Sunday, July 28, 2024

ከኤርትራዊው ብሔረተኛ “መነሻችን አማራ መዳረሻችን አማራ” ጋር የወገነው ትልቁ ሰው አቻምየለህ ታምሩ ሊጥ ሆኖ ተገኘ ከጌታቸው ረዳ አዘጋጅ Ethiopian Semay 7/28/24

 

ርትራዊው ረተኛ መነሻን አማራ መዳረሻችን አማራ ጋር የወገነው ትልቁ ሰው አቻምየለህ ታምሩ ሊጥ ሆኖ ተገኘ

ከጌታቸው ረዳ

አዘጋጅ Ethiopian Semay

7/28/24

አቻምየለህን ያክል አዋቂና በሳላ የትግል ወንድ በሕልም በውም በተቃራኒው ቆ እተቸዋለሁ ብየ አስ አላውቅም፡፡ ወዳጅነታችን እስከመደዋወል የደረሰ ነበር፡፡ ባንድ ወቅት (አመት ይሆነዋል)  ምክንያቱ ባላወቅኩት ነገር ስልክ ብደውል፤ ኢመይል ባደርግ ፤ ስ ቡኩ ላይም መሰንጀር ባደርግ፤ ዘጋኝ፡፡ እሱን የሚያወቁት ጋር ደውየ ሰለ ደህንነቱ ለማረጋገጥ ባነጋገራቸውም “እሱ ለበዙ ሰው እንዲያ ነው፤ ትንሽ የመለዋወጥ ትዕቢት ያጠቃዋል፡ ወዘተ... ይሉኛል፡፡  እንዲያም ሆኖ እስክንድርን “ያለቦታው ነው የገባው እዚህ ውጭ አገር መጠቶ ገንዘብ እያሰባሰብ ትግሉን ቢረዳ ይሻላል” ሲል “ቅር አለኝና ምክንያት ይኖሮው ይሆናል ብየ ብዘገይም ቆይቸ አጭር ትችት ጻፍኩበት፡ ለና እንዳልሆነም ተሰማኝ” ከዚያም ድምጹን አጠፋና የእስክንድርን ስም ለመፍጨትና ማስረጃ ሳያቀርብ ለመወንጀል ብቅ ብሎ ወደ መድረክ መጣ፡፡

ርቀውን ከነበሩበት እንን ብቅ አሉ አቶ አቻምየለህ እላለሁ!!

ኦነጋዊው ያዲሰ አበባ ፖሊስ የለበሰውን ኢትዮጵያዊ ሰንደቅ ከገላው ሲገፈውና ማተቡን ሲበጥስበት በዱላ እየነተረ ሲያራሩጠው ቆመህ ታገለው እያለ ፤ ጫት ቃሚውን ሽቅርቅሩና ልፍሰፍሱ ያዲሰ አበባ የአማራ ወጣት ከምርቃናው ነቅቶ ጠላቱን እንዲጋፈጥ በተግባር ያሳያቸው፡ የአማራ ዘር ጭፍጨፋ ኒውዮርክ ፤ ዋሺንግቶን ድረስና አውሮጳ ድረሰ ተገኝቶ ለዓለም ተወካዮች ያስረዳ ታላቁ እስክንድርን ባማቃለል (ከ disparage አልፎ በመወንጀል) “መነሻም መዳረሻውም አማራነት” ለሚለው ኤርትራዊው ዘመነ ካሴን የወገነው አቻምየለህ ታመሩ በድረገጹ የለጠፈው ትችት አንብባችሁ ይሆናል ብየ እገምታለሁ፡፡

“Nationalism is infantile disease. It is the measles of mankind” (Scientist Albert Einstein)  “ብሔርተኝነት የጩጬነት ሕሊና በሽታ ነው። ባጨሩ “የሰው ልጅ የኩፍኝ በሽታ ነው” ይላል ሳይንቲስቱ አልበርት አንስታይን፡፡ አቻምየለህ ባልጠበቅኩት መንገድ “መነሻችን አማራ መዳረሻችን አማራ” ከሚለው ጠባብ “አምሐራይ”ሔረተኛው ባሕርዳር የተወለድኩ ኤርትራዊ ነኝ ከሚል ፓስፖርት የያዘ ዘመነ ካሴ ጋር በመወገን እስክንድርን ወንጅሎታል፤ ስሙንም በጥቁር ጥላሸት ቀብቶታል፡፡ እነ ዘመነን ጦም አደር ፤ እስክንድር ቅቤና ማር ተመጋቢ ዳገት ቁልቁል የማይወርድ የማይወጣ የጫካ ሚሊዮነር አድርጎ በመይገብ ላሸት ሲቀባው ማየት አስገርሞኛል፡፡

እስክንድርን አላግባብ በቃላት ሲፈጨው፤ ማርሸት የተባለው ጸረ ዲሞከራሲ አጉራዘለልና አለቃው ዘመነ ካሴም ሆነ ጡጦ እንደሚጠባ ህጻን ከዘመነ ጉያ የማይጠፋ  እግሩ ሥር ሆኖ ‘ኩት ኩት’ የሚለው አስረስ ማረ የተባለው ጠበቃ  “ቢ ቢ ሲ አማርኛ” ተጠይቆ መልስ ላለመስጠት ሲሸሽ”

<<ንጽኋን አማራዎች መረሸናችንና በእምብርክክ እንዲዱ ማድረጋችንን በማሕበራዊ ሚዲያ ነው የሰማሁት “እናጣራለን”>> በሎ እያሾፈ፤ ለፋሲል የኔዓለም ቃለ መጠይቅ የሰጠ አስረስ ማረ የመሳሰሉት የዘመነ አሽከሮች ግን አቻምየለህ አንዲት ፍሬ ቃል ሰንዝር አልወነጀላቸውም ፤ አልወቀሳቸውም አልወረፋቸውም፡፡

አቻም ወገንተኛ ሆኖ ለአውራጃው ልጆቹ በሚያዳላ መልኩ ማስረጃ ማቅረብ በማይችልበት ውንጀላው እስክንድርን ብቻ ለይቶ ጥላሸት ቀብቶታል፡

እንዲህ እያለ፡

(ቀደም ብሎ እስክንድር ነጋ ላይ አንድ ነገር ቢሰራ ኖሮ ) በአርበኛ አሰግድ መኮንን ላይ የደረሰው መከራ ላይደርስ ይችል ነበር” በማለት ምስኪኑን እስክንድርን ይወነጅለዋል፡፡ አንድ ነገረ ቢሰራ ኖሮ የሚለው በሞት ወይስ  ከትግሉ ማስወገድ? አልገባኝም!

የሚገርመው አሰግድ መኮንን እጅ ስጥ ሲባል እንደ የጦር መሪነቱ ራሱን በሳይኖይድ ወይንም ሽጉጡን ጠጥቶ መስዋእት ላለመሆን ፈቅዶ ለአብይ አሕመድ አሽከሮች እጁና መሳሪያውን ያሰረከበን የአሰግድ መኮንን  እጅ መስጠት ምርጫ “እስክንድርን ዋና ተጠያቂ አድረጎ መወንጀል” እናቴ ቀሚስ አደናቀፈኝ አይነቱ የነ አቻመየለህ መሸፈኛ ‘’አርቲ ቡርቲ” የቀረበበት ዋና ምክንያት አቻምየለህና መሰሎቹ እስክድር ላይ የሚዘባበኑበት ምክንያት አላቸው፡፡

ይኸውም የአሰግድ መኮንን ሽንፈት መደበቅ ነው፡፡ አሰቀደሞ ጥንቃቄ ያላደረገ ራስን ለመከላከል ፤ ጠላት እጅ ቢወድቅ ፤ አንድ መሪ ቢያዝ ምስጢር እንዳያወጣ ሽጉጡን መጠጣት ባይችል እንኳ ቅጽበታዊ መስዋእትነት ለመቀበል “በኪሱ ምን አማራጭ (እንደ የሳዮናይድ ከኒን መርዝ የመሳሰሉ) መያዝ እንዳለበት የመጀመሪያው “ሀ ሁ” የሽምቅ ጦር አዋጊና ሃላፊ’ ትምሕርት የመሰውያ ሕግ ማወቅ/መማር ነበረበት፡፡ ይህንን “ሀሁ” የማያውቅ የሽምቅ ተዋጊ መሪ የሆነው አሰግድ ልምድሥልጠና” ያልነበረው ሰለነበር ሰተት በሎ እጁን ለጠላት ሲያሰረክብ ፤ እነ አቻምየለህ ያቺን ድክመቱን ላለማጋለጥ ፤ ደክመቱና ተጠያቂነቱ ለእስክንድር ጭነውበታል፡፡

ትግ <<ገሪሙኒ አነ፤ ናይዞም ሸማነ>> ይላል <<የሸማኔ ነገር እኔኑም አስገረመኝ>> ይላል፡፡  ነገረ ሰሪዎችም “የሰው ስም ለማጠልሸት” እንደ ሸማኔው ‘’የሥም ማጥፊያ መወርወርያቸውን’’ ከግራ ቀኝ፤ ከቀኝ ወደ ግራ እየተቀባበሉ ነገር ይጠነጥናሉ፡፡

 በመቀጠል እስክንድርን ጸረ አማራ አደረጎ በመወንጀል፤የጀርባ ታሪኩን በጸረ አማራነት አድርጎ ሲከሰው ታያላችሁ፡

እንዲህ የላል፡-

 <<የኋላ ታሪኩና በአማራው የኅልውና ተጋድሎ ውስጥ ሊያራምደው በሚሞክረው ጸረ አማራ እሳቤው>>

በማለት ይወነጅለዋል፡፡

እስክንድር ጸረ አማራ የኅልውየኋላ ታሪኩ አቻምየለህ ማስረጃ አላቀረበም፡፡ አቻምየለህ የአማራ ተቆርቋሪ እስክንድር  ግን ጸረ አማራ የሚሆነበት በታአምርም መባል ያልነበረበት ጮርቃነት ነው፡፡ አቻምየለህ ከትልቁ ኢትዮጵያዊ ማማ ወርዶ ወደ <<አማራ እ ነኝ ፤ የአማራ አሳቢና ተከላካይ እኔና የተቀረነው ነን >>  በሚል ውስጠ ገለጻ  የአማራ ሕልውና ለማጥፋት አስቦበት የመጣ  በማለት ይወነጅለዋል፡፡

አቻም ከላይ እንደተመለከታችሁት አማራ ማለት እኛ እንጂ እስክንድር የአማራን ሕልውና በመጻረር የሚታወቅ <<የኋላ ታሪኩ>> ሳይመረመር የተቀላቀለን የሚለው የአቻምየለህ ጽሑፍ የሚያሳየን ትምክሕተኛ ወደ ሆነው ወደ ማፈሪያ ካምፕ ተፈጥፍጦ ሊወድቅ እንጥልጥል ላይ ነው (if not already) ያሳዝናል፡፡ካልሆነማ የእስክንድር <<የኋላ ታሪኩ>> አማራ የዘር ማጥፋት እየተፈጸመበት ነው እያለ ዓለም ሙሉ እየዞረ ሲታገል፤ “የግራኝ አሕመዱ” አብይ አሕመድ ጉግ ማንጉግ ፖሊሶችና ገራፊ ሰላዮች ፤ እንዲሁም አዲሰ አበባ ውስጥ በጸረ አማራ የተቀረጹ የወሃቢያ ኦሮሞ እስላማዊ ዱርየዎች ሽጉጥ ይዘው በሞተር ሳይክል ሲፍልጉትና ቁምስቅሉን ሲያሳዩት ፤ ሲታሰር ሲፈታ ፤ አቻምየለህ ግን እዚህ እኛ ጋር ትምሕርቱን ሲያጎለብት ነበር፡፡

ያ ሁሉ የእስክንድር <<የኋላ ታሪኩ>> ለአማራ የከፈለው ታሪካዊ መስዋዕት ነው፡፡ ታዲያ ምን ያደርጋል አለመታደል ብዙዎቹ አማራዎች የሞተላቸውን ፤ የተሰደበላቸውንና የታሰረላቸውን  የሚሰድቡና የሚያግሉ፤ ኤርትራ እንጂ ኢትዮጵያ አይደለሁም የሚልን የሚያሞግሱ የኤርትራ ባንራ የሚያውለበልቡ ማፈርያዎች ናቸው፡፡

“መነሻችን አማራ መድረሻችን ኢትዮጵያ” የሚለው የእስክንድር የትግል ቅስቀሳ “አቻምየለህ ታመሩ” ቅራቅምቦ እያለ አሹፎበታል፡፡

እንደተገነዘበኩት ከሆነ አቻምየለህ ታምሩ ከጎጃሜ ብሄርተኞቹ (ሌሎችም ሰምቻቸዋለሁ) "መነሻቺን አማራ፣መድረሻቺን አማራ" ጋር ፍቅር የያዘው ይመስላል። እንደዚህ ዓይነት ጎበዝ ወገኔ ከኢትዮጵያ ኮረብታ ላይ ሳይታሰብ ወደ ጽንፈኛው የብሄር ብሄረተኛ አማራ ሰፈር ተወርውሮ ሊወድቅ  መቃረቡ ማየት ያሳዝናል።

አቻምየለህ መነሻችን አማራ መድረሻችን አማራ የሚለው የናዚ አይነት ‘ኩፍኝ’ ተለክፎ ካልሆነ እስክንድርን እንዲወገድ መምከር ይበልጥ ትግሉ ያኮላሸዋል እንጂ አያጠናክረውም፡፡

እንዲህም ይላል፡-

<<እስክንድር ራሱ መሪ አድርጎ ሲሾም የሚታየው ድል ለዲሞክራሲ የሚለው ሕዝባዊ መዋቅር በተዘረጋበት አገር የሚታሰብ መፈክሩ እንጂ የአማራ የኅልውና ተጋድሎ አይደለም።>>

የሚገርም ነው!!!! ድል ለዲሞክራሲ ሕዝባዊ መዋቅር በተዘረጋበት አገር የሚታሰብ መፈክር እንጂ በአማራ የኅልውና ተጋድሎ ወቅት አይደለም ሲል ፤ ሕዝባዊ መዋቅር ያልዘረጋው በዲሞከራሲ የማያምነው አማራ መነሻና መዳረሻችን ባዩ በሃሳብ የተለዩትን ሰዎች ዘመነ የገነባው የጉደጋድ ድብቅ እስርቤት ታፍነው የታሰሩት

1 ዶ/ር እንዳለማው

2 ዶ/ር መዝገቡ

3 ጊራወርቅ ወርቁ

4 ጋዜጠኛ ወግደረስ

5 ወግደረስ ጤናው

 6 የአብስራ ሞላልኝ

 7 ዶ/ር ዳዊት ፍስሃ

 8 አንሙት አምሬ

 9 ልዑል ያሳብ

 10 አብርሃም ጎደፋው

የመሳሰሉት አማራዎች ታስረው 1ኛ እና 2ኛ ታሳሪዎች ለመፈታት በሚልዮኖች ብር ተጠይቆባቸው አሁን ጨለማ ውስጥ ያሉት እና 4 ሰዎች “ገርጨጭ” በተባለ ገጠራማ ከተማ ውስጥ በዘመነ ካሴ ታጣቂዎች ጥይት ያለ ምንም ወንጀልና ፍርድ ቤት ቢ ቢ ሲ ዜና የሰራባቸው ተረሻኞች ውስጥ

1) የወረዳው ቤተ ክሕነት ሥራ አስኪያጅ የነበሩት  መሪጌታ ግሩም

2)  አቶ አዘነ ደምሴ

3)  አቶ  አስማማው አቤ

4)  ወ/ሮ ላይን አየሁ ዳኛው   (የጤናኤክስተንሺን ሰራተኛ) ሲረሸኑ  13 ሰዎች በእምብርክክ እንዲንፏቀቁ የተደረገው ሕዝባዊ መዋቅር እስኪደራጅ በዲሞከራሲ እንቀልድ የሚሉት እነ ዘመነና አሁን ደግሞ አሁናዊው  የአማራ ሕልውና የሚረጋገጠው ያለ ዲሞከራሲ በእውር ድምብሩ ሲራመድ ነው  ይለናል አቻምየለህ ታምሩ!

ሳደንቀው የነበረው “ትንታጉ” የአቻምየለህ መመራመርና ማስተዋል ምን ጅብ ነጠቀው?   

አቻምየለህ በሚገርም ጥበት እንዲህ ይላል፡

<<መነሻችን አማራ፤ መድረሻችን ኢትዮጵያ” የሚል ጸረ አማራ ዝባዝንኬ ማዘውተራቸው ለምን ይሆን ብሎ መጠየቅ ያስፈልጋል። ሲጀመር “መነሻችን አማራ፤ መድረሻችን ኢትዮጵያ” የሚለው ጸረ አማራ ማጭበርበሪያ የተፈለሰመው በእስክንድር ነጋም አይደለም። ማጭበርበሪያውን የፈለሰሙት የፋኖን ተጋድሎ ለመጥለፍ የተሰለፉ አሜሪካን አገር የሚኖሩ የምናውቃቸው የግንቦት ሰባት ጉግ ማንጉጎች ናቸው።>> ይላል፡፡

በአቻምየለህ አባባል “መነሻችን አማራ፤ መድረሻችን ኢትዮጵያ” ማጭበረበሪያና  ጸረ አማራ መፈክር ሲሆን “ኢትዮጵያ” የሚል ቃልና መድረሻ  የሚጠቅሱ ሰዎች አማራ ሳይሆኑ ኢትዮጵያዉያን ናቸው ወደ ማለት ይዳዳዋል፡፡

“መነሻችን አማራ መድረሻችን አማራ” የሚለው ትርጉሙ (አቻምየለህ እስካላስረዳን ድረስና ዘመነ ‘አብይ አሕመድ ሥልጣኑ ለአማራ በቻ” ‘ያሰረከብ’ ከሚለው ውጭ ሌላ ትርጉም ከሌለው በቀር ) ትርጉሙ ልከ እንደ ትግራይ በሔረተኞች በ80ዎቹ ጦርነቱ ወቅት ትግራይ ነፃ ካወጡ በ ከዚህ ወዲያ አገራችን አይደለም፤ ኢትዮጵያ ነው፤ << መበገሲትና ትግራይ መዕለቢና ትግራይ>> (መነሻችን ትግራይ መዳረሻችን ትግራይ) ከሚለው መመሪያችን ውጭ) አንንቀሳቀስም! በማለት በርካታ ታጋዮች ወደየ ቤታቸው ከነ ትጥቃቸው በመሄዳቸው አዲሰ አበባ መዝልቅ ሰላለተቻለ በስንት ልመና እነ ሳሞራ የኑስና አመራሩ ወራት የፈጀ ልመና ተደርጎ ነበር አዲሰ አበባ የገቡት ( አድማው “ደውታ” ይሉታል “ባለህበት መቆም” ማለት ነው)፡፡ ካሁን በፊት ይህንን በሚመለከት ሳሞራ የሰጥው ቃለ መጠይቅ አቅርቤ ነበር፡፡

የአማራ ብሔረተኞች፤ ትግራይና ኦሮሞ ብሔረተኞች ኢትዮጵያ የሚል ሐረግ በጆራቸውና በትግላቸው ሊደመጥ አይሹም፡፡ ስለሆነም አዲሱ ወጣት የፋኖ ታጋይ አማራ “አማራዊነት” እንጂ “ኢትዮጵያ” የሚል ቃል በነበር ትውስታ ሕሊናቸው ውስጥ ቀሰ በቀስ እየተቀረጸ ከነ አካቲው “ኢትዮጵያ” አሁን እንዳለው የትግራይ ወጣት ያው አማራው ወጣትና ታጋይ ፋኖው የዚያ ባሕሪ ይይዛል፡፡ እመኑኝ !!! የአማራ ወጣቶች ከሚለቁት የማሕበራዊ ሚዲያ ንግግራቸው አድመጡና ሥጋቱን ታያላችሁ፡፡

የነ አቻምና ዘመነ ትምሕርት “ዲሞከራሲ፤ ኢትዮጵያና አማራ” የሚባል የሚደባልቅ ትግልና ቃል በፋኖ ውሰጥ መፈቀድ የለበትም ነው፡፡“ኢትዮጵያ ለዜጎችዋ አራት ኪሎ ደግሞ ለአማራው” ነው ዘመነ እንደሚለው፡፡ ትግሬና አሮሞ ገዘተውን አሁን ደግሞ በዘመነ ይሚመራ አማራ ሊገዛን አራት ኪሎን አስረክበን እያሉት ነው፡፡

ለመሆኑ የግንቦት 7 መፈክር ስለሆነ ኢትዮጵያ የሚባል መዳረሻ ያለው ጠላት ነውና መወገድ አለበት ብሎ ማስተማር ምን እሚሉት ዝቅጠት ነው? ለመሆኑ አማራን ነጻ ካወጣህ መዳረሻህ ወዴት ነው? ነው ውይስ መነሻችን አማራ መድረሻችን አማራ ያንተው ዘመነ <<ገድለን ከቀበርነው ማን ይደራደራል፤ ሥልጣኑን ሙሉ ለሙሉ ለአማራ አስረከቦ ኢትዮጵያ ደግሞ ለዜጎቻ ያስረክብ” ሲል ዘመነ በዚህ መልክ እስክንድርን “በኢትዮጵያ ካድሬነት ከስሦታል’’፡፡ ኣቻም ይህንን ሰመቶ ትንፍሽ አላለም፡፡

 እግዚሐር ይስጠው ሳይደብቅ የጎጃም አማራ ፋኖ  ብረት ያነሳበት መነሻው <<አራት ኪሎን በሙሉ ለአማራ እንዲረከበው>> መሆኑን መነሻውም መደረሻው ሳይሸሽግ ነግሮናል፡፡ ይህንን ነው አቻምየለህ ያለማፈር ደግፎ እስክንድር ኢትዮጵያ ሰላለ ጸረ አማራ ሕልውና ነው እያለው ያለው፡፡   

አቻመየለህ እወነትነት ቢኖሮው ኖሮ እስክንድርን “የችግሩ መነሻና መጨረሻ ኣድርጎ” መወገድ አለበት ብሎ ከመቃዠት ይልቅ አቻምየለህ የሚደግፈውን “መአት ጉድ ያለው” “መነሻችን አማራ መዳረሻችን አማራ የሚለው የኤርትራ ፓስፖርት የያዘው “የጎጃሙ ዲገላውን ቡድን”  ትንፍሽ ሳይል እስክንድር ላይ መረባረቡን ስመለከት አቻምየለህ አድፈጦ በነበረበት ቦታ ቢቆይ የሻል ነበር እላለሁ፡፡

ይህንን ልበልና ላቁም፡-

ባልተጠበቁ ሁለት ወቅት የማከበራቸውና የምወዳቸው ወዳጆች አጥቻለሁ (1) አብይ ሲመጣ እና (2፟) በእስክንድርና በዘመነ መካከል የተከሰተው ጸብ፡ አሁን በ2ኛው ወቅት ወዳጄ የነበረው አቻምየለህ ጋር ተለያየን፡፡ ከተለያየን የቆየን ቢሆንም (ከተለያየን በእርሱ ትእቢት ቢሆንም)፡፡ አሁን ጎራ ለይተን <<መነሻውና መዳረሻው አማራ ያደረገው> “ጩጬ” ብሔረተኛው ቡደን ጋር ለበጎ ፖለቲካዊ ፍልሚያ ተለያይተናል፡፡

ጌታቸው ረዳ    

አዘጋጅ Ethiopian Semay

 


Friday, July 26, 2024

የጀነራል ተፈራ ማሞ የምርኮኛነት ትርጉም ግብዝ አማርኛ ወይስ ወገንተኛ ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 7/26/24

የጀነራል ተፈራ ማሞ የምርኮኛነት ትርጉም ግብዝ አማርኛ ወይስ ወገንተኛ

ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 7/26/24

ድሮ “የብ አ ዲ ን ተዋጊና አባል” የነበረው  ጀነራልነቱ በሽምቅ ተዋጊነት ልምድ  ወደ ሥልጣን የወጣው ፋሺቱ “ወያነ” ጀነራል ብሎ የሾሞው ጀነራል ተፈራ ማሞ ፍሺቱን ኦሮሙማው አብይን በመቃወም ወደ ጫካ ገብቶ ፋኖን የተቀላቀለው ተፈራ ወደ ጫካ ከገባ ወዲህ ግን ዝምታውን መርጦ ባለው ያዋጊና የሽምቅ ልምድ ፋኖዎቹን ከማደራጀት ይልቅ ፤ ቃለ መጠይቅ በማደረግ ለትችት እየተጋለጠ ነው፡፡

 ተቺውም እኔው ነኝ (መናለባት ሌሎችም ይኖራሉ)፡፡

ስለዚህም የሚቀርቡት ሰዎች የን ምክርና ትችን ቢያደርሱለት ለትግሉና ለራሱ ላለው ክብር ጠቃሚ የሚሆነው እዛም እዚህም እየመጣ በማያውቅበት የፖለቲካ ነገር ባይነካካ መልካም ነው፡፡

አሁን ካንድ ሳዓት በፊት ዮ_ቱብ ከፍቼ ስዳሥስ ፤ ካሁን በፊት ሻለቃ ዳዊት “የመሰረትናትን አገር ለማን ጥለን ነው የምንደው?” ብሎ መልስ የሰጣት “አማራ የራሱን አገር መመስረት አለበት” እያለች ስትጠይቅ የነበረች አንዲት ምስኪን ወጣት የምታዘጋጀው Amhara News Broadcasting Center ABC TV Amhara በሚባል ‘ሚዲያ’ ትንግርቱ ለሚባል ቃለ መጠይቅ አዘጋጅ ቀርቦ ተፈራ ማሞ የሰጠውን ቃለ መጠይቅ ሳዳምጥ ከሰጣቸው መልሶቹ አንዳንዶቹ አስደምመውኛል፡፡

ሁለት ነገሮች ልበል፡

አንዱ ምክር ነው፤ ላው ትችት ነው፡፡

በምክር ልጀምር፡፡

ወደ ጫካ የገባኸው በቅርቡ ስለሆነ ሁኔታዎችን አጥንተህ ነገሮች ሰከን እስኪሉ ድረስ እራስህንም በምታውቅበት የውግያ አመራር ተመቻችቶልህ ስትቀመጥ ያኔ በሙሉ እውቀትና ሓላፊነት ለምትሰጣቸው ቃለ መጠይቆች ምናልባትም ቢያስወቅስህም ተጨባጭ ነገሮች ማቅረብ ስለመትችል ሓላፊነቱን ትወስዳለህ (ሙሉውን መረጃ ይኖራሃልና) አሁን የመትሰጣቸው መልሶች ግን (ለመሳሌ ስለ አሰግድ ጠላት እጅ መውደቅ (መማረክ) ወይንም እጅ መስጠት ፤ ያገኘኸው ከሁለተኛ መረጃ እንጂ ከራስህ የእዝ አመራር ሰላለሆነ ራስህ መሪ ስትሆን (ወታደራዊ ጠቅላይ መሪነት ይገባሃልና) ራስህ በሁኔታው ይገባህበት በወቅቱ የራዲዮ/ ስልክ/ ግንኙነት ከአሰግድ ጋር ኖሮህ ቢኖር ኖሮ ተጨባጩን ስታውቅ እንጂ (የአሰገድ ቡድን ሲጠየቁ መልሳቸው እናጣራለን አጣርተን እንነግራችለን ነው እሚሉት) ፤ በሚሉበት ሁኔታ አንተ መጥተህ ስለ አሰግድ የሰጠኸው ግን የቡድኑ አባል ካልሆንክ በቀር አብረውት ከነበሩት ሰዎች ሰማሁ (ከሁለተኛ ሰው እንጂ ቀጥተኛ ተሳትፎ ባልነበረህ) ሰማሁ፤አግኝቻቸው እጁ አለሰጠም ብለውኛል የሚል የብለውኛል መልስ መስጠት አልነበረብህም፡፡ ያመንካቸው መረጃዎችህስ እጅ ሰጡ ሲባሉስ ሰዎቹ ተታኩሰው ነበር ያመለጡት? አሰግድስ ከላሸኑየት አደረገው? ያየነው ያረጀ ሽጉጡና የሻገቱ 7 (6) የሚሆኑ አሮ ጥይቶች ናቸው) ሰለዚህ ከእንደዚህ ያለ አወዛጋቢ ባትገባ ይመረጣል፡፡

በተጨማሪ አሁን ያለው ፋኖ ወስጥ ያለው እጅግ አስጊ የርስ በርስ በደም መፈላለግ ባለው ክስተት ሁኔታዎች እሰኪረጉ ድረስ ወሰጥ ለwስጥ የሚሰራውን አደረጃጀት እየሰራህ ዝምታን መርጠህ የብረት ትግሉን ብታካሂድ መልካም የሆናል እንጂ <<ከውጭ አገር እንደሚራገበው አይደለም> ማለት መረጃው የለህም ማለት ነው ወይንም ብስለቱ የለህም ማለት ነው፡፡

አሁን ወደ ሰጠኸው ቃለ መጠይቅ ልግባ፡

1)            የምታምነው ሚዲያ Amhara News Broadcasting Center ABC TV እንጂ ሎችን እንደማታምን

2)           አሁን ያለው የፋኖ በደም የመፈላለግ አለመጣጣም አሳነሰሀ ማየትህ

3)           ምርኮኛ ሰለሚለው ቃል ያለህ ግንዛ

 

በ1ኛው ልጀምር፦

ትንግርቱ የተባለው የፕሮገራሙ አዘጋጅ ሲጠይቅህ እንዲህ ብለሃል፦

 

ትንግርቱ፦ “ወደ ፋኖ ከተቀላቀልክ ወዲህ ቃለ መጥይቅ ለማድረግ ይህ የመጀመሪያህ መሆኑና

Amhara News Broadcasting Center መርጥኸው ትናንት እንደነገረከኝ ነው ወደኛ መምጣህ  የገለጽከው፡፡ ጀነራል ለምን የአማራን በሮደካሰትን እንደመረጥክ ብትነግረኝ..?

የተፈራ መልስ፡

አመሰግናለሁ! ኤ ቢ ሲ አማራ ብሮድካስት ቲ ቪ የመረጥኩበት መክንያት ያው መልእክቱን “ለሁሉም ያደርሳል” ከሚል ነው፤ ሌላ አይደለም፡፡ አጋጣሚ ስንከታተለው ሰለነበር መልእክቱን በዚህ ደረጃ  ያሰተላልፋል በሚል ነው፡፡

ትንግርቱ፤ አመሰገናለሁ ወደ እኛ ስለመጣህ! የላል፡፡

የትንግርቱ አነጋገር ፤ልጥቀስ << መርጠኸው ትናንት እንደነገረከኝ ነው ወደኛ መምጣህ  የገለጽከው>> ነው ትንግርቱ የሚለው፡፡ ለቃለ ምልልሱ “ስልክ ደዋዩ” ወይንም “ፈላጊው” ተፈራ ራሱ እንደሆነ ከጥቀሱ ያመላክታል፡፡ ካልሆነ <<ጠይቀንህ ትብብርህ ሰላሳየኸን እናመሰግናለን>> ነው የሚዲያው ሕግ እንጂ ፤ማንኛውንም እንግዳ በተቀሩት ሚዲያዎች እመነት ከሌለው በቀር “ለምን መረጥከን?” የሚል ሰመቼ አላውቅም፡፡

ያንን እንዲህ እንዳለ እንግዲህ ተፈራ ማሞ ይህንን ጣቢያ የመረጠበት ምክያት ሲገልጽ ደግሞ  “የጀነራሉ መልእክት የተቀሩት ሌሎቹ  ጣቢያዎች ለሁሉም አያዳርሱትም” የሚል እምነት ሰላለው “ለሁሉም ያዳርሳል” የሚል እምነት ያሳደረበትን ይህንን ጣቢያ መምረጡ የሚገርም ሆኖ አግኝቸዋለሁ፡፡ (ለዚህ ነው ዝምታን ምረጥ የምለው)

ሌሎቹ የተፍራን መልእክት ሳያዳርሱት ሊያፍኑት ሰለሰጋ ወይስ ስርጭታቸው አቅም ስፋት ሰለሌላቸው? በስርጭት ስፋትና ተደራሽነት ከሆነም  ይህ  ጣቢያ እጅግ ደካማ ከሚባሉት ሚዲያ የሚሰለፍ ነው፡፡ በ 20 ሰዓት ውስጥ 385 ሰው ብቻ ነው ቃለ መጠይቁን ያደመጠው፡፡ የአድማጭ ብዛት ደካማ ከሚባሉት ነው፡፡ ታዲያ ጀነራሉ ይህንን ደካማ ሚዲያ መርጦ ሌሎቹ ለሁሉም አያስተላልፉትም የሚል እመነቱ ማሰረጃውና ምክንያቱ ምን ይሆን?

የማዳረስ ብቃት የላቸውም ለሚላቸው የተቀሩት እልፍ አእላፍ ሚዲያዎች በምን አይኑ ደፍሮ ይሆን እነሱ ጋር ቀርቦ ለወደፊቱ ቃለ መጠይቅ የሚያደርገው?

2) አሁን ያለው የፋኖ አለመጣጣም ጠያቂው ሲጠይቅ፤ እንዲህ የላል፡

 “ሰሞኑን በሆነው ነገረ ያላዘነ ያልታመመ የለም፡ ምን ትላለህ? ምን እየተሰራ ነው?     

ተፈራ ማሞ፡

አሁን አንድ የጋራ ጠላታችን የምንለውን ለመምታት ወታደራዊ እዙን ከላይ እሰከታች እንድ የሚሆንበትን፤ አደረጃጀት የታጠቀ አቋም በወታደራዊ ውጊያ አንድ ዓይነት አስተሳሰብ የውጊያ አካሄዳችን እንዴት መሆን አለበት የሚሉ በዚህ ዙርያ ነው እንግዲህ በሁሉም ቦታ ለመነጋገር እየሞከርን ያለነው፡፡ አሁን ዋነኛው የትኩረት ማእከሉ አንድ ሆነን ይህን ጠላታችን ከዚህ ነቅለን መጣል አለብን በሚል አዙሪት ነው እየተነጋገረን ያለ ነው፡፡ሁሉም ይደግፈዋል፤ አሁን ያለው ሁኔታ በዛው እየሄድን ነው፡፡ ብዙም በከፋ መንገድ አላየሁትም፡ከውጭ እንደሚራገበው አይደለም፡፡>>

ይላል ጀነራል ተፈራ ማሞ፡፡

ጀነራሉ ወይስ እ ነኝ ጫካ ውስጥ ያለነው? እ  ውጭ አገር ሆኜ የምሰማውና በቪዲዮ የማየው <<የፋኖዎቹ የትኩረት ማእከሉ አንድ ሆነው ጠላታቸውን ከአካባቢያቸው ነቅለው መጣል እንዳለባቸው በሚል አዙሪት ሳይሆን እየተነጋገሩ ያሉት፡፡ አንድ መሆኑን ቀርቶ ዘመነ የተባለው “የጫካ ዲገላ” ኮሎል ጌታሁን የተባለውን ጎጃም ወስጥ የሚንቀሳቀስ የፋኖ አንድ ክንፍ ዋና መሪ እስክንድር ነጋን ስለመረጠ፤  “አንቃችሁ ይዛችሁ አምጡልኝ ብሎ ብዙ ጦር ልኮ ለመውጋት የኮሎሉ ትውልድ ቦታ ሕዝብ የክተት ጡሩምባ ነፍቶ ልጃችንን አናስነካም ብሎ የጎጃሙ ዲገላ (ዘመነ ካሴ) ጦር ተመልሶ ወደ መጣበት ቦታው መመለሱና ቀውሱ በዲገላው ምክንያት ወደ ደም መፈላለግ እያመራ መሆኑን ከኮሎሉ አንደበት በቃለ ምልልስ ስምተናል፡፡

 ይህ የሆነው ጀነራል ተፈራ  ከሚለው <<የትኩረት ማእከሉ አንድ ሆነን ይህን ጠላታችን ከዚህ ነቅለን መጣል አለብን በሚል አዙሪት ነው እየተነጋገረን ያለ ነው፡፡በዛው እየሄድን ነው፡፡>> እያለን ባለው ሰዓትና ቀን ነው ይህ እየሆነ ያለው፡፡

ይባስ ብሎ ሕዝብን ወደ ማዳማት የሚጭር አወራጃዊና ወረዳዊ ገጭትና መፈላለግ የዲገላው አደገኛ  አጉራ ዘለልነትና ጋጠወጥነትን እየባሰ የመጣውን “አንዱን ላንዱ” የመጠፋፋት ከፈተኛ ሙቀትን ነው፡ ጀነራሉ  <<ብዙም በከፋ መንገድ አላየሁትምከውጭ እንደሚራገበው አይደለም፡>> እያለን ያለው፡፡

ለዚህ ነው እባክህን ጀነራል ዝምታን መርጠህ ያዋጊ የበላይ ጦር አዛዥ ቦታውን ስትይዝ (ይገባሃልና) ያ በሙሉ ልቦና ያለውን ነገር ትነግረናለህ በየ የምመክረው፡፡ እስከዛው ድረስ ለእነ እስክንድርንና የመሳሰሉ ሌሎች በፖለቲካውና ግንኙነትን ልምድ ላላቸው ለበሰሉ ፖለቲከኞቹ  እንዲተቹበት ተወው፡፡ እነሱ ይወቀሱበት፡፡ አንተ ማድረግ ያለብህን ስራ እንጂ “ቀወሱን አሳንሰህ በክፍት አላየውምከውጭ እንደሚራገበው አይደለም” ማለት ያስገምታሃል፡፡

(3ኛ) ምርኮኛ ሰለሚለው ቃል ያለህ ግንዛቤ

ጀነራል ተፈራ ሰለ አሰግድ መኮንን እንዲህ ይላል፡

<እጅ ሰጠ የተባለው ውሸት ነው> ይልና  ምክንያቱንም ሲገልጽ፤

<<ወደ መርሃ ቤቴ ለመሻገር ሲል ነው ኮመቦልቻ ላይ ይህ ሁታ የገጠመው” ይላል ጀ/ ተፈራ፡፡

እንዲህም ይላል፡፡

<< አሁን እኮ መማረክ ውርደት አይደለም በነሱ ቤት፡፡ መማረክ እንደ ውርደት አያዩትም (የመንግሥት/አብይ የሚያዘው ወታደርን ነው እንዲህ እያለ ያለው) ጥዋትም ማታም እየተማረከ ነው፡፡ ጀነራሎቹ ሁለት ሦስት ጊዜ የተማረኩ ናቸው....።>>

 በማለት ወታደሮቹ ሲማረኩ “ውርደት” እያለ ሲጠራው “አሰግድ መኮንን”  ተማረከ የሚል ቃል ላለመጠቀም “ይህ ሁታ ገጠመው፡፡” በሚል በአዲሰ አማርኛ ለመግለጽ ይሞክራል፡፡

ወታደሮቹ ሲማረኩ ውርደት ሲሆን አዋጊው አለቃ አሰግድ ሲማረክ ግን “አርበኛ” አሰግድ እያለ ይጠራዋል፡፡ መማርክ የሚል  አማርኛ ቃል ወያነ ከመጣ ወዲህ ወይንም ተፈራ የታገለለትን ብ አ ዲን ከመጣ ወዲህ ያላውቅነው አዲስ ትርጉም የተሰጠው ከሆነ አላውቅም እንጂ ፤ ራሱን ላለመሰዋት መርጦ “እጅህን አንሳ” ሲባል እጁን አንስቶ ከነ ሽጉጡ የሚማረክ ተማራኪ “መርኮኛ” የባላል ፡፡ ትልቅ ጦርን የሚመራ መሪ ሽጉጡን ይጠጣል እንጂ እጅ አይሰጥም!

በተፈራ አማርኛ ግን አሰግድ ሲማረክ “አርበኛ” ይለዋል፤ ወታደሮቹና አዋጊ ባለ ማእረጎች ሲማረኩ ደግሞ “ወርደት የሚከናነቡ” የሚል አሰገራሚ ትርጉም አስደምጦናል፡፡ 

በወሎዎቹ አማርኛ ትርጉም  መማረክ “ለወገን” ሲሆን “አርበኛ” ፡ ጠላት ሲማረክ ግን “ሃፍረት የሚያከናንብ ውርደት ነው” የሚባል ከሆነ ንገሩኝ፡ ካልሆነ የጀነራል ተፈራ ማሞ የሙርኮኛነት ትርጉም ግብዝ አማርኛ ወይስ ወገንተኛ?

ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay


Thursday, July 25, 2024

ከመለሰ ዜናዊና ከጉስታቭ ኸርቭ የተማረው የጎጃሙ ሙሶሊኒ! ጌታቸው ረዳ 7/25


ከመለሰ ናዊና  ከጉስታቭ ኸርቭ  የተማረው የጎጃሙ ሙሶሊኒ!

ታቸው ረዳ

7/25/24

ትዝ ይላችሁ እንደሆን << የትግራይ የአባ ሰላማ ቄሮዎች እና የአምሓራ መነኮሳት በአክሱም>> በሚል  Ethiopian Semay  ድረገጽ  ላይ 10/3/23 ያቅረበኩት አክሱም ጽዮን ለመሳለም የዱት መንፈሳዊ እንጂ ፖለቲካዊ እውቀቱ የላቸው የአምሐራ ተወላጆች የሆኑ መነኮሳትን በትግራይ ብሔረተኛነት የተበከሉ (ፋናቲክ) የሆኑ የአከሱም ከተማ ወጣቶች መነኮሳቱን ሰብስበው  ሲያስጨንቁዋቸውና ሲያዋረዱዋቸው እንደነበሩ በቪዲዮ አሳየቻለሁ፡፡

ከዚህ ሌላ ትግራይ ውስጥ በ1968 ዓ/ም ልጆቻችሁን ወደ ሰላማዊ መንገድ ተመለሱ ፤ መንግሥት አዲስ ነውና እንነጋገር ይላችል ብላችሁ ለሽምግልና አነጋግሩዋቸው ተብለው በሕዝብ ተመርጠው ወያነ ወዳለበት ሽ አውራጃ ከተላኩት ሸማግዎች ውስጥ የ የቅርብ ቤተሰብ የሆኑት አቶ ገብረሊባኖሰ መዝገቦ በዓይን ምስክር በአቶ ገዛኢ ረዳ አንደበት ምን እንደተፈጸመባቸው ካሳተምኩት መጽሐፍ ቀንጭላስነብባችሁና ተመሳሳይ ድርጊት ወደ ፈጸሙት ጎጃም የበቀሉ የሙሶሎኒ ቡቃያዎች እንመለከታለን (የዘመነ “ካልቶች” ቢመራችሁም ዋጡት)፡፡

ጥያ ፦ ክቡር አቶ ገዛኢ ሆይ፦ ለሽምግልና የተላኩት ሸማግሌዎችም ሆኑ ከነሱ ጋር ግንኙነት ያልነበረዎት በራስዎም ጭምር ‘ተሓህት’ ያደረሰችባችሁ ግፍ ሊነግሩን ይችላሉ?

 መልስ ፟ አቶ ገዛኢ ረዳ፡-

አዎ ሳስታውሰው ይሰቀጥጠኛል፡፡ መቸም ይህ አረጋዊያንን ማዋረድ በእኔ ላይ የተፈጸመዉ ግፍ በእኔ አልተጀመረም በእኔም ላይም አልቆመም።ብዙ አስረኞች፤ያለ ጥፋት ተደብድበዉ በእሳት ተቃጥለው መላ ሰዉነታቸዉ “ደም” እና “መግል” ቋጥሮ “ለቁስል” እና “ለዘላቂ ስቃይ” “ለአእምሮ መታወክ” ከመዳረጋቸዉ በላይ በየቀኑ በእዉነቱ ከ3 አሰከ 4 አሰከ 7 ወይንም 8 ድረስ ከተለያዩ ቦታዎች የሰበሰብዋቸዉ አስረኞች ይገደላሉ። ሊገድልዋቸዉ-ሲፈልጉ፤ጥዋት-ጥዋት “ተሰናበትዋቸዉ” ይሉናል። እየጠሩ ሲወስድዋቸዉ የሚገደሉት ሰዎች “ለወንድሜ ንገሩልኝ፤ለእናቴ ለአጎቴ ንገሩልኝ”- “ደህና ሁኑ” ከእንግዲህ ወዲህ አንገናኝ ይሆናል! “እግዚአብሐር-ከእናንተ-ጋር-ይሁን”!እያሉ፤ይሄዳሉ።

በጣም ከሚያሳዝን ነገር፤ “አቶ ገብረሊባኖስ መዝገቦ” የተባሉ የተከበሩ ትልቅ ጨዋ ሰዉ በሽሬ አዉራጃ ዋና ከተማ በእንዳስላሴ ከተማ ኗሪ ፤ የሆኑት እኒህ ሰዉ ፤ያዉራጃዉ (ሸረ) ግምጃ ቤት ሂሳብ ሹም ሆነዉ ሲሰሩ፤ በወቅቱ ደርግ ትላልቅ የአገሬዉ ታዋቂ ሰዎች የሚባሉ ሰብስቦ “በረሃ ድረስ ሄዳችሁ “ምንድነዉ ነገሩ? ብላችሁ” አስኪ ነገሩ በሰላም የሚፈታ ከሆነ በሰላም ለመፍታት እንዲቻል በረሃ ድረስ ያሉበት ቦታ ሄዳችሁ የወያኔ መሪዎችን አነጋግራቸሁ ለዕርቅ አነጋግሯቸዉ። በሽምግልና የሚታይ ከሆነ እንሞክረዉ እና አስኪ ሄዳችሁ ህዘቡን ወክላችሁ አነጋግሯቸዉ” ፤በማለት እሳቸዉ እና ሌሎችም እንደዚሁ “ባላምባራስ ተወለደ ገብረስላሴ” የተባሉ የእንዳስላሴ ከተማ ጭቃ ሹም፦ሌላም ገስጥ ኪዳነማርያም የተባለ የትልቅ ባላባት ልጅ ከሽማግሌዎቹ ጋር ለሽምግልና ተመርጦ አብሮ ሄዶ ነበር (ልጁ በወቅቱ አባትየዉ ከሚኖሩበት ከተማ ሄደዉ ወያኔዎች የገደሏቸዉ መሆኑንም ጭራሽ አልሰማም፤ኣላወቀም ነበር)። ሽምግልናዉ ስላልወደዱት “አይሆንም ብለዉ ወደ መጡበት ከመመለስ ፈንታ እነሱንም ያለ ምንም ወንጀል ይዘዉ አስቀርዋቸዉ”።የታሰሩት ቀደም ብለዉ እኛ ከተማ ዉስጥ እያለን ከመያዛችን በፊት ነዉ። አብረዋቸዉ የነበሩ ሌሎች አስረኞች ጭምር ታስረዉበት ከነበረዉ “ግህነም” ከተባለ “የጋሀነመ እሳት አስር ቤት” መጥተዉ እኛዉ ጋር አብረን ተቀላቅለናል። ልክ እኔን በእሳት አቃጥለዉ እንደለበለቡኝ አነሱም ሰዉነታቸዉ በሙሉ በእሳት ተቃጥሎ ለብልበዋቸዋል።ገላቸዉ ቁስል ደም እና መግል ብቻ-ሆኗዋል።

በተለይ አቶ ገብረሊባኖስ መዝገቦ እኔ በእሳት ከተጠበስኩት በላይ ተጠብሰዋል።ምክንያቱም በጀርባቸዉ ደምም መግልም ይንዠቀዠቃል። መተኛት አይችሉም- የቁስሉ መጠን ለዓይን ይዘገንናል።አቶ ገብረሊባኖስ መዝገቦም ሆኑ ባለምባራስ ተወልደ ገብረስላሴ በጣም ደግ የተከበሩ ባላባቶች ናቸዉ።ባላምባራስ ተወለደ ገብረስላሴም የአከባቢዉ፤የሽሬ እንዳስላሴ ከተማ ማዕረግ/አድባር ነበር ማለት ይቻላል።ባላምባራስ ገብረስላሴ ወደ ምርመራ ሲወስዱት “አይዞህ ቆመንም ያዉ ሞት ነዉ፡ ብንሞትም ያዉ ሞት ነዉ- በርታ” ያልዋልክበት አበሳ ንገረን ቢሉህ ያላደረግከዉ ነገር በጭንቅ “አዎ” ብለህ አትመንላቸዉ፡ብየዉ ወስደዉ ደጋግመዉ እንደገና በእሳት እየለበለቡ እየደበደቡ ሲያሰቃዩት፡መከራ ሲበዛበት“የሚሉት ሁሉ ኣዎ! አላቸዉ”። ቀጥለዉም ለወጣት “ገስጥ ኪዳነማርያም “እዚህ የመጣኸዉ አባትህን ስለገደልንልህ የደም ብድር ለመመለስ ነዉ ወደ እኛ አዚህ ድረስ ደፍረህ የመጣኸዉ?” አሉት። አሱ ደግሞ አባትየዉ በእነሱ እንደተገደሉም ጭራሽ-አላወቀም-ነበር።

ሌላዉ ደግሞ ከዓድዋ ሰለኽለኻ ወደ ተባለች ትንሽ ከተማ እህቱን ለመጎብኘት መጥቶ የነበረ አንድ ህፃን ልጅ (ታዳጊ-ወጣት) ይዘዉት አብሮን ነበር። “አንተ ደግሞ እዚህ የመጣኸዉ ከምንጠጣበት ወንዝ መርዝ ልትጨምር ነበር የመጣኸዉ? ብለዉ፤ እሱንም በእሳት ለብልበዉ ገርፈዉ አሰቃይተዉ እንድንምርህ ከፈለግህ “አዎ” ማለት አለበህ ብለዉት “አዎ” አምናለሁ ብሎ ባልዋለበት ነገር አሳምነዉ አክስቱን ለመጠየቅ ወደ ሰለኽለኻ አብሮት ከዓድዋ ወደ ሰለኽለኻ የመጣዉ “ብርሃነ መስቀል ጎሽም” እንደገና መሓመድ የተባለዉ ወጣት ልጅ በአንድነት በአንድ ቀን ሁሉንም ወስደዉ ረሸኗቸዉ።

“…በወቅቱ “ኢድዩ” ወደ አካባቢዉ በብዛት ሰራዊቱን ይዞ እየገሰገሰ በፍጥነት ስለመጣ በድንገት ስለደረሰባቸዉ ወያኔዎች ተደናገጡ። ኢዲዩ መጥቶብናል እና እንግደላቸዉ ብለዉ እኛን ለመግደል ወያኔዎቹ ሌሊትኑ ወደ ታሰርንበት ዳስ ክፍል ገቡ እና አስወጥተዉ በተራ አስሰለፉን።“አዛዉንቱ አቶ ገብረሊባኖስ መዝገቦም ሲመረምሩዋቸዉ ሰዉነታቸዉ በሞላ በእሳት እያቃጠሉ እየደበደቡ ስላደከሙዋቸዉ / መራመድ ስለማይችሉ ልንሸከማቸዉ አንችልም ብለዉ አቶ ገብረሊባኖስ መዝገቦን በእንቅልፋቸዉ ተኝተዉ እንዳሉ በሦስት ጥይት ገደሏቸዉ። የገዛ ታጋያቸዉም በሃይለኛ ወባ ተይዞ ተኝቶ ስለነበር አሱንም አንሸከመዉም ብለዉ በጥይት ገደሉት…።”

ወስደዉ ከረሸንዋቸዉ በግምት ወደ 30 ወይም ወደ 35 የሚሆኑ ሰዎች መካከል ናቸዉ።ዝርዝር ስማቸዉ ቆይቼ ልገልጽልህ ነዉ። የጭካኔያቸዉ መጠን የሰዉ ፍጡረነትክን ያስጠላል። ትግሬነትክን ያስጠላል። በወቅቱ ያ ግፍ ስትመለከት “የትግራዋይነት ትርጉም ሃዘን መሆኑን ይሰማሃል”። ይህ ጭካኔ የሚያራምዱ ባዕዳን ሳይሆኑ ከምድሪቱ ከእኛዉ ትግራይ መሬት የተወለዱ የአምላክን ክብር የሚንቁ ከአብራካችን የወጡ የትግራይ ተወላጆች ያሳደግናቸዉ የምናዉቃቸዉ ልጆቻችን ናቸዉ” ይህ ሁሉ ግፍ በሕዝብ ላይ እየፈጸሙ፤ያሉት።

ገዛኢ ረዳ። ከቃለ መጠይቅ  ክትግርኛ ወደ አማርኛ የተረጎምኩት ክራው መጸሕፍ የተገኘ፡፡  አቶ ገብረሊባኖስ መዝገቦ የዚህ ጽሑፍ አቅራቢ (የጌታቸው ረዳ) ቅርብ ተሰብ ናቸዉ።

አሁን ወደ ጎጃሙ ሙሶሊኒ የዘመነ ካ ታጣቂ ተመሳሳይ ድፍረትና ድርጊት እንመልከት፤

ሰሞኑን በዘመነ የሚመራው <<የአማራ ፋኖ በጎጃም>>  አሸማቃቂ ፤ በጣም ነውር የተሞላባቸው ሁለት ድፍረቶች በኩራት የፈጸማቸው በቪዲዮ ቀርጾ እንዲሰራጩ አድርል፡፡

አንደኛው እሱ ራሱ ለብሶት የሚታይ (የታዋቂ ሰዎች መስል ተደርጎበት የሚለበስ ሰንደቅ ዓላማችን ቀለም ያለበት ካኒተራ) የታላቁ  እስክንድር ነጋ ፎቶ ያለበት የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማን እንዲቃጠል ያደረገ ሲሆን፡

አንደኛው አስነዋሪ ድርጊት!

 ልክ ከላይ የተሓህት ድርጊት እንደተመለከታችሁት ጎጃም አማራ ማሕበረሰብ ላይም የዘመነ ታጣቂዎች ለባሕላዊ ሕክምና እና የወባ በሸታ መከላከል ስርጭት ትምሕርት ከአካባቢ ሪዎች የተውጣጡ ናቸው የሚባልላቸው ሰልጥነው ወደ ገጠር መኖርያቸው ሲመለሱ በዘመነ ካ ታጣቂ ጦር ከየመኖሪያቸው እየተለቀሙ ባንድ ቦታ ተሰበሰበው ገበያ ላይ ሕዝብ በተሰበሰበበት “እኛን ከአብይ አሕመድ ለመሸንገል አብይ አሕመድ የላካችሁ ሸማግዎች ናችሁ” በሚል 4 ቱ ሲረሸኑ ከመረሸናቸው በፊት በርከት ካሉት ሸማግ እናቶችና ታዳጊ ወጣቶች፤ እንዲሁም የዚያ አካባቢ አሰተዳዳሪ ቄስ በእምብርክክ እየተንፏቀቁ ሕዝብ እንዲያያቸው “ዘነዘና ብትርና መሳሪያ የያዙ የዘመነ ካ  ታጣቂዎች ሲያጣድፉዋቸው እምብርክክ እንዲሄዱ የተደረጉ እናቶች፤ አረጋዉያን፤ ቀሳውስት አይተናል፡፡

እነዚህ አዛውንት ደክመው የልጅ ልጆቻቸው ወደ ሆኑት ወረበላ ታጣቂዎች የልመና ገጽታ ቢያሳዩም ይባስ ብሎ ፍጥነት እንዲጨምሩ በማስፈራራት  ሲያስጨንቁዋቸው ዓለም እንዲያያቸው በዩቱብ ተዘርግቶ እየታየ ስንብል፡፡

ይህ የዘመነ ካ ታጣቂ ሎ የፈጸመው አምሐራ በሆኑ አረጋዊያን አባቶችና የሸመገሉ እናቶች  አስነዋሪ ድርጊት የቪዲዮው ርእስ እንዲህ ይነበባል፡፤

<< ስርዓቱ የፈጠረው ምስ ካውንስል ሰብስቧቸው የቆዩ ባንዳዎችን በዚህ መልኩ አቀባበል ተደርጎላቸዋል ፤ የኮሎኔል ታደሰ ሙሉነህ ብርጌድ ፤ አለማየሁ ከ ሻለቃ>> ይላል፡፡

ድርጊቱ የፈጸሙት እየሸለሉ እየፎከሩ እየዛቱ  የታዩት የነዚህ ታጣቂዎች የበርጌድ ስም የተሰየመው “በፈቃዱ እጁን ለሻዕቢያ በመስጠት’’ አይሮፕላን አብራሪዎችን ሲያሰለጥን የነበረ በግፍ የታሰረ፡፡ በ“ዋሾው” አንዳርጋቸው ፅጌ የኢሳያስ መንግሥት ለመፈንቀል ተንኮል ሲሰራ ተነቅቶበት የተያዘ ነው እንጂ በሰላም አሥመራ ወስጥ በክብር ይኖር ነበር በማለት በሐሰት የወነጀለው፡ በግፍ በሻዕቢያ ለዘመናት ታሰሮ አብይና ኢሳያስ ሲዋደዱ መጨራሻ ዕድል አግኝቶ ተፈትቶ እስር ውስጥ ለአመታት ስለቆየ መራመድ ሰለማይችል “በተገፊ ወንበር” እየተገፋ አዲሰ አበባ ወደ አገሩ የገባው በኮሎኔል ታደሰ ሙሉነህ ስም እየተጠራ ያለው አረጋዉያን የደከሙ እናቶች፤ ፊታቸው የጠወለጉ ችጋርና የኑሮ ውጣ ወረድ ያንገላታቸውን ነው እምብርክክ በማስድ በሽለላና በቀረርቶ እየተጨፈረ ዓለም እንዲያያቸው የሆነው፡፡

እነዚህ ሰን ጎጃም ውስጥ ልዩ ስሙ ገርጨጭ በተባለ ወረዳ ሪ የነበሩት በእምብርክክ ካስድዋቸው 13 ወስጥ 4 ቱ ፡ 4ቱ  በጥይት ተደብድበው ከሞቱት ሰዎች ስም ዝርዝር

1)    1) ወረዳው ቤተ ክሕነት ሥራ አስኪያጅ የነበሩት  መሪታ ግሩም

2)   2) አቶ አዘነ ደም

3)   2)  አቶ  አስማማው አ

4)   4)  ወ/ሮ ላይን አየሁ ዳኛው   (የክስተንሺን ሰራተኛ)

ይህ የዘመነ ካ ሙሶሎኒያዊ የጫካ ሕግ /ግፍ/ በሚመለከት ቪ ኦ አማርኛ ዜናም ዘግቦታል፡፡

ሁለተኛው ጉድ ደግሞ አሁንም ዘመነ ካሴ የሚያዘው ሰንደቅ ዓላማችንን የሚያቃጥል ታጣቂ የባንዳዎች ስብስብ ደግሞ የእስክንድር ነጋን ምስል ያለበት ከናቲራ ሲያቃጥል በቪዲዮ አይተናል፡፡ ይህ ድርጊት የፈጸመው የዘመነ ታጣቂ ሰንደቅ ዓላማችንን ባለፉት 36 አመታት ሲቃጠልና ሲረክስ እያዩ ያደጉ ወጣቶች ናቸው፡፡ ዘመነም የነዚህ ትውልድ አንዱ ስለሆነ እርሱ ሳይፈቅድ ትግሬዎችና ኦሮሞች ሲያደርጉት እንደነበረው ሁሉ ድርጊቱ በቪዲዮ ሕዝብ በተሰበሰበበት ተቀርጾ በቪዲዮ አይሰራጭም፡፡

ሲያቃጥሉትም የተከበሩት ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለሰላሴን በዋልጌዎች ሲሰደቡ እንደነበረው ዓይነት ስድብ እሰክንድርንም <<ሌባ>> <<ሌባ>> እያሉ ከዚያም አልፈው እንገድልሃለንገድለንህም ሬሳህንም እናቃጠለዋል>> እያሉ የእርሱ ምስል ያለበት የስንደቅ አላማን ምስል ሲያቃጥሉ ነውር መሆኑን የነገራችው መሪ የለም፡፡

ሁለት ነገሮች አይደፈሩም!

(1) ከጠላት ሸሽቶ ገዳምና ቤተ-ጸሎት በተማጽኖ የገባ ተማጻኝ (የተጠለለ ሰው) ቤተ-ጸሎቱን የሚያስተዳድሩ ሐላፊዎችም  አሳለፈው ለአሳዳጁ አይሰጡም፡ ፈላጊውም የቤተ-ጸሎቱን አጥር ግቢ ጥሶ አምላክ ጥላ ሥር ሮጦ የተሸሸገን ሰው መንጭቆ አይወስድም፡፡ ፈላጊው ግቢውን አይጥስም (ፈጣሪን መጣስ ነውና)፡፡ ቤተ-ጸሎት ላይም ቦምብ ፤ ጥይት አይተኮስበትም፡፡ በእሳትም ማቃጠል ነውርና ወንጀል ነው፡፡

 (2) ምንም ይሁን  ሰንደቅ ዓላማው ላይም ፎቶ ቢለጥፈበትም በጽሑፍ ማወገዝ እንጂ ማቃጠል ነውር ነው፡፡ ሰንደቅ ዓላማ ማለት ገዳምና የማይደፈር ሃገራዊ አርማ/ምልክት ማለት ነው፡፡ የእስክንድር ፎቶ ሰላለበት፤ የዘመነ ምስል ስላለበት፤ አንበሳ ሰላለበት፤ የነገሥታቱ የነ ዮሃንስ፤ምንሊክ እና ሃይለሰላሴ ምስል ሰላለበትና ሰለጠላሃቸው ወድቃ የተነሳቺው ሰንደቅ ዓላማ ያለበተን ቀለም መርገጥና ማቃጠል ነውር ነው፡፡

አንድ ሰው የመለስ ዜናዊ መከራከያ ካልተከተለ በቀር፡፡ እርኩሱ መለስ ያለው፦ “ከጨርቁ በስተጀርባ” ያለው “ኢትዮጵያ፤ ዮሃንስ ፤ ምንሊክ ፤ ሃይለሰላሴ ፤ ኦርቶዶክሰና አማራን” እንጂ ጨርቁን ማንም ሰው ሊያውለበልበው ይችላል!” በማለት ያሰተማረውን አደገኛ ጣሊያናዊ ቅስቀሳና ሕግ ሰንደቃላማችን ይኸው ከላይ በጠቀስኩዋቸው በወጣቶቹ የአማራ ብሔረተኞችም ጭምር ተዋርዳ እየተቃጠለች ነው፡፡

ሰንደቅ ዓላማን ማሳነስና ማቃጠል የጀመሩት “ፋሺስቶች” ናቸው፡፡ የሙሶሎኒ ጀግኖ የሚባሉ ሙሶሊኒ የሚያደንቃቸው ተግባራቸውን የሚጋራቸው ሁለት ሰዎችን ልጥቀስ፡፡የፈረንሳዩ አብዮተኛ (1) Blanqui (the man of the barricades the organization of revolutionary violence) 

(2) Gustave Herv’e), from which Musolini took over the slogan “to us the national flag is a rag to be planted on a dunghill”

(1) ብላንኪ (አመጽ አዘጋጁ አብዮተኛ) 

(2) ጉስታቭ ሄርቪ)፣ “ለእኛ ብሄራዊ ሰንደቅ አላማ ማለት በቆሻሻ ጉድጓድ ላይ የሚተከል ጨርቅ ነው”  ይህ መፈክር ሙሶሊኒ ተረከቦ ያሰተጋባው ነበር፡፡

ከሙሶሊኒ የተረከበው ደግሞ ትግው መለስ ዜናዊ ነው፡፡ ከመለስ ቀጥሎ የጎጃሙ አዲሱ የሙስሎኒ ቡቃያ የዘመን ካሴ ታጣቂው ቡድን  ነው፡፡

በደማቅ የሚታዩ ሦስቱ ሕብር ቀለማት ዓይናቸው እያየ ሲያቃጥሉት ጥላቻ ምን ያህል ከፉ መሆኑ ያሳያል፡፡ ይህ አደገኛ አምሐራዊ በሔረተኛ ቡድን ልክ እንደ ትግሬ ብሔረተኞቹና እንደ ኦሮሞ ብሔረተኞቹ በሰንደቅ ዓላማና በአረጋውያን የሚዘምት “ገድየህ ሬሳህን አቃጥለዋለሁ በማለት ሁለት የፋሺስት ሥርዓቶችን የተጋተረ ፋሺቶች በሚፈንጩባት ከተማ ብቻውን ሰንደቅ ዓላማችንን እያወለበለበ የምኒልክን ሐውልት ሲያቆሽሹት እያጸዳ ፤ ፋሺቶች በደማሚት እንዳያፈርሱት የጠበቀ ፤ ቅርሶች ሲፈርሱ "ኡ ኡ!!" ያለ፡ ዓለም የሸለመው ፤ የተኛውን አዲሰ አበባ ወጣቱን እመቢተኛነትን ያሰተማረ አሰገራሚ የጽናት አርአያ የሆነውን ታላቁን እስክንድርን ገድሎ ሬሳውን ለማቃጠል (ጥላቻ ሕሊናን ያሳውራልና ፤ ስጋውንም ሊበሉት ይችሉ የሆናል) የሚዝት እጅግ አስፈሪ የፋሺስት ሕሊና ስናይ በቀላሉ ቸል ተበሎ መታለፍ የለበትም፡፡

ይህ ሞገደኛ አማራዊ የብሔረተኛ መንጋ (ቫየለንት ግሩፕ) ሕዝብ ሰብስቦአረጋዉያንን እምብርክክ ማስኬድና መረሸን ለሚገድሉት የእስክንድር ሬሳም እንደሚያቃጥሉ እየነገሩን ያሉት “አታቪስት Atavist)” (እንሰሳዊ ብሕሪ የተላበሱ ሰው መሳይ አራዊቶች) ባሕልን ፤ሃይማኖትን ፤ ሕግን የሚጻረሩ ስለሆኑ ካሁኑኑ “በፖለቲካና በብስለት የሚመራ አራሚና መሪ” ካላገኙ እያደገ ሲመጣ <<አማራዊ ኦነግ>> ሆኖ ካሁን በፊት ያየናቸው ኦነግ እየፈጸማቸው ያሉት ትግባሮች በከፋ መልኩ እንዳይፈጽሙ እሰጋለሁ፡፡

በመጨረሻም 

ዘመድኩን በቀለ ሰለተባለ (ካሁን በፊት ብዙም ያላወቅሁት) አሁን አሁን እያወቅኩት ስለ መጣሁት ሰው አንድ ነገር ልበልና እሰኪ ከዚህ በታች የተናገርውን እስክንድር ከአብይ ጋር እየሰራ መሆኑን ከአሥመራና ከብርሃኑ ነጋ ጋር በምስጢር ግንኙነት እንዳለው ውንጀላውን በማስረጃ ያሳየንና የጥንት ወዳጄ የነበረው የሊያስ ክፍሌ ንብረት ነው የሚባለው መረጃ ቲ/ቪ ይህንን ንግግር አስተላልፎለት ይሆን ወይስ በግል “ሚዲያው” ይሆን?

እንዲህ ይላል፡

<< እስክንድር ካለበት መከላከያው 5 ኪ/ሜትር ነው እሚቀመጠው፡፡ እስክንድርን አይነኩትም፡፡ሰንሰለቱ ያለው ከበረሃኑ ነጋ ጋር ነው፡ በብረሃኑ አድርጎ በአስመራ በኩል አድርጎ፤ በእነ ሃብቴ በኩል አድርጎ በእነ ኮሎል ፈንታሁን አድርጎ ሸዋ ነው የሚገባው>> (ዘምድኩን በቀለ)፡፡

ይህ ጤናው የተሟላ ሰው የሚናገረው ሰው አይመስለኝምና የሚያከብሩት ካሕናት ጸሎት አድርጉለት፡፡ይህ በጣም ፤ በጣም ካስገረሙኝ እስክንድር አሳምነውን አስግደሎታል ከሚሉ “እብዶች” ከሰማሁት ሁለተኛው ካሰገረሙኝ ውንጀላዎች ውስጥ ነው፡፡ ቱራማታይዝ የሆኑ ሕክምና የሚፈልጉ ብዙ ወንድሞችና እህቶች እንዳሉን አመላካች ነው፡፡

ሰላም ሰንብቱ

ጌታቸው ረዳ