Wednesday, April 21, 2010

ዉድ ወንድሜ ኩችዬ- ሰለጃዋር ያሉትን አንድ ልበለዎት

ዉድ ወንድሜ ኩችዬ- ሰለጃዋር ያሉትን አንድ ልበለዎት ጌታቸዉ ረዳ www.ethiopiansemay.blogspot.com 20 Aprile 2010

ዉድ ወንድሜ ኩችዬ፡ ሰላምታዬ ከእርስዎ ዘንዳ ይድረስ። ባለፈዉ ሰሞን ዱድ! ብሩን አሳዬኝ! ኩችዬ - ኤፕሪል 12 2010 ዓ/ም በሚል አንድ ጽሁፍ ስለ ወጣቱ ጃዋር መሐመድ አስነብበዉናል። ግሩም ጽሁፍ ነዉ። በጽሁፍዎ ላይ ግን አንድ ልለዎት ፈለግኩኝ። ጃዋር አለ እንደሚሉት “በቃላቶቹም ቃላቶቹን ባጀቡት ስሜቶችም አዲስ የኢትዮጵያዊነት ራዕይ መቀረጽ እንዳለበት ነው አበክሮ ያስተማረው። ለምን በሉ? እንደርሱ ባሉ ወገኖቻችን መንደር እስከዛሬ የምናውቀው “ኢትዮጵያዊነት” በሰሜኑና በደገኛው ባህል እንዲሁም በዚያ ሕዝብ ሳይኪ ዙሪያ የተገነባ ነውና ሌላውን ጮቤ ሊያስረግጠው መጠበቅ የለበትም።ባመዛኙ እንዲያገለግልም እንዲያኮራም የተደረገው የዚያኑ የሰሜን ደገኛ ሰው ስለሚመስል አንዳንዴ ቁጣ ቢያስነሳምመገርም እንደሌለብን ቃላት ሳይልቆጥብ ተናገረ። ከቶውንም “ና በድሮው ኢትዮጵያዊነት ዙሪያ እንሰባሰብ ብትለኝ አይመቸኝምና አቤት ለማለት አልጣደፍም” ነበር ያለው። አንዴ ካልተመቸው ምን ይበል?” ሲሉ ስለ ጃዋር ንግግር ዘግበዉልናል ዉድ ወንድሜ ኩችየ፤ ስለ ለጃዋር ከፍተኛ አድናቆት እንዳለዎት መግለጽዎ ግሩም ነዉ። ጃዋርን እዚህ ሳን ሀዘ ካሊፎርንያ በአካል አግኝቼዋለሁና ቅን ወጣት ነዉ። ብሩህ ና ቀልጣፋም ነዉ፤ ዲያስፖራ ከተማሩ ሽማግሌዎች ይልቅ አገር ዉስጥ ካሉ አዛዉንት ሊቃዉንቶች ያስተዳደር እና የፓለቲካ ልምድ ቢቀስም የሚጠቅሙት ዘዴዎች ብዙ ናቸዉ። ጃዋር ኢትዬጵያዊነት ባዲስ ራዕይ መቀረፅ እንዳለበት አበክሮ ሲያስተምር አሮጌ ኢትዬጵያዊነት እና አዲስ ኢትዬጵያዊነት፤ወጣት እና ሽማግሌ የሚሉት ትንታኔዎች የሚላቸዉ በጥንቃቄና በጥበብ ካልተብራሩ፤ አተረጓጎሙ ላይ ባንድ ብርዳማ ተራራ የተቀመጠ አንድ ቆለኛ ባላገር “ እጅ ቢገኝ የንፍጥ ማለቂያዉ አሁን ነበር!”የሚል ፖለቲከኛ እንዳያስመስለዉ መድረክ ላይ ፖለቲካ ሲነገር “በወንድ ልጅ አምላክ አንድ ጥይት አትንፈጉኝ” እያለ በዉጭም በዉስጥ አገር ቅጥረኛ የጠላት ጥይት ቆስሎ ደሙን እንጠፍጥፎ በየጥሻዉ የቀረዉ ኢትዬጵያዊ ለጃዋርም ሆነ ለኔ እና ለእረስዎ ያስረከበን የድሮይቷ ኢትዬጵያ፦ የዛሬዉ ወጣት በድሮዋ ኢትዬጵያ እና ኢትዬጵያ ባሰኟት ሰዎች ላይ ብዙ ርብርብ ከማድረግ ይልቅ የሚገባዉን ክብር ሰጥቶ የተሻለ መመኮር እና ማቆየቱ ላይ ቢተኮር እንጂ፡ ያለፈዉ ሁሉ እንደ ጠላት እና እንደ ዉዳቂ እንደ አፍራሽ ወይንም የሰሜን እና የደጋ ሕዝቦች የክረስትያን ስም፤ባሕልና አስተዳደር ብቻ ነዉ የተንጸባረቀዉ ወደ ሚለዉ ከንቱ አባዜ ካተኮርን፡ በአገር እና አገሪቷን በሚያስተዳድሩ ክፍሎች/ኤሊቶች/ሊሂቃን ላይ ያለዉን የትርጉም ልዩነት እዉር ድምብሩን እየስኬድነዉ ይመስለኛል። ወጣቱ ክፍል ባስተዳደር እና ባገር ላይ በነዚህ ሁለት ነገሮች ላይ ያሉት ልዩነቶች ካልተረዳዉና ሁለቱም ባንድነት ጠምሮ በጠላትነት ካየ “ያዉ አገሪቷ ዉስጥ ያሉ እና የነበሩ አምባገነን አስተዳደሮች ፍትህ ስላጓደሉ፤ የተወሰነዉ ያገሪቷ ሕዝብ ይዤ ልገንጠል ወይም /አልሰባሰብም…..ወደ ሚለዉ የትም የማያሻግር የዘመኑ አማራጭ መንገድ አማራጭ እንዳልሆነ የተማርን ይመስለኛል። “በድሮ ኢትየየጵያዊነት ዙርያ እንሰባሰብ ብትለኝ አልሰባሰብም ሲል ምን ማለቱ ነዉ”?ድሮ ሲል የትኛዉ ዘመን ነዉ?ድሮ ሲባል ዛሬ ማለት እንዳለሆነ ግልፅ ነዉ። ዛሬ የምንለዉ ግን “ሁሉም በየብሔረሰቡ የሚሰባሰብበት” ዘመን ነዉ። ድሮ የምንለዉ ስብስብ እኔ እስከማዉቀዉ “ብሔረሰብን-ለይቶ-የማይጠራ-የማሕበራዊ-ስብስብ-ነበር።
ሠርግ/ቀብር’ደስታ/ሐዘን/ዕቁብ/ዕድር ወዘተ….ሁሉም ያካተተ። ይሄ አስተዳደሩ ሳይሆን ሕዝቡ ራሱ የተገበረዉ የግንኙነት ስበስብ ነበር። ያ የድሮ ስበስብ “ኢትዬጵያዊነት” ተብሎ ይጠራ ነበር። አሁን /ዛሬ ከድሮዉ ኢትዬጵያዊነት የሚለየዉ ስበስብ ጃዋር ያወቀዉ እና በዛዉ ስብስብ የተራመደበት ስለሆነ ያዉቀዋል የሚል እምነት አለኝ። ስለዚህ ባሮጌዉ ስብስብ ኢትዬጵያዊነት ዙርያ “ተሰብሰብ ብትለኝ “አልሰበሰብም” ማለት የድሮዉ ኢትዬጵያዊነት ስብስብ ከዛሬዉ የጎሰኞች ኢትዬጵያዊነት የተሻለ ስለሆነ በነጠረ መስመር ቢያብራራዉ የተሻለ ይሆን ነበር ብየ እገምታለሁ። ከድሮም ምራቅ የሚያስዉጥ ናፍቆቱ የማይልቅ “ና ብለህ”-ለምነኸዉ “የማይገኝ” ኢትዬጵያዊነት እንደነበር ለወጣቱ ለጃዋር መሐመድ ስገልጽለት በፍጹም ኢትዬጵያዊ ወንድምነት ነዉ። ይህ ደብዳቤ እርስዎ በጻፉባቸዉ ሚዲያዎች ተልኳል፤እንደሚያወጡትም ስለምጠራጠር፤ቅጁ ለራስዎ ልኬአለሁ።ባለ ሚዲያዎቹ የደብዳቤየ መልክት እና ምክር ከሕዝቡ ዓይንና ጀሮ እንዳይደርስ እንዳይከለክሉት አምላክ ከነሱ ጋር እንዲሆን እጸልይላቸዋለሁ። የኢትዬጵያ አምላክ ከርስዎ ጋር ይሁን። ጌታቸዉ ረዳ።www.Ethiopiansemay.blogspot.com Getachre@AOL.com

1 comment:

Anonymous said...

From, Tekuale
Ato Getachew, you have pointed out the weekness of Kuchye. I understood from his writtings that though he is good in bringing points together at the same time he is also a bit faster to give comments for what he felt right.