድረኩ ብቅ ያሉ ስመለከት፤ይህ ክስተት በተለይም እጅግ አሳፋሪ እና ያልጠበቅኩት ክስተት ነበር። ያ እንዳለ ሆኖ፤ ወደ 7 የሚደርሱ ሌሎች አማራዊ ድርጅቶች አሉ ይባላል። እነዚህ ፖለቲካዊ እና ማሕበራዊ ድርጅቶች ናቸው። በፖለቲካ የተደራጁት ታሪክ እንደሚያስተምረን፤ "በጎሳ የተደራጀ ፖለቲካዊ ድርጅት" ዞሮ ዞሮ ወደ ናዚያዊ እንደሚሸጋገር ታሪክ ነግሮናል።ወደ እኛው ታሪክ ስንመለስ "ወያኔ እና ኦነጎች" ለዚህ የማሳያ ምሳሌዎች ናቸው። ጎሳን በፖለቲካ ማደራጀት ወደ ወያኔነት እና ኦነግነት ካባ መከናነብ ነው ስል ግቡ "ሥልጣን ነው" ሥልጣን ለማን? ለተወከለለት ጎሳ ሥልጣን ላይ ለማውጣት። አማራው ወደ ሥልጣን ማውጣት ሳይሆን መሆን ያለበት፤ አሁን ከተጋረጡበት ጠላቶቹ እንዴት መከላከል ይቻላል? ጥፋቱ እንዳይቀጥል ምን መደረግ አለበት፤ ጠላቶቹ እና ወዳጆቹን መለየት፤ማስተማር፤ማንቃት (ሚዲያ)፤ማደራጀትና ማስታጠቅ። ከዚህም አልፎ ለህይወቱ መጥፋት ምክንያት የሆኑ ተጠያቂ ወንጀለኞችን እንዴት ወደ ዓለም ዐቀፍ ሕግ ማቅርብ እንደሚቻል መወያት እንደ ንቦች እና ጉንዳኖች ባንድ እዝ በብልሃትና በጥንቃቄ መጓዝ ነው መሆን ያለበት።
 
 
እነኚህ ድርጅቶች ፖለቲካውን ትተው ወደ ስቪካዊው ሞረሽ ራሳችሁን እና ተከታዮቻችውን ይዘው ደርጅቱን በምሁራን እና ባገር ወዳዶች እንዲሁም በገንዘብ እርዳታ አጠናክረው ቢጓዙ፤ ለጠላት ጠንካራ ተቀናቃኝ እና ለአማራውም መድህን እንደሚሆኑ ጥርጥር የለውም። በአንድ አገር ውስጥ ጦርነት ሲከሰት "አንድ አገራዊ የሆነ የአገር መከላከያ እዝ " እንጂ 7 የመከላከያ እዝ አይኖርም። እርግጥ በውስጡ ለዘመቻው መሳካት የተለያዩ እዞች አሉት፡ እነኚህ ግን በዋናው እዝ የሚንቀሳቀሱ የመምሪያ ቅርንጫፎች ናቸው። አማራውን በ77 ቤት ቅርጫት ውስ ማስገባት ትግሉ አይሰምርም።ለጠላቶች ሰርጎ መግባት ቀላል መንገድ ይሆንላቸዋል።

አማራውም ባንድ እዝ መዋቀር አለበት። ደንቃራ (ኢጎ) ባህሪ ወደ ጎን መተው እና ባንድ መጓዝ ለግቡ አመርቂነት ዓይነተኛ መሳሪያ ነው። ምክንያቱም በአንድ ጠላት ብቻ ሳይሆን አማራው በእልፍ ጠላቶች የተከበበ ነው። ከራሱ አብራክ የተገኙ ጠላቶችም አሉት። ስለዚህ እኔ ለብዙ አመታት አማራው እራሱን ከጥቃት ለመከላከል በአማራዊ ድርጅት ሥር መደራጀት እንዳለበት ስጮህ ስሰደብ እና ስብዕናዬ ሲዘለፍ እንደመኖሬ፤ ዛሬም የምለግሰው ምክር፤ ስዋጋለት የነበረው አማራ ራሱን ስለማደራጀቱ ጉዳይ "ፍሬ አፍርቶ" ማየቴ እጅግ የኮራሁበት እና የተደሰትኩበት ትግል እንደሆነ ብገነዘብም፤ የተተለከው ‘ችግኝ’ እራሱን መስለው በዙርያው በሚበቅሉት ‘ሙጃዎች’ እንዳይዋጥ ዛሬም እርማት ያስፈልገዋል። በርካታ የአማራ ድርጅቶች ተመሰርተዋል፤ አያስፍልግም። ምጽአተ አማራን ደጋግማችሁ አንብቡ። አስቀድማችሁ ስላልደረሳችለት ይቆጫችል። ልቦናችሁ ይቃጠላል። የአማራው እልቂት ዘገባ የሚገልጹ ዘገባዎች በመጽሐፍ ተዘግቧል። በበዴኖ፤ ግራዋ ኩርፋ ጨሌ፤ ላንገ፤ከርሳ፤ሶካ፤ ደደር፤ሒርማ ፤ቁኑ፤መሰላ፤ ገላቲ፤ ዶባ፤ሓበሮ፤ ቦክ ፤በደሳ ገለምሳ ሜንጫ አርሲ ነገሌ ወለጋ፤ በጉራ ፈርዳ በቤንሿንጉል እና ሌሎች ቦታዎች… የደረሰው ግፍ ማንበብ ፤መዘከር የስፈልጋል።
 
በነዚህ ቦታዎች ሴቶች ጡታቸው ፤ወንዶች ብልታቸው ተቆርጧል። ህጻናት፤ከእናቶቻቸው ጉያ ተነጥለው ተለያይተው እስከመቸውም እንዳይገናኙ ተደርጐ እንዲበተኑ ተደርጓል፤ ሽማግሌ፤ወጣቶት ሴቶች እና ወንዶች መኖሪያ ቤቶቻቸው ተቃጥሎ፤ ንብረታቸው ተዘርፈው በገፍ ከአካባበዊው እየተገፈተሩ ተባርረው በአማራዎች ላይ ያነጣጠረ የዘር ማጥፋት ወንጀል ተፈጽሞባቸዋል። ዛሬም ፤በወልቃየት (ጎንደር)፤በወሎ በጎጃም፤በሸዋ …በአራቱ የአገሪቱ መዓዝን ሁሉ ጥቃቱ ቀጥሏል፡ የአማራ ወጣት በወያኔ ጎስታፖ ወታደሮች እየታፈሰ፤እየተገረፈ፤ግፍ እየተፈጸመበት ነው። ዜናው ትኩስ ነው፤ ቀይ መብራት በርቷል! ግን ማን ይቁም? ሁሉም እያየው እየጣሰው ያልፋል፤ ዳኛ የለም፤ ምሁር ተብየው እና ተቀዋሚው አማራ እና ሌላው ዜጋ "የአማራ ሕብረተሰብ በዘረኞች እየተገደለ በዓይኑ እያየ "ቀዩን መብራት" እየተጣሰበት ኑሮው ቀጥሏል። አቶ ተክሌንም ሆነ ስለ አማራው መብት የቆሙ ዜጎችን እንደ ወያኔ አድርጎ መሳል፤ ስማቸውን እና ስብእናቸውን ጥላሸት ቀብቶ ማጉደፍ፤ ጥቃት ከሚፈፈጽሙባቸው ወያኔዎች አይተናነስም። ከላይ የጠቅስኳቸው ጸረ አማራ የሆኑ የተቃዋሚ ድርጅት ጀሌዎች የማስተላልፈው መልእክት በቅርቡ ከዚህ ዓለም የተለየው እውቁ ገጣሚ ገሞራው (ሃይሉ ገ/ዮሐንስ) የገጠመውን ግሩም ጥቅስ ወዳጄ ሐኪም አሰፋ ነጋሽ አንዲህ ሲል ይጠቅሳል፦
"አንደበት ላጣ ሕዝብ ካልተናገሩለት፤
ወንጀል አይሆንም ወይ ወገኑ ነኝ ማለት"
ይላል። ታዲያ አንደበት ላጣ አማራው ተዘርዝሮ የማያልቅ ግፍ የተፈጸመበት ይህ ሕብረተሰብ ‘ልሳኑ’ ሆኖ መናገር (ያውም ከአማራ ልጆች የተወለዱ አማራዎች) ባስገራሚ ዘለፋ ተጠምደው ሞረሽን ሲዘልፉ ማየት ፈረንጆች "ስትረንጅ" የሚሉት "አዲስ ክስተት" ነው፤ ይህ ባሕሪ ካልቆመ ወደ ቀጣይ የቁርቁስ አዙሪት ውስጥ የሚጠመደን ይመስለኛል። ያውም ለአማራው መጮህ የተጀመረው እኮ ለጋምቤላ ለኦጋዴኖች ለኦሮሞች ከተጮኸ በኋላ ነው ዘግይቶ ከስንት አመት በኋላ ተቃዋሚው ስለ አማራው መጮህ (ዳበስ ዳበስ ማድረግ) የጀመረው! ማስረጃ ላቅርብ።

 ታማኝ በየነ እንዲህ ይላል

"ትናንት የጋምቤላ ወንድሞቻችን በግፍ ሲረሸኑ፤ ትናንት ኦጋዴን ባውሮፕላን ሲደበደብ፤ ትናንት አዋሳ..ሁላችንም ጮኸናል። ዛሬ ሁላችን ለነዚህ ድሃ ኢትዮጵያዊያን መጮህ አለብን።" ታማኝ በየነ ከኢሳት መሳይ ጋር ያደረገው የስልክ ቃለ መጠይቅ ያገኘሁት ።
ድሃ ኢትዮጵያዊያን" እያላቸው ያለው "አማራ" ለማት ነው። ታማኝ ‘አማራ’ ለማለት አልፈለገም ማለቴ ሳይሆን (ኋላ ደጋግሞ ብሎታል) ‘አማራ’ የማለት ልምድ ስላልተለመደ "ድሃ አትዮጵያዊያን" ወደ ሚለው በብዙ ተቃዋሚ አንደበት የተለመደ የሽፋን ስም ነው።

ታማኝም ከኔው ጋር እንዲህ ሲል ይስማማል፡

"ዛሬ ማንኛውም ሰው ሲታሰር ወይንም ሲገደል የምንጨኸውን ያህል አማራ ሲሆን ግን፤ ሌሎቻቻን አማራ እንዳንባል እንሸሸዋለን ያንን ሃሳብ፤ ምክንያቱም ሁሉም የዘመተበት ስለሆነ ፤ አማራነትን እንደ ወንጀል አድርጎ የማት….ሕዝቡ ግን እንዲያውቀው የምፈልገው፤ ኢትዮጵያ በምትባለው አገር ውስጥ ቢያንስ ከ20 እስከ 22 ሚሊዮን ያላነሰ ቁጥር ያለው ሕዝብ ነው። ይህንን ሕዝብ እንደጠላት ፈርጆ ወይንም እንደማይመለከተው አድርጎ ማየት "ኢትዮጵያ" ስለምትባለዋ አገር እያሰብን ነው ወይ? የሚለው የሚያጠያይቅ ይመስለኛል። ስለዚህ በተለያየ ጊዜ ኢትዮጵያ ውስጥ የተለያዩ ቀውሶች ሲከሰቱ ድምጻቸው የሚያሰሙ ተቃዋሚዎች እዚህ ነጥብ ላይ ዝም ማለታቸው፤ ለኔ አልገባኝም።" ታማኝ በየነ፤ በሚከተለው ቪዲዮ ያድምጡ The Silent Genocide on the Amhara
https://youtu.be/z1qyhUOOW3s እዛው ቪዲዮ የተካተቱ የተፈናቀሉ አማራዎች ድምጽ ሰምታችሁ ልባችሁ አንዳይሰበር በተቻለ ዝግ ብላችሁ እየቻላችሁ አድምጡት። ይህ የአማራዎች አሳዛኝ ብሶት ስታደምጡ፤ ግራ የገባው ተቃዋሚው ስለሚሰብካችሁ "ዲሞክራሲ" ነው ወይስ ስለ እነዚህ ሰዎች ህይወትና አቤቱታ ቅድሚያ መስጠት ያለባችሁ?

አመሰግናለሁ ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ) getachre@aol.com (Ethiopian Semay)
 

 

No comments: