የኤርትራ ባንዳዎች ለ26ኛው የባርነት
በዓላቸው ሲያከብሩ በኢሳያስ አፈወርቅ ትዕዛዝ የአባቱ እና የእናቱ የሆነችውን የኢትዮጵያ ሰንደቃላማ ተቦጫጭቃ “ኮምቢሽታቶ” ጎዳና
ላይ በሰልፈኞች እንድትረገጥ አዘዘ!
ጌታቸው ረዳ (የኢትዮ ሰማይ አዘጋጅ)
የግንቦት 7 ምርጥ ባንዳዎች በጥብቅና
ስራ!
እንደምን ሰነበታችሁ። በተቃዋሚው እና በወያኔ መሪዎች ላይ
የምሰነዝራቸው ትችቶች በብዙዎቹ የተቃዋሚ ድረገጾች በኢትዮጵያ ሕዝብ እንዳይነበቡ በእራሴው እና በወዳጅ ድረገፆች የምለጥፋቸውን
የታገዱትን ትችቶቼን አፈላልጋችሁ የምታነቡና የምታሰራጩልኝ ሁሌም በደብዳቤም በስልክ መልዕክትም እየደወላችሁ እርካታችሁን የምትገልጹልኝ
ወገኖቼን አመሰግናለሁ። ገብርኤል፤ ፈረደ፤ሜላት ..ስንታችሁ ብዬ ልጥራ። በተለይም በታላቅ አክብሮት ጎምበስ ብዬ እጅ እየነሳሁ
ለማመስገን የምፈልገው ወዳጄ ኢትዮጵያዊው የቁርጥ ቀን ሰው፤ የተከበረው ሊቀሊቃውንት አቶ “ጉዱ ካሳ” በዛው በተዋበው ብዕርህ፡”የኢትዮ
ሰማዩ ጌታቸው ረዳ በጨረፍታ” በሚል ርዕስ እኔን በማመስገን ሰፊ
ጽሁፍ ጽፈህ በወዳጅ ጠላት ፊት ለኢትዮጵያ ሕዝብ በማሳወቅህ እጅግ፤ እጅግ፤እጅግ አመሰግናለሁ።
በዚህ አጋጣሚ ጽሑፉን የላክሀላቸው ተቃዋሚ ድረገፆች “አናሳትምም’
ብለው ትግሌን ከታሪክ ማሕደር ለመደበቅ የጣሩ ከወያኔ የባሱ ድረገጾች በሌላ ርዕስ አምለስበታለሁና ጠብቁኝ።ሆኖም ጽሑፉን ላሳተሙት
ለወዳጆቼ “ለኢትዮ-ፓትርዮት” ፤ “ለወልቃይት.ካም” ድረገጽ፤ “ለሳተናው” ድረገጽ አዘጋጆች እና ‘ለኢትዮ-ኤክስፕሎረር” አዘጋጆች፤አጅግ
ከልብ አመሰግናለሁ። ከእይታዬ ውጭ ያሳተማችሁት ብትኖሩ እባካችሁ አሳውቁኝ ሳላመሰግናችሁ ከዘለልኩኝ ወይንም በሕዝብ ፊት ለታሪክ
የሚነበብ ስለሆነ እንዳትቀየሙኝ እባካችሁ አሳውቁኝ። ውድ ጉዱ ካሳ
ስለ እዚህ አክብሮትህ በሌላ ቀን እምለስበታለሁ። አመሰግናለሁ።
አሁን ወደ ርዕሳችን።
ከላይ በጸሑፌ ርዐስ አንደገለጽኩት የሙሶሎኒ ልጆች 26ኛው
የባርነት ነፃነታቸውን ሰሞኑን አክብረዋል። የሰልፉ ትዕይነተ ስም “የኤርትራ ካርኒቫል” ብለው ሰይመውታል። “ካሬቢያን ካርኒቫል”
እንደማለት!! ደግነቱ የወንዱን ላሃጭ የሚያዝረከርኩ እንደ ካረቢያኖቹ ሰውነተ ምልምል ኮረዳዎች እርቃናቸው ወጥተው የሚወዛወዙ ሰልፈኞች
አልነበሩበትም። አሳዛኝ የሚያደርገው የትዕይንቱ ጉልህ ነገር ጎልማሳ ወጣቶች ከኣሳያስ ነብሰገዳዮችና ገራፊዎች እየሸሹ ወደ ስደትና
ሞት በመሄዳቸው፤ 85% የሰልፉ ተካፋዮች አቅመ-ሄዋን ለመድረስ ብቅ ያሉ እምቡጥ ወጣት ሴቶች፤ መካከለኛ እና አዛውንት ሴቶች ነበሩ።
የሰልፈኛው ትዕይንት የጀመረው እንደተለመደው ብዙዎቹ የአምባገነኖች
ሰርዓት እንደሚያደርጉት፤ ይህ ትዕይንትም ለአምባገነኑ ኢሳያስ በሚሰግዱ ጋዜጠኞች ፕሮፐጋንዳ መግቢያ ነበር የተከፈተው። እንዲህ
በሚል፦
“የቅኝ ገዢዎችን በማስወገድ በዚህ ታሪካዊ በዓላችን ኤርትራ በህይወትዋ አይታው
የማታውቀው የሰላም፤ የደስታና የብልጽግና አየር እያስተነፈሰች ባለችበት ወቅት መከበሩ ልዩ በዓል ያደርገዋል!” በሚል ገና በወጣትነቱ
ዕድሜ ሽበት በወረረው ወጣት ጋዜጠኛ ፕሮፓጋንዳ አስተናጋጅነት ነበር የጀመረው።
ቀጥሎ፤ሞጀሌ ያሸፈፈው እግር የሚመስል የ “ቻርሊ ቻፕሊን”
ሸፋፋዊ የእግር አረማመድ በሚራመድ የሙዚቃ ባንድ መሪና ድንክየዎች የሚመስሉ ካለልካቸው የተሰፋ ቀይና ጥቁር ወታደራዊ ደምብልብስ
የለበሱ የሙዚቃ ባንድ ሰልፈኞች፤ ‘ኮምቢሽታቶ’ ብሎ ጣሊያን በሰየመው
ጎዳና እየተመሙ ትዕይነቱን ለማድመቅ ወታደራዊ ማርሽ ያስሰማሉ።
ትዕይንቱ የተከናወነው በማታ ሲሆን፤ ጎዳናዉ በኮርያዎች ተሳታፊነት
የተቀረጹ ‘ቦግ-ጭልም’ በሚሉ መካከለኛ መብራቶችና ቅርጾች አሸብርቀውታል። አሳዛኙ ግን በዓሉ እንዳለቀ ለኗሪዎች ተለቅቆ የነበረው
አስጎምጂው የኤሌክትሪክ የቤት መብራት ፤ ለእራት የጣዱትን ድስት ሳይበስል ‘እንዲጠፋ’ ተደርጎ፤ እንደተለመደው ወደ ‘ፈረቃው’
የጭለማ ህይወት እንዲደናበሩ ተደርጓል ።
ይቀጥልና፤ አሁንም ከሙዚቃው ባንዱ የከፋ እየተወላገዱ ለመውደቅ
የሚዳዳቸው ከቅርጽ ውጭ የሆኑ ሽማግሌ ባለስልጣኖች ‘የክብር ሪባን በመመቀስ የካርኒቫሉን በዓል መርቀው ሲከፍቱ ያሳያል።
በጎዳናው ግራና ቀኝ በዓሉን ለማክበር ተገደውም ፈርተውም ወድደውም
ሆነ ለጉብኝት ከውጭ አገር የሄዱ ተመልካቾች፤ ይታያሉ። ቅጠላ ቅጠል እንዲሁም በፕላስቲክ የተሰራ ‘የሟሽላና ስንዴ’ እሸት’ ቅርጽ
እያውለበለቡ፤በሴቶች ብዛት የታጀበው ሰልፈኛ፤ በአጉል ጉራና ውሸት በተሞላ በተለቀቀላቸው አስጨፋሪ ሙዚቃ እየጨፈሩ፤እየዘለሉ፤ ያልፋሉ።
እንዲህ፤ እንዲህ.. እያለ አንባቢዎቼ በዓይናችሁ ለማየት የማትሹትን
የሚያስቆጣ እንደ ካሁን በፊቱ በሳባ መሰብሰቢያ ‘ስታድዮም’ በተከበረው
በዓላቸው በ2004 (ካልተሳሳትኩ)
የኢትዮጵያን ሰንደቃላማ ኢሳያስ ቆሞ እያየ አንዲቦጫጨቅ እና አንዲረገጥ
እንደተደረገው ሁሉ፤ ዛሬም ‘የሙሶሎኒ ልጆች’ ያንኑ ያደጉበትን ጋጠወጥ ባሕሪያቸውን በመድገም የኢትዮጵያን ሕዝብ ምልክት የሆነው
አርማችንን ቦጫጭቆ በመጣል፤ በሰልፈኞች ጫማ እተረገጠና በታዳጊ ወጣቶች
መጫማያ እየተቀላ ሲጨፍሩና ሲተፉበት ወደ እሚያሳየው የዱርየዎች ግብረ ትዕይንት ትደርሳላችሁ።ይህንን ለማየት 2017 Eritrean Independence Carnival Show ምርኢት ካርኒቫል (May 22, 2017)
በዩቱብ የተለጠፈውን ከ49 እስከ
55 የተለጠፈው You Tube ርዝመት ስትደርሱ ታዩታላችሁ። ኢሳያስ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ያለው ጥልቅ ጥላቻ ያን ያህል እንደሆነ የገለጸበትን ማስረጃ በቀላሉ ማየት
ያስችላችኋል። ኢሳያስ የኢትዮጵያ ወዳጅ
እያሉ እነ ካሳ ከበደ፤ ዳዊት ወ/ጊዮርጊስ፤ብርሃኑ ነጋ አንዳርጋቸው ጽጌ፤ንአምን ዘለቀ፤ ሲሳይ አገና እና የተቀሩት “አስመራ
ደርሶ መልስ” ብየ የምጠራቸው (የኢሳት ጋዜጠኞች) ወዘተ ወዘተ….የሰበኩዋችሁን ውሸት ዛሬ ይኼውና እንድታዩት ማስረጃውን
አቅርቤላችኋለሁ።
ይህ ሁሉ አስገራሚ ወንጀልና የ104 ሚሊዮን ሕዝብ ጥላቻ በሕዝብ
ላይ እንዲሰፍን ሕዝብ ለሕዝብ እንዲጣላ ትዕዛዝ የሰጠው ኢሳያስ እና አሽከሮቹ ‘ይህ አስነዋሪ ድርጊት’ ጥላቻን ከማስፋፋት
በቀር፤ ምን ጥቅም ያመጣል ተብሎ ተደረገ? ብለው የኢሳያስ አድናቂዎችና ወዳጆች ከሚባሉት የግንቦት 7 ጋዜጠኞች እንደማይጠይቁ እናውቃለን።
እንዴት ተደርጎ!? ያውም እነ ሲሳይ አገና? ታስታውሳላችሁ ሲሳይ አገና፤ የማነ ገብረአብ የተባለ የሻዕቢያው ቁንጮ ኢሳት ላይ
ጋብዞ ቃለ መጠይቅ ሲያደርግለት? የቃለ መጠይቁ ጠቀሜታ ‘ኤርትራኖች ኢሳያስን ወደ አለም ፍርድቤት ለማቅረብና እንዲሁም በኤርትራ
ማዕቀብ ለመጣል ጀኔቫ ላይ ክስ ሲመሰርቱ” እነ ንአመን ዘለቀ ለኢሳያስ ጥብቅና በመቆም ‘ለኢሳያስ ድጋፍ ሲሉ በመላ ዓለም
ከሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ፌርማ ሲያሰባስቡና እንዲሁም የግንቦት 7 ደጋፊዎች ከሻዕቢያ ደጋፊዎች ጋር ሰልፍ በመውጣት ወራዳ
ትዕይነታቸውን ታስታወሳለችሁ? ያንን በፎቶ አስደግፌ ከዚህ በታች እንድታስታውሱ
ት አቀርባለሁ። ያንን ፕሮፓጋንዳ ለመስራት ሲሳይ አገና የማነን ለቃለ
መጠይቅ ሲጋብዘው፤አስቀድሜ እንደገለጽኩት የቃለ መጠይቁ ዋና ዓለማ ኢትዮጵያዊያኖች
ስለ ሻዕቢያ ያለንን አመለካከት ለመቀየርና ፌርማ ለማሰባሰብ የተሞከረው ሙከራ ድጋፍ ለማግኘት እንደነበር
ታስታውሳላችሁ (የደሞዝ ከፋዩን ብድር ለመመለስ ማለት ነው)፤ የማነ ገብረአብ፤”ኤርትራ ስደተኞች የሚባሉት አብዛኛዎቹ ‘ኢትዮጵያዊያን’ ናቸው ብሎ ሲዋሽ፤ ሲሳይ አገና ይህ ውሸት ሳይጋፈጠው‘’ሆን ብሎ” እያወቀ እንዲለቀቅ ማድረጉን ታስታውሳላችሁ። እንዲያ ባለ በአድርባይ ባሕሪ የተሞሉ የግንቦት7/አሲት-ጋዜጠኞች
ስለ ሰንደቃላማችን መረገጥ አለቃቸውን “ለምን” ብለው የሚጠይቁበት ሃሞት ይኖራቸዋል ብለን ቅዠት ውስጥ መግባት በራስ ላይ
መቃዠት ነው።
ያም ሆነ ይህ ኢሳያስ የወላጆቹና የአጎቶቹ የነ ደጃዝማች ሰለሞን
አብርሃም ሰንደቃላማ ተቀዳድዳ ምንም በማያውቁ ታዳጊ ህጻናት መጫሚያ መሬት ተወርውራ አፈር ጋር እንደትረገጥ ትዕዛዝ ማስተላለፉ
የመጀመሪያው ሳይሆን ጋጠወጥነቱን በይፋ በዓለም ፊት ሲፈጽመው ዛሬ
ሁለተኛው ጊዜ ነው። ሆን ተብሎ ይህ 104 ሚሊዮን ሕዝብ አርማ በተደጋጋሚ ሲረገጥ እያዩ ‘አይተው እንዳላዩ’ መስለው “ኤርትራና
የኢትዮጵያ አምባሳደሮች ነን” የሚሉን የግንቦት 7 ባንዳ መሪዎች የሕሊና ሓኪም እንዲያዩ እንመክራለን። በኛ በኩል መጪው ትውልድም
ይሁን አሁን ያለው በቁጭት እንቅልፍ ያጣው የትም ይኑር የትም የተበታተነውም የተደራጀውም የድሮም ያሁኑም የኢትዮጵያ
ወጣትም ሆነ ነባር ወታደርና ስቪል ወጣት ዜጋ በጋራ ብድር ሳይመልስ ‘ፍቅርና ሰላም” ይወርዳል ማለት ዘበት ነው። የጊዜ ጉዳይ
ነው! ኡፎይ እንላለን ተብሎ ሲጨፈርለት የነበረው የባንዳዎቹ ነጻነት፤ ወደ ቀውስና ሲኦላዊ ህይወት ተለውጦ በሚሊዮኖች ወደ
‘ኋላ ዙር” ሸሽተው ላለመመለስ ‘ምለው ተገዝተው’ ‘እርም!” ብለው ‘ሰደብዋት’ የሄዱት
አጓጉለኞች ነፃ በወጡ በሳልስቱ/በሦስተኛ ቀናቸው ወደ እመዬ ኢትዮጵያ ጉያ እየገቡ እያየን አይደለም እንዴ? የኤርትራ የዓሰብ ጉዳይ በተባበሩት መንግሥታት ያለቀለት የጸደቀ ጉዳይ
ነው፤ አይሆንም፤ ያለቀለት ነገር ነው፤ እያሉ እነ ዳዊት ወ/ጊዮርጊስና ግንቦት 7ቶች ወጣቱን ለማጃጃል እየሞከሩት ያለውን ባንዳዊ
የሕሊና አጠባ እንደሚሉት ‘ያለቀለት’ አይደለም።ያልተወራረደ ሂሳብ አለ፤ ይወራረዳል!
አማራው ሞቷል፤ አማራ የለም፤ ሲሉ የነበሩት፤ አማራ አይነሳም፤ አያደርገውም ሲሉን የነበሩት፤ አማራ አለ፤ ይነሳል፤
አልሞተም፤ ብለን ስንሞግታቸው፤ሲሳለቁብን እና ሲሰድቡን “አይደረግም”፤ “አልቆለታል” የተባለው፤ ይኼው አማራው በመብረቃዊ
ቅጽበት ተደራጅቶ ከጠላቶቹ ጋር ሲንተጋተግ እያየን አይደለም እንዴ?
የኤርትራም ጉዳይ አላለቀም፤ ይደረጋል ያልነውን ይደረጋል! የጊዜ ጉዳይ! ይህንን በምሳሌ እንድታነብቡ እጋብዛለሁ፤ የክራሚያና የሩስያ ጉዳይ ስለኢትዮጵያና ኤርትራ ያልተዘጋ አጀንዳ ምንን ያስተምረናል? (አክሊሉ ወንድአፈረው - የግል አስተያየት መስከረም 2, 2007 (ስፕተምበር 12 2014 )፡
(Ethiopian Semay)
ግንቦት 7ቶች ‘ወዳጃችን የኤርትራ መንግሥት” እያሉ የሚጠሩትን
ሰንደቃላማችንን ደጋግሞ በመርገጥ ‘የገዛ ሞቱን’ እየጠራ ያለው ጋጠወጡ ኢሳያስ (በቅርብ ይሰናበታል! ቃሌን በእርግጠኛነት ውሰዱት)
በውስጥ ሰላዮችና በውጭ ሰላዮች የሳተላይት ዕርዳታ፤ የስንቱን ደም ኢትዮጵያዊያን ጀግኖች ደም እንደጠጣ፤ ላስታውሳቸው እወዳለሁ።
አሁንም ኢትዮጵያዊያኖች ሰንደቃላማችን ተረግጦ እንደማንተኛለት ግንቦት 7ቶችና አለቅላቂዎች እንዲያውቁት መልእክት እያስተላለፍልን
እየጠየቅን፤ የጀግኖቻችን ደም በከንቱ ፈስሶ እንደማይቀር ጀግኖቻችን በአደራ ያስተጋቡትን ቃላቸው ዛሬም ሕያው ነውና ‘አለቅላቂዎች’
ከዚህ በታች ያለውን ቃል እንዲያነብቡ እያስታወስኩ በዚህ የጀግኖች
ታሪካዊ ግብግብና ልሳን ልሰናበታችሁ።
አይ ምጽዋ ከሚል በመቶአለቃ ታደሰ ቴሌ ደራሲነት ለታሪክ የተዘገበ መጽሐፍ (ገጽ
187 አስከ 198)
በዓይናቸው ያዩትና በግብር ጦርነቱን የተካፉሉበትን የምጽዋ
ጦርንት እንዲህ ያቀርቡታል።
“የካቲት 9 ቀን 1982 ዓ.ም ምፅዋ ከተማ ለተከማቸዉ አብዮታዊ ሠራዊትና አመራሩ ክፉ ቀን ነበረች። ሻዕቢያ ደግሞ እንደ ልደት ቀን ይቆጥረዋል። ምክንያቱም ለመጀመሪያ ጊዜ ምፅዋ ከተማን የረገጠዉ በዚች ዕለት ነዉና።
ሻዕቢያ በ1970 ዓ.ም ከጀብሃ ተዋጊዎች ጋር በመሆን አብዛኛዉን የኤርትራ ግዛት ተቆጣጥሮ ነበር። አሥመራ፤ባሬንቱ፤ምፅዋና ዓዲቀይህ ከተማ የነበሩትን የአብዮታዊ ሠራዊት አባላት ደምስሶ እነዚህን ከተሞች መቆጣጠር ግን አልቻለም። በመሆኑም የሃያ ስምነት ዓመታት ምኞቱን ሻዕቢያ በምፅዋ እዉን ያደረገበት ቀን የካቲት 9 ቀን 1982 ናት።
የ6ኛ ክፍለ ጦር አዛዥ ጀኔራል ተሾመ ተሰማ (ከርዕሴ ግርጌ የለጠፍኩት ፎቶአቸው) ካቲት 9 ቀን 1982 ዓ.ም ከጠዋቱ 1፡30 ሰዓት ላይ በምፅዋ ከተማ ‘ርዕሲ ምድሪ’ በተባለ አካባቢ በከባድ መሣሪያ በፈራረሱ ቤቶች ጥግ ሆነዉ የተወሰኑ የጦር መኮንኖችን እና ባለሌላ ማዕረግተኞችን ሰብስበዉ ንግግር አደረጉ። እንዲህም አሉ፤-
“ሻዕቢያ ያለ የሌለ ሃይሉን ተጠቅሞ በእጅ ቦምብና በክላሽን በአሁኑ ሰዓት የከተማ ዉስጥ ዉጊያ በማድረግ ላይ ነዉ። ሻዕቢያ ከባድ መሣሪያ ድብደባ አቁሞ በእግረኛ ብቻ ለመዋጋት አዲስ ተዋጊ ሃይሉን በመኪና እያመላለሰ ዕዳጋ ከተማ ላይ እያከማቸ ነዉ። በአዲስ ጉልበት ተዋግቶ ምጸፅዋን ለመያዝ ቆርጦ ስለመነሣቱ ጥርጥር የለዉም።… “እኔ የሚፈለግብኝን አደራ ተወጥቻለሁ። ከጥር 30ቀን 1982 እስከ ዛር የካቲት 9 ቀን 1982 ሞት ሽረት ትግል አድረጌአለሁ።የሻዕቢያን የጥፋት ዓለማ ለመግታት ያላደረግኩት ጥረት የለም። ከዚህ በኋላ ግን የራሴን ሕይወት በክብር ከማጥፋትና ለኢትዮጵያ ጀግኖችና ታሪክ ፀሐፊዎች ታላቅ ተምሳሌት ከመሆን ሌላ አማራጭ የለኝም። ጀግንነት ማለት በሁሉም መልክ ለጠላት አመች ሆኖ አለመገኘት ማለት ነዉ።…
“በዚች የኢትዮጵያ ሕዝብ የባሕር በርና ዓለም አቀፍ ወደብ በሆነችዉ በምፅዋ ከተማና በቀይ ባሕር ጠረፍ ላይ ቆሜ ሽጉጤን ለመጠጣት ዝግጁ ሆኜአለሁ። በ እዉነት እኔ ዛሬ በሞት ብሸነፍም በታሪክና በመጭዉ የኢትዮጵያ ትዉልድ ፊት አልሸነፍም። የአፄ ቴዎድሮስን ዕድል በማግኘቴም በጣም እኮራለሁ። እኔ አሁን የተዘጋጀሁለት ሞት ዘለዓለማዊ ክብርና ሕይወት ይሰጠናል። በሻዕቢያ እንደ እነ ጀኔራል ጥላሁን እና ጀኔራል ዓሊ ሓጂ ተማርኬ የሻዕቢያን መሪዎች ዓይን ማየት ግን የሞት ሞት ነዉ። አፄ ቴዎድሮስ በእንግሊዞች እጅ ወድቀዉ ከመዋረድ ሞትን መርጠዉ የራሳቸዉን ሕይወት መቀቅደላ ላይ አጠፉ። እኔ ደግሞ በተራየ ከኢትየጵያ ሕዝብ መንግሥት የተሰጠኝን የጄኔራልነት ማዕረግ ሳላስደፍር ለመንግሥትና ለሕዝብ በገባሁት ቃል ኪዳን መሰረት አስቀድሜ የፈቀደዉን ያህል ተዋግቼና አዋግቼ ሻዕቢያን አራግፌአለሁ። እንደ ጦር መሪም እንደ ተራ ተዋጊም ሁኜ ክላሽንኮቭ ጠመንጃ ይዤ ተፋልሜአለሁ። አሁን ግን ለመጨረሻዋ መስዋዕትነት ህይወቴን ለማጥፋት የቀሩኝ ጥቂት ደቂቃዎች ናቸዉ።… “ጎበዝ ስሙኝ! ይህ አደራ መልዕክቴ ነገ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ይደርስ ይሆናል። ምናልባት አምላክ ካለ ከእናንተ አንዱ መልዕክቴን ለኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት አደርስ ይሆናል። ዛሬ ሻዕቢያ ምፅዋን ተቆጣጥሬአለሁ በማለት የዓለምን መገናኛ ብዙሃን እንደሚያጨናንቅ ጥርጥር የለዉም። ይህ ደግሞ ለኢትዮጵያ ሀገርና ሕዝቧ ትልቅ አደጋ ነዉ። በቀይ ባሕር በራችን በኩል ብዙዉን ጊዜ ወረራ ፈጽመዉብን በተደጋጋሚ የሳፈርናቸዉና ፊት ለፊት ያልቻሉን ምዕራባዉያን ሀገሮችና ዓረቦች ዛሬ የሻዕቢያን ጊዜያዊ ድል ሰምተዉ ይፈነጥዛሉ። ምናልባትም የኢትዮጵያ የተፈጥሮ ድንበር የሆነዉንና ለዘመናት በአባቶቻችን የደም ዋጋ ፀንቶ የቆየን የባሕር በራችንን በመዝጋት እንዲሁም ቀይ ባሕር የኢትዮጵያ ባሕር አይደለም በማለት በምድር ተወስነን እንድንቀር ይደረግ ይሆናል። ይህ ደግሞ የሞት ሞት ነዉ። “ይሁን! ምንም ማድረግ አልችልንም። ሁሉም ነገር ከቁጥጥሬ ዉጭ ሆኗል። ከሙታን ዓለም መጥቼ ማረጋገጥ ባልችልም የፈለገ ጊዜ ይጠይቅ እንጂ ጀግናዉ የኢትዮጵያ ሕዝብ የባሕር በር አልባ ሆኖ ፤በኢምፔርያሊስቶችና ጋሻ ጃግሬዎቻቸዉ ተሸንፎና እጁን አጣጥፎ አይቀመጥም። ይህ ከሆነማ የአፄ ዮሐንስ የቀይ በሕር ተጋድሎ እና የጀግናዉ ራስ አሉላ አባነጋ አጥንት እንዲሁም የእኔን ጨምሮ የአበዮታዊ ሠራዊት አባላት አጥንትና ደም የኢትዮ ያን ትዉልድ ሁሉ እሰከዘላለሙ የፋረዳል። ኢትዮጵያ ሀገሬ የጀግኖች መፍለቅያና ገናና ታሪክ ያላት ሀገር ናት። በመሆኑም ጀግናዉ ሕዝቧ ሕዝባዊ የባሕር በሩ በሻዕቢያ ተይዞና የጠላቶቹ መፈንጫ ሆኖ አይኖርም። የፈለገ ጊዜ ይቆይ እንጂ ሻዕቢያ ምፅዋን እንደያዛት ለዘላለሙ አይኖርም”። ጊዜዉ ጠብቆ የኢትዮጵያ ጀግና ጠላትን ደምስሶ ምፅዋን ለኢትዮጵያ ሕዝብ እንደሚያስረክብ እምነቴ የፀና ነዉ።”
አሉና
ትንፋሽ ዋጡ:
የትንሽ ፋታ
ወሰዱ። የጀኔራል
ተሾመ ዓይን
የቆሰለ የነብር
ዓይን መስሏል፡
ከንፈራቸዉ በዉሃ
ጥም ደርቆ
ቅርፊት ይዟል።
ፊታቸዉ በደረቅ
ላብ ዥንጉርጉር
ሆኗል። ሆዳቸዉ
ከወገባቸዉ ተጣብቋል።
በተሰበሰበዉ አባል
ዉስጥ በሰፈነዉ
ጸጥታና ዝምታ
መሃል “እናንተ አብየታዊ መኮንኖች ባለሌላ ማዕረጎች! ስሙኝ፤ አንድ ምሳሌ ልንገራችሁ።” አሉ
ጀኔራል ተሾመ
ቆጣ ብለዉ።“አንድ ሰዉ ቤት ሲሰራ የሚሠራዉ ቤት በርና መስኮቶች አሉት። አንድ ሰዉ ደግሞ ሞተ እንበል። መቃብር በርና መስኮት የለዉም። በርና መስኮት የሕይወት ምልክቶች ናቸዉ። በመሆኑም ያለሀገር ነፃነትና ያለባሕር በር ብልጽግና ስለሌለ የኢትዮጵያ ሕዝብ የባሕር በር ተነጥቆ የሚኖር ሕዝብ አይደለም። ከሻዕቢያ ጀርባ ሆነዉ ቀይ በሕር የኢትዮጵያ አይደለም የሚሉ ሀገሮችና ጋሻ ጃግሬዎቻቸዉ ሁሉ በቀጥታም ሆኑ በተዘዋዋሪ ፍላጎታቸዉ የኢትዮጵያ ሞት ነዉ።
“ይህ ምሳሌ ከገባችሁ የባሕር በር የሌላት ሀገር ሞቶ ከተቀበረ ግለሰብ የምትለየዉ በትንሹ ነዉ። ምክንያቱም የባሕር ሀብት ከማጣቷ በላይ ምርቷን ወደ ዉጭ ለመላክ የግዴታ ወደብ ስለምትከራይ ለወደብ ክፍያ የምትከፍለዉ የገንዘብ ዉጭ ዜጎቿን ያደኸያል። በአኳያዉ ጠላቶቿን ባለወደቦቹን ያበለጽጋል። ይህ ዕድል ለኢትዮጵያ እንዳይደርሳት ቀይ ባሕር የኢትየጵያ ትዉልድ ይፋረድ።፡ቀይ ባሕር ለእኔ ዘላለማዊ ቤቴ እንዲሆን ወስኛለሁ። ደስተኛ እና ዕድለኛ ጀኔራል ነኝ። እኔ ብሞት ታሪኬ አይሞትም። የእኔ ታሪክ በእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ሕሊና ዉስጥ እንደሚኖር አምናለሁ። ቻዉ!
ቻዉ!ቻዉ!” አሉና ጀኔራል ተሾመ ፤መኮንኖቹን ከሰበሰቡበት ቦታ ተፈናጥረዉ ወደ ቀይ ባሕር ጠረፍ አመሩ። የባሕሩ፡ጠረፍ ከስብሰባዉ ቦታ በግምት ከስልሳ ሜትር አይበልጥም። በፍጥነት ወደዚህ በሕር ጠረፍ ገሰገሱ። ክላሺንኮቭ ጠመንጃዉን አቀባብለዉና አዉቶማቲክ ላይ አድርገዉ በቀኝ እጃቸዉ ጨብጠዋል፡ከምፅዋ ወደብ በስተቀኝ ከሚገኘዉ ወታደራዊ ወደብና መደብር ላይ ሲደርሱም ለቀይ ባሕር ዉሃ መገደቢያ በተሰራ ግንብ ጠርዝ ላይ ጀርባቸዉን ወደ ቀይ ባሕር ፊታቸዉን ወደ ምፅዋ ከተማ አድርገዉ ቆሙ። ቀጥሎ በእጃቸዉ የነበረውን ክላሺንኮቭ ጠመንጃ ወደ ቀይ ባሕር ወረወሩት። ከዚያም በወገባቸዉ ታጥቀዉት የነበረውን ኮልት ሽጉጥ አወጡና የሽጉጡን አፈሙዝ በአፋቸዉ ጎርሰው የካቲት 9 ቀን 1982 ዓ.ም ከጥወቱ 2፡10 ሰዓት ሲሆን ቃታዉን ሳቡት። የሽጉጥ ቶክስ ድምፅ እንደተሰማ ወደ ጀርባቸዉ በቀይባሕር ዉሃ ላይ ወድቀዉ ሰጠሙ። ከጭንቅላታቸዉ የሚፈስ ደም በቀይ ባሕር ዉሃ ላይ ቀልቶ ይታይ ነበር።
ወዲያዉም ይህን የጀኔራል ተሾመ ሞት በምስክርነት ቆመዉ ከአዩት መካከል ከ150 የማያንሱ የጦር መኮንኖች ባለሌላ ማዕርጎች በሽጉጥ፤ በእጅ ቦምብና በክላሽ ጠመንጃ ሕይወታቸዉን አጠፉ። ከእነዚህም መካከል ሻለቃ ሮሪሣ ዳዲ በእጅ ቦምብ፤ሻምበል ሸዋንታዮ ዓለሙ በማካሮቭ ሽጉጥ፤ሻምበል አዲሱ በማካሮቭ ሽጉጥ፤ሻምበል ባሻ አማረ ናጂ በክላሽ፤ሻምበል ወንድወሰን በሽጉጥ የሃምሳ አለቃ ፈቃዱ ቦጋለ በክላሽ፤ወታደር ሽንገረፋ በክላሽ ሕይወታቸዉን አጠፉና በስም የሚታወሱ ናቸዉ። ሌሎችም በብዛት ራሳቸዉን ገድለዋል። በአጭር ደቂቃ ዉስጥ አካባቢዉ ሬሳ በሬሳ ሆነ።”…
ካሉ በኋላ ኮለኔል በላይ አስጨናቂ ስለተባሉ ሌላ ጀግና
ወታደርና የቀኑን እጅ ለእጅ አስጨናቂና አኩሪ የገድሎ መሞት ውግያን በሚመለከት ደራሲው በሰፊው ይተነተኑታል። “ኮሎኔል በላይ አስጨናቂ የኢትዮጵያን ሰንደቃላማ ለብሰዉ ከቀይ ባሕር ሆቴል በረንዳ ላይ በአንዲት ጥልፍልፍ የቃጫ ወንብረ ላይ ተቀምጠዉ አጠገባቸዉ ለነበሩት ጥቂት አባላት መልዕክት ያስተላልፋሉ። “ጀግና ቢሞት በእልፍ እአላፍ ጀግና ይተካል።የእኔ ታሪክ ለትዉልድ ይቀራል። ታሪክ ይናገራል እንጂ እኔ አልናገርም።” የምትል መልዕክት እያስተላለፉ …..ራሰቸውን መስዋዕት አደረጉ። “ኮሎኔል በላይ አስጨናቂ ክላሽንኮቭ ጠመንጃቸዉ እንደያዙ ወንበር ተደግፈዉ ተዝለፍልፈዋል። የለበሱት የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ባንዴራ በላያቸዉ ላይ ደምቆ ይታያል።ይህነን ትዕይንት ሻዕቢያ በፎቶግራፍ አንስቶታል። በቪዲዮ ካሜራም ቀርጾታል፡ የወታደዊ ሸሚዝና ሱሪያቸዉን ኪስ ሻዕቢያ ሲበረብርም ከንጽህና ወረቀት በስተቀር ምንም አላገኘም። አንድ የሻዕብያ ተዋጊ ኮሎኔል በላይ አስጨናቂ ለብሰዉ የተሰዉትን የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ባንዴራ ካላያቸዉ ላይ ገፈፈና ክብሪት ጭሮ አቃጠለዉ። የኮሎኔሉ አስከሬን ከወንበሩ ላይ ገፍትሮ በመጣልም በደም የተጨማለቀዉን ወንበር በአንድ እጁ ወደ ላይ አነሳዉ። ይህ ድርጊት ጋብ ያለዉን ተኩስ በመጠኑ ቀሰቀሰዉ። ከአንድ አቅጣጫ የተተኮሰች ጥይት ያን የሻዕቢያ አባል ከወንበሩ ጣለችዉ።ከዚያ መሬት ቀውጥ ሆና የጨበጣ ውግያው
እንደገና ተፋፋመ፤….”
በማለት የጀግንነት ገድላችንን ሲያስታውሱን ለጠላት
ያደሩ መረጃ ሲያቀብሉ የነበሩ ከፍተኛ የሰራዊቱ ቁንጮ አዛዦች የነበሩ ሰላዮችም አብረው ለምጽዋ መውደቅ የተጫወቱት ሚና
በመጽሐፉ በሰፊው ይገልጻሉ።
ያልተወራረደ የወላጆቻችን ደም ሂሳብ አለ፤ እሱን እናወራርዳለን።ለጊዜው
ኤርትራ ግድያ፤ ዘር ማጥፋት፤ ሕዝብን ወደ ባርነት መለወጥ፤ ጥቁር ገባያ፤ ሌብነት፤ ስም ማጥፋት፤ ውሸት፤ ጉራ፤ ወንጀል፤ጦርነት፤ሽብር፤ስደትና ዕብደት፤ ሁሉንም ሞክራዋለች። ከዚህ ወዲያ የሚቀራት መደምደሚያዋ ወደ አመድነት መጓዝ ነው።ከዚያ ጣረ ሞት መዳን ከፈለገች “የቀራት አማራጭ” ኢትዮጵያዊነትዋን “በቁርባን” ተቀብላ ከዘላለማዊው ቅዠት (ደሉዥን) እና ሞት መዳን ነው። አመሰግናለሁ፤
ጌታቸው ረዳ የኢትዮ-
ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ) getachre@aol.com
(Ethiopian Semay)
No comments:
Post a Comment