Saturday, September 28, 2024

መልዕክተ ጌታቸው ረዳ ለመላው የፋኖ አመራሮች በሙሉ ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay) 9/28/24

 

መልዕክተ ጌታቸው ረዳ ለመላው የፋኖ አመራሮች በሙሉ

ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)

9/28/24

                                                                                    

ይህ ልዩ መልዕክት በ16ኛው ክ/ዘመንና በ1983 ዓ.ም በተለያዩ ወራሪ ጎሳዎች የተለወጡ የቤተ አምሐራ የክ/ሃገር ፤ የከተማ ፤ አውራጃ፤ የወረዳ ፤ የወንዝና የሸንተረሮች የስም ለውጥ በሚመለከት ነው።

ከላይ በተጠቀሱት ዘመኖች  በወረራ አመጽ ወደ ሌላ የጎሳ መጠሪያ ስም የተለወጡ ሥያሜዎች እንዳሉ ይታወቃል። እናንተ ፋኖዎች ነፃ ባወጣችሁዋቸው ቦታዎች ሁሉ በሃይልና በሴራ የተለወጡ የቦታ ስሞች ስትደርሱ ወደ ጥንታዊ ስያሜአቸው እንዲለወጡና ጥንታዊ ስማቸውም በዝረዝር ይዛችሁ እንደገና  እየሰየማችሁዋቸው ሕዝቡም በምትሰጥዋቸው የስም ዝርዝሮች እንዲጠራቸውና በፍትሕ በፖሊስ ተቋማት በመሳሰሉ ተግባዊ እንዲሆኑ ስያሜን ነፃ የማውጣት ኦፐሬሺን የትጥቃችሁ መርሃ ግብር ውስጥ በሕልውና ትግላችሁ ውስጥ በሁለተኛ ረፍ ጎን ለጎን እንዲካሄድ  ጥሪ አስተላልፍላችኋለሁ።

ስለዚህ የጥዬ ዋና መልዕክት ይህ ታስቦበት የማያውቅ አዲስ ጥሪ ተግባራዊ እንድታደርጉት ለማስተላለፍ ነው። “’’ሕግ ያልገዛው ነፃነት ሃይል ይገዛዋል”” ይህንን አስታውሱ!

ያነሳሳኝ ምክንያት ልግለጽ። ሰሞኑን አንድ የልብ ወዳጄ “ዐምሓራ-ኀብራዊ ማንነቱና ተግዳሮቱ” የሚል ከደራሲ ባንተአምላክ አያሌው ባለ 617 ገጽ የተጻፈ መጽሐፍ እንዳነብ ጠቁሞኝ አማዞን ውስጥ አግኝቼው ማንበብ ጀመርኩ። መጽሐፉን ያገኘሁት ትንናት ነው።  ደራሲው ያበገነው የኦነጎችን ደባ በማንሳት “በዛሬው አጠራር “ወሎ” ተብሎ የተጠራው የጥንት ስሙ “ቤተ አምሓራ” የኦሮሞዎች መሆኑን የሚሰብኩ ኦነጎችና ጸረ ኢትዮጵያ ሃይላትን ማቆሚያቸው የት እንደሆነና የአምሓራው ምሁር ዳተኛነትና ዝምታ ተጨምሮበት ይህ የስም ለውጥና የመሬት መስፋፋት ነጠቃ እስከመቸ መቀጠል እንዳለበት ሲጠይቁ ወደ ሕሊናየ የመጣ ለዚህ መልስ አስገኚው “ፋኖ” አንደሆነ  ተሰማኝና መልዕክት ማስተላለፍ አለብኝ ብየ ወሰንኩ።

ይህም ተግባራዊ ለማድረግ መርሃ ግበሩን ለማስፈጸም ከፋኖ በላይ ሌላ ኃይልና ምሁር እንደማይኖር ስለማምን “ዘመቻው አሁንኑ ይጀመር” ዘንድ በተንቀሳቀሳችሁባቸው በነዚህ ቦታዎች ሁሉ ነፃ ባወጣችሀዋቸው አዳዲስ አስተዳደር በሾማቸሁባቸው አውራጃዎች ወረዳዎች ቀበሌዎችና ከተሞች ሁሉ  በጥንት ስማቸው እንዲጠሩ (አንደ አመላችሁ አምሓራ ትግል ውስጥ ትግሬ ምን አገባው ካላላችሁኝ በቀር ዝምታንና ኢፍትሓዊ አመጽን የማብቂያው ወቅቱ አሁን ነውና) ዝርዝር ጥናት አድራጋችሁ ተግባራዊ እንድታደርጉ እጠይቃለሁ።

አመጸኞቹ ዛሬም ቢሆን አምሓራውን እያስወጡ አሁንም በደረሱበት ቦታ ሁሉ አዳዲስ ስሞች እየሰየሙ እያየን ነው። አናንተም ይህንኑ “በቃ ማለት በቃ ነው!” የሚል መልዕክት የምታስተላልፉበት መንገድ አሁን እየመከርኩዋችሁ ያለውን የሕልውናችሁ “ሁለተኛው ኦፔረሺን” ነው።

ለምሳሌ ልጥቀስ (እናንተም ጨምሩበት)

አዲስ አበባን ለኦሮሞ ባለ ጊዜ ሹሞኞች ፤ አባ ገዳዎችና ሕዝብ ሰብስበው ሲናገሩ “ፍንፍኔ” እያሉ እነ አብይ አሕመድ ሳይቀሩ ይህ ስም በመጥቀስ የስም ለውጥ እያለማመዱዋቸውና ሕጋዊ ለማድረግ ነው። ታስታውሱ እንደሆነ ደንቆሮው የ አሜሪካ አምባሳደርም አዲስ አባባን “ፍንፍኔ” ብሎ በመግለጫው እንዳሰራጨ ታስታውሳላችሁ።

ስለዚህ ዓለም ያወቀው ሕጋዊ  ስሟ አዲስ አበባ  አዲስ አበባ ነው።

ሀገረ ሕይትን አምቦ ብለውታል ዓለም ማያን ሃሮ-ማያ ብለውታል፤ ናዝሬትን አዳማ ብለውታል፤ ደብረዘይትን  ቢሸፍቱ ብለውታል። ቤተ አምሓራን ወሎ ብለውታል፤ አንጎትን ራያ ብለውታል፤ ቢዛሞን ወለጋ ብለውታል፤ግራርያን ሰላሌ ብለውታል፤ ደዋሮን ሐረር ብለውታል፤ አናርያን ኤሊባቡር ብለውታል፤ፈጠጋርን አርሲ ብለውታል፤ ወዘተ….ወዘተ…..ወዘተ…።

ከዚህም በማያያዝ ደራሲው የዶ/ር ምስጋናው ታደሠ  መጽሐፍ ከቤተ አምሓራ እስከ ወሎ በሚል መጽሐፍ በገጽ 134 የተጠቀሱ የጥንቱ ቤተ አምሓራ አካባቢዎች ተስፋፍተው በመጡ ኦሮሞ ጎሳዎች ስም ተሰይመው ጠፍተዋል። ወረሂመኒ፤ ባሶ፤ ጋባቴ፤ ቃሉ፤ ቆቦ፤ ኮምቦልቻ፤ አቧሬ፤ አራርሳ፤ ለጎ ጎራ፤ግንደ ጎራ፤ ወረኖሊ፤ ተሁለደሬ፤ ቦረና፤ ለገሃዲ፤ ለጋምቦ፤ የመሳሰሉ የቤተ አምሓራ ስሞች የኦሮሞ ጎሳዎች የአካባቢውን ስም ቀይረው በራሳቸው ስም የሰየሟቸው ቦታዎች ናቸው (134 ዶ/ምስጋናው ታደሠ - ባንተአምላክ አያሌው  ገጽ 87)

በስለዚህ በዚህ የዓይን አውጣ ድፍረት ዛሬም እየቀጠለ ስለሆነ አንድ ቦታ ላይ እልባት እንዲያገኝ 1) አምሓራ እንዳይኖር እየተፈጸመበት ያለውን ጭፍጨፋ ለማስቆም ጠመንጃ መታጠቃችሁ አስፈላጊ አንደነበር ስወተውታችሁ መኖሬን ብዙዎቻችሁ ስለምታስታውሱት ሕልውናችሁን ለማስከበር መፋለማችሁ ቀዳሚው ኦፔረሺን (ኦፐረሺን ሕልውና) ሲሆን 2ኛው የሕልውናው ኦፔረሺን ዘመቻው ክፍል ደግሞ የባሕልና የቦታ ስም ለውጥ መደረጉን ወደ ጥንታዊና ታሪካዊው ቦታው መመለስ “የባለርስት ሕጋዊነት ኦፐረሺን” ማረጋገጫ ስለሆነ አንድ ሕዝብ ታሪኩና ስሙ ተነጥቆ “አምሓራ” በሕይወት እያለ “አምሓራ የሚባል ነገድ የለም” የሚለው ዘመቻ ከቦታ ነጠቃና የስም ለውጦች የተያያዘና የስም ለውጥ የተደረገበት ዋና ምክንያትም ያንን ለማረጋገጥ እንደሆነ ማወቅ ብልህነት ነው።

ሰላም እንሰንብት!

ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)

No comments: