ክፉ ዓይን አየን!“ክፉእ ርኢና!”
ጌታቸው ረዳ (www.ethiopiansemay.blogspot.com)
አሜሪካ ውስጥ “ካምፕ ዴቪድ በተባለው የተከበረ የመሰብሰቢያ አዳራሽ”
ባለፈው ሰሞን “ቡድን 8” ተብሎ የሚጠራው የሞገደኛ አገሮች የምጣኔ ሃብት ጉዳይ ውይይት ስብሰባ ውስጥ “ለማጣፈጫ” ተብለው
ከተጋበዙ ጥቂት ኮስማና የአፍሪካ አገሮች መካካል አንደኛዋ ኢትዮጵያ ስትሆን በወያኔው መሪ “መለስ ዜናዊ” ተወክላ ነበር።
ታዲያ በዛው አዳራሽ ውስጥ የመለስ ዜናዊ “የሕሊና ሱሪ እና ውስጣዊ ጤንነቱን” የሚፈታተን በዚህ መጣ ያልተባለ ማንም
ያልጠበቀው ድንገተኛና መብረቃዊ የተቃውሞ ድምፅ ሲስተጋባ “ፓኒክ አታክ” ተብሎ በሕሊና ሓኪም ተመራማሪ ሊቃውንቶች የሚጠራው
የፍርሃት ሰመመን መለስ ዜናዊ አጥንት ውስጥ ገብቶ ለአንድ አፍታ ያክል ሕሊናው በመሳቱ፤ “አንገቱ ወደ መሬት ደፍቶ፤ዓይኑን
በእንቅልፍ ሰመመን በግድ ሲከፍትና ሲዘጋ፤ አገጩም ደረቱ ላይ ተጣብቆ” ክፉ ዓይናችን ያየንበት (ኩፉእ ርኢና/ የትግርኛ
አባባል)፤ ጋዜጠኞች የቀረጹት ዜና በአብዛኛዎቹ የተቃዋሚ ድረገጾች ተለጥፎ እንዳያችሁት አምናለሁ።
በዚህ ትንታኔ የበኩሌን አንድ ለማለት እፈልጋለሁ። በስብሰባው አዳራሽ
ተገኝቶ መብረቃዊ የተቃውሞ ድምፅ በማስተጋባት የመለስ ዜናዊን ማንነት እና “ቦቅባቃ ሕሊና” ሙሉ በሙሉ እንድንመለከተው
ያደረገው ጀግና የኢሳቱ አበበ ገላው አመሰግነዋለሁ። በኔ እና በአበበ ገላው መካከል ሸካራ ንትርክ አድርገን እንደነበር በዚህ
በራሴው ድረገጽ ገልጬላችሁ እንደነበር የሚታወስ ነው። በኔና በእርሱ መካካል የግል ጠብ ሳይሆን የፖለቲካ ንትርክ ነው፡
ስለሆነም እኔ የምፈልገውን ዓላማ ዛሬ በመፈጸሙ እና እንደ እኔ ሆኖ፤እኔን ወክሎ ጩሆቴን በማስተገባቱ አስደስቶኛል እና
“እንኳን ደስ ያለህ” ብየው በዚህ ተነጋግረን ተስማምተናል። ለወደፊቱ ባንሰማማም የሚያስገርም አይሆንም። እኔ በጎ ምግባር
ስሰራ ወይንም እሱ ሲሰራ አንደገና “በርታ”፤“በርታ” መባባላችን አይቀርም እና አንባቢዎቼ በዚህ አንድትመለከቱልኝ አሳስባለሁ።
መለስ ዜናዊ ሲደነግጥ “ክፉ ዓይን” ያየንበት ትዕይንት የናንተን አላውቅም
እንጂ ለኔ የመጀመሪያ ጊዜ ነው። ተፈጥሮ ነውና እንስሳም ሆነ ሰው በተለያ ሁኔታዎች እና ምክንያቶች ይደነግጣል። ነገር ግን
የአንድ አገር መሪ ያውም፤ “እንኳን ሰው፤ ፈጣሪን የማይፈሩ” (በእሳትና በፈላ ውሃ የተሰቃዩት የወያኔ ሰለባ አቶ ገዛኢ
ረዳ ፤ ምንጭ ይድረስ ለጎጠኛው መምህር፤ ደራሲ ጌታቸው ረዳ) የተባለላቸው “ወያኔዎችን” በመሪነት እስካሁን ድረስ
የሚገኘው መለስ ዜናዊ እንዲህ “እስኪበላሽ” ድረስ እናያለን ብየ ገምቼው አላውቅም ነበር። እርግጥ ገብረመድህን አርአያ በኢሳት
ቃለ መጠይቁ ውስጥ“መለስ ዜናዊ እኮ “ድንጉጥ፤ቦጅቧጃ ፤ፈሪ እኮ ነው!!!” ሲል ሰምቼዋለሁ። የዓድዋ ባንክ ለመዝረፍ
አስተባባሪ ሆኖ ሲገባም፤ ባጋጠመው የተኩስ መልስ “ደንግጦ፡ ከቦታው መብረሩ ተደጋግሞ እንደተነገረ ይታወቃል። ሆኖም በምያሳዝን
መልኩ አንገቱ ቆልምሞ፤ አገጩ ወድቆ ልሃጩ ለማዝረክረክ የተቃረበ የመሪ ድንጋጤ ሰምቼም አይቼም አላውቅም።
እርግጥ አበበ ገላው የሚመሰገን ጀግንነት መስራቱ እርግጥ ነው፡ ማንም
ጋዜጠኛ ተቃዋሚም (ቆራጥ ከከሆነ ማለቴ ነው)የአበበን እድል ቢያገኝ እንደዚሁ እንደሚያደርግ አልጠራጠርም። ሆኖም አበበን
ያገዙት ክስተቶች ስትመለከቱት፤ የድምጹ አስደንጋጭነት እና እጥር ምጥን ያሉ ነጥቦቹን ስታጤኑት፤በተለይ የድምፁን
መብረቅነት፤ከዚህ መጣ ያልተባለ “የድምፅ ማጉያ” እገዛን ስትታዘቡ መለስ ዜናዊን የሚያክል ትምክህተኛ እንዲሸማቀቅ ያገዘን
“የኢትዮጵያ አምላክ”መሆኑን እወቁ። የአምላክ ስራ እና ጥበብ ብዙ መንገዶች አሉት።
ብዙ የፈረንጅ ሊቃውንት እንደሚሉት ከማንኛውም ሃይል ማለትም
ከእሳት፤ከጐርፍ፤ከመሬት መንቀጥቀጥ ከኑክሌር ጥፋት የበለጠ ሕሊናን የሚገድል “ፍርሓት” የሚባል የሕሊና ሃሳብ ነው
ይላሉ።ፍርሓት ሕሊናን የሚገድል ሞገድ ነው ማለት ነው።
መለስ ዜናዊ የሰራቸው ሃጢያቶች በርካታ ናቸው፡፡ ከሰው ልጅ ሕይወት በመርዝ
ከማስገደል ጀምሮ የቤተሰብ መበታተን፤የዘር ማጥፋት ወንጀል እና በአገር ክሕደት ወንጀል…ተጠያቂ ነው። የወንጀሉ ብርታት እና
በርካታነት ስለሚያውቅም “በነብሰ ገዳይ” ጠባቂዎቹ ተከብቦ ይንቀሳቀሳል። የህ ትርኢት ለተመልካቹ ሕዝብ ብቻ ሳይሆን በውስጡ
ለራሱም ፍርሓት ውስጥ ከትቶታል። አጀቡ የሚያመለክተው ነገር ቢኖር “ሁሌም አደጋ እንደከበበው” የሚነግረው ምልከት ነውና
ሰሞኑን የተከሰተው የመለስ /ፓኒክ አታክ/ “ድንገተኛ ድንጋጤ”/ ከዚያ የመነጨ የሕሊና አለመረጋጋት ነው። ባጭሩ የትግርኛው
ቃል “አለና!!!” (አለን) የሚለው የተቃዋሚዎች ድምፅ በመለስ ዜናዊ ሕሊና ውስጥ ተወሽቆ እረፍት እንደነሳው “ዓይነተኛ”
ጠቋሚ “ቴርሞ ሜተር/መለኪያ” ነው።
በሰው ልጆች ነብስ እና ደም የተጨማለቀው መለስ ዜናዊ ሰው መስሎ ለመታየት
ውድ ሱፍና ክራባት ለብሶ እሱን በመሰሉ በቁመናቸው የሞቱት እነ ብርሃነ ገብረክርስቶስን የመሰሉ የግል አሽከሮቹን አስከትሎ
አዳራሽ ውስጥ ተኰፍሶ እንደሰው ለመታየት የተቻለው ያህል ቢጥር እና “ድምጻችን በልቶ የከዳን ኦባማ” የመሳሰሉት ምዕራባዊያን
ጌቶቹ ከልክ ያለፈ እንክብካቤ በማድረግ ወንጀሉን ለመሸፈን ቢጥሩለትም፤መለስ ዜናዊ በፍርሃት እና በድፍረት መካካል የተቀረቀረ
ሰው ስለሆነ ድንገት የተከሰተበት የተቃውሞ ነጐድጓዳዊ ድምፅ“ፓኒክ አታኩን” ሊቋቋመው አልቻለም። ለዚህም ነው በትግርኛ ምሳሌ “ፈራሕ
አይሞተ፤ ተባዕ ኣይሞተ፤ ላንግላንጋ ሞተ” የተባለው። ትርጉሙም“ፈሪ አልሞተም፤ደፋርም አልሞተም፡ የሞተው በደፍርት እና
በፍርሓት መካከል የቆመው ተጠራጣሪው ነው።” የሚባለው።መለስ ሁሌም በጥርጣሬ ዓለም የተከበበ ሕይወት ውስጥ ነው ያለውና በድንጋጤ
የተወረረ ሕሊና አለው።
የሰው ልጅ ቀርቶ የነፋስ እንቅስቃሴ ሳይቀር በሰለጠኑ ተኳሾች እና ዘመናዊ
ካሜራዎች ቁጥጥር የሚገኝ ፀጥተኛ አዳራሽ ውስጥ በደረሰበት ድንገተኛ አስደንባሪ ድምፅ ማማን ስላልቻለ “ደፋር ለመምሰል”
ቢሞልርም፤ እንደ ወፍ ደንብሮ ከቅርጸ አከላቱ ተለይቶ የነሳው ትከሻው ለመቆጣጠር ሲል ሳያስበው ዓይኑን “አፍጦ ቀረ”፤
በድንጋጤ የፈጠጠው አይኑን መቆጣጠር ስላልቻለ፤ ከአበበ ገላው በተቃራ እቅጣጫ አንገቱን ወደ ቀኝ በኩል ከሕዝብ እይታ ለማሸሽ
ሲሞክር በድፍረት እና በፍርሃት መካካል ስለተጐተተ ሳያስበው “በፓኒክ አታክ” ተሸንፎ ወደ መሃል እይታ ገብቶ አንገቱን ቆልምሞ
ደፍቶ አይኑን መቆጣጠር አቅቶት “ለአጭር ጊዜም ቢሆን “ጊዜያዊ ሞት” ሞተ”። መሞቱን እኛም ሆነን እሱ ያወቀው ጸሓይ እየሞቀች
ከሕልሟ እንደባነነች እንደ የቀን “ደሮ” ሲባንን ነው። ፈረንጆች “ኒር ዴዝ - ኤክስፐርያንስ” ይሉታል።
ለዚህም ነው ሊቃውንት ከጎርፍና ከመሬት አንቀጥቅጥ ይልቅ ፍርሓት የሚባል
ሞገድ የሰው ልጆች ስብእናን በመጋራት ማንንትን ይነጥቃል የሚሉት። አበበ ገላው መለስ ዜናዊን ያለ ጥይት የገደለበት “ዓይናችን
ክፉ ዓይን ያየበት” የሰለጠነ የጦርነት መድረክ ነበር ብል የተሻለ ነው። መለስ ዜናዊ “የሰለጠ ፓለቲካ” አውርድልኝ እያለ ውሸቱን-ሲወተውተን
የሰለጠነውን ፖለቲካ እንደሚቋቋመው መሪ “የሰለጠነ ፖለቲካ” ሲገጥመው ወደ “ፎሲል”ነት ተቀየረ። ወደ ማይናገር ግዑዝ ተቀየረ።
ተንቀሳቃሽ ነገር ሙት ሆኖ ወደ ግዕዙነት ለመቀየር፤መጀመሪያ
ሞመት አለበት። ፈረንጆች እንደሚሉት “For something to become a fossil it has to die under very
special circumstances” ይላሉ። መለስ ዜናዊ የሞተው “ስፔሺያል ሰርካምስታንስ ውስጥ ነበር። መለስ ዜናዊ ሲሞት አንደ “የጓሮ
አትክልት እባብ” ወይንም አይጥ እንደሚመስለው “ኦፖስመሰ” የመሳሰሉ ነብሳት ጥቃት ሲወረወርባቸው መቋቋም ሲያቅታቸውና ሲሸነፉ
እንደሞቱ መስለው በማወቅ ይሞታሉ። መለስ ዜናዊ ግን የሞተው “ እንደ እንሰሳዎቹ” ወደ ሞት ጨዋታው የገባው ካልኪዩሌትድ ዴዝ
(አስቦበት) ሳይሆን የሞተው “ባልጠበቀው ሰርካምስታንስ” ስለነበረ ሕሊናው “በፍርሓት ጐርፍ ስለተጥለቀለቀ” የሚያስብበት ጊዜ
ስላልነበረው “ሕሊናው ታጠፈ” (ኮላፕስ) አደረገ፡፤ ሞተ!
እውነት ለመናገር ጠላት እንዲህ ሲሰቃይ
ማንኛችንም ብንሆን አንወድም (ስለ ራሴ ልናገር)። ምክንያቱም መለስ የተሰቃየው የመንፈስ ስቃይ (ቶርመንት ኤንድ ፐይን)
ከአካል ስቃይ የባሰ ስለሆነ፤ በዛች እለት ለመለስ ዜናዊ እና ተከታዮቹ “የገሃነም ያከል አሰቃቂ ትዕይንት” ነበር። መለስ
ዜናዊ ከፎሲልነት/ከቅሬት ወደ ዳግም ትንሳኤ ለመመለስ ከእዛ ስብራት ለማጋገም የሚወስድበት ጊዜ አምላክ እንጂ ሰው አያውቀውም።
የጠባቂዎች፤ካድሬዎቹ፤ አሽከሮቹ፤ሱፍ መልበሱ እና አጀቡ እንደ“ቅብ”/ ሜክ አፕ/ ሆነው የሕሊና ስብራቱን ለማሳመር ይጥሩ
ይሆናል፤ ነገር ግን የመለስ የሕሊና ስብራት ምስጢራዊ ሕክምና ካላደረገ በቀር “ከሞት ያመለጠ”
miraculous escapee ስለሆነ “በፍላሽ ባክ”/ የድህረ አደጋ የትውስታ ስቃይ” መንገላታቱ አይቀርም።
ይህ አባባል ሕክምና ለማያውቁ ሰዎች
እየቀልድኩበት እያለሁ የሚመስላቸው ሰዎች ሊኖሩ ይችላሉ።ላጭር ጊዜ በሞተባት “ኒርሊ ዴዝ ኤክስፔርያነስ” ውስጥ የለያዩ ጥቁር
ልብስ፤ነጭ ልብስ የለበሱ ቀንድ ያበቀሉ ፤ያገጠጠጡ አስፈሪ ነብሳት በብዥታ እየታዩት “ወደ መንበሪያህ ወደ “ገሃነመ እሳተ ሰማይ”
እንውስድህ ብለው” ሲጐትቱት፤ እሱም “እባካችሁ ለዛሬ ማሩኝ” እያለ እየተንገታገተ ሲለምናቸው ታይተውት እንደነበር የታወቀ
ነው። ኒር ዴዝ ኤክስፐርያንስ ውስጥ ያለፉ ሰዎች የሚነግሩን ይህንኑ ነው። አገጩና ሎምቦጩ ክራባታው ድረስ ተለጥጥጦ ሰመመን ውስጥ ሲጋባ ማየት “ክፉእ ርኢና”ያልኩበት-ምክንያትም-ይሄው-ነው።
መለስ ሃይማኖት ስለሌለው እንጂ “አበ ነብስ” ቢኖረው “ያየወን ሁሉ” ይናዘዝ ነበር። በዛውም “ጠበል ተረጭቶለት፤ጸሎት ተደግሞለት ይቀለው ነበር። አለመታደል ግን “አበ ነብስ” ስለሌለው “ኒርሊ ዴዝ አክስፐርያንሱ” በውስጡ አጭቆ ሲይዘው “ፍላሽ ባኩ” (ድህረ ስቃይ ትውስታው) ሕሊናውን እረፍት ይነሳዋል እና ክፉ በሽታ ነው። በዚህ ቁጭትና የስቃዩ ሰበብ ብዙ ሰው ሊገድል ይችላል። ያየነው ትርዒት ክፉ ነው፡ ”ክፉ ርኢና” የሚያሰኝ ነው።
መለስ ሃይማኖት ስለሌለው እንጂ “አበ ነብስ” ቢኖረው “ያየወን ሁሉ” ይናዘዝ ነበር። በዛውም “ጠበል ተረጭቶለት፤ጸሎት ተደግሞለት ይቀለው ነበር። አለመታደል ግን “አበ ነብስ” ስለሌለው “ኒርሊ ዴዝ አክስፐርያንሱ” በውስጡ አጭቆ ሲይዘው “ፍላሽ ባኩ” (ድህረ ስቃይ ትውስታው) ሕሊናውን እረፍት ይነሳዋል እና ክፉ በሽታ ነው። በዚህ ቁጭትና የስቃዩ ሰበብ ብዙ ሰው ሊገድል ይችላል። ያየነው ትርዒት ክፉ ነው፡ ”ክፉ ርኢና” የሚያሰኝ ነው።
ይህ ሃቅ ነው፤ ለድንገተኛ ድንጋጤ የመጣ
“ፓኒክ አታክ” ቀደም ብየ የገለጽኩላችሁ እንሰሳዎችም ቢሆኑ “ካልተዘጋጁበት”ከጥቃት ለመዳን “ያስመሰሉትን ማስመሰያ ሞት”
ከሞቱበት አጭር ሞት ለመነሳት ከባድ ጫና ተጫጭኖባቸው ይነሳሉ፤ ወይንም አንዳንዶቹ በዛው ይዟቸው እንደሚሄድ አንዳንድ ሊቃውንት
ይጽፋሉ።መለስ ዜናዊ ከእንሰሳዎቹ የባሰ ሰርካምስታንሰ/ድንገተኛ “ዱብ እዳ” ነው የወደቀበትና ለማጋገም (ሪኩፕ)ለማድረግ ጊዜ
ሊፈጅበት ነው። ማስታወስ ያለባችሁ ነገር ቢኖር “የሕሊና ስብራቱን” ለመሸፈን ሲል ምንም አንዳልነካው ለማሳየት እንደ መንግስቱ
ሃይለማርያም ‘ሟሃይት” መንቀሳቀስ እንደሚችል “መለስ ዜናዊም” ማስተንፈስ አቋርጦ የነበረው ሰምባው፤የተደፋው አንገቱና ወደ
ደረቱ ያጐነበሰው አገጩና በሰመመን ተውጠው በግድ ሲከፈቱና ሲከደኑ የነበሩ ዓይኖቹ አሁንም ሰርአታቸው ጠብቀው ወደ ነበሩበት
ስርዓት እንደተመለሱ ለማሳየት በየአዳራሹ ስብሰባ ከሚገባው በላይ ሲቀደድና ሲንቀሳቀስ ታዩት ይሆናል። አሽከሮቹም የተቀረጹ
ስዕለ ድምፃች አን ንግገሮቹ እንድናያቸው ይለጥፉለት ይሆናል ያ ግን የውሸት የመንቆራጠጥ ትእይንት ነው። መቸም ሁላችሁም
አይታችሁታል።የሆነውን አይተነዋል፤ አንኳን ብቻ ከዛ የባሰ “ክፉ አላየን” በዛው አንኳን አልቀረ ማለቱ ይሻላል። ምክንያቱም
አበበ ገላው በመለስ ግድያ ለመከሰስ ከጠበቃ ፍለጋ እንኳን አዳነን ማለቴ ነው። እንጂ የዓለም ነገሥታት እና ታላላቅ ጋዜጠኞች
በተሰበሰቡበት አዳራሽ ያየነው ትግሬዎች“ክፉእ ርኢና” የሚሉት “ክፉ አይን” የሚባለው ነው ዓይናችን ያየ። እና “ክፉ ነገር ከማየት ይሰውረን” ወንድሞቼ።
አበበ ገላው አምላክ ይባርክህ! ቪ ኦ ኤ የሚባለው ግን በዛው ዘገባው ወደ
“ግምኛ” ተለውጦ የመለስ ዜናዊ “አጭር ሞት”ሳያስተላልፍ መቅረቱ በጣም ነበር የገረመኝ። ዘጋቢው የአገር መሪዎች እንዲህ ባለ
አዳራሽ ውስጥ በድንጋጤ ተውጠው “አጭር ሞት” ሲሞቱ በአይኑ አይቶ ስለማያውቅ እሱም ደንግጦ የሆነው ሁሉ ሳያያይ ቀርቶ
አምልጦት ይሆን? ማን ያውቃል። “ክፉእ ርኢና” ማለት እኮ ይሄ ነው። ክፉ ያየ ሰው እኮ ያየውን መናገር ይከብደዋል። አብሮ
ይደናገጣል። ሁላችንም “ክው” ብለን ነው የቀረነው።“ለዚህ ጉድ ምን ተብሎ ለሰው ይነገራል”? ጋዜጠኛው “ከብዲ ይጽሮ” (ሆድ
ይቻለው) ብሎ የሚለው ብሂልና ባሕል አጥቅቶትም ሊሆን ይችላል።
ለማንኛውም መለስ ዜናዊን ከምድረ ኢትዮጵያ አንከብክባ ወደ አሜሪካ
አስመጥታ ክፉ አይናችን እንድናይ ማርያም አኽሱም ያሳየችንን ጉድ፤ ለስሎቷ ላደረገቺልን ውለታ ለመቅደሷ ሻማ፤ጧፍ እና ቅዱስ
ዕጣን የሚመልሳት አይመስለኝም። እኔ በግሌ ልጇ ስለሆንኩኝ በታምራቷ ስለማምን “ክብርሽ ይመስገን፤ ታምራትሽ አይለየን” ብየ
ሰግጃለሁ። አመሰግኛታለሁና እናንተም እንዲሁ። ነፃነት!ነፃነት!ነፃነት!አለ; አበበ። እውነትም የአሜሪካ የመናገር ነፃነት መለስ
ዜናዊ ሲሞት“ክፉ አይን አሳየን”። ክፉእ ርኢና !!!!!!!- ክፉእ ርኢና!!!!!!!-ክፉእ-ርኢና!!!!!!!- እውነትም
“ኩፉእ ርኢና”። አመሰግናለሁ።
ጌታቸውረዳ(www.ethiopiansemay.blogspot.com)getachre@aol.com (408) 561-4836
No comments:
Post a Comment