Friday, January 9, 2026

በእኛነታችን ላይ የተዘመተብንን የተቀነባበረ “ራስን” የማርከስ “ኢትዮጵያን” የማንኳሰስ ባህሪ ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay) 1/9/26 ክፍል 2

 

በእኛነታችን ላይ የተዘመተብንን የተቀነባበረራስንየማርከስኢትዮጵያንየማንኳሰስ ባህሪ

ጌታቸው ረዳ

(Ethiopian Semay) 1/9/26 

ክፍል 2

ይህ ክፈል 2 ትችት ፥«ኢትዮጵያዊያን ፈላሻዎችን በሚመለከት ቤተ እስራኤል የሚለው ቃል ምንም አይነት የነገድ ፍቺ የለውም! ይህ የኢትዮያን ማሕጸን መደፈር ነጋሪ ምልክት ነው!» ከሚለው ባለፈው ሰሞን በክፍል 1 ቀርቦ ከነበረው ትችት የቀጠለ ክፍል 2 ነው። መልካም ንባብ

ባለፉት 50 አምታት በላይ ስንቶቻችን በማንነታችን እንደተዘመተብን የምናውቅ መሆናችንን ባላውቅም፤ ጥቃቱ ምንኛ ሥር ሰድዶ እራሳችንን በማጣትእራስ ፍለጋቀውስ ገብተንበተጠነጠነብን ገመድገብተንወጥመዱን መበጠስ አቅቶን የገዛ ሰውነታችንነክሰን እየጐተትንየራስ ጉዳተኞች ለመሆን እንዴት እንደበቃን ከተሰነዘሩብን የተለያዩ ጠቃቶቻችን በማን ላይ እንዳነጣጠሩና በእነማን ተዋናይ አጥቂዎች እንደተከናወነ ይህንን ጥቃት ለማስርዳት ጠቂቶቻችን እጅግ እልክ አስጨራሽ በሆነ ክርክር ውስጥ ያለንን ሁሉ መስዋዕት ሰጥተናል።

በጥቃቱ ዘምቻ ለምን እንደተጠቃና አጥቂዎቹ እነማን እንደሆኑ ሕዝቡ እየነቃ መምጣቱ ያደረግነው ረዢም የትግል አስተዋጽኦ ፍሬ እያፈራ መምጣቱ ምልክት ቢሰጥም፤ የተፈለገው ያህል ግብ ግን አላስገኘም።አሁንም ቀጣይ ትግል እየጠየቀን ነው። በሕይወት እሰካለን ድረስ ያለንን ሁሉ እንሞክራለን የተቀረው ትግል ደግሞ ላዲሱ ትውልድ አስይዘን እንዲቀጥሉበት መንገዱን እያሳየናቸው እንገኛለን።

 የጥቃታችን ብዛት አቅማዳው ሞልቶታል። በዩሉኝታ ቢስ የውስጥ ባንዳዎች እና በውጫ ጠላቶች ቅንብር ከተሰነዘሩብን ዓይን አውጣ ጥቃቶች (Subversion) መካከል፥

 1ኛው-ጥቃት

ባሕራችንን ያጣንበት «በዓረቦችና በምዕራባዊያን» የተደገፈው የባሕር ወደቦቻችንን ያሳጣን ኤርትራን የማስገንጠል  ሴራ  ሲሆን፤

2ኛው ጥቃት

በፋሺት ጣሊያን ወራሪዎች ፖሊሲ የተቀረጸው   ሺስት ፖለቲካ የሚያምኑ የወያኔ  ታጣቂዎች የመሰረቱት በኢትዮጵያ ምድር ውስጥ በትግሬዎች መንግሥት የተደነገገው አፓርታይዳዊው በቋንቋ፤ በደምና በአጥንት ጥራት መድቦ የለየ  እሰካሁን ድረስ ስራ ላይ ያለው የነገድ አስተዳደር ሲሆን

 3ኛው-ጥቃት

 ሰሞኑን በክፍል 1 የተነተኩት ”እኛ እስራኤሎች እንጂ ጥቁር አፍሪካ ኢትዮጰያዊያን አይደለን" የሚሉ አፍሪካነታቸውንና እናት አገር ኢትዮጵያን የካዱ የፈረንጆች አገር የናፈቃቸው “ቤተእስራል” ነን ብለው ራሳቸው የሚጠሩ “በአሪካ የሲ. አይ. ኤ. እና “የእስራኤል” ሞሳድ የስለላ ድርጅቶች ቅንብር በኢትዮጰያ ማህጸን ላይ የተቃጣው የጥቃት ዘመቻ “ ነው።

ዛሬ በክፍል 2 የምንመለከተው  ካለፈው ክፍል 1 የቀጠለ ነው።

ሰሞኑን በዓጋዓዚያን ፌስቡክ ላይ ተለጥፎ ካነበብኩት ቀልቤን ከሳበው የወዳጄ የዓምደ ጽዮን ዓጋአዚን ጽሑፍ አሽሽየ ካቀረብኩት ዘለላ ልጀምር፡ እንዲህ ይላል፤

«የእስላሞች የክርስትያኖችና የተለያዩ ሃይማኖት ዕምነት ተከታዮች ምድር፥ የነገሥታትና የአፄዎች ሀገር ፥ የሥልጣኔ መስራች፥ እስከ ሕንድ ውቅያኖስ የተዘረጋ የምድርና የባሕር መስመር ገዢዎች የነበረን ፤ ፈሪሀ እግዚአብሔር ያላቸው፣ ምድራዊና ሰማያዊ ሕግ ያጠኑ፡ ዓለም የዘገባቸው ጥናታዊ የባህልና የቅርስ ባለቤቶች ፤ የርሕሩሃን ፣የጥበበኞች ፤ የፈላስፎች ፤ የዘማሪያን፤ የፈዋሾችና የአርበኞች ሀገር ፥  የደጋጎቹ ቅድሥት ሀገር ኢትዮጵያ፥ የአግአዝያን ጥበብ ተረካቢትዋ ፥ በቸኛዋ የልሳን እና የጽሑፍ አፍላቂትዋ አፍሪካዊት የትልቅ ሕዝብ ሀገር፡ ያጠቁዋትን አጥቀታ ዳግም የመነሳት ታሪክ ያላት፤የመላ ጥቁር አሕዛቦች የነፃነት ምልክት፤ ስትጠቃም ክርስትያኑንም እስላሙም ሌላውም በጉያዋ አቅፋ፤ እጆችዋን  ወደ ፈጣሪዋ ወደ «አምላከ ኢትዮጵያ» የምትዘረጋ በገናናዋ ምድር እንድወለድ ኢትዮጵያዊ አድርጎ የፈጠረኝ- “አምላከ ኢትዮጵያ”’ ሁሌም የተመሰገነ ይሁን።አሜን»

ይላል አሻሽየ ከጻፍኩት የወዳጄ ጸሐፊ ‘ዓምደ ጽዮን ዓጋአዚ’ ጽሑፍ።

ይህ ካልኩ ዘንድ ወደ ሐተታየ ልግባ

ፈላሻዎቹ ‘’እኛ አፍሪካዊያን (ኢትዮጰያዊያን) አይደለንም፤ እኛ “ከፈረንጆች የተገኘን ዘር” ነን ቢሉም፤ ፈረንጆቹ (ፈረንጅ እያልኩ  የምጠቀምበት ቃል ምክንያት ባለፈው በክፈል 1 ገልጫለሁ፡ ዛሬም እንደገና ልድገመውና ፤ እራስዋ “ዶ/ር ጸጋ መላኩ” እስራኤልን “የፈረንጆች አገር” ብላ ስለምትጠራ ነው ፈረንጅ የምለው። ፈረንጅ የሚለው ቃል እንደምታውቁት “ነጭ” ማለት ነው) ፡ በዚህ እሳ «ቤተ እስራኤሎቹ» (ፈረንጆች) ነን ቢሉም፤ ፈረንጆቹ «ከልባቸው» የኛ ወገኖች ይሁዲ ናቸው ብለው ሳይሆን ፤ ሃያምኖታቸው “ይሁዲ” ሰለሆነ እንጂ በዘራቸው ወይንም በደማቸው አይቀበልዋቸውም።

ለዚህም እራሱ የእሰራኤል መንግስት የፈላሻ ሙራ  ክርክር የተከታተላችሁ ካላችሁ «የፋላሻ ሙራ የአይሁዶችን የአይሁዳዊነት ደረጃ እውቅና አልቀበልም፤ አላምንበትም» ብሎ ነበር: ምክንያቱም ሲገልጽ «ቅድመ አያቶቻቸው ክርስትናን ስለተቀበሉ እውነተኛ አይሁዶች ናቸው ብየ አልቀበላቸውም» በማለት ጥቂቶቹ በስንት መከራ ሲቀባላቸው በዙዎቹ አላመናባቸውም።

ይህ የሚያሳየን “ሃይማኖታቸውን እንጂ አይሁድነታቸውን እንዳልሆነ ግልጽ ነው»። አይደለም እንዴ? ስለዚህ ነው የነዚህ ወገኖቻችን ማንነት ጥያቄ ውስጥ የገባው። እስራኤ በይሁዲ ሃይማኖት ተከታይነት የምታምን  በJewish religious-ethnicity ”ሃይማኖታዊ ጎሰኛነት”  እንጂ " -«የአይሁድ ነገድነት» የሚቀበሉት ለፖለቲካ ፍጆታ እንጂ በዘርነቱ እስከዚህም ናቸው።  እንዲህ የምለውም ከራሳቸው  በማስረጃ በመነሳት ነው።

ከነዚህ ወገኖች ጋር መከራከር የጀመርኩት ዛሬ ሳይሆን ሱዳን ውስጥ በፋርማሲስትነት ስም (NGO ሽፋን)  ወደ ሱዳን ተልኮ በሞሳዶች የተቀነባበረው የፈላሻዎች የማስወጣት ዕቅድ በድብቅ ሥራ ሲሰራ እንደነበር ሲታወቅበት በኋላ እንደሰማሁት ከሱዳን በድንገት ሾልኮ ከውጣ ውጭ አገር ብዙ አመት የኖረ ‘’ቀይ ፤ መልከ መልካም፤ እጅግ ትዕግስተኛና ዝምተኛ’’ ከሆነው ከዚህ ኢትዮጵያዊ ጋር፤ በወቅቱ “ሳይመን” ከሚባል እንግሊዛዊ የUNHCR የስደተኞች ዋና መርማሪ (ኦፊሰር) አለቃየ በኩል ተዋውቀን ፤ስለ ወቅቱ የሃገራችን ፖለቲካ እና የኒመሪ ሱዳን አንስተን ስናወራ ፤ መጨረሻም የነዚህ ፈላሻዎች ጉዳይ በኢትዮጵያ ኑሮና ማንነት በጎን በጎን እየሰነዘርብኝ ጠይቆኝ ስናወራ፤ አለን የሚሉት ችግር ካለ በደል የደረሰው በነሱ ብቻ  ሳያሆን ሁላችን ጋር የደረሰ የማይመች አስተዳደርና ባሕል ሰላለን ለነሱ ልዩ አይሆንም ብየው አሁን እነ ዶ/ር ጸጋ መላኩ እንደሚናገሩት እሱም ተመሳሳይ ክስ ሲያቀብ ሰምቸው ዛሬ ለእነ ጸጋ የምሞግተው አይነት አስተያየት ሰጥቸው እንደነበር፡ ሆኖም ወዳጅነታችንን ተጠናክሮ ባለበት ወቅት የሱዳን መንግሥት ስለ ነቃበት ጠፋ የሚል ሰማሁ ። በቅወቱ ሰውየው በጣም ቁጡብና  አስተዋይ ሰለነበር ፤ የዚህ ዓይነት ሥራ በደብቅ ይሰራ እንደነበር ምንም ፍንጭም አልነበረኝም ፤«ታሪኩን ስሰማ ነው የገረመኝ»።

 ለበርካታ ሺሕ አመታት በእስራኤል አምላክ እንድንምል ተደርገን መቆየታችን ሳስበው በመሰሪ ጠላቶቻችን ዓረቦች በኩል እስካሁን ድረስ ያልተወን ከዘመነ አከሱም ጀምሮ የተዘረጉብንንን የጠለፋ ዕንቅፋቶች እንዳይበቃን ፣ በዚህ ዘመን ደግሞ የአካላችን ክፋዮች የሆኑት ወገኖቻችን፥ ኢትዮጰያዊያን አይደላችሁም ተብለው  «የብረዛ ሥራ» (ሳብቨርዥን) ተሰርቶብንና ተሰረቶባቸው እነሆ  ወገኖቻችንመራመድ እንኳ የማይችሉ አዛወንቶች በሰው ጀርባ እየታዘሉ  እትብታቸው ከተቀበረበት አገር እንዲነቀሉ ሲደረግ ማንነታቸው የማያውቁ ሕጻናት የሰው ሃገር ስንደቃላማ ግምባራቸው ላይ ተተክሎባቸው በገፍ ወደ እስራኤል እንዲጎርፉ ተደርጓል።

 የሚገርመው እንዴት ወደ ኢትዮጵያ እንደመጡ ሳይነግሩን.....የ 3000 አመት የቅዠት ትረካቸው ውሃ እንደማይቋጥር እያወቁ በፈጣጣ ዓይን ሲዋሹ ማድመድጥ የሚገርም ዘመን ነው።

 3000 አመት (በነሱ ቀዥታም ትረካ አተራረክ) ኢትዮጵያ ውስጥ ስንኖር እስራኤሎች እንጂ ኢትዮጰያዊያን አይደለንም ቢሉም እኛም ለ3000 አመት በደም ፥ በአጥንት እና በሥጋ ስለተዋሃዱን (በነሱ ትረካ እንሂድ እና) የኛ ደም በሴራ ወደ ፈረንጅ ሃገር  መሻገሩ የመቃወም መብት የተጠበቀ ነው እንላለን።አንድ ከዚህ መጣ የማይባል የውጭ  ሰው ከጉያው ልጁ ፤ እህቶቹና ወንድሞቹ ሲነጥቁት እንድሚጮኸው ያህል የኔ ጮሆትም በዛው መንገድ ይታይልኝ።

ከሱዳን ውስጥ የሞሳድ አባል ነው ከተባለው ከገጠመኝ በኋላም ሌላ ደግሞ ካንዲት «ሃና መከተ» ከምትባል እስራል የምትኖር ፈላሻ ጋር በ2012 (በፈረንጆች ዘመን) ለረዢም ወቅት ክርክር አድርገን ነበር። ከገረመኝ ክርክርዋ አንዱን ልጥቀስላችሁ፤ እንዲህ አለቺኝ፡

«እኔም ሆነ አያት ቅድመ አያቶቼ ለ-2500 ዘመን ኢትዮጵያ ስንኖር እስከ እኔ እድሜና ልጆቼ እድሜ ድረስ በተለይ አንተና እናት አባትህ፣ አያት ቅድመ አያቶችህ ይህን ያህል ዘመን ሰው መሆናችን ዘንግታችሁ "ፈላሾች" "ካይሎች' "ሰው በላዎች" ቀን ሰው ፤ ማታ ጅብ"፣....ወዘተ እያላችሁ ስትሰድቡንና ለዚህች ኢትዮጵያ ለምትባል ሀገር እንዳልተዋደቅንላት እርስትና ሀብት መሬት የላችሁም እያላችሁ ከሰው ሳንቆጠር እንድንኖር ማድረጋችሁን፣ በተለይ እናንተ አማራዎቹ ባለጊዜ የነበራችሁት፣ እንደዛሬ ሳይሆን! ትዘነጋዋለህ ብዬ አላስብም።

ምንም እንኳ አንተና ቤተሰቦችህ የተጠናዎታችሁ ሁዋላ ቀር ባህል አለቃችሁ ብሎ፣አጽማቸውን እየፈነቀላችሁ መድሃኒት እያላችሁ አንገታችሁ እንደምታስሩት ብናውቅም፣ እናንተ እናነተ አማራዎች የወላጆቻችን አጽማቸው ያረፈበትን ለም መሬት እየፈነቀላችሁ በማረስ እህል እያበቀላችሁበት መሆኑን ብንረዳም፣ አንድ ቀን ጥሩ አስተዳደር ሲሰፍን መልሱን ትሰጡናላቸሁ ብዬ አምናለሁ።>>

ስትል ልክ እንደ ዶ/ር ጸጋ መላኩ እስዋም እነሱ ሌላውንም ሰው በፈንታቸው የሚያዩት እና የሚያደርጉትን ይደብቁና የነሱ በደል “እያገዘፉ” እንዲህ ተባልን የማለት «በዩኒፎርምቲ» (ቪክቲማይዘሽን) ባሕል አድርገውት «ከሃገር የመውጪያ መሸፋኛ» አድርገው ተጠቅመወታል።

 ፈረንጆቹም ይህንን ለዕቅዳቸው አመች ሆኖ ሰላገኙትም «የተጎዳሁ ለቅሷቸው» እጥፍ ድርብ አድርገው ያስተጋቡላቸዋል።

የኔ መልስ እንዲህ ይላል፤

« አንቺ እንደምትቀባጥሪው ኢትዮጵያ ውስጥ ርስትና መሬት ለፈላሻዎች እምነት ተከታዮች ብቻ የተከለከለ አልነበረም ። በነገራችን ላይ ፈላሻዎች ከብቶችና መሬት ነበራቸው። የራሳቸው በነጻ የሚኖሩበትና፤ አካባቢያቸውን ከማንኛውም ማሕብበርሰብ በበለጠ የሚቆጣጠሩት መንደር ነበራቸው (Wanderings among the Falshas in Abyssinia- by Henry Arron Stern) የሚለው 18ኛው ክ/ዘን የጻፈውና ዋና ዋና የተባሉት በስም የጠቀሳቸው የዘመኑ የፈላሻ መሪዎች ከይሁዳ ወደ ክርስትና እምነት እንዳጠመቃቸው የጻፈልሽን “ሚሺነሪ” እይው።

 ለመሆኑ “ስደተኛ ነኝ” ካልሺስ ‘መሬት እና ርስት አልሰጡኝም ማለት ትችያለሽ? ባንዳንድ ቦታ የተከለከሉበትም ከኖረም እገዳው ለፈላሻዎች ብቻ አልነበረም፤ እሳለሞችም ነበሩ እኮ። አንቺ ብቸኛ ተጠቂ ያደረገሽ ማን ነው? አማራም እኮ ትግራይ ውስጥ በተለይ “አክሱም” ውስጥ መሬት  የለውም።

በምስራቅና ደቡብ አካባቢ ክርስትያኑም እስላም መንደር ሄዶ ቤተክርስትያን መስራት የመይፈቀዱለት፣መንደሮች አሉ። እስላሙም እንዲሁ (አክሱም ከተማ ብቻ) ፥አማራም ከትግሬ በጋብቻ ለመጋባት በአሳር ነው። ትግሬ ለትግሬ ሆኖም “ደሙ አጥንቱ፤ጨዋነቱ” እየተመረመረ፤እየተቆጠረ፡ ነው የሚጋባው። የተወሰኑ ጐሳዎች ትግራይ ውስጥ መሬት በርሰትነት ወይንም በጉልትነት አንዲያርሱ አይፈቀድለትም።

ዓፋርም እኮ ትግራይ መጥቶ መሬት - ርስት አይቀበልም/አይፈቀድለትም።ዓፋሮችም እንዲህ ቤተከርስትያን መስራት አይቻልም። ትግራይ ውስጥ በሁሉም ጐሳዎች ስም “ትግራይ ክልል” በሚል የመጠርያ የተጠሩ ይሁኑ እንጂ ለተወሰኑ ትግርኛ ተናጋሪ ትግሬዎች ብቻ የተከለለ መብት ነው። ማንም ትግሬ ኩናማ መንደር ሄዶ መሬት ማረስ ይችላል። ኩናማ ወይንም ዓፋር ግን አክሱም/ዓድዋ ሄዶ ማረስ አይችልም።

 የአክሱም አንጠረኞች፤ሸማኔዎች፤የነጠላ ጥበብ ጠላፊዎች፤እስላሞች፤አማራዎች…. ከሕብረተሰቡ ብዙ የስድብ እና የጋብቻ ክልከላ ነበራቸው።

ስለዚህ የፈላሻ እምነት ተከታዮች ብቻ ተጠቂ ነበርን የምትይው “ታሪክ አላዋቂነትሽን” የሚያሳይ ብቻ ሳይሆን “ጭፍን፤ገራገር፤የዋህ፤ተላላ” መሆንሽንም ያሳያል» በማለት መልስ ሰጠኋት።

ትቀጥልና በዙ ጅላጀሎች እና ኢትዮጰያዊያን ፈላሻዎች በጅልነት ወይንም ባታወቀ ምክንያት «ወርቅ ማንጠር ፥ ሰፌድ እና እንስራ ፥ እንዲሁም ሸክላ ጥበብ ምስራትን ፈላሻዎች ከእስራኤልዘውት የመጡት ጥበብ ነው እያሉ የሚያስቅ ጅልነት ሲሰብኩ መቆያታቸውና ጥገኝነት በሚጠይቁ ፈላሻዎች ያልሆኑ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ስደተኞች ላይም ያላትን ንቀት የታዘብኩት ከዚች ሴትዮ  ጋር ያደረግሁት ክርክር እዩና ከኔው መልስ ተማሩበት።

እንዲህ ትላለች

«<<አኔ የዚህችን ሀገር መሬት አየር ማረፊያ ላይ እንደረገጥኩ ነው ዜጋ የሚለው መታወቂያ ያለልመናና ደጅ ጥናት የተሰጠኝ። ግሪን ካርድ፣ ዩ.ኤን.ኤች.ሲ.አር፣ ሁማን ራይትሰ-ዎች፣ .....ወዘተ ብዬ ለምኘና የሆነ ያልሆነውን ቀባጥሬ አይደለም የተቀበልኩት።>> ስትል ለስደተኞች ያላት ቀት ስትገልጽ፡

የኔው-መልስም-እንዲህ-ይላል፡

አንቺ አፍሪከዊ አይደለሁም “ይሁዳ ነኝ” ብለሽ እስራል አገር ስትደርሺ ‘አየር ማረፊያ ላይ” የመግቢያ ወረቀት ሰጥተውሽ ስለገባሽ ያለ ምንም ችግር አይሁድ ሆንሽ። አይሁድ አይደለንም “አፍካዊያን፤ኢትዮጵያዊያን፤ሱዳናዊያን፤ኡጋንዳዊያን፤ናጄሪያዊያን ነን” ብለው ማንነታቸውን ጠብቀው “ለመኖርያ ግሪን ካርድ አይሁዶቹን ቢለምኑ ታዲያ ምን ነውር አለው? ትንሽ ለሰው ሳይሆን “ላንቺ” ክብር ብለሽ ለሰው ልጅ፤ለስደተኛ ያለሽ ንቀትብትቀንሺ” ምን አለበት። ከሲኦል፤ ከችግር፤ ከሰሓራ፤ ከሲናይ በረሃ፤ ከአመጽ ፤ ከባርነት ሸሽተው አርግዘው የሚመጡትን እህቶቻችን “መጠያ” ለማግኘት “ቢቀባጥሩ ቢለምኑ” አንቺን የሚያኩራራ እነሱን ዝቅ አድርጐ አንደትመለከቺ ያደረገሽ የዘረኝነት የደንቁርና በሽታ “ምንነትሽ ላይ ነው ከእነሱ ልዩ ያደረገሽ?

ብዙ ገራገር ፈላሻዎች በራዲዮናቸውና በንግግራቸው አድምጫለሁ፤ አንዳንቺው ያለው መስመር የዘለለ፤ ለወንድም እና እህቶች/ወንደሞቿን ስደተኞች ፡’’የሚንቅ’ ሰው ገጥሞኝ በሕይቴ አላውቅም። በዚህ ባሽበት አስፈሪ ምጥቀት ድንገት ፓርላማ ውስጥም ሆነ መንግስታዊ ሥልጣን ባለሺበት አገር ብትይዢ እነዚህ አፍሪካዊያን ምን ታደርጊያቸው እንደነበር ሳስበው ያስደነግጣል።

ትቀጥልና እንዲህ ትላለች፤

<<(እኛ የሰራነው) ዛሬ ዘመዶችህ ሲንቁት የነበረውን ጥንት ከሀገራችን ጠበብ የዘነው የመጣን የምጣድና የድስት ስራ ጥበብ ዛሬ ዘመዶችህ ይሰሩት ገብተዋል።ሲንቁን የነበረው ዛሬ ከእኛ ጋር ለመጋባት እሽቅድድሙን ታውቀዋለህ ብዬ እገምታለሁ። እና አንተን ያንገበገበህ ወያ የወሰደው ገንዘብ?ወይስ እኔን ዜጋዬ ብላ ሳልንገላታና ሳልለማመጥ የእሥራኤልን ምድር ስረግጥ ዜግነት መቀበሌ ነው ያንገበገበህ? >>

ስትል ትጠይቀኝ እና ቀጠል አድርጋም፡

<<ድሮም በእውቀታችንና በሙያችን ኢትዮጵያን ጠቅመናት ኖረናል፣ ሰንሄድም በገንዘብ ጠቅመናት ሄድን።? >>

በማለት በገዘብ የተለወጡበትን የሽያጭ ልውውጥን ነው “ስንሄድም በገንዘብ ጠቅመናት ሄድን” እያለች ያለቺው።

 የኔው መልስም እነሆ እንዲህ አልኩኝ፤-

”የኔ-ዘመዶች-አናንተን-ለማግባት ሲሽቀዳደሙባችሁ እሺ እያላችኋቸው ወይንስ ያው “አይሁድ ላይሁድ ብቻ ነው የምንጋባው” እምቢ አላችቸው? እናንተን ለማግባት ሲሽቀዳደሙስ አንቺ ማንን አገባሽ? አይሁዳዊ ወይስ ዘመዶችህ የምትይኝን “አማራ” ነው ያገባሺው? ይህን ታሪክሽን ብትነግሪኝ በጣም አመሰግንሻለሁ።

ለምንስ ነው አናንተን ለማግባት “እሽቅድድም ውስጥ የገቡት”? ልትነግሪኝ ትችያለሽ? እንደ ሁለተኛ ዜጋ ስለማትታዩ ይሆን? እስራኤል አገር ውስጥ በጥገኝነት ሲኖሩ በናንተ ተጠልለው “ከዘረኝነት ስድብ እና ጥቃት እንድታድኗቸው ነው እናንተን ለማግባት እየተሽቀዳደሙባችሁ ያሉት? ወይስ “ቆዳችሁ ወደ ነጭነት ስለተለወጠ? እራስሺን ከዘረኞች አይሁዶች ጥቃት እና ውርደት ሳትድኚ “የኔን ወገኖችን ከጥቃት ስለማድናቸው ነው እየተሽቀዳደሙብን ያሉት ካልሺኝ” ከመገረም አልፌ ፣ምን አንደምል እውነት አሁን እየጨነቀኝ መጥቷል።

የእጅ ጥበብ ምጣድ እና ድስት አስተማርናችሁ አልሺኝ። ታዲያ ያ ሙያችሁ ከእስራኤል ነው የመጣው? በመላ ኢትዮጰያ ምድር ያ ሙያ እንዳለ አታውቂም? ምስራቅ ኢትዮጵያና ደቡብ ኢትዮጵያ ምን ዓይነት ሙያ እንዳላቸው አይተሽ ታውቂያለሽ? ሞያ የምትይው እስራኤሎች ወደ ኢትዮጵያ ያመጡትን “የምጣድ እና የድሰት ስራ ነው” ብሎ ያስተማረሽስ ማነው?

 አይሁዶች የጤፍ አንጀራ “በሙጐጐ/በሸክላ አየተሰራ ምጣድ” እየጋገሩ ይበሉ ነበር ያለሽ የትኛው አይሁዳዊ ሊቅ ነው? በየትኛው የታሪክ መጽሐፍ ነው ጤፍ እስራል ውስጥ ይበቅል ነበርና ሙጐጐውም/ ፃሕሊ(የእንጀራ መጋገሪያ እና ወጥ መስሪያ ምጣድ ድስት) እዛው ነበር የተፈለሰፈው ሎ ያስተማረሽ ማን ነው? ”ልታብራሪሊኝ ትችያለሽ”?

አይሁዶቹ ዓለም አንደሚያያቸው “ነጮች አንጂ ጡቁሮች አይደሉም”። የሚመገቡት እና የሚሰሩበት ምጣድም ያው የፈረንጆች ባህል ነው። ሙያቸውስ ተይው “ቆዳቸው እና ጸጉራቸውስ ባንቺ ፀጉር እና ባንቺ ቆዳ ለምልክት እንኳን የለም። የለሰለሰው ፀጉራቸው ፤የዓይናቸው ቀለም፤ እና ፈረንጅ ቆዳቸው ሳትላበሺ /ባንቺ ላይ አንኳ ለምልክት አንዲት ነጥብ  ሳይተውልሽ እንዴት ከአፈር የተሰራ መጐጐ/ምጣድ/ድስት “ሞያቸውን ብቻ” ወዳንቺ አስተላልፈው ኢትዮጵያን በድሰት ስራ ሙያ  አንድታሳድጓት ሸክላውን ብቻ አስይዘው ላኳችሁ?

 “የድስት፤ምጣድ ስራ” ሙያ እንድታስተምሩን ሲልኩሽ ለመሆኑ ዘመዶችሽ የነሱን መሳይ “ቆዳ እና ፀጉር” ሳይተውልሽ እንዴት “አይሁድ ነኝ” ልትይ በቃሽ? ትንሽ እንኳ ምልክት ምነው ካንቺ ‘የሰራ አካላት’ (biological) ለምልክት ሊታይ አልቻለም? ልትነግሪኝ ትችያለሽ? አልኳና በእዚህ አበቃን

 

በነራችን ላይ በዚህ ሁሉ ሳምንት የፈጀ ክርክራችን አንድ የወደድኩላት ነገር እንዲህ ያለቺውን ነው።

«እንተ አንድ ቀን ወደዚህች ቅድስት ሃገር ለመምጣትና በዚህም አድርገህ ቤተ-ልሄምና ራማላ ፍልስጤሞቹ ጋር መሄድ ከፈለክም በኢትዮጵያዊነቴ በሚገባ አስተናግድሃለሁ። በመኪናም ያለምንም ወጭ እገዛ ለማድረግ ቃል እገባልሃለሁ። ማየት ማመን ነውና!>> ስትል ደግነዋን ማስተናግደዋና በጨዋ መሰናበትዋን ወደድኩላት።

ሆኖም እርስዋ ባደግቺበት ኢትዮጵያዊ ባሕል በጨዋነት ታስተናግደኝ ፈቃደኛ ብትሆንም፤ መግሥትዋ ግን በሓሳብ የተለዩትን ሰዎች እንዲህ ያለ እንግዳ አስተናጋጅነት እንደሌለው በብዙ ሁራን ፤ በበዙ ጋጠኞች እና ጎብኚዎች ያየነው ነውና ፥ ስለ ደግነትዋ ግን አምስግኛታለሁ።

ከዚያ በፈረንጆች ዘመን ከ2012 የጀመረኩት ውይይት እነሆ ዛሬ  ደጎም ከእስራኤል የፓርላማ አባልዋ ከ ዶ/ር ጸጋ (ቀደም ብሎ በአማርኛ ክ/ጊዜ የስደተኞች (?) ሕይወት ምክርና ግንዛቤ የሚያስተላልፍ “Reka” የተባለ ራዲዮ ጣቢያ ዋና አዘጋጅ የነበረች) ጋር በኢትዮጵያዊያን ላይ ተመሳሳይ ክሕደትና እሮሮ “ዕግረኛ” ከተባለው ሚዲያ ጋር ያደረገቺው ቃለ መጠይቅ መረን የለቀቀ መሆኑን ባለፈው ሰሞን 35,698 አንባቢዎች ከፈል 1 ጽሑፌን አንብበውታል።

ትችቴ ተከታዮችዋም እርስዋም በቀና ልቦና እንዳዩትና ይህ ኢትዮጵያን የመክሰስም ሆነ አማራን የፈላሻ ጨቋኝ አድርጎ በነሱ እና በፈረንጆቹ የሚሰነዘረው ክስ መልክ እንዲኖሮው ነው የምጠይቃቸው።

የዩሁዳዎቹ ኮፊያ ራሳቸው ላይ አጥለቀው አማራን እየከሰሱ የአምርኛ ሙዚቃ ከፍቶ አዳራሽ ላይ ዳንክራ መምታት አብሮ ስለማይሄድ የትችቴ ማጠንጠኛ የማደርገውም ይህ ነጥብ ነው።

እኛ እናንተ አይደለንም ብለው በሚያስገርም ቅዠታም ትርክት ተነትርሶ ወደ 3000 አመት ሄደው እኛ እገሌ እንጂ እገሌ አይደለንም ካሉን ተጠያቂው እኛ ሳንሆን እነሱ ናቸው። ይህ ሁሉ በሃገራችን ሕዝብ እና ክብር ጠላፋ ሲደረግብን ጥቂት አገር ወዳድ ኢትዮጰያዊያን ካልሆኑ በስተቀር  ምሁራን ተብየዎቹ ሆዳሞች ሆዳምነታቸው እና ተሸማቃቂው ፍርሓታቸው ወደ ሰማየ ሰማያት አሻቅቦ የሚያሳያቸውን ወገባቸው ስለታጠፈ፥ በዚህ ጉዳይ ለአመታት ምንም ቃል አልተነፈሱም። በዚህ አጋጣሚ ሰሞኑን አንዱ (ሴት ትሁን ወንድ አላውቀኩም የተጻፈልኝን ላስነብባችሁ፤

« በሃሳብህ ባልስማማም፤ ድፍረትህ ሳየው አንተን የኛ ወገን ብትሆን አሰኘኝ» ሲል ጽፎልኝ፤ እኔ ደግሞ « ወገኔ ነህ ባትለኝም ቁጭቴን በጨዋ ደምብ ሰላየህልኝ ወይንም ሰላየሺሊኝ ፤አምሰግናለሁ/አመስግኒሻለሁ» አልኩ እና «በናነንተ መለየት እኒያ ዝምታን የመረጡ ሆዳሞቻችንስ ምን ትላቸዋላችሁ?» ብየ ስጠይቅ የሳቅ ምልክት (ኢሞጅ) ልኮልኝ/ልካልኝ፥ በዚህ ተለያየን። 

ይህ ሁሉ ሰበብ ነገሥታቶቻችን በወቅቱ በነበረው ነባራዊው የዘመኑ አስተሳሰብና ዕውቀት ለዘውዳቸው እና ለሥልጣናቸው ማጠናከሪያ ሲሉ ሥልጣናቸው ከሃያምኖት ጋር በማዋሃዳቸው እነሆ ሰበቡ እዚህ ድረስ አድርሶናል።

 መላ ኢትዮጵያ ለዘመናት ያንን በሕሊናው ተቀርፆ “የእስራኤል አምላክ” እንዲል “የአእምሮ አጠባ” ተደርጎበት የኖረ ቢሆንም፤ ዛሬ ያ ልምድ ቀስ በቀስ ማንነቱን እና አምላኩን እያወቀ ፥ በሌላ አገር ሳይሆን በገዛ አገሩ አምላክ እና መንፈስ የማወደስና የመፀለይ ልምድ ተለማምዶታል።

መዝሙራችን “የእስራል ልጆች” ተብሎ እንዲለወጥ የተሞከረውን ያህል ዛሬ በጠንካራ ኢትዮጵያዊያን ልጆቿ አሁንም በድጋሜ “የኢትዮጵያ ልጆች ነን” አንጂ “የእስራል ልጆች” አይደለንም ማለት ጀምረናል።

ይህ ዘመቻ ነው የኔ ግምባር ቀደም አስተምህሮ። አንዲህ እራሳችንን አውቀን በማንነታችን እንድንኰራ ያደረገን “የኢትዮጵያ አምላክ” በድጋሜ ክብር ምስጋና ይግባው።

ክፍል 3 በዶ/ር ዓለሜ ምሁራዊ ሰነድ እመለሳለሁ፡

በእኛነታችን ላይ የተዘመተብንን የተቀነባበረ “ራስን” የማርከስ “ኢትዮጵያን” የማንኳሰስ ባህሪ  ይብቃ። ሳብቨርዢኑ አንድ ቦታ ላይ እንዲቆም ካልተደረገ መጪው ትውልድ ራሱን እያጣ ፤ የፈረንጅ ታሪክ የፈረንጅ ባሕልና ቋንቋ እንዲናገር ተደርጎ «ያለሆነውን ነህ እየተባለ» የባዕድ ማንነት እያቀፈ አዙሪት ቀለበት ውስጥ ገብቶ በማነነት ፈላጋ ላይ ሲንከዋለል ይኖራል። ክፍል 3 ይቀጥላል

ሰላም ሰንብቱ

ጌታቸው ረዳ

(Ethiopian Semay)