Friday, April 16, 2010

ጋዜጠኛ ኢየሩሳሌም አርአያ ከሞት አደጋ አመለጠ

ጋዜጠኛ ኢየሩሳሌም አርአያ ከሞት አደጋ አመለጠ

ጌታቸዉ ረዳ www.Ethiopiansemay.blogspot.com

ከላይ የሚታየዉ ፎቶ ጋዜጠኛዉ ኢየሩሳሌም አርአያ ነዉ።

Friday, April 16, 2010

ለኢትዬጵያዊያን ጋዜጠኞች ማሕበር

ለኢትዬጵያ ድረገፅ እና መጽሄት ባለቤቶች

ለኢትዬጵያ የሰብአዊ መብት ተማጓቾች ማሕበር

ለኢትዬጵያ ሲቪክ፤ሴቶች እና ወጣት ማሕበራት

ለኢትዬጵያ እስላሞች እና አብያተ ክርስትያን ተቋማት

ለኢትዬጵያ የፖለቲካ ተቃዋሚ ድርጅቶች ሆይ!

የተከበራችሁ አገር ወዳድ ኢትዬጵያዊያን ሆይ!

የኢጦብ መጽሄት ከፍተኛ ጋዜጠኛ/ዘጋቢ የነበረዉ ኢየሩሳሌም አርአያ ከወያኔ የደህንነት ክፍሎች በተሰነዘረበት የድብደባ ጥቃት ትናንት Thursday, April 16, 2010 ) ፈረንጆች አቆጣጠር( በሕንድ አገር በኒዉ ዴልሂ ከተማ ከሞት አደጋ ማምለጡን ካንደበቱ በስልክ እንደተነገረኝ ለናነተዉ ለዉድ ኢትዬጵያዊያን ዜጎች ለመግለጽ እወዳለሁ

ጋዜጠኛ ኢየሩሳሌም አርአያ 14 ዓመት ታዳጊ ወጣት ሴት ልጁ በበሽታ በመሰቃየቷ ከዓመት በላይ ሕንድ አገር በዋና ከተማዋ ኒዉ ደልሂ በጊዚያዊ ጥገኝነት ተመዝግቦ እየኖረ እንዳለ በተከታታይ በቀርቡ የወያኔ ሰላዬች ከሚኖርበት ሕንድ አገር ድረስ በመከታተል በተንቀሳቀሰበት ሁሉ በመከተል ዛቻ እና ማስፈራርያ በመሰንዘር፤ተከራይቶ ሲኖርበት ከነበረዉ የመኖርያ ቤቱ ድረስ አከራዩን ባለቤት በመደወል እንዲያሰወጣዉ ካልሆነ ግን በአከራዩ ባለቤት የሕይወት እርምጃ እንደሚወሰድበት ማንነታቸዉ ያልታወቁዩ ሰዎች በስልክ ደዉለዉ ስላስፈራሩት፤ ኢየሩሳሌምን ያከራየዉ ህንዳዊዉ ባለቤትም በዛቻዉ በመደናገጥ ሲኖርበት ከነበረዉ ቤት እንዲለቅለት በማድረጉ፤ አባት እና ልጅ መጠለያ በማጣት ሲንከራተቱ የሚጠለሉበት መኖርያ በማፈላለግ እያሉ፤ ትንናት ከላይ በተጠቀሰዉ ቀን እና ዓመተምህረት ኢየሩሳሌም እና እዛዉ ከሚያዉቃቸዉ አበሾች ጋር ሆነዉ ከሆስፒታል ግቢ ሲወጡ በአገሬዉ አቆጣጠር ከምሽቱ 2 ፡ሰዓት አካባቢ ማንነታቸዉ ያልታወቁ ሰዎች ኢየሩሳሌም አርአያን ከመሃል ነጥለዉ እንዲያነጋግራቸዉ በመጥራት፤ እሱም አገር አማን መስሎት ወደ ጠሩት ሰዎች በገርነት ሲጠጋ ጭንቅላቱ ላይ በብረት ዱላ በመቀጥቀጥ ሊገድሉት በማሰብ የሰነዘሩበት ድብደባ ጭንቅላቱን ላለማስመታት በእጆቹ በመከላከል በእጆቹ እና በተቀረዉ አከላቱ ላይ ክፉኛ በመቀጥቀጡ "ግራ እጁ ላይ ሃይለኛ ምት ስለደረሰበት መንቀሳቀስ አቅቶት በአስቸጋሪ ስቃይ ላይ ይገኛል።

የትግራይ ተወላጅ የሆነዉ እዉቁ ብዕርተኛዉ "ኢየሩሳሌም አርአያ" ከኒዉደልሂ በአደራነት በስልክ ደዉሎ እንደነገረኝ፤ ከላይ ለተጠቀሱ ድርጅቶች በሙሉ ስላለሁበት ሁኔታ ለዓለም የሰብአዊ ድርጅቶች እና ጋዜጠኞች እንዲሁም ለኢንተርኔት ባለቤቶች እና ለኢትዬጵያ ነፃ ጋዜጠኞች ማሕበር በአደራነት ጭሆቴ እና ስለገጠመኝ እና ለወደፊቱም በሚገጥመኝ ችግር ሁሉ ከለላ እና መከታ ሆነዉ እንደ ዜጋ እንዲተባበሩኝ የጠበቀ አደራየን እንድታስተላልፍልኝ ብሎ ስለጠየቀኝ፡ አገር ወዳድ ነኝ ፤ኢትዬጵያን እወዳለሁ ፤የኢትዬጵያዊነት ትርጉም እገነዘባለሁ፤ የምትሉ ወንድሞች እና እህቶች በሙሉ በያላችሁበት የገንዘብ ዕርዳታ እና የሚድያ ሽፋን እንደዚሁም፤ ባለሃብቶች ካላችሁ ጥገኝነቱም ወደሌላ ዓለም እንዲዘዋርለት በማስተናገድ እና በማገዝ፤ ከዚህ አልፎም የሰብአዊ ተሟጋች ማሕበሮች እንወከላለን/እንሰራለን/ያገባናል የምትሉ ዜጎች ሁሉ ስለሁኔታዉ ከሚመለከታቸዉ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች እና ኢምባሲዎች እንደዚሁም ዋሽንግተን ለሚገኘዉ የሕንድ አማባሳደር እና ዋሽንገተን እና ኒዉ-ደልሂ ወደ ሚገኘዉ UNHCR ጽ/ቤት ድረስ በመጻፍ እና በመደወል ስለሁኔታዉ እንድታስታዉቁለት በ14 ዓመቷ በሽተኛዋ በታዳጊ ህጻን ልጁ በ“ኢየሩሳሌም” ስም እንደዚሁም በጋዜጠኛዉ ስም፤እና በራሴ ስም እንደዚሁም እንወዳታለን በምትሏት ኢትዬጵያ ስም ሁላችሁንም እማጸናለሁ።

በተለይም ነፃ ፕሬስ ማሕበር በስራ ላይ ካለ የባልደረባቸዉ አስፈሪ ሁኔታ ለዓለም እና ለመላ የ ኢትዬጵአ ሕዝብ እንድታሳዉቁለት እንደዚሁም የገንዘብ ዕርዳታ እንዲዋጣለት በናንተ በኩል እንድታስተባብሩለት አደራየ የጠበቀ ነዉ። አገር መዉደድ ማለት በጣት የሚቆጠሩ ዝና ያተረፉ አርቲስቶች ወይንም ሊሂቅ ፖለቲከኞች ችግር ሲገጥማቸዉ/ሲታሰሩ/ሲታመሙ/ሲሰደዱ በነሱ ብቻ ትኩረታችን በመለገስ ሳንወሰን አጋርና ቡድን፤ ስብስብ እና ክለብ የሌላቸዉ ጊዜ የጣላቸዉ ብርቅየ ዜጎቻችን ጊዜ ሲያዳላቸዉ ከጎናቸዉ በመቆም ችግራቸዉንና ልቅሶአቸዉ ስቃያቸዉና መከራቸዉ ተካፋዬች በመሆን የኢትዬጵያዊነት ትርጉም በግብር ለማሳየት ላገራቸዉ ክብር እና ፍትህ በመቆም ከየተደበቁ የወያኔን ገበናዎች ፈልፍለዉ በማዉጣት ለታሪክ ዘጋቢዎች እና ለሕዝባችን የሚያሳዉቁ እንደ ኢየሩሳሌም አርአያ የመሳሰሉ ኢንቬስቲጌቲቭ ዘጋቢዎች ለወያኔ ጥቃት ሲጋለጡ ጥቃታቸዉን በሚገባ መከላከል እንደምንችል በግብር ማሳየት ይጠበቅብናል።

ስለ የወያኔ የገበና ማሕደር ማንኛዉም ዘጋቢ ያልዘገበዉ ጉድ ማወቅ ለሚፈልግ ሁሉ የኢየሩሳሌም አርአያ ዘገባ በቅርቡ በዘሃበሻ ኦን ላይን መጽሄት ላይ የተዘገበዉ ስለ ኪሮስ አለማዮሁና ሱራፌል ወልደሚካኤል በቅርቡም በዛዉ መጽሄት ላይ የጀኔራል ሳዓረ መኮንን እና ባለቤቱ ሻለቃ ጽጌ ካሁን በፊት ተገልጾ የማያወቅ የተደበቀ ምስጢር “የሻለቃ ጽጌ መዘዝ እና የጀኔራል ባለቤቷ ጭፍን እርምጃ” በሚል ርዕስ ዘግቧል። የወያኔ ሹማምንት የገበና ማሕደር እና ያስተዳደር ብለሹነት በተከታታይ በዚህ ወር ዕትሞች እንሚቀጥልበት ቃል ገበንቶልን እያለ ነዉ ወያኔዎች ይህንን ለማኮላሸት ኢየሩሰሌም አርአያን ቀጥቅጠዉ ለመግድል ኩፍኛ ደብድበዉ አከላቱ በብረት ዱላ ለስቃይ ተዳርጎ በችግር ላይ በሕክምና ላይ የሚገኘዉ።

ጋዜጠኛዉ ኢየሩሳሌም አርአያ እና የ 14 ዓመት ታዳጊ ወጣት ሴት ልጁ በገንዘብ በሞራልም ሆነ በዜና ማሰራጫ ጣብያዎቻችሁ በመጋበዝ ስላለበት ሁኔታ ለሕዝብ እንዲያስረዳ ለመተባበር ፈቃደኞች የሆናችሁ ሁሉ በራሴ ስልክ እና በራሱ የኢመይል አድራሻ አስፈላጊዉ ግንኙነት ማድረግ እንደምትችሉ ለማሳሰብ እወዳለሁ።የ ኢየሩሳሌም ኢመይል አድራሻ eyerusaraya7777@yahoo.com ለኢትዬጵያዊነት ሕልዉና ሲሉ ሕይወታቸዉ ለአደጋ የተጋለጡ ዉጭ አገር የሚኖሩ ዜጎቻችን ተረባርበን ከገጠማቸዉ ፈተና አብረን እናዉጣቸዉ።

ኢትዬጵያዊነት ሕሊና ለዘላለም ሕያዉ ነዉ!

ጌታቸዉ ረዳ (የኢትዬጵያን ሰማይ ዌብ ላግ አዘጋጅ) Getachre@AOL.com

www.ethiopiansemay.blogspot.com

1 comment:

Unknown said...

Weyane never sleep for real Ethiopians. They will do more upon us. It is not their fault but ours.
Thank you to relay this message.