በአረጋዊ ራስ ሁለት ምላስ
ጌታቸዉ-ረዳ www.Ethiopiansemay.blogspot.com
ተጋድሎ ሓርነት ህዝቢ ትግራይን ከመሰረቱት መሃል ሦስቱ ማለትም ዶ/ር አረጋዊ በርሀ (“በሪሁን”) አቶ ግደይ ዘርአጽዬን (“ፋንታሁን”) ደ/ር ዓለምሰገድ መንገሻ (ሃይሉ) እንዲሁም የሕዝባዊ ሓርነት ትግራይ የእስር ቤቶች እና የድርጅቱ ስለላዉ ክፍል ከፍተኛ ባለስልጣን የነበረዉ አቶ ብስራት አማረ፤ በርሀ ሓዱሽ፤መኮንን ዘለለዉ (ፋኑስ) እና ሌሎቹ ሆነዉ በየካቲት ወር 1987 ዓ.ም (በፈረንጅ ፌብሩዋሪ 1995) TAND Tigrean Alliance for National Democracy በመባል የሚመሩት የፖለቲካ ድርጅት፣ ሰሞኑን “የሗሊት ጉዞ አገራችንን ይበታትናል” በሚል ርዕስ ለጀነራል ሃይሌ መለስ የትግራይ ሕዝብ ወደ ትግሉ አልቀላቀልም አለ፤ ዝምታዉ እስከመቸ ነዉ? በማለት የተቹት ጽሁፍ የተሰጠ የድርጅቱ መግለጫ ሳነብብ፣ ድርጅቱ እቃወመዋለሁ የሚለዉንን ህወሓትን “እኛ የወያነ ስርአት ተቃዋሚዎች ” ‘በዘር/በጎሳ ያነጣጠሩ የግድያ የእንግልት እና የእስራት ድርጊቶች የምንላቸዉን ህወሓት የፈጸማቸዉ የጎሳ ጥላቻ መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች “ታንድ” ሲያብራራ “ህወሓት/ኢሕአዴግ ሰዉን የሚገድለዉና የሚያንገላታዉ ሥልጣኑ ላይ ሊያደርሰዉ ከሚችለዉ አደጋ አንጻር (ለአምባገነኖቹ አገዛዝ የማያመቹ በመሆናቸዉ ካልሆነ) እንጂ በዘሩ ነዉ ብለን አናምንም፣፣ በዘር ቢሆን ኖሮማ ከላይ የጠቀስናቸዉና ያልዘረዘርናቸዉ የትግራይ ልጆች በ(ህወሓት) ባልተገደሉ ነበር፣፣” በማለት በአረጋዊ፣ በግዳይ፣ በስብሓት እና በመለስ ዜናዊ የሚመራዉ የጥንቱም ሆነ የዛሬዉ “ወያነ ትግራይ” *አምባገነን ድርጅት* እንጂ *ጎሰኞች አይደለም!* ሲል “ምን ታመጡ!” በማለት ብዙዎቻችን በታንድ ላይ ያልነበረን ዕዉቀት የታንድ ማንነት ገሃድ ወጥቶ እንዲገለጽለጽልን መግለጫቸዉ ረድቶናል፣፣
ከዚህ ተያይዞ ሁለት ሌሎች የምተችባቸዉ ነገሮች አሉ። ልተችበት የምፈልገዉ ነጥብ “የትግራይ ሕዝብ ዝም ብሏል” ወደ ትግል አልገባ ብሎ በጣም አድፍጧል እና ለምን?” ብሎ ለጠየቀ ሁሉ “ጸረ ትግራይ ነዉ” እያሉ የሚለጥፉበትን ስም ነዉ። በዚህኛዉ ልጀምር፦ አዎ የትግራይ ሕዝብ ወደ ትግሉ አልተቀላቀለም፤ አድፍጧል ብሎ ያለዉ ሌላዉ የተቃዋሚ ክፍል ኢትዬጵያዊዉ ብቻ ሳይሆን ከእራሱ ከታንድ መሪዎች (የታንደ የሚዲያዉ ክፍል ሓላፊ) አቶ መኮንን ዘለለዉ በነሓሴ ባለፈዉ ወር ያረጋገጠዉ ነዉና ለምን ድነዉ ሌላዉ ሲለዉ ታንድ የሞቆጣዉ? አቶ መኮንን ዘለለዉ ከአዲስ ድምጽ ራዲዬ አዘጋጅ ከአቶ አበበ በለዉ ጋር ቃለ መጠይቅ ሲያደርግ ይህንን አረጋግጦታል። ልጥቀስ፤
ጥያቄ፦ ብዙ ሰዎች የትግራይ ሕዝብ ወደ ትግሉ አልተቀላቀለም፤ እያሉ ብዙ ሰዎች ይተቻሉ፤-ለምንድነዉ ወያኔን በስማችን መነገድ አቁም፤ በማለት በይፋ የማይቃወሙት?ሲሉ ብዙ ሰዎች ይተቻሉ እና እዉነት የትግራይ ሕዝብ ለምን ድምጹን በይፋ አያሰማም? ተብሎ ለቀረበዉ ጥያቄ ሲመልስ፤
አቶ መኮንን ዘለለዉ እንዲህ ብሎ ነበር “ (የትግራይ ሕዝብ) 90 ወይም መቶ በመቶ (የወያኔ) ተቃዋሚ ነዉ፤ ሚስቱ የከዳችዉ ሰዉ ተሎ ለመታገል ዝግጁ የሚሆን አይመስለኝም። የትግራይ ሕዝብ ባሳደጋቸዉ፤በልጆቹ የተከዳ ሕዝብ ነዉ። አንድ ሰዉ -የሚያምናት ሚስቱ በሚስቱ የተከዳ ሌላ ሚስት ለማግባት የሚሮጥ አይመስለኝም። ቆም ብሎ ማሰብ ያስፈልገዋል። ልጆቼ ብሎ ወደ ትግሉ የላከ ልጆቹ የካዱት ሕዝብ ነዉ። እና አሁን በቀጥታ ወደ ትግሉ ለመግባት የሚችል አይመስለኝም። እና ቆም ብሎ በማሰብ ላይ ነዉ። አርቆ የሚያስብ እዉነተኛ የሚታመን የትግል ድርጅት እስካሁን አልተገኘም። እከሌ አለ የምትልም አይመስለኝም። .......አሁን -የትግራይ ሕዝብ በጠቅላላ አሁን ኢትዬጵያዊ ዕምነት ያለዉ የትግራይ ሕዘብ እየጠፋ ነዉ….።” ሲል በግልጽ አቶ መኮንን ዘለለዉ የፍትሒ ራዲዬ አዘጋጅ በማያሻማ ቃል አስቀምጦታል ።የቃለመጠይቁ ቅጅ/አዉድዬዉ አሁንም በአዲስ ድምጽ የህዋ ሰሌዳ በመግባት ማዳመጥ ይቻላል።
አቶ መኮንን “በጠቅላላ አሁን ኢትዬጵያዊ እምነት ያለዉ የትግራይ ህዘብ እየጠፋ ነዉ” ሲል “ምን ማለቱ” እንደሆነ አዘጋጁ ለምን እንዲያብራራለት በዝምታ እንዳለፈዉ ግራ ገብቶኛል። “ለመታገል ዝግጁ የሆነ አይመስለኝም። ቆም ብሎ በማሰብ ላይ ነዉ…” የሚሉት ሐረጎች ምንን ያመላክታሉ?18ዓመት ቆም ብሎ በዝምታ እያሰበ ነዉ ብሎናል። ዛሬም የሚታመን ኢትዬጵያዊ ድርጅት ካጣ “ታማኙና ተቆርቋሪዉ የትግራዋይ ታንድ ድርጅት” እንዴት አላምንም አለዉ? ወይስ ታንድም እንደሌሎቹ ኢትዬጵያዊ ድርጅቶች የትግራይ ሕዝብ አላምንህም በሎታል?ታንድ ከተመሰረተ ዓመታት አስቆጥሯል ለምን እሱን እንኳ አላመነዉም? የተቀሩትተቃዋሚ ኢትዬጵያዊ ድርጅቶች መኮንን ዘለለዉ ዉን ተመርኮዞ “ዝምታ በዛ፡ ቆም ብሎ ማሰቡ ረዘመ፤” ብሎ ለሚል ተቺ እንዴት “ጸረ ትግራይ ሕዝብ ያስብለዋል?
ይህ ከላይ የተጠቀሱት የድርጅቱ ሁለቱ ኮምጣጣ አቋሞች ለሕሊናየ አስቸጋሪ ግብግብ ሆኖ አግንቼዋለሁ፣፣ ሌላዉ 2ኛዉ ነጥብ፤-ታንድ ባሰራጨዉ ጽሑፍ በገጽ 8ላይ ““ህወሓት/ኢሕአዴግ ሰዉን የሚገድለዉና የሚያንገላታዉ ሥልጣኑ ላይ ሊያደርሰዉ ከሚችለዉ አደጋ አንጻር (ለአምባገነኖቹ አገዛዝ የማያመቹ በመሆናቸዉ ካልሆነ) እንጂ በዘሩ ነዉ ብለን አናምንም” (ገጽ 8) ሲል፣- የአባባሉ ቀጥተኛ ትርጉም የሚሰጠን ህወሓት “አምባገነን” እንጂ “ጎሰኛ/ዘረኛ” አይደልም ማለት ነዉ፣፣ ይሄ በመጨረሻዉ ላይ ስለምመለስበት መጀመርያ ሌላዉ አስቀያሚ ወደ ሆነዉ “የታንድ” መግለጫ፣- ወያኔ በዘረፋም፣ በሽፋንም፣ በጋህድም በምኑም እያመካኘ የትግራይን ከተሞች እና ገጠሮች እያለማ ነዉ ለሚሉት ግለሰዎች/ድርጅቶች፣ በጸረ ትገሬነት መኮነኑን በሚመለከት ጉዳይ ትንሽ ልበል፣፣
በተለይም ታንድ ኢትዬጵያዊዉ ዶ/ር አሰፋ ነጋሽን በጸረ ትግሬነት ሲኮንን ዶ/ር አሰፋ ነጋሽ ጸረ-ትግሬ የሆነበትን ነጥብ አስካሁን ድረስ ማስቀመጥ አልቻለም። በደፋና “ስድብ መለጠፍ” “ስም ማጥፋት” ከታንድ የሚጠበቅ አይደለም እና ታንድም ሆኑ ሌሎቹ ዶ/ር አሰፋ ጸረ ትግራይ የሚያሰኘዉ አንዲት ነጥብ በማስረጃ በጽሁፍ አስደግፎ የቀረበልን አንድም ሰዉ ወይንም ድርጅት እስካሁን ማቅረብ አልተቻለም። ስለዚህ ስም መለጠፉ ይቁም ወይንም በማስጃ አስደግፎ ይቅረብ። ብዙ ሰዎች የሚያምኑትን፦ ማለትም አስካሁን ድረስ ወያነ ትግራይ በመንግሥትነት ተቀምጦ እየዘረፈና ሥልጣኑን ተጠቅሞ በተለያዩ መንገዶች የትግራይን ልማት ለማፋጠን የወሳዳቸዉ አድልኦዊ የበጀት እና የሰዉ አደረጃጀት ፍጥነት እና ጥራት እንዲሁም የፍጆታ አቅርቦትና ተጠቃሚነት ከተቀሩት ክፍላተ ሃገሮች ከሚኖሩ ነገዶች (ብዛት ያለዉም ይሁን ትንሽ ቁጥር ያለዉ)ዕድገት፣አደረጃጀት፣አቅርቦት እና ፍጆታ አድሎአዊ በሆነ መንገድ እያስተዳደረ መሆኑን ጸሃይ የሞቀዉ እዉነታ ነዉ።
የዕድገታቸዉ ልዩነትም በዓይን የሚታይ መሆኑን እየታወቀ፣ ከሌሎቹ ጋር አወዳድሮ ማመሳከር የሚቻለዉን ወያኔ የወሰዳቸዉ ኢፍትሓዊ አርምጃዎችን በማስረጃ አስደግፎ መከራረከር ሲቻል በደፈናዉ አድሎአዊነት የተመረኮዘ የባጀት እና የሰዉ ሃይል ድልድል (አሎከሺን) አድሎአዊ የሆነ የሥራ አቀጣጠር፣ አድሎአዊ የሆነ የንግድ ፈቃድ አሰጣጥ እና “ፋስሊተሽን/እንክብካቤ”ተደርጓል ባልን ቁጥር “ጸረ- ትግራይ ህዝብ ናቸዉ” እያለ የሚኮንነን በአረጋዊ በርሀ እና በግደይ ዘርአጽየን የሚመራዉ “ታንድ” እራሱን የትግራይ ሕዝብ ተጠሪ እና አፈቀላጤ፣ተቆርቋሪ አድርጎ “ሲሾም” ፣ ከታንድ አመለካከት ዉጭ ያለነዉ የትግራይ ተወላጆች “ሕጋዊ የትግራይ” ልጆች አይደላችሁም ለማለት የሚዳዳዉ በሽታዉ ድሮ በራሃ እያሉ የትግራይ ተወላጆች የሆኑትን “የኢሕአፓ”መሪዎች እና ታጋዬች “ሕጋዊ የትግራይ ተጠሪዎች እና ትግሬዎች አይደላችሁም” በማለት ጎሰኛ ፖለቲካ ሲያራምዱት የነበረዉን በሽታቸዉ ከብዙ ዓመት በሗላ ያገረሻቸዉ ይመስላል፣፣
የታንድ መሪዎች ያልተረዱት ነገር፣- - - “ኢትዬጵያ አንድ ሕብረተሰብ እና ቤተሰብ ነዉ፣፣ ስለሆነም፣ እንኳን እና ከጎሳ ጎሳ የተደረገ አድልዎ ይቅር፣ ትግራይ ዉስጥ በትግራይ መሃል ዉስጥም ከቤተሰብ ወደ ቤተሰብ፣ በድረጅት አባልነት እና በድርጅት አባልነት በመንግሥት ባለሥልጣን ቅርበት እና ርቀት ሁሉ ጎሳዊ/ቤተሰባዊ አደልዎ ይደረጋል፣፣ የጎሰኛ ሥርዓት አስተዳደር የመጀመርያ ባሕሪ መመርያዉ አድሎአዊ አሰራር ማድረግ ነዉና ዜጎች አድልኦ ተደረገ ባሉ ቁጥር “ጸረ-… “ ጸረ-…” የሚል ቅጽል ስም መስጠት አንድም የጎሰኛ ባሕሪ አለመረዳት ነዉ ወይንም ሆን ተብሎ አደሎአዊ አስተዳደሩ እንዲቀጥል የሚደረግ ጥረት ነዉ፣፣ይሄ የእገሌ ጎሳ “መሳያ” (መድህን) እኛ ብቻ ነን የሚለዉ የወያኔ ነበር በሽታ ዛሬም ታንድ ኩፉኛ ሲጠናወተዉ ይታያል፣፣
ወያኔ ከሸዋ ከጎጃም ከጎንደር ከኦሮሞ….ሕዝብ ይልቅ ለትግራይ እና ለኤርትራ ጥብቅና እንደሚቆም “ታንድ”ራሱን ማሞኘት መብቱ ነዉ፣፣ ነገር ግን ሕዝቡን ማሞኘት የለበትም፣፣ የወያኔ ደጋፊዎች እና የወያኔ ታጋዬች የነበሩ ወይንም ደጋፊዎቹ ብቻ ናቸዉ ተጠቃሚዎች እንጂ ሕዝቡ ከልማቱ አልተቋደሰም የሚሉት ሞኝነት ይቁም። ሰፊዉ ህዝብ በተቋቋሙት የልማት ዘርፎች ተጠቃሚ አይደለም ደጋፊዎቹ ፤ታጋዬቹ ማለትም እኮ እነዚያም ቢሆኑ ድርጅቱን በህይወታቸዉ እና በጉልበታቸዉ አስካሁን ድረስ የሚደግፉት አባሎች ታንድ የትግራይ ዜጎች መሆናቸዉን እያጣዉ/እየከዱት ይመስላል፣፣
የትግራይ ወያነ ከጎሳዉ ዉጭ የረባ ታአማኒ አይደለምና ጠቀሜታዉ ፣አትኩሮቱ ለትግራይ በትገሬዎች የሚገኝ ምላሽ ነዉ ይላል (ሰልፍ ረላያንስ)፤የሚተማመነዉም በትግራይ እንጂ በኦሮሞ ወይንም በሶማሌ በአማራዉ አይደለም፣፣ በዚህ ልዩ የትግራይ ተቆርቋሪነት ስሜት እና ዉጤቱን ስንመለከት ወያነ የመንግሥት ስልጣኑን ተጠቅሞ በትግራይ ለዓይን የሚታዩ ለእጅ የሚዳሰሱ ልማቶች በገፍ በትግራይ አቋቁሟል፣፣ እነ ገብሩ እነ ስየ ከድርጅታቸዉ ከመነጠላቸዉ በፊት የነበሩት ወቅቶች እንኳ ብንመለከት ከሌሎች ነገዶች (በወያኔ አጠራር ክልል) የነበረዉ የባጀት ስርጭት/የሰዉ ሃይል/የጎሳ ቁጥር፣ በስልጣን ምደባ፣ ፓርላማዉን ሰራዊቱን የመንግሥት ዘርፎችን፣ንግድ፣መገናኛ አዉታሮች ፣ማተምያዎች፣ ሚዲያዎች ጤና፣ ኩባንያ ዲፕሎማቲክ ዘርፉ፣ የዉጭ አስመጪ እና ላኪ ንገድ አዉታሮች፣ ደህንነቱን-ባጠቃላይ “በትረ መንግሥቱን” በመቆጣጠር ተገን በማድረግ ትግራይ ዉስጥ የተቋቋሙት ድርጅቶች ብዙ ነበሩ፣፣
ሆስፒታሎች የትምህርት ተቋሞች እና ማሰልጠኛ ጣቢያዎች፣የምስማር፣ቆርቆሮ የሰሜንቶ፣የጫማ የጨርቃጨርቅ፣የመኪና መገጣጠሚያ፣የመገናኛ፣ የዓይን እና የጀሮ ሕክምና ተቋማት…ለመለስ ለስዩም ለስብሓት ለቴድሮስ ሓጎስ ልጆች እና ቤተስብ መታከሚያ መማርያ ማሰልጣኛ መጠለያ ብቻ የተቋቋመ የሚል ማገጃ ስለሌለበት (ተቋማቱ በዋነነት የወያኔ መሳፍንት ባለቤቶች ቢሆኑም-) ነገም ወደ መቀሌ ለጉብኝት ብሄድ ድንገት ብታመም የምታከምበት ተቁዋም ወያኔ ዘርፎም ይሁን አጭበርብሮ ጋሃድ ይሁን በድብቅ በአድልዎ ባቋቋመዉ ሆስፒታል ዉስጥ ነዉ ምታከመዉ፣፣ለመሰል ወይንም ለስብሓት ቤተሰብ ብቻ የሚል ጽሑፍ አልተለጠፈበትም እና አረጋዊም ሆነ ግደይ ወደ ትግራይ ቢሄዱ እና ቢታመሙ የሚታከሙበትም ሆነ መድሃኒት የሚያገኙት “ታንድ” አድልዎ አልተደረገም እያለን ባሉበት ተቋማት ዉስጥ ሄደዉ ነዉ ሚታከሙት ወይንም የሚጓዙበት የገጠር ጥርጊያ/አስፋልትም እንዲሁ፣፣
ጋምቤላ ቢሄዱ መቀሌ ያለዉ ቅምጥል አይገኝም፣፣ ኦሞ አካባቢ ያሉት በድሮ ባሕል ሚተዳደሩ ዜጎች ቢሄዱ መቀሌ ያለዉ የተቋም ትምርት ማሰልጠኛ ቅምጥል አይገኝም፣፣ የትግራይ ገጠር ኗሪዎች እና በሌሎቹ ነገዶች የሚኖሩበት ገጠር የሚያገኙት ጠቀሜታ እና አኗኗር ለየብቻ ነዉ ብለን አፍ ሞልተን መናገር እንችላለን፣፣ ወያኔዎች ለዚህ መልስ ሲሰጡ ‘ጋምላዎች እና የተቀሩት… የተማረ የሰዉ ሃይል ልምድ፣ ስሌላቸዉ ወደ ሗላ ቀርተዋል” ይላል፣፣ ይግረም ብሎ “ የሌሎቹ ክልሎች ባለስልጣኖች እንደ የትግራይ ባለስለጣናት እና ሕዘብ (ዴዲኬሽን) ታታሪ ሰራተኞች ስላልሆኑ ከትግራይ ወደ ሗላ ቀርቷል ብሎናል (ተማሪዎቹም ባለስልጣኖቹም በኢትዬጵያ የሚወዳደር ፍጡር የለም እና ተማሪዎቹም የመልቀያ ፈተናዉ አንደኝነቱን እንደያዙት በመምራት ላይ ይገኛሉ)፣፣
ከደቡብ እተፈናቀሉ ወደ አገራችሁ ሂዱ እየተባሉ በዱላ በዝርፍያ በጥይት የሚገደሉት እና የሚሰቃዩት ህጻናት እና አዛዉንት፤ነብሰጡሮች እመጫቶች የትግራይ ተወላጆች ሳይሆኑ ያማራ ሕብረተሰብ መሆናቸዉ ከሰሞኑ በጀርመን የተገኘዉ ዜና ማዳመጥ በቂ መረጃችን ነዉ (በዚህ ብሎግ ወደ ቀኝ ከላይ ተለጥፎ ያለዉ የሚታየዉ አዉድዬ ቪድዮ ክፍል ያዳምጡ)፣፣ታንድ ይህ ሊክደዉ አይችልም፣፣ አዲስ አባባ ዉስጥ አንድ ከትግራይ የመጣ “ለማኝ” አለ ብሎ ጠቁሞ ለማኙን ጎትቶ (ለዚህ ተግባር የተቋቋመ ልዩ ክፍል) ለመንግስት ላሳየ ሰዉ አንድ ሺሕ ብር ይሰጠዋል (ምንጭ ፓል ቶክ “ገዛ ተጋሩ”፣፣ ለዚህ ተግባር ከተቋቋመ ድርጅት ከፍተኛ ባለስልጣን ጋር የተደረገ የቃለምልስ አዉድዬ)፣፣ አያ (አጋር)ያለዉ አርፍዶ ይሞታል!-የሚል የትግርኛዉን ብሂል ያስተዉሱ፣፣
“ሳኣን ኣያ ሳን ኣያ
ትግራይ ዓደይ ኣማዕድየ ርኤያ”
የሚለዉን የማሕበር ገስገስቲ ትግራይ (ተሓህት)የመጀመርያ ዘፈኑ ልብ ይለዋል (አያ/ትግራዋይ የሆነ ጠበቃ/ተቆርቋሪ በማጣቴ ሃገሬ ትግራይን አሻግሬ በሩቅ እንዳያት ተገደድኩ)(ስደት በዛብኝ፣ ልመና በዛብኝ፣ ስደት ረሃብ በሽታ በዛብኝ…ማለቱ ነዉ)፣፣ ዛሬ ከደቡብ “ዉጣ!” እተባለ ከሚንገላታዉ የአማራዉ ሕብረተሰብ ጋር “ሲነጻጸር፣- “አያ” ያጣዉ አማራዉ መሆኑን ታንድ ሽንጡን ገትሮ ሊክደዉ አይቻልም!ባለፈዉ ሓምሌ ወር 2002 ዓ.ም 12,000 (አስራሁለት ሺሕ) አማርኛ ተናጋሪ ዜጋ ከደቡብ ዉጣ ተብሎ ሲባረር ፣የትግራይ ሕብረተሰብ ቢሆን “ታንድ”-ምን መግለጫ እንደሚያወጣ ወይንም የወያነ ትግራይ መንግሥት መሪዎች እና ደጋፊዎቹ ምን እርምጃ ይወስዱ እንደነበሩ መገመት አያዳግትም (በዉጡ ባዮች ላይ መሬቱ ከቆሙበት ተደርምሶ ሰማዩም በላያቸዉ ላይ ይደፋ እንደነበር አያከራክርም፣፣ “ሳኣን ኣያ ሳኣን ኣያየ….” የተባለዉ ያ የጥንቱ ዘፈን ከትግራይ ሕብረተሰብ ለሁለተኛ ጊዜ ዛሬ በድብቅም በይፋም አልተደመጠም፣፣
ጭቆና ትግራይ ዉስጥ አለ? አዎ አለ፣፣ ወያኔ አምባገነን ነዉ? አዎ፣ ያዉም ፋሽስታዊ! ወያኔ ጎሰኛ ስርዓት ያራምዳል?አዎ፣ ወያኔ ጎሰኛም አምባገነንም ፈሽስታዊም ነዉ፣፣ ወያኔ መስፍናዊ እና ጠባብ ነዉ፣፣ በመሆኑም ከመሳፍንት ከጠባቦች ከጥንትም ሆኑ ከዘመናዊ ማሳፍነቶች ጭቆና ጠፍቷል የሚል እምነት አላቀረብንም፣፣ ቤተሰቦቻችን ታርደዋል፣ በእሳት ተቃጥለዋል እና ስለ ወያኔ ጨካንነት ስለ “አረጋዊ በርሔ” ጭካኔነት በቅርብ ስለምናዉቀዉ፣- ወያኔ ገራገር ነዉ የሚል አቋም የለንም፣፣
ነገር ግን የወያነ ትግራይ ጎሰኛ ባሕሪይዉና የሚፈጽማቸዉ አድልዎ ስናጋልጥ “ታንድ በደፈና “ጸረ ትግሬዎች”-ሊለን ካልሆነ አንድም ነጥብ በማስረጃ አስደግፎ ጸረ-ትገሬነታችን ማቅረብ አይችልም”! ወያኔ የትግራይን ሕዝብ እንደጭሰና መያዙን ታንድ ሊነግረን አይችልም፣፣ እናዉቀዋለን፣፣ ነገር ግን እያልን ያለነዉ “የጭሰኛዉ ጌታ” ከጭሰኛ ጭሰኛ አድልዎ ይፈጽማል፣ “ፌቮራይት” ጭሰኛ አለዉ፣ ነዉ እያልን ያለነዉ፣፣ የባርያ እና የጭሰኛ ጌቶች ከባርያ ባርያ ከጭሰኛ ጭሰኛ ከሰራተኛ ሰራተኛ አንዱ ከሌላዉ ለየት ባለ ሁኔታዎች የተለያዩ ድርጊቶችን እና ላላ ያሉ ሁኔታዎችን ችሮታ እና ልገሳ (Treatment) ይፈጽማል፣፣ ጭሰኛዉ ይሄ ስለተደረገለት በጣላትነት ይታይ ማለት ሳይሆን “የጌታዉን” “የገዢዉ ቡድን” ባሕሪ ድርጊት መግለጻችን ነዉ፣፣ ክርክሩ ላንዱ ጭሰኛህ የምታደርገዉ ለየት ያለዉ ዕረፍት (ችሮታ፣ ፈቃድ-ጠቀሜታ…) ትንሽም ብትሆን ለሁሉም ጭሰኞችህ እኩል ይደረግ ነዉ፣ ክረክሩ፣፣ ይህ ደግሞ ጸረ ጭሰኛ አያሰኘንም፣፣
ወደ ሌላዉ መግለጫዉ እንለፍ፣-
““ህወሓት/ኢሕአዴግ ሰዉን የሚገድለዉና የሚያንገላታዉ ሥልጣኑ ላይ ሊያደርሰዉ ከሚችለዉ አደጋ አንጻር (ለአምባገነኖቹ አገዛዝ የማያመቹ በመሆናቸዉ ካልሆነ) እንጂ በዘሩ ነዉ ብለን አናምንም፣፣ በዘር ቢሆን ኖሮማ ከላይ የጠቀስናቸዉ የትግራይ ልጆች እና ያልዘረዘርናቸዉ የትግራይ ተወላጆች (በወያኔ) ባልተገደሉ ነበር” በማለት የወያኔን ጎሰኛነት ለመከላከል ቢሞክርም የታንድ መሪዎች ከእዉነታዉ ሊደበቁ ቢሞክሩም የወያኔ ዘረኛ ግፎች ጸሃይ የሞቃቸዉ ናቸዉና ለመደበቅ አይቻላቸዉም፣፣ አስቀድሜ ግን ከወደ መጨረሻዉ በዘር ቢሆን ኖሮማ ከላይ የጠቀስናቸዉ የትግራይ ልጆች እና ያልዘረዘርናቸዉ የትግራይ ተወላጆች (በወያኔ) ባልተገደሉ ነበር” ከሚለዉ ልጀምር፣፣ አባባሉ በጣም አስገራሚ ነዉ፣፣ ደርግ ከመነሻዉ 59-የቀዳማዊ ሃይለስላሴ ከፍተኛ ባለስልጣኖች ጀምሮ ከትግራይ ይልቅ ብዙ አማራዎችን በቀይ ሽብር ዘመቻዉ እና በጦር ሃይሉ ከፍተኛ ጄኔራሎች የነበሩ አማራዎችን ገድሏል፣፣ በታንድ ሙግት ደርግ አማራ ስለገደለ “ዓሳዉን ለማድረቅ/ለመግደል ዉሃዉን ባሕሩን ማንጠፍ” እያለ ደርግ የትግራይን ሕዝብ በዘረኛነት በጸረ ትግራይ አቋሙ የትግራይን ሕዝብ ኑሮ አኮላሽቷል ተብሎ ሲከሰስ የነበረዉ “ታንድ” ነፃ አዉጥቶታል ማለት ነዉ፣፣ምክያቱም እነ አረጋዊ እነ ግደይ (ታንድ)-እንደሚሉን ከሆነ ‘ወያነ ትግራይ/ኢሕአደግ አምባገነን እንጂ ጎሰኛ/ዘረኛ አይደለም”-ከሆነ “ደርግ አምባገነን እንጂ የትግራይ ጠላት አልነበርም ምክንያቱም በራሱ ዉስጥ የነበሩ ብዙ አማራዎች (ደርግ አማራ ከተባለ-ማለትም በወያኔ አጠራር “አማራ ስለሚሉት”- ስለገደለ ከዛሬ ጀምሮ ታንድ ደርግን በዘረኛ/በጸረ ትግራይነት መክስ የለበትም፣፣
ለመሆኑ ወያነ ማን ነዉ? “መጀመርያ ድርጅቱ ማንነት መፈተሽ ነዉ፣፣ ከዚያ ድርጅቱ የሚመራበት መመርያ መፈተሽ ነዉ፣፣ ቀጥሎ ድርጅቱ ያስተማራቸዉ ትምርቶችን መፈተሽ ነዉ፣፣ መጨረሻ ድርጅቱ የወሰዳቹ እርምጃዎች ከምን አንጻር የተያያዙ እንደነበሩ ማገናዘብ አስፈላጊ ነዉ፣፣
እነዚህ አንድ ባንድ ባጭሩ እንመልከታቸዉ፣፣
የድርጅቱ ማንነት ስንፈትሽ፣ -ድርጅቱን የመሩት እነማን ነበሩ/ናቸዉ?ኢትዮጵያዊነታቸዉ የካዱ ትግራይን ከተቀረዉ ኢትዬጵያ ክፍል ለመገንጠል አቅደዉ ለሕዝብ ይፋ መግለጫ ያሰራጩ ጠባብ ብሔረተኞች፣ በኢትዬጵያ ላይ በተለይም በአምሐራዉ ሕብረተሰብ ላይ አብሶ ደግሞ በሸዋ አማራ ላይ ጥላቻቸዉ ያልደበቁ ጎሰኞችና ኮሚኒስቶች ናቸዉ ድርጅቱን እየመሩ ያሉት፣፣ ባጭሩ ባበስብሓት ነጋ ቃል “የትግራይ አብዬት ልክ እንደ ኤርትራዉ የቅኝ ግዛት ጥያቄ ነዉ” (አረጋዊ የጻፈዉ አዲሱ መጽሐፉ ላይ በገጽ 72 ይመልከቱ political History of TPLF) በሚሉ ግለሰዎች የተመራ እና እየተዳደረ ያለ ነዉ፣፣
የድርጅቱስ መመርያ ምን ነበር? ድርጅቱን ማለትም ሰብሐት፣አጋአዚ፣ግደይ፣ሃይሉ፣ አባይ፣ ስዩም አረጋዊ፣ መለስ፣አስፋሃ (ቴድሮስ ሐጎስ) እናሌሎቹ ሲመሩት መመርያዉ የጎሳ ፖለቲካ መሰርት ያደረገ “ኮሚኒስታዊ-ፋሺዝም”ነበር፣፣ ባጭሩ ትግራይን የምንወክል ሃቀኛ/ሕጋዊ ተጋሩ (Legitimate sons and daughters of Tigraya) እኛ እንጂ ሌላዉ ኢትዬጵያዊ (ለምሳሌ ኢድዩም ይሁን ኢሕአፓ) ትግራይ ዉስጥ ገብቶ ስለ ትግራይ ህዝብ ችግር መነጋገር መብት የለዉም እያለ የተከራከረ ፋሽስታዊ ክልልተኛነትን(extremist) እንደመመርያ የተከተለና ያፀደቀ ድርጅት ነበር፣፣በኢሕአፓ አመራር የነበሩ የትግራይ ተወላጆች እንደ እነ ብርሃነ ኢሳያስ (ድሮ ያዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትግራይ ተማሪዎች ማሕበር አባል ነበረ በማለት አረጋዊ የጻፈለት)፣ እነ ዶክተር ተስፋይ ደበሳይ እነ ጋይም ሃይለሚካኤል፣ መሓሪ/ሰለሞን ወዘተ…ወዘተ በወያኔ ትግራይ ጽንፈኛ ድርጅት እምነት “የትግራይ ተወላጆች ሳይሆኑ”“ሸዋዉያን ተጋሩ/የሸዋ ትግሬዎች”-የሚል የተጸዉኦ ስም በመስጠት የዜጎችን የትዉልድ አካባቢ የሚነፍግ “ፋሽስታዊ-ክልልተኛነት” የሚከተል ትምክህተኛ ድርጅት ነዉ፣፣ይህንን በሚመለከት ከኢሕአፓ ጋር ያጣላቸዉ አንደኛዉ ነጥብ እንደነበር አረጋዊ በርሄ በተጠቀሰዉ አዲሱ መጽሐፉ 226 ይመልከቱ፣፣
ድርጅቱ ያስተማራቸዉ ትምህርቶችስ ምን ነበሩ?ድርጀቱ ጎሰኛ/ክልለተኛ እና ፋሽስታዊ እንደመሆኑ መጠን ታጋዬቹን ስያስተምር በትግራይ ብቻ ተወስኖ አመለካከቱ እንዲጠብ አድርጎ ስላስተማረዉ የራሱን ድርጅት ፈጠር ባንዴራ በመፍጠር የትግራይ ሕዝብ ባንዴራ ብሎ የኢትዬጵያ ሕጋዊ ሰንደቃላማ በታዳጊዎቹ የትግራይ ወጣቶች (በወያኔ አጠራር “ሰገናት” እና “ብርኪ ሰገናት”… የሚባሉት ታዳጊ ወጣቶች) ሕሊና እንዳይቀረጽ ባንገት የሚጠለቅ መሃረም የህወሓት ባንዴራ በማስሰፋት አንገታቸዉ ላይ “ቢጫ እና ቀይ ቀለም ያለበት የወያኔ ባንዴራ እንዲያስሩ በማድረግ በሕሊናቸዉ እንዲያያዝ በማድረግ ብሔራዊ ክህደትን አስተምሯል፣፣ ክልልተኛ እና ጎሰኛ ከመሆኑ የተነሳ ታጋዬቹ ትግራይ እንጂ ኢትዬጵያ የሚባል ሀገር አናዉቅም በማለት ወደ 15 ሺሕ የሚሆኑ የወያኔ ታጋዬች ትግራይ ከደርቅ ቁጥጥር ሙሉ በሙሉ ነፃ እንደወጣች ወደ ተቀሩት የኢትዬጵያ ክፍላተ ሃገሮች አንንቀሳቀስም፣ “እኛ ትግሬዎች አንጂ ኢትዬጵያዊያን አይደለንም”“ሲፈልግ ሌላዉ ራሱን ከደርግ ነጻ ያዉጣ”-በማለት አምቢ ብለዉ በግምት ስድስት ወር የፈጀ ክርክር (ሌሎቹ ከ አንድ ዓመት ወደ ሁለት ዓመት የፈጀ ክርክር ተደርጎ ነበር ይላሉ)-ተድረጎ ነበር፣፣ ከዚያ በሗላ ነበር ወደ ጎንደር እና ወሎ ጎጃም በሙሉ ሃይል ራቅ ወደ አሉት ድምበሮችን መዝለቅ የተጀመረዉ (አስከ ዛዉ ግን በጣም በተመናመነ ሃይል ነበር የወያኔ አዋጊዎች ይዘዉ ሲዋጉ የነበሩት፣ የደብረታቦርን ዉግያ ሲዋጉ አብዛኛዎች ቦታዉን እየለቀቁ አንዋጋም ነጻ ወጥተናል ሌላዉ ራሱን ያዉጣ እያሉ ምሽጎቻቸዉን እየተዉ ወደ ትግራይ ከተማ እና ገጠር ግብተዉ ነበር፣፣ ቁጥሩን/ጊዜዉን ባላስታዉስ “የሳሞራ የኑስ” ቃለ መጠይቅ በሃዋርያ አቅርቤዉ ነበር፣፣)
፣ የአረጋዊ በርሔን “ማለሊት ዘላሊት” በሚል ጽሑፉ ላይ የምንመለከተዉ የሚከተለዉን ጠባብ ብሔረታኛነት ትምህርት እና ቅስቀሳ በድርጅቱ ዉስጥ እንደ ዓለማ እና የትግል መቀስቀሻ ተደርጎ የተወሰደዉ “ጥላቻ እና ጎሰኝነትን ነበር” አረጋዊ “በማሌሊት ዘላሊት ጽሁፉ ላይ ልጥቀስ ፣ “የሕብረት ትግሉ እንዳይፋጠን ብቻ ሳይሆን ይባስ ብሎ የተለያዩ ድርጅቶች ትምክህታዊ አመለካከት እግዶናል፣የሕብረተሰባችን ጠባብ መስፍናዊ አመለካካት የፈጠረዉ ችግር ነዉ”እየተባለ መደባዊ ወገናዊነት አበጥሮ የማይመለከት” “ፀረ አማራ” የሚል ቅስቀሳ ነበር። ባሕላዊ ትርኢቶች፣ትያትሮች፣ቀልዶች፣አባባሎች በዚህ ጠባብ መርዝ እየተለወሰ ቀርበዋል።" አረጋዊ በርሀ- ማሌሊት ዘላሊት፤፣
ር “Political History of TPLF በሚለዉ ተጠቀሰዉ በእራሱ መጽሐፉም በገጽ 163 ቀርቧል፣፣ እንግሊዝኛዉም ልጥቀስ “…Contrary to its publicly stated objective, anti-Amhara propaganda was subtly encouraged within the movement. Cultural events, theatrical performances as well as jokes and derogatory remarks were used to disseminate this poisonous attitude. Fuelling some historical grudges perpetrated by the ruling classes, the Sebhat function tried cast doubt on the possibility of living in unity with “the Amhara”.” (A Political History of the TPLF P.163 Aregawi Berhe)
በመጨረሻ በዚህ ትምህርት የመነሻ ባሕሪይ ድርጅቱ በዜጎች ላይ የፈጸማቸዉ ድርጊቶች ምንድናቸዉ?በሚለዉ እንነጋር፣፣ ድርጅቱ የፈጸማቸዉ ብሔራዊ ወንጀሎች ፣ የባሕር ወደባችንን ለጠላት አሳልፎ ስለ መስጠት ፣ ከጠላቶች ጋር ወግኖ ሳሕል እና ምፅዋ ላይ ያደረገዉ ጸረ ኢትዬጵያ ዉግያ የመሳሰሉት ራሳቸዉ የቻሉ ርዕሶች ስለሆኑ እዚህ እናልፋቸዋለን፣፣ የምንነጋረዉ በአረጋዊ/በታንድ መግለጫ ላይ ወያነ ሲገድል ሲያንገላታ ከስራ ሲያባርር ሲያስር ጎሳን መሰረት በማድረግ ሳይሆን ለመንግስቴ እንቅፋቶች ናቸዉ በሚል አምባገነናዊ ባሕሪ ተነሳ ነዉ በሚለዉ የታንድ ክርክር ብቻ ነዉ የምናተኩረዉ፣፣ ከላይ እንደተመለከትነዉ ባጭሩ የድርጀቱ መሰረታዊ ቅስቀሳዎች/ትምህርቶች እና መመርያ ጠባብ ጎሰኝነትን ያማካለ እንደሆነ አይተናል፣፣ ወያኔ የወሳዳቸዉ አብዛኛዎቹ ያገሪቱ ፖሊሲዎችም ሆኑ በግለሰብ እና በድርጅት ላይ የፈጸማቸዉ ሕገወጥ ድርጊቶች አብዛኛዎቹ ጎሳን ያነጣጠሩ ነዉ፣፣ ለዚህም ነበር በጎዴኦ እና በጊጂ ማሕበረሰብ መካከል መሬት በቋንቋ/በጎሳ እየሰነሸነ/እየከለለ “የኛ ነዉ፤የኔ ነዉ!” እየተባባሉ በሺዎቹ አርስበርስ እንዲተላለቁ ያደረገዉ፤፤ካሁን በፊት ያልተሰማ ያልተደረገ ታሪክ እና እልቂት፤፤
ድመት የአይጥ ጠላት ነች፣ ቀበሮ የበግ ጠላት ነዉ፣ ጅብ ሰዉም የእንሰሳም ጠላት ነዉ፣፣ እነኚህ በጠላትነት ከመተያየት አልፈዉ ወደ መጠፋፋት ይደርሳሉ፣፣ አንዱ አጥፊ አንዱ ራሱን ለማዳን ይሸሻል ማለት ነዉ፣፣ ወያነ ትግራይ ከመመርያዉ እና ከሰጠዉ ትምህርት ታጋዬቹም ከትግራይ ወዲያ አልፈን የምንጓዝበት አገር እና ሕዝብ የለንም ያሉትን ያህል “አማራ”የትግራይ ሕዝብ ጠላት ነዉ ከሚለዉ አቋሙ እና ትግራይ የኢትዬጵያ ኮሎኒ ናት ወይንም የመቶ አመት ታሪክ ያላት ሚኒሊክ ያቀናት አገር ናት ወይንም የአክሱም ሓዉልት ለከምባታዉ ምኑ ነዉ፣”ጭርቁ ሚያመክተዉ…” በማለት የሃገር ሰንደቃላማ በጨርቅነት ያጣጣለ…ክልልተኛነት እና ጠባብ ጎሰኛ ባሕሪዉ ስንነሳ ወያኔ በጠላትነት የሚመለከተዉ “አማራዉን እና ኢትዬጵያን” ከሆነ ቀበሮ ‘በግዋን’ ድመት ‘ዓይጢቷን’ እንደሚያጠፋት ሁሉ ጅብም እንዲሁ ጠላቱን ሲከታተል ወያኔም “አማራዉ እና ኢትዬያዊነት” ለማጥፋት እርምጃ ወስዷል፣፣ የወያኔ ጎሰኛ ቡድን ማንን እንዳጠቃ እና እያጠቃ እንዳለ ሕሊናዉ የታወረ ካልሆነ ጠነኛ ሕሊና ሊስተዉ አይችልም፣፣ሌላዉ ቀርቶ የኢንጂነር ሃይሉ ሻዉል ድርጅት “የአማራ ድርጅት”-እየተባለ የሚደረገዉ ቅስቀሳ ከምን የመነጨ እንደሆነ እነ ማን እንደሚያመነጩት እና ሃይሉ ሻዉልን ፤ደ/ር ታየ ወልደሰማያትን በአማራነት የሚከስሱ እነ ማን እንደሆኑ እና ይሁነኝ ተብሎ በዛ በኩል ዘመቻዉ እንደተጧጧፈ የፓለቲካዉን ዓየር የምትከታተሉት ወገኖች የምታዉቁት ነዉ (ከዓይጋ ድረገጽ አዘጋጅ አስከ ከአብራሃም ያየህ አስከ የጉንበት 7 መሪ ብርሃኑ ነጋ ድረስ ያለዉን)፣፣ ፖለቲካን ተንተርሶ ጎሳን ሚያነጣጥር ጥቃት አየሩ በእራሱ በወያኔ እና የወያኔ ቅስቀሳን በሚደግሙ ተቃዋሚ ነን ባዬች በጸረ አማራ ሕሊናቸዉ ተበክሏል!
መጀመርያ ወያኔ ያካሄደዉ ዘመቻ “ኮራኹር አምሓሩ” (ያማራ ቡችሎች) ወይንም “ሽዋዉያን ተጋሩ” (የሸዋ ትግሬዎች) በሚላቸዉ የትግራይ ተወላጆች ላይ “ትግሬነታቸዉን ነጥቋል”፣፣ የመጀመርያ የሕሊና ዉግያ የጀመረዉ በእኛ ላይ ነበር፣፣ ለምሳሌ የአሞራ ደራሲ አቶ ግደይ-ባሕሪሹም በመጽሓፋቸዉ ዉስጥ እንዲህ ሲሉ ለታሪክ ዘግበዉታል“የሻዕቢያ ቅጥረኛ ወያኔም ትግራይ ዉስጥ ኢትዬጵአዊነቱ ያልካደ እና እምነታቸዉን አላመነዉን ገበሬ የከተማ ወዝ አደር ምሁር ‘ኮራኹር አምሓሩ” ሸዋዉያን ተጋሩ” (የአማራ ቡችሎች) ሸዋዉያን ትግሬዎች እያለች የ ኢድህ ታጋይ ቤተሰብ ዘመድና አዝማድ የተባሉትን ሁሉ በጠቅላላ በሬና ላሙን በግና ፍየሉን አህያ በቅሎና ዶረ፤ጎተራ እህሉን ማርና ቅቤዉን እየወረሰች ለወሬ ነጋሪ ሳይቀር ..” ይላሉ አቶ ግደይ ባሕሪሹም፣፣ ይህ ወንጀል ጎሰኛነትን/የዘርን ጥላቻ ተንተርሶ የወሰደዉ እርምጃ መሆኑን አረጋዊ በርሔም ሆነ ታንድ ዉስጥ ያሉት የሚክዱት አይደለም፣፣ ይህ የዜግነትን ማንነት የሚጻረር “ ቤተሰቦችህንም ጨምሮ ትግራይ ተወልደዉ የትግራይ ተወላጅነት የላቸዉም፣ ባዕድ ነህ፤ ከማዶ ነህ..,” በማለት ትዉልድ አካባቢን የሚነጥቅ ትምክህት “የጎሰኛነት ፋሽስታዊ የጎሳ ንፅሕና/ “በሽታ” ሰዉን ከማሰር እና ከመግደል የባሰ መሆኑን ለፍትሕ ቆሜአለሁ የሚሉንን “የታንድ አመራሮች” መገንዘብ እንዴት እንዳቃታቸዉ አልገባኝም፣፣ የድርጅቱ መሪ አረጋዊ እና ግደይ ይህንን ቅስቀሳ እና ትምክህተኝነት ሲደረግ የድርጅቱ መሪዎች ነበሩና ይረሱታል ብለን አናምንም (አረጋዊም በመጽሃፉ ላይም ያወሳዉ ጉዳይ ነዉና)፣፣
ታድያ የታንድ አመራሮች “ህወሓት/ኢሕአዴግ ሰዉን የሚገድለዉና የሚያንገላታዉ ሥልጣኑ ላይ ሊያደርሰዉ ከሚችለዉ አደጋ አንጻር (ለአምባገነኖቹ አገዛዝ የማያመቹ በመሆናቸዉ ካልሆነ) እንጂ በዘሩ ነዉ ብለን አናምንም” ማለት ወያኔ በቋንቋ ከልሎ የሃገሪቱን ነገዶች እያበጣበጣቸዉ ነዉ ሲሉን የነበሩትን የድርጅቱ መሪዎች በተለይ አረጋዊ በርሄ በድርጅቱ ስምም በግልም ይሁን በኢትዬጵያ ተቃዋሚዎች ሕብረት ስም ወያኔ “ጎሰኛ” ነዉ የሚለዉን ድርጅታዊ መግለጫዉ ዛሬ “ወያኔ አምባገነን እንጂ /ዘረኛ ጎሰኛ” አይደለም ወደ ሚለዉ አቋም ለመለወጥ ያአስገደደዉ እነ ስብሓት እነ መለስን ስዩምን…. በተለይም ደግሞ “ተዋህዶ ቤተክርስትያን የነፍጠኞች መደብቂያ ነች” በማለት ዘረኛ ቅስቀሳ ያሰራጨዉ “የዋየኔዉ ጊላ/ ባርያ” ተፈራ ዋሉዋ እና መሰል ወያኔዎች ምን ከሚሉት ከዘረኛነት ባሕሪይ የሚፈዉስ ሓኪም ዘንድ ሄደዉ ታክመዉ እንደዳኑ ታንድ ሊነግረን በተገባዉ። የመለስ ወያኔ “ሰዉንና ድርጅትን ሲዘልፉ፣ ሲያንገላታ፣ሲገድል ሲያስር በዘረኛነት ተነሳስተዉ የገደሉት የበደሉት አላየንም ሲሉን ለጎሳ ሰለባዎች ለተጠቂዉ ሃገር እና ግለሰብ የንቀት ንቀት ነዉ፣፣
ወያኔ ጎሰኛ ነዉ የሚሉን ከሆነ ደግሞ “ጎሰኛ” መጀመርያ የሚያጠቃዉ ማንን ነዉ? በጠላትነት የሚያየዉን ሌላኛዉ ዘር አለ ማለት ነዉ፣፣ ዘር ቀለም ብቻ አይደለም፣፣ ዘረኛነት ‘ባህልን፣ ምግብን፣ ቋንቋን፣ አለባበስን፣ ሃይማኖትን ወዘተ….ያነጣጠረ ጥላቻ/ትችት/ዘመቻ ማካሄድ ማለት ነዉ፣፣ የጽንፈኛ ጎሳ ድርጅት መነሻዉ “በዘር ማትኮር ነዉ”፣፣ ድርጅቱ አብዛኛዉን ጊዜ ሰዉን ድርጅትን (ቤተክረስትያኒቱን ጨምሮ) ሲያጠቃ ጎሳን ተመርኩሶ ነዉ፣፣ በ1991 ዓ.ም 41 ያዲስ አባባ ዩኒቨርሲቲ አስተማሪዎች ሲያባርር፣ ጎሰኞች ሁኑ ሲላቸዉ የጎሳ አመለካከት አንከተልም፣ዘረኞች አንሆንም፣ አናዳላም አገር አንበጠብጥም፣-ስላሉ በራሱ የዘረኛ ግምገማ ተሞርኩዞ ነበር ያባረራቸዉ፣፣ ትገሬዎች ከነበሩዋቸዉም ከተባለ “ኮራኹር አመሓሩ-“ (የሸዋ ቡቹሎች) ከሚለዉ ግምገማ ነበር ያባረራቸዉ (አባሪ ተባባሪ በሚል)። አይጋ በሚባለዉ ዘረኛ እና የኩታራዎች ጭንቅላት የሚያንጸባርቅበት ድረገጽ ላይ ሲለጠፍ የነበረዉ ስለ ዶ/ር ሃይሉ አርያን መመልከቱ እራሱ የቻለ ማስረጃ ነዉ ፣፣ የሀገሪቱ ሠራዊቶች በረንዳ ላይ ከነ ቤተሰቦቻቸዉ ሲጥሏቸዉ ኢትዬጵያዊነትን ለማጥፋት እና ለማራከስ የኢትዬጵያዊነትን ጥላቻን ተንተርሶ እንደነበር ከማንም የተሰወረ አይደለም፣፣
ይህ ጽያፍ ድርጊት ብዙዎቻችን ያሳዘነ ጎሰኛ ብቻ ሳይሆን ኢትዬጵያዊያን በኢትዬጵያዊነታቸዉ ከዛ ቀን ጀምሮ እንዲጠሉ በዜግነታቸዉ እንደማይተማመኑ እና ደማቸዉ ጠኔአቸዉ ከንቱ መፍሱስን ከተመለከቱ በሗላ ደም አንብተዉ “ሃገሬ ገደል ግቢ!” ብሎ ሕሊናዉ እንዲርቅ፣ የመጨረሻ ኢትዬጵያዊነታቸዉ የተሰረዘበት ጎሰኞች የፈጸሙት አሳዛኝ ደርጊት ነበር፣፣ታንድ ወያኔ/ኢሕአዴግ ሰዉን በዘሩ አይገደልም፣ አያንገላታም አያስርም ሲል የታሪክ ጎርፍ አይፈራም?
የአረጋዊ በርሔ “ታንድ” በጎሳዉ የተንገላታ/የታሰረ/የተገደለ ካለ ማስረጃዉ ይሰጠን እና አብረን እናወግዛለን ሲል መግለጫ ሲበትን በእዉነቱ እኔ ስለ አረጋዊ ሳይሆን አረጋዊ በሊቀመንበርንትና በአባልነት የሚመራዉን የኢትዬጵያ ተቃዋሚዎች ሕብረት ማሕበር እጅጉን አፈርኩለት፣፣ ኢትዬጵያ እራስዋ እንደሀገር አሳሳቢ ሁኔታ ላይ ያደረሳት የወያኔ ጎሰኛ ፖሊሲ መሆኑን እየታወቀ “የተንገላቱ ግለሰቦች ካሉ” መረጃ ይሰጥን ሲል ታንድ እንደ ፖለቲካ ተቃወሚ ድርጅት የሰጠዉ መግለጫ ትልቅ ቡግር እንደሚጥልበት አያጠራጥርም፣፣ አንጋፋ የፖለቲካ መሪዎች ከሚባሉት ጋር አብሮ የሚሰራዉ አረጋዊ በርሔ፣ ኢትዬጵያ ዉስጥ በጎሳዉ ምክንያት የታሰረ/የተንገላታ የለም ሲል ያወኔን ነፃ ሊያወጣ የሞከረበት መግለጫዉ ለምን እንዲህ እንዳለ ማብራርያ ሊጠይቁት ይገባል እላለሁ፣፣”It was about this time that the rank and file began raising questions about fighting outside Tigrai. This whispering campaign spread, recalling the ethno-nationalist agitation of the leadership, and many fighters began running away from their regiments to their villages. Some 10,000 fighters virtually spontaneously withdrew and return to Tigray” (Young).
ይህ አሳፋሪ ታሪክ ካንድ ኢትዬጵያዊ ታጋይ ወይስ ከጎሰኛነት እና ከጸረ ኢትዬጵያዊነት አመላከከት ካሳደረ የጎሳ ነጻ አዉጪ ነበር የተከሰተዉ? አማርኛ ቋንቋ ሲሰማ እንዲሸሽ የተማረ፣ የሃገሪቱ ሰንደቃላማ ጥሎ በረሃ ፈጠር ባንዴራዉ በጠበምንጃዉ አፈሙዝ ላይ ሰቅሎ ከጠላት ሀገር ከሚባለዉ ሌላ ሃገር (ኤርትራ- ሌላ ሀገር በወያኔ አመለካከት) ተዋጊ ጋር ወግኖ ወገኑን ገድሎ ወደ ወሎ ወደ ጎንደር ጎጃም ኤሉባቡር አልገስግስም ብሎ ፊቱን ወደ ትግራይ አዙሮ የሚለግም?ይህ ጎሰኛ ትምህርት ያስተማረዉ ማን ነበር? አረጋዊ? ግደይ፣ መለስ፣ ስብሓት ስዩም…..ማን ነበር? የትግራይ ካርታና ባንዴራ ማን እና በመቸ ጊዜ ነበር የታቀደዉ? ለዚህ ጉደኛ ድርጅት ጥብቅና ተቁሞ “ግለሰቦች በዘራቸዉ የተገደሉ/የተንገላቱ/የታሰሩ ካሉ ስም ዝርዝር ይቅረብል ብሎ መከራረከር ከመቸዉ ጊዜ አብሮ አደግ የጋደኛየ የዑቑባዝጊ በየነ (አክሱም ወዲ ርዕሰ ደብሪ በየነ) እና ሌሎቹ ኢትዬያዊነት አቋም በመያዙ ግድያ ተረሳ?
በድርጅቱ ዉስጥ የነበሩት የትግራይ ተወላጆች የተገደሉት በፓን ኢትዬጵያኒዝም/ኢትዬጵያዊ አመለካከታቸዉ ለመሳፍንቶቹ ለእነ ስብሓት፣ ለእነ መለስ እና ስዩም ወዘተ..ስላልጣማቸዉ የመረሸኑ ታሪክ በኢትዬጵያዊነት እና በጎሰኛ ክልልተኛነት የተደረገ ትግል እንደነበር ከመቸዉ አረጋዊ እና ግደይ ረሱት? ይህ ግድያ የሚያሳየን ዘረኛነትን በመዋጋት የተዋደቁ እና ዘረኛነትን ለማስፋፋት ለማስተማር የተደረገ ትግል እንደነበር እንዴት ለአረጋዊ እና ለግደይ እኔ ሳስታዉሳቸዉ ያምርብኛል?
በጣም የገረመኝ ደግሞ ወያኔ ሲገድል/ሲያስር ለስልጣን ከመጣ ማንንም አይምርም ትገሬም ቢሆን ይለናል፣፣ ለዚህ ደግሞ ወያኔ ዘረኛ እንዳልሆነ ለመከላከል ሲሞክር “በስልጣን ከመጣ ደግሞ ከትግራይ የመጣ በመሆኑ የሚተርፍ ቢሆን ኖሮ አብሮአቸዉ ታግሎ የአስፈጻሚዉ አባል የነበረዉ ስዬ አብርሃ ለእስር አይዳረግ ነበር…”ይሉናል፣፣ ስየም ሆነ እነ አረጋዊ በርሄ ግደይ ከወያኔ የመጣላታችን መሰረቱ “ሉአላዊነትን” ለጠላት ክፍት አድርጎ በማስነጠቅ እና ላለማስነጠቅ ተደረጉ ምክንያታዊ ትግሎች ነበሩ ሲሉ በተለያዩ ጽሑፎች ነግረዉናል፣፣ የአልጄሪሱ ስምመነት “እንፈርም- አንፈርምም” በሚል ንትርክ እንደሆነ ነግረዉናል፡ አሁን ግን አረጋዊ እየነገረን ያለዉ “አምባገነንነት እንጂ” በጎሰኛነት/በክልልተኛነት እና ኢትዬኦጵያዊነት” መሃል የተደረገ ትግል አልነበረም ሲል ደግሞ ሽረዉታል፣፣ የትኛዉን እንያዝላችሁ?
የታንዶቹ የአረጋዊ እና የግደይ ባላዉቅም የስየ አብርሃ የማሳሰርያ ምክንያት ከኢሳያስ ኤርትራ ጋር በተደረገዉ ጦርንት ምክንያት-መለስ ኤርትራዊ/ኢሳያሳዊ ፍቅር አንገብግቦት- ስየ ደግሞ ‘ትግራዋይነት አንጀቱ ብያይልበትም በወቅቱ ኢትዬያዊነት ስሜት ገንፍሎበት እንደነበረ የሚካድ አይደለም፣፣ በበዚህም ነበር ንትርኩ የጀመረዉ፣፣ ስየ ምንም ኢትዬጵያዊነት ስሜቱ አልነበረዉምም እንበል፣ ጥሩ!ግን “ትግራይ ተደፈረች” ብሎ ኢሳያስን ድምጥማጡ መጥፋት አለበት” ብሎ ወደ አስመራ እንገስግስ ሲል መለስ ደግሞ የሚያይለዉን ኤርትራዊነት ስሜቱ ተነሳስቶ አሰረዉ እንበል (ነገሩ ከዚያ የመነጨ ነዉና)፣ ስየ እና መለስ ያጣላቸዉ ስልጣን ስኩቻ ሳይሆን ብሄረተኛነት ነበር ማለት ነዉ፣፣ ከዚህ ከሁለቱ አያልፍም፣፣ ስየ ለስልጣን ቋምጦ ነበር ወይንም ስልጣን ለመያዝ አስቦ ነበር ከተባለም መነሻዉ ስልጣን ሳይሆን “ከብሄረተኛነት ፍትጊያ” አያልፍም፣፣ ስለነበርም መለስ ወቅቱን ጠብቆ ጎሰኛ ኤርትራዊነቱን አይሎበት ትግራዊዉ ስየ አብረሃን እሰር ወረወረዉ ብንል ስህተት አይሆንም፣፣ ስለዚህ ህወሓት “ወያኔ/ኢሕአዴግ (በታንድ አጠራር) ጎሰኛነቱ አሁን በስየ ላይ አንጸባርቋል እና ወ ያኔ ጎሰኛነቱ በግለሰቦችም በራሱም ላይ አልማረም ፣፣ታንድ በዚህ ምን እንደሚለን አናዉቅም፣፣ ወያኔ ባሕሪ ጎሰኛነትን ያማከለ ማአከላዊነትን የሚያጠብቅ ነዉና አምባገነንነቱም ጎሰኛነቱም አብሮ ተላብሶታል፣፣ ወያኔ ሲሾም ሲሸልም ሲጠቅም ስያሳድግ ሲጣላህ ጎሳን፣መንደርን፣ጎጥን፣ሰርን፣ትዉልድ ሐረግን መመርያ ያደረገ ነዉ፣፣ስለሆነም የፖሊሲዉ ተጠቂ አለ ማለት ነዉ፣፣ ዘርዘር አድርጌ የወያኔ አመራር በገብሩ አስራት ላይ የደረሰዉ ዘረንኝነት እና ገበሩ አስራት ከዚያ ጥቃት ለመዳን ሲል እንዴት ወደ አድርባይነት ተለዉጦ ድርጅቱ ላይ መቆየት እንደቻለ በምስጢር አዋቂዉ አንደበት የተጻፈዉን ታሪክ ልገለጽ፣፣
በመሰረቱ ታንድ እንደ ድርጅትም ሆነ እንደ አመራር አረጋዊ በርሔ በመጽሐፉ ዉስጥ የ1969 ዓ.ም የ “ዓ.ሽ.ዓ.” ሕንፍሽፍሽ (ብጥብጥ) መነሻዉ አዉራጃዊነት አልነበረም፡ ሲል ሲከራከር የድርጅቱ ጎሰኛ ባሕሪ አዉቆም ይሁን ሳያዉቅ ሊሸፍንለት ሞክሯል። በድርጅቱ የደህንነት እና የስለላ ከፍተኛ ባለስልጣን የነበረዉ አክሱም አዉራጃ ተወላጅ “ብስራት አማረ”- “ከዚያ ያደረሰ መንገድ ሲመረመር” በሚል ተከታታይ ረዢም የድርጅቱ ታሪካዊ ጽሑፍ በሐዋርያ (ካናዳ) ጋዜጣ ላይ እና በኢጦብ መጽሄት ታትሞ የነበረዉን ለታንድ መሪዎች እና አባሎች ድርጅታቸዉ ጎሰኛ እና አጥቂ/በቀልተኛ/ቂመኛ እንደነበር በጓዳቸዉ አንደበት የተጻፈዉን መረጃ ላስታዉሳቸዉ እወዳለሁ።
ብስራት የሕንፍሽፍሹ መጠነኛ መልክ ገብሩ አስራትን እንደማስረጃ እንዲህ ሲል ያብራራልናል፣፣ “በ1969-ዓ.ም.በድርጅቱ ተነሳስቶ የነበረዉ ቀዉስ/ትርምስ (ሕንፍሽፍሽ) እያሉ የሚጠሩት የደቡብ ትግራይ ልጆች ገብሩን መሃል አድርገዉ ከሌሎች የዓድዋ እና የአክሱም ተወላጆች በማነጻጸር የሃላፊነት ቦታ (የደቡብ ሰዉ) ማለትም የእንደርታ ሰዉ በመሆኑ አልተሰጠዉም፣፣ መለስ ዜናዊ (ዓድዋ)፣ አታኽልቲ ቀጸላ፣ ሸዊት ዳኘዉ (የአክሱም ልጅ) በመሆናቸዉ የማአከላዊ ኮሚቴ ዉክልና ተሰጥቷቸዋል፣፣ ገብሩ አስራት ግን ባስተዳደር እና በመሳሰሉት ከእነሱ የተሻለ እንጂ ያነሰ አይደለም ብለዉ የመከራከርያ ነጥባቸዉ አድረገዉ እንደወሰዱት ይታወቃል፣፣ በዚህ ጉዳይ ላይ ገብሩ በአሉታም በአዎንታም ያለዉ ነገር እንደሌለ ቢታወቅም ያኔ የተሓህት መሪዎች በገብሩ ላይ ጥርጣሬ እንደነበራቸዉ ግልፅ ነዉ፣፣….”
ካለ በሗላ ግብሩ በራሱ የሚተማመን ጥሩ ባሕርይ የነበረዉ ታታሪ፣ የሕዝብ ወገን እነደነበር ራሴ ታዝቤዋለሁ፣- ይል እና “ማሌሊት በ1977 ዓ.ም. ከተመሰረተ በሗላ ግን መለስ ዜናዊ ያለዉን ሁሉ እሺ አሜን ብሎ የተቀበለ የለየለት ታማኝ አገልጋይ በመሆን ስልጣኑን ማሳደግ እና ማቆየት ቻለ።” ካለ በሗላ “በ1981/82 ዓ.ም አቤራ ላይ በተደረገዉ የማሌሊት/ህወሓት ጉባኤ ገብሩ አስራት ለማሌሊት/መለስ ለስላሰ ለም መሬት ሆኖለት ያለዉን ሁሉ በታማኝነት ለማረጋገጥ በፖሊሲያቸዉ/ባመለካከተቻዉ ለየት ያለ አቋምና ጥንካሬ ያላቸዉ ጓዶቹን {አንዳንዱም በእንደርታ ተወላጆች ላይ ሳይቀር ማለቱ ነዉ ለምሳሌ እንደ እነ መስፍን አማረ ላይ፣፣(ኮሎኔል) መስፍን አማረ በ1969 /70 ገብሩ አስራት ለአመራር ብቁ ነዉ ፣ አድልዎ መፈጸም የለባችሁም ብሎ ስለ ገብሩ የቆመ ፣ ከድርጅቱ መሪዎች ጋር የተከራከረ የእንደርታ ተወላጅ፣- የሗላ ሗላ ገብሩ ከመለስ ዜናዊ ጋር ሆኖ ስሙን በማጥፋት በመወንጀል መስፍን አማረን አመራር እንዳይወጣ እንቅፋት በመሆን ቀደም ብሎ በአዉራጃዊነት አድልዎ የተጠቃዉ ገብሩ አስራት በአድረባይነት ለመለስ ካደረ በሗላ (ለ ዓድዋዎች እና አክሱሞች.. አድሮ) ስልጠኑን ለማቆየት ችሏል-ይላል በረዢሙ ጽሑፉ አሳጥሬ ሳቀርበዉ፣፣ የተጨመረ የኔዉ) ………..ላይ ስም የማጥፋትና መወንጀል ተግባር ሲያቦካና ሲጮህ ታይቷል፣፣”
በማለት ወያነ ትግራይ አማራሮች በጎሰኛ ባሕሪያቸዉ ለትግራይ ተወላጆች ሳይቀር ያላጎበደደዉን እና ለባለስልጣኖች ያላደሩትን በአዉራጃዊነት ተሞርኩዞ የገዛ ታጋዬቹንም ሳይቀር ያጠቃ እንደነበረ ከዉስጥ አዋቂዉ ከብስራት አማረ ያነበባችሁት ጉዳይ ነዉ፣፣
ባሁኑ ሁኔታ ድረጅቱ እና ኢትዬጵያን እየገዛ ያለዉ ግለሰብ ማን ነዉ? መለስ ዜናዊ፣፣ መለስ ማን ነዉ? አሁንም በብስራት አማረ አቀራረብ ባጭሩ ላቅርበዉ “ ስለ ኤርትራ ጥብቅና ቆሞ ሁለት መጽሃፍ ሲጽፍ ሃገሬ ብሎ በመንግሥትነት ተቀምጦ ለሚመራት ስለ ኢትዬጵያ አንዲት ብጣሽ በጎ ወረቀት ያልጻፈ፣ ሃገሬ የሚላት ኢትዬጵያ ኤርትራ የመትባለዋን ሀገር ጎትታ ወደ ሗላ እንዳስቀረቻት በዉስጧ የሚኖሩ ብሔረሰቦችን በማድቀቅ መብትን ምታፍን ሗላ ቀር እና የፊታዉራሪዎች ሀገር ናት ሲል የነገረን፣፣ መለስ ዜናዊ ማለት ከኢትዬጵያ ትምሕርት አይገኝም ብሎ የሚያምን የሌሎችን ሃገሮች የትግል ተሞክሮ እና ታሪክ በማንበብ የትግል ዘመኑን ታጋዮችን ሲያስጠና ጊዜዉ ያሳለፈ ግለሰብ ነዉ፣፣ በ1980 ለማሌሊት መጽሔት እትም ባቀረበዉ የታሪክ ገጽ- ኢትዬጵያ ማለት የተቃጠለ ፊት ማለት ሆኖ የግሪክ ቋንቋ ነዉ፣ ካለ በሗላ ኢትዬጵያ የምትባል ሚኒሊክ የፈጠራት ኮሎኒያሊስቶች አፍሪካን ሲከፋፍሏት አብራ የተፈጠረች ነች ብሎ የጻፈ እና ያስተማረ፣፣ ሕዝብን ሃገርን ሰንደቃላማን የሚያንቋሽሽ በማን አለብኝነት ተገፋፍቶ በራዲዬ በይፋ ለሕዝብ የተናገረ፣፣ ሃገሪቷን ወደብ አልባ ያደረገ የዉጭ እንጂ የሃገሩ ታሪክ የማያዉቅ ያልተደረገዉን የሚዘባርቅ፣ በቀላል ቋንቋ “ኢትዬጵያን የማይወድ” ብለን መደምደም ይቻላል፣፣
በማለት ድርጀቱ እና ሀገሪቱ የሚመራት ማን መሆኑን በቀላል ቋንቋ የተመለከትነዉ ጎጠኛዉ የወያኔ ቡድን ታንድ ይህንን በበጻረር ““ህወሓት/ኢሕአዴግ ሰዉን የሚገድለዉና የሚያንገላታዉ ሥልጣኑ ላይ ሊያደርሰዉ ከሚችለዉ አደጋ አንጻር (ለአምባገነኖቹ አገዛዝ የማያመቹ በመሆናቸዉ ካልሆነ) እንጂ በዘሩ ነዉ ብለን አናምንም”-በማለት እንኳን ግለሰብ በጥላቻ መግደል ማሰር መወንጀል ማንገላታት ይቅር እና “ኢትዬጵያ እና ኢትዬጵያዊ”-የሚለዉ ሰም ሚያንገሸግሰዉ ቅጥረኛ እና ጎሰኛ ቡድን ሀገሪቱ “በኢትዬጵያዊነቷ”-ምክንያት የተነሳ ጥላቻዉ አይሎበት ሰንደቃላማዋ አዋርዶ፣ ሰድቦ፣ ለዉጦ፣ ታሪኳን ዘልፎ፣ እያሰቃያት እና እየጨመቃት ያለቺዉን ሃገር ታንዶች ወያኔ በጎሳ/በዘሩ የገደለዉ ካለ ማስረጃ አቅርቡልን ሲሉን መጪዉ ትግላችን ከሁለተኛዉ የወያኔ ቅርንጫፍ ቡድኖች ጋር እንደሚሆን ስጋቴ እየጠነከረ ሄዷል ብል የምሳሳት አይመስለኝም፣፣
ትግሉ እየጠራ እያየለ ሲሄድ እንኚህ ሰዎች ወዴት እንደሚያዘነብሉ መተንበይ አያዳግትም፣፣ ወያኔና ፖሊሲዉ የተቸ ሁሉ “በጸረ ትግራይነት”-መመደብ ሰዎቹ ከነበራቸዉ አቋም አልተላቀቁም ወይንም የወያኔ ፖሊሲ አልገባቸዉም ወይንም ለ18 ዓመት የሚሰጡት/ሚተመዘገቡት የጎሳ ሰለባዎች አና ግጭቶች “የነፍጠኞች ዘገባ/ወሬ/አሉባልታ…..”-ናቸዉ በሚል ስሕተት ዉስጥ እየወደቁ ናቸዉ ማለት ነዉ፣፣ለምሳሌ ትግራይ መገንጠልዋ አይቀርም፤ ወይንም ወያኔዎች የትግራይን ሕዝብ ከኢትዬጵያ ለማስገንጠል እያቀዱ ነዉ ወዘተ…ወዘተ.. የሚል ጥርጣሬ በጻፉ ቁጥር “ይህ የሃይሉ ሻዉል፤ ይህ የአማራዎቹ ቅዠት፤ ይህ የደርጎቹ፤ይህ ቅዠት ነዉ፤ይህ የደ/ር አሰፋ ነጋሽ ጸረ ትግሬ ፕሮፖጋንዳ ነዉ…ይህ የዲያስፓራዎቹ ኤክስትሪሚሰት ዉሸት ነዉ ….እያሉ በሰነድ የተደገፉ ዕዉነታዎችን በጸረ ትግራይነት በመመደብ ራሳቸዉን ሲያወናብዱ ይታያሉ፤፤
አምና 22-ገጽ ያካተተ ከመለስ ዜናዊ ተለቀቀ ምስጢራዊ ሰነድ “ትግራይ ካስፈለገ ራስዋን ችላ ለመጓዝ እንድትችል በሚሊየነሙ ዘመን ያቀደዉ ምስጢራዊ ዕቅድ ‘ኢንዲያን ኦሽን” የዘገበዉን ላሁኑ ወደ ጎን በመተዉ Two Groups of the TPLF and Two Issues of Ethiopia By Tesfay Atsbeha, and Kahsay Berhe SEPTEMBER 2002 ከዚህ በታች በቅንፍ የሚነበበዉ የትግራይን የመገንጠል ምስጢር ዛሬም ህያዉ እንዳለ እንገነዘባለን፤፤ ምስጢሩ በተዘገበዉ ዘገባ ስንመለከት አረጋዊ በርሀ ከድርጅቱ ከተሰናበተ በሗላ ሌሎቹን ምስጢሮች በመደበቅ ስለ ትግራይ መገንጠል ብቻ በሚመለከት እነማን አቅደዉት እንደነበር አጋልጧል፤፤(አረጋዊ፤ግደይ፤ስየ፤ገብሩ፤አዉዓሎም፣አረጋሽ.…ከድርጅቱ ከተሰናበቱ በሗላ ለምን አስካሁን ድረስ በምስጢር የተያዙ ብዙ ሰብአዊ መብት ጥሰቶች (ግድያ፤ግርፋት “ሰቆቃ”-አፍኖ መሰወር፤ ….) የድርጅቱን የወንጀል ምስጢሮች ማጋለጥ እንዳልፈለጉ መፈታት ያለበት እንቆቅልሽ ነዉ፤፤ የትግራይን መገንጠል ታሪክ በ አምባሳደር አዲስ ዓለም ባሌማ ሳይቀር ዉጭ ላሉ የትግራይ ተወላጆች ምን ይል እንደነበር በተስፋይ አጽበሃ እና በካሕሳይ በርሀ የተጻፈዉ ምስጢር ያንብቡ “….The reaction of the members of the TPLF was confused, when they simultaneously heard the news about the manifesto and the fact that it was opposed by the EPLF. Kahsay remembers Asfaha Hagos, one of the founding leaders asking him if anyone had ever mentioned the word secession the previous year. They could not dismiss the criticism of the EPLF as a fabrication because they were confronted by a manifesto which was supposed to be theirs. But the opponents of secession and the authors of the manifesto in the leadership joined hands after some outbreaks of initial emotions and created the impression that all were responsible for the manifesto. The names of the authors of the secessionist manifesto were not known to none- CC members of the TPLF for more than 10 years, until Aregawi Berhe disclosed them after he was forced to leave the TPLF and MLLT by Meles, The problem caused by the first program did not develop into a crisis. Although the members of the CC had hidden their differences on national sovereignty, the cadres of Meles, like Addisalem Baliema (for instance in a discussion on 6.6.1988 in Cologne) were agitating for a referendum for the people of Tigray till the eve of the ascent of the EPRDF to power. Since the relative military strength of the TPLF convinced him that he can control the whole of Ethiopia, Meles seems to have at least postponed the secession of Tigray.”
ይህንን አደጋ ላነበቡ ተቆርቋሪ ኢትዬጵያዉያን ለጊዜዉ “በይደር” የተላለፈዉ የትግራይ ሪፑብሊክ ግንጠላ እቅድ ስያነብቡ፤ ስብሓት ነጋ፤ መለስ ዜናዊ እና ገንጣይ ተባባሪዎቻቸዉ ባላቸዉ ያልተቋጨ እቅድ መሰረት እዉን ለማድረግ ወደ ትግራይ የሚያግዙትን የልማት የባጀት ያቅርቦት፤ እንዲሁም ሥልጣን ከወያነ ትግራይ በመጣዉ ቡድን የመያዙ ጉዳይ በጣም አስጊ እና አጠራጣሪ ሆኖ ሲያገኙት ፤- ተቺዎቹ በዚህ አንጻር የሚሰማቸዉ ስጋት ቢሰነዝሩ “ጸረ ትግሬ”-የሚለዉ መልስ አብሮ አይሄድም፤፤ ሕዝብ እንደ ሕዝብ የሚጠሉ የሚዘልፉ ግብዞች የሉም ማለት ግን አይደለም፣፣በየነገዱ መጥፎ ግለሰብ እንዳለ ሁሉ ከትግራይም ከአማራዉም ከማንኛዉም ፍጡር ጥላቻ የሚሰነዝር ሞልቶ ተርፏል፤፤
በመጨረሻ ኢትዬጵያን እየገዛት ያለዉ ቡድን የወያኔ ትግራይ ትግሬዎች (የትግራይ ተወላጆች መሆናቸዉን መዘንጋት የለብንም) መሆናቸዉን በሚቀጥለዉ አንድ ፍርድ ባጣ ኢትዬጵያዊ ዜጋ ልደምድም እና ይሄንኑን በጸረ ትግራይነት ሰዉየዉን እንደማትከሱት ተስፋ አደርጋለሁ፤፤
“ዉሻ ነከሰኝ ብሎ ለጅብ አይነግሩም”
(ከወያኔ ትግሬዎች ፍርድ ቤት) ከሕሊና ፈረደ
ይህን በርእሱ ላይ የተጠሰዉን ዘይቤ በችሎት ላይ የገለጻዉ አንድ ፍትሕ እንደማያገኝ የገባዉ ተከሳሽ ነዉ፤፤ ነገሩ እንዲህ ነዉ፤ የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 2ኛ ወንጀል ችሎት ስብሳቢ ዳኛ ትግሬ ናቸዉ፤ አቶ ሐጎስ ወልዱ ይባላሉ፤፤ እሳቸዉ የፍርድ ቤቱ ምክትል ፕረዚዳንት ናቸዉ፤፤ በ1989ዓ.ም. በግድያ ወንጀል ተከስሶ ከእሳቸዉ ችሎት የቀረበዉ ይህ ተከሳሽ “ገደልከዉ የተባልኩት ሰዉ ባለቤቴን ዉሽምነት ይዞ ሲያማግጥ የነበረ ባለጊዜ ትግሬ ነዉ፤፤ የገደልኩትም እጅ ከፍንጅ ይዤዉ ነዉ፤፤ ለምን ገደልከዉ እያሉ እያሉ ትግሬ ፖሊሶች ሲያሰቃዩኝ ቆይተዋል፤፤መዝገቡን ከፖሊሶች ተቀብሎ የከሰሰኝ ትግሬ ዐቃቤ ሕግ ነዉ፤፤ ወህኒ ቤት የሚጠብቁኝ ትግሬ ፖሊሶች ናቸዉ፤፤ አሁን ክሱን ሊያይ የተሰየመዉ ሰብሳቢ ዳኛዉ ጣልቃ ገብተዉ ሊያስቆሙት ይሞክራሉ፤፤ ተከሳሹም “እኔ የምናገረዉ በግራና ቀኝ ለተቀመጡት ዳኞች ነዉ፤ ለአንተማ “ዉሻ ነከሰኝ ብየ ለጅብ አይነግሩም የሚባለዉን ዓይነት ነዉ።” አላቸዉ። ኢትዬጵያን ረጅስተር ፌብሩዋሪ 1998 (በፈረንጅ) ገጽ 55 ) ከላይ ያነበባችሁት እሮሮ፤- የዕለቱ ችሎት የተከፈተዉ እነ ዶክተር ታየ ወልደሰማያት ፍርድ ቤት ቀርበዉ በነበሩበት ዕለት የተከፈተዉ የችሎት መክፈቻ በአንድ ፍትሕ እንደማያገኝ ያወቀዉ ከላይ የሰማነዉ ተከሳሽ የተሰማ ችሎት ነበር።
የወያነ ትግራይ ፖለቲካ በጠባብ የጎሳ ፖለቲካ የተመሰረተ እና ጥላቻን ተንተርሶ በአንድ ጎሳ ላይ ያነጣጠረ ጥቃት የፈጸመ እና ሀገርን በማፈራረስ ያቀደ ድርጅት መሆኑን የታንድ አመራር አባላት በራሳቸዉ ሰነድ የሰነዱት ዛሬ ተመልሰዉ ““ህወሓት/ኢሕአዴግ ሰዉን የሚገድለዉና የሚያንገላታዉ ሥልጣኑ ላይ ሊያደርሰዉ ከሚችለዉ አደጋ አንጻር (ለአምባገነኖቹ አገዛዝ የማያመቹ በመሆናቸዉ ካልሆነ) እንጂ በዘሩ ነዉ ብለን አናምንም፣፣ በዘር ቢሆን ኖሮማ ከላይ የጠቀስናቸዉ የትግራይ ልጆች እና ያልዘረዘርናቸዉ የትግራይ ተወላጆች (በወያኔ)-ባልተገደሉ ነበር። በዘሩ የተገደለ/የታሰረ ሰዉ ማስረጃ የለንም፡ ካለም ይቅረብልን እና አብረን እናወግዛለን።” በማለት ማስረጃ አቅርቡልን ሲል የበተኑት ድርጅታዊ መግለጫ ሁላችሁም እንደኔዉ ሳይደንቃችሁ እንደማይቀር እርግጠኛ ነኝ። ባንድ ራስ ሁለት ምላስ።/-/-/ ጌታቸዉ ረዳ September 8, 2009 www.Ethiopiansemay.blogspot.com
Wednesday, September 9, 2009
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
1 comment:
A very transparent and balanced commentary of an Ethiopian (Tigrian) David confronting head-on to a narrow minded Goliath in the same province.
What a fascinating piece!
With eternal respect
O. Ujilu
Post a Comment